"ምርጡ ጓደኛዬ በእኔ ውስጥ ያለውን ምርጥ ማንነት እንዳወጣ የሚረዳኝ ነው" የሄንሪ ፎርድ አባባል ነው። ከምርጥ ጓደኞቻችን መካከል አንዱን መፅሐፍ ብናደርገው ብዙ እናተርፍበታለን።
ውብ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
ሁሌም ማመስገን ልማዳችን መሆን አለበት
ዝነኝነት ማለት በሰዎች መወደድና መደነቅ ነው፤ ደስተኝነት ማለት ግን ራስን መውደድና ማድነቅ ነው። ሁሌም በተሰጠን ነገር ፈጣሪን እያመሰገነንን ራሳችንን የምንወድ ከሆነ ብዙ ነገር ይጨመርልናል።
ሁልጊዜም ስናመሰገን የሆነ ነገር እንዳለን እናምናለን፤ እንዳለን ስናምን ብዙ ይጨምርልናል ምክንያቱም መፅሀፍ ቅዱስ ላለው ይጨመርለታል ከሌለው ላይ ደግሞ ያለውም ይወሰድበታል ይላል።
ብሩህ ቀኝ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ትኩረት !
ትኩረትህ አንድ ነገር ላይ ብቻ ሲሆን ያንን ነገር ሊያሳድጉት የሚችሉ ብዙ
ሀሳቦችን ማፍለቅ ትችላለህ ጥሩ ቦታ ላይ ስታተኩር ታድጋለህ መጥፎው ላይ ስታተኩርም ራስህን ይበልጥ ትጥለዋለህ !
ስለዚህ ለውጥ ስትፈልግ ትኩረት የምታደርግበትን ቦታ አስተካክል !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ራስህን ተቀበለው !
ራሱን የማይወድ ሰው ሁሌም በማያምንበት ሀሳብ ውስጥ ይኖራል ፤ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲል የሚያምንበትን ሁሉ ይተዋል የማይፈልገውን ህይወት ይኖራል በስተመጨረሻ ግን ከሁለት ያጣ ይሆናል !
"ከሁሉም ነገር በላይ ፈጣሪህ እንደተቀበለህ እና አንተም ራስህን እንደተቀበልከው እርግጠኛ ሁን ከዚያም በደስታ ተራመድ ያኔ ከልቡ የሚቀበልህ ወዳጅ ታገኛለህ "
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
እመን !
አንተ ብቻ እመን ከልብህም የምትፈልገውን ነገር ጠይቅ እናም ስራበት ፈጣሪ በምን መንገድ እንደሚያሳካልህ አታውቅም እርሱ ካንተ የሚፈልገው እምነትህን ብቻ ነው !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
መስጠት !
የእውነተኛ ደስታን ማግኘት ከፈለግህ ከልብህ መስጠትን ልመድ የእውነት ለሌሎች ለመትረፍ ኑር የአንተን እገዛ ለማግኘት ለሚሹ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ዋጋ ክፈልላቸው ! ለራስህ ሳይሆን ለሌሎች ኑር ! ያኔ የህይወትን ትልቅ እና ትክክለኛ ዋጋ ታገኛለህ !
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ውሳኔ !
ህይወትህን በፈለግኸው መንገድ ለማስተካከል ከፈለግህ እያንዳንዳቸው ውሳኔዎችህ ላይ ብልህ ሁን ትንሽ ብለህ የምታስባት ነገር በህይወትህ ላይ በጣም ትልቅ የሆነ ተፅዕኖ እንደምትፈጥር አትዘንጋ !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ይሳካል !
ከልብህ የምትሻውን ነገር ታገኘዋለህ ልታሳካው ያሰብከውን እያንዳንዱን ነገር አጥብቀህ እስከፈለግኸው ድረስ ታገኘዋለህ!
ግዜው መች እንደሆነ እና በምን መንገድ እንደሚሳካ አታውቅም አንተ ግን ለእርሱ የሚያስፈልግህን ሁሉ ለመሆን ራስህን አዘጋጅ የሚያስፈልገውን ዋጋ ከመክፈል ወደኋላ አትበል ፈጣሪ በሰዓቱ እና በጊዜው ያደርግልኋል !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
እረፍት !
ዛሬ ለሰራተኛውም ለተማሪውም እረፍት የሚያገኝበት ቆንጆ ቀን ነው !
እረፍታችን ከሳምንቱ ሩጫችን እና ከነበረን ሀሳብ ነፃ ሆነን ምን ሰራን ምን አደረግን ብለን ራሳችንን ለመፈተሽ እና ለቀጣይ ሳምንታችን ራሳችንን በሚገባ ለማዘጋጀት የተሰጠን ትልቅ እድል ነው ! እንጠቀምበት !
የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ብንሞክረውስ !
ብዙ ሰዎች ቅድሚያ ራሳችሁ ላይ ስሩ ሲባሉ ይቃወማሉ ፤ በጣሞ በብዙ ግን ስራቸው ላይ ይለፋሉ ከሚገባው በላይ ይደክማሉ ነገር ግን ስኬታማ አይሆኑም !
በስተመጨረሻ ዋጋ የከፈሉለትን ነገር ሁሉ ትተው ተስፋ ቆርጠው ወደማይሆን ህይወት ይገባሉ ወይም እዛው ሲደክሙ ይኖራሉ ነገር ግን :-
በጣም በሚገርም ሁኔታ ራሳቸው ላይ ሲሰሩ እና በደንብ አቅማቸውን ሲያውቁ በትንሽ ጊዜ ተዓምራዊ የሚመስል ለውጥ ያመጣሉ ስለዚህ ያለህበት ቦታ አልሳካ ካለህና ሌሎች መፍትሄ እየነገሩህ ከሆነ ከመቃወም ብትሞክረውስ ሌላ መንገድ ማየት ብትጀምርስ ?
አመለካከትህን ለመቀየር ጊዜ ስጥ !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ራስን ማወቅ !
'ሚካኤል አንጄሎ' የዳዊትን ቅርፅ ከድንጋይ ፈልፍሎ ሲሰራ ሰው ሁሉ ተገርሞ እንደምን አድርገህ ሰራኸው ሲሉት "ቅርፁን እኔ አልሰራሁትም መጀመሪያም ውስጡ ነበር እኔ ያደረግኹት የማያስፈልጉትን ነገሮች ከላዩ ማንሳት ነው!"
ስኬታችንን እኛ አንፈጥረውም ውስጣችን ነው ያለው ከእኛ የሚጠበቀው ራሳችንን ማወቅ እና አላስፈላጊ አመለካከቶቻችንን ነቅሎ ማውጣት ነው።
በዚህ ቪድዮ 👇 ራሳችንን እንዴት ማውጣት እንደምንችል በሚገባ እንማርበታለን !
https://youtu.be/dfFQafqeYCU
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለውጥ ከውስጥ ነው !
"ተዓምርን ከውጪ የሚጠብቁ ሰዎች ተዓምረኛ አእምሮ እንዳላቸው የማያውቁ ናቸው " ይለናል ሁልጊዜም ለውጥ የሚመጣው ከውጪ በሚመጣ ኋይል አይደለም !
እኛ ስንቀየር ሀሳባችን ሲያድግ ማድረግ ያለብንን ነገር እንድናውቅ እና አቅማችንን ከልባችን እንድንጠቀም ያደርገናል ያኔ ስኬታችን ከእኛ እኩል እያደገ ይመጣል !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ራስህን አሳድግ !
ራስህን ከማሳደግ ወደኋላ አትበል ብልጥ ሁን እያንዳንዱን ግዜህን ራስህን ለሚያሳድግልህ ነገር ስጥ !
በፌዝ እና በማይጠቅም ነገር የምታሳልፉቸው እያንዳንዱ ጊዜያት ነገ ላይ ፀፀት ውስጥ ይከቱኋል ነገ የህይወት አጣብቅኝ ግዜያት ላይ ከምትነቃ ቀድመህ በጥሩ ግዜያትህ ላይ ንቃና ራስህን ሰርተህ ጠብቅ !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
✅ 2 ቀን ቀረው !
ምን አጋጥሞሃል ?
ለፍቶ ውጤት ማጣት ፣ ኪሳራ ፣ መከዳት ፣ ተቀባይነት አለማግኘት ፣ ተስፋ መቁረጥ ወይስ ብቸኝነት ?
ምንስ ትፈልጋለህ ?
በራስ መተማመን ፣ ቆራጥነት ፣ የሚያበረታህ ቤተሰብ ፣ የይቅርታ ልብ ፣ ገቢህን በእጥፍ ማሳደግ ፣ ትዳርህን ማስተካከል ወይስ ልጆችህን መቀየር ?
ለአንቺም ይሰራል የኔ እህት !
19ነኛው ዙር የኦንላይን ስልጠናችን የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት ይጀምራል ( 📍ባሉበት ቦታ በምቾት )
ነገ ማክሰኞ ከምሽቱ 12:00 በሮች ሁሉ ይዘጋሉ ከወዲሁ ተመዝግባችሁ ቦታ መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ !
ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።
☎️ +251944314544
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
በመልካምነት አሸንፍ !
በተቻለህ አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም ሁን ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ አታውቅም እና አትክፋባቸው!
ክፋ ለመሆን የተፈጠረ ሰው የለም ሁኔታዎች ግን ሰዎችን ይቀያይሯቸዋል ! የእኛ ጥሩ መሆን ግን በእነዚያ ሰዎች ህይወት ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም !
ስለዚህ በተገኘህበት ቦታ ሁሉ የጥሩነት ምሳሌ ሁን ፤ ሁኔታዎች አይገድቡህ የበላያቸው ሆነህ አስደንግጣቸው !
የ19ነኛው ዙር ስልጠናችን ሊጀመር 4 ቀን ብቻ ቀርቶታል !
ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
አልተፈፀመም!
ብዙ ፊልሞች አይታችሁ ከሆነ አጨራረሳቸው ያማረ ነው። የምንፈልገውን ነገር ለማሳካት ስንሮጥ እንደዛ ማሰብ መጀመር አለብን፤ በቃ አጨራረሱ ካላማረ ያ ነገር አልተፈፀመም ማለት ነው! ስለዚህ እጃችን እስኪገባ እንታገላለን እንጂ ማቆም የሚባል ነገር የለም!💪
የተለየ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
የተሰጠንን ዋጋ እንወቅ !
በፈጣሪያችን ትልቅ ዋጋ የተከፈለልን ክብር የተሰጠን በምድር ላይ ካሉ ፍጥረታት በሙሉ ታላቅ እና ገዢ ተደርገን የተሰራን የፈጣሪ ድንቅ ስራዎች ነን!
ታድያ ታላቅ ሆነን ተፈጥረን ለምን እንደታናሽ እንኖራለን ክብር ተሰጥቶን ለምን ራሳችንን ለማዋረድ እንኖራለን ? የሚያስብ አዕምሮ ተሰጥቶን ለምን ሳንጠቀምበት እንሞታለን ?
ለምንም ሳይሆን በፈጣሪያችን ብቻ ካመንን እርሱን ላለማሳዘን እንኳን ስንል የሰጠንን እናክብር !
የአካል ስልጠናችን ሊጀመር 5 ቀናት ብቻ ቀሩት!
የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሁኔታዎች አይገድቡህ !
የሰው ልጅ በሁኔታዎች አይገደብም በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ ስኬታማ የሆነ ብዙ የጀግንነት ተግባሮችን የፈፀመ አለ ! በጥሩ ሁኔታዎች አልፎ ደግሞ የሰነፈም አለ ስለዚህ ላለህበት ቦታ ያሳለፍካቸውን ችግሮች ሰበብ አታድርጋቸው እንደውም የበለጠ በርታባቸው !
ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
✅ የምስራች ለተመረጡት !
እንግዳችን ይሁኑ !
ብዙ ቤተሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማፍራት የቻለው 'ኢንስፓየር ኢትዮጵያ' በእናንተው በቤተሰቦቹ ጥያቄ መሠረት በአዲስ መልክ መጥቷል !
አዲስ ሀይል ፣ አዲስ ማንነት እና አዲስ ህይወትን አብረን እንድንሰራ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ልዮ ዝግጅት በቤቱ አዘጋጅቷል።
📍 ቀድመው ለሚወስኑ 10 ሰዎች ብቻ !
ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር ይደውሉ ፤ በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።
☎️ +251944314544
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ዋጋ አለን !
እዚህች ምድር ላይ ከንቱ የተባለ ፍጥረት የለም ሁሉም ወደዚህች ምድር የመጣው ለመልካም ነው እያንዳንዳችን ትልቅ ዋጋ አለን ! ፈጣሪ የሰጠንን ትልቅ ዋጋ ማንም እንዲነጥቀን አንፍቀድለት !
ሰናይ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ይቅርታ !
ይቅርታ ማድረግ ለራስ ትልቁን ስጦታ መስጠት ነው ይቅር አለማለት ውስጥ እኔ ጋር ይሁን መጥፎውን ሁኔታ ልሸከመው አይቅለለኝ የሚል ማንነት አለ ሁሉ ይቅር ከእኔ ይውጣ ስንል ግን ውስጣችንን ሰላም እንሸልመዋለን ማንም ሊሰጠን የማይችለውን ደስታ ለራሳችን እንሰጠዋለን !
መልካም ውሎ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
✅ 1 ተጨማሪ እድል ለሚወስኑት ብቻ !
► ህይወት ባላሰብከው መንገድ እየሄደ ነው ? ቀጣይስ ምን መወሰን እንዳለብህ አላወቅህም ?
► ስራህ ፣ ትዳርህ ነገህ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው ?
'አብርሀም ሊንከን' እንዲ ይላል "ዛፍ ለመቁረጥ 6 ደቂቃ ቢሰጠኝ 4ቱን ደቂቃ መጥረቢያዬን ለመሳል ነው የምጠቀምበት።"
📍ከአንተ / ከአንቺ የሚጠበቀው አንድ ውሳኔ ብቻ ነው !
የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት የሚጀምረውን የኦንላይን ስልጠና ባለህበት ሆነህ መመዝገብ !
ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።
☎️ +251944314544
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ምስጋና !
ቀናችንን በመልካም ስላስፈፀመልን አምላካችንን እናመስግን ቀን እና ሌሊቱን ሳይሰስት እያፈራረቀ ለሰጠን እና ሁሌም ሳያዛንፍ እየጠበቀ ላኖረን ፈጣሪያችን ምስጋና ልንሰጠው የምንችለው በጣም ትንሹ ነገር ነው !
ስራ በዝቶብኛል ጊዜ የለኝም ብዙ ማድረግ ያለብኝ አለ ብንል መጨረሻ ውጤት ሰጭው እርሱ ነው እና ከምንም ነገር የማይበልጥብንን ፈጣሪያችንን ቅድሚያ መስጠትን እንለመድ ምስጋና ለእራስ ነው !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ዋጋ ክፈል !
የምትፈልገውን ህይወት ለመኖር መደመርያ የሚያስፈልገውን ዋጋ መስጠት መቻል አለብህ ፤ ዋጋ ያልተከፈለበትን እቃ መውሰድ እንደማትችል ሁሉ ዋጋ ያልከፈልክበትም ስኬት ያንተ ሊሆን አይችልም !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ጥልቅ መሻት !
የሰው ልጅ ከፈለገ ፈለገ ነው ፤ አንድን ነገር ከልባችን አጥብቀን ከፈለግነው የትኛውንም አይነት ዋጋ ከፍለን እናገኘዋለን !
ነገር ግን ከልባችን ለማንፈልጋቸው ነገሮች ሲሆን ሰበብ እናበዛለን ፤ አንድን ነገር ለማሳካት ፈልገሀል? ነገር ግን የሆነ ሰበብ አለህ ስለዚህ ራስህን ጠይቅ ሰነፍ አይደለህም የምር ለዚህ ነገር ጥልቅ የሆነ መሻት አለህ !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ራስን ማሸነፍ !
የማታምንባቸውን ነገሮች ለማድረግ እምቢ ማለት ዋጋ ያስከፍላል ግን በህይወትህ ታሪክ ትሰራለህ ፤ ሁኔታዎች ገፍተው የሚመጡት ሊያበረቱህ ነው እንጂ አቅም ሊያሳጡህ አይደለም !
የኔ እና ያንተ አድዋ ጣሊያንን ማሸነፍ አይደለም፤ ስንፍናችንን ማንበርከክ እና ራሳችንን ለውጠን በመንፈሳዊም በአለማዊም ስኬታማ መሆን ነው! ድል ለሁላችን💪
ታሪካዊ ሀሙስ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ሰላም🙌 ውድ የInspire Ethiopia ቤተሰብ 19ተኛ ዙር ስልጠና ዛሬ ማታ ይጀምራም::
የተመዘገባችው ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ 😊
👉ላልተመዘገባችሁ ጥቂት ቦታዎች ብቻ ስለሚቀሩ ፈጥነው ይመዝገቡ
👉ስልጠናው የሚሰጠው በኦንላይን ( ZOOM App )ባሉበት ቦታ ነው::
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
በፈጣሪህ ብቻ ተመካ !
እዚህች ምድር ላይ ብዙ የምትወዳቸው ሰዎች ይኖራሉ ነገር ግን አንዳቸውም የፈጣሪን ስራ አይሰሩም እርሱ የሚያደርግልህን ሊያደርጉ አይቻላቸውም !
"በፈጣሪ የማይሆን አንዳች ነገር የለም ሁሌም በእርሱ ተስፋ አድርግ "
የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ድል እየመጣ ነው !
ያለህበት ሁኔታ ግራ እያጋባህ ነው? እየለፋህ እየጣርህ ነገር ግን ውጤቱ ቅርብ ሚታይ አልሆን ብሎሀል ማለፍ የምትችለው ነገር እንዳልሆነ እየተሰማህ ነው? አካባቢህ ያሉ ሰዎች ባንተ ተስፋ እየቆረጡ ነው?
በጣም ጥሩ ሰዓት ላይ ነህ ይበልጥ ማሸነፍ እና ማብራት የምትፈልግ ከሆነ ይሄ ያንተ ጊዜ ነው ጠንክር ቆሟል ስትባል በዝግታ ተራመድ ባትጠበቅም ለማብራት መሮጥህን አታቁም ከባድ ጊዜያት ራስህን መገንቢያ ናቸው በደንብ ተጠቀምባቸው !
መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