inspire_ethiopia | Unsorted

Telegram-канал inspire_ethiopia - Inspire Ethiopia

-

Inspire_ethiopia™ |Youtube|TIKTOK|facebook For private discussion @sinework_taye @danielwodajo

Subscribe to a channel

Inspire Ethiopia

ዝም ብለህ ስጥ !

ዝም ብለህ ሳትጠብቅ መስጠትህን ቀጥል የምታገኘውን መቁጠር ከጀመርክ የተሰጠህ በቂ ላይመስል ይችላል !

እናም ወደኋላ እንድትመለስ ይገፋፋሀል የሰጠኸው ዋጋ ከምንም በላይ ነውና ሳትሰስትና ሳትጠብቅ መንገድህን ቀጥል የመስጠትህ ዋጋ ያለው ፈጣሪህ ጋር ነው !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ዝግጁ ሁን !

💧በህይወት ውስጥ እድለቢስ የምንባለው  ትክክለኛው ሰው በተሳሳተ ጊዜ ወደ ህይወታችን የመጣ ጊዜ ነው፤ በየትኛው ሰዓት የህይወት ዘመን ጓደኛ ወይ ፍቅረኛ እንደሚመጣ ስለማናውቅ ሁሌም ራሳችን ላይ መስራት አለብን።

ፍቅር የሞላበት ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከፍ ሊያደርጉህ ነው !

"ፈተናዎች ህይወትን አጓጊ ያደርጉታል፤ እነሱን ማሸነፍ ደግሞ ህይወትን ትርጉም ይሰጡታል" ይለናል ጆሽዋ ማሪን። ከባድ ፈተናዎች የሚገጥሙን ማንነታችንን እንድናሳይ ነው እንጂ አዝነን እንድንቀር አይደለም!

ወዳጄ ከችግርህ አንተ ትገዝፋለህ ምክንያቱም ጥሎ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ማንነት ስላለህ።

ውብ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምክንያት ይኑርህ !

ሁላችንም
የምንኖርለትን ምክንያት እስክናውቀው ድረስ ሙሉ አቅማችንን አንጠቀምም፤ ስለዚህ ሌሎች ድክመታችንን አይተው እሱ እኮ ሰነፍ ነው ይሉናል፤ እሷ እኮ ግድየለሽ ናት ይሉናል።

ወዳጄ የምትኖርለትን ምክንያት ሳታውቀው ቀርተህ እንጂ ከማንም አንሰህ አይደለም! እህቴ የሚያበረታሽን ጉልበት የሚሰጥሽን ምክንያት አተሽ እንጂ የሚገርም አቅም ነው ያለሽ! ምክንያታችንን እንፈልገው ቤተሰቦች✊

ውብ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

🧤በዚህ አለም 3 አይነት ሰዎች አሉ

1⃣  ነገሮችን በጥረታቸው የሚያሳኩ
2⃣  ነገሮች ሲሳኩና ሲበላሹ ቆመው የሚመለከቱ
3⃣  ጭራሽ ምን እየሆነ እንዳለ የማያውቁ

ይሄን ፅሁፍ የምናነብ ሁሉ ምርጫችን የቱ እንደሆነ ይታወቃል፤ ግን ታዲያ ምን እያደረግን ነው?  °እየጣርን ነው? ወይስ °ቆመን እያየን ነው? ወይስ °ጭራሽ አንቀላፍተናል?
ዳይ ወደ ጥረታችን!

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰው ሁን !

ዳዊት ሰለሞንን
ምን እንዳለው ሁላችንም እናስታውሳለን አይደል? 'ልጄ ሰው ሁን' አለው። ሰው ከመሆን በላይ ለኛ ምን ስጦታ አለ? ሰው የመሆን ትልቁ ትርጉም ደግሞ ማሰብ ነው። ምን እንደምትፈልግ አስብ! ከዛ የምትፈልገውን እንዴት እንደምታገኝ አስብ! በዘፈቀደ መኖር አቁመን ሰው መሆን መጀመር አለብን።


ሰናይ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ስህተትህን እመን !

ለመለወጥ እና ካለንበት ቦታ ወደተሻለ ለመራመድ ከፈለግን መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ስህተታችንን ማመን ነው ! ስህተቱን የማያምን ሰው በአጭር ገመድ ታስሮ ነገር ግን ወደፊት ለመራመድ የሚታገል ሰው ነው መቼም ካለበት አይሻገርም !

ብልህ ሰው ስህተቱን አውቆ ይማርበታል !

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ልበ ሙሉ ሁን !

በተቻለህ አቅም
ምንም ነገር ስታደርግ በግማሽ ልብ ሆነህ እያመነታህ መሆን የለበትም፤ ስታመነታ ብዙ ነገር ያመልጥሀል፣ ሰዎች ባንተ እርግጠኛ መሆን አይችሉም።

ልበሙሉ ከሆንክ ግን ስህተት እንኳን ብትሰራ በሌላ ልበሙሉ ተግባር ስህተትህን ታስተካክላለህ። የሚያመነታ ሰው ሁለት ቦታ ስለሚረግጥ ከአንዱም ሳይሆን ከመንገድ ይቀራል።

አሪፍ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ወደ ፈጣሪ ቀና በል !

ችግርህን ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪ ንገረው ፡

እርሱ አያቃልልብህም ያሳልፍሀል ፤ አያባብልህም መፍትሄ ይሰጥኋል !

" አሸናፊዎች ችግራቸውን ከሰው በላይ ለፈጣሪ የሚያማክሩ ናቸው ማሸነፍ ከፈለግክ ፈጣሪህን ተመልከተው "

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ትልቅ ማሰብ !

"ትንንሽ ሀሳቦች ሁሌም ትንንሽ ናቸው ግን የትልቁን ቦታ ይይዛሉ" ይለናል አዘርግ የተባለ ደራሲ። ሰዎች ስለኔ ምን ያስባሉ ብሎ ከማሰብ በላይ ምን ትንሽ ሀሳብ አለ?

በዚህ አለም አንድ ነገር አትርሳ ዋናው አንተን ደስ የሚልህ ወንጀል ወይ መጥፎ ተግባር አይሁን እንጂ.....የምትሰራው የምትማረው አንተን ደስተኛ የሚያደርግህ ነገር ከሆነ እኮ ትልቅ ሀሳብ ነው! በትንሽ ሀሳብ አትጠመድ፤ አለዛ የትም አትደርስም!

አስደሳች ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፍርሀትህን ለማሸነፍ !

ደፋር ሰው ማለት ፍርሀት የማይሰማው አይደለም ግን ከፍርሀቱ ጋር ፊት ለፊት የሚፋለም ነው' ይለናል ኔልሰን ማንዴላ።
ፍርሀታችንን የምናስተናግድበት መንገድ የህይወት መዳረሻችንን በሁለት መንገድ ይወስነዋል ፦

1⃣አዲስና አስገራሚ የህይወት አጋጣሚዎችን እናጣጥማለን
2⃣ምንም ሳንሞክር እንደፈራን እናልፋለን

ስለዚህ መጋፈጥን ልማዳችን እናድርገው !

ቆንጆ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በከባድ ፈተና ውስጥ ራስህን መፍጠር እንደምትችል ታውቃለህ ?

📍 የህይወትህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ልትሆን ትችላለህ ምኑን ከምኑ እንደምታቻችል ፣ ወቅቱ ለስራህ አልመች ብሎህ የትኛውን ማስቀደም እንዳለብህ ፣ የቱን መተው እንደሚጠበቅብህ መላቅጡ ጠፍቶህ ይሆናል ፤ አይዞህ ብዙ ሰው ጋር ይሄ ስሜት አለ ።

ችግሩን መካድ አይጠበቅብህም 'በጥበብ' ማለፍ ግን ትችላለህ !

🔹 ኢንስፓየር ኢትዮጵያ ኮሮና በከፍተኛ ደረጃ በተስፋፋበት ፣ ሁሉም በሩን ዘግቶ በተቀመጠበትና ኑሮ ባሻቀበት ወቅት እንደተፈጠረስ ያውቃሉ ?

ህይወትህን ለመቀየር አንድ ውሳኔ በቂ ነው !

📍በኛ በኩል ከየትኛውም ሀገር ቢሆን ከቤትህ ሆነህ በምቾት ራስ ላይ መስራት የምትችልበትን አማራጭ አመቻችተናል !

ነገ ቅዳሜ ምሽት 3:00 የ21ኛው ዙር የኦንላይን ስልጠናችን ይጀምራል

ለመመዝገብና ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

☎️ +251944314544

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈጣሪ ሲሰጥ ቆጥሮ አደለም !

የሚያስገርመን የምንደነቅበት ይሆናል አይሆንም እያለ የሚያንገበግበን ነገር በሙሉ በፈጣሪ አይን በጣም ጥቂት ነገር ነው እኛ ከጠየቅነው በላይ እርሱ ብዙ አለው !

ስጠን ስንለው ሰስቶ ሳይሆን ሰፍሮ ነው አርግልን ስንለው የሚሰጠን ውለታ እየቆጠረብን አይደለም እናም በአለም ላይ ያለ ሁሉ እርሱን እስከያዝን ፍፁም አያስገርመን ከጠየቅነው በላይ ብዙ የሆነልን ገናም የሚሆንልን አለን ! ተመስገን 🙏


ግሩም ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከምንም በላይ ራስህን ስራ !

ታላቅ ስለመሆን ስለማሸነፍ ስታስብ የአንድ ቀን ብቻ አይደለም ወይም ስለጊዜያዊ ድል ብቻ አይደለም እዛ ስኬት ውስጥ ስለመቆየት አስብ !

ድል ካልተዘጋጁበት ወጥቶ መውረድንም ያመጣል አግኝተህ ለማጣት ምን አደከመህ አሳክተህ ማጣጣም ከፈለግህ ግን ዝግጁ ሁን ለምታመጣው ስኬት መጥን ራስህን አሳድግ የሚያምርብህም ያኔ ነው !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከራስህ ቅደም !

"ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው፤ ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል" ይለናል አልበርት አንስታይን።

ከትላንት ግን ዛሬ ቀድመን መገኘታችንን አንርሳ ነገር ግን እኛን የሚዳኘን የራሳችን መስፈርት ነው፤ የሌሎች መንገድማ የሌሎች ነው !

በደስታ የተሞላ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፈጣሪን አስቀድም !

ፈጣሪ ያለበት ቦታ በሙሉ ምቹ ነው ሁሉንም ነገር እርሱን አስገብተህ ስትመራው አዎ መንገድህ የቀና ቤትህ የሰመረ ህይወትህ በሙሉ ያማረ ይሆናል !

ስለዚህ ወዴትም ለመሄድ ስትነሳ አንድ ነገር በለው አንተ ቅደመኝ ያኔ በተባረከው መንገድ ትጓዛለህ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ጠብቅ !

አንዳንዴ ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው።

እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም።

ሰናይ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ያለህን ውደደው !

❤️ ፍቅረኛ የሌለኝ ቀልድና ጨዋታ ስለማልችል ነው አትበል! ቁምነገኛነትህን የምትወድ መምጣቷ አይቀርም። ወሳኙ ነገር መጀመሪያ ብቻህንስ ሆነህ ደስተኛ ነህ ወይ ነው፤ ምክንያቱም ደስተኛ ሰው ፈላጊው ብዙ ነው።

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ማጣጣም ልመድ !

ድግስ ላይ ከቡፌው የምትፈልገውን የምግብ ዓይነት ሁሉ አንስተህ ስትጨርስ ምግቡን ፊት ለፊትህ አስቀምጠው አይንህ እንዲያየውና አፍንጫህ እንዲያሸተው ብቻ ቢደረግ አያበሳጭም?

በህይወትም ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች አንብበህ፣ ሰምተህ፣ በአይምሮህ ሰብስበህ ግን ተግባር ላይ ካላዋልከው አሪፍ ምግብ ሳይበሉ ከማሽተት በምንም አይለይም። ብዙ ነገር ማወቅህ ጥሩ ነው፤ ወደ ተግባር ሲለወጥ እውቀት ኃይል ይሆናል።

ሰናይ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ቤተሰቦች 🙌 ከአሁን ጀምሮ ወደ ፈንዲሻ ሰዓታችን መግባት ትችላላችሁ !

Zoom link - https://us06web.zoom.us/j/82517076006?pwd=UGZtYVlvK0hnZytIU3MwQzdBeGl2dz09

Meeting ID - 82517076006
Passcode - 162667

Youtube live link - https://www.youtube.com/live/bzUX1sM6YLc?feature=share

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ፍቅር !

የፍቅር ግንኙነት ደካማውን ብርቱ ሰነፉን ጎበዝ ወይ ደግሞ ጀግናውን ልፍስፍስም የማድረግ ትልቅ አቅም አለው ፤ ጤናማ እና የሚያበረታን ግንኙነት እንዲኖረን ሁሌም ማወቅ ማጥናት እና ራሳችንን ማሳደግ መቻል አለብን ያኔ ሁሌም የሚያበረታውን ፍቅር እናገኘዋለን !

📍ዛሬ ምሽት በፈንዲሻ ሰዓታችን ስለ አምስቱ የፍቅር ዲሲፕሊኖች በጥልቀት እንወያያለን ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ትንሿን ጠብቅ !

በህይወት
ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተስ ። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው።

በቀን ውስጥ አደርጋለው ያልከውን ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ ቀንህን ከማሳመር ነው የሚጀምረው።

የተባረከ ቀን ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

የህይወት ወቅቶች !

