inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

አትፍራ !

ምድር ከፈጣሪ የተቸረችህ ትልቅ ስጦታህ ናት ከጥፋት በስተቀር ሁሉን ታደርግባት ዘንድ ፈቃድ ተሰጥቶኋል የፈለግከውን ነፃ ሆነህ ታደርግ ዘንድ መብት አለህ ማንም ሊነፍግህ አይችልም ስለዚህ ህልምህን ለማሮጥ ምንድነው የሚያስፈራህ ?

ነፃ እኮ ነህ በርትተህ ወደፊት ሂድ  🏃‍♀

ቆንጆ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ያልፋል አዎ !

ጥፋት አጥፍተህ እያመመህ ነው? ምነው ባላረኩት ብለህ ፀፀት ውስጥህን እየበላው ነው ? የማትቀይረው ነገር ሆኖብህ ከብዶሀል ?

አይዞህ ሁሉ የሆነው ባለማወቅህ ነው ብታውቅ ኖሮማ ይሄ ሁሉ ባልሆነ ነበር አሁን ግን አውቀሀል ዛሬ ሌላ ቀን ነው ይሄንን ስህተት ነገ አትደግመውም ይበልጥ እያወቅህ እኮ ነው !

እናም ዛሬም ያልፋል አዲስ ቀን ይመጣል ጥፋትህ ይቅርታ በጠየከው ፈጣሪህ ይረሳል አንተም ታርመህ መልካም ፍሬ ታፈራለህ !

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሌላ ነገር ሞክር !

መቼ ነው ከዚህ ህይወት ወጥቼ የምፈልገው ደረጃ ላይ መድረስ የምችለው የሚል ሀሳብ ውስጥህ ይመላለሳል! አንድ ነገር ሞክር እስኪ ሌሎች መንገዶችን ለማየት ጣር እየሄድክበት ያለኸው መንገድ ልክ ባይሆንስ ከሌሎች ካለፉት ተማር ፤ ህይወትን በሌሎች መነፅርም ለማየት ሞክር !

✅ እስከ ግንቦት 19 የአመለካከት ለውጥ ስልጠናችንን ለሚመዘገቡ ሰዎች ያደረግነውን የ10% ቅናሽ ለመጠቀም የመጨረሻው እድል ዛሬ ብቻ ነው !

ለተጨማሪ መረጃ 'Join' 👇
@Inspire_Ethiopia_Training

ምርጥ ቅዳሜ ተመኘን 🙏

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አዲስ ነገር !

ተመሳሳይ ነገር ብቻ ማድረግ አሰልቺ ነው አዲስ ነገር ህይወታችን ላይ ማየት ያስፈልገናል ስለዚህ እንማር ለውጥ ለመፍጠር ራሳችንን ዝግጁ እናድርግ !

ባለን ነገር ላይ ብቻ ተደላድለን ከመቀመጥ ይልቅ የተሻለ ልዩ ነገርን ስለማድረግ እንዘጋጅ የተለየ ደስታን እናገኝበታለን !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህ?😁

አንዴ ዞር በልማ አካባቢህ ምን አለ ማን አለ 😍 እየተዟዟረ እየቃኘ ያለውስ ሰው ደህና ነው አደል አለህ አይደል ፈጣሪ እድል ሰጥቶህ አንቅቶሀል አይደል ታድያ ተመስገን አያስብልም ?🙏

ለመደሰት ብዙ ምክንያቶች የሉንም ?አሁን ያሉንን ነገሮች ብንነጠቅ አይከፋንም ?ታድያ እጃችን ላይ ካሉ ማመስገን ለምን ከበደን?

ተመስገን 🙏🙏🙏

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትዋሽ !

ማንንም አይደለም- ራስህን አትዋሽ

ከሰዎች ልትደበቅ ትችላለህ ፤ ከራስህም ጥቂት ጊዜ ትሸሽ ይሆናል ነገር ግን ሌሊቱን ማን ይተኛልሀል ?

አዕምሮ ሞኝ አይደለም ሸውደኸው ፀጥ አይልህም ስለዚህ ንቃበታ አዎ ንቃ

የማትችለው ነገር አለ እመን - ከዚያም ተማር የከበደህ ነገር አለ - ራስህን አጠንክርለት
የሰዎች አስተያየት ፈርተሀል - አንተስ አያስፈልግህም ?

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ባለመመረጥህ አትዘን!

ምርጫ ውስጥ ባለመግባትህ አትገረም ያለቦታው ምንም ነገር አያምርም ያልተመረጥክባቸው ያልተፈለግክባቸው ቦታዎች ባንተ ልክ የተሰፉ ስላልሆኑም ነው !

አንዳንዴ ደግሞ ልክህ እስኪሆኑም እየጠበቁ ይሆናል ስለዚህ የሚገባህ ልክህ የሆነ ቦታ ስለመገኘት ብቻ አስብ!

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አታቁም !

አለማለም አይቻልም ይብዛም ይነስም ሁሉም ሰው ሊያሳካው የሚፈልገው የሆነ ነገር አለው ነገር ግን ስኬታማውን ሰው ይበልጥ ወደ ከፍታ የመራው የሚፈልገውን ጠንቅቆ ማወቁ እና ለእርሱም ከልቡ ወደኋላ ሳይል መልፋቱ ነው !

"ላመንክበት ነገር እስከ ጥግ ጣር !"

ቆንጆ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኘ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉ መልካም ነው !

የፈጣሪ ረቂቅ ስራ የሚደንቀው በምን ሰዓት ምን ሊሰጥህ እንደሚችል አለማወቅህ ነው በሚደንቅ ሁኔታ ተዓምር ያሳይሃል እናም ዛሬ ላይ የሚሆን ባይመስልህም አይግረምህ ሁሉም በጊዜው እና በሰዓቱ መልካም ነው !

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለፈጣሪ ስጥ !

ይቅር ባይ የሆነ መሀሪ አምላክ አለን የሚያስፈልገንን በግዜው የሚሰጠን እኛን ከመጠበቅ ወደ ኋላ የማይል ሁሌም ስለኛ ስለፍጡሮቹ የቆመ ካሰብነው በላይ ረቂቅ የሆነ ብዙ ተዓምራቶችን የሚያሳየን ፈጣሪ አለን !

ታድያ ምንድነው የሚያስጨንቀን ነገአችን ለምንድነው አብዝቶ እንቅልፍ የሚነሳን ሁሉ ሄዶ ከእርሱ አያልፍ ታድያ ለምን ሸክሜን አቅልልኝ ብለን አንሰጠውም ያኔ በሰዓቱ ነገር ሁሉ ውብ ይሆናል!

ቆንጆ ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ትከበራለህ !

ሰዎች የሚያከብሩህ በምትሰጣቸው ማንነትህ ልክ ነው ! ቃላቶችህ ማንንም አይሸውዱም ዛሬ ላይ በእነርሱ ብትከበር ነገ ተግባርህ መልሶ ሊጥልህ ይችላል !

ለሰዎች ከምትነግራቸው በላይ ስጣቸው ከልብህ ሁንላቸው አስብላቸው ያኔ ስጡኝ ሳትላቸው የሚገባህን ክብር የሚሰጡህ እነርሱ ናቸው ከምንም ነገር በላይ ግን መልካም ሁን !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉም አንድ አይደለም !

አንዳንድ ሰዎች ብዙ ተስፋ ይሰጡህ እና ጠብቀሀቸው ተስፋህን የሚያመነምን ነገር ያደርጉብሀል ሌሎች ደግሞ ብዙም ሳትጠብቃቸው ካሰብከው በላይ የሆነ ነገር ይሰጡኋል !

እናም ሁሉም ሰው አንድ አይደለም አንዱ ባስቀየመህ በብዙዎች አትፍረድ እምነትህም አይጓደል ! ፈጣሪ ላንተ ያዘጋጃቸው ብዙ ቀና ሰዎች አሉህ ከልህ ከፈለግካቸው ይመጣሉ !

ደስ የሚል ሀሙስ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተስፋ እንሁን !

በሚገርም ሁኔታ ትንሿን ፈገግታ በማየት ብቻ ከትልቅ ተስፋ መቁረጥ የወጡ ስንቶች እንዳሉ ሰምተሀል?

መልካምነት ያለህን መስጠት ነው ለማይከፈልበት ጥርሳችን ምናለበት ጠዋት በሰላም ነቅተን ስንራመድ ለምናያቸው ሁሉ ፈገግታችንን ብናካፍል!ለስንቱ ተስፋ እንሆናለን 😁

የደስታ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትጨነቅ !

እርሱ የከፈተውን ቀዳዳ ሳይደፍን አያድርም ሁሌም ቢሆን ለእኛ ስለእኛ የቆመ አምላክ እንዳለን አንዘንጋ !

አብዝቶ ያስጨነቀህን ያሳሰበህን ነገር ሁሉ ለእርሱ ስጠው ሁሉን ሙሉ ያደርግልሀል!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምርጫ የኛው ነው !

ሁላችንም ከሁለት አንድ ምርጫ ልንመርጥ እንገደዳለን የዲሲፕሊን ህመምን ወይም ደግሞ የፀፀትን ህመም የትኛው እንደሚሻለን የምናውቀው እኛ ነን !

አዲሱን ለስልጠና መረጃ ብቻ የተዘጋጀውን ቻናል ለመቀላቀል 👇
@Inspire_Ethiopia_Training

የስኬት ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የሚገባህን ኑሮ ኑር !

ለሌሎች ብለህ ማንነትህን አትቀይር አንተ እዚህች ምድር ላይ የተፈጠርከው አንተን ለመሆን ነው ብዙ ልዩ ነገር ይዘኋል!

ስለዚህ ራስህን አትጣው ያለህ አንድ እድል ነው ማንም ሌላ እድል አይጨምርልህም እናም እንዳትፀፀት ዛሬ ጀምረህ መኖር ጀምር 😊

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን አዳምጥ !

ለራስህ እውነተኛ ግዜ ስጠው እያደረግከው ካለኸው ነገር ጋር የእውነት ተስማምታችዋል ወይ ነው ወይስ ማድረግ አለብኝ ብለህ ስለተሰማህ ብቻ ነው እያደረግከው ያለኸው ? እንደዚህ ሆነህ እስከመጨረሻው ለመኖር ተስማምተሀል?

የፈለግከውን እውነተኛ ህልምህን ለመኖር ከጫጫታ ውጣና ከራስህ ጋር አውራ !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈርተህ እንዳትመለስ !

አዎ አዲስ ነገር ሁሌም ያስፈራል ልክ ስትጀምረው ምነው ወደኋላ ብመለስ ቢቀርብኝ ወይ ባልጀምረው ኖሮ የሚል መመላለስ ውስጣችን ይመጣል !

ነገር ግን ይሄ ለውጥ ነው የስኬታችን መጀመሪያ መንገድ ነው ይሄንን ልክ አዲሱን ነገር መቀበል ስንጀምር የምንፈልገው ለውጥ እየተሳካ ይመጣል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ህግ ይኑርህ !

የማትደራደርበት ህግ አውጣ ማንም የማይጥስብህ ፣ምንም ነገር ቢፈጠር የማትቀይረው ፣ በማንኛውም ሁኔታ ልታከናውነው የሚገባ ወደ ስኬትህ ለመጓዝ መርህ የሚሆንህ ህግ ይኑርህ !

ወደኋላ ላለመመለስ ቆራጥ መሆን አለብህ!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ውድድር !

በቃ ውድድሩን አቁም አንተ ራስህን ስታሸንፍ እና እንደራስህ ስትሆን ነው የሚያምርብህ አዎ እነርሱ የራሳቸው የሆነ ተሰጥኦ እና ማንነት አላቸው !

አዎ አንተም እንደዛው እስኪ አንዴ ቀና ብለህ ራስህን ተመልከት ስንት ልዩ የሆነ ነገር አለህ ?

እናም ከሰው ይልቅ ትላንትህን ለመቅደም ጣር !

የደስታ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ገንዘብ !

ገንዘብ መጥፊያ ነው ባክህ ስለገንዘብ ብዙ አትጨነቅ የሚሉህ ሰዎች አሉ? ባለሀብት መሆንን የሀጢያት መለኪያ ተደርጎ ተስሎልሀል 😁

😳 እውነት ነው ገንዘብ መጥፊያ ነው - አዎ አጠቃቀሙን ያላወቅከው እለት ትጠፋበታለህ

😄ነገር ግን ከፈጣሪም መታረቂያ ይሆናል - መቼ ? በተባለለት ቦታ ሲውል !

ሲኖርህ ቃል ጠብቅ ለሚገባቸው አካፍል ለተራቡት አብላ ላጡት ዋስ ሁናቸው ያኔ ከፅድቅም የፅድቅ መንገድን ይከፍትልሀል!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የማይሳካ የለም !

የእውነት የምነግርህ ነገር ፈጣሪ የፈለግከውን ነገር ያሳካልሀል ! ነገር ግን የምትፈልገውን ጠንቅቀህ ማወቅ አለብህ ነካ ነካ አታድርግ !

በሙሉ ልብህ ሆነህ የጀመርከውን ቀጥል እዛ ውስጥ የሚያጋጥሙህን መሰናክሎች በድል ለመወጣት ጣር አሁንም እመነኝ ፈጣሪ ያግዝሀል !

ደስ የሚል ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለስኬታማ ሳምንት !

ደስ የሚል የዕረፍት ቀን አሳለፍክ አይደል? ነገ የስራ ቀን ነው ከዛሬ ቆንጆ የእረፍት ቀን በኋላ ነገ መልካም ውጤት ለማምጣት ምን ያህል ጓጉተሀል ?

ሁሌም ጥራት ያለው ነገር መስራት ያኮራል አይደል ስለዚህ ትንሽ ለራስህ ግዜ ስጥ እና እቅድ አውጣ ሳምንትህን የምትመራበት ፕሮግራም አዘጋጅ ከዛም ቀለል እያለህ ወደስኬት !🏃‍♂

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትፍረድ !

ሰዎች ላይ አትፍረድ ብዙዎች የሚጠፉት ወደው አደለም ካለማወቅ እንጂ አንዳንዴ ያወቅን ሲመስለን ያላወቅነው ብዙ እንዳለ እናውቃለን !

እናም ለነበሩት ጥፉቶቻችን ትልቁ ምክንያት አለማወቃችን ነው ሁሌም ለማወቅ ከመጣር ወደኋላ አትበል ብትቸል ለሌሎችም ከምትፈርድባቸው የምታቀውን አሳውቃቸው !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሞክር ይሳካል !

ሞክር ትወድቅ ይሆናል ነገር ግን የምትወድቀው ወደፊት ነው ያኔ የተወሰነ እርምጃ ከነበርክበት ትቀድማለህ ያሰብከውን በሰዓቱ ባታሳካው እንኳን በአዕምሮ ፣ በአቅም ታድጋለህ ያኔ ድጋሚ ለምትሞክረው ሙከራ ይበልጥ አድገህለታል !

"ብዙ ሙከራ ብዙ እድገት ያመጣል እና በስተመጨረሻ ያሰብከው የለፋህለት ሁሉ ዋጋ ይከፍልሀል"

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ማረጋገጫ አትጠብቅ !

አንዳንዴ አንዳንድ ነገሮች ላይ ልክ መሆንህን የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ እናም በምታደርገው ነገር በሙሉ ማረጋገጫ የሚሰጥህ ላታገኝ ትችላለህ ያኔ ቆም በልና ለራስህ ይሄንን ንገረው :-

" አንተ ካመንክበት በቂ ነው !"

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እምቢ በል !

አንዳንዴ እምቢ ማለት ልክ ነው ስለራበህ ብቻ መርዝ አትበላም የቀረበልን ነገር ሁሉ መልካም አይደለም በረሀብ ላለመሞት ብሎ ማንም በመርዝ ራሱን አያፋጥንም !

እናም አንዳንዴ እምቢ የምትለው መቆየት ስላለብህ ነው መልካሙን ፍሬ የምታገኝበት ቀን ስለሚመጣ !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምክንያትህን አሸንፍ !

ቆንጆ እድል ምክንያትን ትጋብዛለች ልክ የሆነ መልካም ነገር ስናገኝ እርሱን እንዳንጠቀምበት ወይም ይበልጥ እንድንበረታ የሚያደርግ ነገር ይፈጠራል እና ግን ከምክንያቱ በላይ ስንሆን ህይወት ከጠበቅነው በላይ ብሩህ ይሆናል !

"አንድ እርምጃ አንድ ለውጥ ነው እና ሁሌም ከለውጡ ጋር ተራመድ "

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እድል አለ !

እድል በየትኛዉ ቀዳዳ በኩል እንደሚመጣ አታዉቅም ስለዚህ አትዘናጋ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀም ወደኃላ አትበል !

ወደ ፊት ሂድ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏🏽
@Inspire_Ethiopia
የእናንተዉ ምርጥ ጓደኛ ☺️

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ትንሽ ስራ ለብዙ ለውጥ !

ለውጥ ለመፍጠር - ከልብህ ታትር
ስኬታማ ለመሆን - አጥና
ማንነትህን ለማስተካከል - ልማድህ ላይ ስራ

በዚህ መንገድ ከሄድክ የፈለግከው ማግኘት እጅግ በጣም ቀላል ይሆንልካል !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel