እውነተኛ እረፍት !
ዛሬ ለአብዛኞቻችን የዕረፍት ቀናችን ነው ከስራ ጫና ፣ ከአለቃ ትዕዛዝ ፣ ከአስተማሪ ቁጣ ፣ ከተማሪ ረብሻ ወጥተን የራሳችንን ፈቃድ የምናደርግበት የሳምንቱን ጫና ኡፎይ ብለን የምናራግፍበት ቀን ነው!
እናም ይበልጥ ኡፎይ ለማለት የአእምሮዓችንን የውስጣችንንም ጫና እርግፍ አድርገን መጣል አለብን። በምን?ካላችውኝ
በይቅርታ እላችዋለው ውስጣችን የተቀበረ ቂም ያልተውነው ነገር ሁሉ ሸክም ነው የፈለገ እረፍት ላይ ነኝ እየተዝናናው ነው ብትሉ ይቅር ያላላችውት ነገር ካለ ሙሉ ለሙሉ ልባችው አያርፍም!
ከዛሬ ጀምሮ የማረፍ ኡፎይ የማለት እድል ተሰጥቷችዋል ! ዛሬ ጀምሮ ላስቀየሟችው በመደወል ይቅር ብያለው በሉ ለራሳችውም ይቅርታ አድርጉለት! ተጠቀሙበት !
መልካም ሰንበት ተመኘኝ 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ያልፋል!
የማይቻል ነገር የለም ማለፍ ያቅተኛል ያልከው ሁሉ ይታለፋል አይቻልም የተባለ ሁሉ ሲቻልም አይተናል ዛሬ ላይ አልመስል ይበል እንጂ ነገ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል !
"በፈጣሪ የታመነ እናም የበረታ ሁሉ ከጫፉ ሳይደርስ አይቆምም!"
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
እውቀት ነፃ ያወጣል!
ብዙ ግዜ ዋጋ የምንከፍለው ባለማወቅ ነው! ሳናውቅ ወደ ጥፋት እንገባለን ሳናውቅ ስህተቶችን እንሰራለን ሳናውቅ እንበድላለን!
እናም ይህን ያደረጉት እኮ ስላላወቁ ነው ብሎ ስህተታችን ልክ ሆኖ አይገኝልንም ነገር ግን ከስህተትም ቢሆን መማር በራሱ ማወቅ ነው!
"ስለዚህ አለማወቃችን ሰበብ ስለማይሆንልን በተቻለን መጠን ለማወቅ እንጣር በየግዜው እንማር"
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
መሄጃህ ከፊት መሟሪያህ ኋላ ነው!
ሁሌም ስትራመድ ወደፊት ተራመድ ስትወድቅም ወደፊት ውደቅ ምክንያቱም ከወደቅህበት ስትነሳ ከነበርክበት ትንሽም ብትሆን ከነበርክበት ወደፊት ሄደህ ነው ምትነሳው !
"ነገር ግን ወደኋላ ዞር ብለህ ማየትህን አትርሳ ምክንያቱም የኋላው ታራክ ብዙ ትምህርት አለው እናም ደሞ ምን ያክል ርቀት እንደተጓዝክ መለኪያም ነው!"
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ራሳችንን እንስራ !
ጆርጅ በርናንድ ሾው ባንድ ወቅት "ህይወት ማለት ራስን ማግኘት አይደለም ራስን መስራት እንጂ " ብሏል ፤ እኔ ማነኝ ምንድነው መስራት የምችለው አቅሜስ ምንድን ነው ብለን በጠየቅ ቁጥር የማያልቅ ምላሽ አናገኛለን!
ሁሌም ቀን እየጨመርን ከፍ እያልን በሄድን ቁጥር ይበልጥ ከፍ ያለ እውቀት ይበልጥ ከፍ ያለ አቅም እየኖረን ነው የሚመጣው!
" ስለዚህ ማነኝ ስለሚለው ሀሳብ ከመጨነቅ በላይ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ያኔ አቅማችን እኛነታችንን ይገለፀዋል !"
ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለመሙላት እንጂ ለሟሟላት የመጣ የለም!
አዚህች ምድር ላይ የተፈጠርነው ያለ ምክንያት አይደለም ! አሁን ያለነውም እድል ስለተሰጠን ነው ስለዚህ ይህችን ምድር ምቹ መልካም እና ሰላማዊ የማድረግ ግዴታ አለብን !
" ለውጥ መፍጠር ለእከሌ ወይም ለአንድ ሰው ብቻ ተብሎ የተፃፈ አይደለም የሁላችንም ስጦታ ነው!"
መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሳታልፍ በፊት ኑር!
በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው።
ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ!
ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
የምናወጣው ቃል !
ዝም ማለት ያለማወቅ ምልክት አይደለም ወይም ስለተናገርን ጠንቅቀን አውቀናል ማለትም አይደለም ነገር ግን የምንናገራቸውን ነገሮች ጠንቅቀን መለየት መቻል አዋቂነት ነው !
" እያንዳንዱ ከእኛ የሚወጣ ቃል ሌሎች ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም እና ልንጠነቀቅለት ይገባናል !"
መልካም ቀን ተመኘኝ 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
እሺ ዋጋ ያስከፍላል !
ስቲቭ ጆብስ " አሁን ላለሁበት ስኬት ያበቃኝ እሺ ካልኩት ይልቅ እምቢ ያልኩት በመቶ እጥፍ ስለሚበልጥ ነው " ይላል
ሁሌም ያላመንባቸውን ትክክል ያልሆኑ ነገሮች ወደ እኛ በመጡ ቁጥ አይሆንም አምቢ ካላልናቸው መልሰው እኛንው ዋጋ ያስከፍሉናል !
"ስኬታማ ለመሆን የፈለገ ሰው እምቢ ማለትን መልመድ አለበት "
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
የራሱ ግዜ አለ!
ፈጣሪ ለሁሉም ግዜ አለው ስራህን ዝም ብለህ ስራ መቼ እንደሚወጣ ፣ መቼ እንደሚከፍልህ ፣ መቼ ዋጋ እንደምታገኝበት አታውቅም ስለዚህ መሞከርህን አታቁም !
" ከእኛ ግዜ በላይ የፈጣሪ ግዜ ድንቅ ነው "
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
አዳምጥ !
የማናውቀው ነገር ካለ ሁሌም መጠየቅ መልካም ነው ነገር ግን ስንጠይቅ ለማወቅ እንጂ ለመከራከር ወይንም አስተያየት ለመስጠት ብለን አይሁን ለማወቅ ከልብ ማዳመጥ ያስፈልጋል !
" አለማወቅ ክፋ ነው ከመንገድ ያስቀራል "
መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ጌታችን እኛን ለማዳን ሲል ስለሀጢያታችን ብዛት ሳይሆን ስለፍቅሩ ኋያልነት ሰው ሆኖ ተወልዶ ስቃያችንን ሊሰቃይልን ሞታችንን ሊሞትልን መጥቶ የፍቅርን ጥግ አስተምሮናልና !
ለሰዎች ያለንን ፍቅር ምን ያህል መሆን ይገባዋል ስንል ጌታችን ምን ድረስ ሰጠን ብለን እንመልከት ያኔ የፍቅር ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ገብቶን እርስ በእራስ ስንፋቀር እንኖራለን ! ፍቅር በምድራችን ይብዛልን !
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችው በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የአብሮነት ይሁንልን ይሁንላችው !
የፍቅር በዓል ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
እመን !ፈጣሪን ጠይቀኸዋል አይደል? የምትፈልገውን የማትፈልገውን ሁሉን ያውቃል አይደል?
ታድያ የምን መጨነቅ ነው ችግርህን ከሁሉ በላይ ለሆነው እኮ አሳልፈህ ሰጥተኸዋል የሚስተካከልበት ትክክለኛ ቦታ እኮ ልከኸዋል ! ከፈጠረህ ፈጣሪ በላይ ስለራስህ ታውቃለህ ?
ጠይቀኸዋል አይደል ይደረግልሀል ! ስለዚህ ነፃ ሆነህ ደስ ብሎህ ኑር !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለራስህ ዋጋ ስጥ !
በህይወትህ እያጋጠመህ ያለውን ችግር ችላ አትበለው ! እህቴ እያወላወልሽ ከተቸገርሽ ነገሮችን በምታስቢያቸው ሳይሆን ባልፈለግሻቸው መንገዶች እየተከናወኑ ከሆነ !
ያቀድሽውን ነገር ለማሳካት ከተቸገርሽ እድልሽ ሆኖ ሳይሆን አንድ ሳታውቂው እየያዘሽ ያለ ያለፈ ታሪክ ፣ ልማድ ወይም ደግሞ ያልታከመ ማንነት ኖሮ ነው!
እናም ወደራስሽ ዞር ብለሽ የችግሩን መሰረት ከስሩ ለማጥናት እና ለመቀየር ስሪ ! ሁሌም ለራሳችን ትኩረት ሰጥተን መንገዳችንን የማስተካከል ግዴታ አለብን!
ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
✅ የአንቺ ምርጫ ነው !
ዝናቡን ማስቆም አትችይ ይሆናል ዣንጥላ መያዝ ይሁን በዝናቡ መደነስ የአንቺ ምርጫ ነው !
በህይወት የሚያጋጥምሽንም ኪሳራ ፣ መከዳት ፣ ተቀባይነት አለማግኘት ፣ መከልከል ፣ ተስፋ መቁረጥና ሀዘን ማስተካከል ለአንቺ ከብዶሽ ይሆናል ፤
ታዲያ ከዝናቡ ጋር ምን አገናኘው ?
አሁንም የሚገባትን የምትጠይቅ ፣ ወደቀች ሲሏት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ሆና የምትነሳ ፣ መብትዋን የምታስከብር ፣ የይቅርታ ልብ ያላት ደፋር እና ከማንም የማትጠብቅ በራሷ የምትተማመን ሴት ለመሆን እኛን መቀላቀል የአንቺ ምርጫ ነው !
ባለሽበት ቦታ ሆነሽ በኦንላይን ለ 6 ሳምንታት በሚቆየው ስልጠናችን ከዚህም በላይ ብዙ ታተርፊያለሽ !
18ተኛው ዙር ስልጠናችን ረቡዕ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ይጀምራል !
ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን ፣ በቴሌግራምና ዋትስአኘ መልዕክት ይላኩ !
☎️ +251944314544
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ፍርሀት !
ለምንድነው የምትፈራው ? ምን ላለማጣትስ ብለህ ነው ከመንገድህ የቆምኸው? ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ላለማድረግ ምን ገደበህ?
አለም ላይ የተሰጠህ እድሜ በሙሉ ያንተ ውድ ስጦታ ነው ! እያንዳንዷን ግዜህን በፈለግኸው መንገድ ልትጠቀምባት ተፈቅዶልኋል የምታደርገውን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው!
ብትከስር እንኳን መነሳት ትችላለህ ብትወድቅም ድገሚ ከፍ ማለትህ አይቀርም ስለዚህ ወንድሜ ባታደርገውም የሚሆነው መሆኑ አይቀርምና ወደፊት መራመድን አትፍራ !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ይሄን ጥያቄ ጠይቅ!
አሁን እያደረግህ ያለኸውን ነገር እያደረግኸው ያለኸው ለምንድን ነው? ሰዎች አድርግ ስላሉህ? ይሄን ማድረግ ይገባኛል ብለህ ታስብ ስለነበረ ?
ወይንስ ድንገት አጋጣሚ ሳታስበው እያደረግኸው ነው ራስህን ያገኘኸው?
"ዛሬ አንድ ነገር ብቻ ላስቸግርህ ትንሽ ደቂቃ ቆም በልና ይሄንን ጥያቄ ለራስህ ጠይቀው ለራሳችን መልስ ስናገኝ ነው ነገሮቻችንን ማስተካከል የምንችለው !"
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም በፍቅር በጤና አደረሳችው አደረሰን መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችው!
መልካም በዓል ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሁሉም በግዜው ነው የሚሆነው!
በጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ሀይለኛ ፀሀይ ብትወጣ እና ለማየት ብትሞክር ምን ያጋጥምኋል? ፀሀዩ አይንህን ያጨናብስሀል !
ይህች ፀሀይ ድምቅ ያለችው ቀን ስድስት ሰዓት ላይ ቢሆንስ ይህን ያህል አትረብሽህም አይደል? ምክንያቱም ብርሀኑን ለምደኸዋል እንደጠዋቱ ከጨለማ አይደለም የተቀበልካት!
"ስለዚህ ህይወትም እንደዚህ ነው በአንዴ ሁሉን ነገር ልወቀው ወይ ይሳካልኝ አትበል ሁሉም በጊዜው እና በሰዓቱ መሆኑ አይቀርም አንተ ግን ከብርሀኑ ጋር እየተለማመድክ ጠብቀው !
"ፀሀዩ መች እንደሚወጣ አታወቅም"
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ህግ ይኑርህ !
ሁሌም ቢሆን መስመር ማበጀት አለብህ ፣ የራስህ ህግ ይኑርህ ፣ ማንም የማያልፍብህ ማንም የማይጥስብህ ህግ አውጣ !
ይህን ስታደርግ ለማሸነፍ ስትጓዝ የሚረብሽህ አይኖርም መጀመሪያም ካልፈቀድክላቸው መስመርህ ጋር አይደርሱም ! ስለዚህ በነፃነት ትጓዛለህ።
የፈጣሪ ድንቅ ፍጡር ነህና ድንቅ ነገር ብቻ ስራ!
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ብቻ አንተ አታቁም !
የሰው ልጅ ተዓምር የሚፈጠርለት ቀን አለው ! አያውቀውም ነገር ግን እየለፋ እየጣረ ከልቡ እየሞከረ ከቆየ እና መልፉቱን ካላቆመ የሆነ ቀን ታሪኩ ይቀየራል የሚያልመው ሁሉ ይሳካል !
"ስለዚህ እንዳትቆም ተስፉም እንዳትቆርጥ ግዜህ ሲደርስ ሁሉም ይሳካል "
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
አክብር !
ሁሉም ሰው የተለያየ ነው በመልክ ፣ በቁመና ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ ባለው የሀብት መጠን በመሳሰሉት ሁላችንም የየራሳችን ልዩነት አለን ነገር ግን አንድ የሚያደርገን ትልቅ ነገር አለ
" ሰውነት ! "
ፈጣሪ ከፍጡሩ ሁሉ የበላይ አዛዥ አድርጎ ሰርቶናል ! በሀብት መጠናችን ወይ በዝናችን አልለየንም ለሁላችን እኩል ክብር ሰጥቶን እኩል ፀሀይ ና ጨረቃን ያበራልናል !
" ታድያ የፈጠረው ፈጣሪ ባለው ነገር ያልናቀውን ሰው እኛ ምን ብለን ነው የምንንቀው እኩል ያከበረን ፈጣሪ ነውና ሁሌም መከባበር እንልመድ "
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
በራስህ እመን!
ለራስ አነስተኛ ግምት አትስጥ! ፈጣሪ ለታላቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር ያመጣህ። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ነገ ከፍታው ላይ እንደምትወጣ ማሰብ እና ማመን ከዛ የምትችለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብህ!
ሰዎች ባንተ ከማመናቸው በፊት አንተ በራስህ እመን፤ ወዳጄ አሁን ያለህበት ሁኔታ ነገ የምትደርስበትን ትልቅ ቦታ አይወስንም!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
🛑 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው
1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ አላማና ህልም ያለው አገልጋይ ትሆናለህ፤
2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤
3. የመጣህበትን አትርሳ ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
✅ 1 ቀን ቀረው !
ነገ ማክሰኞ ከምሽቱ 12:00 በሮች ሁሉ ይዘጋሉ ከወዲሁ ተመዝግባችሁ ቦታ መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ !
18ተኛው ዙር የኦንላይን ስልጠናችን የፊታችን ረቡዕ ይጀምራል ( 📍ባሉበት ቦታ በምቾት )
ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።
☎️ +251944314544
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
በፍቅር ኑሩ !
ምድር ላይ ስትኖር ከልብህ ፍቅር ካለህ እና ከልብህ በፍቅር ከኖሮክ ጊዜያት ያጥሩብኋል መቼ እንደሚያልቁ እንኳን ሳታውቀው ያልቃሉ !
ምክንያቱም ሰው ደስተኛ የሆነበት ቦታ ላይ አስር ዓመት ቢቆይ እንደ አስር ቀንም አይቆጥረውም !
ስለዚህ አለም እንድታስደስትህ አንተም ከልብህ ፍቅር በመስጠት አስደስታት !
የደስታ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
አልተፈፀመም!
ብዙ ፊልሞች አይታችሁ ከሆነ አጨራረሳቸው ያማረ ነው። የምንፈልገውን ነገር ለማሳካት ስንሮጥ እንደዛ ማሰብ መጀመር አለብን፤ በቃ አጨራረሱ ካላማረ ያ ነገር አልተፈፀመም ማለት ነው! ስለዚህ እጃችን እስኪገባ እንታገላለን እንጂ ማቆም የሚባል ነገር የለም!💪
የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ከሰዎች ብዙ አጠብቅ!
ሰዎች የማይረዱህ አንተ ጋር እውነት ስለሌለ አይደለም፤ ልፋትህን የማያደንቁልህ እየጣርክ ስላልሆነ አይደለም፤ ለመልካምነትህ መልሳቸው ተቃራኒ የሆነው አንተ ጋር ችግር ኖሮ አይደለም።
ችግሩ ካንተ መልካምነት አይደለም፤ ችግሩ ከነሱ አንድ ነገር መጠበቅህ ላይ ነው። ከሰዎች ምንም አጠብቅ፤ የማይታለፍ የሚመስለውን አሳልፎ ለዛሬ ያደረሰህ ፈጣሪ ነው፤ ከሱ ብቻ ጠብቅ! አለቀ! ወዳጄ ካንተ የሚጠበቀውን ግን ሁሌም ማድረግ አትርሳ!
የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
እንደምትቀይረው እመን!
ጂም ሮን የተባለ ደራሲ ላንተ ብሎ ፑሽ-አፕ (ስፖርት) እንዲሰራልህ ሌላ ሰው አትቀጥርም ስለዚህ ከሌላ ሰው ብዙ አጠብቅ ይለናል። የኛን ሸክም ማንም አይሸከምልንም፣ እንደውም እኛ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሸክም ማቅለል እንደምንችል ማመን አለብን።
አሪፍ ነገር ስናገኝ በልፋቴ እንደምንለው ከባድ ነገር ሲገጥመንም በጥፋቴ ማለት አለብን። የኛ ጥፋት መሆኑን ስናምን ለመፍትሄው ግማሽ መንገድ ተጉዘናል። ሰበብ እንደሚያበዛ ሰው ቆሞ የሚቀር የለም!
ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል!
ታሪክ መስራት ከፈለክ አብዛኛው ሰው የማያደርገውን ማድረግ አለብህ፤ ሌላው ሲተኛ አንተ ትነሳለህ፣ ሌላው ጊዜውን በከንቱ ነገር ሲያጠፋ አንተ ራስህ ላይ እና ስራህ ላይ ታጠፋለህ፣ ሌላው ገንዘብ ሲያጠፋ አንተ ታስቀምጣለህ፣ ሌላው ወደ ፈጣሪው ለመቅረብና ፀሎት ለማድረስ ጊዜ ሲያጣ አንተ ይበልጥ በመንፈሳዊነትህ ትጠነክራለህ!
ወዳጄ የተለየ ነገር ከፈለክ የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል፤ ደስ የሚለው ምን ማድረግ እንዳለብህ አውቀህ መንገዱን ጀምረሀል፤ ማን እንደሆንክ ለራስህ ሳታሳየው ማቆም የለም!
አስደናቂ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!