ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
🔴የዚህ ዑምራ አድራጊ ጉዞ ምስል ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ምግብና መጠጥ ፍላጎት ወይም ከዚያ በላይ ዐቂዳውን መማር እንደሚያስፈልግ ያሳያል።
የሰውዬው አለባበስ እና ቁመናው ብቻ ከፊሎቹ፣ ከመላኢኮች አንዱ ነው እንዲሉና ሌሎቹ ደግሞ ከሰሀቦች አንዱ ነው፣ ብለው እንዲናገሩ አድርጋቸዋል። አንዳንዶችም ከሱ ተበሩክ እንዲፈልጉ ዳርጓቸዋል። ስለሰውዬው ብዙ ግምቶች መላምቶች ተሰጥተዋል። ይሁንና ከተራ እና ቀለል ብለው ከሚኖሩ ሙስሊሞች አንዱ ሰው መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ ህዝብ ደጃል ቢመጣ እንዴት ሊሆን ነው?! እርሱ ጽድቅን፣ ሷሊህነት፣ ዙህድ የሚታይበት አስመሳይ ነው። አሱ ተገልጦ ሰማይን "ዝነቢ" ሲል ዝናብም ይዘንባል እርሱም ዘንድ ጀነት፣ ጀሀነም እና ሌሎች ከተለምዶ ወጣ ያሉ ተአምርን ያሳያል ፣ ያኔ ነቢይ ነኝ፣ ጌታ ነኝ ይላል። የሰውዬ አለባበስ ቀለል በማለቱ እና በሰውነት ቅርፁ የተሸወደ ይህ ህዝብ ደጃል ከባባድ ተኣምራትን ሲያሳይ ምን ልሆን እንደሚችል መገመት አይሳንም።
አላህ ሆይ ከፈተና ጠብቀን!
ሸይኽ ኢብራሂም አልሙሐይሚድ
/channel/sultan_54
ዒድ እና ጁሙዓ ከተገጣጠሙ
በነቢዩ ﷺ ዘመን ዒድና ጁሙዓ ተገጣጥመው ዒድን ካሰገዱ በኋላ ወደ ህዝቡ በመዞር እንዲህ አሏቸው፦
«ሰዎች ሆይ! ዛሬ ሁለት ዒዶች ተገጣጥመዋል። ዒድን የሰገደ ሰው ለጁሙዓ ይበቃዋል። እኛ ግን ጁሙዓን ለመስገድ እየሄድን ነው።»
(አል-ሐኪም/ አቡ-ዳውድ1073)
🔷 ከዚህ በመነሳት ኢማም አህመድ፣ ኢብን ተይሚያህ፣ አል-ሸውካኒ እና አብዛኛው ዑለማዎች ተከታዩን አስቀምጠዋል፦
♦️ ዒድን የሰገደ ሰው ከጁሙዓ ወይም ከዙሁር አንዱን መርጦ መስገድ ይችላል።
♦️ ዒድን ያልሰገደ ሰው ጁሙዓን መስገድ ግዴታው ነው።
♦️ ዒድን የሰገደ እስከ ዐሱር ሶላት የለውም የሚለው በአብዛኛው ዑለማዎች ውድቅ የተደረገ ነው።
(አል-ሙግኒ 2/265/ ፈታዋ ኢብን ተይሚያህ 24/211)
🔷 ኢማም አቡ-ሐኒፋ፣ ኢማም ማሊክ እና ኢማም አሽ-ሻፊዒይ ደግሞ፦
ሐዲሱ የተነገረው ዒድን ለመስገድ ከሩቅ ቦታ ለመጡት ስለሆነ በከተማ የሚኖሩት ጁሙዓን መስገድ ግዴታ ይሆንባቸዋል። ዒድ ሱንና ነው። ለሱንና ተብሎ ፈርድ ሶላት አይሻርም ብለዋል።
(ሐሺያህ አል-ደሱቂ 1/391)
👉 በጥቅሉ ሁሉም የተስማሙበት ዒድን የሰገደ ጁሙዓን ወይም ዙሁርን መስገድ ግዴታ አለበት። እስከ ዐሱር ሶላት የለም የሚለው ውድቅ ነው።
🛑ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
🎈ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡ ለግንዛቤ ያህል ዘካተል ፊጥር ከዘካተል ማል ይለያል ።
🎈እያንዳንዱ አባወራ ወይም እማወራ ወይም አስተዳዳሪ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር እየቀለባቸው ላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይኖርበታል ፡፡
🛑 ማስረጃ
🎈 አብዱላህ ኢብን አባስ አላህ ይውደዳቸውና እንዲህ ይላሉ፤
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም
በ እርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር ለፆመኛ በጾሙ ወቅት ከፈፀማቸው ጥቅም አልባ ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች ጥፋት እንዲሁም የተቃራኒ ፆታ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮቹ ጥፋት ማፅጃ ይሆንለታል ። ለሚስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውላታል ። ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከ ኢድ ሶላት ቦሃላ ዘካውን የሰጠ እንደማንኛውም ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል ።))
(አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)።
🎈 ኢብኑ ሙንዚር አል ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው
ዑለሞች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን
ተስማምተውበታል›› በማለት የ ኡለሞችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዎል ።
🛑 የተደነገገበት ጥበብ
ከላይ ግዴታነቱን ለማመላከት በተጠቀሰው ሀዲስ እንደተጠቀሰው ፣ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ።
🛑 መጠኑ
* የዘካተል ፊጥር መጠን ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይዘው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል: – ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ቁና መስጠት በ እያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያም ሆነ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም )
1 ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣
— አንድ ቁና (ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2.5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·85 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·75 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·63ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ
🛑 ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው
— ሙስሊም በሆነ
— ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ
— በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ።
— * ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ።
🛑 ግዜው
* ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት
ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች (ረዲየላሁ አንሁም) ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት እንደሚቻል ይገልጻሉ ሲተገብሩትም ነበር ።
* ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።
🛑 የሚሰጠው ነገር
* ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ይሆናል ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች
ነው ። ይህን አስመልክተው የአላህ መልእተኛው ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲሳቸው የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች ( ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ፣ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስረዳሉ ። በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን ማውጣት ይችላል፡፡
🛑 ለማን ይሰጥ
* ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው አብደላህ ብኑ አባስ ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ስለገለፁ ።
🛑 በዘካተል ፊጥር ስለመወከል
* ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ወቅት የተገደበና ግዜውም አጭር ከመሆኑ አንፃር አውጪዎች ባሉበት ሀገር ወይም ሁኔታ ምክንያት በተወሰነለት ግዜ ማውጣት ካልቻሉ ወቅቱ ሳያልቅ ዘካውን ሚያወጣላቸው ሰው መወከል ይችላሉ ። በተመሳሳይ ዘካተል ፊጥርን የሚቀበሉ ምስኪኖችም ራሳቸው መቀበል ካልቻሉ ሚቀበልላቸውን ሰው መወከል ይችላሉ ።
* ተወካዪች ከሁለቱም ከሰጪና ከተቀባይ ወገን ከተወከሉ ወቅቱ ካለፈም በኋለ ለምስኪኖች ቢሰጡ ችግር የለውም ነገር ግን የተወከሉ በሰጪዎች ብቻ ከሆነ የግድ ወቅት ሳያልፍ ለሚገባቸው ሰዎች ማድረስ ይኖርባቸዋል ።
🛑 ለሌላ አካባቢ ስለመስጠት
* አግባቡ ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ ከመላክ
እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ማውጣቱ ቢሆንም የሚቀበል ሚስኪን ከሌለ ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይቻላል ።
ጣፋጭ አቀራር #24
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
"ዱዓእ" ማለት፡- የምትፈልገውን ነገር ሊሰጥህ፣ የምትመኘውን ነገር ሊያሳካልህ፣ ከምትጠላውና ከምትፈራው ነገር ሊጠብቅህ እንደሚችል አምነህ ለዚህ አካል የምታቀርበው ተማጽኖና ልመና ማለት ነው፡፡
አንድ ሙስሊም ዱዓእ አደረገ ማለት፡- የሚፈልገውን ነገር ከአላህ ለማግኘት፣ ከሚፈራው ነገር በአላህ ለመጥጠበቅ ጌታውን አላህን አጥብቆ ለመነ፣ ተማጸነ ማለት ነው፡፡ "ዱዓእ" ልብ ከምላስ ጋር በመጣመር ከሚፈጸሙ የዒባዳ ዘርፎች ውስጥ የሚመደብና ተቀዳሚ ተግባርም ነው፡፡
ዱዓእ በዱዓነቱ ብቻ ለባለቤቱ አጅር ያስገኛል፡፡ ሶላት የሰገደ በሶላቱ፣ ዘካት ያወጣ በዘካው፣ ሶደቃህ ያወጣ በሶደቃው አጅር እንደሚያገኘው፤ እጁን ወደ ላይ አንስቶ ያ አላህ! ያ ረቢ! የሚል ጌታውን የሚማጸን ባርያም የዱዓውን ምላሽ ወዲያው ቢያገኝ፤ ወይም ምላሹ ቢዘገይም በዱዓው ብቻ አጅርን ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ዱዓእ ዒባዳህ (አምልኮ) ነውና!፡፡
ከአቡ ሀይደር ትምህርት የተወሰደ!
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በፌስቡክ ለመከታተል
Www.fb.com/islamictrueth
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች...
🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው የተገበሩት ተወዳጅና ሱናህ ዒባዳህ ነው።
የተራዊሕ ሰላት በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት፤
ከነዚህም በጥቂቱ:-
① ቀኑን በጾም፣ ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች መሆን ያስችላል።
② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኝበታለን።
③ ተራዊሕ በዛ ያለ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን።
④ ከወንጀልና ከማይጠቅሙ ነገሮች ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን።
⑤ ዒባዳህ ላይ መታገስን እንማርበታለን።
⑥ አመቱን ሙሉ ሰላተል-ለይል ለመስገድ ልምምድ እናደርግበታለን።
⑦ በተደጋጋሚ ከኢማምና ከማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል።
⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል።
⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል።
①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን።
①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል።
①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅና ዲን ላይ ቀጥ ማለት ለሚፈልገው ወጣት መልካም አርዓያና ማበረታቻ እንሆናለን።
①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እንረዳበታለን።
①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማታችን እንገሰጻለን፤ እንዲሁም የተለያዩ አንቀጾችን በተደጋጋሚ በመስማታችን ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራር ለማወቅም ይረዳናል።
①⑤ በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን።
①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እናገኛለን።
①⑦ ለሰላት ረጅም ጊዜ መቆማችን የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፤ ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውምና።
①⑧ ሰግደን ስንመለስ አላህ የሚወደውን ስራ በመስራት የሚገኘውን የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን።
💠ሌሎችንም የዱኒያም የኣኺራህ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን መቼም አንተው! አላህ ያግራልን።
اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين
✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ ረመዷን 1444 ዓ.ሂ
🔸 🔹 🔸 🔹 🔸 🔹
🌐/channel/ahmedadem
8 ሰሂህ የነብያችን ሀዲሶች ስለ ረመዷን ወር ትሩፋት!
ትርጉም በፅሁፍ ©Tᴏʟᴇʜᴀ Aʜᴍᴇᴅ
ከ ድግምት፣ ከክፉ ዐይን(ምቀኝነት) ለመጠበቅ የሚወሰዱ ቅድመ ጥንቃቄዎች!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው!
1) ሙአዊዛትን(ሱረቱል ኢኽላስ፣ ፈለቅ፣ እና ናስ ምእራፎችን) ደጋግሞ ማንበብ!
ሰኢድ አል ኸድሪያ(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከጅንና ከአይነ-ናስ መጠበቂያን ይጠቀሙ ነበር። እነኚህ ምዕራፎች በወረዱላቸው ጊዜ ግን የተቀሩትን(መጠቀምን) ትተዋል። ሲሉ አስተላልፈዋል። [ኢብኑ ማጃህ ዘግበውት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል]
2) በረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተነገሩን የዘውትር ዱአዎችን መጠቀም።
ማለትም የጠዋት፣ የማታ፣ የመኝታ፣ ከሰላት ቡኃላ እንዲሁም ሌሎችን ዱአዎች የሚባሉትን ያለማቋረጥ ማድረግ!
3) ለማድረግ ያሰብነው ነገር በይፋ ሳንገልፅ በፊት ጉዳያችንን መፈፀም!
ምክንያቱም አይነ-ናስና ምቀኝነት መነሻው አድናቆት ነውና። ለዚህም ነው ለሙአዝ ኢቢኑ ጀበል(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አውስተዋል፦
"ማድረግ የምትሹትን እስክታከናውኑ ድረስ፤ ባለመናገር በዝምታ ታገዙ! ለባለፀጋ ሁሉ ተቀናቃኝ(ምቀኛ) አለበትና።" [በይሀቂ ዘግበውታል]
4) የሚያምር ነገር ስናይ ተበሩክ(መባረክን መፀለይ) ማድረግ!
አንድ አማኝ በወንድሙ(በእህቷ) ላይ የሚያስደምም ነገር ሲመለከት "ማሻአላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ፣ ማሻአላህ"(አላህ ያሻው ተፈፀመ። በአላህ እንጂ ሀይል የለም! እና መሰል ዱአዎችን ልንል ይገባል።
መልካም ነገር አይቶ ይህንን ዱአ ያለ ጉዳት አይደርስበትም!
አነስ(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አውስተዋል፦ "አንዳች የሚያስደምመውን(የማረከውን) ነገር ባየ ጊዜ እንዲህ ያለ አንዳችም አይጎዳውም። *ማሻ አላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ ለም የዲሩ*(አላህ የሻው ተፈፃሚ ሆነ፣ በአላህ እንጂ ሃይል የለም።) [ኢብኑ ስሪን ዘግበውታል]
5) ተውሂዳችን ማጥራትና ማስተካከል!
አላህን የሚፈራ ሰው አላህ መመኪያ መጠበቂያ መሸሻ ይሆነዋል። አላህን የሚፈራ፤ ለእርሱ መውጫ ያበጅለታል።
ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ወቅት ከነቢዩ ጋር ነበርኩኝ እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ:- ልጄ ሆይ! ጥቂት ቃላትን አስተምርሀለሁ! አላህን አስታውስ እርሱ ይጠብቅሀል፤ አላህን አስታውስ ቅርብህ ሆኖ ታገኘዋለህ፤ መጠየቅህ የፈለግክ ጊዜ አላህን ብቻ ጠይቅ፤ እርዳታን ስትሻ ከአላህ ብቻ እርዳታን ፈልግ፤ ጠንቅቀህ እመን፣ አላህ ይጠቅምህ ዘንድ የወሰነው እንጂ ፍጥረታት ሁሉ ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አይጠቅሙህ፤ እንዲሁም ፍጥረታት ሁሉ ሊጎዱህ ቢሰባሰቡ በአንዳች አይጎዱህም በእርግጥ አላህ ሊጎዱህ ቢወስነው እንጂ።” (አል-ቲርሚዚ ሀዲስ ቁጥር 2442)
6) ተውበት(ንሰሀ) በማድረግ ወደ አላህ መመለስ!
ከጥፋት ታቅበን ንሰሀ(ተውበት) ማድረግ፤ ከብዙ አስከፊ ነገሮች እንደሚያስጥለን እሙን ነው። እንዲሁም ከእንደዚህ ያለ በሽታ ይገላግለናል።
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ [ሱረቱል ሹራ 30]
የአላህ ፍቃድ ከሆነ በሚቀጥለው ክፍል በሰው አይን የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው አንዳንድ ምልክቶችን እናያለን!
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋና ጠቃሚ መረጃ በዚህ ይከታተሉን!
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በፌስቡክ ለመከታተል
Www.fb.com/islamictrueth
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
ለረመዷን አቅመ ደካሞችን የወር አስቤዛ በመስጠት የማስፈጠር ስራችን ዘንድሮም በአሏህ ﷻ ፍቃድ እናካሒዳለን። በዚህ መልካም ተግባር ላይ ተሳታፊ ለመሆን ለአንድ ቤተሰብ ወርሐዊ ወጭ 3,000 ብር ሲሆን የአቅምዎን በመደገፍ ማስፈጠር ይችላሉ።
ድጋፍዎን ለማድረግ በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አካውንት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በሒዳያ የቴሌግራም ቁጥር መላክ ይችላሉ፦
1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር ቁጥር - 8212
ደረሰኙን ለመላክ በቴሌግራም፦
t.me/Hidayaislamiccenter
የድግምት ህክምና መንገዶች
ድግምትን ከተደገመበት ግለሰብ ላይ መፍታትና ማከም “አል-ኑሽራ” ተብሎ ይጠራል፡፡
ሸይኽ ሱለይማን ቢን አብደላህ ቢን መሐመድ ቢን አብድልወሀብ ከአቢ አልሰዓዳት “ተይሲሩ አል አዚዝ አል ሀሚድ” ከተባለው መፅሐፍ ላይ በመውሰድ ሲያብራሩ፦
«አል ኑሽራ ጂን የተለከፈውን ግለሰብ የማከምና ሩቃ የማድረግ ሂደት ነው፡፡ አል ኑሽራ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በሽታው ለውጦት የነበረውን ግለሰብ ስለሚያስወግድለት ነው» ብለዋል፡፡።ሸይኽ መሐመድ ቢን አብድልወሀብ ከኢብኑ አልቀይም እንዳወሩት “አል ኑሽረቱ” ድግምትን ከተደገመበት ግለሰብ ማላቀቅ ነው፡፡ እሱም ሁለት አይነት ነው፡፡
አንደኛው፦ ድግምት በድግምት መፍታት ይህ የሰይጣን ተግባር ነው፡፡ የሀሰን ንግግርም “አል ኑሽራ ከድግምት ነው” የሚለውና “ድግምትን ደጋሚው እንጂ ማንም አይፈታውም” የሚለው ንግግር የሚተረጐመው በዚህ ነው፡፡ ድግምት አድራጊውና ድግምት የተሰራበት ግለሰብ ሰይጣን ወደሚወደው ነገር በመቃረብ ድግምቱ ውድቅ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ የተፈቀዱ ንባቦችን መጠበቂያዎችንና መድሃኒቶችን በመጠቀም መፍታት የተፈቀደ ነው፡፡ የመጀመሪያው አይነት በጃቢር ሀዲስ የተጠቀሰውን ትርጉም የያዘ ነው፡፡
ነብያችን ﷺ ስለ አል ኑሽራ ተጠይቀው «እርሱ የሰይጣን ተግባር ነው» ብለዋል፡፡ ይኸውም ድግምትን በድግምት መፍታት ነው። ይህ አይነቱ ድግምት ወደ ሰይጣን በመቃረብ ካልሆነ በስተቀር አይሟላም ምክያቱም ሰይጣናትና ደጋሚዎቹ እስካልታዘዟቸውና በአላህ እስካልካዱ እና በዚህ ተግባራቸው ወደ እነርሱ ካልተቃረቡ በስተቀር አይታዘዟቸውም፡፡ ስለዚህ አንድ ግለሰብ ድግምቱ እንዲፈታለት ወደ ደጋሚው ጋር ሲሄድ ለሰይጣን እንዲያርድ ወይም በማንኛውም መቃረቢያ ወደ ሰይጣን እንዲቃረብ ያዘዋል፡፡ ይህ አይነት ተግባር የተከለከለ ለመሆኑ ማንም አይጠራጠርም፡፡ ምክንያቱም በአላህ ላይ መካድና ማጋራት ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዳሉት “እርሱ የሰይጣን ተግባር ነው” ይህም በሽታን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም፡፡ ምክንያቱም ደጋሚ እርኩስ ነው እርኩስ የሆነ ደግሞ የሰውን ጉዳት እንጂ ማስተካከልን አያስብም፡፡ ደጋሚው የወንድሙን ድግምት መፍታት አይሆንለትም ምክንያቱም በወንጀል ላይ አንድ ናቸውና፡፡ ነገር ግን ግራ ሊያጋባውና ለሰይጣን ስለት የገባውን ይሞላ ዘንድ በሽታውን ረገብ ያደርግለታል፡፡ ከዚያም በድጋሚ ይመለስበታል፡፡
ሁለተኛ አይነት፡- የተፈቀደ ህክምና ሲሆን ይኸውም የተፈቀደ ሩቃ ከቁርአን፣ ከአዝካር፣ ከትክክለኛ ዘገባ ከነብያችን በተገኙ መጠበቂያዎች፣ የተፈቀዱ መድሃኒቶችን፣ የዘምዘም ውሃን የመሰለ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ የዘይቱን ዘይት፣ የመዲና ተምር መጠቀም ይቻላል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ሁሉ በትክክለኛ ዘገባ ከነብያችን(ﷺ) የተገኙ ናቸው፡፡
ድግምትን ለመከላከል የሚረዱ የመድሃኒት ዓይነቶችና የአጠቃቀማ ሁኔታ!
1) የዘምዘም ውሃን ከሲድር ጋር ከተነበበት በኃላ መታጠብ ፣ ሰባት የሲድር ቅጠል በመቀጠንስ እናቀርባለን ከዚያም በደንብ አድርገን እንፈጨዋለን ከዚያም በዘምዘም ውሃ ውስጥ እንከተዋለን፡፡ ሲድር በተደባለቀበት ውሃ ውስጥ ሩቃ ሸርዒያ (የተፈቀደ ሩቃ) እና በሲህር ዙሪያ የሚናገሩ ቁርአናዊ አንቀፆች እናነባለን፡፡ ከዚያም በሽተኛው ሶስት ጊዜ ከተጐነጨ በኃላ በየቀኑ ለሰባት ቀን ያህል ይታጠብበታል፡፡ ይህን ካደረገ በአላህ ፍቃድ ይፈወሳል፡፡ ሲህርን በመፍታትና ቋጠሮን በማስፈታት ተሞክሮ ውጤታማ የተሆነበት ነው፡፡
2) ማርና የተፈጨ ጥቁር አዝሙድ
አንድ ኪሎ ትኩስ የሆነ ማር እናዘጋጃለን፡፡ በሻይ ማንኪያ አንድ የተፈጨ ጥቁር አዝሙድ በደንብ አድርገን ከማሩ ጋር እንለውሳለን፡፡ ከዚያም የተፈቀደውን ሩቃ እና ከሲህር ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቁርአናዊ አንቀፆችን እናነባለን፡፡ ከዚያም ዘውትር ጠዋት ከምግብ በፊት በሾርባ ማንኪያ አንድ እንወስዳለን፡፡ ይህ በአላህ ፍቃድ በመጠጣት ወይም በመብላት ድግምት ለተሰራበት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
3) የመዲና ተምር
ዘውትር ጠዋት ምግብ ከመመገብ በፊት ሰባት ፍሬ የመዲና ተምር መመገብ፡፡ አላህ በዚህ ሰበብ ድግምትም እንዳያገኘው ይጠብቀዋል፡፡ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት፦
«ዘውትር ጠዋት ሰባት ፍሬ የመዲና ተምርን የበላ በዛ ቀን በመነደፍና በድግምት አይጠቃም፡፡» [አህመድ ዘግበውታል]
4) የዘይቱን ዘይት
ንፁህ የዘይቱን ዘይት ማዘጋጀት ከዚያም የተፈቀደውን ሩቃ ማንበብ ከዚያም በሽተኛው ዘውትር ከመተኛቱ በፊት ሰውነቱን መቀባት። በአላህ ፍቃድ ድግምትን ለመከላከል የሚረዱ ናቸው!
አላህ እኛንም ቤተሰባችንን እንዲሁም ሙስሊሙን ዑማ ከዚህ መጥፎ በሽታ እንዲጠብቀን እንለምነዋለን!
#ሺፋእ
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!
/channel/islamictrueth
ዛሬ 🗓️ March 8️⃣ የሴቶች ቀን ነው አሉ 😀 🧕🏻 የሴቶች ነፃነት በሚል ሰበብ፣ ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷና በባሏ ላይ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
🧕 ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላለው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡
🧕🏻 እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡
🧕 አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይደሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
🧕🏻 እህቴ ሆይ! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩ ንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል❓እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል❓
🧕 ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል❓ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል❓ እመኚኝ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡
🧕🏻 ለሰው ልጆች አጥፊና አውዳሚ ከሚባሉት ሁለት ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የስሜትን ፈተናን በሂጃብ ልጎም እንዳታስሪው እስልምና ያስተምርሽል፣ ከዚህ ፈተና መጠበቁ ዋነኛ ተጠቃሚውም ተጎጂዋም አንቺ ነሽ
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብ - ዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡
🧕 ሸሪዐውን የተከተለ ኢስላማዊ አለባበስ የአማኝ ሴት መገለጫ የንጽህናሽ ማስታወቂያ ነው። እንዳትደፈሪና ክብርሽ እንዳይነካ መከላከያሽ ነው።
🧕 ሂጃብ በመልበስሽ ወንዶች እንቺን አይተው ከመፈተን ይጠበቃሉ፡፡ ኧረ እንዲያውም አይናቸውን ሰበር ለሚያደርጉ ብርቅዮዎች ብቻ ሳይሆን ላይ ታቹን ለሚያማትሩትም አደብ ታስገጂበታለሽ
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 በተቃራኒው የምትገላለጪ ከሆነ የፈተና የጥፋት በር በማይዘጋ መልኩ ይበረገዳል፡፡ በዘመናችን ያለውን ሁኔታ ያስተዋለ አላህ ያዘነላት ካልሆነች በስተቀር ሴት ልጅ በገዛ እራሷ ክብሯን አሽቀንጥራ ወርውራዋለች፡፡
🧕 አይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ዳሌሽ ብለው በማማለል የማይረግብ ስሜታቸው ማርኪያ ሎሌ ያደርጉሻል፡፡ አንቺም ፊቴ አምሮ ቅርፄ ተስተካክሎ ይሆን እያልሽ የነሱ የወሲብ ማርኪያ ትሆያለሽ
✴️ መገላለጥ አንዱ የቂያማ መድረስ ምልክት ነው፣ ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች በስፋት መታየት። ከፊል ገላቸውን ይሸፍናሉ። የሰውነታቸው ቅርፅ ለይቶ የሚያሳይ ጥብቅብቅ አልባሳትን ይለብሳሉ።
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡
🧕 በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ
🧕🏻 ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡
🧕 ተጠንቀቂ!! ከሸሪዐው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቅሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡
🧕🏻 ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከኢስላም ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው፣ ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ተቆርቋሪ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡
🧕 ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ ጆሮሽን ሰጥተሽ?! ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡
🧕🏻 በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት ውስጥ ይነክርሻል፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🧕🏻 ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ❓እውነት ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከ1400 አመት በፊት ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት❓
🧕 እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ/አለብን፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡
⚠️ እናም እልሻለሁ በMarch 8 ሳይሆን ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡
የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📩 ሼር በማድረግ ለእህቶች እንዲደርሳቸው ያድርጉ 🤲🏻 አላህ ሆይ፣ ቅኖችና ለሌሎችም መቀናት ምክንያት የሚሆኑ ሰዎች አድርገን
📗ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “ወደ ቅን መንገድ የተጣራ ሰው፣ የተከተሉት ሰዎች ሁሉ የሚያገኙት አጅር ምንም ሳይጎድልባቸው ለሱም ይኖረዋል…"📗(ቡኻሪና ሙስሊም)
➡ ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen
⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪
🅾️ በተወሰኑ ሰዎች/ብሄረሰቦች ዘንድ ከረመዷን ዒድ ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን (ሸዋል 8) ሸዋል ዒድ ወይም ትንሹ ዒድ በማለት ዐመት እየጠበቁ ያከብሩታል
⚠️ የሸዋል/ትንሹ ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡
🅾️ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን 6 ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🅾️ የሸዋል/ትንሹ ዒድ ከሚያከብሩበት ምክንያቶች ውስጥ የተወሰነው ይህን ይመስላል፡-
የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ረመዷንንም ሸዋልንም እንጨርስና 7ተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡
ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ ጋር ለመዘያየር አይበቃም የሚል ነው
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🅾️ እዚህ ጋር ሊታሰብባቸው የተገቡ ጉዳዮችን ቀጥሎ እናኛለን፡-
1️⃣ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡
እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡
2️⃣ የሆኑ ሰዎች ልክ እንደ መደበኛ ዒድ ቋሚ ልምድ አድርገው ሳይዙ በሆኑ ቀናቶች ላይ ቢሰባሰቡ ይሄ አይጠላም። ነገር ግን ወቅት በዞረ ቁጥር አብሮ የሚዞር ልምድ አድርጎ መያዙ የተጠላ ነው። ሸሪዐን መቀየር እንዲሁም የተደነገገውን ካልተደነገገው ጋር ማመሳሰል አለውና።
3️⃣ ይህ የሸዋል ዒድ ተብሎ በሰዎች የተወሰነው ቀን፣ በዘልማድ ሲተገበር ቆይተዋል፣ አሁንም በአንዳንድ አከባቢዎች በሰፊው ሊከበር ዝግጅት እየተደረገ ነው። ይህም በብዙ ሙስሊሞች ዘንድ ስድስቱ የሸዋል ቀኖች መጾም ያለባቸው ከዒድ ማግስት ጀምሮ - ማለቅ ያለበት ደግሞ በሸዋል 8 እንደሆነ በሙስሊሙ ዘንድ አምኖ እንዲቀብል ሆነዋል
ይህ ደግሞ ሰዎች ሸዋልን እንዳይጾሙ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው፣ ሰው በረመዳን የደከመውን ሰውነቱን ማሳረፍ፣ መብላት መጠጣት በሚፈልግበት ሰዐት ጾም መጾሙ ከባድ ይሆንበታል፣ ወሩ ሳይወጣ በተለያየ ቀን በማፈራረቅ መጾም እንደሚቻል በዚህ የሸዋል ዒድ ምክንያት ተዘንግተዋል።
4️⃣ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፣ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡
5️⃣ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ይህን ማድረግ የሚቻለው ያለው ማነው?
የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም?
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🅾️ ነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው። እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው
📗አነሥ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሐዲሥ፡-
"የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፣ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው።
የአላህ መልእክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል እነርሱም፡- ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን" አሏቸው
📗(ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745)
🤲 አሏህን በብቸኝነት አምልከን፣ የመልእክተኛውን ፈለግ ተከትለን የምንሞት ባሮቹ ያድርገን! አሚን
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📩 በሸዋል ዒድ ዙርያ የግንዛቤ እጥረት ስላለ ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ
➡ ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen
⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪
ይህ ነሺዳ ለፊሊስጤም ህዝቦች አሊያም ከቂያማ ምልክቶች አንዱ የሆነዉ ስለመህዲ የሚዘምር ሳይሆን ስለ ሺዐ ኢማም መህዲ የተዘመረ ነዉ። የነሺዳዉ ትርጉሙ በአማርኛ ተተርጉሟል ተመልከቱ። ለተጨማሪም መረጃ በጓግል ላይም ተመልከቱ።
/channel/islamictrueth
ኢድ ነገ ጁምዐ ነዉ!
እንኳን ለ 1444 አመተ ሂጅራ ኢድ አልፈጥር በዐል በሰላም አደረሳቹ።
በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ ይሁንላቹ!
አላህ ፆማችንን መልካም ስራችንን ይቀበለን!!!
🗓️ ዛሬ ለይሉ 2️⃣7️⃣ ነው
🌔 ለይለተል ቀድር ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ተኛዋ ለሊት ላይ ነው። 27ተኛዋ ለሊት ለይለተል ቀድር የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው ለዚህም የሀዲስ ማስረጃዎች አሉ። (ፈታዋ አል-ላጅናህ አል-ዳኢማህ ሊኢል-ቡሑት አል-ኢልሚያህ ወአል-ኢፍታ፣ 10/413)
⚠️ ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሌሎች ለሊቶች አትሆንም ማለት አይደለም።
👉ዛሬ ለሊቱን በዚክር፣ በዱዓእ፣ በኢስቲግፋር፣ በቁርኣን፣ በለይል ሶላት፣ በነቢያችን ላይ ሶላዋት በማውረድ… እንበራታ፡፡ አላህ ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን
🌓 ለይለተል ቀድር በኢባዳ ፈልገው እንጂ በረንዳ ላይ በመሆን ሰማይ ላይ የሚንቀሳቀስና የሚበር ነገር በመፈለግ አታባክነው። ትልቅ ሞኝነት ነው
🌓 አንዳንዶች ኮከብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲወረወር ሲያዩ ለይለተል ቀድር አየነው በማለት ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ቤታቸው የሚገቡም አሉ
📩 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ
➡ ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen
⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪
ዝንብ ለማንሳት ዱላ ማንሳት እቃ ያሰብራል!
«ዳእዋ ላይ መረጋጋት በጣም ያስፈልጋል። አንድን መጥፎ ተግባር ያየ ሰዉ፤ ያንን ስህተት ለማስወገድ የሚያደርገዉ የሚወራጨዉና አደብ ማጣቱ የበለጠ ሌላ መጥፎ ነገር ያመጣል። ዝንብ ለማንሳት እሽሽ ብትላት ትሄዳለች። ነገር ግን ዱላ ካነሳህ ዝንቧም ታመልጥሀለች እቃም ታሰብርህና ትፀፀታለህ። ስለዚህ ከመቸኮል የምናገኘዉ ጥቅም የለም። ከመረጋጋት ግን ብዙ ጥቅም እናገኛለን።»
ሼይኽ መሀመድ ሀሚዲን
ጣፋጭ አቀራር #23
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
የረመዷን ስጦታ
ረመዷን ሙባረክ ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት!
በ 13 አርስት የተሰደረ መጣጥፍ በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት!
1. ሶውም
/channel/Wahidcom/3136
2. የጦም ትሩፋት
/channel/Wahidcom/3470
3. ረመዷን
/channel/Wahidcom/2727
4.. የረመዷን ወር
/channel/Wahidcom/3107
5. የክርስትና ጦም
/channel/Wahidcom/3176
6. የጨረቃ አቆጣጠር
/channel/Wahidcom/2717
7. ጨረቃ እና ኮከብ
/channel/Wahidcom/2360
8. የሚታሰሩ ሰይጣናት
/channel/Wahidcom/2724
9. ሡሑር
/channel/Wahidcom/2726
10. ተራዊህ
/channel/Wahidcom/833
11. ኢዕቲካፍ
/channel/Wahidcom/2286
12. ለይለቱል ቀድር
/channel/Wahidcom/2289
13. መሓላ እና ማካካሻው
/channel/Wahidcom/2336
ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ!
ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
#ረመዳን ነክ ጉዳዩች
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿فَصْلُ ما بيْنَ صِيامِنا وَصِيامِ أَهْلِ الكِتابِ، أَكْلَةُ السَّحَرِ.﴾
“በእኛ ፆምና በአህለል ኪታቦች ፆም መካከል ያለው ልዩነት ሱሑር መብላት ነው።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1096
ጆይን፡‐ /channel/BuhariMuslimAmharic
#ረመዳን ነክ ጉዳዩች
#የመንገደኛ ፆም
ሐዲስ ①
አነስ (رضي ﷲ عنه) እንዲህ ይላል፦
﴿كُنّا نُسافِرُ مع النبيِّ ﷺ فَلَمْ يَعِبِ الصّائِمُ على المُفْطِرِ، ولا المُفْطِرُ على الصّائِمِ.﴾
“ከረሱል (ﷺ) ጋር መንገድ እንወጣ ነበር። የሚፆመው ያፈጠረውን (የማይፆመውን) አያነውርም። የማይፆመው የሚፆመውንም እንደዛው።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1947
ሐዲስ ②
ጃቢር (رضي ﷲ عنه) እንዲህ ይላል፦
﴿كانَ رَسولُ اللَّهِ ﷺ في سَفَرٍ، فَرَأى زِحامًا ورَجُلًا قدْ ظُلِّلَ عليه، فَقالَ: ما هذا؟، فَقالوا: صائِمٌ، فَقالَ: ليسَ مِنَ البِرِّ الصَّوْمُ في السَّفَرِ.﴾
“ከረሱል (ﷺ) ጋር ጉዞ ላይ ነበርን።
ሰዎች ከበውት ያጠለሉለትን ሰው አይተው ይህ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ። ‘ፆመኛ ነው’ አሉዋቸው። ጉዞ ላይ ሆኖ መፆም መልካም አይደለም አሉ።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1946
ሐዲስ ③
ከአዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ: ቢን ዐምሪ አልሰለሚይ ለነቢዩ (ﷺ) እንዲህ አላቸው፦
﴿أأَصُومُ في السَّفَرِ؟ - وكانَ كَثِيرَ الصِّيامِ -، فَقالَ: إنْ شِئْتَ فَصُمْ، وإنْ شِئْتَ فأفْطِرْ.﴾
መንገደኛ ሆኜ እፆማለሁን? ብዙ ይፆም ነበር። ነቢዩም (ﷺ) አሉት፦ ከፈለክ ፁም። ከፈለክ ደግሞ አፍጥር።
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል 1943
ጆይን፦ /channel/BuhariMuslimAmharic
🛑 ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብና ለመስጂድ ጀመዓዎቸ የተላለፈ ጥሪ
ነገ እሁድ መጋቢት 3 | 2015 ከጠዋቱ 12:30 ሰዐት ጀምሮ ጉለሌ በሚገኘው የሙስሊሞች መካነ መቃብር ቅጥር ግቢየማይቀርበት ቀጠሮ ይዘናል።
ቀጠሮው ወጣት ወንዶችን ይመለከታል።
ስራው ወደጫካነት ተለውጦ የጅቦች መራቢያ፣ የሌቦች መደበቂያ፣ የሱሰኞች መነሀሪያ የሆነውን ጉለሌ መካነ መቃብርን ጫካውን በመመንጠር ምቹ የቀብር ስፍራ ማድረግ ነው።
በዚህ ትልቅ አጅር በሚያስገኘው በጉልበታችን ብቻ በሚሰራው ኸይር ስራ ላይ ወላጆች እና ሴቶች ወንድ ልጆቻችሁን እና ወንድሞቻችሁን በመላክ እና በማበረታታት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
ነገ በፍፁም አይቀርም ጠዋት 12:30 ሰዐት ላይ ጉለሌ የሙስሊም መቃብር እንገናኝ።
አድራሻውን ለማታውቁ
🛑 ከፒያሳና አካባቢው ለምትመጡ:-
እንቁላል ፋብሪካ አደባባዩን አልፋችሁ ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ በስተ ግራ በኩል
🛑 ከአለም ባንክ፣ ጦርሀይሎችና አካባበከው ለምትመጡ:- ከአውቶብስተራ ወደ ፓስተር ስትሄዱ በስተቀኝ በኩል ሁለተኛ አስፓልት ቂያስ ወደ ሀግቤስ በሚወስደው መንገድ ላይ ወደ ግራ በሚወስደው በመታጠፍ በስተቀኝ በኩል ቀብሩን ታገኙታላችሁ
🛑 ከአስኮና አካባቢው ለምትመጡ:- ከፓስተር አደባባይ እንዳለፋችሁ ኖክ ማዲያ ፊትለፊት በስተቀኝ በኩል ወደ ጨው በረንዳ ስትታጠፉ ቀብሩን በግራ በኩል ታገኙታላችሁ
🛑 ከጥቁር አንበሳና አካባቢው ለምትመጡ ደግሞ አንዋር መስጂድን አልፋችሁ በቀኝ በኩል ወደ አዲሱ ገበያ የሚወስደውን አስፓልት አልፋችሁ ወለጋ ሆቴል በሚገኝበት አስፓልት ወደቀኝ በመግባት ውሀ ልማቱ ፊት ለፊት ታገኙታላችሁ።
ለበለጠ መረጃ
0962 38 37 37
0911 11 42 42
ይደውሉ
⛔️ ሻዕባን 15 ን በተመለከተ ወሳኝ ማሳሰቢያ
🎙 በኡስታዛችን ሑሴን ዒሳ ሀፊዘሁላህ
🔗 Download Link
/channel/nesihastudio/2038