"لا تتردّد في الرجوع إلى الله حتى وإن كثرت معاصيك، فالذي سترك وأنت تحت سقف المعصية لن يخذلك وأنت تحت جناح التّوبة 🤍
Читать полностью…አንድ ሙስሊም ለሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ነው ።
አይበድለው፣ እርዳታን አይንፈገው፣ አይናቀውም....
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)❤️
@islamic_quate
ከመናገርህ በፊት አስብ
ቃላት ከመሰንዘርህ በፊት መዝን
ምክኛቱም የተናገርከው ነገር የሰውን ልብ ሊጎዳ ይችላል !!
ምናልባት ይቅርታ ብለን የነሱን ይቅርታ ልናገኝ እንችላለን !
ግን ይቅርታ ነገሩ እንድንተወው እንጂ ወደነበረበት አይመልስም !!
የፈሰሰ አይታፈስ ትላንት አይመለስ ከመናገርቻን በፊ እናስብ ብለን መለስ !
🦋Ruhi🦋......✍️
ያ ዝምታህን የማይረዳ... ንግግርህን ሊረዳ አይችልም... ንግግርህን የማይረዳ... ደግሞ አስተሳሰብህን ሊገምት አይችልም🤔
@islamic_quate
ከመጠን በላይ አታስብ ግን
ብዙ መሃርታን ከአላህ ጠይቅ
ምክንያቱም አላህ በኢስቲغፋር እንጂ በመጨነቅ ብቻ በሮችን አይከፍትልህም
@islamic_quate
ከመሞቱ በፊት ምን ነበር የተናገረው? ምን ነበር የፃፈው ይላሉ ሰዎች🤔
ሞት ድንገት ነው
ንግግርህን አሁንም አሁንም አሳምር።
@islamic_quate
😁ፈገግ ያደርጋል!😁
አንድ አዲስ ሰለምቴ ጓደኛዬን መስጂድ እንዴት ነበር ? ሰገድክ ? አልኩት ።
አዎ ሰግጄ ፀለይኩኝ አለ ።
ከሰላት በኋላ ዐሪፍ ስብከት ሰማህ ?
"ምንም አይልም ። ሼኪው የሆነች ዱኒያ የምትባል ሴት ክዳቸዋለች መሰለኝ ። ዱኒያ ከሃዲ ናት ፣ ተጠንቀቋት ፣ አታባሯት ፣ አታላይ ናት ምናምን ሲሉ በማይገባህ አትግባ ስላልከኝ ቶሎ ወጣሁኝ ።"😂😂😂
ከአብዱረህማን አማን....✍
........የቀጠለ
11💦 ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡
12💦 የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡
13💦በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡
14💦ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡
15. 💦ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡
ይቀጥላል...
@islamic_quate
በጀነት ውስጥ ...
ቁርአንን እንስማለን❤️🩹
በውዱ ነቢያችን በሙሀመድ ድምፅ 😍
ይሄንን የፈለገ በሳቸው ላይ ሰለዋት ያውርድ💚
ሰሉ አለይሂ ወሰሊሙ ተስሊማ!🥰
@islamic_quate
ሰዎች ከአንተ እንዲማሩ እና አንተም ከእነሱ እንድትማር ተቀላቀላቸው። ሰዎች ልክ እንደ ዝግ ሳጥኖች ሲሆኑ
ብርቅዬ የሆኑ ክምችቶችን በውስጣቸው ታገኛለህ … ከፊሉ ባዶ እንኳን ቢሆኑ ለምን ባዶ እንደሆኑ ትማራለህ።🤔
@islamic_quate
✨በዱንያ ጉዳይ የበታቻችሁን ተመልከቱ።ከበላያቹ ያሉትን አትመልከቱ።ከበታቻችሁ ያሉትን መመልከት የተሻለ ነው ። ያን ጊዜ አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ለመመልከት ያግዛቹሀልና።
@islamic_quate
ጓደኝነት
ረሱል ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም❤ ) ሲናገሩ :-
" የመልካም ጓደኛ ምሳሌ ከሽቶ ነጋዴ ጋር ሲገናኙ
ካልዎት ገዝተው ፥ ከሌለዎት ; ከሽታው መልካም ጠረንን እንደሚያገኙ ያህል ነው :: "
( ሙተፈቁን ዐለይሂ )
ትክክለኛ ጓደኛ ማለት
~ እሱ ጋር መሆን ስታበዛ የማትሰለቸው
~ ስትለየው የማይረሳህ የሚናፍቅህ
~ ስትርቀው የሚቀርብህ ; የማይሸሽህ ካንተ
ላለመለየት የሚጥር
~ ላንተ ያለውን ውዴታ ከቃላት ይልቅ በተግባር
የሚገልፅልህ ነው ::
🌸
💜 አማኝ ተምር ይተክልና እሾህ ያፈራ
ይሁን? ብሎ ይፈራል። ሙናፊቅ ደግሞ
እሾህ ይተክልና ተምር ይጠብቃል።
(አልፉደይል ኢብን ዒያድ [ረሂመሁላህ])
🌷
=>ህይወት ሁሌም ጣፋጭ አትሆንም አንዳንዴም የጣፋጩን ጣዕም ለማወቅ መራራ መቅመስ ያስፈልጋል !
በተለይ ዱንያ ላይ ሁልጊዜ ደስታ ብቻ የሚጠብቅ ሰው ይህ ሰው ሞኝ ነው፡ ፡ እውነተኛ ደስታ ያለው አኼራነው !!
ነቢዩላህ ኢብራሂም(ዐ.ሰ) አባታቸው ሙስሊም ይሆኑላቸው ዘንድ ተመኙ
ነቢዩላህ ኑህ(ዐ.ሰ) ልጃቸው እስላም ይሆን ዘንድ ብዙ ታገሉ
ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) አጎታቸው ሸሀዳ እንዲይዙላቸው ለፉ
ለእኔና ለናንተ ግን ኢብራሂም(ዐ.ሰ), ኑህ(ዐ.ሰ) እና ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጠይቀው ያልሰጣቸውን ሳንጠይቀው ሰጠን 🥹
ታዲያ አልሃምዱሊላህ አንልምን?
አልሃምዱሊላህ ❤️🩹🙏🙏
@islamic_quate
ያረብ❤️🩹
የጠየኩትን ብትሰጠኝ ከእዝነትህ
ብትከለክለኝ ደሞ ከጥበብህ ነው
እኔ ግን ካንተ ደጃፍ ላይ ከመጠባበቅ መወገድን አልሻም!🤎
@islamic_quate
.........የቀጠለ
16.💦 ከአላህ (ሱብሀነ ወተአላ.) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡
17.💦 ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡
18💦. የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ አንጠራጠር፡፡
19.💦 ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ ዕድል ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡
20💦. የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡
አለቀ😊
@islamic_quate
🥀የትም መሄጃ በሌለህ በሱ ምድር ላይ እየኖርክ ወንጀል ስትሰራ ያይሃል። ወደሱ እስክትመለስ ጊዜ ሰጥቶህ ኃጢኣትህን ይደብቅልሃል። ከዚያም ለተውበት ይወፍቅህና ይቅር ይልሃል። በተውበትህም ይደሰታል። ኢስቲግፋር ስታደርግ ላንተ ያለው ውዴታ ይጨምራል። ክፉ ስራህን ወደበጎ ሀሰናት ይቅይርልሃል።
🥀☝️እሱ የላቀ የሆነው «አዛኙ ጌታህ አላህ ነውና!»
...
🥀🥀ሰባሀል ከይር ??
🦋Ruhi🦋......✍️