ህይወት ምንጊዜም በጋ እና ክረምት የሚፈራረቅባት መድረክ ናት፤ አስተዋይ ሰው ሁለቱም ወቅቶች በህይወት ራሳቸውን እንደሚደግሙ ስለሚያውቅ ምንም ቢመጣ አይገርመውም።

አንዳንዴ ከባድ ቀን ማሳለፍ ያለ ነው፤ የዋንጫ ቡድንም እኮ ይሸነፋል። ግን ለትናንት ውድቀት ዛሬውን መስዋዕት የሚያደርግ ሞኝ ብቻ ነው። ራስህን መውቀስ አቁም ወዳጄ!

የሚገርም ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ምስጋና !

ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ !

በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ በምስጋና ስትታጀብ ቤትህ ይደምቃል ኑሮህ ይሞቃል በረከት ሁሉ ወደአንተ ይመጣል!

የተባረከ ሰኞ ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ከትላንትህ ታረቅ !

ትላንት ምንም ነገር አጋጥሞህ ሊሆን ይችላል ዛሬ ግን ሁሉ አልፎ እዚህ ተገኝተሀል ዛሬ ላንተ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቶልሀል 😄

ነገር ግን አሁንም ትላንት ስለነበረ ነገር እየተከፋህ እያዘንህ እያማረርህ ከሆነ ዛሬህን ብቻ ሳይሆን ነገህንም እያበላሸህ ነው ስለዚህ ትላንትህን ታረቀው እንዳለፈ ሁሉ አንተም እለፈው ዛሬን ላሻገረህ እያመሰገንህ ውብ ህይወት ኑር 💪

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ጊዜህን ጠብቅ !

በጣም ከባድ እቃ ተሸክመህ ረጅም መንገድ መሄድ ቢኖርብህ የሆነ ቦታ ላይ ወይ መቆምህ ወይ መውደቅህ አይቀርም !

ያኔ ውድቀቱ ከጠባሳ እና ከህመም ጋር ነው የሚሆነው ስለዚህ ለምን አላገኘሁትም ብለህ የምትከፋበት ነገር አቅምህ የማይፈቅደው ይሆናል እና እስክትጠነክር ጠብቀው!

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ሰላም ቤተሰቦች 🙌 ከአሁን ጀምሮ ወደ ፈንዲሻ ሰዓታችን መግባት ትችላላችሁ !

Zoom link - https://us06web.zoom.us/j/85654129358?pwd=M0ZlQlUvTi8zNmp4ajVjZ0lzQnI2QT09

Youtube live link - https://www.youtube.com/live/MLLls_4MEt0?feature=share

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

በራስ መተማመን !

በዛሬ
ፈንዲሻ ሰዓታችን የምንወያይበት ርዕስ ነው !

በህይወታችን ላይ የምንፈልገውን ዉጤት ለማምጣት ከፈጣሪ ቀጥሎ በራሳችን ማመን የግድ ይለናል !

እንዴት ነዉ ታዲያ በራስ መተማመኔን የማሳድገዉ ካላችሁ ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይቭ እንገናኝ

📍በነፃ መሳተፍ የምትችሉበትን የ ‘Zoom’ እና ዩቲዩብ ሊንክ ሰዓቱ ሲደርስ በዚሁ ቻናል እንልካለን ይጠብቁ !

ልዩ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተዉ ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

ታላቁን ፈጣሪ ይዘህ 😃

ለታላቁ ፈጣሪህ የችግርህን ትልቅነት ከምትነግረው ለታላቁ ችግርህ የፈጣሪህን ታላቅነት ንገረው።

እህቴ ለፈጣሪ 'ያጋጠመኝ ችግር እኮ ከባድና አስፈሪ ነው እንዴት እንደምወጣው አላውቅም' ብለሽ ከምትነግሪው፤ ለገጠመሽ ችግር 'አንተ እኮ አታስፈራም ሀያሉ ፈጣሪ ፊት ሁሉም ነገር ቀላል ነው' ብለሽ ንገሪው።

ጣፋጭ ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Inspire Ethiopia

🥏 ከመጥፎ ልማዶች ለመላቀቅ !

እንዴት አድርጌ ላቁም የምንል ከሆነ መጀመሪያ ለምን ማቆም እንደምንፈልግ ለራሳችን ብዙ ምክንያቶች መደርደር አለበን፤ ምክንያቶቹ ልባችንን አልፈው ሲገቡና ሲያሳምኑን ያኔ ለማቆም አይከብደንም።

ነገር ግን አንድ ነገር እናስታውስ በሂደት የጀመርነውን ልማድ በሂደት ነው ምናቆመው።

በሱስ ውስጥ 4 ዓመት የቆየ ሰው በ 2 ዓመት በሂደት እየቀነሰ እየቀነሰ ይሄዳል እንጂ ለምን ባንዴ አላቆመውም ብሎ ራሱን ማስጨነቅ የለበትም። 'ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም' አይደል የሚባለው? 😁

ደስ የሚል ምሽት ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…
Subscribe to a channel