የሚጠብቀን አይተኛም !
ሁላችንም የፈጠረን ፈጣሪ እጅ ላይ ነን በራሳችን የቆምን አደለንም የምድር ባለቤት የሁላችን ፈጣሪ ሁሌም እኛን ለመጠበቅ አይተኛም አያንቀላፋም ስለዚህ ምንድነው ታድያ የሚያስፈራን ?
ቤታችንን ከሌባ ለመጠበቅ ዘበኛ ወይም አደገኛ አጥር ወይ ደግሞ ውሻ አስቀምጠን ነፃ ሆነን ያለስጋት እንተኛ የለ ታድያ ከሁሉ በላይ ሁሉን የፈጠረ ፈጣሪ እየጠበቀን ካለ ምንም ነገር ሊያሸንፈን እንዴት ይቻለዋል ?
የተባረከ ቀን ተመኘኝ 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለትርፍ ድከም !
ይደክማል አይደል? የምትፈልገው ቦታ ሩቅ ሲሆን ያን ሁሉ መንገድ መጓዝ ይደክማል መሀል ላይ ስትደርስ አቁም አቁም በቃህ ይልሀል አይደል ግን ደግሞ አስበኸዋል ሲበቃህ ስትቆም ልትመለስ ስታቅድ ያን ሁሉ ደክመህ ደክመህ ልፋትሀሰ ያለምንም ውጤት ባዶ ሲቀር ? ደ
ግሞ
ይበልጥ የሚያሳዝነው የመጣህበትን መንገድ ድጋሚ ስትመለስ የምትለፋው ልፋት መልሶ ያው መሆኑ ነው ለህልምህ ብትደክም እኮ ለውጤት ነው ለመመለስ ግን መድከም ትርፉ ኪሳራ ነው !
መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለመጠየቅ አትፍራ !
አስቀይመናቸው ይቅርታ ልንጠይቃቸው የሚገቡ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ ነገር ግን ምላሻቸውን በመፍራት ይሁን ወይ ኩራት ይዞን ለመጠየቅ ወደኋላ እንላለን ነገር ግን ልባችን ላይ ይዘነው የምንዞረው ፀፀት ከብዙ ነገር ወደኋላ እንድንቀር ያደርገናል!
ለምትወዳትም ሴት ፍቅርህን በመግለፅህ እንደምታጣት አስበህ ዝምታህን በመምረጥህ ምክንያት ስታጣት ምነው በነገርኳት ኖሮ ብለህ መፀፀትህ አሁንም ይመጣል ስለዚህ ልብህ ውስጥ አፍነህ ራስህን ከምታስጨንቅ የመጣው ይምጣ ብለህ መጠየቅ ያለብህን ጠይቅ!
የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ለማወቅ አንስነፍ !
አንዳንዴ ልክ ነን ብለን እናውቃለን ብለን ያሰብናቸው ነገሮች ፈፅሞ ያላወቅናቸው ገና ብዙ የሚቀሩን እና ልንሰራባቸው የሚገቡ ነገሮች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ ስለዚህ ሁሌም ለመማር ለማወቅ ራሳችንን ክፍት አድርገን አንጠብቅ እውቀት ጥግ የለውም !
ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሁሉ መልካም ይሆናል !
ነገሮች ከብደውሀል? ያለህበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም ? ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ነው መውጣት የምችለው ምን ውስጥ ነው የገባውት እያልሽ ነው ? አንድ ነገር ልንገርሽማ ፈጣሪ ሁሌም ቢሆን ከጎንሽ ነው ሁሌም ቢሆን አንቺን ከመጠበቅ ወደኋላ አይልም የጌዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ሁሉም አልፎ ቁጭ ብለህ ትስቅበታለህ !
መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
የሚጠበቅብህን አድርግ!
ፈጣሪን ባርክልኝ ስንለው ምን ይዘን ነው ? ምንም የሌለው ሰው ምን ይባረክለታል? አንድ የያዘ ሁለት ይሆንለታል ሁለት ያለው አራት ይደረግለታል አስር ያለው መቶ ይሆንለታል ለማስባረክም መያዝ አለበት ! ተቀመጠን ብቻ ፈጣሪን አንጠብቀው !
የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
መለወጥ አለብህ!
ስኬትና የህይወት እርካታ ዋጋ ያስከፍላሉ፤ በነፃ አይገኙም። አንተ ደግሞ እንኳን ለሚጠቅምህ ለማይጠቅምህም ነገር ዋጋ ከፍለህ ታውቃለህ፤ አሁን ሰዓቱ ራስህን እስከ መጨረሻው ስለ መቀየር የምናወራበት ነው!
ከማይጠቅሙህ ሰዎች ጋር መሆን የምታቆመው መቼ ነው? ጊዜህን በዋዛ ፈዛዛ የሚያባክኑ ነገሮችን ከህይወትህ ቆርጠህ የምታወጣው መቼ ነው? እውነተኛ ለውጥ የምታየው ለራስህና ለጊዜህ ቦታ መስጠት ስትጀምር ነው!
ታሪካዊ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ከሰው መጠበቅ አቁም!
ልብህን የሚሰብረው ከሰዎች ብዙ መጠበቅ ነው፤ ስለዚህ ከሰዎች ብዙ አጠብቅ። እህቴ የሚከፋሽ ሌሎች የሚያደርጉልሽን ጠብቀሽ ስላላገኘሽ ነው።
ከሰው መጠበቁን አቁመን ደስታችንን ከፈጣሪና ከራሳችን ልብ ውስጥ ማግኘት ነው ያለብን፤ ያኔ አንዱን ቀን ደስ ብሎን ሌላኛውን ቀን አይከፋንም ምክንያቱም ደስታችን ሌሎች ላይ ጥገኛ አይደለም።
ሰላማዊ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ተስፋ መቁረጥ የለም!
ወዳጄ ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው።
ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ 'አንተ ስትጨርስ እሱ ይጀምራል!' ተስፋ መቁረጥ የለም ወዳጄ!
የሚገርም የኢድ በዓል ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ተመስገን!
"በዚህ አለም ከባዱ ነገር የሚወዱትን ማጣት ነው እጅግ ከባዱ ነገር ግን የሚወዱትን አግኝቶ ማጣት ነው" ይለናል ጆርጅ በርናርድ ሾው የተባለ ደራሲ።
አንዳንድ ነገሮች እንደነበሩህ ራሱ የምታውቀው ስታጣቸው ነው፤ ወዳጄ አሁን እጅህ ላይ ያለውን መልካም ነገር ሁሉ ተመልከትና ተመስገን በል! የጎደለህን አብዝተህ የምታስብ ከሆነ ግን ሌላ ጎዶሎ ነው የሚጨመርልህ!
የምስጋና ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
የምትወደውን አትልቀቅ !
የምንፈልጋቸው ልንይዛቸው የምንሞክራቸው ነገሮች ፈተና ሊያበዙብን ይችላሉ ፤ ከምንግዜውም በላይ ትግል ሊያበዙብን ሊያደክሙን ይችላሉ ነገር ግን መጨረሻ ስንይዛቸው ያለው እረፍት ከየትም ልናገኘው የማንችለው ነው!
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ከጎናችን ያለውን አንርሳ !
አብዛኛውን ግዜ ከእኛ ራቅ ላለ በድንገት ወይም በቅርብ ግዜያት ላገኘነው ወይንም ህይወታችን ላይ ያን ያህል ድርሻ ለሌለው ሰው በይሉኝታም ይሁን በተለያዩ ምክንያቶች ብዙ ነገር እናደርጋለን አጠገባችን ሆኖ ለእኛ እየደከመ ለእኛ እየለፋ በየትኛውም ሁኔታ አብሮን ላለ የቅርብ ሰው ግን ቦታ አንሰጥም የት ይሄዳል በሚመስል ሀሳብ ጣል ጣል እናደርገዋለን በወደቅን ሰዓት ግን ከጎናችን የሚገኝልን ለእኛ ከልቡ የሚያስብልን ነው እና የሚገባውን ክብር እና ቦታ ለሚገባው ሰው መስጠታችንን እናስተውል!
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ከጥቂቶቹ አንዱ እንሁን!
ትልቁን ቦታ ሁሉም ይፈልገዋል ጥቂቶች ብቻ ያገኙታል ! ለምን? ምክንያቱም ቦታውን ለማግኘት የሚገባውን ልፉት የሚለፉት ጥቂቶቹ ብቻ ስለሆኑ ነው ሌሎቹ ብዙዎቹ በሀሳባቸው ስላለሙት ብቻ እንደሚገባቸው በማሰብ ራሳቸውን ሲያታልሉ ይኖራሉ !
"የሚሰራ ሰው ይገባኛል ብሎ አያወራም እንደሚገባው ቦታው ላይ ቁጭ ብሎ ነው የሚያሳየው !"
የተቀደሰ ሀሙስ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
መነቀፍ አይግረምህ !
ሰዎች አስተያየት መስጠታቸውን አያቆሙም ፣ ልክ ስላልሆንክ መታረም ስላለብህ ብቻ ሳይሆን ለእነርሱ ምቹ ስላልሆንክም ነው ለምን የሚሉህ ! ስለዚህ መገረም አቁም ለምን እንደዚህ አሉኝ አልረባም ልክ አልሰራውም ማለት ነው ብለህ አትጨነቅ ፈጣሪህን እያመንክ መንገድህን ቀጥል ! የሚጠቅምህን ግን አገናዝበህ ውሰድ !
ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
የጊዜ ጉዳይ ነው!
አንተ ነገህን መወሰን አትችልም፤ አንተ የምትችለው ደጋግመህ የምታደርገውን ልማድ መወሰን ነው፤ ከዛ ያ ልማድህ ግን ነገህን መወሰን ይችላል! የጊዜ ጉዳይ ነው ምርጥ ልማድ ካለህ ምርጥ ቦታ ያደርስሀል!
ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ራስህን እመነው!
ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ። የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው።
ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!
አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia✊
የእናንተ ምርጥ ጓደኛ!
ሳይንስ እና ፈጣሪ
ሳይንሱ "ሰው ደጋግሞ ያሰበው ሀሳብ ህይወቱ ላይ ይገለጣል" ይላል። ይሄንን ብናውቅም ብዙ መጥፎ ሀሳቦችን ደጋግመን እናስባለን ግን አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን ከሀሳብ በዘለለ እውነት ሆነው አያውቁም። ያሰብናቸው ጥቂት መልካም ሀሳቦች ግን ተሳክተው አይተናል።
አየህ ፈጣሪ ከሳይንስ በላይ ነው፤ ደጋግመህ ያሰብከውን ብዙ ክፉ ነገሮች ሁሉ አስቀርቶ ትንሿን በጎ ሀሳብህን እውነት ያደርጋል። ሀያሉ አብሮህ ከሆነ አንዲት 'ተመስገን' የምትል የምስጋና ጠጠር ሚሊየን ግዙፍ ጭንቀቶችህን አመድ ታደርገለች። ወዳጄ አትጨነቅ አልልህም ግን አመስግን!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ሁሉንም መቀየር!
ትላንት ላይመለስ አልፏል ራስህን መውቀስ አቁም! አሁንን መኖር ጀምር፤ ዛሬ ቆራጥ ከሆንክ ሁሉንም መቀየር፣ ሁሉንም እንደ አዲስ መጀመር፣ ያበላሸኸውን ማስተካከል ትችላለህ። ወዳጄ እድልህን ተጠቀምበት ይሄንን ቀን ያላዩ ብዙዎች አሉ።
ታላቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
በፍፁም አናቆምም!
ጥረትህን አይቶ ማንም አይገረምም፤ ውጤትህ አሪፍ ከሆነ ሰዎች ያደንቁሀል ካልሆነ ግን ይንቁሀል፤ አየህ ይቺ አለም ውጤትን እንጂ ጥረትን አትሸልምም።
ካቆምክ መውደቅህን አረጋግጠሀል፤ ከቀጠልክ ለማሸነፍ እየተቃረብክ ነው፤ እርግጠኛ የምሆንልህ ግን የሚፈልጉትን ሁሉ የሚያገኙ ሰዎች በሙሉ ጥረታቸውን ያላቆሙት ናቸው! ስለዚህ አናቆምም!💪
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
አታመንታ!
ቁጭ ብለህ እንዲህ ባደርግ እንዲህ ቢሆን አትበል! አድርገው! ወደ ተግባር ግባ! ወዳጄ ባህሩ ላይ ማፍጠጥ አያሻግርህም ተነስተህ ጀልባውን መቅዘፍ አለብህ።
ከአልጋህ ተነስ፣ ስፖርቱን ስራ፣ መፅሀፉን አንብብ፣ በጊዜህ ወደ ስራህ ግባ ፤ ወዳጄ የተግባር ሰው ካልሆንክ በሀሳብ መንሳፈፍ ነው ስራህ! ዳይ ተነስ!
ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ተቀይረህ አሳያቸው!
ህይወትና ኑሮ ቀላል እንዲሆን አትመኝ አንተ መክበድ አለብህ፤ ሰዎች ለምን አልተረዱኝም ብለህ አትዘን በተግባር ተለውጠህ አሳያቸው! አለም ለጠንካሮች በጣም ታዳላለች፤ ሰዎችም ቢሆኑ ደካማ አይወዱም፤ ፈጣሪ ብቻ ነው እንዲሁ የሚወድህ።
ከሁሉ በላይ ግን ለራስህ ስትል ቆራጥ መሆን አለብህ! ምክንያቱም በምንም ነገር ውስጥ ብታልፍ ጥሎ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ወርቅ ማንነት ስላለህ። ወርቅ ጭቃ ውስጥ ቢወድቅ እንኳን ውድ ነው፤ ወዳጄ አንተ ደግሞ ከዛ በላይ ውድ ነህ!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ግዜያችንን አናባክነው !
የተገደበ ግዜ ነው ያለን ስለዚህ ግዜያችንን ያለ አግባብ ከማባከን እንቆጠብ ፤ አንዳንዴ ህጎችን እንጣስ ማህበረሰባችን የጫነብንን እኛ ግን ልክ አይደለም ብለን በምክንያት ያላመንበትን ነገር እንቀይረው ሰዎች ያለችንን ግዜ እንዲወስዱብን አንፍቀድላቸው ያ ማለት ከመስመር እንውጣ ነገሮችን ወደ ማይሆን አቅጣጫ እንውሰድ ሳይሆን ያመንበትን ከማድረግ ግን እንዳንቆም !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
አበቃልኝ አትበል !
በዚህ ደስ የሚል የሚያምር ጠዋት ነቅተሀል ፤ ማታ ስትተኛ ዛሬ እንደምትነቃ ማረጋገጫ አልነበረህም ነገር ግን ተስፋ ነበረህ ነገ ይሄን አደርጋለው ብለህ ያቀድኸው ነገር ነበር ! እናም ነቅተህ የማድረግ እድል ገጥሞሀል ስለዚህ ዛሬ ያነቃህ ዛሬ እድል የሰጠህ ፈጣሪ አብሮህ ነበር አሁንም አብሮህ አለ ከዚህም በኋላ አብሮህ ነው እስካለህ ድረስ እስከጠየቅኸው ድረስ እስከለፋህ ድረስ መቼም አይተውክም !
የተባረከ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ጥሩ ጎናቸውን አሳያቸው !
ሰዎችን ከልብህ ማቅረብ ከፈለግህ ብዙ ወቀሳ አታብዛባቸው ! ሁሉም ሰው የራሱ ጥያቄ አለው ራሱን በብዙ መንገድ ይወቅሳል ስለዚህ የሚያበረታው የሚደግፈው ይፈልጋል እንጂ በቁስሉ ላይ ይባስ የሚጨምርለት አይሻም !
መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሰላም ቤተሰቦች፤ አንድ ወንድማችን በሰው ሀገር ላይ ከባድ ችግር ላይ ነው፤ እባካቹ የዚህን ልጅ ህይወት እንታደግ፤ አቅም ኖሮን መርዳት ባንችል እንኳን ሼር በማድረግ እንተባበር።
ከ 10 ብር ጀምሮ ያለንን ለመስጠት ለምንፈልግ
- የንግድ ባንክ 1000183128098
- አቢሲኒያ ባንክ 14543384
🔵 በስልክ ቁጥር ደውለው ማነጋገር ይችላሉ
📞 +251988120258
ፍቃዱ ሰለሞን
📞 +251910474176
እዮል ዩሀንስ
📞+251940088059
ምንተስኖት አስመሸ
ለምታረጉልን ትብብር በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን🙏
https://gofund.me/3d06f4e8
ታገስ!
አውሮፕላን ውስጥ ሆነህ አንድ የሚያበሳጭ ነገር ቢገጥምህ "ወራጅ አለ!" አትልም እኮ ብስጭትህን ዋጥ አርገህ መሬት እስክታርፍ ትታገሳለህ። አሁን የሚገጥሙህን ፈታኝ ነገሮች በትዕግስት ማሳለፍ ከቻልክ የጊዜ ሚዛን ላንተ ማዳላቱ አይቀርም፤ ታገስ ወዳጄ!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
በደስታ ለመቀበል ተዘጋጅ!
የተሻለ ነገር እንዲሰጥህ ጠየክ አይደል? ታዲያ ለምንድነው አንዳንድ አላስፈላጊ ነገሮች ከህይወትህ ሲቀነሱ የምትደነግጠው? ለውጥ እኮ ህመም አለው፤ ወዳጄ አዲስ ነገር በህይወትህ ሊፈጠር ስለሆነ በደስታ ለመቀበል ተዘጋጅ!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ራስህን አትውቀስ!
በየትኛውም ወቅት በፍፁም ራስህን አትውቀስ ምክንያቱም
👉 ጥሩ ቀናት ደስታ ይሰጡሀል፤
👉 መጥፎ ቀናት ልምድ ይሰጡሀል፤
👉 በጣም ከባድ ጊዜያት የህይወት ትምህርት ያስተምሩሀል
👉 በጣም ምርጥ ጊዜያት ልዩ ትዝታ ይሆኑሀል
ዋናው ከትናንት የተሻለ አመለካከት እና ብስለት ይኑርህ እንጂ የምትፈልገው ሁሉ ቀስ እያለ እጅህ ይገባል፤ እጅ መስጠት የለም ወዳጄ!
ተዓምረኛ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ትንሽ ፈገግታ !
መልካም ስትሆን ለሰዎች ምን እየሰጠኃቸው አንዳለህ አታውቅም ፈገግ ብለህ በማየትህ ብቻ ትልቅ ተስፋ የሰጠኃቸው ብዙዎች አንዳሉ ገምተህስ ታውቃለህ? ስለዚህ ወዳጄ ምንም ማድረግ ባትችል እንኳን ከልብህ ፈገግ ብለህ ለሰዎች ሰው እንዳላቸው እንዲሰማቸው አድርግ ውጤቱ ብዙ ነዉ!
ደስ የሚል ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
አትጨነቁ!
"ተጨንቆ ከቁመቱ ላይ አንድ ክንድ የጨመረ የለም" ብዙ እናስባለን እንጨነቃለን እንመኛለን እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ እንላለን ከሁሉም የሚሻለው የቻልነውን መሞከር ከዛም የቀረውን ውጤት ለፈጣሪ ሰጥቶ ሲያመሰግኑ መኖር ነው!
የተቀደሰ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