inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ለስኬትህ አትቁም!

ትክክለኛውን መንገድ ስትመርጥ ግራ መጋባት ይፈጠርብሀል አሰልቺ እና አድካሚ የሚሆኑ ግዜያት ይኖራሉ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች የስኬት መንገዶችህን የሚወስኑ ናቸው !

መጥፎ ስሜቱን መቆጣጠር ካቃተህን እና ከቆሞክ ትሸነፋለህ ነገር ግን ይሄን ስሜት ከፈጣሪህ ጋር በድል ከተወጣኸው ስኬት በእጅህ ናት !

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን አክብረው !

ራስን መናቅ የፈጠረህን ፈጣሪ መናቅ ነው አክብሮ የሰጠህን ማንነትህን የመጠበቅ ትልቅ ግዴታ አለብህ !

አንተ የተሰጠህን ትልቁ ስጦታህን ጠንቅቀህ ካልያዝከው ማንም ሊይዝልህ አይችልም ! አንተ የተሰጠህ ራስህን ካልተንከባከብከው ማንም ሊንከባከብልህ አይችልም !

ቆንጆ ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

👋በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች !

    1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።
    2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታደርግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ ።
    3⃣ ስትፈልገዉ ያጣከውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ።
      
መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለሁሉም ጊዜ አለው !

አሁኑኑ ካልሆነ ብለህ ስላሰብክ ብቻ አለመሆኑን ውደደው ነገሮች ጓጉተህላቸው ከልብህ ፈልገሀቸዉ ለፍተህላቸዉ ነገር ግን ባሰብከው ግዜ እና ሰዓት የማይከናወኑት ለእነርሱ የተዘጋጀ ቆንጆ እና ትክክለኛ ቀን ስለተዘጋጀ ነው !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በፍቅር ኑር !

ሰላማዊ ህይወት እንዲኖርህ ከተመኘህ አካባቢህ ካሉ ሰዎች ጋር ሁሉ በፍቅር ኑር በማንነት በምንነት ሳትለይ አክብራቸው
የሚገባቸውን ክብር ስጣቸው ፈጣሪ በነፃ የሰጠህን ፍቅር አትሰስተው !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ያለህን ነገር እወቅ !

አንዳንዴ በእጅህ ላይ ብዙ ነገር እያለ የሌለህን ነገር በመፈለግ ያለህን አጥተህ መቆጨት ይመጣል እናም ከዚህ ለመዳን ትልቁ መፍትሄ ያለኝ የተሰጠኝ ምንድን ነው ብለህ ራስህን ጠንቅቀህ ለማወቅ መሞከር እና ባለህ አቅም በርትተህ መጠቀም ነው !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አልፈከዋል እኮ !

ያሳለፍካቸውን ግዜያት ወደኋላ ዞረህ ብታያቸው በራስህ ትገረማለህ ! ብዙ ነገራቶችን አሳክተኋል አደርገዋለው አልፈዋለው ብለህ ያላሰብከውን ሁሉ አልፈህ ለዚህ ግዜ በቅተኋል ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ነገንም እርሱን ይዘህ ታልፋለህ እናም አትፍራ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የሚታመን ፈጣሪ አለህ !

ማመንህን ቀጥል የሚያጋጥሙህ ነገሮች ማንነትህን አይለውጡብህ ሁሌም መልካም ሁን ማድረግ ያለብህን ሁሉ የፈጣሪን መንገድ እየተከተልክ አድርግ!

ከዚያም የምታገኘውን እኔ አልነግርህም የማታስበው ሲሳይ አንተ ላይ ሲወርድ ታየዋለህ የያዝከው ረቂቅ አምላክ ነው እና ሁሉ ህይወትህ በረቀቀ መንገድ ይዋባል!

የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለመጠየቅ አትፍራ !

አንድን ነገር አጥብቀህ ከፈለግከው ያንን ነገር ለማሳካት የሚያግዙህ ሰዎች ጋር ሂድ በድፍረትም አናግራቸው ምን ይሉኝ ይሆን ብለህ እንዳትቀር ምንም ቢሉህ ግድ የለም ግፋ ቢል መከልከል ብቻ ነው ስለዚህ የሚገጥምህ ካለመጠየቅህ ግን ብዙ ቁጭት ይኖራል እናም ሳትፈራ ወደፊት በል !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሀላፊነት ውሰድ !

ራስህን ለመለወጥ እና መንገድህን ማስተካከል ከፈለግህ ሀላፊነት ውሰድ ባንተ ህይወት ላይ የሚመለከትህ አንተ ነህ ሌሎች ሰዎች ላይ ጣትህን መቀሰር አቁም እና ካንተ እየተጠበቀብህ ያላደረግከውን ነገር አስተውል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከፈለግኸው !

ዋጋ መስጠት ዋጋ ያሰጥኋል ችላ ያልከው ነገር ግን መልሶ ችላ ይልኋል ስለዚህ አብዝተህ የተመኘኸውን እና የወደድከውን ነገር የሚገባውን ዋጋ ስጠው ! እርሱ መልሶ ይከፍልኋል!

ቆንጆ ሀሙስ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ካልጀመርክ....

ለመጀመር አስበህ ቆይ ይሄ ይሙላልኝ እያልክ ነው? ስለዚህ አስታውስ ጠብታ ውሀ ታርሳለች ያ የሚሆነው ግን ስትጠራቀም ነው ከጠብታዋ ካልጀመርክ ግን የሚሞላ ነገር አይኖርም

"ባለህ ነገር ተነስ እና የጎደለህን ቀስ በቀስ ሙላ "

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሌም ወደፊት !

ወድቀኋል ብለው ጥለውህ ሲሄዱ ተነስና ጠብቃቸው ወድቀህ የምትቀር ደካማ አለመሆንህን ለሁሉም አሳይ አንተ ውስጥ ያለው ፈጣሪ ሁሉን ቻይ መሆኑን አትርሳ !

ዛሬ እሁድ ከቀኑ 8 ሰዓት አድማ በዶሻ ሆቴል እንገናኝ

መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለተሻለ እያዘጋጀ ነው !

የምንፈልጋቸው ነገሮች እኛ በምንፈልገው አቅጣጫ ካልሄዱ ብለን ራሳችንን መጫን የለብንም፤ ግን እኛ በምንፈልገው መንገድ እንዲሄዱ ጥግ ድረስ እንሞክር።

እንደዛም አርገን ካልተሳኩ ይሄን አባባል እናስታውስ 'ላልተመለሰው ፀሎትህ ፈጣሪህን አመስግን' ምክንያቱም ካንተ በተሻለ የሚያስፈልግህን ያውቃል፤ ያ ነገር እንዲሳካ ወይ ጊዜው አልደረሰም ወይ ደግሞ እኛ ከፈለግነው የተሻለ ነገር ሊሰጠን ስለሆነ ነው።

የሚያረካ ውሎ ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ቤተሰቦች 🙌 ከአሁን ጀምሮ ወደ ስልጠናው መግባት ትችላላችሁ መልካም ቆይታ !

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

እምነት !

ውጤትህን የሚወስነው አቅምህ ነው አቅምህ ማለት የሰውነትህ ቅርፅ ክብደትህ የመሳሰለው ሳይሆን እምነትህ ነው!

ያመነ ሰው ብዙ ፖውንድ ክብደት ከሚያነሳ ሰው የበለጠ ጥንካሬ አለው ስለዚህ አቅምህን በእምነትህ ገንባው !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መመስገን ላለባቸው !

አንዳንዴ እንረሳዋለን ከጎናችን ያሉ ሰዎች በህይወታችን ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ እንዳላቸው ምን እንዳደረጉልን እንረሳዋለን !

ከፈጣሪ ቀጥሎ እነርሱ በመኖራቸው ምክንያት ህይወታችንን የለወጡልን እነርሱ በከፈሉት መስዋዕትነት ምክንያት ህይወታችን ዋጋ እንዲኖረው ያገዙን ምን ያህል ናቸው ? ዛሬ እስኪ ከልባችን እናመስግናቸው ክብር እንስጣቸው !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለመጣስ ተዘጋጅ!

አዲስ ነገር ሁሌም አዲስ ነው ለመጀመር ሊከብድ ግራ ሊያጋባ ማወላወል ውስጥ ሊከተን ይችላል!

ነገር ግን ይሄንን ሁሉ ነገር ጥሰን ልንጀምረው ካልወሰንን የለመድነውን ህይወት እንቀጥላለን ውድቀት የሚጀምረው ወደፊት መራመድ ስናቆም ነው!

ስለስልጠና አዳዲስ መረጃ ለምትፈልጉ Join 👇
@Inspire_Ethiopia_Training

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈጣሪህን አስቀድም !

🪄አንዳንድ በሮች ይዘጉብሀል፤ ቦታህ ስላልሆኑ
🪄አንዳንድ በሮች ይዘጉብሀል ጥንካሬህን ሊፈትኑ
🪄አንዳንድ በሮች ይከፈቱልሀል ፤ ያንተ ስለሆኑ
🪄አንዳንድ በሮች ይከፈቱልሀል ፤ በግድ ስለታገልካቸው

እናም ተዘጋ ማለት በቃ ማለት ብቻ አይደለም ተከፈተም ማለት ሆኗል ማለት አይደለም እናም አስተውልና ከፈጣሪህ ጋር ተማክረህ መንገድህን ቀጥል ከፊትህም ፈጣሪህን አስቀድም !

ደስ የሚል ረቡዕ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ነፃ ነህ !

ምርጫ የተሰጠህ እንድትመርጥ ነው አስታውስ እንድትመርጥ! የሚጠቅምህን ከሚጎዳህ የሚያስፈልግህን ከማያስፈልግህ ለይተህ ነቅለህ ለማውጣት የሚጠቅም ነፃነት ተሰጥቶኋል እና ምን እየጠበቅክ ነው ተጠቀምበት እንጂ !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አመስግን !

ይህንን የመሰለ ቀን ነግቶልናል በአዲስ መንፈስ አዲስ ቀንን እንድንገነባ ቆንጆ እድል ተሰጥቶናል ይህንን ያደረገልን አምላክ መመስገን ሲያንስበት ነው ! ስለዚህ ሳትዘናጋ አመስግን ያለን ካሰብነው ሁሉ ይበልጣል!

ውብ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለስኬታማ ሳምንት !

ዛሬ የእረፍት ቀን ነው ከድካም ከሳምንቱ ግርግር ከነበረው ሩጫ ሁሉ እርፍ ብለህ ራስህን የምታዳምጥበት ቀን ነው !

እናም ይህችን ቀን ሳታንጠባጥብ በደንብ አድርገህ ተጠቀምባት ከዛም ሳምንትህ ውጤታማና ስኬታማ ሲሆን ታየዋለህ !

ቆንጆ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ለእውነተኛ ለውጥ !

መሰረት የሚጣለው ከስር ነው መጀመሪያ ያልጠነከረ ነገር ባማረ መልኩ አይፈፀምም በእያንዳንዷ የምትሰራት ነገር ላይ የማይንገዳገድ መስረት ጣል ሳትሰላች ስራበት ከዚያም ትክክለኛውን ውጤት ታገኝበታለህ !

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

አትፍራ !

እዚህች ምድር ላይ እስከተፈጠርክ እና ሰው እስከሆንክ ድረስ ፈጣሪ ትልቁን እድል ሰጥቶካል ማለት ነው ስለዚህ ምንድነው የምትፈራው ምን ማጣት ነው ያሳሰበህ ምንስ እንዳይቀርብህ ነው ከስኬትህ ከመንገድህ የምትቆመው?

መልካም ጁምዓ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ይሄንን ቻናል በተመለከተ ...

እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም በዚህ ቻናል የተለያዩ የስልጠና እና የቪድዮ ማስታወቂያዎችን ስንለቅ የቆየን ሲሆን !

ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውንም የስልጠና መረጃዎች ብሎም የሀሙስ ነፃ ስልጠና ሊንኮችን ማግኘት ለምትፈልጉ ብቻ ሌላ ቻናል የከፈትን ሲሆን ይህንን ቻናል ለመቀላቀል ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ 👇
@Inspire_Ethiopia_Training

✨ ከዚህ በኋላ በዚህ ቻናላችን ሁሌም ጠዋትና ማታ አነቃቂ እና አስተማሪ ፅሁፉችን እና ድምፆችን ብቻ የምንለቅ መሆኑን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው !

መልካም ቀን ለመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

መንገድህን ለእርሱ ስጥ !

ታሪክህን የሚቀይርልህ ፈጣሪህ ብቻ ነው ስለዚህ ነገራቶችህን በሙሉ ለእርሱ ስጥ አንተ የሚገባህን ካደረግህ በኋላ እርሱ የሚያስፈልግህን በሙሉ እንደሚሰጥህ እመን ያኔ ታሸንፋለህ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ራስህን አበርታ !

በህይወትህ እየተፈጠረ ያለውን እያንዳንዷን ጥቂት የምትባለዋን ለውጥህን የምታየው አንተ ብቻ ነህ ከትላንት ዛሬ የተወሰነ ያህል ከፍ ብለሀል ነገር ግን ማንም በለውጥህ አያደንቅህም !

ስለዚህ አይግረምህ ላንተ እየታየህ ያለው ለሌሎች እየታየ አይደለም ሁሉም የራሱን በማየት ላይ ነው እና ራስህን እያበረታህ ጠብቅ !

መልካም ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሁሉም ይሳካል!

"የማይነጋ ሌሊት የማያልፍ ቀን የለም " ብቻ አንተ ታገስ እንጂ በቀኑ እና በሰዓቱ ሁሉም ውብ ነው ! የምትፈልገው ነገ እየተሰራ ያለውም በዛሬህ ላይ ነው እና እስከጥግ ታግሰህ ጠብቅ !

መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

https://us06web.zoom.us/j/85840695226?pwd=N3R6QWdOLzZuYjY4TTZDOVR5ajBXUT09

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስኬት !

ስኬታማ መሆን የሚቻል እና ቀላል ነገር ነው ምክንያቱም ብዙዎች አድርገውታል ከእኛ የሚጠበቀው የእነሱን መንገድ መከተል ብቻ ነው !

ዛሬ ማታ እንደተለመደው 3 ሰዓት ላይ ይጠብቁን በዚሁ ቻናል የስልጠና ሊንክ ይላካል !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel