inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ከፍ ማለት ትፈልጋለህ?

ክፍተቶችህን ለመሙላት ራስህን ለማስተካከል ከነበርክበት ተነስተህ ወደ ከፍታ ለመጓዝ ትሻለህ ?

የያዝከውን ብቻ እንደያዝክ ለመሄድ ከሞከርክ ብዙ ርቀት ለመጓዝ ይከብድኋል ነገር ግን አዳዲስ ነገሮችን ለመቀበል ራስህን ክፍት ካደረግህ ስህተቶችህን ለማረም ዝግጁ ከሆንክ የምትመኘው ቦታ ብቻ አይደለም ከዛም በላይ ከፍ ብለህ መብረር ትችላለህ !

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ያለህ በቂ ነው !

መስጠት የተለየ ነገር መያዝን አይጠይቅም ! አይደለም ሰው ሆነን የተፈጠርን እኛ ይቅርና ድንጋይ እንኳን ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም ይሰጣል !

ገንዘብ የለኝም ምን ኖሮኝ ጠቅማለው ምንስ መስጠት እችላለው አትበል ባንተ እጅ መዳበስ በርታ መባል በቂው የሆነ ብዙ ሰው አለ ! ካለህ ንብረት በላይ ፍቅርህን ለማግኘት የሚጓጓው ብዙ ነው የማያልቅ በነፃ የተሰጠህ ፍቅርህን ለሁሉም ስጥ!

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ትልቁ መድኋኒት !

ማመስገን ምንም ጉልበት ሳናፈስ ብዙ ደሞዝ የምናገኝበት መንገድ ነው ! ለንዴት ፣ ለድብርት ፣ ለመጥፎ ስሜት በሙሉ መድኋኒት መዋጥ ሳይጠበቅብን የምንፈወስበት ትልቁ መዳኛችን ነው !

"ስለዚህ መድኋኒታችንን በየቀኑ ሳናዛንፍ እንዋጠው የእድሜ ልክ ፈውስን እናገኝበታለን !"

መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያችሁን 🙏

የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ወደ ትዳር ይገባል ነገር ግን ከገባ በኋላስ ?

ከዚህ በፊት አስበናቸው የማናውቃቸው ትዳር ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ ብለን ከግምት ያላስገባናቸው 3 መፍትሄዎችን ዛሬ እናያለን ከዚህ ቪድዮ በኋላ የትዳራችን ብቻ ሳይሆን የእኛም ሰላም ይመለሳል!

በ Inspire ethiopia media ላይ ታገኙናላችው !

https://youtu.be/70O3Tg8j8xI

መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዛሬም ተሰጥቶናል !

ነቅተናል ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ፤ የሰው ልጅ ከነቃ አዲስ ቀን ከተሰጠው እድል አለው ማለት ነው ረፍዷል የሚባል ነገር የለም!

እድሜዬ ሄዷል አቅም የለኝም ከዚህ በኋላማ ምን ሊፈጠር ብሎ ነገር የለም ዛሬም እስካለህ ድረስ ማድረግ የምትፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ መጀመር ትችላለህ !

"ፈጣሪን የምናመሰግነው በአፋችን ብቻ ሳይሆን በምግባራችንም ነው !"

መልካም ሀሙስ ተመኘኝ 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን አክብር !

ሰዎች ላንተ
የሚሰጡህ አክብሮት አንተ ለራስህ ከምትሰጠው ቦታ አይበልጥም። ስለዚህ ሰዎች እንዲያከብሩህ ከፈለግክ መጀመሪያ ራስህን አክብር ፤ ግድ የለሽ አትሁን !

በጣም የምታደንቃቸው የምታከብራቸው ሰዎች የሚያደርጉትን ተመልከት ፣ ኮርጅ እንደውም የእነሱን ጥሩ ልማዶች ስረቅ። ፖብሎ ፒካሶ "ጥሩ አርቲስቶች ይኮርጃሉ ፤ ምርጦች ግን ይሰርቃሉ" ይለናል።

አስደሳች ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እንችላለን !

ለራሳችን የምንነግረው ነገር ህይወታችንን ሊያስተካክለውም ሊያበላሸውም ይችላል።

በህይወት ውስጥ ከባድ ነገር ቢገጥመን እንኳን በተቻለን አቅም ለራሳችን እንደማንችል መንገር የለብንም ምክንያቱም እያንዳንዱ የምናወጣው ቃል ለጆሮአችን ቅርብ ነው።

ጣፋጭ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የፈለግኸው ይሆናል !

" ከልባችን አጥብቀን የፈለግነውን ነገር እንድናገኝ በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ ይመሳጠራሉ" ይለናል ፖውሎ ኮሊዮ

ብቻ የእውነት ፈልግና ከልብህ ሞክር ፈጣሪ የሚያመቻቹልንን ሁሉ እየቀደመ ያዘጋጅልናል !

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከሰው አትጠብቅ !

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ
ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ።

የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው። ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

የተባረከ ሰንበት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወደ ከፍታ !

ረጅም ፎቅ መሥራት የሚያስብ ሰው ወደታች ረጅም መሠረት መሥራት አለበት ። እኛም በህይወታችን ትልቅ ነገር መሥራት ሥናስብ ልክ ፎቅ ወደ ላይ ለማቆም ወደ ታች አንቆፍርም አንደማንለው ሁሉ 

በህይታችንም ፈተና ሲያጋጥመን ወደ ላይ ነጥረን ለመውጣት ጠንካራ መሠረት እየሰራን አንደሆነ አስበን በደስታ እና በምስጋና ከስህታችንም አየተማርን እንጠብቅ !

ጣፋጭ ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ህይወት ጣፋጭ ናት!

ልክ እንደ ፊልም በፍፁም የማይጠበቁ ነገሮች አሏት እኛ የሆነ አንድ ነገር ልናሳካ እየሄድን ሌላ ብዙ ያልታሰበ ነገር አሳክተን እንመለሳለን! ነገን ስለማታሳውቅ ታጓጓለች!

መቼና እንዴት መሆኑን ባናውቅም ለማሳካት እንሂድ እንጂ የማናሳካው ነገር አይኖርም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉ መልካም ይሆናል!

መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወደ ተግባር !

ወንዙ ላይ አፍጥጠህ ስለ መሻገር ማሰብ እና ማቀድ ብቻ አያሻግርህም መርከብህን አስጠግተህ መቅዘፍ መጀመር አለብህ !

ስኬትም እንደዚሁ ነው አብዝተህ ስላሰብከው ወይ ስላወራህለት ብቻ አታገኘውም ውጤቱ የሚመጣው ወደ ተግባር መግባት ስትጀምር ነው! ሰዓቱ አሁን ነው ምንም ሳታቅማማ ከአሁን ጀምር!

ብሩህ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እያደረግህ ነው !

'የሞተን ውሻ ማንም እንደማይደበድብ እወቅ' ይለናል ዴል ካርኒጌ፤ በህይወታችን ውስጥ ጫና እየደረሰብን ችግሮች ፈተናዎች እየተደራረቡብን ከሆነ እየኖርን ነው ማለት ነው። ችግሩ ምንም ጫና እና የሚያሳስበን ነገር ከሌለ ነቃ ማለት አለብን!

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አቅምህን እወቅ !

የምትችለውን ብቻ አድርግ ከአቅምህ በላይ የሆኑትን ለፈጣሪህ ስጥ ! ራስህን በብዙ ካስጨነቅኸው ቀላል የሆኑትንም ነገሮች ማድረግ የምትችልበትን አቅም ታጣለህ !

እናም ከሁለት ያጣ ሆኖ ከመቅረት የያዝከውን ይዘህ በርታ !


መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉንም ለማስደሰት አትሞክር!

አንድ ሹፌር በመንዳት ላይ ሳለ ለመሻገር ሰፍ ብለው ከፊቱ የቆሙ ሰዎችን ለማሻገር ቢቆም ፦

ተሻጋሪዎቹ እያመሰገኑት በደስታ ያልፉሉ ከኋላ ያሉ አሽከርካሪዎች ግን አስቁሟቸዋል እና በስራው በጣም ይናደዳሉ! ሁሉም ይደሰቱብኝ ካለ ግን ምን ያደርጋል? ስለዚህ ልብህ የሚጠይቅህን እንጂ ሰዎች ያስቡታል ምትለውን አታድርግ!

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ኮርጅ !

መሆን የምንፈልገውን ነገር ምን እንደሆነ ካወቅን ብዙ አቋራጭ መንገዶች አሉ፤ ምክንያቱም ከኛ ቀድመው እኛ መሆን የምንፈልገውን ያሳኩ ብዙ ሰዎች አሉ

ከእነርሱ የህይወት ልምድ ብዙ ነገር ለራሳችን መውሰድ እንችላለን። 'ከሌሎች ህይወት መኮረጅ ጥሩ ነገር ነው፣ መስረቅ ግን ታላቅነት ነው' ይለናል ታላቁ አርቲስት ፒካሶ።

ውብ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ማን ያውቃል !

ለማማረር አትቸኩል ለመውቀስም ፋታ ስጥ ነገሮች የሚሆኑበትን ምክንያት አታውቅም የጠየከው ጥያቄ የሚመለስበት አንዱ መንገድ አሁን በዚህ ሰዓት የተፈጠረብህ አጋጣሚ ይሆናል!

ስለዚህ እንዳይቆጭህ ስትል መውቀሱን ትተህ በተስፋ ጠብቅ ሁሉም ለበጎ ነው!

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ውብ ጊዜያትን ለማሳለፍ!

🔴ሁለት ነገር ቀናችንን ያበላሽብናል
         1. ስለ ትናንት ማሰብና
         2. ከሰው ጋር ውድድር

🟡ሁለት ነገር ቀናችንን ያስተካክልልናል
         1. ያለንን ማመስገንና
         2. ዛሬን መኖር

🟢ሁለት ነገር ነጋችንን ያሳምርልናል
         1. እቅድ ማውጣትና
         2. በቂ ምክንያት ማስቀመጥ

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አንተ ቅደም !

ከራሱ ጋር ሲሆን ሰላም ያልሆነ ሰው ከቀረው አለም ጋር ሊስማማ አይችልም ፤ ስለዚህ መጀመሪያ ከራስህ ጋር ታረቅ! ያኔ ለአለም ሁሉ መትረፍረፍ ትጀምራለህ !

መልካም ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

🫡 ወደፊት ... ሂድ !

እኛ ስንወድቅ የምንወድቀው ብቻችንን አይደለም ፤ በእኛ የተማመኑ ለእኛ እዚህ መድረስ ዋጋ የከፈሉ ፣ በብዙ የተፈተኑ ቤተሰቦቻችንም አብረው ይወድቃሉ!

ላንተ/ላንቺ እዚህ መድረስ ዋጋ የከፈለው ማን ነው? ልትቆም ስታስብ ያንን ሰው አስታውስ ለእርሱ/ሷ ስትል በርታ !!!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አሸናፊ ለመሆን!

እነዚህን 3 ነገሮች አድርግ

1. ጥፋቶችህን በሰው አታመካኝ
2. ራስህን አትውቀስ
3. ስለተደረገልህም ስላልተደረገልህም  ነገር አመስግን

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የአንተም ጊዜ አለ!

ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አያበሩም፤ እኩል እናብራም ቢሉ ተፈጥሮ አትፈቅድላቸውም ግን ሁለቱም በራሳቸው ጊዜ ማብራታቸው አይቀርም።

አንተም አጠገብህ ያለ ሰው ሲሳካለት አይተህ የእኔስ ቀን መቼ ነው ? ምነው ፈጣሪ ዘገየ ካልክ እንደፀሀይ በቀን እንደጨረቃም በጨለማ የምታበራበት ቀን አለና በተስፋ ተራመድ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ብቻ አትቁም !

'መሮጥ ቢያቅት ተራመድ...መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል....ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተኝፏቀቅ...ግን እንዳታቆም' ይለናል ማርቲን ሉተር።

ወዳጄ ያበቃልህ የተሳሳትክ ወይም የወደክ ጊዜ አይደለም...የሚያበቃልህ በቃኝ ብለህ ያቆምክ እለት ነው።

"ስለዚህ የጀመርከውን በፍፁም እንዳታቆም! እንዳታቆሚ! አናቆምም!"

ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተስፋ !

"ተስፋ ያለው ሰው የሚመለከተው መከራዎቹን ሳይሆን መከራዎቹን እንዲያሸንፍ የሚያደርገውን ፈጣሪውን ነው !"

ነገሮች እንዳሰብካቸው እየሄዱልህ ባይሆንም ,እዳ ውስጥ ተዘፍቀህ መውጫው የጠፉህ ቢመስልም መንገዱን ፍለጋ ስትወጣ ፈጣሪን በእምነት ያዘው ያኔ አይሆንልኝም ያልከው ሁሉ ሆኖልህ ታየዋለህ !

ሰናይ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉም ይቻላል !

ኦፕራ ዊንፍሬ "የዚህ አለም ትልቁ ምስጢር ምንም ሚስጥር አለመኖሩ ነው ስራውን ለመስራት ዝግጁ ከሆንን አላማችን ምንም ይሁን እናሳካዋለን!" ትለናለች።

በህይወታችን ልናሳካ ለምንፈልገው ነገር የምንከፍለው ዋጋ ተመጣጣኝ ከሆነ በእጃችን የማይገባበት ምንም ምክንያት የለም። እውነት ነው ምንም ምስጢር የለውም።

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈጣሪ ሁሌም አለ !

"በምትሄድበት ሁሉ ፈጣሪ ከአንተ ጋር ነው እና ጽና አይዞህ አትፍራ ! "ይላል ታላቁ መፀሀፍ ማድረግ አልችልም እንዴት ይሆንልኛል ያልነው ሁሉ በማይተወን እና በማይለየን አምላክ እገዛ ሆኖ እናየዋለን!

ብቻ መሄድ የምንፈልግበት ትክክለኛ ቦታ ሁሉ ሳናቅማማ እንሂድ ለማሳካቱ አብሮን ያለው ፈጣሪ ያግዘናል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አሁኑኑ ጀምር !

አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን የሚመነጩት ልንሰራ ያሰብነው ነገር ከባድ ወይም ብዙ ስለሆነ አይደለም የጀመርነውን ቀላል ነገር ስላልጨረስን ነው።

እጅህ ላይ ያለው ምንድን ነው ? ስለዚህ አሁኑኑ ምንም ጊዜ ሳትወስድ ተነሳና አስተካክለው ! የጀመርከውን ቶሎ ጨርስ ያኔ ለቀጣዩም መንገድ ትከፍታለህ!

መልካም ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምን ሊያስተምረኝ ነው?

ትልቁን ትምህርት የምታገኘው ከትልቁ ስህተትህ ነው፤ የማትረሳውን ደስታ የምታገኘው ከከባድ ጭንቀትህ በኋላ ነው።

ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው፤ የገጠመኝ ነገር ምን ሊያስተምረኝ ነው በል ምክንያቱም የአንድ ነገር መጨረሻ የሌላው ነገር መጀመሪያ ነው።

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተረስተህ አይደለም !

የምትፈልገው ነገር አልሆን ሲልህ ሲዘገይብህ ፈጣሪ ረስቶኝ እኮ ነው አትበል ፤ በደንብ ጮክ ብለህ ጥራው በአፍህ ሳይሆን በምግባርህ ጥራው !

በቃላትህ ሳይሆን በምትሰራው መልካም ስራ ጥራው ! ፈጣሪ በፍፁም አይረሳም ነገር ግን የራሱ ግዜ አለው !

መቼ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል ስለዚህ ሁሌም ወደራስህ ተመልከት የሚገባህ ሰው ለመሆን ጣር ምግባርህን አርቅ እርሱም ያይሃል ሲገባህ ይሰጥሃል !

ደስ የሚል ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለራሳችን ነው !

መልካምነት ለራስ ነው መስጠት ለራስ ነው መቀበልም ለራስ ነው የምናደረገውን ሁሉ የምናደርገው ለሌላ ለማንም ብለን ሳይሆን ለራሳችን ነው !

ጓደኛዬ እንዳይደብራት ብዬ እኮ ነው ያደረግኹት ብንል በእርሷ መደበር ውስጥ እኛ የምናጣው ነገር አለ ማለት ነው !

ስለዚህ ሰዎች ውለታችን እንዳለባቸው አንቁጠር የሆነው ሁሉ የሆነው እንዲሆን ስለፈለግነው ነው ከዚህም በኋላ ስታደርግ፣ስትሰጥ ሌሎች ስለሚጠቅማቸው ብቻ ሳይሆን አንተ ስለሚያስፈልግህ እንዳደረግኸው ልታውቅ ይገባል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel