inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ምን ይታይሻል?

አሁን ካለሽበት ቦታ ሆነሽ ምንድነው የሚታይሽ ? ምን ማድረግስ ትፈልጊያለሽ ? ሁሌ አደርገዋለሁ ብለሽ ቃል እየገባሽ የተውሽው ነገር ምንድነው ?

የመረጥሽውን ሁሌ ለማድረግ የምትመኚውን ከማድረግ ጀምሪ የግድ መጨረሻውን አውቀን መጀመር አይጠበቅብንም እሱ የኛ ስራ ሳይሆን የፈጣሪ ስራ ነው !

ከምን ለመጀመር አሰብሽ ?


መልካም ጊዜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

https://us06web.zoom.us/j/81129335440?pwd=Z0VJN091bmN0V1UzaVEwVXdjQUxNZz09

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መልካም ዜና ለተመረጡት !

ሰላም እንዴት ቆያችሁን ቤተሰቦች 🙌 ዛሬ ማታ 3:00 ላይ ነፃ የኦንላይን ( Zoom ) ስልጠና ይኖረናል ።

ለራስ ስለሚደረግ ይቅርታ በሰፊው እንወያያለን !

ስንቶቻችን ትናንት ባጠፋነው ጥፋት ዛሬ ላይ ራሳችንን እየወቀስን ነው ? አሁን ማድረግ የምንችለውን እንዳናደርግ የተለያዩ ምክንያቶች ልናስቀምጥ እንችላለን አንዱ ምክንያት ራስን አብዝቶ መውቀስ ነው።

በሰዎች ላይ ያለንንም ቅያሜ ይቅር ለማለት ከመነሻው ከራሳችን ጋር መታረቅ ወሳኝ ነው።

➡️ ቀድመው የሚገኙ 100 ሰዎችን ብቻ ስለሆነ የምንቀበለው በሰዓታችሁ ቀድማችሁ ተገኙ !

❗️ማሳሰቢያ : 100 ሰዎች ከገቡ በኃላ ሊንኩ አይከፍትም !

ዛሬ ማታ ልክ 3:00 ላይ ሊንኩ በዚሁ ቻናል ይለቀቃል

ከላይ ያለውን የ (zoom) ቪዲዮ ተመልክታችሁ ለስልጠናው ራሳችሁን አዘጋጁ

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከትንሽ ጀምር !

አንድን ነገር ስትጀምር በጣም በሚገርም ሞራል ውስጥ ሆነህ ትጀምር እና ልክ ከተወሰነ ቀናት በኋላ በቃኝ ይቅርብኝ በለህ እያቆምክ ተቸግረሀል ? ብዙ ሰው ይሄ ነገር ያጋጥመዋል !

ግን ለምን እንደሆነ አያውቀውም አንድ ሚስጥር ልንገራችው ከትንሽ ጀምሩ ሞራላቸው ስለመጣ አቅም ስላላቸው ብቻ ብዙ ነገር ባንዴ አትሞክሩ ቀስ እየተባለ የተሰራ ነገር ውጤቱን ቅስ እያለ እየጨመረ ይሄዳል !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተጋፈጥ !

ፈተና በህይወታችን የሚመጣው እንድም ሊያጠነክረን አንድም በህይወታችን ምን እንደተማርን ሊፈትሸን ነው ! ወደኋላ ካልንለት ይጥለናል ከተጋፈጥነው እና ወደኋላ ሳንል ካሸነፍነው ግን ይሸልመናል!

መልካም ጊዜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወደኋላ እንዳትል !

መሞትን መፍራትህ ሳያንስ መኖርማ እንዳፈራ! በየቀኑ የምታምንበትን ለማሳካት ከመሞከር እንዳታቆም! በየቀኑ አዲስ ነገር ከማወቅ የሚያግድህ ምንም ነገር የለም!

በተመሳሳይ መንገድ እየሞከርክ የተለየ ውጤት አትጠብቅ! ....እያንዳንዱን ቀን የላብራቶሪ ምርምር እንደሚያደርግ ሰው ግድየለሽነትን አሽንቀንጥረህ ጥለህ ህይወትህ ላይ መሞከር ያለብህን ሳታመነታ ሞክር!

ለወፎች የሰማይ አምላክ ምግባቸውን ያዘጋጅላቸዋል ቢባልም አድኖ መብላት ግን የነሱ ፋንታ ነው...እኛም የተዘጋጀልንን ለማግኘት ተነስተን ማደን አለብን!

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለስኬት..

ቤትህ እንዲስተካከል ትፈልጋለህ ሁሌም ፅዱ እና ቅንጆ ሆኖ ማየት ያስደስትኋል እቃ የት እንዳደረግህ እየጠፋብህ መፈለግ ደክሞኋል?

ስለዚህ ለእያንዳንዱ ነገር ቦታ ይኑርህ ሁሉንም ነገር መቀመጫ የራሱ የሆነ ቦታ ስጠው ተጠቅመህም ስታበቃ በቦታው መልሰው ያኔ ከብዙ ድካም ትድናለህ የፈለግከውንም ታሳካለህ ታድያ ስኬትም እንደዛው ነው ቦታ ቦታውን ሲይዝ ...🤭

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ይሳካል !

ህልምህ መቼ በማን አማካኝነት በምን መንገድ እንደሚሳካ አታውቅም ነገር ግን የሆነ ያላሰብከው ቀን ሁሉ ነገር መልካም ሲሆን ታየዋለህ አይሆንም በቃ ብለህ ተስፋ የቆረጥክበት ነገር ሁሉ ይሳካል አንተ ብቻ ታግሰህ ጠብቅ !

መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

" ነገር ሁሉ ለበጎ ነው "

ምን ላይ እንዳለህ አላውቅም ምን እያሳለፍክ እንደሆነም አላውቅም ነገር ግን አንድ ነገር አውቃለው እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው ነገሮች ሊያበረቱህ እንጂ ፈፅመው ሊጥሉህ አይመጡም !

ምክንያቱም "ሁሉ የሚከወነው ካንተ በላይ ስላንተ በሚያስብልህ አምላክህ ነው !"

➡️ 20ኛው ዙር የኦንላይን ስልጠናችን ሊጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል ቀድመው በመመዝገብ ቦታ ያስይዙ !

ከታች ባለው ቁጥር አሁኑኑ ይደውሉ ፤ በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

☎️ +251944314544

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

https://us06web.zoom.us/j/88625851279?pwd=b0xraFl2MTVhUWVveGYxRzZZeTBxZz09

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በምን ታድጋለህ ?

አሁን ያለህ ማንነት በዉርስ ያገኘኸው አይደለም ፤ በትምህርት ብቻም የዳበረ አይደለም እንዲህ ሆነህም አልተፈጠርክም ታድያ በምን ገነባኸው ? በልማድህ!

በየቀኑ በምታደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ራስህን እየገነባኸው ነው አንተን አንተ የሚያረግህ ያለህበትን ቦታ የምትሄድበትን መንገድ የሚወስንልህ ፦

ዛሬ የምትውለው ውሎ እና ማድረግ የለመድካቸው ነገሮች ናቸው ስለዚህ አሁን ወደ ቀንህ ስታመራ ትንሽ ጊዜ ለራስህ ስጥና የምታደርገውን ወስን !

መልካም ውሎ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እድልህን ተጠቀም !

መውጣት መውረድ ያለ ነው ሁሉ መንገድ ቀጥ ያለ አይደለም ነገር ግን አኛ ካወቅንበት ልናደላድለው እንችላለን እያንዳንዱን ወቅታችንን ለበጎ መጠቀም !

ስራ ሲቀዘቅዝ ከራስህ ጋር ከተጠፋፋሀቸው ወዳጆችህ ጋር የምትገናኝበት ምርጥ ጊዜ አንደሆነ አስብ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አስታውስ !

አሁን እጃችን ላይ ያለውን ሁኔታ እናይና ምንም ነገር ማሳካት እንደማንችል ሊሰማን ይችላል !

በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ መስለው ሊታዩንም ይችላሉ ግን አንድ ነገር መርሳት የለብንም ለምንወደው ነገር ጥግ ድረስ ለፍተን ማንነታችንን ስናሳይ ፈላጊያችን ብዙ ነው፤ አጨብጭቦ የሚቀበለን ብዙ ነው።

አሸናፊዎች አያቆሙም! የሚያቆሙም አያሸንፉም!

ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ቃላችን !

