inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ሁሉም በግዜው ውብ ነው !

አይሆኑልኝም ያልኳቸው ሁሉ በፈጣሪ ሆነውልኝ አይቻለው ትናንት የማያልፍ የመሰለኝ ሁሉ ዛሬ አልፎ ታሪክ ሆኗል !

ከብዶህ ይሆናል ባለመሳካቱ እያዘንህ ይሆናል ነገን ማየት ቀላል የማይሆን መስሎህ ይሆናል ነገር ግን ሁሉም ያልፋል ሁሉም መልካም ይሆናል እኛ ባሰብነው መንገድ ሳይሆን ፈጣሪ ባሰበልን መንገድ ሲሆን ሁሉም ብሩህ ነው!

19ነኛው ዙር ስልጠናችን ሊጀመር 5 ቀን ብቻ ቀርቶታል !


መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

6 ቀን ብቻ ቀረው !

19ነኛው ዙር  የኦንላይን ስልጠናችን ሊጀምር ነው !

🔸በየትኛውም የአለም ክፍል የምትገኙ ( አውሮፓ ፣ አሜሪካ ፣ አፍሪካ ፣ የተለያዩ አረብ ሀገራት እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች  ) ፤ በራሳችን ቋንቋ ፤ የእጅ ስልካችሁን ብቻ በመጠቀም መሳተፍ የምትችሉበት ልዩ ስልጠና !

ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር ይደውሉ ፤ በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

☎️ +251944314544

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የምናስበውን እንሆናለን !

አእምሮአችን ልክ እንደ ማግኔት ነው ይስባል የምንናገረውን የምንመኘውን ይስበዋል ሁሌም !

ትልቅ ነገርን ስለማሳካት የምናስብ ከሆነ ትልቁ ቦታ ላይ እንገኛለን ትንሽም ካሰብን ትንሹ ቦታ ላይ እንቀራለን !ስለዚህ ሁሌም ለራሳችን የምንነግረው ነገር ላይ እንጠንቀቅ!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ውሎህን አስተካክል !

አሁን ያለህበትን ቦታ የማትፈልገው ከሆነ እና የተሻለ ነገር እንደሚገባህ ካመንክ ከአሁን ጀምረህ የምትውልበትን ቦታ ቀይር የምትሰማውን የምታየውን እያንዳንዱን ነገር አስተካክል !

ከማይጠቅሙህ ነገሮች ረስህን አውጣ ነፃ ሆነህ ለማሰብ ሞክር ይሉኝታን ቀንስ ነገ ላይ ተነስተህ ራስህን ከምትወቅስ ዛሬ ላይ የሚገባህን ነገር ማድረግ ተለማመድ !

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ልማድ !

አላማ አንተ ውስጥ መሰራት የሚጀምረው ለዚያ አላማ ማስፈፀሚያ የሚሆን ጀግና ሰው ሆነህ መገኘት ስትችል ነው ይሄን ጀግና ሰው የሚፈጥረው ደግሞ የየእለት ልማድ ነው!

"ልማድ ሲሰለጥን ተፈጥሮ ይሆናል "ይለናል ቮልቴር የምንፈልገውን ማንነት ራሳችን ላይ ለመገንባንት እያንዳንዷ የየዕለት ልማዳችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላት ! ስለዚህ ልማድሽ ላይ አጥብቀሽ ስሪ!

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አሸናፊ ሁን !

ምንም ነገር ከአላማህ ሊያሰናክልህ እና ወደኋላ ሊጎትትህ ካልቻለ ወደፊት ለመጓዝ ትልቅ እድል አለህ ፤ ትልቅ ነገር ስናስብ ብዙ ግዜ ብዙ ሊያስቆሙን የሚፈልጉ ነገሮች ይከሰታሉ !

እነርሱን ረግጠን ተራምደን ማለፍ ስንችል አሸናፊዋች ሆነን ትልቁ መድረክ ላይ እንሸለማለን!

መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምስጋና !

ጎደለብኝ በምንለው ጎን ብቻ ነገሮችን ካየን ህይወት መቼም አትሞላም ! ያለንን የሞላውን ግን በደንብ ስንመለከተው ህይወት በራሷ እርካታን ትሰጠናለች ! ያለን የለንም ከምንለው ሁሉ ይበልጣል !

"ስለዚህ ጠዋት ልክ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፈጣሪዬ ሆይ ስላደረግህልኝ ሁሉ ነገር አመሰግንሀለው ብለን ያሉንን ሁሉ በዝርዝር እንመልከት "

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዛሬን በደንብ ኑር !

አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን የሚመነጩት ልንሰራ ያሰብነው ነገር ከባድ ወይም ብዙ ስለሆነ አይደለም የጀመርነውን ቀላል ነገር ስላልጨረስን ነው።

ትላንት አልፏል አንጨብጠውም ነገንም ገና አላየነውም ማስተካከል የምንችለው ዛሬን ነው ያውም አሁንን።

ብሩህ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የተፈጠርነው በምክንያት ነው !

እዚህች ምድር ላይ የመጣነው ልንሞላ ነው እንጂ ልናሟላ አይደለም ! እያንዳንዳችን የተፈጠርንበት አላማ አለ የትኛውም እድሜ ክልል ላይ እንሁን ምንም አይነት የእውቀት ደረጃ ላይ እንድረስ አንድ ማሳካት የምንችለው ነገር አለን !

"ስለዚህ ራሳችንን አላማ ያለው ምድርን በመልካም ነገር ለመሙላት የተፈጠረን ሰዋች መሆናችንን እናስታውሰው "

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ማድረግ ያለብህን .....

በሰው ዘንድ ስለሚሰጥህ ዝና እና ክብር ብዙም አትገረም ፤ በፈጣሪ ዘንድ እውቅና ማግኘትህ ግን ያሳስብህ ! ልብህን የማይሞላ ነገር ከማድረግ ተቆጠብ !

" እውነተኛ መልካም ምግባር የማንንም ማረጋገጫ ወይም ሽልማት አይሻም ስለዚህ ጥሩ ለማድረግ መስፈርት አታውጣ "

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከልብህ እመን !

በሰው መሆን አይቻልም የተባለ ሁሉ በፈጣሪ ሲደረግ አይቻለው ! የሰው ልጅ ከልቡ ሲያምን ሀይሉን ሁሉ ለፈጣሪው እየሰጠው ነው በእርሱ ላይ ታላቅ ነገር እንዲፈፀም እየፈቀደ ነው !

የፈለግኸው ምንም ይሁን ፣ የተመኘኸው የትኛውንም አይነት ነገር ይሁን ፣ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሁን ፈጣሪህን ከተደገፍህ ከልብህ ካመንህ ታሳካዋለህ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መፍትሄው ላይ አተኩር !

ፈተና በገጠመህ ሰዓት አብዝተህ የምታስበው ስለገጠመህ ፈተና እና ችግር ብቻ ከሆነ ያለህበትን ሁኔታ የሚያባብሱ ነገሮች ያጋጥሙኋል !

ነገር ግን መውጫ መንገዱን እና ማሸነፊያ ጥበቡን ማግኘቱ ላይ ይበልጥ ትኩረት ካደረግህ ዛሬ ካሳሰበህ ነገር ሁሉ ገላግሎ የሚያሶጣ መንገድ ታገኛለህ!

ስለዚህ በተቻለን አቅም እየሆነብን ስላለው ነገር ከመጨነቅ መፍትሄ ለመሆን የሚችል ብርቱ ለመሆን እንዲያበቃን አምላካችንን ቀርበን እንጠይቅ!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉም ያልፋል !

ከባድ ጊዜያት ይመጣሉ ግን ለዘላለም አይዘልቁም የመጡት ሊያልፉ ነው !

"ከእኛ በላይ ለእኛ የሚያስብልን ፈጣሪ ነው ያለን " ስለዚህ ምንም ነገር ሊያስፈራን እና ወደኋላ ሊወስደን አይገባም ! ሁልጊዜም ፈጣሪን ይዞ ወደፊት መጓዝ ነው!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ይሳካል!

የሰው ልጅ ለለውጥ እራሱን ካስነሳ እናም በቀና ልቡ መንገድ ከጀመረ ፈፅሞ የሚያቆመው አይኖርም ! መሰናክሉም ይሰበራል  ምንም አይነት ፈተና ቢመጣ ያንገዳግደዋል እንጂ አይጥለውም ! ሁሌም ወደፊት 💪

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የእውነተኛ ደስታ !

በሁሉም ነገር ቀና ሁን እኔን ብቻ አትበል ለሌሎች መልካም አስብ አለም እኔን እኔን ብቻ ካሉባት አሰልቺ ናት እኛ ስንኖር ለሌሎች ስንተርፍ እድሜያችን ይረዝማል ፣ መንገዳችን ይቀናል ፣ ተስፋችን ይለመልማል ፣ ህልማችንም እውን ይሆናል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ !

ይሄኔ በዚህ ሰዓት የሆነ ሰው ስላንተ ስኬት እየፀለየልህ ነው ! ያ ሰው ቤተሰብህ አይደለም በአካልም አያውቅህም አታውቀውም !

ግን ደግሞ ድጋፍህ ያስፈልገዋል ያንተ አላማ መሳካት ለእርሱ ህይወት እጅግ በጣም ጥልቅ ተፅዕኖ አለው ህልምህን ስታሳካ አንተ ብቻ ሳትሆን ብዙ ሰዎች ይድኑበታል !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የበፊት ሞራላችንን ለመመለስ !

🔹 በቪዲዮ ማግኘት ለምትፈልጉ ብቻ ነገ ጠዋት 2 ሰዓት በ "Inspire Ethiopia Media" ዩቲዩብ ቻናል ታገኙታላችሁ !

የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የእኛ ድርሻ ነው !

ፀሀይም ጨረቃም እኩል ነው ለሁሉም ሰው የሚያበሩት ለእከሌ አላበራም ለእከሌ ብቻ ነው የምወጣው አይሉም !

ፈጣሪ ለሁላችንም እኩል እንደሚያስብልን የምናውቀው በዚህ ተፈጥሮ ነው!

ስለዚህ ወንድሜ እኔ ተረስቻለው ብለህ ማማሪሩን ትተህ የተሰጠህን እድል ተጠቀምበት ፈጣሪ ለሁላችንም ሳያዳላ አኩል አድርጎ ሁሉን ሰጥቶናል እይታችንን ብቻ መቀየር ነው የሚጠበቅብን !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለውጤት አድርግ !

ካደረግኸው አይቀር ከልብህ አድርግ ፤ ተማሪ ከሆንክ መማርህ ካልቀረ ከልብህ ወጥረህ ተማር ለትምህርትህ መክፈል ያለብህን ዋጋ በሙሉ ክፈል !

ሰራተኛም ከሆንህ መስራትህ ካልቀረ ወጥረህ ስራ በምትሰራበት ቦታ ሁሉ ለስራህ የሚያስፈልግህን እያንዳንዱን ነገር ሳታጎድል አከናውን ፤ አደረግኩት ለማለት ብቻ ምንም አታድርግ መሆኑ ላልቀረ ነገር ታላቅ ውጤት የሚያስገኝህን ነገር አድርግ!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተጠቀምበት !

ፈተና በህይወታችን የሚመጣው እንድም ሊያጠነክረን አንድም በህይወታችን ምን እንደተማርን ሊፈትሸን ነው ! ወደኋላ ካልንለት ይጥለናል ከተጋፈጥነው እና ወደኋላ ሳንል ካሸነፍነው ግን ይሸልመናል!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ግዜህን ጠብቀው !

በገንዘብህ ጊዜንን ልትገዛው አትችልም በጊዜህ ግን ገንዘብን መግዛት ትችላለህ ፤ ይሄ ምን ያሳያል ጊዜ ንጉስ ነው  ከፈቀድህለት እና በአግባቡ ከያዝኸው ወደመልካም ጎዳና ይመራኋል !

የፈለግኸውን ሁሉ ለመጨበጥ እጅህ ላይ ለማድረግ ከፈለግህ ወይ አብረኸው ተራመድ ወይ ቅደመው ከኋላው ከሆንክ ግን ይባስ ይርቅሀል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ይቅርታ

"ይቅርታ አለማድረግ ትላንት ይቀየራል ብሎ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው " ትላንት አንዴ አልፏል ምንም ብናደርግ አንቀይረውም ዛሬ ግን በእጃችን ነው የመረጥነውን የማድረግ እድል አለን !

ነገር ግን ዛሬን ለማዘዝ ነገን መታረቅ የግዴታ ነው ካልሆነ በማንቀይረው ነገር ራሳችንን ስናባክን እንኖራለን !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የተፈጠርነው በምክንያት ነው !

እዚህች ምድር ላይ የመጣነው ልንሞላ ነው እንጂ ልናሟላ አይደለም ! እያንዳንዳችን የተፈጠርንበት አላማ አለ የትኛውም እድሜ ክልል ላይ እንሁን ምንም አይነት የእውቀት ደረጃ ላይ እንድረስ አንድ ማሳካት የምንችለው ነገር አለን !

"ስለዚህ ራሳችንን አላማ ያለው ምድርን በመልካም ነገር ለመሙላት የተፈጠረን ሰዋች መሆናችንን እናስታውሰው "

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለማወቅ ክፍት እንሁን !

ሁሌም ለመንቃት ዝግጁ ሁን ፤ ሰው ሆኖ ፍፁም የሆነ የለም ትላንት ልክ ነኝ አውቄዋለው ብለን ያሰብነው ነገር ሁሉ ዛሬ ተጨማሪ ነገር ስናውቅበት ለካ ገና ነበርኩ ያስብለናል !

" እውቀት ጥግ የለውም ሁሌም ለመማር ራስህን ክፍት ስታደርገው ሁሌም የማደግ እድልን ለራስህ እየሸለምከው ነው!"

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አስተውል !

የምታደርጋቸውን እያንዳንዶቹን ነገሮች ስታከናውን በማስተዋል ይሁን ለምንድን እንደምታደርጋቸው እወቅ ፣ ከአፍህም ለሚወጡት ቃላት ተጠንቀቅላቸው !

ምክንያቱም አንዴ ከአንተ ያመለጠን ነገር መልሰህ ልትጠግነው አትችልም ይሄን በማድረጌ ማን ምን ይጎዳል ብለህ ስታስተውል ግን ላንተም ከፀፀት የፀዳህ ለሌሎችም እረፍት የምትሰጥ ሰው ትሆናለህ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለዛሬ ያበቁህን አትርሳ !

ትላንትን ለማለፍህ መሰላል የሆኑልህን ሰዎችም ዛሬ ማማው ላይ ወጥቻለው ካለሁበት የምፈልገው ርቀት ደርሻለው ብለህ እንዳትገፋቸው !

ነገ ማማው ላይ ያለው ምግብ ያልቅ ይሆናል የያዝከውን ስንቅ ትጨርሰው ይሆናል መልሰህ ለማምጣት ያ መሰላል ያስፈልግኋል ስለዚህ ተረማምጄ ያለፍኩበት ሁሉ ይውደቅ ስትል መጨረሻህ አያምርም ውለታ አትርሳ!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የስኬት ሚስጥር !

በህይወትህ ላይ ምንም የተሻለ ነገር ሊፈጥርልህ በማይችል ነገር ላይ ራስህን አታባክን !

ጊዜህን እያሳለፍክ ያለኸው በምንድን ነው? ለነገ ህይወቴ የተሻለ መንገድ ይከፍትልኛል ህልሜን አሳካበታለው በምትለው ነገር ነው? ወይንስ ሁሉም ሰው እንደሚያደርገው በሶሻል ሚዲያው ፣ በማይጠቅም ሀሜት ፣ በፀብ እና በፌዝ ነው?

ስኬታማን ሰው ስኬታማ ያደረገው ሌላ ምንም አይደለም ለጊዜው የሚሰጠው ዋጋ ነው ! ሰኬትህን ለማየት ከፈለግህ ዛሬ ጀምረህ ለጊዜህ ዋጋ ስጥ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የተሻለ ሊሰጥህ ነው !

ፍቅረኛህን ማጣትህ በጣም ሊያሳዝንህ ይችላል ፤ ከስራህ በመባረርህ በጣም ያናድኋል የጠበቅኸው ነገር መፈፀም ባለመቻሉ የእኔ ነገር ዋጋ የለውም አስብሎህም ይሆናል!

እኔ ግን አንድ ነገር ብቻ ልበልህ ሁሉም ነገር የሚሆነው ለትልቅ ምክንያት ነው እነዚህ ማጣቶች ትልቅ እድሎች ናቸው በእነርሱ ምክንያት ራስህን ታገኛለህ ወደተሻለው አንተ የመሄጃ ድልድዮች ናቸው !

ሁሌም በማጣት ውስጥ ስትሆን ራስህን ፈትሽ ያኔ የተሻለውን ታገኛለህ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እድልህን ተጠቀምበት !

መሞከር ያለብህን የምትፈልገውን ሁሉ ሞክር መሳሳትም ካለብህ ተሳሳት ማደግ የምትችለው ለመሞከር ፈቃደኛ ስትሆን ነው እንዳንድ ህመሞች ሲገጥሙህ ደግሞ ይበልጥ ያጠነክሩኋል ! ጠንካራ ለመሆን ከፈለግህ መሞከርን እና መውደቅን መለማመድ አለብህ!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉም መልካም ይሆናል !

"ክርስቶስ ለሰቀሉት ሰዎች የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው"ብሏል በምድር ላይ ክፉ የሆነ ሰው የለም የሚያደርገውን የማያውቅ እንጂ!

ስለዚህ ወንድሜ የተፈጠረው ነገር ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ትልቁ መሳሪያ ግን በእጅህ ነው በፀሎትህና በመልካም ሀሳብህ ተዋጋው የሚያደርጉትን ለማያውቁትም በንፁህ ልቦና ሆነህ እዘንላቸው "አቤቱ ጌታ ሆይ ማራቸው" በል እና ለምንላቸው!!!


መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel