inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ምን አይነት ዕድለኛ ነህ?!

እሳትን የሚያበርደው ውሀ ነው፣ አልጫን የሚያጣፍጠው ጨው ነው፣ ያንተን ህይወት ጣዕም የሚሰጠው ፈጣሪ ነው። ደስታን ለማግኘት ማንኛውንም ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ፤ ብዙ ነገር አሳክተው ደስታን የጨበጡ የመሰላቸው ሰዎች ዘግይተውም ቢሆን ንፋስ እንደዘገኑ አውቀዋል።

እውነተኛ ደስታ ከፈለክ ፈጣሪ እስከዛሬ ባደረገልህ፣ አሁን ባለህ ነገር አመስግን፤ "ምን አይነት ዕድለኛ ነኝ?" በል፤ ገና በሚመጣው ሳይሆን አሁን ህይወትህ ላይ ያለውን እይና ተደሰት! አበቃ!

የሚያምር ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትፍረድ !

ሰዎች ምን አይነት ነገር እያሳለፉ እንደሆነ አታውቅም በምን መንገድ እንዳለፉ እንዴት እየሄዱት እንዳሉም አታውቅም ስለዚህ በማታውቀው ነገር ላይ ምንም አስተያየት አትስጥ ከቻልክ ፀልይላቸው ያንተም ህይወት በምን እንደሚያልፍ አያውቁም እና አንተም በሚሰጡህ አስተያየት አትገረም !

መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከእኛም ይጠበቃል !

ፈጣሪ ከፃፈልኝ ውጪ የሚሆን ነገር የለም በቃ እርሱ ያለው ይሆናል ብሎ እጅን አጣጥፎ መቀመጥን የመሰለ ሞኝነት የለም ፈጣሪ ታሪክ ይቀይራል ተግተን ስናደርግ የሚገባንን ይሰጠናል ቁጭ ካልን ግን ከታሰበልንም እናጣለን !

የስኬት ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አንጣደፍ !

ሁላችንም በዚች ምድር ላይ ስንኖር ትልቅ አሻራ ጥለን ማለፍ እንፈልጋለን ፤ ፍላጎታችን መልካም ሆኖ ሳለ ግን ነገሮች በአንዴ ካልጠቀየሩ እያለን ከራሳችን ከሚገባው በላይ ስንጠብቅ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ሳናደርግ እንቀራለን !

እውነት ነው ትልቅ ደረጃ መድረስ አለብን ግን ትንሽ ለራሳችን ጊዜ እንስጥ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

1 ቀን ቀረው

ውድ ቤተሰቦች ታላቅ የህይወት መድረክ ተዘጋጅቷል !

► መናገር ፈርተህ ብቻህን እየታመምክበት ያለ ሀሳብህ ሌሎች ጋር እንዳለ ስትሰማ እናም የሚፈታ ችግር መሆኑን ስታውቅ ምን ይሰማሀል? እዚህ መድረክ ላይ ብዙዎች ተገርመዋል ብቻቸውን እንዳልሆኑ እናም ማሸነፍ እንደሚቻል በዓይናቸው አይተዋል !

► ማልቀስ መጮህ እንደፈለጉ ሆኖ ስሜትን መግለፅ እዚህ መድረክ ላይ የሚሰጥ ትልቁ መብት ነው ሁሉም ሰው ነፃ ነው ማንም ማንንም አይገምትም በምንናገረው ፣ በምናደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ስም የሚሰጠን የለም በነፃነት የምንራመድበት በራስ መተማመናችንን የምናዳብርበት እድል ነው!

ከምንም በላይ የሚከብደው እዚህ ቤተሰብ ውስጥ ተቀላቆሎ መለያየት ነው !

► በጣም ለረጅም ዓመት ጥያቄ ሲፈጠርባችው የነበረ ፤ ምንድነው እየጎተተኝ ያለው ? ምንድነው ተመልሼ አንድ ቦታ ላይ የምገኘው ? ምን አይነት ችግር ነው ያለብኝ ? ብለው ከብዙ ነገር ጋር አያይዘው ሲቸገሩ የነበሩ ብዙዎች በዚሁ መድረክ ጥያቂያቸው ተፈቷል የአመታት ታሪክ በ6 ሳምንታት ጊዜ ይለወጣል !