ለራሳችን የምንነግረው ነገር ህይወታችንን ሊያስተካክለውም ሊያበላሸውም ይችላል። ለምሳሌ ለራሳችን በጠዋት መነሳት እንደማንችል ደጋግመን ከነገርነው በቃ አንችልም።

ግን 12 ሰዓት ተነስተቼ ስፖርት መስራት እችላለው፤ ወደ ፈጣሪዬ እፀልያለው፤ አሪፍ መፅሀፍ አነባለው አደርገዋለው እችላለው ካልን እንችለዋለን እናደርገዋለን! 

በህይወት ውስጥ ከባድ ነገር ቢገጥመን እንኳን በተቻለን አቅም ለራሳችን እንደማንችል መንገር የለብንም ምክንያቱም ለራሳችን የነገርነውን ነው የምንሆነው።

የተባረከ ሰንበት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የትልቅ ስኬት መነሻ ጥልቅ ፍላጎት ነው!

ይሄን ሁሌም በአይምሯችን ማሰብ አለብን፤  ብዙም ያልተቀጣጠለ እሳት ብዙ ሙቀት እንደማይሰጠን ሁሉ ደካማ ፍላጎትም ደካማ ውጤት ነው የሚሰጠን። ሁሌም የማይማበርድ ፍላጎት የማይቋረጥ ፅኑ መሻት ያስፈልገናል።


ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከአሁን ጀምሮ መግባት ትችላላችሁ !

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የ zoom አጠቃቀም ሙሉ ማብራሪያ !

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ግንኙነትህን ለማሳመር !

ከሰዎች ጋር ያለህን ቅርበት ይበልጥ ለማሳመር ከፈለግህ አዳማጭ ሁን ምን እንደሚፈልጉ ምን እንደሚያስፈልጋቸው ቀድመህ ተረዳቸው !

የሚያሳዩት እያንዳንዱ ፀባይ ምክንያት አለው እና ቀድመህ ምክንያታቸውን ተረዳ ያኔ መቀያየም ጠፍቶ የበለጠ ቅርበት ይዳብራል!

መልካም ሀሙስ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ቤተሰቦች 🙌 እንዴት አመሻችሁ !

የፍቅር ህይወታችሁን ለማስተካከል ፈልጋችሁ ከምን ልጀምር ብላችሁ ግራ ለተጋባችሁ ሁሉ በዚህ ቪዲዮ መልስ ታገኛላችሁ !

ከታች ያለውን 👇 ሊንክ በመጫን ቪዲዮን ማየት ትችላላችሁ

https://youtu.be/GPS1pY6pLx4

የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዝም ብለህ ስራ !

ሁሉንም ነገርህን ከመናገር ተቆጠብ አንዳንዴ ከምትናገረው በላይ ሰርተህ አሳይ ብዙ ቃል ገብተህ ያልፈፀምካቸው ነገሮች ይኖራሉ !

ስለዚህ ቃልህ ምግባርህ ይሁን !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከመሞከር አትመለስ !

ለምንድነው የማትሞክረው? መሳሳትን መውደቅን ፈርተህ? ከዚያስ ምን እንዳይመጣ አየህ የሆነን ነገር መስራት ስትጀምር አንተ ያንን ሰው ሆነህ እድሜ ልክህን ልትኖር ሳይሆን ከዚያ ነገር የሆነ ያክል ልትማር የምትችልበትንም አጋጣሚ ለራስህ እየፈጠርክ መሆኑን አስብ!

ስለዚህ ብትሳሳትም ነገህን የተሻለ ለማድረግ እንጂ ልትወድቅ አይደለም !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እመን !

ለአምላክህ የጠየቅኸው የለመንኸው ሁሉ እንደሚሆን እመን ጠይቀሀል አደል በቃ አትጠራጠር ለእርሱ ከነገሩ በኋላ መጨነቅ መረበሽ የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም የጠየቅነውን ሁሉ ይፈፅምልናል ከእኛ የሚጠበቀው ዝም በሎ ማመን ብቻ ነው!

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በዚህ ቪድዮ ምንም አይነት ገንዘብ ፣ ዝና እና እውቀት ሳያስፈልገን እንዴት ወደምንፈልገው ማንነት እንሄዳለን የሚል መፍትሄ ይዘን መጥተናል !

ከዚህ በኋላ ከዜሮ እንዴት ልነሳ የሚል ሁሉ መልስ ያገኛል !.

ከታች ባለው ሊንክ ያገኙታል👇

https://youtu.be/_N8BWfpOi1I

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

https://us06web.zoom.us/j/86979167791?pwd=SU5zdnczWnIvWkVsOVBBSitQcGVXUT09

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መልካም ዜና ለተመረጡት !

ሰላም እንዴት ቆያችሁን ቤተሰቦች 🙌 ዛሬ ማታ 3:00 ላይ ነፃ የኦንላይን ( Zoom ) ስልጠና ይኖረናል ።

በዛሬው ቆይታችን በየቀኑ ደስተኛ የመሆኛ ሚስጥሮችን እናያለን። በየቀኑ ያለህበትን ስሜት ስትቆጣጠር ግንኙነትህ ፣ ጤናህ ፣ ስራህ ብሎም ከኪስህ አልፎ ባንክ አካውንትህ ውስጥ የሚገባውን ገንዘብ ተቆጣጠርክ ማለት ነው።

➡️ ቀድመው የሚገኙ 100 ሰዎችን ብቻ ስለሆነ የምንቀበለው በሰዓታችሁ ቀድማችሁ ተገኙ !

❗️ማሳሰቢያ : 100 ሰዎች ከገቡ በኃላ ሊንኩ አይከፍትም !

ዛሬ ማታ ልክ 3:00 ላይ ሊንኩ በዚሁ ቻናል ይለቀቃል

ከታች👇 ያለውን ቪዲዮ ተመልክታችሁ ለስልጠናው ራሳችሁን አዘጋጁ

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እውነተኛ ደስታ !

ትክክለኛ ሰላምን ለማግኘት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ወደ ፈጣሪህ ቅረብ አጥብቀህ ፈልገው ትዕዛዛቶቹንም ጠብቅ ፣ በመንገዱ ሂድ ያኔ ገንዘብ የማይገዛው ዝና የማይሰጠው ጥልቅ ደስታ እና ሰላም በቤትህ ወለል ብሎ ይገባል !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትፍራ !

በእያንዳንዱ የምንጓዝበት መንገድ ፈጣሪ አለ ስንቆም ስንተኛ ስንነሳ ሁሉንም እንቅስቃሴያችንን የሚቆጣጠርልን እርሱ ነው ታድያ ለምንድነው የምንፈራው? ለምንድነው ብቻዬን ነኝ የምንለው ለምንድነው ደጋፊ ያጣን እንደሆንን የምናስበው ?

በምታደርገው ነገር በሙሉ ማንም ሰው ባይደግፍህ ነገርግን ፈጣሪ ከጎንህ እንደሆነ ካመንክ ከሁሉ በላይ የሆነው ካንተ ጋር ነውና በፍፁም አትፍራ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተዎ ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተነሳ !

አንድ ብለህ ካልጀመርክ ሁለት ተብሎ መቀጠል አይቻልም ህይወት እርምጃህን ትቆጥራለች የት እንደደረስክ የምትነግረህ ያለህበትን ቦታ አይታ ነው!

"መድረስ የምትፈልገው ቦታ ሁሉ ተነስተህ ሂድ እንጂ እርሱ ራሱ ተነስቶ ወደ አንተ አይመጣም "
ስለዚህ በተሰጠህ እድል ሁሉ ተጠቀም ወደኋላ አትበል ሞክር ያኔ ታሸንፋለህ!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስህተትህን ....

ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል።

ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን።

ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አድርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

ብሩህ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሙከራህን ......!

ህይወት በራሱ ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል ግን በዚህ ምድር ላይ ከሁሉም ነገር ዋጋ የሚያስከፍለን የምናስበውን ለማሳካት ምንም አለማድረግ ነው።

ጥላሁን ገሰሰ የሰው ልብ ውስጥ ገብቶ የሙዚቃ ንጉስ እስኪባል ድረስ 300 በላይ ሙዚቃዎችን ሰርቷል፤ ቶማስ ኤዲሰን አንድ አምፖል እስኪበራለት ብዙ ሺ አምፖሎች ተቃጥለውበታል። የሚሞክር ሰው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የሚፈልገውን በእጁ ማስገባቱ አይቀርም።


አስደሳች ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel