📌ፖንዚ ስኪም (ponzi scheme) ምንድነው ?
❇️ፖንዚ ስኪም በግሩፕ የተደራጁና ሃብትን በጋራ እናፈራለን ብለው በማሳመን ተጠቂውን ገንዘብ ኢንቨስት እንዲያደርግ በማታለልና ለራስ በመሰብሰብ የሚሰራ ወይም የማጭበርበር ወንጀል ነው።
❇️አሰራሩም አዲስ ምልምል ተጠቂዎች ኢንቨስት ያደረጉትን ገንዘብ ቀድመው ለገቡት መክፈል ፣ ቀድመው ከገቡት የተወሰደውን ገንዘብ ደግሞ አዲስ ለገቡት በትንሹ ያካፍላሉ።
❇️ዘረፋቸው እንዲቀጥልና ገንዘብ ስብሰባው እንዳይቋረጥ አዲስ ምልምል ያስፈልጋቸዋል፣ ለዚህም ትንሽ ኮሚሽን በመክፈል ብዙ ሰዉ እንድታሰገቡ ይጠይቃሉ።
🛑በሃገራችን በዚህ ሰዓት ብዙ ተጠቂዎችን በማጭበርበር ላይ የሚገኝ ፖንዚ ስኪም ግሩፕ ምሳሌ Fias 777 የሚባል የደላሎች እና ባለቤትነቱ የማን እንደሆነ ማይታወቅ ድርጅት ነው
‼️ፖንዚ ስኪም ግሩፕ ባህሪዎች
1⃣ ተጠቂው ምንም ስራ ሳይስራ ገንዘብ በማስገባቱ ብቻ ሃብታም እናደርጋለን ብለው ቃል ይገባሉ።
2⃣ አዲስ ተመዝጋቢ ወይም ተጠቂ እንድታሰገቡ ጫና ያደርጋሉ።
3⃣ ስለ ድርጅታቸው እና በጠቃላይ ስለ አሰራራቸው ሲጠየቁ ቀጥተኛና ግልፅ መልስ መስጠት አይፈልጉም።
4⃣ በመንግስት የታወቀ ህጋዊነት ወይም ላይሰንስ የላቸውም። ሕጋዊነት ማሳያ ሲጠየቁም ብዙ ምክንያት ይሰጣሉ።
5⃣ ተጠቂዎች ኢንቨስት ያደረጉትን ወይም ትርፍ ገንዘባቸውን እንዳያወጡ ይዘገይባቸዋል።
6⃣ ለተወሰኑ ደላሎች ጥሩ ክፍያ በመክፈል የነሱን ምሳሌ ብቻ በማሳየት አዲስ ምልምሎችን ማታለል እና ብዙ ብር ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማሳመን።
7⃣ አዲስ ምልምል ቁጥር ሲቀንስ ወይም ገንዘብ ሚያስገባ ሲጠፋ ቀድመው ለገቡት ሚከፍሉት ስለማይኖር ዘረፋቸው ይቋረጣል ከዚያም የሰበሰቡትን ገንዘብ ይዘው ይሰወራሉ።
‼️ገንዘብዎን ከፍለው ከተበሉ ምን ማድረግ ይችላሉ
1⃣ በእርስዎ አካውንት ገንዘብ ያስገባልዎትን ደላላ ሙሉ ስም እና በየትኛው ባንክ እንደላከሎት መያዝ።
2⃣ ወደ ህግ አስከባሪ አካል ወይም ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ማድረግ።
3⃣ እርስዋ እና ሌሎች ተጠቂዎች ባመለከቱት መሰረት ፖሊስ የደላላውን አድራሻና ማንነት ከባንክ መታወቂያው ላይ ያገኛል።
4⃣ ምንም እንኳን ገንዘብዎ ተመላሽ ባይደረግም ደላላውና ግብረ አበሮቹ በህግ ቁጥጥር ስር ይውላሉ።
‼️#Share በማድረግ ለሌሎች ላልሰሙ እናድርስ
══════════════════
🆔 @info_tech_et
🆔 @info_techs_group
💠 ሮስግራም | Rossgram
🔻ሩሲያ የፌስቡክ ኩባንያው ኢንስታግራም በሀገሯ እንዳይሰራ አግዳለች የሩሱያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የስራ ፈጣለሪዎች ከኢንስታግራም ጋር ተመሳሳይነት ያለው አዲስ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያ መስራታቸው ተስምቷል።
🔻የቴክኖሎጂ ዘርፍ የስራ ፈጣለሪዎቹ አዲሱን የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያ የሰሩት ሩሲያ ኢንስታግራም የተባለው መተግበሪያ በሀገሯ ውስጥ እንዳይሰራ ክልከላ መጣሏን ተከትሎ የሚፈጠረውን ከፍተት ለመሙላት ተስቦ ነው ተብሏል።
🔻ሩሲያ በፌስቡክ ላይ ገደብ ጣለች አዲሱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያ “ሮስግራም” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን ከቀናት በኋላ ለተጠቃሚ እንደሚቀርብ ተነግሯል
🔻አዲሱ የሩሲያው ሮስግራም የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያ ከኢንስታግራም ጋር ተመሳሳይ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ተጨማሪ አገልግሎቶችን ያካተተ እንደሆነም ተነገሯል።
🔻ከእነዚህም ውስጥ የገቢ ማሰባሰቢያ ማከናወን የሚስችል እንዲሁም በክፍያ ብቻ የሚታዩ ይዘቶችን መጫን የሚያስችል አገልግሎቶች እንደተካተቱበትም ታውቋል።
🔻ሜታ የፌስቡክንና ኢንስታግራምን በመላው አውሮፓ ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ
የሩሲያ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ ኢንስታግራም በሀገሪቱ ውስጥ እንዳይሰራ መታገዱን ማስታወቁ ይታወሳል።
🔻ፌስቡክ እና ኢንስታግራምን የሚያስተዳደርው ሜታ ኩባንያ በዩክሬን ብቻ ተግባራዊ የሚሆን የጥላቻ ንግግር ፖሊሲውን በጊዜያዊነት መቀየሩን ተከትሎ ነው ሩሲያ እርምጃውን የወሰደችው።
ሜታ ኩባንያ በጥላቻ ንግግር ፖሊሲው ላይ ባደረገው ለውጥም በዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች “ሞት ለሩሲያ ወራሪዎች” የሚሉ እና መሰል መልእክቶችን እንዲያሰራጩ መፍቀዱ ይታወሳል።
══════════════
🆔 info_tech_et
🆔 info_techs_group
✳️ ሰላም ውድ ቤተሰቦች ስልካቹ Stack/Busy ወይም እየደረቀ ካስቸግሮት እነዚህን 10 ነጥቦችን ይተግብሩ👇
➀. በብዛት የመትጠቀሙበት አፕሊኬሽን ብቻ Install አርጉ ማለትም እላስፈላጊ የሆኑ አፕዎችን ማጥፋት ወይንም Uninstall ማረግ
➁. Screen Animation እና ተንቀሳቃሽ Wallpaper Disable ማረግ ወይም ማጥፋት
⓷. RAM Management የሆኑ አፕሊኬሽኖችን በጭራሽ Install አያርጉ
⓸. የአፑን Cache Memory አፅዱ ይሄም Setting >> Storage >> Cache Data
⓹. ትንሽ ነፃ ቦት ማስቀረት Setting >> Storage
⓺. Widgetቱን አስወግዱ
⓻. ሁል ጊዜ ጥዋት ጥዋት ስልካትን Restart ወይም Reboot አርጉ
⓼. ሁሉንም የስልኩን አፕሊኬሽን Update ማረግ
⓽. Bloatwareኡን ማጥፋት ይሄም Setting >> All Apps >> በመግባት Disable ማርግ
⓾. Custom ROM Install ማርግ.
📱እነዚህን ከላይ ያሉትን ነጥቦች በመተግበር ስልኮትን ፈጣን ያርጉት።
🚻ለወዳጆችዎ ያጋሩት።
═══════════════════
🆔 @info_tech_et
🆔 @info_techs_group
✳️ SnapTube
📌ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በጣም እያስጠላ የመጣው Vidmate adware የተሞላ አፕ ነው ። የራሴን Player ካልተጠቀማቹ እያለ በግድ Playit የተባለውን አፕ ያስወርዳችኋል። ብቻ ከዚህ በጣም የተሻለ ምርጥ የዩቱብ Downloader Application እንጦቁማችሁ።
📌Snap Tube ከ Vidmate በጣም የተለየ ነው ከ YouTube የፈለጋቹትን Video በፈለጋቹት ጥራት እና በፍጥነት Download ያደርግላቸዋል።
@info_tech_et
@info_techs_group
🔵የባህር ማዶ ሙዚቃዎችን English,Hindi,Bollywood,JioTunes ስብስቦችን በውስጡ የያዘ አፕሊኬሽን ነው።
@info_tech_et
@info_techs_group
ቻይና ታይዋንን በምንም አይነት ሁኔታ ለመደገፍ የሚሞክር ካለ ጣጣውን ይሸከማል ስትል ዛተች‼️
ለዘመናት ፣ ሉአላዊ ግዛቴ ነሽ ፣ የለም ራሴን የቻልኩ ሃገር ነኝ በሚል ሲነታረኩ የቆዩት ታይዋን እና ቻይና አሁን ወደየለት ቀውስ እንዳያመሩ ተሰግቷል፡፡
ቻይና ለታይዋን በምንም አይነት ሁኔታ በተለይ ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዘ ድጋፍ አደርጋለው ያለ አፀፋው የከፋ ይሆንበታል ብላለች፡፡ የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ኮሎኔል ታን ኪፊይ የታይዋን ጉዳይ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ነው ሲሉ የተደመጡ ሲሆን በውስጣዊ ጉዳዮቻችን የማንንም ጣልቃ ገብነት አንሻም በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ሃገራችን ሉአላዊ ግዛቷ ከሆነችው ታይዋን ጋር የምታደርገውን ውህደት አደናቅፋለው ላለ አካል ውጤቱ እጅግ አስከፊ ይሆናል ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
@info_tech_et
@info_tech_et
ውድ ቤተሰቦቻችን ሰሞኑን በየሚዲያው የምንሰማው ነገር ሁሉ ከጦር ሀይል እና ከጦርነት ጋር የተገናኙ ነገሮች ናቸውና በአለማችን 9 ከፍተኛ የጦር ሀይል ካላቸውን ሀገራት ጋር ተዋወቁ።
🔫የሩስያ🇷🇺 እና ዩክሬ🇺🇦 ቀውስ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በቅርቡ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የትኛውም ሀገር ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረገችው ወረራ ላይ ጣልቃ ለመግባት ቢሞክር የኒውክሌር ጦር መሳሪያቸውን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
📌በዚህ ጽሁፍ Info Tech ትልቅ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ያላቸውን 9 ሀገራት ይነግራችኋል።
9⃣ ሰሜን ኮሪያ 🇰🇷
እ.ኤ.አ. በ2020 መጀመሪያ ላይ ከ30 እስከ 40 የሚጠጋ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላት ይገመታል። እ.ኤ.አ. በ 2022 ኦፊሴላዊ ዘገባዎች 50 የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እንዳሏት ይገልፃሉ።
8⃣ እስራኤል 🇮🇱
እስራኤል ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ይዛለች። ኦፊሴላዊ ዘገባዎች 90 የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እንዳሏት ይገልጻሉ።
7⃣ ህንድ 🇮🇳
እ.ኤ.አ. በታህሳስ 18 ቀን 2021 ህንድ አዲሱን አግኒ-ፒ መካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤልን ከአብዱል ካላም ደሴት ከተቀናጀ የሙከራ ክልል የሞከረች ህነድ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 156 የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች አሏት።
6⃣ ፓኪስታን 🇵🇰
ተማሪዎችን ወደ ውጭ በመላክ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ የአቶም ፎር ፒስ ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል። በአሁኑ ጊዜ 165 የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች አሏት።
5⃣ እንግሊዝ 🏴
በአሁኑ ሰአት አራት ባለስቲክ ሚሳኤል የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ይዛለች፤ እንዲሁም በአሁኑ ሰአት 225 የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች አሏት።
4⃣ ፈረንሳይ 🇫🇷
በአሁኑ ጊዜ በዓለም አራተኛውን ትልቁን የኒውክሌር ክምችት ይዛለች ፣ በአሁኑ ጊዜ 290 የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችም አሏት።
3⃣ ቻይና 🇨🇳
እንደ ሪፖርቶች ከሆነ ቻይና ይህንን ማስፋፊያ ለመደገፍ ፕሉቶኒየም የማምረት አቅሟን የሚያሳድጉ “ፈጣን አርቢ ሪአክተሮች እና ሪፕሮሰሲንግ ፋሲሊቲዎች” በመገንባት ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ጊዜ 350 የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች አሏት።
2⃣ አሜሪካ 🇺🇸
ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ 5,550 የሚገመት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በማሰማራትም ሆነ በማጠራቀሚያነት አላት።
1⃣ ሩሲያ 🇷🇺
ሩሲያ ወደ 6,257 የሚጠጋ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ነች፣ ሩሲያ የኒውክሌር ሀይሏን ለመገንባት እና ለማቆየት 8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ አውጥታለች።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@Info_Tech_Et
@Info_Techs_Group
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ፑቲን ጦራቸው ሙሉ ዩክሬን ላይ እንዲሰማራ እና እንዲቆጣጠር አዘዙ‼️
ከዩክሬን ጋር ውጊያው ተጀመረ። ዩክሬንን አለንልሽ ሲሉ የነበሩት አሜሪካ እና ምእራባውያን ጦር እነደማይልኩ ተናግረው ስትወረር ቆመው እያዩ ነው። የዩክሬን ፕሬዝደንት ሩሲያዊያን ወዳጆቻችን ናቸው ነገር ግን ለሚቃጣብን ጥቃት ራሳችንን እንከላከላለን ማለታቸውም ተሰምቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን እንዲያቆም እየተማጸኑ ይገኛሉ።
@Info_Tech_Et
@Info_Techs_Group
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ በ07 መነሻ ኮድ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መጀመር ስለሚችልባቸው ሁኔታዎች ለብዙሀን መገናኛዎች ማብራሪያ ሰጥቷል።
በድርጅቱ የቴክኖሎጂ ቺፍ ኦፊሰሩ ፔድሮ ራባካል በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፊታችን ከሚያዝያ 1 ቀን 2014 ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀምራል።
የጽሁፍ አገልግሎት፣ የዳታ፣ የድምጽ በአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የቴሎኮም አገልግሎቶችን ይሰጣል ያሉት ቺፍ ኦፊሰሩ ከሰኔ በኋላ ደግሞ ሁሉንም የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀመራልም ብለዋል።
አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል።
በቀጣይ አሥር ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ1 ነጥብ 5ሚሊየን ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገለጿል።
#Share
@Info_Tech_Et
እስከ 2010 ድረስ እርግቦች ፋይል ለመላላክ ከኢንተርኔት የፈጠኑ ነበሩ። በተደረገ ጥናት አንድ እርግብ 50 ማይል እርቀት ላይ ወዳለ ኢንተርኔት ፕሮቫይደር ሀsB ስቲክ ለመዉሰድ 1 ሰዓት ሲፈጅባተ በኢንተርኔት አፕሎድ ለማድረግ ግን ከ 2 ሰዓት በላይ ፈጅቷል።
Channel @Info_Tech_Et
Group @Info_Techs_Group
ዉድ ቤተሰብ ስለጠፋዉ ይቅርታ🙏
ስለ #ፖንዚ_ስኪም (ponzi scheme) አጠር ያለች መረጃ አለችኝ ( በተለይ በቅርቡ Fias 777 በሚባል ዌብሳይት ብር የተበላቹ ካላቹ 1:00 ላይ ጠብቁኝ )
📌ኢንስታግራም ሩሲያ ውስጥ #መታገዱን ተከትሎ ሩሲያውያን የራሳቸውን #Rossgram የተሰኘ ሶሻል ሚድያ ለአለም አስተዋውቀዋል።
ስለ #Rossgram ዝርዝር መረጃ ነገ በዚሁ ቻናል ይጠብቁን።
@info_Tech_Et
@info_techs_group
🌐Wi-Fi Talkie Free
በ #WiFi hotspot በመጠቀም chat, call ማድረግ ትችላላችሁ።
⚠️ያለምንም ክፍያ።
@info_tech_et
@info_techs_group
💻🕹IDM DOWNLOAD MANAGER
በIDM download ስታደርጉ ለተቸገራችሁ ምርጥ መፍትሄ
ይህ IDM ማንኛውን በኮምፒውተር ላይ በመጫን የፈለጉትን
የአጫጫን Steps
1ኛ idman629build2.exe ይጫኑ
2ኛ Patch የሚለውን ፎልደር ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር OS bit 32 ከሆነ 32 Bit patch build 2.exe
64 ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ ይጫኑበት
በይበልጥ ግን How to install የሚለውን ያንብቡት።
Serial number አይጠይቃችሁም ከዚህ በኋላ
@info_tech_et
@info_techs_group
እንቅልፍ መተኛት የሚያስቸግራችሁ ይህቺን አፕ ያውርዱ።
ከመተኛትዎ በፊት መተግበሪያውን ይክፈቱ እና ጥሩ እንቅልፍ ይወስዳቹሃል።
@info_tech_et
@info_techs_group
📌 Telegram
🔘በአሁን ሰዓት ቴሌግራም በሩስያ ቀዳሚው እና ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሆኗል።
🔘በተለይ ሩስያ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን ማገዷን ታከትሎ ቴሌግራም በቀዳሚነት ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሊሆን ችሏል።
🔘የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌስንኪን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን እና የሩስያ ባለስልጣናት ፣ ሚዲያዎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ተቋማት መልዕክት ለመለዋወጥ ቴሌግራምን የሚጠቀሙ ሲሆን በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በመረጃ ልውውጥ ትልቁን ስፍራ የያዘ የማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል።
🔘ቴሌግራም ከዚህ በፊት ማለትም በ2018 ላይ በሩስያ ባለስልጣናት ለሁለት ዓመታት ታግዶ እንደነበር እና እገዳው 2020 ላይ መነሳቱ ይታወሳል። በወቅቱ እገዳው የተጣለበት የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲሰጥ ተጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር።
🔘በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ቴሌግራም የዩክሬን ተጠቃሚዎቹን መረጃ ለሩስያ ያቀብላል ተብሎ ስሙ ቢነሳም የኩባንያው መስራች በትውልድ ሩስያዊው እና በኡሁን ሰዓት በዩኤኢ #ዱባይ ነዋሪነቱን ያደረገው ፓቨል ዱሮቭ ኩባንያው የዩክሬን ተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ እንዳልሰጠ ፥ ይህንንም እንደማያደርግ በምንም ሁኔታ ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም ገልጿል።
🔘የቴሌግራም መስራቹ ፤ በእናቱ በኩል ቤተሰቦቹ ከኪየቭ እንደሆኑ ጠቁሞ እስከ አሁን ድረስም በዩክሬን የሚኖሩ ብዙ ዘመዶች እንዳሉት ገልጿል። አሁን ያለው አሳዛኝ ግጭትም " ለእኔም ሆነ ለቴሌግራም ግላዊ ነው " ሲል ነው ሁኔታውን የገለፀው።
🔘የድምፅ እና ቪድዮ ጥሪዎችን፣ የምስጥራዊ የመልዕክት ልውውጦች (ቻት) እንደማያነብ የሚናገርለት ቴሌግራም በምንም ሁኔታ የተጠቃሚዎቹን መረጃ አሳልፎ እንደማይሰጥ የገለፀ ሲሆን ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም አረጋግጧል።
🆔 @info_tech
🆔 @info_tech
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።
በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።
ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።
@info_tech_et
@info_tech_et
ጎግል ( Google ) ሌላ አንድሮይድ መተግበሪያን ከልክሏል! አሁን ይሰርዙት ( uninstall ያድርጉት ) አለበለዚያ በጣም ከባድ ዋጋ ይከፍላሉ።
ስሙ: ሱፐር ክሊነር ( super cleaner ) ይባላል
በኤንሲሲ ( NCC )ግሩፕ የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በፕሌይ ስቶር ( play store ) ላይ የሚታየው የቅርብ ጊዜ አፕ Antivirus ሱፐር ክሊነር #ሻርክቦት በተሰኘው አጸያፊ ማልዌር የታጨቀ ሲሆን ይህም በአውቶማቲክ ማስተላለፊያ ሲስተም (ATS) የገንዘብ ዝውውሮችን የማስጀመር ችሎታ አለው።
ሻርክቦት በሚገርም ሁኔታ የረቀቀ ተንኮል አዘል ማልዌር ሲሆን ከግል አካውንቶች ገንዘብ ለማውጣት ብዙ ተንኮል አዘል ስልቶችን ይጠቀማል። በመጀመሪያ፣ ይህ ስህተት ተጠቃሚው መለያቸውን በጠላፊዎች ለማግኘት እየሞከረ እና የተጠቃሚ ስሞችን ( username ) እና የይለፍ ቃሎችን ( password ) መስረቅ በሚችልበት ጊዜ የውሸት የመግቢያ ገጽን ሊሸፍነው ይችላል ፤ ሻርክቦት ከዚያ በኋላ ወንጀለኞች ስማርትፎን በሩቅ እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@Info_Tech_Et
@Info_Techs_Group
🖥 ቴክኖሎጂያዊ እውነታዎች
#Part_Two
📌 ሰዎች ስልኬን እጥላለው ወይም የ ኔትዎርክ ችግር ያጋጥመኛል በሚል ሰቀቀን የሚይዛቸው በሽታ Nomophobia በመባል ይታወቃል።
........................................
📌 አንድ ሰው በቀን በአማካይ 110 ግዜ ስልኩን unlock ያደርጋል።
............................................
📌 አለም ላይ ከሚሰሩ የ ሞባይል ቫይረሶች 99% የሚሆኑት android system የሚጠቀሙ ሞባይሎችን ያጠቃሉ።
.
.
🔘 Part 3 ይቀጥላል
@Info_Tech_Et
@Info_Techs_Group
🖥 ቴክኖሎጂያዊ እውነታዎች
#Part_One
📌 አለም ላይ በቀን 160 ቢልዬን የኢሜይል መልእክቶች ይላካሉ።
📌 Nokia 1100 እስከ ዛሬ ከወጡ ስልኮች ብዙ በመሸጥ ሪኮርድ የያዘ ሲሆን እስከ ዛሬ 250 ሚልየን ቀፎ ተሽጦአል።
📌 እንግሊዝ አገር ውስጥ በ አመት 100,000 (መቶ ሺህ) ስልኮች ሽንት ቤት ውስጥ ወድቀው ይጣላሉ።😵
@Info_Tech_Et
@Info_Techs_Group
✳️ሞባይል ስልክ ቻርጀር ሲሰካ በተገቢው ጊዜ ያለመሙላትና መዘግየት ዋነኛ ናቸው የሚባሉት 10 ምክንያቶች:
1⃣.ሞባይሉ ቻርጅ ማድረጊያ ኬብል ጥራት የሌለው ሲሆንና የኬብሉ መስመር ላይችግር ሲኖርበት
2⃣.የኤሌክትሪክ ሀይል ማነስ ከምንጩ ወይም ቻርጀሩ ከሚሰካበት ሶኬት ቦታ የሚወጣው ሀይል ዝቀተኛ መሆን
3⃣.የቻርጂንግ ኬብል መሰኪያ አዳብተር ጥሩ ሳይሆን ሲቀርና ብልሽት ሲገጥመው
4⃣.የሞባይል ስልኩ📱 ብዙ ጊዜ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን
5⃣.በሞባይሉ📱 ውስጥ የሚገኘው ባትሪ ጥሩ ሳይሆን ሲቀርና ሲበላሽ
6⃣.ሞባይል ስልኩ ቻርጅ እየተደረገ ግልጋሎት ሲሰጥ ለምሳሌ ጌም ሲጫወቱ ቪዲዮ ሲመለከቱና ኢንተርኔት ሲጠቀሙ
7⃣. ለሞባይል ተጠቃሚው በማይታይ መልኩ አፕሊኬሽኖች ከበስተጀርባ ሲሰሩ (ፕሮሰስ) ሲያደርጉ
8⃣. በሞባይሉ📱 ላይ የሚገኘው ቻርጅ መሰኪያ (Usb port) ብልሽት ሲገጥመው... ሲጣመም ሲሰበር
9⃣. በሞባይሉ ላይ የሚገኘው ቻርጅ መሰኪያ (Usb port) በቆሻሸ ሲያዝና ሲደፈን
🔟. በሞባይሉ ላይ የሚገኘው ቻርጅ መሰኪያ (Usb port) የመስመር ወይም ውስጣዊ ችግር ሲኖርበት።
‼️Join & Share
📢 @Info_Tech_Et
👥 @Info_Techs_Group
🚨Safaricom
⚠️ሳፋሪኮም እስካሁን ምንም አይነት #የቴሌግራም_ቦትም ሆነ በሪፈራል ሊንክ ሽልማት የሚያስገኝ ነገር የለውም።
‼️ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ።
‼️መረጃዉን በማጋራት ወዳጆን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።
@Info_Tech_Et
✳️ WPS WPA TESTER #PREMIUM V4.0.1:
Wi-Fi hack ለማድረግ ለምትፈልጉ
°Wifi ያለበትን ቦታ ከነ ፓስወርዱ የሚነግር ምርጥ app ነው።
°ስትጠቀሙ #Wfi እና #Location ማብራት እንዳትርሱ🙏
°እናንተ ቻናላችንን ለወዳጆ በማጋራት እና #Notification #On በማድረግ ድርሻ ይወጡ!