inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

የፈጣሪህ አይተውህም 🧎‍♀🧎

ፈጣሪ ዝም እያለህ እየተወህ እየረሳህ አይደለም ዛሬም አለ አንተን እየጠበቀ ነው ዛሬም ከጎንህ ሆኖ እንዳትወድቅበት ድጋፍ እየሰጠህ ነው 🤲

የራቀህ ያላየህ የሚመስልህ ግዜ እርሱ ውድቀትህን ለማረም አንተን ከፍ ለማድረግ ከስርህ ያሉ እንከኖችህን እያፀዳልህ ነው ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን በማይጥልህ ለምክንያት በሚደግፍህ አምላክህ እመን !🧎‍♀🧎

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዝቅ ማለትህን ለከፍታ...💪

ረጅም ፎቅ 🏢 መሥራት የሚያስብ ሰው ወደታች ረጅም መሠረት መሥራት አለበት ። እኛም በህይወታችን ትልቅ ነገር መሥራት ሥናስብ ልክ ፎቅ ወደ ላይ ለማቆም ወደ ታች አንቆፍርም አንደማንለው ሁሉ  ፦

በህይታችንም ፈተና ሲያጋጥመን ወደ ላይ ነጥረን ለመውጣት ጠንካራ መሠረት እየሰራን አንደሆነ አስበን በደስታ እና በምስጋና ከስህተታችንም እየተማርን እንጠብቅ !

ጣፋጭ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ኮርጅ !

መሆን የምንፈልገውን ነገር ምን እንደሆነ ካወቅን ብዙ አቋራጭ መንገዶች አሉ፤ ምክንያቱም ከኛ ቀድመው እኛ መሆን የምንፈልገውን ያሳኩ ሰዎች ብዙ ሰዎች ስላሉ ከነሱ የህይወት ልምድ ብዙ ነገር ለራሳችን መውሰድ እንችላለን።

'ከሌሎች ህይወት መኮረጅ ጥሩ ነገር ነው፣ መስረቅ ግን ታላቅነት ነው' ይለናል ታላቁ አርቲስት ፒካሶ።

ውብ ቅዳሜ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከጭንቀት ነፃ መሆን !

አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን የሚመነጩት ልንሰራ ያሰብነው ነገር ከባድ ወይም ብዙ ስለሆነ አይደለም የጀመርነውን ቀላል ነገር ስላልጨረስን ነው !

ትላንት አልፏል አንጨብጠውም ነገም በእኛ እጅ አይደለም ማስተካከል የምንችለው ዛሬን ነው ያውም አሁንን ስለዚህ ይህችን ቆንጆ ቀንህን ተጠቀም እና ነገን ስራ ! ነፃ ትሆናለህ

የ21ኛው ዙር ኦንላይን ስልጠናችን ሊጀምር 6 ቀናት ብቻ ቀርቶታል ለመመዝገብ አሁኑኑ ይወስኑ

ለተጨማሪ መረጃ 👇

☎️ +251944314544 ይደውሉ

ብሩህ ቅዳሜ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ግብ አስቀምጥ !

አንድ የሚገርም ኳስ ጨዋታ እያየን ከዛ ግን ጎል 🥅 የሚባል ነገር ባይኖረው ምን እንደሚሰማን አስቡት 🤔

ህይወታችን ላይም ተመሳሳይ ነገር ነው  ፤ ዋናው ነገር እዚም እዚያም ስራ መሥራት እና መቀያየር አይደለም ጨዋታውን ማሳመር እንጂ
  
ስለዚህ ጎል ይኑረን ⚽️

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትጠብቅ !

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ
ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ።

የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው። ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

አስገራሚ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተ ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዛሬን ስራ !

አልበርት አንስታይን
'ከትላንት ተማር፤ ዛሬን በደንብ ኑር፤ ነገን ደግሞ ተስፋ አርግ' ይለናል። ብዙዎቻችን ትላንትናችን ውስጥ እየኖርን ነው፤ ከአመታት በፊት የሰራነውን ስህተት አሁንም እየተፀፀትንበት እየተቆጨንበት ምናለ እንዲህ ባደርግ እያልን ነው።

አንዳንዶቻችን ደግሞ ነገ ውስጥ ገብተን እየዋኘን ነው፤ ስለነገ ማሰባችን አሪፍ የሚሆነው የዛሬ ድርጊታችንን የማይሻማን ከሆነ ነው። በህይወታችን ወሳኙ ግን ዛሬ ነው! ቢያንስ እጃችን ውስጥ ነው።

ውብ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ህይወት ይሰለቸኛል ምን ላድርግ?

አስባችሁት ከሆነ አብዛኛው ሰው 10 አመት የስራ ልምድ አለኝ ሲል የአንድ  አመት የስራ ልምድ አለኝ ግን አስር ጊዜ ደጋግሜዋለው ቢል ይቀላል። ምክንያቱም በአስር አመት ውስጥ የጨመረው ችሎታ ያሳደገው አዲስ ልማድ የለም።

ታዲያ ምን ይሻላል?
መልሱ ቀላል ነው! ሁልጊዜም ከትላንት የተሻለ ቀን ለማሳለፍ መጣር፤ አዲስ ነገር በመሞከር ወይ ደግሞ የነበረውን ልማድ በማሻሻል።

ጣፋጭ ጊዜ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ባንተ እይታ ተመልከት !

ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ የእይታ መነፀር አለው አንዱ የሚያምንበት ነገር ሌላው ላያምንበት ይችላል እየሰራኸው ያለኸውን ነገር ምን ያህል ለውጥ እንደምትፈጥርበት የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ !

ሌሎች ይሳካል ስላሉህ ብቻ ይሳካል ማለት አይደለም አይሆንልህም ስላሉህም ብቻ አትወድቅም !

ቆንጆ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እረፍት !

በእረፍት ቀንህ ምን ማድረግን ወስነኋል? ይህችን ቆንጆ ቀን በምንድነው ማሳለፍ ያሰብከው ? ሳምንትህ ላይ ምን ተከሰተ ?

ዛሬ የማወራረጃ ቀን ነው ምን ታቅዶ ምን ተከወነ ምን ታስቦ ምን እውን ሆነ ለሚል ጥያቄ ሁሉ መልስ የሚሰጥበት ቀን ነው ስለዚህ ትንሽ ደቂቃ ውሰድ እና ራስህን መርምርበት !

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወደፊት ብቻ !

መቀየር ያሉባቸውን ነገሮች ቀይር ለመቆም ሳይሆን ለመራመድ ተነስ ወደኋላ ሳይሆን ወደፊት የምትሄድበትን መንገድ ብቻ አስብ ያለህበት ሁኔታ ከዛሬ የማያሻግርህ ከሆነ አሁኑኑ ወስን ቆም በልና መቀየር ያለበትን ነገር ሁሉ ቀይረህ እርምጃ ጀምር ! ወደፊት ብቻ🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀

ቆንጆ ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እመን !

በማንኛውም ሰዓት አለሁልህ ላንተ ያሰብኩትን ነገር ማንም አይቀማህም ሁሉን በጊዜው እና በሰዓቱ አደርግልሀለው ትቼህ አላውቅም መቼም አልተውህም የሚል ፈጣሪ አለን !

በተግባር ከእኛ በላይ ለእኛ ሲያስብልን ሲደግፈን እያየን ነው ዛሬ ነገሮች ቅር ቢያሰኙንም ነገ ዳግም እናበራለን ከእኛ የሚጠበቀው ከልባችን ማመን ብቻ ነው !

የደስታ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለማደግ ተነስ !

ህይወት በይስሙላ የምትሞላ ነገር አይደለችም ማሰብ መመራመር መጣር ሁልግዜም ማደግን ትፈልጋለች ካልሆነ መመላለጥ ይመጣል !

ስለዚህ ብልጥ ሁን ይሄ ቢሆንስ ያ ቢደረግስ ብለህ መጠበቅን ትተህ ራስህን ለማሳደግ ጣር ወደኋላ አትበል !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈጣሪ ሰጥቶናል !

በረከትህን ከራስህ ላይ አትንፈገው ፈጣሪ አክብሮ የሰጠህን ንቀህ አትጣልበት እርሱ ከሰጠህ የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም !

ለተሰጠህ ሁሉ አመስግን ባለህ ሁሉ ደስ ይበልህ ከልብህ አክብራቸው እናም እንዳይከስሙ ከስር ከስር ተንከባከባቸው ያኔ ይጨመርልሀል !

ደስ የሚል ረቡዕ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የስኬት ህግ!

🪄ራስህን ክፍት አድርግ ለምን? - ምክንያቱም ብዙ አዲስ ነገር ይጠብቅሀል !

🪄ነፃ ሁን ለምን? - የተቀበልከውን አዲስ ነገር ለመቻል ብቁ መሆን አለብህ !

🪄 ጠንክር ለምን? - የገባህበት ቦታ ሊያንገዳግድህ ይሞክራል !

🪄 ቆራጥ ሁን - የጀመርከውን ማቋረጥ አይፈቀድም ! ምክንያቱም አሁን የቆምከው ላንተ ብቻ አይደለም ባንተ ማሳካት ውስጥ ብዙዎችን ታበራለህ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከትላንትህ ጋር ተወዳደር !

በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም።

ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም።

ደስታ የሞላበት ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የምትፈልገውን ሰው ለመስራት !

መመጥፎ አመልን ለመተው ስትነሳ እነዚህን ሁለት ስህተቶች አትሳሳት ፦

☝️ ከመነሻው ስህተት የፈጠርክበት ቦታ ላይ ሆነህ ስህተቱን ለማስወገድ አትጣር !
☝️ በአንዴ ያልጀመርከውን ነገር በአንዴ ለማቆም ብለህ አትጨነቅ !

የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የራስህ ቀመር ስራ !

አብዛኞቻችን በህይወታችን ደስታ የራቀን በሌሎች መንገድ ለህይወታችን ቀመር ለመስጠት ስለምናስብ ነው።

ይሄ ካልሆነ አይሳካም ይሄ ካልሆነ አይሆንልኝም ብለን እናስባለን ።

አውነት ነው  ብዙ ነገር ሊያስፈልገን ይችላል ማወቅ ያለብን ነገር ግን ህይወት እንደ ት/ት ቤት ለሁሉም አንድ አይነት  ፈተና  አትሰጥም ።

ዋናው ነገር ግን ለኛ የሚሆነውን የህይወት ቀመር መፍጠር ነው።

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላምታዬ ይድረስ🙌

Inspire Ethiopia 12ኛ ክፍሎች በዚህ አጭር ጊዜ ማትሪክን ከ 500 በላይ እንዲያመጡ የሚረዳቸውን ኮርስ እየሰጠ ነው። ኮርሱን የምታገኙበት አፕሊኬሽን FutureX ይባላል።

አፕሊኬሽኑ

👉 ያለ VPN በፍጥነት ይሰራል
👉 በቅርቡ ከ 9-12ኛ ክፍል Maths ትምህርት ይለቀቃል
👉 Download ለማድረግ 1 ደቂቃ አይፈጅም ምክንያቱም 9mb(ሜጋ ባይት) ብቻ ነው

🛑 ኮርሱን ወዲያው ለመጀመር
ይሄንን በመንካት 👉@futurexethiopia የቴሌግራም ቻናል አባል መሆንና FutureXን Google Play Store ወደ ስልክዎ መጫን ነው። በኮርሱ እንገናኝ!

ምርጥ ውጤት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ልዩ ምሽት ነበረን 👩‍🎓👨‍🎓

የትናንትናው ምሽት በኢንስፓየር ኢትዮጵያ የታሪክ መዝገብ📚 ተመዝግቧል !

ስልጠናዎቻችንን ስናዘጋጅ በእርግጥም ሰዎች የተግባር ሰው እንዲሆኑ እና የሚታይ ለውጥ እንዲያመጡ በማሰብ ነው ፤ የመጣው ውጤት ግን እጅግ የተለየ እና ከጠበቅነው በላይ ነው 😊

በትናንትው ምሽት ላሳያችሁን ፍቅርና ፍፁም ቤተሰባዊነት 👨‍👩‍👧‍👧 ምስጋናችንን ልናቀርብላችሁ እንወዳለን በትክክል የዘራነው ዘር ፍሬ ማፍራቱን አስመስክራቹሃል !

✨ለሰልጣኞቻችን ሰርተፍኬት መስጠት ብቻ ሳይሆን ፤ ለየት ባለ መልኩ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶልናል !

በድጋሚ ለ20ኛው ዙር ስልጣኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ከልብ እናመሠግናለን 🎇

🍿የፈንዲሻ ሰዓት ቤተሰቦቻችን ቀጣይ ሳምንት ሀሙስ እንገናኝ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ብዙ አታስብበት !

🤔 እንዲ ባደርግ...እንዲ ቢሆን...እያልክ ስታሰላስል ጊዜው ይነጉዳል ከወደቅክ አይቀር ቶሎ ውደቅ፤ ግን ስትወድቅ ወደፊት ውደቅ !

የ 42 ኪሎ ሜትር ማራቶን በአንድ እርምጃ ነው የሚጀመረው...ፍጥነትህንና ስትራቴጂህን ለመቆጣጠርም እዛው እየሮጥክ ሁኔታዎችን እያየህ አይሻልም? አልጋ ውስጥ ሆነህ እንዲ ባደርግ ከዛ ይሄን ባደርግ ከምትል፤ መጀመሪያ ስራውን ጀምረው ከዛ እያየህ ትጨምርበታለህ።

ዳይ ወደ ስራ!

ቆንጆ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስህተትህን አርም ! 🤔

ስህተትህን ለመቀበል ዝግጁ ካልሆንክ እመነኝ ትወድቃለህ ! ያለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነው አንድ ልክ ያልሆነ ነገር እየተከናወነ ስለሆነ ነው !

ስለዚህ ራስህን ተመልከት ሌሎችን ከመተቸት ውጣና ምንድነው ያጎደልኩት ብለህ ራስህን በሚገባ መርምር ማለፍ እና ማሸነፍ ከፈለግህ ከዚህ ውጪ አማራጭ የለህም !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምረጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስታ !

ደስተኛ ለመሆን አዲስ ተዓምር መፈጠር የለበትም ደስታ ባንድ ቀን ክስተት ብቻ የምትፈጠር የህይወት ጣዕም አይደለችም !

በየቀኑ እኛ በመኖራችን ብቻ አዚህ በመገኘታችን ብቻ ደስተኛ መሆን አለብን ያለንን ሁሉ እያየን ደስ ይበለን ፈጣሪ ስለደገፈን ስላለልን ስለማይተወን አምላክ ደስ ሊለን ይገባል ! እውነተኛ የማያቋርጥ ደስታ ከዚህ ይፈጠራል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስኬት ላንተ ምንድነው ?

በገንዘብ መበልፀግ ? ዝነኛ መሆን ? በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፍ? ከራስ አልፎ ለሌሎች መትረፍ መቻል ?

ሁሉም የሰዎች ፍላጎት ይሆናሉ ፤ ነገር ግን መምረጥ ያለብህ እውነተኛ እርካታ የሚሰጥህን ማንንም ሳይሆን አንተን ሰላም የሚሰጥህን ተከተል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ታገስ !

የታገሰ መልካሙን ፍሬ ይበላል ለጠበቀ ሰው ሁሉ መልካም ነዉ በጌዜው የማይሆን አንዳች ነገር ለማይኖር በችኮላ ለፀፀት የሚዳርግህ ነገር ውስጥ አትግባ ለሚያልፍ ዛሬ የማያልፍ ታሪክን አትፃፍበት ትንሽ ብቻ ታገስ ብዙ ታተርፋለህ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እስቲ ተመልከት !

አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ነገር አጋጥሞህ ያውቃል?🧐 ብዙ ከቁጥር የሚያልፉ በረከቶች ተሰጥተውክ ሳለ በአንዲት የማትጠቅም ምኞትህ ተሸፍነህ ጎዶሎ እንደሆንክ ተሰምቶክ ያውቃል ?በብዙ መመስገን ላለበት ፈጣሪ ምስጋና ነስተከዋል?

በል ንቃ እና በረከቶችክን ተመልከት እናም ፈጣሪህን ይቅርታ ጠይቅ አመስግነው ያንስበታል !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሀላፊነትህን ተወጣ !

የራስህን ሀላፊነት ብቻ ተወጣ ሁሉም ሰው አንተን ሊሆን አይችልም እንዳንተ ሊያስብ እንዳንተ ሊረዳ አይችልም ስለዚህ ከማንም ምንም ሳትጠብቅ የራስህን መንገድ ብቻ ቀጥል ያኔ ካንተ አልፈህ ለሌሎች ምሳሌ ትሆናለህ !

🍿 የፈንዲሻ ሰዓት ኘሮግራማችን ከ1:00 ሰዓት በኋላ ይጀምራል ነፃ የ 'Zoom' እና ዩቲዩብ ሊንክ ለማግኘት ከታች ያለውን ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀላሉ 👇
@Inspire_Ethiopia_Training

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዋናው ረዳት አለልህ !

የዚህን አለም ዋናው ቁልፍ ያለው ፈጣሪ ጋር ነው የፈጠረን ፈጣሪ እዚህ ያቆመን ፈጣሪ መንገዳችንን የሚመራን ፈጣሪ !

ስለዚህ ወዴት ትሄዳለህ ወደእርሱ ቀና በል እንጂ የጥያቄህ መልሱ ያለው እኮ እርሱ ጋር ነው ስለዚህ አትፍራ ጠይቀው ይመልስልሀል አትጠራጠር !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለህልምህ ቦታ ስጥ !

የምትፈልገው ቦታ ላይ ከመገኘት ወደኋላ አትበል ብዙ የማይጠቅሙን ቦታዎች ላይ አላስፈላጊ ጊዜያትን እናባክናለን ለህልማችን ግን ዛሬ ነገ እያልን ቀጠሮ እንሰጠዋለን !

ከዛሬ ጀምሮ ቀጠሮ የምንሰጠው ለማንፈልገው ውሎአችን ይሆናል ነገ ከነገ ወዲያ እያልን አስቀርተነው ዛሬን ለህልማችን እንክፈለው !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰበብ ይቅርብህ!

ለምን ሰበብ ትፈልጋለህ? አሁን እየሰጠኸው ያለው ምክንያት ካንተ እና ከሰዎች አልፎ ለህይወትህ ውጤት እያመጣልህ ነው ?

እመነኝ ምንም ነገር ብትል ህይወት ምክንያትህን ሳይሆን በጥረትህ የምታመጣው ውጤትህን ነው የምትሸልመው ስለዚህ አታሳብ ለሁሉ ነገርህ ተጠያቂው አንተ ነህ ስለዚህ ወደራስህ ተመልከትና ለውጤትህ ተነሳ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel