ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
ረመዳን ያደረግንለትን አቀባበል ጌታችን ፊት የሚመሰክር ልዩ ታዛቢ እንግዳ ነው
🏁 T.me/ahmedin99
ረመዳንን ለመቀበል ቀናቶች ቀርተዋል። ግን ብዙዎች ሳይጠቀሙበት ያልፋቸዋል። ይህም ከሚሆንበት ምክንያቶች ውስጥ በቂ ዝግጅት አለማድረግ ነው። በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ ድንገት ረመዳን ይገባል። እራሳቸውን በኢባዳ ሳያስለምዱ ረመዳን ሲገባ ነገሩ አዲስ ይሆንባቸዋል ከዚያም ከረመዳን ጋር ለመላመድ ቀናቶችን ይፈጃሉ። ታላቁን እንግዳ ሳይጠቀሙበት ጥሏቸው ይሄዳል።
ረመዳን ሙእሚኖች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ትልቅ እንግዳ ነው። ረመዳን ያደረግንለትን አቀባበል ጌታችን ፊት የሚመሰክር ልዩ ታዛቢ እንግዳ በመሆኑ
🔴 ወንጀልን እርግፍ አድርጎ ትቶ በመቶበት፣
🔴 ለመልካም ስራ ከውስጥ ራስን በማዘጋጀት፣
🔴 እያንዳንዱ ቀን በድጋሚ የማይገኝ ትልቅ ዕድል ነው በማለት ከወዲሁ እቅድ አውጥተን ለትርፍ በመዘጋጀት፣
🔴 ወደ መጥፎ ቦታ የሚወስዱን መንገዶችንና ሰዎችን በመራቅ፣
🔴 አላህን እገዛና ተውፊቅ በመጠየቅ ረመዷንን ልንቀበለው ይገባናል❗
አላህ ያድርሰን
🏁 🏁 🏁 🏁 🏁
Ramadaanni mu'iminoota biratti kessummaa guddaa hawwiin eeggamuu dha.
Kessummaa kabajuun amala islaamummaati ramadaanni simannaa isaaf goone Fuula Rabbii keenyaa duratti kessummaa addaa kan ragaa ba'uu dha.
🔺kanaafis:‑
🔴 badii(maasiyaa) akkuma jiruun dhiisnee tawbatuun
🔴 hojii gaariif keessaan of qopheessuun
🔴 guyyyaan maraa carraa guddaa deebi'ee hin argamnee jechuun ammumarraa karoora baasnee faayidaaf of qopheessuun
🔴 namootafi karaalee gara badiittii nugeessaniirraa fagaachuun
🔴 Rabbiin gargaarsaafi Tawfiiqa(qunnama waan gaarii) gaafachuun
👉Ramadaana simachuun nurra jira
ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ
በእስልምናችን እንዴት ይታያል?
ነብያችን (ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ) በዚህ ዙሪያ ምን እንደተናገሩ እንመልከት:-
" ﻷﻥ ﻳﻄﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺃﺱ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺑﻤﺨﻴﻂ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺪ ﺧﻴﺮ
ﻟﻪ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻤﺲ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺤﻞ ﻟﻪ "
"የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ የአንደኛችሁ ጭንቅላት
በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።" (ጦበራኒ ዘግበውታል)
ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ቡዙ መስሊም ወንዶችና
ሴቶች የማይፈቀድላቸውን ሰዎች በመጨበጥ እራሳቸውን
እየበደሉ ይገኛሉ። አልፎ ተርፎም ከወንጀሉ የበለጠ የሚያስጠሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ ለናሙና ያህል:-
* "ልባችን ንፁህ ናት" ይላሉ! የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ልብ የበለጠ ንፁህ ናትን? ለመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ ከነቢዩ(ﷺ) የበለጠ ልቡ ንፁህ የሆነ ሰው አለ? ከርሳቸው በላይ ልቡ መልካም ነገር የሚያስብ ሰው አለን?
* "ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል" ይላሉ እስልምና የመጣው ነብያችንም (ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ) የተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ፣ ለኢትዮጲያ፣ ለዓረብ፣ ለፈረንጅ፣ ለጥቁር ለሀብታም፣ ለድሀ ብለው በመለየት አይደለም አላህ እንዲህ ይላል:-
ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ
"ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም"
ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል! እስቲ ሁላችንም አንዴ ቆም ብለን እናስተውል በሚስማር ጭንቅላታችን ተወግቶ በአንድ ጎን ገብቶ በሌላ ጎን ቀዶ
መውጣቱ የማትፈቀድን ሴት ከመጨበጥ ይሻላል መባሉ
አያሰደነግጥምን? አላህ እርሱን የሚፈራ ልብ ይስጠን!!!
በመጀመርያ ደረጃ መጨበጥ የተፈቀዱ ዘመዶች እንመልከት
ውድ ወንድሜ
እናትህ፣ እህትህ፣ የወንድምህ ልጅ፣ የእህትህ ልጅ፣ ሚስትህ፣ ልጅህ፣ አክስትህ፣ የሚስትህ እናት ለአንተ እንድትጨብጥ የተፈቀዱ ናቸው።
ውዷ እህቴ
አባትሽ፣ ወንድምሽ፣ አጎትሽ፣ ባልሽ፣ ልጅሽ፣ የወንድምሽ ልጅ፣ የእህትሽ ልጅ፣ የባልሽ አባት እነዚህ መጨበጥ የተፈቀዱልሽ የቤተሰብ አባላት ናቸው።
ውድ ወንድሜ መጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችህ እወቃቸው
❌የአጎትህ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የአክስትህ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የወንድምህ ሚስት
❌የሚስትህ እህት
👉እነዚህ ሴቶችና ሌሎችም ልትጨብጣቸው አልተፈቀደልህም! እነዚህ ካልተፈቀዱልህ ከነዚህ የራቁት ደግሞ የባሰ ነው።
እህቴ ሆይ! መጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችሽ እወቂያቸው
❌የአጎትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የአክስትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
❌የባልሽ ወንድም
❌የእህትሽ ባል
👉እነዚህና ሌሎችም ወንዶች ልትጨብጫቸው
አልተፈቀደልሽም! እነዚህ ካልተፈቀዱልሽ ከነዚህ የራቁት ደግሞ የባሰ ነው።
ወንድምና እህቶቼ ሆይ! ይህ በወንጀል ላይ ችክ ማለታችን
እስከመቼ ነው? ቀብር እስክንገባ? የሰዎችን ወሬ እየፈራን! ከሰዎች እናፍራለን ከአለማቱ ጌታ ያለን ፍራቻ የታል? ከሰዎች እያፈርን ከሰዎች ጌታ አናፍርምን? አላህ እርሱንና መልክተኛውን ከሚታዘዙት መልካም ባሮቹ ይጨምረን !!! አሚን
/channel/islamictrueth
የ የካቲት ወር የአዲስ አበባና አካባቢዋ የሶላት ወቅቶች
إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا
ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ [4:103]
/channel/islamictrueth
ከመንግስት አካል ጋር ያለውን ጠብ በተቻለ መጠን በራሳችሁ መንገድ እዚያው ለመፍታት ሞክሩ። በዚህ መሀል መስሊሙ ምንም የሚያገባው ነገር የለም። በጉዳዩ ውስጥ ደም ለማፍሰስ አይደለም ጎራ ለይቶ አስተያየት ለመስጠትም አያስፈልገውም። በግድ ጠላት የማብዛት ስትራቴጂም ለምን እንደምትከተሉ አይገባኝም፥ በቂ ጠላት አላችሁ የማይመለከተውን ሁሉ እየጎተታችሁ ሚስኪን ስለመግደል አትዘባበቱ። ይህ ዛቻ የት አካባቢ እንደሚፈጸም ከልምድ ስለምናውቀው ትንሽም ቢሆን ማስጠንቀቅ ይኖርብናል። ከ300 ሺ በላይ ተከታታይ ያለው፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ የፈለገው ሊቃነ ጳጳሳት ጋ በቀላሉ በስልክ ማነጋገር የሚችል አልፎም አንዳንዴ መልዕክት በደብዳቤ የሚቀበልና የሚያደርስ ሲያሻውም ሙልጭ አድርጎ በዱርየ ቃላት የሚሳደባቸውና "ጎሽ" የሚሉ በርካታ መንጋዎች ያሉት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው። በቅስቀሳው ብዙ ምዕመን ዘንድ የሚደርስ ግለሰብም ጭምር ነውና በሱ ሳቢያ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጠሩ ግፎች አብዝተው ያሰጉኛል።
_______________
© የሕያ ኢብኑ ኑህ
/channel/Yahyanuhe
አምስት ምክሮች ለላጤዋ እህቴ!
ከሸይኽ ኡበይድ አልጃቢሪይ ምክሮች
ጥያቄ፦ ትዳር ሳትይዝ በመዘግየቷ ሀዘን ውስጥ ተዘፍቃ ላለችዋ እንስት ምን ይመክራሉ ?
ምላሽ፦ ማንኛውም ሰው ወንድም ይሁን ሴት፤ ከሀራም ለመጠበቅ፣ ጉድለቱን ለመጠገንና፣ አላህ የፃፈለትን ልጅ ለማግኘት ሲል፤ ገና በጊዜ ቢያገባ ደስ ይለዋል ይፈልጋልም ።
★ ነገር ግን የብዙሃኑ ሰው ትዳር ይዘገያል፤ በተለይ ደግሞ የእንስቶች ይበልጥ ይዘገያል።
የእንስቶችን ጉዳይ በተመለከተ፤ አላህ ካዘነለት በስተቀር በሁሉም ስፍራዎች ቤቶች ትዳር በሌላቸው ሴቶች ተሞልተዋል። ከላጤ ሴቶች ነፃ የሆነ ቤት የለም።
ለእነዚህ እንስቶች የምመክረው
1) ሰብር(ትዕግስት)
መልዕክተኛው(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአጎታቸው ልጅ ለዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ ረዘም ባለው ሀዲሳቸው እንዳሉት:- እወቅ(ግንዛቤ ይኑርህ) ድል ከትዕግስት ጋር ነው! ስኬት የሚገኘው በትዕግስት ነው። ከጭንቀት ግልገልም ከችግር ጋር ነው። ጭንቀትን ለመገላገል ችግርን መቋቋም ግድ ይላል። ከችግር ጋርም ገር ነገር አለ።
ይህንን የነቢዩን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምክር አትርሺ:- "የምትፈልጊው ምቾት መምጫው ቀርቦ ይሆናልና፤ ያለሽበት ችግር ትካዜ ውስጥ አይዝፈቅሽ"
2) ዚክር፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት
~ አላህን በማውሳት በዚክር።
~ ቁርኣንን በመቅራት።
~ በተስቢህ(ሱብሃን አላህ በማለት)
~ በተህሊል (ላኢላሃ ኢለላህ በማለት) ራስሽን ወጥሪ(ቢዚ አድርጊ)።
~ እሱን በመለመን በዱዓእ። በተለይ ምርጥ ወይም ብልጫ ባላቸው ወቅቶች።
* የሌሊቱ ሁለት ሶስተኛው ካለፈ ቡኋላ።
* የጁምዓ የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ።
* ዝናብ እየወረደ(እየዘነበ) ባለበት ወቅት።
ሙስሊሟ፤ ለዲኗም ለዱንያዋም የሚደግፋትን የትዳር ጓደኛ ከአላህ ትለምን። ዋናው ነገር ባል ማግኘቱ ብቻ አይደለም። ይህ ባል የሚጠቅማትና የምትደሰትበት ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ባሎች ፀጋ(ምቾትና ድሎት) አይደሉም። እንዲያውም ቅጣት፣ መከራና ስቃይ ናቸው። ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው በእንዲህ ዓይነቱ ትዳር ሰበብ በስቃይ ተንገላተው የተፈተኑ። ከምሬት የተነሳም በወንጀሎች ላይ የወደቁም ቀላል አይደሉም። ስለዚህ ጥሩ ባል እንዲገጥመሽ ዱአ አድርጊ።
3) አላህ ከዚህ የላጤነት ችግር እንደሚያወጣት እርግጠኛ መሆን ይገባታል።
አላህ እሱን ፈሪ ለሆኑት በሙሉ ቃል የገባዉን(በማሰብ ከችግሯ እንደሚያላቅቃት) እርግጠኛ መሆን አለባት። ይህም ጉዳይ ወንዱንም ሴቷንም የሚያጠቃልል ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ [الطلاق ٢]
“አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫውን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ያደርግለታል” (አል ጠላቅ 2)
4) ወደ ሀዘን አትዘፈቂ!
ሀዘን ወይም ትካዜ ከበስተጀርባው ጉዳት ያስከትላል። ሃዘን አይጠቅምም፤ ወደ ሴቶቻችን ልቦናቸው ሸይጣን እንዲገባም መንገድ ይከፍታል። እኔ እንደሚታየኝ ሀዘን ሙስሊሟን ተስፋም ያስቆርጣታል። ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ሀራም ነው፤ ጭራሽ ወደ መጥፎ አካባቢዎች ይወስዳትም ይሆናል። ወደ መጥፎ እርምጃም ይከታት ይሆናል።
♦ አላህን ትፍራ
♦ ትታገስም
♦ ከአላህ ጋርም ትተሳሰብ(በደረሰባት እንግልት ከአላህ መልካም ምንዳን ትከጅል።)
♦ እሱ ያለችበትን ህይወት ወደ መልካሙ የሚቀይርላት ጥራትና ልቅና የተገባው አምላክ ነውና።
5) አንዳንድ እንስቶቻችን የሚፈፅሙት ስህተት አለ!
የሚያጫትን ሰው በራስዋ መንገድ ለራስዋ ማፈላለጓ ነው። ታፈላልጋለች ከዚያም ወደ ቤተሰቦቿ ታመጣዋለች። ሁሉም ሰው የየራሱ አስተያየት አለውና እነርሱ ባልተቀበሏት ግዜ ትቆጫለች፣ ቅስሟ ይሰበራል፣ ሀዘንም ላይ ትወድቃለች። ሙስሊም እንስቶች ሆይ! ይህ አካሄድ ስህተት ነው። በቤትሽ እርጊ። አላህ የለገሰሽን ዲን ኢስላምን ተላብሰሽ በሃይማኖተኝነትሽ ፅኚ። ቀድሞ የመከርኩሽንም ደግሜ እመክርሻለሁ። ራስሽን ለውርደት አትዳርጊ። ከውርደትም አንዱ ወንድ ልጅ በውጭ አፈላልገሽ ወደ ቤተሰቦችሽ ማምጣትሽ ነው። ይህ ደግሞ በባህላችንም ሆነ በሸሪዓችን ጉድለት ነው።
ኢስላም የጥፋት በሮችን ከጅምሩ ይዘጋል፤ የሁለትዮሽ ግንኙነትና መለማመድ የሚያስከትሏቸው መዘዞች ከባድ ናቸው። ሸይጣንም ሶስተኛ ነውና አጉል በራስዎ አይተማመኑ።
ይጠንቀቁ
#Abufewzan
/channel/islamictrueth
❝..አዛን ለምን በኦሮምኛ አይደረግም?..❞
..
ውዝግብ ያስነሳውን የሊቃነ ጳጳሳት ሹመት የሚቃወሙ የኦርቶዶክስ ሰዎች እያስጮሁት ያለው ሀሳብ ነው። እዚህ ውስጥ "አዛን" ምን ሊያደርግ እንደገባ ባላውቅም ይህ ጉዳይ በእስልምና ግልጽና የተብራራ ሀሳብ ስለሆነ ማንም ሰው በቋንቋየ አዛን ይደረግ ብሎ ጥሪ አያቀርብም። በመሠረቱ አዛን "ኑ ወደ ሰላት" የሚል ጭብጥ ያለው ጥሪ ነው። ማንኛውም ሰው ግን የትኛውንም የሀይማኖት ክፍል በቋንቋው እንዲማር እስልምና ያስተምራል። ይህ እናንተ እንዳሰባችሁት ለብሔርተኝነት ፉክክር ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ የሚተገበርና አላማውም ሰዎች እምነታቸውን እንዲያውቁ በማሰብ የሚደረግ መሠረታዊ ቀናዒ ተግባር ነው። እስልምና በዚህ በኩል ክፍተት የለበትም፥ ምዕመኑም ይህንን ጠንቅቆ ያውቃልና በጥቃቅን እውቀታችሁ ተመርኩዛችሁ ጥሩ ማነጻጸርያ ያመጣችሁ እየመሰላችሁ ራሳችሁን ትዝብት ውስጥ አትጣሉ..!
..
በተረፈ መሠል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትናቆሩን ግራ እያጋባችሁንም ነው። በኛ በኩል ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ስለሆነና ስለማይመለከተን ነው ዝም ያልነው..?! መቸ ነው ምርኩዝ ሳታደርጉን እዚያው ችግራችሁን የምትፈቱት ግን? እናንተ እንደምታደርጉት በጠባችሁ መሀል ሁሉ ሳይድ እየያዝን እሳት እንድናቀጣጥል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ነውርማ እወቁ..!
___
© የሕያ ኢብኑ ኑህ
/channel/Yahyanuhe
የትዳር ዉስጥ ሚስጥርን የማዉጣት አደጋ!
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
ሂጃብ ምንድን ነው???
'ሂጃብ' ማለት ቋንቋዊ ፍቺው መከለያ፣ መጋረጃ፣ መሸፈኛ እንደማለት ነው። አማኝ የሆነች ሴት ባዕድ ሊያየው የማይገባውን የሰውነት ክፍሏን መሸፈን እንደሚገባት የሚያመላክት ቃል ነው።
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
ዉዷ እህቴ የትኛዉም ቦታ እንደሚገኘዉ ድንጋይ ሳይሆን ልክ ዉድና ብርቅ እንደሆነዉ ዳይመንድ ሁኚ!
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
አላህ የዱንያም የአኼራም ምኞትሽን ያሳካልሽ!
ልታይ ልታይ በባዛበት የኢስላምን ስም እያጠፉ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሴቶች በበዙበት አንቺ የፀሀዩ መክበድ ሳይበግርሽ በሙሉ ሂጃብ ክብርሽንና እምነትሽ ለጠበቅሽው እህቴ አላህ በአዱኛም በአኼራ ያሰብሽው ያሳካልሽ!
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
” اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِى تَقْشَعِرُّ مِنْهُ جُلُودُ الَذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمْ وقُلُوبُهُمْ إلَى ذِكْرِ اللَّهِ” (الزمر23)
"አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፤ ከርሱ(ግሣጼ) የነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፤ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ(ተስፋ) ማስታዎስ ይለዝባሉ… (ዙመር 23)
በሌላ አንቀፅ ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
” لَوْ أَنزَلْنَا هَذَا القُرْآنَ عَلَى جَبَلٍ لَّرَأَيْتَهُ خَاشِعًا مُّتَصَدِّعًا مِّنْ خَشْيَةِ اللَّهِ” (الحشر 21)
“ይህንን ቁርአን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ፣ ተሰንጣቂ ኾኖ ባየኸው ነበር…” (አልሀሽር 21)
Www.fb.com/islamictrueth
እስልምና ላይ ለሚጠየቁ ጥያቄዎችን ከምንሰጣቸው ምላሾች ጎን ለጎን የጥያቄ ማቅረብና በጨዋ ደንብ መሞገት/Polemics/ ስራዎችንም መስራታችንን ቀጥለናል። የቲክቶክ መገኛውን ሼር በማድረግ ትምህርቶቹ ለበርካታ ሰው እንዲደርሱ ያድርጉ።
..
https://vm.tiktok.com/ZMYJDy8dQ/
እስልምናን ለቅቄ የወጣሁት የዘላለም ዋስትና ስለሌለዉ ላለዉ ሰዉዬ የተሰጠ መልስ!
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
ጣፋጭ አቀራር #22
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
አንድ ስሙን ማልጠቅስላቹ የሚዲያ ስሙ ኡስታዝ ምናምን ነዉ፤ አንድ ሰሞንም ሲያስተምር ትዝ ይለኛል። ዛሬ ላይ በሚዲያ ላይ ለሽልማት መድረክ ላይ አጅነብይ ሲስም ሳይ በጣም ደነገጥኩኝ። ታዋቂ መሆን ከችግሮቹ ዋነኛዉ አላህን መፍራት ቀስ በቀስ ከልብ ይወጣል።
አላህ ጀዛዉን ይክፈለዉና አህመዲን ጀበል አጅነቢይ መጨበጥ ለየትኛዉም ግለሰብ ላይ የማይፈቅ መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስተር ባለቤት በአደባባይ አሳይቷል። ይህ ለኛ ትልቅ ሸክምን ያቀለለ እንዲሁም የእምነታችንን ትእዛዝ ያሳየ ተግባር ነዉ።
ታዋቂ ወይም ኡስታዝ የሚባል ሰዉ ተግባሩ ሁሉ ለምእመናዉ ትክክል የሚመስለዉ ማህበረሰብ ብዙ ነዉና በተቻለን መጠን ዲናችንን ማሳወቅ ለኛም ለዲኑም ክብር ነዉ ባይ ነኝ።
ዉለታ ለመመለስ ሲባል...
አንዳንዴ ስሜታችንን ባለመቆጣጠራችን የተነሳ ምን ማለት እንዳለብን ላናዉቅ ስለምንችል ስሜታዊ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ ከቻልን በዝምታ ካልሆነ ለንግግራችን መስመር እናበጅለት።
ፆም ከአላህ ለአላህ የሚደረግ ትልቅ የአምልኮ ተግባር ነዉ። ይህንን አምልኮ ለሌላ አካል መስጠት የድርጊቱ ወንጀልነት ስለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም።
በተረፈ እኛ እንደ ኢስላም ለኢባዳችንም ሆነ ዲናችን የሚስፋፋዉ በሰላም ነዉና እንኳን ለዉዷ ሀገራችን አደለም ለአለም ሰላምን እንመኛለን። በሌላ ወቅት የሚደረግ ዱአ ይቅርና ከእያንዳንዱ የሶላት መጨረሻ አላህን ሰላምን እንድንጠይቀዉ ታላቁ ነብይ ሙሀመድ(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዙናል።
ከሠውባን(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ(ﷺ) ሶላታቸውን እንዳጠናቀቁ ፡-
« አላህ ሆይ! ይቅርታህን እጠይቃለሁ ሶስት ጊዜ ከዛም፤ አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ። ሰላምም የሚገኘው ካንተው ነው። የታላቅነትና የልግስና ባለቤት የሆንከው ጌታ ሆይ! ረድዔተ ብዙ ነህ። ይሉ ነበር» [ሙስሊም ዘግበዉታል]
/channel/islamictrueth
በኢስላማዊ መደብሮች የንጽጽር መጽሀፍት እንዳይሸጥ መከልከሉን ከሰሞኑ ሰማን..! እስልምናን የሚሳደቡ ሰዎች በነጻነት ስድባቸውን በሚናገሩበት ሀገር፥ በስነ ስርአት ሀሳብ ላይ አተኩሮ የተጻፈን መጽሀፍ መከልከል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ ነው። ጥሩነቱ ጊዜው የኢንተርኔት ነው፥ ከመጽሀፍት በተሻለ በይነ መረቡ ተደራሽ ነውና እጃችንን እስኪይዙት ድረስ ደግሞ ባለን አማራጭ መታገል ነው።
Читать полностью…ጥብቅ ሴቶችን (በዝሙት) የሚወርፉ ግለሰቦችን አላህ(ሱብሀነሁ ወተአላ) በቁርአኑ እንዲህ ይላል...
{ وَٱلَّذِینَ یَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَـٰتِ ثُمَّ لَمۡ یَأۡتُوا۟ بِأَرۡبَعَةِ شُهَدَاۤءَ فَٱجۡلِدُوهُمۡ ثَمَـٰنِینَ جَلۡدَةࣰ وَلَا تَقۡبَلُوا۟ لَهُمۡ شَهَـٰدَةً أَبَدࣰاۚ وَأُو۟لَـٰۤىِٕكَ هُمُ ٱلۡفَـٰسِقُونَ (٤) إِلَّا ٱلَّذِینَ تَابُوا۟ مِنۢ بَعۡدِ ذَ ٰلِكَ وَأَصۡلَحُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ (٥) }
[سُورَةُ النُّورِ: ٤-٥]
«እነዚያም ጥብቆችን ሴቶች (በዝሙት) የሚወርፉ ከዚያም አራት ምስክሮችን ያላመጡትን ሰማኒያ ግርፋት ግረፏቸው፡፤ ከእነርሱም ምስክርነትን ምን ጊዜም አትቀበሉ፤ እነዚያም አመፀኞቹ (ፋሲቆቹ) ናቸው፡፡
እነዚያ ከዚህ በኋላ የተፀፀቱና (ስራቸውን) ያሳመሩ ሲቀሩ፤ አላህ በጣም መሓሪው አዛኙ ነውና።»
[አን‐ኑር 4–5]
———
{ إِنَّ ٱلَّذِینَ یَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَـٰتِ ٱلۡغَـٰفِلَـٰتِ ٱلۡمُؤۡمِنَـٰتِ لُعِنُوا۟ فِی ٱلدُّنۡیَا وَٱلۡـَٔاخِرَةِ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِیمࣱ (٢٣) یَوۡمَ تَشۡهَدُ عَلَیۡهِمۡ أَلۡسِنَتُهُمۡ وَأَیۡدِیهِمۡ وَأَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُوا۟ یَعۡمَلُونَ (٢٤) یَوۡمَىِٕذࣲ یُوَفِّیهِمُ ٱللَّهُ دِینَهُمُ ٱلۡحَقَّ وَیَعۡلَمُونَ أَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ ٱلۡمُبِینُ (٢٥) }
[سُورَةُ النُّورِ: ٢٣-٢٥]
«እነዚያ (ስለ ዝሙት ጭራሽ) ዘንጊና አማኝ የሆኑትን ጥብቅ ሴቶችን (በዝሙት) የሚወርፉ፤ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተረገሙ፤ ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ታላቅ ቅጣት አላቸው)።
በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል፤ አላህም (ሁሉን ነገር) ገላጭ የሆነው እውነተኛው ጌታ መሆኑን ያውቃሉ፡፡»
[አን‐ኑር 23–25]
ሼይኽ ኤልያስ አህመድ
/channel/islamictrueth
ሴት ልጅ የተሟላ ሂጃብ በመልበስዋ ወንዶች እርሷን አይተው ከመፈተን ትጠብቃለች፤ መከላከያ ትሆናለችም። እንዲህ በማድረጓ አይናቸውን ሰበር ለሚያደርጉ ብርቅዬዎች ብቻ ሳይሆን ላይ ታቹን ለሚቀላውጡትም አደብ ታስገዛበታለች፡፡ ምክንያቱም ውበቷ፣ መስህቧ ስለተደበቀ ምንም ቢቁለጨለጩ የሚያገኙት ነገር የለምና ነው፡፡
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
ሂጃብ ኢባዳ እንጂ ባህል አይደለም!!
አላህ ሂጃብ መልበስን ያዘዘው ከሰላት እና ከዘካ ጋር አጣምሮ ነው፡ ሂጃብ አላህን መታዘዝ ግዴታ የሆነበት አምልኮ "ኢባዳ" እንጂ ባህል እንዳልሆነ ለመግለፅ ነው አላህ ሰላትንና ዘካን በግዴታነት እንዳዘዘ ሁሉ ሂጃብንም ግዴታ አድርጎ አዟል!!
وقرن في بيوتكن ولا تبرجن تبرج الجاهلية الأولى وأقمن الصلاة وآتين الزكاة وأطعن الله) الأحزاب 33 (ورسوله
«በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ቀድሞው የመሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ!» [አል አህዛብ 33]
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
ሴት ልጅ ሙሉ ሂጃብ ባለማድረጓ ለስሜታቸው ላደሩት መቀለጂያና መጠቋቆሚያ ሆናለች።
እኒህ አይነቶቹ ቂሎች ለራሳቸው ተጃጅለው እሷንም ለማደንዘዝ አይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ዳሌሽ ውብ ነው ቅብርጥሴ እያሉ በማማለል ለማይረግበው ስሜታቸው ማርኪያ ሎሌ አድርገዋታል፡፡
እርሷም እነዚህ መርዘኛ ቃላቶች ባሳደሩባት ተፅዕኖና ባሳረፉባት ጠባሳዎች ተደንቃ ውብ መሆኗ የተነገረላት እስኪመስላት በሐሴት ተሞልታ እነሱ ለፈለጓት አላማ በማደር የወሲብ መግነጢሳቸው ሰለባ ሆናለች።
#ሂጃብ_ምርጫዬ_ነው
#ሂጃብ_ለአላህ_ያለኝን_ውዴታና_ታዛዥነት_ምገልፅበት_ነው
#ሂጃብ_ዒባዳ_ነው
#የተሟላ_ሂጃብ_መልበስ_እርድና_ነው
/channel/islamictrueth
በቁርአን ውስጥ የሚገኙ ስምንት የተአምራት መገለጫዎች
1) የመጀመሪያ መገለጫ
የቁርአን ያማረ ቅንብሩ፣ የቃላት አሰካኩ፣ የተሳካና ልብ የሚማርክ መልእክቱ፣ የማብራራት ምጥቀቱና የአረቦችን የቋንቋ ክህሎት ሰንጥቆ ያለፈ ያገላለፅ ኃይሉ፣ ከጥበበኛውና ከምስጉኑ(አምላክ) የወረደ፣ አንቀፆቹ በጥበብ የተቀመሩ፣ ቃላቶቹ በሚገባ የተብራሩ፣ ያገላለፅ ምጥቀቱ አእምሮን የዘለለ፣ የቋንቋ ፍሰቱ ንግግርን ሁሉ ያስናቀ መሆኑ።
2) የሁለተኛው መገለጫ
አስገራሚ ሰርኣታዊ ቅንብሩ፣ እንግዳ የሆነና ከአረቦች የንግግር ዘይቤ እንዲሁም የቋንቋ ህግጋትና ስርአት የተለየ መሆኑ፣ ቁርአን የመጣበት የአነጋገር ስልት፣ የአንቀፆቹ አከፋፈልና የመቆሚያ ቦታ ስኬት፣ የቃላቶቹ መጣጣምና የመለያ ክፍፍላቸው ጥምረት፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ ቡኋላ ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሆኑ፣ አንድም ሰው በከፊል እንኳን የርሱን ተመሳሳይ ማምጣት አለመቻሉ። ለዚህ ነው(ቁርአን) በጥላቻው ቁንጮ ደርሶ የነበረው ኡትባ ብኑ ረቢዓ ቁርአንን በሰማ ጊዜ እንዲህ ያለው፡- ‘’ሰዎች ሆይ! እኔ አንድን ነገር በእርግጥ ሳላውቀው፣ ሳላነበውና ሳልናገረው እንደማልተወው ታውቃላቸሁ። በአላህ እምላለሁ! እርሱን የሚመስል ሰምቼ የማላውቀውን ንግግር በእርግጥ ሰማሁ። እርሱ ግጥምም አይደለም፣ ድግምትም አይደለም፣ ጥንቆላም አይደለም።’’
3) ሶስተኛው መገለጫ
ነብዩ ሙሐመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ማንበብና መፃፍ የማይችሉ ሆነው ሳለ ቁርአን ከህይወት መፈጠር ጀምሮ በርሳቸው ላይ እስከወረደበት ጊዜ ድረስ ቀድመው የተከሰቱ ነገሮችን መዘገቡ አንዱ ተአምር ነው። ቁርአን የነቢያቶችና የህዝቦቻቸውን ታሪክና በዘመኑ የጠፉ ህዝቦችን ሁኔታ ዘግቧል። ከመጽሐፉ ባለቤቶች ለቀረቡ ዋሻ ውስጥ (ሦስት መቶ ዘጠኝ አመት) ሲኖሩ ስለነበሩ ህዝቦች፣ ስለ ሙሳና ኸድር (ሰላም በእነርሱ ላይ ይውረድና)፣ ሰለ ዙል-ቀርነይን ሁኔታና ስለሌሎችም ፈታኝ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል።
4) አራተኛው መገለጫ
በወህይ(በጅብሪል አማካኝነት ከአላህ በቀጥታ ለነብዩ ሙሐመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚወርድ መልእክት) ካልሆነ በስተቀር በወቅቱ ሊታወቁ የማይችሉ ወደፊት የሚከሰቱ ክስተቶችን መዘገቡ ሌላው ተአምር ነው። ቁርአን እንደሚፈፀሙ የተናገራቸው እነዚህ ክስተቶች ከንግግሩ አንድም ነገር ሳይቀር የተፈፀሙ አሉ፡፡ ከነዚህ መካከል በሱረቱል ፈትህ ቁጥር 27 ላይ
"አላህ ለመልእክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲሆን አላህ የሻ እንደሆነ ፀጥተኞች ሆናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ…" ያለውንና በሱረቱል-ሩም ቁጥር 2-3 ‘’ሩም ተሸነፈች፤ በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር። እነርሱም ከመሸነፋቸው ቡኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)…’’ ያለውን መጥቀስ ይቻላል።
5) አምስተኛው መገለጫ
እርሱነቱ ዘውታሪ፣ ተአምሩ ዘላለማዊ፣ የአመታት መቀያየር ምንም የማይበግረው፣ እስከ ዕለተ-ቂያማ ድረስ የዘመን መለዋዎጥ ክብሩን የማይቀንሰው መሆኑ ሌላ ተአምር ነው። ቁርአን ዘውታሪና ዘላለማዊ ከመሆኑ ጋር አላህ (ሱ.ወ.) ሊጠብቀው ቃል ገብቶለታል፡-
” إنا نحن نزلنا الذكر وإنا له لحافظون ” (الحجر 9)
‘’ቁርአንን እኛው አወረድነው፣ እኛም ለርሱ ጠባቂዎቹ ነን’’ (አል-ሂጅር 9)
” لا يَأْتِيهِ البَاطِلُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ ولا مِنْ خَلْفِهِ تَنـزِيلٌ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ” (فصلت 42)
‘’ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው’’ (አል-ፉሲለት 42)
6) ስድስተኛው መገለጫ
ባጠቃላይ አረቦችም ሆነ በተለይም ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከነብይነታቸው በስተፊት በዘመኑ የማያውቁት፣ በዚያን ጊዜ አሉ የሚባሉ ሊቃውንቶች ያልደረሱበት፣ በወቅቱ ከነበሩት ጽሁፎቻቸው ያልተጻፈ ትምህርትና ዕውቀትን ቁርአን ሰብስቦ የያዘ መሆኑ ሌላኛው ተአምር ነው። አላህ እንዲህ በማለት እውነትን ተናገረ፡-
” ولَقَدْ ضَرَبْنَا لِلنَّاسِ فِى هَذَا القُرْآنِ مِن كُلِّ مَثَلٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ” (الزمر 27)
‘’በዚህም ቁርአን ውስጥ ለሰዎች ይገሠጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን’’ (አል-ዙመር 27)
7) ሰባተኛው መገለጫ
የቁርአን ሳይንሳዊ ተአምራት፡- ቁርአንን ለሚያነብና በሰው ልጅና በዩኒቨርስ እንዲሁም በሌሎች የሳይንስ ጥናት ዘርፎች ግንዛቤ ያለው ሰው የሚረዳው ነገር ቢኖር በሰው ልጅ አእምሮ ለተገኙ ማንኛውም አይነት ሳይንሳዊ እውነታዎች በሙሉ በምልከታ ወይንም በቀጥተኛ መልኩ በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰ መነሻ እንዳላቸው ነው። (ሳይንሳዊ ተአምሮች በተከበረው ቁርአን ውስጥ፤ ሽህ ዘንዳኒና ዶክተር ዘግሉል አል-ነጃር የተወሰደ)
ይህ የቁርአን ባህሪ መቆሚያ የሌለው ነው። የሰው ልጅ የሳይንሳዊ ዕውቀቱ እየሰፋ በሄደ ቁጥር የቁርአን ተአምራዊነት፣ አስደናቂነትና ታላቅነቱ ለሳይንቲስቶች የበለጠ ግልፅ እየሆነ ይመጣል። አላህ እንዲህ በማለት እውነትን ተናገረ፡-
” سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِى الآفَاقِ وفِى أَنفُسِهِمْ حَتَّى يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الحَقُّ أَوَ لَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ” (فصلت 53)
"እርሱም(ቁርአን) እውነት መሆኑን ለነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአፅናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተአምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን። ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃችሁምን?" (ፉሲለት 53)
8) ስምንተኛው መገለጫ
ቁርአን እርሱን የሚያዳምጡ ሰዎችን ልብ በአስገራሚ ሁኔታ የመማረክ ሀይሉና በሚያነቡት ሰዎች ላይ የሚፈጥረው ከባድና ብርቱ ተፅኖ ሌላኛው የተአምር መገለጫ ነው። ቁርአን በአስተባባዮች ላይ የሚያሳድረው ጫና በጣም ከባድና አደገኛ ነው። ከዚህም የተነሳ(አስተባባዮች) ለራሳቸው፣ ለሴቶቻቸውና ለልጆቻቸውም ጭምር ቁርአንን ማዳመጥ ከሚፈጥርባቸው ተፅኖ በመፍራት እንዲህ ይሉ እንደነበር በሱረቱል-ፉሲለት ቁጥር 26 ተገልጿል፡-
‘’ “لا تَسْمَعُوا لِهَذَا القُرْآنِ والْغَوْا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ”
"ይህንን ቁርአን አትስሙ ታሸንፉም ዘንድ በርሱ ውስጥ (ሲነበብ) ተንጫጩ” (ፉሲለት 26)
የአማኞችን ሁኔታ ስንመለከት የቁርአን ድንቅ ማራኪነት፣ በነፍሶቻቸው ላይ የሚያሳድረው ብርቱ ተፅኖና እንዲሁም በልቦቻቸው ላይ የሚፈጥረው ልዩ የክብር ስሜት ይህንን መለኮታዊ መጽሐፍ እንዲናፍቁት፣ ሌሎች ስነ-ጽሑፎችንም ሆነ ንግግሮች እንዲርቁና ከምንጭ አጠገብ እንደበቀለ ቡቃያ ልባቸውን የሚያረጥቡበት የህይወታቸው አካል አድርገውት እንዲኖሩ አስችሏቸዋል። ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ሚስጢሩ ምንድን ነው? በሙእሚኖች ደም ውስጥ የተሰራጨው ይህ አዲስ ሩህ ምን ይሆን? የሙስሊሞችን ነፍስ በበላይነት የማረከው ይህ ተአምር ምን ይሆን? እርሱ በርግጥ አላህ (ሱ.ወ.) ይህንን የማድረግ ሀይል የቸረው የራሱ የአላህ (ሱ.ወ) መጽሐፍ (ቁርአን) ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ስለ ቁርአን በሱራ-አልዙመር እንዲህ ብሏል፡-
ይህ ስብከት ይቅርታ ሁከት በተግባር በሀዲያ ሙስሊሞች ላይ ተጀምሯል። መጅሊስም አንድ ቀን እነዚህ አይነቶችን አንታገስም አለ፤ ማህበረ ምናምንም ክስ መሰረትን አሉ እነሱ(እዩ ጩፋ) ግን በዚሁ ፕሮግራም ላይ በስልጣንና በሀያል እንሰብካለን ብሏል!!!
Читать полностью…ከባድ አጣብቂኝ ዉስጥ ስትገባ...
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman