islamictrueth | Unsorted

Telegram-канал islamictrueth - ኢስላማዊ እውነታ

11751

ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

Subscribe to a channel

ኢስላማዊ እውነታ

የዚህን ሰዉዬ የአላህ ፍራቻ ለራሴ ተመኘዉ!

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አላህ በጣም ይደሰታል!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሊጋቡ ብለዉ እንተያይ ብለዉ ከዛም ዚና ሰሩ፤ ልጅቷ አግብታ ታዉቃለች ከፋራ አለዉ? ወይስ ተዉበት ብቻ ነዉ የሚያስፈልገዉ? እሱንስ ማግባት ትችላለች?

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አልሐምዱሊላህ ስርጭታችን ተመልሷል። ስላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

11555 ነሲሓ ቲቪ

📡 Satellite: Nilesat
Fequency: 11555 or 11554 
Polarization: Vertical
Fec. 5/6
Symbol rate: 27500

@nesihatv

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ «እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ» እያለ ይናገራል!

يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

«እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ»፡፡ [29:56]

إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

«ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ»፡፡ [21:92]

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ [21:25]

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

«ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም»፡፡ [51:56]

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

በዩናታን ጉዳይ ሙስሊሞች የሚሰደቡት ለምንድን ነዉ?

አንድ የፕሮቴስታንት አማኝ አስተማሪ ተሳደበ ብለዉ የሚሳደቡትና የሚወነጅሉት ሙስሊሙን። አመቱን ሙሉ በቤተክርስቲያን እና በዩቱብ ትልልቅ የሚባሉ የኦርቶዶክስ እምነት ሰዎች የሚሰድቡት ሙስሊሙን። የኛን የእምነት ተቋም የሚመራቹን እንምርጥላቹ የሚሉን እነሱ።

ቆይ ሙስሊሙ ምን ያድርጋቹ?

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

እስካሁን በነበረን የማኅበራዊ ሚዲያ ቆይታ በዋናነት ትኩረት አድርገን የተጠቀምነው ፌስቡክን፣ ቴሌግራምንና ዩቲዩብን ነው። በኛ ጥረት ሳይሆን በአሏህ ﷻ እገዛና ብዙ ሰው በነዚህ ፕላትፎርሞች በነበሩ የንጽጽር ዳዕዋዎች ተጠቅሟል። ለቁጥር እንኳን የማናቃቸው በርካታ ወገኖቻችንን እስልምናን ተቀብለዋል፥ አልሐምዱሊላህ። ይህ ሁሉ የአላህ እገዛ መሆኑን እና የኛን ደካማነት ደረጃ ልኩን ስለምናውቀው ቅንጣት አያኮራንም።
...
አሁን ላይ ለዳዕዋ የተሻለውና በርካታ ሰው ያለበት ቦታ ቲክቶክ ነው በሚል አንዳንድ ወንድሞች ጠቁመውን ከአመት በፊት ለመግባት ብንሞክርም የቦታው ለፋሂሻ ቅርብ መሆንና ቪዲዮ ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው ጊዜም የራሱ አድካሚ ነገር ስላለው ችላ ብለን ትተነው ነበር። አሁን ላይ ግን በላይቭ ትምህርቶች በኩል የምንሰማቸው ሹበሀዎች በርካታ ከመሆናቸው አንጻርና በዚህ ዙሪያም ምላሽ የሚሰጡ ወንድምና እህቶች ብዙ ባለመሆናቸው ምክንያት ለላይቭ ትምህርት ሲባል ቲክቶክ ላይ ያለውን ዳዕዋ ለመሞከር ወስነናል። አካሔዱን አይተን እንደሁኔታው እናስቀጥለዋለን ኢንሻአላህ።
...
ይህ ከሆነ ታዲያ ላይቭ ለመግባት በትንሹ 1,000 ፎሎዎር ያለው አካውንት ያስፈልጋልና ይህንን በመሙላት ረገድ የናንተ ሚና ወሳኝ ስለሆነ ወደናንተ አምጥተነዋል። ከዚህ በታች የኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድና የኡስታዝ አቡ ዩስራ የቲክቶክ አካውንቶች ይገኛሉ። እነሱን ሼርና ፎሎው በማድረግ አንድ ሺ እንሙላቸው። በአሏህ ﷻ ፍቃድ አንድ ሺ ሲሞላ በተለያዩ የንጽጽር አርዕስቶች ዙሪያ በቋሚነት ማስተማር የምንጀምር ይሆናል።

➭ የኡስታዝ አቡ ዩስራ አካውንት

abuyusrahidaya" rel="nofollow">http://tiktok.com/@abuyusrahidaya

➭ የኡስታዝ ኢልያህ አካውንት

eliyahmahmoud" rel="nofollow">http://tiktok.com/@eliyahmahmoud

➭ የእኔ ቲክቶክ

yahyaibnunuhe" rel="nofollow">http://tiktok.com/@yahyaibnunuhe

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ውበተ ኢስላም ፓምፕሌት
-------------

የኢስላምን ውበት የሚገልፅ ፓምፕሌት። 

ለሰለምቴዎች፣ ሙስሊም ላልሆኑ ወገኖት፣ ለሙስሊም ወንድሞች እህቶች የሚሆን

በየትምህርት ቤቱ የሚበተን ለተማሪዎች የተዘጋጀ

ሁዳ ሪሳላ ቁጥር 3
ውበተ ኢስላም

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አንድ ሙስሊም ቢታመም ፀበል መጠቀም ይችላል?

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሸሪዐዉ የሚያዘዉን ነገር ማጥበቃችን እንዲሁም ያግራራልን ነገር ማግራራት ግዴታችን ነዉ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የሰዶማውያን ተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት ግላዊና ማኃበራዊ የሚያስከትላቸዉ ችግሮች!

በአቡ ሀይደር

1) ከተፈጥሮአዊ ማንነት መጣረስን፡- ይህን ተግባር ንጹህ ህሊና ያወግዘዋል፡፡ ስሜታችንም አይቀበለውም፡፡ በዚህ ስራ ላይ መገኘት ከተፈጥሮ ስርአት መውጣት ነው፡፡

2) ወጣቱን አካል ማኮላሸትን፡- ወጣቶች ከወዲሁ እራሳቸውን ተጣማጃቸውን በመፈለግ በትዳር ካልታቀፉ፤ ለዚህ ተግባር በቀላሉ ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ ስሜታቸውም ያለ አግባብ ይባክናል፡፡

3) የዘር መቋረጥን፡- ዘር ሊገኝ የሚችለው በወንድና ሴት ጋብቻ እንጂ፤ በተመሳሳይ ፆታ አይደለም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰው ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ግንኙነትን ከቀጠለ ትውልዱ ቀጣይነት አይኖረውም፡፡ ዘር ይቋረጣል፡፡

4) የሴቶች ብሉሹነት፡- ባለቤቶቻቸው ፊታቸውን ወደ መሰል ፆታቸው ካዞሩ፤ ሴቶችም ስሜታቸውን ለማብረድ በመፈለግ ወደ ሐራም ተግባር የመዘፈቅ እድሉ የሰፋ ይሆናል፡፡

5) ያልተፈቀደ ግንኙነት፡- ከወንዶች ጋር ያንን አስቀያሚ ተግባር የለመደ ሰው፤ ወደ ሴቶችም ሲመጣ ስሜቱን ማርካት የሚፈልገው ዘር ከሚገኝበት ቦታ ሳይሆን፤ ከተወገዘው ሌላኛው ስፍራ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ብሉሹነት ነው፡፡

6) የቤተሰብ መበታተንን፡- ተግባሩ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ፤ የቤተሰብ ህይወት ይናጋል፡፡ በመሀከላቸውም ጸብና ጥላቻ ይሰፍናል፡፡ ህይወት ይበላሻል፡፡ ሌሎችም…

አላህ ወንድሞችንና እህቶቻችንን ከዚህ አስቀያሚ ተግባር ይጠብቅልን፡፡

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

መስክረውለታል። ዛሬም በሀገረ ኳታር የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ ሺዎችን ወደ ኢስላም እየጠራ ይገኛል። አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው ረጅም ሐያትም ይወፍቀው።

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

https://www.facebook.com/100003707505003/posts/2782473391886217/?flite=scwspnss

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ላልመለስ በሃሩን ሚዲያ ተዘጋጅቶ የቀረበ ልዩ ዶክመንተሪ ||ሃሩን ሚዲያ
https://youtu.be/1GGR1xDAgAM

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የአላህ እ*ርግ*ማ*ን በበደለኞች ላይ ይሁን!

ዘገባዉ እዉነት ከሆነ

https://www.facebook.com/100022948355060/posts/pfbid0279Bbt9WKNwwzKbiquCJ7eX7pqtKskwFWjzWnDbDWbqdEQ5p3MHC9XTjAqbyfG7Fzl/?app=fbl

የሳዑዲ ባለስልጣናት የሼክ ኻሊድ አል ራሺድ የእስር ቅጣት ለሁለተኛ ጊዜ አራዝመውታል።

የሳዑዲ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሼክ ኻሊድ አል ራሺድ ላይ የተላለፈውን የእስር ቅጣት 17 አመታትን በመጨመር ወደ 40 አመታት ከፍ አድርጓል።

ሼክ ኻሊድ አል ራሺድ መጋቢት 19 ቀን 2006 ከባለቤታቸው ጋር የዑምራን ጉዞ ሲያጠናቅቁ በመካ ነበር የታሰሩት።ለእስር የተዳረጉት ምክንያቱ ደሞ በዴንማርክ በረሱል(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ የተሰሩ ካርቱኖች በማውገዝ፣ የነቢዩ ክብር እንዲጠበቅ የሳዑዲ ፖሊሲዎችን በመተቸታቸው ነበር ።

በሱና በመሰሎቹ ላይ የግፍ በትር በሚያሳርፍ ላይ እንዲሁም የሀገሪቷን ክብርና የእምነት እሴቷን በሚጥሱ ከላይ እስከ ታች በሚገኙ ባለስልጣን ላይ የአላህ ቁጣ ይዉረድባቸዉ። ሀገሪቷን፣ ሸሪዐን፣ ዑለማዎቻችንን የሚያከብሩትን አላህ ይሹምልን።

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ከሞት በኃላ መቀስቀስና ህይወት ስለመኖሩ ለሚጠራጠሩ...

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ለሶላት ስንቆም ነወይቱ ዑሰሊ... እያሉ መጀመር?

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ቁርአን ስለ ክርስትና ተሳስቷል?

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ፈትዋ

በአንድ ወቅት አንድ ዓሊም ስለማይሰግድ ሰው ፈትዋ/ብይን ተጠየቁ፡፡ እርሣቸውም ‹የማይሰግድ ሰው ብይኑ ወደ መስጊድ እጁን  ይዘኸው መሄድ ነው፡፡› በማለት መለሱ፡፡
ከዱላ በፊት ደዕዋ
ከቁጣ በፊት ሒክማ
ከዘለፋ በፊት እዝነቱ
ከፍርድ በፊት ማጣራቱ ይቅደም የሚል መልዕክት ያዘለ ነው ብይኑ፡፡
.
/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

https://www.facebook.com/100003707505003/posts/2818974004902822/?flite=scwspnss

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አንዳንድ የማይደረጉ(የአላህ ነገራቶችን) ወደ አላህ ባሪያ ማስጠጋት ሽርክ አደለም። ቁርአን ላይ ጅብሪል(አለይሂ ሰላም) ለመርየም ልጅ ሰጥቷል ብሎ ለቀጠፈዉ ግለሰብ ሼይኽ ኤልያስ እንዲህ መልሶለታል!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ኡስታዝ ስዑድ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ይፈልጋል

በበርካታ ዳእዋዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናውቀው እንዲሁም ቤተል መስጂድ ላይ በዳእዋው የምናቀው ኡስታዛችን ኡስታዝ ሱዑድ አብዱ በአይን ግፊት አይኖቹ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አስቸኻይ ህክምና ካላደረገ የአይኖቹን ብሌኖቹን ሊያጣ እንደሚችል ጅዳ ሓይል ሓይፋ ዘጋፍ ሙስተሽፋል ዑዮን ሀኪሞች ነግረውታል ።

አዲስ አበባ ላይ አንድ ግዜ የቀዶ ጥገና ህክምና ያደረገ የነበረ ሲሆን ውጤት ባለማምጣቱ ወደ ሳውዲ ለህክምና ሄዶ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ከቅርብ ጓደኞቹ ማወቅ ትችሏል። ለህክምናው ወደ 750ሺ የኢትዮጲያ ብር የተጠየቀ ሲሆን ኡስታዝ ስዑድ ይህንን ገንዘብ ከፍሎ መታከም እንዳልቻለ ከቅርብ ወንድሞች ሰምተናል። ስለዚህ የኡስታዝ ስዑድ ዓይኖችን ለመታደግ ገንዘቡ መሸፈን የምትችሉ አህለል ኸይሮች ኡስታዝ ስዑድን ከታች ባሉት አካውንቶች መርዳት ትችላላችሁ።

📌ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
📌1000243569749
📌ሱዑድ አብዱ

በስልክ ለማግኘት

+966 53 505 4896

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አይንአዉጣነት፣ ደረቅ መሆንና...

የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-

«የኢስላም ውበቱ ሐያዓ(ዕፍረት) ማድረግ ነው።» [ኢብኑ ማጃህ]

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ጣፋጭ አቀራር #21

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

በቁርአን ላይ አላህ እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ የሚል የለም ላለዉ ሰዉዬ አድርሱለት!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አንድ ሰዉ በቀደር አመነ የሚባለዉ እንዴት ነዉ?

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

╔══════════════╗
የንፅፅሩ ንጉስ ዶክተር ዛኪር ናይክ
╚══════════════╝

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

ብዙዎች የንፅፅሩ ንጉስ ሲሉ ያሞካሹታል። ያየውና የታዘበውን ያለ ምንም ይሉኝታ ከቁርአንና ከሐዲስ በተቀዳ አንደበት ፍርጥርጥ አድርጎ የሚናገር ሲሉም ያንቆለጳጵሱታል። የእስልምናን እውነታ ፍትሃዊነትንና ጥበብን ለመላው የሰው ልጅ ለማድረስ ሌት ተቀን የሚባትል በቀን ውስጥ ከሶስት ሰዐት በላይ የማይተኛ፣ መድረክ ላይ ሲወጣ ለሚናገራቸው ንግግሮች እጅግ ጥንቁቅ የሆነ ሰው ነው በማለት ያሞግሱታል። በእርግጥም ይህ ሁሉ ለእርሱ ይገባዋል። በእውቀት የሞገተ፣ ወደቀጥተኛው መንገድ የተጣራ፣ ስለኢስላም የሰበከ አንደበተ ርቱዕ ነው። እርሱ ሱፍና ከረባት የማይለየው ዘናጭ፣ የአደምና ሃዋ መገናኛ በሆነችው ሃገረ ህንድ የተወለደው ዶክተር ዛኪር ናይክ ነው።

ገና በለጋ ዕድሜው በህክምና የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን ቢይዝም ዓላማው ትልቅ ነበርና ከስጋ ይልቅ የነፍስ ሃኪም መሆን ይበልጥብኛል በማለት እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1991 ሁሉን ነገር ትቶ የዳዕዋ ስራውን ሀ ብሎ ጀመረ። እርሱ ለቁጥር የሚታክቱ ልጆችን የእውቀት አባት ያደረገውን ኢንተርናሽናል ኢስላሚክ ትምህርት ቤት ያቋቋመ፣ ስለ ኢስላም ብዙ የተቀመረበትን ኢስላሚክ ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ የምርምር ማዕከል የገነባ ከሁለት መቶ ሚሊየን (200,000,000) በላይ ተመልካች ያለው የፒስ ቲቪ መስራቹ ዶክተር ዛኪር ነው። በወቅቱ የዳዕዋው ንጉስ በነሩት ሼኽ አህመድ ዲዳት የተማረከው ዶክተር ዛኪር ናይክ የእሳቸውን ፋና በመከተል በንጽጽር ዘርፍ አለምን ማስገረም ቻለ። ሸኽ አህመድ ዲዳትም የዛኪርን የአእምሮ ብቃትና የማሳመን ልዩ ችሎታ በመመልከት ዲዳት ፕላስ በማለት አሞካሹት።

ሙሉ ስሙ ዶክተር ዛኪር አብዱልከሪም ይሰኛል። ትውልድና እድገቱ በህንዷ ቦምቤይ ማሃራሽታ ጆአ ከተማ ውስጥ ነው። የትውልድ ጊዜው እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1965 ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በትውልድ ከተማው ቦምቤይ ቅዱስ ፒተር ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ደግሞ በህክምና ሰርጀሪ ትምህርት በአመርቂ ውጤት ተመርቋል። ከአራት ሺህ በላይ አጥንት ሰርስረው የሚገቡ የመድረክ ላይ የዳዕዋ ስራዎችን ሰርቷል።
ዶክተር ዛኪር ናይክ በዳዕዋ ስራ ከተሰማራበት ጊዜ ጀምሮ ኢስላም ላይ ያነጣጠሩ ውንጀላዎችን የሚያነውሩ የምዕራባውያን ሚዲያዎችን ሃሳብ ውድቅ በማድረግ ተሳክቶለታል። እልፍ አዕላፍ ጥያቄዎችንና ክርክሮችን በበሳል ትንታኔው ረቶ ብዙዎችን ሸሃዳ አስያዘ። መጪውን ትውልድ ለመገንባትና ታዳጊዎችን ለማብቃት ልዩ ልዩ ስራዎች ሰራ። ዶክተር ዛኪር ናይክ ከህንድም ባሻገር የተለያዩ ሃገሮች እየተጋበዘ እስልምናን ሰበከ። በእኛዋ አፍሪካ በሃገረ ጋምቢያ በ2014 በሃገሪቱ ገዥ የህያ ጃሚ ጋባዥነት በዩኒቨርስቲ ኦፍ ጋምቢያ ኦክቶበር 11 እና 22 2014 በመገኘት ዳዕዋዎችን አቀረበ።

በ2013 በዱባይ በተደረገው አስራ ሰባተኛው አለም አቀፍ የቁርአን አዋርድ ፕሮግራም ላይ ኢስላሚክ ፐርሰናሊቲ ኦፍ ዘ ይር በሚል ዘርፍ ተሸለመ። ኖቨምበር አምስት 2013 በማሌዥያ ከፍተኛውን የሃገሪቱን ሽልማት ለማግኘት በቃ። በሃገረ ሳዑድ አረቢያ በንጉሥ ፋይሰል ለኢስላም የተጉና የሰሩ በሚል ዘርፍ ተሸላሚም ሆነ። በአህጉረ አፍሪካ በጋምቢያው መሪ የህያ ጃሚም እጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የሚያሰጥ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ዶክተር ዛኪር በ2006 በዌልስ ከተማ ካርዲፍ ተገኝቶ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ በተያዘበት ወቅት የዌልስ የፓርላማ አባል የሆነው ዴቪድ ዴቪስ "ዛኪር የጥላቻ ሰባኪ ነውና ቀጠሮው መሰረዝ አለበት" ሲል ተሟገተ። ይህ ከእውነት የራቀ ክስ መሆኑን የካርዲፍ ከተማ ነዋሪዎች በተወካያቸው ሰሊም ኪድዋይ አማካኝነት በማሳወቅ ዶክተር ዛኪር ሃይማኖታዊ ንፅፅሮችን በመስበክ አብሮ ለመኖር የሚያስችሉ ሃሳቦችን የሚያነሳ እንጂ ጥላቻን የሚሰብክ አለመሆኑን በመጠቆም ዝግጅቱ እንዲካሄድ አደረጉ። በሌላ በኩል የቀድሞዋ ሆም ሴክሬተሪ የኋላ ኋላ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር የነበረችው ቴሬዛሚ ዶክተር ዛኪርን በመወንጀል ሙስሊሞችን ወደ አሸባሪነት ይጣራል። እኔ አክራሪ ነኝ ይላል በማለት እንግሊዝ እንዳይገባ አሳገደችው። በወቅቱ ዶክተር ዛኪር የቴሬዛሚ ውሳኔ የመናገር ነጻነትን የሚገድብ እንታገልለታለን ሲሉ የሚሰብኩትን ዲሞክራሲ የማይገልጽ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናገረ። ምስጋና ለአላህ ይሁንና ወደ እንግሊዝ መግባት ባይችልም በተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች ምክንያት ኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ በኢንተርኔት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙን እንዲያቀርብ በማመቻቸቱ አስደማሚ ንግግሩን አቀረበ።

በዚህ ዝግጅት ላይ "እንዲህ ያለ መልካምና ለሰው ልጅ ጠቃሚ ንግግር እያደረክ ሰዎች ስለምን ይጠሉሃል?" በማለት አንድ ተማሪ ጥያቄን አቀረበ። "እንኳን እንደ እኔ ዓይነቱ ሰው ይቅርና የመልካምነት መገለጫ የሆኑት መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንኳ በሰው ልጅ ታሪክ የጥላቻ መጽሐፍ ከተጻፈባቸው ቀዳሚ መሆናቸው በሰዎች ዘንድ ተቀባይነቱ እያደረገ የመጣ ሰው ጠላት እንደሚሚበዛበት ማሳያ ነው" ሲል አስረዳ።

ዶክተር ዛኪር ናይክ የእስልምናን የበላይነት፣ የሙዚቃን ክልክልነት፣ የስርቆትንና የዝሙትን ወንጀልነት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በመኮነኑ የምዕራባውያንን ኢ ዲሞራሲያዊ ማንነት ግልፅ አደረገ። ከሴፕቴምበር 11 ጥቃት ጋር በተያያዘ አሜሪካ የሰራችውን በግልጽ መናገሩ እንዲሁም ከፍልስጤምና በደል ከሚደርስባቸው የሙስሊም ሃገራት ጎን ቆሞ መከራከሩ በምዕራባውያኑ ጥርስ ተነከሰበት። ጥላቻና ቂም ተረገዘበት። በትውልድ ሀገሩ ህንድ ሳይቀር ሽብርተኞችን በማነሳሳት፣ በገንዘብ ማጭበርበርና በርካታ ፓስፖርቶችን በመያዝ በሚል ክስ ቀረበበት። በዚህም ፒስ ቲቪ በሀገረ ህንድ እንዳይታይ ታገደ። ባንግላዲሽና ስሪላንካ ይህንን ውሳኔ ተከትለው ፒስ ቲቪን ሃገራቸው እንዳይታይ ከለከሉ። ታይም ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ዶክተር ዛኪር የተከሰሰው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መሆኑን ጠቅሶ በ2019 በባንግላዴሽ ዳካ ከተማ ለተፈጸመው ጥቃትም እጁ አለበት ሲል የህንድ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዘንድ ክስ ቀረበበት። በ2016 VHP ተብሎ የሚጠራው አክራሪ የሂንዱ እምነት ተቋም ዶክተር ዛኪርን ገድሎ ላመጣልን ሰባ ሁለት ሺህ ዶላር እሰጣለሁኝ ማለቱ የወቅቱ እጅግ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር።

ምንም እንኳን ሃገሩ ባታከብረውና ከፍ አድርጋ ባታልቀውም አለም ግን በዕርሱ እውቀት እጅግ ተደምሟል። እስልምና ትክክለኛ እምነት መሆኑን ከማስተማርም ባለፈ አንገታቸውን ከፍ ያደረጉ በርካታ የንጽጽር ዳኢዎች እንዲፈጠሩ አድርጓል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር ከ2015 ጀምሮ መኖሪያውን በማሌዥያ ያደረገ ሲሆን የሃገሪቱ መንግስትም ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ሰጥቶት በነጻነት ከልዩ እንክብካቤ ጋር እንዲንቀሳቀስ ፈቅዶለታል። የማሌዥያው ጠቅላይ ሚንስትር ማሃቲር ሙሐመድ ደጋግሞ ስለ ዶክተር ዛኪር ናይክ ለሚናገረውና አሳልፎ እንዲሰጠው ለሚጠይቀው የናሬንድራሞዲ መንግስት ዶክተር ዛኪር ናይክን በፍጹም አሳልፈው እንደማይሰጡ በግልጽ ተናግረዋል። በማሌዥያ እንዲሁም በኢንዶኔዥያና በዙሪያው ባሉ ሃገራት ይንቀሳቀሳል። ዶክተር ዛኪር ናይክ በሁሉም የዳዕዋ ዘርፎች የተካነ ልዩ ሰው መሆኑን ብዙዎች

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የክፉዎች ሁሉ ቁልፍ!

ለትራፊክ አደጋ ምክንያት ነዉ!
ለበሽታ ምክንያት ነዉ!
ለሞት ምክንያት ነዉ!
ለዝሙት ምክንያት ነዉ!
ለቤተሰብ መበተን ምክንያት ነዉ!
ከእምነት ለማፈንገጥ ምክንያት ነዉ!

የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ አሉ:-

አስካሪ መጠጥን ተቆጠቡ። እሷ ለክፉዎች ሁሉ ቁልፍ ናት። [ሲልሲለቱ ሶሂህ 2798]

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሀላል ከስብ(ሪዝቅ) የሰላም እንቅልፍን ይሰጣል!

አላህዬ ሀላል ሆኖ ሰፊ ሪዝቅን ወፍቀን!

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ያስነጠሰ ሰው አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን ለምኑለት! ካላመሰገነ ግን...

وعن أَبي موسى رضي الله عنه، قَالَ: سَمِعْتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقولُ: إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَحَمِدَ اللهَ فَشَمِّتُوهُ، فَإنْ لَمْ يَحْمَدِ الله فَلاَ تُشَمِّتُوهُ [رواه مسلم]

የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቺያለው በማለት አቡ ሙሳ(ረዲያላሁ አንሁ) አሰተላልፈዋል፦

”ከእናንተ አንዳንቹ ሲያስነጥስ አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን በመመኘት መልሱለት። አላህን ካላመሰገነ አትመልሱለት።” [ሙስሊም ዘግቦታል]

عن أَبي هريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم،
قَالَ: إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَلْيَقُلْ: الحَمْدُ للهِ، وَلْيَقُلْ لَهُ أخُوهُ أَوْ صَاحِبُهُ: يَرْحَمُكَ الله. فإذَا قَالَ لَهُ: يَرْحَمُكَ اللهُ، فَليَقُلْ: يَهْدِيكُمُ اللهُ وَيُصْلِحُ بَالَكُمْ [رواه البخاري]

አቡ ሁረይራ(ረዲያላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦

"ከናንተ አንዳቹ በሚያነጥስ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ለአላህ ምስጋና ይድረሰው) ይበል፡፡ ወንድሙም 'የርሐሙከላህ አላህ ይዘንልህ) ይበለው፡፡ እርሱም መልሶ 'የህዲኩሙላህ ወዩስሊሕ ባለኩም' (አላህ ቅኑን መንገድ ይምራቹ፣ ጉዳያቹንም ያስተካክልላቹ)' ይበል፡፡ [ቡኻሪ ዘግበዉታል]

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com

Читать полностью…
Subscribe to a channel