islamic_quate | Unsorted

Telegram-канал islamic_quate - Islamic quotes

518

Subscribe to a channel

Islamic quotes

🎁 የሻዕባን ልዩ ማስታወሻ

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
እንደሚታወቀው መልካም ስራችን በአሱር ወቅት፣ በየ ሳምንቱ ወደ አላህ ይሄዳል ይህ ሁሉም ተድምሮ በዚህ በሻእባን ወር ላይ ይወጣል። ወሩን አስደንጋጭ የሚያደርገውም ይሄ ነው። ይሄ ማለት ያለፈው ረመዳን በዚህ ወር ነው ሚወጣው፣ ሃጅ ያደረግነውም፣ሶደቃችን አሁን ነው የሚወጣው። ለዚህም ነው ነብያችን ይሄንን ወር አብዘሃኛውን እንደፆሙት የተነገረው። ሰራዎቸም ፆመኛ ሁኜ እንዲወጡልኝ ፈልጌ ነው ብለዋል። እናታችን አይሻ እንደዘገበችው የአላህ መልእክተኛ ከረመዳን ውጭ እንደ ሸእባን የበለጠ ወሩን የፆሙት ወር የለም ብለዋል። ትልቁም ትኩርታቸው በዚህ ወር ስራችን ወደ አላህ ስለሚወጣ ነው።

የተከበራችሁ ወንድም እህቶቸ በዚህ ወር ውስጥ በድብቅም በግልፅም፣ ትንሽም ይሁን ትልቅ መጥፎም መልካምም ስራዎቻችን ናቸው የሚወጡት። ስለዚህ አንዘናጋ ባለፈው ወንጀላችን ከአላህ ጋር ልንታረቅና የወደፊቱንም ህይወታችንን ለማስተካከል ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል። ልንዘናጋ አይገባም ለነብያችን እንኳ አላህ ምን እንዳላቸው እንመልከት

وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ
ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ እያላቸው ነው።


ሽእባን ማለት የረመዳን መዘጋጃ ነው። ይሄን ወር ነፍሳችንን ልናዘጋጅበት፣ ከወንጀል ልንርቅበት፣ልንፆም፣ዚክር ልናበዛ፣ለይል ልንቆም፣ ያበላሸናቸውን ነገሮች ልናስተካክልበት ይገባል። ያሲሆን ረመዳንንም መጠቀም እንችላለን። ነፍስያችንን ማሰልጠኛ የሆነ ወር ነው።

የሻእባን አጋማሽ ሲሆን አላህ(ሱብሃነወተአላ)ለግርማ ሞገሱ ለክብሩ በተገባው መልኩ ወደሰማ አዱንያ ይወርድና ባሮችን በሙሉ ይምራቸዋል። ሁለት ሰዎች ሲቀሩ ብለዋል ነብያችን

1.አንደኛ በአላህ የሚያጋራ የሚያሻርክ ነው። መሽሪክን አላህ አይምረውም። እንደማይምርም አላህ አጠንክሮ ተናግሯል።

2.ሁለተኛ ሁለት የተጣሉ ሰዎችን አይምራቸውም። ሱብሃናልህ! የነዚህን ሰዎች ሰራቸውን እስኪታረቁ ድረስ አቆዩት፣ አታምጡት ይላል አላህ ሱብሃነ ወተዓላ። እስካልታረቅን ደረስ አላህ ምህረተን ይይዝብናል ማለት ነው። ይሄም መሆኑ ለዛ ለታላቅ ለራህመት ወር ለረመዳን እንድንዘጋጅ ነው።

ነብያችን(ሰለላሁአለይሂ ወሰለም)ታላቅ ወር ነው ርመዳን መጣላችሁ እያሉ ሶሃቦችን ያበስሯቸው ነበር። በውስጧም ያለች አንድ ውድ ለሊት አለች ኸይሯን ያገኝ ኸይራን በሙሉ አግንቷል።ኸይሯን የተነፍገ ደግሞ ኸይርን የተባለን ነገር ተነፍጓል አሉ። ለዚህ የተከበረ ወር ዝግጅት የሚደረገው በሸእባን ወር ውስጥ ነው። ስለዚህ ረመዳን ሊመጣ ትንሽ ቀናት ነው የቀረው። ስራችንም ወደ አላህ ይወጣል ሲባል ሊያስደነግጠን ይገባል ምን ያክል ነው መልካም ስራችን መጥፎ ስራችንስ ምን ያክል ነው የሚለው ሊያስጨንቀን ይገባል። ምን ያክሉ ነው አላህን በመታዘዝ የተሞላው ምን ያክሉስ ነው በመጥፎ ነገር የተሞላው። ራሳችንን እንፈትሽ። ኢስቲግፋር ተውበት እናድርግ። ወላሁ አእለም



🚨ሼር ሼር ሼር እናድርገው! ብዙ ሰው ሚዘናጋበት ወር ነው።

Читать полностью…

Islamic quotes

@DailyAyaBot ➔ 18:87

Читать полностью…

Islamic quotes

መልካም አዳር❤


ትላንት ስላልለቀኩ ይቅርታ💔

Читать полностью…

Islamic quotes

ሻዓባን 4


{ إِنَّ ٱللَّهَ لَا یَغۡفِرُ أَن یُشۡرَكَ بِهِۦ وَیَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَ ٰ⁠لِكَ لِمَن یَشَاۤءُۚ وَمَن یُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَـٰلَۢا بَعِیدًا }
[Surah An-Nisāʾ: 116]



አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈፅሞ አይምርም። ከሽርክ በታች ሌላ ያለውን . 116ጥፋት ግን ለሚሻው ሰው ይምራል። በአላህ የሚያጋራ ሰው ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ

ያሉት አናቅፅ የወረዱበት ምክንያት፦ ጡዕመት ቢን ኡብይሪቅ (105-116)ከሴቶች ምዕራፍ ከ የተባለ ሰው ቀእዳህ ከተባለው ሶሃባ ቤት ልብስና ዱቄት ከሰረቀ በኋላ እንዳይታወቅበት አንድ አይሁዳዊ ቤት ውስጥ ይደብቀዋል። ሆኖም በተደረገው ክትትል ንብረቱ ከደበቀበት ቦታ ተገኘ። ንብረቱ የተገኘበት አይሁድም ጡዕመት ቢን ኡብይሪቅ እንዳስቀመጠው አስመስክሮ ተናገረ። የጡዕመት ዘመዶች ግን ጡዕመት ሌባ እንዳልሆነ ከደሙ ንፁህ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ነብዩ ለጡዕመት ጥበቃ እንዲያደርጉለት አማላጅ ሆነው ቀረቡ። በዚህ ወቅት ነበር ይህ አንቀፅ የወረደው። ከዚያም ይሀ ግለሰብ ወደ መካ ሸሽቶ ፈረጠጠ። እምነቱንም ቀየረ በመካ ቆይታውም የለመደውን ሌብነት አጧጡፎ ቀጠለና በመጨረሻም እንደለመደው በሌሊት ለመስረቅ የሰው ቤት ሲሰብር ግድግዳው ወድቆበት ሞተ። (ዋሒዲ፤ ኢብኑ ከሲር፤ ኢብኑልጀውዚ እና ሱዩጢ)



Andulkarim 🇵🇸✍️

Читать полностью…

Islamic quotes

የሐጅ ኢሕራም ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?

Читать полностью…

Islamic quotes

ወደ አላህ የተመለሱ ሴቶች እንባ


ኢብኑ ቁዳማ (አትተዋቢን) በተሰኘው መጽሀፋቸው ውስጥ እንዳስነበቡት መጥፎ የሆኑና ከአላህ መንገድ የወጡ ሴቶች :- አንዲት ሴት ለረቢዕ ኢብኑ ኹሠይም ዘንድ በቅርብ እንድትገላለጥና እንድትፈታተነው አነሳሷት። ይህን ያደረገች እንደሆነም አንድ ሺህ ዲርሀም እንደሚሰጧት ቃል ገቡላት

እሷም ግዜ ወስዳ በጉዳዩ ላይ ተዘጋጀችበት። በቻለችው ሁሉ ተኳኳለች ተቆነጃጀች ተበጃጀች። ምርጥ ያለቺውን ሽቶ ሁሉ ተቀባች። ምርጥ የሆነ ልብሷንም ለበሰች።

ከዚያም አርረቢዕ ወደ መስጊድ ሲመጣ መንገድ ለይ ጠበቀችና ተፈታተነቺው። እሱም ተመለከታት። ሁኔታዋ አስደነገጠው። እርቃኗን ለማየት በሚያስችል መልኩ ነበር ፊትለፊቱ የቆመቺው።

ረቢዕም ባያት ግዜ እንዲህ አላት :- አንቺ ሴት አሁን ወረርሺኝ ነገር ወርዶብሽ ይህን ገላሽንና ቆዳሽን ቢቀያይረውስ?...በዚህ ባለሽበት ሁኔታ ድንገት የሞት መልአክ መቶ የደም ስርሽን ቢበጣጥሰውስ?... መቃብር ውስጥ የገባሽ ዕለት ነኪርና ሙንከር በጥያቄ ቢያጨናንቁሽ ምን ሊውጥሽ ነው?...አላት።

ረቢዕ የተናገረው ነገር ከጆሮዋ አልፎ ልባን ነካ። ወዲያውኑ #እሪ_ብላ_ጮከች። አለቀሰች። ከዚያም ፈጥና ወደ ቤቷ ተመለሰች። ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ አላህን ወደ ማምለክ ፊቷን አዞረች። እስከ እለተ ሞቷ ድረስ በዚሁ ፀናች

ያረብ በዚህ ተግባር ላይ ያሉ እህቶቻችንን መልሳቸው ቅኑን መንገድ ምራቸው ወደ ደጃፍህ አስጠጋቸው🤲🤲

ኢላሂ እኛንም ጠብቀን ካንተ የሚያርቀንን ከኛ አርቅልን ጌታዬ ሆይ በቅኑ ጎዳና ላይ አፅናን ያረብ መዳረሻችንን ጀነት አርግልን

#አሚን_አሚን🤲🥹


🥀🥀

Читать полностью…

Islamic quotes

👉🌊 በባህር የሰመጠችው  ጥቡቅ ጨዋ የሆነችዋ ሙስሊም ሴት አስተማሪ ታሪክ ይነበብ

⚔በባግዳድ እንሰሳት እያረደ ሥጋ በመሸጥ የሚተዳደር አንድ ሰው ነበር ገና ሳይነጋ በፊት ወደ ሱቅ ይሄድና የሚሸጠውን በግ አርዶ በማዘጋጀት ወደ ቤቱ ይመለሳል ።

🌕ፀሐይ ከወጣች በኋላ ደግሞ ተመልሶ በመውጣት ሱቁን ይከፍታል ያዘጋጀውን ሥጋ ለመሸጥ

ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ ሥጋውን አርዶ ሲመለስ በድቅድቅ ጨለማ በመመለስ ላይ እያለ በመንገዱ ላይ ከጨለማ ውስጥ የጨኸት ድምጽ ሰማ ባረደው የበግ ደም ልብሱ ተበላሽቶ ነበር ፈጠን ብሎ ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ አመራ ወዲያውኑ በተደጋጋሚ በጩቤ የተወጋ አንድ ሰው ላይ ወደቀ ሰውዬው ደሙ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሰው ነበር ጩቤውም ሰውነቱ ላይ እንደተተከለ ነው ጩቤውን ነቅሎለት።

🫴በእጁ ይዞ ሰውዬውን ለመርዳት ብሎ ሊሸከመው ተንደረደረ የስውዬው ደም ልብሱን አጠበው በዚሁ ሁኔታ ላይ እያለ ጨኸት የሰሙ ሰዎች ከያቅጣጫው ተሰባሰቡ ጩቤውን በእጁ ሲያዩና ልብሱ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን ሲያስተውሉ ሰውዬውን የገደለው እሱ ሰለመሆኑ እርግጠኛ ሆኑ ።

🔫ከዚያም እንዲገደል ወሰኑበት ግዲያው ወደ ሚፈፀምበት ቦታም ወሰዱት እንደሚገደል እርግጠኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ድምፁንሸ ከፍ አድርጎ ጮኸ ሰዎች ሆይ ‼️ወሏሂ ይህንን ሰውዬ እኔ አልገደልኩም ነገር ግን ከሀያ አመት በፊት ሰው ገድዬ ነበር በዚህ ወንጀል ምክንያት ዛሬ ቅጣት እየተፈፀመበኝ እንደሆነ ይገባኛል አላቸውና ታሪኩን ማውጋት ጀመረ

🚢 ከሀያ ዓመት በፊት በባህር ላይ ጀልባ ሰዎችን የማመላልስ ወጣት ነበርኩኝ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሀብታም ወጣት ከእናቷ ጋር ሆነው ወደ ባህር ማዶ ለመሻገር መጡ እኔም አሻገርኳቸው በሁለተኛው ቀንም መጡና ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ አሻገርኳቸው ቀናት አለፉ ልቤ በዚህች ወጣት ላይ ተንጠለጠለ ወደድኳት እሷም ወደደችኝ እንዲድሩልኝ ብዬ ለአባቷ ሽማግሌ ብልክም በድህነቴ ምክንያት ጥያቄዬን ውድቅ አደረጉት።

ከዚህ እሷም ምን እንደገጠማት አላውቅም ብቻ ቀረች ተጠፋፋን እሷንም ሆነ እናቷን ለረጅም ጊዜ ማግኘት አልቻልኩም ልቤ ግን እየወደዳት ኖረ።

👉⛴ ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ነበር አንድ ቀን ጀልባዬን ይዥ ተሳፋሪዎችን በመጠበቅ ላይ እያለሁ አንዲት ሴት ትንሽ ልጅ ይዛ መጣችና ወደ ዚያኛው ማዶ እንዳሻግራት ጠየቀችኝ ተሳፍራ መሃል ባህር ላይ በደረሰች ጊዜ ተመለከትኳት ያቺ አባቷ የለያየን ሴት መሆኗንም አወቅኩኝ ሰላገኘኋት ደስ አለኝ ያለፈውን ጊዜ አስታወስኳት

🍃 ውዴታ መቼስ የማይሸር እዳ ነው እሷ ግን ሰርዓት ባለው መልኩ አናገረችኝ እንዳገባችና የያዘችውም ህፃን መሆኑን አስረዳችኝ ቀስ በቀስ ሸይጣን በኔ ውስጥ ሥራውን ይሰራ ጀመር መጥፎ ነገርም አሳሰበኝ ተጠጋኋት ጮኸችብኝ አላህን እንድፈራ አስታወሰችኝ ።

🧿ሆኖም ግን ማስጠንቀቂያዋ ምንም ግድ አልነበረኝም እሷ የቻለችውን ያህል ትከላከል ትገፋኝ ጀመር ህፃን ልጇ ያለቅሳል ይህንን ባስተዋልኩ ጊዜ ይበልጥ እልህ ያዘኝ ልጇን ወሰድኩና ወደ ውሃው አስጠጋሁት ፈቃደኝነቷን ካልገለፀችልኝ አሰመጥዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት ።
አለቀሰች ለመነችኝ ተማፀነችኝ አልሰማኋትም የልጁን ጭንቅላት ይዥ ውሃ ውስጥ እየነከርኩ እየመለስኩ አስፈራራታለሁ እሷ ታለቅሳለች ትማፀናለች አልራራሁላት ልጁን አጥብቄ ውሃው ውስጥ ነከርኩት ትንሽም አቆየሁት እሷ ታያለች ክስተቱን ላለማየት ዐይኗን ትሸፍናለች ልጁ ተንፈራፈረ ተልፈሰፈሰ ከውሃ ውስጥ ሳወጣው በድን ሆኗል ሞቷል በድኑን ውሀሰ ውስጥ ወረወርኩት ከዚያም ተነሳሁና ወደሷ ሄድኩኝ ።

💧በቻለችው ሁሉ ተከላከለችኝ ጮሃ አለቀሰች ፀጉሯን ይዠ በመጎተት ወደ ውሃ አሰጠጋኋት አየነከርኩ አስወጣታለሁ ደጋግሜ ባደርግም በእንቢተኝነቷ ፀናች በፍፁም አላደርገውም አለች እጄን ሲደክመኝ ነክሬ አቆየኋት እሷም እንደ ልጇ ሁሉ ተንፈራፈረች ከዚያም ፀጥ አለች ሞተች ።

🌊ውሃው ውስጥ ወረወርኳትና ተመለስኩኝ ይህንን ወንጀሌን አንድም ሰው ሳያውቅ ለዓመታት ኖርኩኝ ቢያቆይ እንጂ የማይረሳው የሆነው ጌታ ዛሬ ያለ ወንጀሌ ያዘኝ አላቸው ሰዎች ታሪኩን ሲሰሙ አለቀሱ አንገቱ ተቆርጦ እንዲገደልም አዘዙ ።

🫵አሏህ በዳዮች የሚፈጽሙትን ወንጀል የሚረሳ አይደለም እስቲ የዚህችን ወጣት እናስተውል ዐይኗ እያየ ልጇ ለፊቷ ተገደለ እሷም ሞተች ይህ ሁሉ ለምን ሆነ ክብሯን ከማስደፈርና በዝሙት ከመዋረድ በሞት መገላገልን መረጠች ።

🥀ይህ ከጨዋ ሴቶች ታሪክ መጠነኛ ማሳያ ነው ብዙ ትምህርትም እናገኝበታለን ።

Читать полностью…

Islamic quotes

ማ‌‌ስ‌‌ታ‌‌ወ‌‌ሻ‌‌
ሸ‌ዕ‌ባ‌ን‌ ከ‌መ‌ው‌ጣ‌ቱ‌ በ‌ፊ‌ት‌
:
የቀደመ የረመዳን ቀዷ ያለበት መጪው #ረመዳን ሳይገባበት ቀዷውን አውጥቶ ይጨርስ። ቀዷ ማውጣት እየቻለ ሳያወጣው ተከታዩ ረመዳን የገባበት ሰው: ‐
⚀ ኃጢኣተኛ ይሆናል፤
⚁ ቀዷእ ማውጣቱ አይቀርለትም፤
⚂ ፊድያ (ቤዛ) ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል። ፊድያው ለአንድ ቀን አንድ እፍኝ ነው። አመቱ በጨመረ ቁጥርም ፊድያው ለአንድ አመት አንድ እፍኝ እየጨመረ ይመጣል።
:
በህመም፣ በማጥባት፣ በእርግዝና ወይም በሌላ ሸሪዓዊ ምክንያት ቀዷውን መክፈል ያልቻለ ሰው ግን በተመቸው ጊዜ ብቻ ቀዷ ማውጣት ይበቃዋል።
ይህ የሻፊዒዮች እና የአብዝሃኛዎቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው!
ረመዷን ሊገባ ነውና እንተዋወስ!

Читать полностью…

Islamic quotes

ጥር 25፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት የሚካሄደው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን የፍፃሜ ውድድር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን የውድድሩ ታዳሚዎች በብዛት ወደ ስታዲየሙ እየገቡ ነው።

ዝርዝር መረጃውን እየተከታተልን እናቀርባለን።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።

@yasin_nuru

Читать полностью…

Islamic quotes

መልካም አዳር❤

Читать полностью…

Islamic quotes

﴿مَّا يَفۡتَحِ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ مِن رَّحۡمَةٖ فَلَا مُمۡسِكَ لَهَاۖ وَمَا يُمۡسِكۡ فَلَا مُرۡسِلَ لَهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ﴾
[فاطر: 2]

🎧 القارئ محمد صديق المنشاوي
📚 تفسير الآية هنا 💚👇
https://surahquran.com/aya-2-sora-35.html

Читать полностью…

Islamic quotes

ثَمَٰنِيَةَ أَزْوَٰجٍۢ ۖ مِّنَ ٱلضَّأْنِ ٱثْنَيْنِ وَمِنَ ٱلْمَعْزِ ٱثْنَيْنِ ۗ قُلْ ءَآلذَّكَرَيْنِ حَرَّمَ أَمِ ٱلْأُنثَيَيْنِ أَمَّا ٱشْتَمَلَتْ عَلَيْهِ أَرْحَامُ ٱلْأُنثَيَيْنِ ۖ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
﴿الأَنۡعَامِ؜ ١٤٣

“Eight males and females; one pair of sheep and one of goats”; say, “Has He forbidden the two males or the two females, or what the two females carry in their wombs? Answer with some knowledge, if you are truthful.”
{An interpretation of "Al-An'aam: The Cattle", Sura 6 Aya 143}

Читать полностью…

Islamic quotes

የአሕዛብ ምዕራፍ الأحزاب 33:56

۝إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا۝

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡


/channel/islamic_quate
/channel/islamic_quate

Читать полностью…

Islamic quotes

فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ لَعَنَّٰهُمْ وَجَعَلْنَا قُلُوبَهُمْ قَٰسِيَةًۭ ۖ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ ۙ وَنَسُوا۟ حَظًّۭا مِّمَّا ذُكِّرُوا۟ بِهِۦ ۚ وَلَا تَزَالُ تَطَّلِعُ عَلَىٰ خَآئِنَةٍۢ مِّنْهُمْ إِلَّا قَلِيلًۭا مِّنْهُمْ ۖ فَٱعْفُ عَنْهُمْ وَٱصْفَحْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
﴿المَائـِدَةِ؜ ١٣

So We cursed them because of them constantly breaking their covenant, and hardened their hearts; they shift the Words of Allah from their places, and have forgotten a large portion of the advices that were given to them; and you will constantly learn of deceits from them, except a few; so forgive them and excuse them; indeed Allah loves the virtuous.
{An interpretation of "Al-Maaida: The Table", Sura 5 Aya 13}

Читать полностью…

Islamic quotes

Aselamu Aleykum Werahmetulahi Weberekathu


🍂🌹ነገ የጁምአ ቀን ነው🌹🍂
~~~~

🍂ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም )እንዲህ ብለዋል ፡-🍂
አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ
፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡

ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል።

እነሱም
🍃1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
🍃2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
🍃3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣
🍃4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
🍃5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል።

በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል።

በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ።

የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

🍂🌱የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።🌱

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:910)

[የጁመአ ቀን ሱናወች] ~‌
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

  اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ


@M_S_T_H_N.........

Читать полностью…

Islamic quotes

የሩሕ ቀለብ🤌

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ      ⌲  
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ
መልካም ቀን ✨

Читать полностью…

Islamic quotes

قَالَ أَمَّا مَن ظَلَمَ فَسَوْفَ نُعَذِّبُهُۥ ثُمَّ يُرَدُّ إِلَىٰ رَبِّهِۦ فَيُعَذِّبُهُۥ عَذَابًۭا نُّكْرًۭا
﴿الكَهۡفِ؜ ٨٧

He submitted, “Regarding one who has done injustice, we shall soon punish him – he will then be brought back to his Lord, Who will punish him severely.”
{An interpretation of "Al-Kahf: The Cave", Sura 18 Aya 87}

Читать полностью…

Islamic quotes

ሐዲሥ አል-ቁድስ


የመጀመሪያው ፍጥረት

ዑባደት ኢብኑ ሷሚት ረ ዐ እንዳስተሊለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) የሚከተለውን ሲናገሩ ሰምቻለው ብለዋል:-

"አላህ መጀመሪያ የፈጠረው ብዕርን ነው። እርሱንም #«ጻፍ» አለው። “ጌታዬ ምንድ ነው የምጽፈውን?” አለ። #«እስከ_ዕለተ_ትንሳኤ_ያለውን_የማንኛውንም_ነገር_ውሳኔና_ሂደት» ተባለ።"

Читать полностью…

Islamic quotes

في بعض ألأحيان عليك أن تمر بألأسوأ حتئ تصل إلئ ألأفضل كن صبورآ

አንዳንድ ጊዜ ምርጡን ለመድረስ በጣም መጥፎውን ማለፍ አለብህ፣ ታጋሽ ሁን😞

           🧡

Читать полностью…

Islamic quotes

فِى مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍۢ مُّقْتَدِرٍۭ
﴿القَمَرِ؜ ٥٥

Seated in an assembly of the Truth, in the presence of Allah, the Omnipotent King.
{An interpretation of "Al-Qamar: The Moon", Sura 54 Aya 55}

Читать полностью…

Islamic quotes

አህባቢ ይሄን ታሪክ በደምብ አንብቡት ዝምብላቹ እንዳታልፉት

Читать полностью…

Islamic quotes

.
ምንም ያህል ውሃ ቢጠማችሁ መርዝ እንደማጠጡት ሁሉ....

ምንም ያህል ብቸኝነት ቢሰማችሁ...
ወደ ተዋችሁ ሰው አትመለሱ 👌

Читать полностью…

Islamic quotes

ረሱል (ﷺ)አዛኞችን አዛኙ ያዝንላቸዋል። በምድር ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል።”
አቡ ዳውድ፡ (4941) ቲርሚዚ፡ (1924)

Читать полностью…

Islamic quotes

كَلَّا ۖ بَل لَّا تُكْرِمُونَ ٱلْيَتِيمَ
﴿الفَجۡرِ؜ ١٧

Not at all – but rather you do not honour the orphan.
{An interpretation of "Al-Fajr: The Dawn", Sura 89 Aya 17}

Читать полностью…

Islamic quotes

🖋ጌታዬ ከኔ ጋር ነዉ 👍👂

🍂ክፍል~8

«በኡስታዝ ካሊድ ክብሮም
:¨·.·¨: ❀ ሼርር↓↓
·. ┈┈••◉❖◉●••┈,,
/channel/islamic_quate
/channel/islamic_quate

Читать полностью…

Islamic quotes

@DailyAyaBot ➔ 6:143

Читать полностью…

Islamic quotes

🫀የምሽት ስንቅ 🫀
ለቀልብዎ

Читать полностью…

Islamic quotes

@DailyAyaBot ➔ 5:13

Читать полностью…

Islamic quotes

መልካም አዳር❤

Читать полностью…

Islamic quotes

አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱሊሂ ወበረካቱ እንዴት ዋላቹህ የተከበራቹ የ አላህ ባሮች☺️

እነኚን ውብ የሆኑ አባያና ኪማር ከፈለጋቹ
@Umukholsum
@atika_ay
👆👆👆👆👆👆በውስጥ አናግሩኝ

Читать полностью…
Subscribe to a channel