🔸 በየትኛውም የአለም ክፍል የምትገኙ ( አውሮፓ ፣ አሜሪካ ፣ አፍሪካ እና የተለያዩ አረብ ሀገራት ) ፤ በራሳችን ቋንቋ ፤ የእጅ ስልካችሁን ብቻ በመጠቀም መሳተፍ የምትችሉበት ልዩ ስልጠና !

ነገ ማታ 3:00 ሰዓት የ 6 ሳምንት ጉዞአችን ' ሀ ' ተብሎ ይጀመራል !

ስልጠናው ላይ ለመሳተፍ 📲 +251944314544 ይደውሉ ወይም በቴሌግራምና ዋትስአኘ መልዕክት ይላኩ

የተለያዩ አማራጮች ስለተዘጋጁ ከላይ ባለው ስልክ ተጨማሪ መረጃ ይጠይቁ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለራስህ ቃል ግባ!

ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው!

ተስፋ የሞላበት ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የአይምሮ ሰላም

ሁሉንም ለማስደሰት እንደሚጥር ሰው ከንቱ የለም! ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ነገር አይደሰትም እኮ፤ በተለያየ ነገር ለሚደሰቱ ሰዎች ስንል ደግሞ እኛ እንደ ወረቀት መተታጠፍ የለብንም።

ህሊናችን የሚነግረንን አይምሮአችን የሚያዘንን ልባችንን በደስታ የሚቀበለውን ብቻ መርጦ ማድረግ፤ ያኔ ሰዎች ቢደሰቱም ባይደሰቱም ህሊናችን ግን ምን ነካህ እያለ አያስጨንቀንም። ወዳጄ ለህሊናህ ስትታመን ሁሌም ውስጥህ ሰላም አለ!

ሰላማዊ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስኬት የየዕለት ማንነታችንን ይፈልጋል !

በህይወታችን የምናወጣቸው እቅዶች የምናልማቸው ህልሞች እንዲህኑልን የምናስባቸው ትልልቅ ስኬቶች እያንዳንዱ ቀናችን ላይ እያንዳንዱ ግዜያችን ላይ ሰርተንባቸው የሚሳኩ ናቸው ! ዛሬን በማይጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ካሳለፍነው የምንፈልገውን ስኬት ከመሆን እያራቅነው ነው ስለዚህ ሩቁን ብቻ እያሰብን ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገቡንን አንዘንጋቸው !

የደስታ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መስነፍ አያዋጣህም!

በህይወትህ በጣም ወሳኙ አሁን የገጠመህ ችግር ወይ የሁኔታዎች ከባድ መሆን አይደለም፤ ያንተ ቆራጥነት ነው! ምን ድረስ ላመንክበት ለመጓዝ ወስነሀል ነው ጥያቄው!

ረሀብ ቢሰማህ "ካገኘው እበላለው ካላገኘው ችግር የለው የለውም" አትልም እኮ፤ ያንን ምግብ ለማግኘት በቆራጥነት ዋጋ ትከፍላለህ እንጂ አይንህ እያየ በረሀብ አትሞትም።

አሁንም አይንህ እያየ መስነፍ የለብህም፤ ማመንታት የት ላያደርስህ? ተነስና ዋጋ ክፈል! ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለምትወዳቸውና ለብዙዎች የምትደርስ አስፈላጊ ሰው ነህ! ዳይ ወደ ተግባር!

ውብ ምሸት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

🤝"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር "

እንደሚባለው ከእኛ ስራ እና ጥረት በበለጠ የእናንተ ገንቢ አስተያየት ለእኛ መበርታትና የተሻለ መስራት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው እናም ስለሰጣችውን ገንቢ አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን እያንዳንዱን ሀሳብ አንብበነዋል በቀጣይ ስልጠና ላይ በደንብ አካትተን እንደምንሰራበት ቃል እንገባለን ! ሁሌም የእናንተው ምርጥ ጓደኛ በመሆን ምርጥ ሀሳባችውን እየተቀበልን ምርጥ ማንነታችውን እስከመጨረሻው አብረን እናወጣለን !

ቀጣይ ስልጠናችን የሚጀምርበትን ቀን በቅርብ ቀን እናሳውቃለን!

ደማቅ የሆነ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

✅ Uሳብ ስጡን ?

በቅድሚያ መርጣችሁ የዚህ ትልቅ ቤተሰብ አባል ስለሆናችሁ ከልብ እናመሠግናለን 🙏

ኢንስፓየር ኢትዮጵያ 'ሀ' ብሎ ከተጀመረ ሶስት ዓመት እንኳን በቅጡ አይሞላውም ፤ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ግን ከፍተኛ ተቀባይነትን አትርፏል ለዚህ ደግሞ ከፈጣሪ ቀጥሎ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው በተለያየ መልኩ ከእናንተው ከቤተሰቦቻችን የሚሰጡንን አስተያየቶች መቀበላችን እና ወደ ተግባር መለወጣችን ነው ።

ታዲያ የተለመደው ትብብራችሁን የፈለግነው ከጥቂት ቀናቶች በኋላ 17ተኛው ዙር የኦንላይን ስልጠናችን ይጀምራል ስለሆነም በስልጠናው መነካት ይገባዋል የምትሉትን ማንኛውንም ሀሳብ እና እንዲመለስ የምትፈልጉትን ጥያቄዎች ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ?

በተጨማሪም ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

☎️ +251944314544

@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የምትመጥን ሁን !

አንዳንዴ የጎደልን ይመስለን እና እራሳችንን በቁስ ልንሞላው እንነሳለን ፤ ጥሩ ኑሮ መኖር ጥሩ ቤት መኖር ቆንጆ መኪና መንዳት ጥሩ ልብስ መልበስ ብዙ ንብረት ማፍራት በጣም ጥሩ ነው ያስፈልገናል ከጣርን ደግሞ ይገባናልም ነገር ግን ከእነርሱ የሚቀድመው ሙሉ ሰው መሆን ነው ውስጥን ሙሉ ማድረግ ራስን ለሚኖረን ትልቅ ሀብት የምንሆን ሰው አድርጎ ማዘጋጀት የምንይዘው ሀብት እና ዝና ልካችን እንዲሆን ስብዕናችን በደንብ ሊገነባ ይገባል በደንብ ልንሞረድ በደንብ ልንሳል ይገባል ! እንዴት ካልን :- እናንብብ , ያወቅነውን ለመኖር እንጣር ከእኛ ከተሻሉ ጥሩ አስተሳሰብ ካላቸው ጋር አብረን እንዋል ከእነርሱም ብዙ እንማር ከሀይማኖት ቦታዎቻችን ጥሩ እውቀት ሊመግቡን ከሚችሉ ተቋማት እንማር ያኔ ውስጣችን በደንብ ስለሚሞላ ውጪው ይትረፈረፋል !

መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስተኛ መሆን!

ደስተኛ የመሆን ትልቁ ሚስጥር ገና የሚመጣውን ማሰብ ብቻ አይደለም፤ ወደ ህይወታችን የመጣውንም ማሰብ ነው። ወደ ህይወታችን ከመጣው ምርጥ ስጦታ አንዱ የዛሬው ቀን ነው።

የዛሬዋን ቀን ከዚህ በፊት ቀድሞ ያየው አለ? የለም! አዲስ ስጦታ ነው። ለሀብታሙም ለደሀውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ ለሴቱም ለወንዱም ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ስጦታ! እየተነፈስክ ተደሰትና ፈጣሪህን አመስግን ወዳጄ።

የደስታ ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የዘራኸውን ታጭዳለህ!

አይምሮህ ውስጥ ምንድነው የምትዘራው? መልካም ሀሳብ ወይ መጥፎ ሀሳብ? አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ፤ የዘራኸውን ታጭዳለህ! ደጋግመህ ያሰብከው ሀሳብ በህይወትህ ውስጥ በተግባር ይገለጣል።

ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ብቻ ዋል፤ በጎ ነገር ብቻ ስማ፤ ብቻህን ስትሆን ራስህን አድንቅ፤ እንደምትችል ለራስህ ንገረው፤ አየህ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባው እንደዚህ ነው።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተረስተህ አይደለም !

የምትፈልገው ነገር አልሆን ሲልህ ሲዘገይብህ ፈጣሪ ረስቶኝ እኮ ነው አትበል ፤ በደንብ ጮክ ብለህ ጥራው በአፍህ ሳይሆን በምግባርህ ጥራው ! በቃላትህ ሳይሆን በምትሰራው መልካም ስራ ጥራው ! ፈጣሪ በፍፁም አይረሳም ነገር ግን የራሱ ግዜ አለው መቼ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል ስለዚህ ሁሌም ወደራስህ ተመልከት የሚገባህ ሰው ለመሆን ጣር ምግባርህን አርቅ እርሱም ያይሃል ሲገባህ ይሰጥሃል !

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምን አይነት ዕድለኛ ነህ?!

እሳትን የሚያበርደው ውሀ ነው፣ አልጫን የሚያጣፍጠው ጨው ነው፣ ያንተን ህይወት ጣዕም የሚሰጠው ፈጣሪ ነው። ደስታን ለማግኘት ማንኛውንም ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ፤ ብዙ ነገር አሳክተው ደስታን የጨበጡ የመሰላቸው ሰዎች ዘግይተውም ቢሆን ንፋስ እንደዘገኑ አውቀዋል።

እውነተኛ ደስታ ከፈለክ ፈጣሪ እስከዛሬ ባደረገልህ፣ አሁን ባለህ ነገር አመስግን፤ "ምን አይነት ዕድለኛ ነኝ?" በል፤ ገና በሚመጣው ሳይሆን አሁን ህይወትህ ላይ ያለውን እይና ተደሰት! አበቃ!

የሚያምር ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መፍራት የለም!

ከባድ ጊዜያት በፍጥነት የሚቀይሩህን ያህል ምንም ነገር አይቀይርህም፤ ከምቾትህ ወጥተህ አዲስ ነገር ስትሞክር የተሻለ ነገር ወደ ህይወትህ ይመጣል።

የምትፈራው ወይ የምታመነታው እስክትጀምር ነው፤ ከጀመርክ በኋላ ግን ወደኋላ አትይ። በምታምንበት ጉዳይ ጨክኖ ራስን መለወጥ ህመም አለው ውጤቱ ግን አንጀት ያርሳል! ዳይ መፍራት የለም ወዳጄ!

የለውጥ ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁለት ሰዎች!

ውስጡ ሰላም የሌለው ሰው ትንሿ ነገር ታስከፋዋለች፤ የሰማውን ያየውን በራሱ መንገድ ተርጉሞ ሲናደድ ያድራል።

መንፈሱ የሰከነ ሰው ግን የሰዎች መጥፎ ድርጊት ሁሉ ማንነታቸውን ሳይሆን የደረሰባቸውን የውስጥ ስብራት እንደሚያሳይ ስለሚረዳ ያዝንላቸዋል፤ ወዳጄ ለነገሮች የምትሰጠው ትርጉም ህይወትህን ይወስነዋል።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የማይለወጥ ነገር የለም!

ትልቁ ነጥብ ስህተት መስራትህ አይደለም ማስተካከልህ ነው፤ ችግሩ መውደቅህ አይደለም ግን መልሰህ ካልተነሳህ ነው፤ ልብስም እኮ ይቆሽሻል ግን አጥበህ መልሰህ ትለብሰዋለህ።

አንተም ስትሳሳት ራስህ ላይ አትጨክንበት፤ ያጠፋ ሰው አንዴ ነው የሚቀጣው፤ በየቀኑ "እኔኮ አልረባም" እያልክ ራስህን አትውቀሰው! ልብሱ ከታጠበ አንተ የማትለወጥበት ምክንያት የለም!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስልጠና በነፃ

ሰላም ለእናንተ ቤተሰቦች 🙌 ዛሬ ማታ እንገናኝ !

ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

☎️ +251944314544

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከራሳችን አንደበቅ!

አንዳንዴ ራሳችንን ማየት ያስፈራናል ፤ ቁጭ ብለን ከራሳችን ጋር መወያየት ምን እያደረግሁ ነው ምንስ ማድረግ አለብኝ ብለን መጠየቅ እንፈራለን ስለዚህ ከሰዎች ጋር ፣ ከሶሻል ሚዲያ ፣ ከቴሌቪዥን ከመሳሰሉት ጋር ያለንን ግንኙነት በጣም ጥብቅ እናደርገው እና ግዜያችንን በሙሉ እነሱ ላይ እናጠፋለን ከውስጣችን ጩኸት ለመደበቅ የውጬውን ጩኸት ከፍ እናደርገውዋለን ግን እስከመቼ ራስን ማታለል ይቻላል? እስከመቼ ከራስ ተደብቆ መኖር ይቻላል እስከመቼስ የምንፈልገውን ውጤት ሳናገኝ በመኖር እንደሰታለን? ስለዚህ ሁልግዜም ቢሆን ቀን እየተደበቀ ማታ ከሚረብሽ ሀሳብ ለመላቀቅ ራሳችንን አድምጠን መልስ እንስጠው!

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ጊዜው መሄዱ አይቀርም!

በዚህ አለም ትልቁ ሽልማት ይሄ ቅፅበት ነው፤ ይቺ ቅፅበት ካለፈች አለፈች ነው፤ ማንም አይመልሳትም። የማይጠቅምህን ወሬ ስትሰማ ወይ ተራ ቪዲዮ ስታይ ከእድሜህ ላይ 10 ደቂቃም ቢሆን ቀንሰህ እየሰጠሀቸው መሆኑን አስታውስ።

እድሜህን እንዴት በነፃ ትሰጣለህ?! የምናደንቃቸው ታላላቅ ሰዎች ከፍታው ላይ የወጡት ዕድሜያቸውን ለሚጠቅማቸው ነገር ሰጥተው ነው። አንተ ብታነብ ባታነብ ጊዜው መሄዱ አይቀር፤ ብትሰራ ስራ ብትፈታ አመቱ ማለፉ አይቀር፤ ብትማር ባትማር ደቂቃው መክነፉ አይቀር፤ ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ! ነገ የተሻለ ቦታ ለሚያደርስህ ነገር ቅድሚያ ስጥ!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ለእናንተ 🙌 የኢንስፓየር ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ስለስልጠናው ለሰጣችሁን ሀሳብ እና አስተያየት ከልብ እያመሰገንን🙏

የሰጣችሁንን ሀሳብና እና አስተያየቶች አካተን 17ተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ ተጀምሯል ‼️

🔑 ስልጠናው የተዘጋጀው

► ለትልቅ ነገር እንደተፈጠረኩ አስባለው ነገር ግን ያንን ለማሳካት  ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማወቅ አልቻልኩም ?

► አሁን አየኖርኩ ያለሁት ህይወት እና የምመኘው ህይወት በፍጹም ሊገናኝልን አልቻለም ?

► በጣም ጠንካራ ፣ በራስ መተማመን ያለኝ ሰው ነበርኩ ብዙ ነገርም በህይወቴ ቀይሬያለው ከራሴ አልፌ ለሰዎችም ተርፌያለው ምን ያረጋል ነበርኩ
ሆኜ ቀረው አሁን እንዴት ወደራሴ ልመለስ ?

► ሁሌም ራሴን ለመቀየር ወስኜ ወደተግባር እኮ እገባለው ምን እንደሆነ ግን አላውቅም ወደኋላ
ይጎትተኛል በሞራል የጀመርኩትን ነገር ተሰላችቼ አቆማለው ?

► ሁሌም በአዕምሮዬ እየተመላለሰ የሚበጠብጠኝ አንድ ነገር አለ እሱን መርሳት እፈልጋለሁ ?

► በህይወቴ ብዙ የማመሰግንበት ነገር አለ ፤ አማራሪ አይደለውም ነገር ግን ሁሌ ሰላም የሚነሳኝ አንድ ነገር አለ ( የፍቅር ግንኙነቴ ፣ የገንዘብ አያያዜ ፣ መጥፎ ልማዴ ) ምን ላድርግ ?

ለምትሉ ሁሉ ጥያቄያችሁን ለመመለስ ነው❗️

ስልጠናው የሚሰጠው በኦንላይን ( ZOOM App )📍ባሉበት ቦታ ነው

17ተኛ ዙር የግሩኘ ስልጠናችን ሁለት አማራጮችን ይዟል

🔹 የመጀመሪያው 🔷

👉ስልጠናው ለ 1 ወር ከ15 ቀን ይቆያል የሚሰጠው ረቡዕ እና ቅዳሜ ማታ ከ 3:00 - 5:00 ሰዓት (በኢትዮጺያ ሰዓት አቆጣጠር)

ለስልጠናው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች "በሶፍት ኮፒ" ወይም በስልክ ይደርሶታል !

📍አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ ሰዎች ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያሉበት በ"ሀርድ ኮፒ" እናደርሳለን ! በነፃ

ምንም እንኳን ስልጠናውን ተገኝቶ መካፈል ወሳኝ ቢሆንም በተለያዩ አጋጣሚዎች በስልጠናው ሰዓት ባይገኙ የድምፅ ቅጂ ይደርሶታል !

ለሰልጣኞች ብቻ የሚከፈት የቴሌግራም ግሩፕ አባል በመሆን ከተለያየ የአለም ክፍል የሚሳተፉ ሰዎች ጋር ሀሳብ መለዋወጥ ይችላሉ !

ስልጠናው ሲያልቅ ቀድመው ስልጠናውን ከጨረሱ የኢንስፓየር ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጋር በመቀላቀል የተለያዩ ልምዶችን በየሳምንቱ ያገኛሉ !

🔸 ( 2ተኛ ) በብዙዎች ተመራጭ 🔸

👉ስልጠናው ለ 1 ወር ከ15 ቀን  ይቆያል የሚሰጠው ረቡዕ እና ቅዳሜ ማታ ከ 3:00 - 5:00 ሰዓት (በኢትዮጺያ ሰዓት አቆጣጠር)

ለስልጠናው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች "በሶፍት ኮፒ" ወይም በስልክ ይደርሶታል !

ምንም እንኳን ስልጠናውን ተገኝቶ መካፈል ወሳኝ ቢሆንም በተለያዩ አጋጣሚዎች በስልጠናው ሰዓት ባይገኙ የድምፅ ቅጂ ይደርሶታል !

ለሰልጣኞች ብቻ የሚከፈት የቴሌግራም ግሩፕ አባል በመሆን ከተለያየ የአለም ክፍል የሚሳተፉ ሰዎች ጋር ሀሳብ መለዋወጥ ይችላሉ !

ስልጠናው ሲያልቅ ቀድመው ስልጠናውን ከጨረሱ የኢንስፓየር ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጋር በመቀላቀል የተለያዩ ስልጠናዎችን በየሳምንቱ ያገኛሉ !

በተጨማሪ :

ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያሉበት ሀገር በ"ሀርድ ኮፒ" እናደርሳለን !

ከመደበኛው ስልጠና ሰዓት በተጨማሪ (ከ5:00 - 6:00 ሰዓት) ሁሌም የተለያዩ የግል ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ እና ተጨማሪ ስልጠናዎችን ያገኛሉ !

ከስልጠናው በኋላ ለ 1 ዓመት ያክል በወር 1 ቀን ተጨማሪ ስልጠና እና ክትትል ያገኛሉ !

ለ2ተኛ ደረጃ ተመዝጋቢዎች ብቻ የሚከፈት የቴሌግራም ግሩኘ ተሳታፊ ይሆናሉ !

ስልጠናው ላይ ለመሳተፍ 📲 +251944314544 ይደውሉ ወይም በቴሌግራምና ዋትስአኘ መልዕክት ይላኩ

🔹ሶስተኛ አማራጭ የግል ስልጠና የምትፈልጉ ከላይ ባለው ስልክ ደውላችሁ መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉንም ታልፋለህ!

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን አስብ!

መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!

ማራኪ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስ የሚል በቀል!

እልህ ይዞህ ያውቃል? የሚንቁህና የበታችነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሰዎች ህይወትህን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልግ ንብረት ለማውደም ትጠቀምበታለህ ስትፈልግ ደግሞ ምግብ ታበስልበታለህ፤ ታዲያ ለናቁህ ሰዎች ማንነትህን ለማሳየት ጠንክረህ ሰርተህ ራስህን ለውጠህ በስኬትህ የያዘህን እልህ ለምን አትወጣም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁህ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው!

አሰደሳች ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዛሬ ያንተ ነው!

"ይሄ ቀን ለኔ ነው" በል! እንዴ ላንተ ባይሆንማ ጠዋት ወጥተህ ማታ በሰላም አትመለስም ነበር፤ ስንቶች በወጡበት ቀሩ? ስንቶች በተኙበት ሞተው አደሩ? ከዛሬ እንዲያልፉ አልተፈቀደማ! እኛ ግን ተፈቅዶልናል፤ የነገን እርግጠኛ መሆን ባንችልም ዛሬ ግን የኛ ነው!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ልዩ ቪዲዮ ይዘን መጥተናል !

ብዙ ጊዜ የአንድን ቤተሰብ ህይወት የሚቀይረው አንድ ሰው ነው ፤ ታዲያ ያ ታሪክ ቀያሪው ሰው አንተ ብትሆንስ ?

ቪዲዮውን በ ኢንስፖየር ኢትዮጵያ ዩቲዩብ ቻናል ከአሁን ጀምሮ ያገኙታል !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ባለህ ነገር መደሰትን ልመድ !

ስታማርር ያለህን በአግባቡ ሳታጣጥም ስትቀር ነገ ሌላ አዲስ የምታማርርበት ግዜ ይዞልህ ይመጣል የባስ የምትከፋበት የምታዝንበት ነገር ያመጣብሀል ትላንት ለካ ሁሉ ነገሬ ውብ ነበር ምነው በአግባቡ ብደሰትበት ምነው በጥሩ ባሳለፍኩት ኖሮ የሚያስብል ግዜ ይወጣል ስለዚህ ዛሬህን በደንብ ኑር ባለህ እየተደሰትህ የሚያስፈልግህን ጨምር ስታመሰግን ባለህ ደስታ ላይ ይበልጥ ትጨምርበታለህ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ነገሮችን በቀና እይ !

ከምንም ነገር በላይ ሰው ላይ አትክፋ መልካም ሁን ሲያሸንፉ ስታይ አይንህ ደም አይልበስ ተደሰት ጠይቃቸው እንዴት አድርጋችው አሳካችውት በላቸው እንጂ ፈጣሪ ለእነርሱ አደላ አትበል ሌሎች ቀድመው ማሸነፍ ስለቻሉ አንተ ወድቀህ የቀረህ አይምሰልህ ከቀደሙህ ተምረህ የባሰ ከፍ እንድትል ነው ከእነርሱ ኋላ ያለኸው ስለዚህ ወዳጄ የሰዎችን ስኬት ከማኮሰስ እና በመቀደምህ ከማዘን እንኳን ተሳካላቸው እኔስ ከእነርሱ ምን ልማር በል!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስታችን በእጃችን ነው !

በህይወትህ በጣም ደስተኛ መሆን ከፈለግህ ደስተኛ የምትሆንበትን መንገድ ከሌሎች አትጠይቅ ወይም ሌሎች ሰዎች ይሄንን ስታደርግ ነው ደስተኛ የምትሆነው በሚሉህ ልክ ደስታህን አትለካው ! ደስታ መጠጣት፣ መጨፈር የመሳሰሉትን ማድረግ ማለት አይደለም ! መፅሀፍት ማንበብ ፣ ለብቻ ግዜ ማሳለፍ የራሳችን ነገር መፍጠር የምንወደውን ስራ መስራት ደስተኛ ሊያደርገን ይችላል ደስታችን ያለው በእጃችን ነው ! ራሳችን ደስታችንን መፍጠር እንደምንችል እንወቅ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel