inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ተሳክቷል !

ተሳክቷል ብቻ ዝም ብለህ አመስግን ! አሁን ያለሽበት ሁኔታ ከአቅምሽ በላይ ከባድ የሆነ የማያልፍ አስቸጋሪ ጊዜ ላይ እንዳለሽ ተሰምቶሽ ይሆናል !

ነገር ግን ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሆኖ እስኪረሳ ድረስ ያልፋል !

ፈጣሪ ሁል ጊዜም ትክክል ነው ! ስለዚህ አሁን ያለንበት ህይወት የተሳሳተ ሳይሆን መሆን ያለበት ነው ስለዚህ ለሆነው ሁሉ እናመስግን !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ጠይቅ !

ለምን ማለትን እንልመድ የማይገባ ነገር ሲደረግ ስናይ ለምን ሆነ እንበል ! የማናውቀው ነገር ሲከናወን ምንድነው ? ምን እየተደረገ ነው ? ለምንስ ? ብለን እንጠይቅ!

የማይመቸንን ያልፈለግነውን ነገር መቀበል እና መሸከም ግዴታ የለብንም እምቢ አይሆንም ማለት መብታችን ነው !

" ልክ ያልሆኑ ነገሮች ልክ እንዳልሆኑ የሚነግራቸው ካጡ ልክ መስለው ይኖራሉ ስለዚህ ለማቆም አንስነፍ "

ደማቅ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እረፍት !

እረፍት ማለት በስራ ቀናቶቻችን ለራሳችን ማድረግ ያልቻልነውን ነገር ማድረግ የምንችልበት እድል የምናገኝበት ወደራሳችን ወደማንነታችን መለስ ብለን የማየት እድል የምናገኝበት ቀን ነው ስለዚህ በደንብ አድርገን በሚገባ እንጠቀምበት ሲያመልጠን እንዳንቆጭ ያለንን አናባክን !

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉንም ታልፋለህ!

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው።

ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ አንተ ከዛ በላይ ከባድ ነህ! ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!

ማራኪ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወስን!

ህይወትህን እስከመጨረሻው የሚቀይረው አንድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል! በቃ ህይወቴን የምቀይረው እኔ ነኝ! ማንንም አልጠብቅም ከፈጣሪ ጋር ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ። ያኔ አይምሮህ ራሱ የምትፈልገውን እንታሳካ ክፍት ይሆናል! ወዳጄ ወስንና ወደ ተግባር ግባ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ደስ ይበልህ!

እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት። ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! በፈተና ደስ ይበልህ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወሳኝ ፀሎት!

ፈጣሪ ሆይ 'መቀየር የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል እርዳኝ፤ መቀየር የምችላቸውን እንድቀይር ድፍረቱን ስጠኝ ከሁሉ በፊት ግን ሁለቱን መለየት እንድችል ማስተዋሉን ስጠኝ።' እርካታ የሞላው ህይወት ለመኖር ወሳኝ ፀሎት ነው።

የሚያረካ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ግዜህን ጠብቀው !

እያንዳንዷን ደቂቃ እና ሰዓትህን በአግባቡ ተጠቀምባት ፣ ካለፈ በኋላ ወይኔ ለምን ማለቱ አያዋጣም ምክንያቱም ልንመልሰው አንችልም ስለዚህ ከዛሬዋ ቀን ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ራስህን በደንብ ንገረው ያለ አግባብ የሚባክን ግዜ የለም !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የራስ መንገድ!

ሁልጊዜም የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም፤ መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ።

አየህ በህይወት ውስጥም የሚገጥሙህን ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች፣ አስቸጋሪ የሰው ፀባዮችን ሁሉ መቆጣጠር አትችልም፤ ያንተን ህይወት ግን እንዲወስኑት አለመፍቀድ ያንተ ምርጫ ነው ምክንያቱም የመርከብህ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ጉዞ ወደ ለውጥ!

ድግስ ላይ ከቡፌው የምትፈልገውን የምግብ ዓይነት ሁሉ አንስተህ ስትጨርስ ምግቡን ፊት ለፊትህ አስቀምጠው አይንህ እንዲያየውና አፍንጫህ እንዲያሸተው ብቻ ቢደረግ አያበሳጭም?

በህይወትም ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች አንብበህ፣ ሰምተህ፣ በአይምሮህ ሰብስበህ ግን ተግባር ላይ ካላዋልከው አሪፍ ምግብ ሳይበሉ ዝምብሎ ከማሽተት በምንም አይለይም። ወዳጄ ከምትፈልገው ያስቀረህ አለማወቅ አይደለም፤ ያወከውን አለማድረግህ ነው። ዳይ ወደ ተግባር!

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መቸኮል አቁም!

ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! ሁሉም ነገር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ፤ በተለይ ደግሞ አትጓጓ! ለህይወት ጣዕም እንድታጣ ያደረገህ መጓጓት ነው።

ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ በቅርቡ መውጣቷ አይቀርም!

የተስፋ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከአሁን ጀምር !

መሪ መሪነቱን የሚጀምረው ቦታው ላይ ሲወጣ ሳይሆን ገና ማንም ሳያየው ማንም ሳያውቀው ነው ! ራሱን ይሰራል ፣ ማንነቱን ይገነባል ፣ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ይሳላል እናም ብቁ መሆኑ ሲታመንበት ይወጣና ቦታ ይሰጠዋል !

" ቦታውን ስናገኝ ሳይሆን መምራት የምንችለው መምራት ስንችል ነው ቦታውን የምናገኘው "

የተመቸ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ያለንን እንይ !

ያገኘነው ነገር ካጣነው እጅግ በብዙ ይበልጣል እኛ ግን ከብዙው ስጦታ እና መልካም ነገር ይልቅ አንዷ ችግር ገዝፋ ትረብሸናለች አዕምሮዋችንን ይዛ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለን አድርጋ ታሰማናለች ትንሽ ቆም ብለን ግን ብናየው የሌለን ነገር ሁሉ የሌለን ወይ ዋጋ ለመክፈል ስለሰነፍን ወይ ደግሞ ስለማይጠቅመን ነው !

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እናመስግን !

እኛ ከምናስበው የቀደመ ከእኛ በላይ ለአኛ ያለን ደግነቱ ከአእምሮም በላይ የሆነ ጭንቀታችንን የሚያቀልልን ከገባንበት ችግር ነቅሎ የሚያወጣን እንዳንወድቅ የሚደግፈን እንዳንሸነፍ የሚያበረታን ፈጣሪ አለን ታድያ እሱን ለማመስገን ምን እንጠብቃለን !
🪄 ስላለኸን ተመስገን 🙏
🪄 ልጆችህ ስላደረግኸን ተመስገን 🙏
🪄 የእኛ ስለሆኖክ እና ሁሉን ነገራችንን ሽፍን አድርገህ ስለያዝከን ተመስገን እንበለው 🙏

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አስተያየታችን ላይ እንጠንቀቅ !

ለሰዎች አስተያየት ለመስጠት ከመነሳታችን በፊት የምንሰጠውን አስተያየት ልክ መሆን አለመሆኑን እናረጋግጥ ! ሰዎቹ ምን አይነት ነገር እያሳለፉ እንደሆነ ምን እንዳጋጠማቸው ምን እንደቻሉ ምን እንደሚፈልጉ እና ምን እንደሚያስፈልጋቸው እንወቅ ከቻልን እናግዛቸው ካልቻልን ግን ዝም በማለት እንተባበራቸው ብዙዎች አስተያየት የሚሰጣቸው አላጡም ከጎናቸው ሆኖ የሚያግዛቸው እንጂ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ተዓምር!

ተኝተህ ማደርህ እኮ ተዓምር ነው፤ ወተህ መግባትህ ተዓምር ነው ምክንያቱም ዛሬን ማየት ያልቻሉ ብዙ ናቸው፤ መተንፈስህ እኮ ተዓምር ነው ምክንያቱም ከማሽን ውጪ የማይተነፍሱ ሞልተዋል። የሚያስጨንቅህ ነገሮች በሞት ፊት ተራ ናቸው!

ከጎደለህ ይልቅ የተሰጠህን ተመልከት፤ ከስንቱ ችግር አልፈሀል፤ አበቃልኝ ብለህ ተስፋ የቆረጥክባቸው ጊዜያት እንደ ቀልድ አልፈዋል እኮ፤ ወዳጄ አላስተዋልከውም እንጂ ህይወትህ የተሞላው በተዓምር ነው።

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወስን!

በየቀኑ የምትወስናቸው ትናንሽ ውሳኔዎች የነገ መድረሻህን ይወስኑታል። ማንበብ ውሳኔ ነው፤ ስፖርት መስራት ውሳኔ ነው፤ በጠዋት መነሳት ውሳኔ ነው፤ ለህይወትህ ከሚጠቅሙህ ሰዎች ጋር መዋልም ውሳኔ ነው።

ተኝቶ መዋልም ውሳኔ ነው፤ ብር ማጥፋትም ውሳኔ ነው፤ ቲቪ እያዩ ማምሸትም፣ ፊልም በማሳደድ እና ስልክ ላይ ተጥዶ ጊዜን ማባከንም ውሳኔ ነው።

ወዳጄ እጅህን ወደ ውሀው ወይ ወደ እሳቱ መስደድ ያንተ ምርጫ ነው! ግን አስብና የሚጠቅምህን ወስን!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምስጋና !

የሰው ልጅ ሊሰጠው የሚችለው ውድ ስጦታ ጊዜውን ነው !

ይሄን መተኪያ የሌለውን ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ወደ ትልቅ ለውጥ አብራችሁን ለመሻገር ቪዲዮዎቻችንን ስትከታተሉ እና ስልጠናዎቻችንን ስትወስዱ ስለቆያችሁ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው !

➥ የእናንተን አስተያየት በመቀበል በየጊዜው አዳዲስ ለውጦችን በማምጣት የሚታወቀው የ 'Online' ስልጠናችን 17ተኛውን ዙር በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ቀናቶች ቀርተውታል !

🔸 አምናችሁ ለሰጣችሁን ውድ ጊዜ እንታመናለን !

18ተኛው ዙር ስልጠናችን ረቡዕ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ይጀምራል !

ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን ፣ በቴሌግራምና ዋትስአኘ መልዕክት ይላኩ !

☎️ +251944314544

የተባረከ ጊዜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተንው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስ ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያችሁ 🙏 ከቆይታ በኋላ በቆንጆ ርዕስ መጥተናል

አብዛኛው ሰው በንዴት ምክንያት ብዙ ነገሩን ያጣል ለትንሽ ነገር ማለፍ አቅቶት የረጅም ጊዜ ችግር ውስጥ ይገባል ንዴት ባህሪያችን አይደለም ይቀየራል !

እንዴት ለሚለው Inspire Ethiopia Podcast ዩቲዩብ ቻናል ላይ ወይንም https://youtu.be/eDwLXNU5Nhs በዚህ ሊንክ ገብታችው ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ታገኙታላችሁ !

መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በፅናት ቁም !

ያመንክበትን ትልቅ እና መልካም ነገር ለማሳካት ስትታገል ብዙ ነቀፌታ ይደርስህ ይሆናል ብዙም ግዜ ልትወድቅ ትችላለህ እንቅፉት ሊበዛ ልትደክም ትችላለህ ነገር ግን ፅናት ካለህ ታግሰህ ከታገልህ እመነኝ በስተመጨረሻ ድል ያለችው በእጅህ ናት !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ማንም የማይነግርህ ብዙ አለህ !

ማንም ሰው ከማንነትህ አውርዶ ዝቅ እንዲያደርግህ እና ያለህን የተሰጠህን በረከት ሁሉ እንደሌለህ እንደጎደለህ እንዲሰማህ እንዲያደርግህ አትፍቀድለት ፈጣሪ ብዙ ድንቅ ስጦታዎችን ሰጥቶህ ሳለ ምንም እንደሌለህ የሚያሰሙህን ሰዎች አትስማ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን መጉዳት አቁም!

ፀሀይ ስትጨልም ስራ አቁማ አይደለም፤ ሌላኛውን የመሬት ክፍል ልታበራ ዞር ብላ ነው። እናቱ ገበያ የሄደችበት ልጅ እናቱ ከሞተችበት ልጅ እኩል ያለቅሳል፤ ግን እኮ መመለሷ አይቀርም።

ህይወትን በቀጥታ እየተረጎምክ ራስህን መጉዳት አቁም! የተወሳሰቡና ግራ ያጋቡህን ነገሮች ተረጋግተህ በተለየ መንገድ ለማሰብ ብትሞክር ብዙ እንቆቅልሽ ትፈታለህ። ኑሮ፣ ስራ፣ የፍቅር ግንኙነት የፈተና ድንጋይ ሲወረውሩብህ አንተ ሰብስበና ተዓምረኛ ቤት ስራበት!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እስክታጣ አትጠብቅ !

የመኖርህ ደህና የመሆንህ ጥቅም የሚገባህ ስትታመም ነው ! የተሰጠህ እድል ከምንም በላይ ትልቅ እንደሆነ የምታውቀው ለማጣት ስታጣጥር ነው !

በፊት ታማርርባቸው የነበሩ ነገሮች በሙሉ የሚያማርሩ እንዳልነበሩ የምታውቀው በጠና ስትያዝ ነው !

ነገር ግን ዋጋ ለማግኘት እና ባለህ ለማመስገን የግዴታ ማጣትህንና መቸገርህን ለምን ትጠብቃለህ ቆም ብለህ እስኪ ራስህን አስበው አሁን ያለህን ነገር በሙሉ ብታጣ ምን የሚፈጠር ይመስልኋል?

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አመስግን !

በጠዋት ተነስተህ ማማረር አትጀምር ነቅተሀል እኮ ስለዚህ ለተሰጠህ ትልቅ እድል ፈጣሪህን አመስግን ደስ ይበልህ ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ ይሄ ጎድሎኝ ያን አጥቼ አትበል ከሁሉም በላይ ህይወት አግኝተሀል እኮ ስለዚህ ደጋግመህ አመስግን !

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምርጫ !

ሁለት አማራጮች ፊትህ ቁጭ ተደርገው የቱን መወሰን እንዳለብህ ግራ የሚገባህ ግዜ አለ አይደል የቱን ልስራ ምን ልማር ማንን ላግባ መቼስ ይሁን የትኛውን ትምህርት ላጥና ...... ብዙ ከከባድ እስከ ቀላል የሆኑ ምርጫዎች ይቀርቡልሀል እናም አንድ ነገር ብቻ ልምከርህ ራስህን ብዙ አታስጨንቅ ፀልይ ፈጣሪህን ጠይቅ ከዛም በደንብ ትኩረት አድርገህ አስተውል ጥቅሙንም ጉዳቱንም ዝርዝር አድርገህ እይ ከዛ ቶሎ ወስን የሚመጣው ነገር ካለው በላይ አያስፈራህ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

"የራስ ዋጋ"

እውነተኛ መውደድ የሚገለፀው መጀመሪያ ራስን በመውደድ ነው፤ ሰዎች አንተን ከማክበራቸው በፊት አንተ ራስህን አክብረው። እነሱ ሁኔታህን አይተው ነው የሚለዋወጡት።

የአንድን ዕቃ ዋጋ የሚያወጣው ሻጩ ነው፤ ካላዋጣው እኮ መቼም አይሸጥም፤ የራስህን ዋጋ የምታወጣው አንተ ነህ! ቦታህን እወቅ! ራስህን ከምንም ነገር በላይ አክብረው ወዳጄ!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን አታታል !

ብዙ ግዜ የእኛ ችግር አንሰራም ወይም ማድረግ ያለብንን እናውቃለን ግን ደግሞ አናደርግም ከዚያ ግን ያደረጉ ሰዎችን እንተቻለን እንደዚህ እዞ ባያደርጉት ኖሮ ይሄን ቢጨምሩ ምን አለበት አሁን አደረግን ብለው ነው እያልን እንተቻለን ስንፍናችን እንዳይሰማን ጎበዞችንን እናኮስሳለን ወንድሜ ካልሰራህ ማድረግ ካልቻልክ እና ከተቸህ አዎ ሰነፍ ነህ ስለዚህ ወሬውን ተውና ዳይ ወደተግባር ግባ እሱ እሷ አትበል አንተ ምን እያደረግህ ነው?

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች

1. የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።
2. ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ።
3. ስትፈልገዉ ያጣከውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ።

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ 🙏
@inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አሁን ሞክር!

ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው
ይቆጩሀል፣ 'ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ' ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ።

አሪፍ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉንም መቀየር!

ትላንት ላይመለስ አልፏል ራስህን መውቀስ አቁም! አሁንን መኖር ጀምር፤ ዛሬ ቆራጥ ከሆንክ ሁሉንም መቀየር፣ ሁሉንም እንደ አዲስ መጀመር፣ ያበላሸኸውን ማስተካከል ትችላለህ። ወዳጄ እድልህን ተጠቀምበት ይሄንን ቀን ያላዩ ብዙዎች አሉ።

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel