ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
አስሩ ወርቃማ ቀናቶች!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشْرِ﴾
“በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆንባቸው ቀናት የሉም።”
📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 757
ጆይን፦ /channel/BuhariMuslimAmharic
እንኳን ለአባቶች ቀን...
ዛሬ ዛሬ ከቁርአን ከሀዲስ ህይወት መዉጣታችን የሚያመላክቱ በርካታ ነገሮች እየታዩብን ነዉ። አንድ የነብዩ ሙሀመድ(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ አለ እሱም:- የከሀዲያን መንገድ እግር በእግር ትከታተላላቹ ብለዉ ነበር። እነሱን ያልመሰልንበት ነገር የለም። አበላላችን፣ አኗኗራችን በእነሱ ተንጠልጥለናል።
በጣም ከሚያበሳጩ ነገሮች ደግሞ ቀን እየተሰጣቸዉ የሚከበሩና የሚታወሱ ነገሮች አንዱ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር ፈፅመዉ ሊሄዱ የማይችሉ 2 በአላት አሉ እነሱም የእናትና የአባት የሚባሉት ናቸዉ።
አላህ በቅዱስ ቁርአን ላይ እኔን ብቻ ተገዙኝ ብሎ ካስጠነቀቀዉ ከባድ ትእዛዝ በመቀጠል ያስቀመጠዉ ለወላጆች መልካም መዋልና መታዘዝ ነዉ። በአመት አንዴ እንድናስባቸዉ ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ሙሉ ማሰብና መንከባከብ እንደሚገባን የሚያዝ ዲን ነዉ ያለን። በል እንደዉም ከሞቱም በኃላ ምህረትን እንድንለምንላቸዉም የሚያዝም ጭምር ነዉ።
ፎቶ እየፖሰቱ አባቴ እናቴ እወዳቹሀለዉ በማለት ፍቅርን መግለፅ አይቻልም። እዉነተኛ ፍቅር በተግባር ማሳየትን ይፈልጋል። ሲጠሩን አለመበሳጨት፣ ሲሉኩን ወዴት፣ ሀሳባቸዉን ማድመጥ፣ ዱአቸዉ ለመቀበል መሽቀዳደም፣ ከእርግማናቸዉ መጠበቅ።
ይሄን ካደረግን በእዉነትም ወደናቸዋል ዱንያ አኼራችንም ያምራል። አለበዛ እራሳችንን አንሸዉድ!!!
/channel/islamictrueth
ማስታወሻ:- ይህ ሀዲስ በግልፅ እንደሚያሳየን በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፈን በሸሂድነት ብይን ተሰጥቶበታል። ነገር ግን የእያንዳንዳችን ኒያ(ሀሳባችን) የሚያዉቀዉ አላህ ነዉ። በዚህ ተግባር ላይ የአላህን ምንዳ ብቻ በማሰብ ለሚሰማራ ስራዉ አማረ። በዚህ ተግባር የተሰማራ ሁሉ ደግሞ ሸሂድ ነዉ ማለት አንችልም ምክንያቱም የዉስጡን አላህ ብቻ ስለሚያዉቅ። በተመሳሳይ ሁኔታም ሸሂድ አደለም ማለትም አንችልም። ዉስጥ አዋቂዉ አላህ ስለሆነ፤ ነገር ግን በዚህ ተግባር ላይ ሆኖ ስናገኘዉ ግን ከአላህ የሸሂደነት ማእረግ እንዲላበስ እንመኝለታለን።
Читать полностью…የህዝበ ሙስሊሙን ቁልፍ ችግር መፍታት የሀገርን ችግር መፍታት ነው። ችግሩንም አለመፍታትም የሀገር ችግር እንዲቀጥል መፍቀድና መስማማት ነው።
Читать полностью…መስጂዶች ለመሬት ወረራ የሚሰሩ አይደሉም፡፡ የግለሰብ ሀብት ተደርገው የሚቆጠሩ አለመሆናቸውና በህዝብ ሀብት ተሰርተው ለትውልድ የሚያገለግሉ እሴት መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡
#በመስጂዶች_ፍርስራሽ_የምትገነባዋ_ከተማ_ሸገር
#ሕገወጥ_አስተዳደር_እንጂ_ሕገወጥ_መስጂድ_የለም!
#ዓሳ_ያለ_ውሃ_ሙስሊም_ያለ_መስጂድ_መኖር_አይችሉም!
#መስጂዴን_አታፍርስ_ያፈረስከውንም_መልስ።
#Magaala-Diigama-Masjiidota-Irratti-Ijaaramtu-Shaggar
#Bulchiinsa-Seeran-Alaa-Malee-Masjidni-SeeranAlaa-HinJiru
#QurxummiinBishaanMalee-MuslimniMasjiidaMaleeJiraachuuHinDanda'an
#MasjiidakooHinDiiginKanDiigdesDeebisi
የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ከእናንተ አንዳችሁም በአላህ ላይ መጥፎን ጥርጣሬ እያለው መሞት የለበትም።» [ሶሂህ ሙስሊም]
/channel/islamictrueth
አቡ ሁረይራ(ረዲየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነብዩ ሙሀመድ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«አላህ ዘንድ ተወዳጅ ቦታ መስጅድ ነዉ።» [ሶሂህ ሙስሊም]
/channel/islamictrueth
አቡ ሁረይራ(ረዲየላሁ አንሁ) እንዳወሱት ነቢዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ዕውቀት(ዒልም) ይሰበሰባል፣ መሃይምነት መከራና፣ 'ሐርጅ' ይባባሳል። "የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) ሆይ ! 'ሐርጅ' ምን ማለት ነው" የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። በእጃቸው የመገዳደል ምልክት አሳዩ። የቂያማ ምልክቶች ናቸው።» [ሶሂህ ቡኻሪ ዘግበዉታል]
/channel/islamictrueth
«ወላሂ የትኛዉም ሀይማኖት፣ የትኛዉም System፣ የትኛዉም የህይወት መንገድ፤ የትኛዉም ነገር ኢስላም እንደተጠቃዉ ቢጠቃ ኖሮ ወላሂ ከአመታት በፊት ይጠፉ(ይፈርሱ) ነበር። ነገር ግን ኢስላም አሁንም አለ፣ አሁንም እንደቆመ ነዉ፣ አሁንም እየተስፋፋ ነዉ።» ኡስታዝ ሙሀመድ ሆብሎስ
/channel/islamictrueth
ነቢዩ(ﷺ) እንዲህ አሉ:-
«መልካም ዜና ይህ ቁርኣን ፍጻሜው በአላህ እጅ ነው፤ ፍጻሜውም በእጅህ ነው። ስለዚህ ለእናንተ ያዙት። ለራሳቹ አትጠፉም። ከእርሱ በኋላ ፈጽሞ አትሳቱ።» [ሶሂህ ጃሚእ 34]
/channel/islamictrueth
«በአንዳች ነገር የፈለገ ብትጫወት በሃይማኖትህ ግን እንዳትጫወት።» [ኢማሙ ማሊክ]
/channel/islamictrueth
በቤቲንግ ቁማር የተጓዳ ወንድማችን የደረሰበትን ችግር እንዲህ ገልፆል!
ቁማር ከሰይጣን ሥራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው። [ቁርአን 5:90]
አምስት ጥፋቶች ማካካሻ የላቸውም!
ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡- “አምስት ጥፋቶች ማካካሻ የላቸውም፡፡ በአላህ ማጋራት፣ ያለ አግባብ ነፍስን ማጥፋት፣ ሙእሚንን መዝረፍ፣ በጂሃድ ላይ በፍጥጫ ሰዓት መሸሽ እና ያለ አግባብ ገንዘብ የሚበላበት ሀሰተኛ መሀላ!!” [አልኢርዋእ፡ 2564]
/channel/islamictrueth
ቤቲንግ ከአባወራዎች አልፎ ወደ እማወራዎች ተጉዟል!
Betting(የኳስ ዉርርድ) እና መሰል የቁማር አይነቶች የሚያመጡት ተፅእኖ!
1) በእጃችን ያለን ንብረት እስከ መሸጥ ያስደርሰናል።
2) በስራ መበልፀግን ሳይሆን easy money የሆነ አስተሳሰብ በዉስጣችን ገብቶ ከስራ አለም ያሸሸናል።
3) በትዳራችን እና በቤተሰባችን ላይ ሰላምን ያደፈርስብናል።
5) ተማሪ ትምህርቱን እንዳይከታተልና ቦዘኔ እንዲሆን ተፅእኖ ይፈጥራል።
6) ለዚህ ቁማር የሚሆን ብር ስናጣ ከሰዉ እስከ መበደር ከዛም አልፎ ወደ ስርቆት ሁሉ ያስደርሰናል።
7) አላህን እንዳታስታዉስና ሰላትም እንዳትሰግድ ያደርገሀል።
ቁማር የሚያመጣዉ ችግሮች ታላቁ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቁርአኑ በሁለት አንቀፆች አስቀምጦልናል።
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ #ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው። (እርኩስን) ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና #በቁማር በመካከላችሁ
ጠብንና ጥላቻን ሊጥል ኣላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡
ታዲያ እናንተ (ከእነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን? (ተከልከሉ)፡፡» [አል ማኢድህ ፡ 90-91]
/channel/islamictrueth
እናት ልጇን አይነ ስዉር አደረገች እንዴት ካላቹ ቪዲዩን ይመልከቱ!
tiktok.com/@sadamsuleyman
/channel/islamictrueth
🗓️ ነገ ሰኞ June 19/ ሰኔ 12 ወይም ማክሰኞ የዙል-ሒጃ ወር 1️⃣ ብሎ ይጀምራል። አላህ ካላቃቸው እና ካከበራቸው አራት ወራቶች መካከል የዙልሒጃ ወር አንዱ ነው።
ከቀናቶች ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስር ቀናቶችም ያሉት በዚሁ በተከበረው የዙልሒጃ ወር ውስጥ ነው። በዚህ የዙል-ሒጃ ወር ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 🔟 ቀናት ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው።
በእነዚህ ቀናቶች የሚሰራ መልካም ስራ ከሌሎቹ ቀናቶች ከሚሰሩ መልካም ስራዎች በእጥፍ ድርብ ይበልጣል። መልካም ሥራ ከዙል-ሒጃ አሥርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም።
🗓️ ለዛሬ ስለ ዙል–ሒጃ አሥርቱ ቀናትና በውስጡ መሰራት ስለሚገባቸው መልካም ስራዎች እናኛለን፡-
ሁሌም ቢሆን ስለ ዲናችን ወቅቱን የጠበቀ ትኩረት ሊኖረን ይገባል። ረመዳን ሲመጣ ስለረመዳን፣ በሐጅ ወቅት ስለሐጅ ወዘተ ብናተኩርና ብንማማር በዚያ ጉዳይ የበለጠ እንድንጠቀም ያደርገናል።
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🗓️ እነዚህ ቀናቶች ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ ናቸው፣ ረሱላችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጩ (የዙል-ሒጃ) አሥሩ ቀናት ናቸው”። (📗 ሶሒሕ አል-ጃሚዑ ሰጊር 1133)
በእነዚህ ቀናቶች የሚሰራ መልካም ስራ ከሌሎቹ ቀናቶች ከሚሰሩ መልካም ስራዎች በእጥፍ ድርብ ይበልጣል ለዚህም ረሱል (ﷺ) በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ በሌሎች ቀናቶች ከሚሰሩ ስራዎች የበለጠ ተወዳጅ እንደሆነ እንድህ ሲሉ ተናግረዋል፡-
📗ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡-
«አላህ ዘንድ መልካም ስራ ተወዳጅ የሆነበት ከእነዚህ አስር ቀናቶች የበለጠ ማንም ቀን የለም። ሶሐቦች አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ መታገል (ጅሃድ እንኳ) ቢሆን አሉ፣ ረሱልም (ﷺ)፡-
«በነፍሱም በገንዘቡም ጅሃድ ወጥቱ ከእርሱ በምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጅሃድ) እንኳ ቢሆን (በእነዚህ አስር ቀናቶች ከሚሰራ መልካም ስራ አይበልጥም)» አሉ። (ቡኻሪ (2/457) እና ሌሎችም ዘግበውታል)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🗓️ በነዚህ በተከበሩ ቀናቶች ወንጀልን መራቅ አለብን፣ ኢብኑ ረጀብ እንድህ ይላሉ:-
«ወንጀልን ተጠንቀቁ እርሷ በሚታዘንባቸው አጋጣሜዎች መሀርታን ትከለክላለች» «ወንጀል (አላህን ማመፅ ከአላህ እዝነት) የመራቅ እና የመባረር ሰበብ ስለሆነች ተጠንቀቁ» (ለጧኢፉል መዓሪፍ (254)
በእነዚህ 🔟 ቀናቶች ውስጥ ሁሉም መልካም ስራ ይወደዳል ስለዚህ ከእነዚህ መልካም ስራዎች የተገራልንን በመስራት የብዙ አጅር ባለቤት ለመሆን እንጣር። ይህ በእኛ ላይ የተዋለለን የአላህ ትልቅ ኒዕማ እንደሆነ ማወቅ እዚህ ትልቅ ኒዕማ ላይ ጤና እና እድሜ ሰጥቶን በሰላም ከደረስን ይህን ኒዕማ ሳናባክን ሌሎችን በሞት ወይ በበሽታ እንዳለፋቸው እኛንም የሚያልፍብን ቀን ሳይመጣ የተሰጠን እድል ሳያልፍ በአግባቡ እንጠቀም
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🗓️ በእነዚህ ቀናት ከሚሰሩ መልካም ስራዎች መካከል፡-
1️⃣ ሐጅና ዑምራህ፡-
ሐጅ ማድረግ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት አቅሙ ለቻለ ሰው የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ክፍያው ጀነት ነው
📗"ዑምራህ ቀጣዩ አመት ዑምራ እስኪመጣ ድረስ (በመሃል ለተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአት) ማስተሰረያ ነው፣ ትክክለኛ ሐጅ ደግሞ ከጀነት ውጪ ክፍያ የለውም”። (ቡኻሪና ሙስሊም)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
2️⃣ ጾም፡-
የፈለገ ሙሉውን ዘጠኝ ቀን፣ ካልሆነም የቻለውን ያክል መጾም ይችላል
"መልካም ስራ ከዙል-ሒጃ አስርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" በዚህ ሐዲሥ መሠረት ጾም "መልካም ሥራ" የተባለው ሐዲሥ ውስጥ ስለሚካተት በጾሙ የቻለውን ያክል መበርታት
በዙል-ሒጃ ወር 9ኛው ቀን፣ የዐረፋ ቀን ነው፣📗 አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል" (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
3️⃣ አላህን ማውሳት፡-
ዚክር ማብዛት: አልሐምዱሊላ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ተሕሊል (ላኢላሀ ኢለላህ) ተስቢሕ (ሱብሓነላህ) እና ቁርኣን መቅራትን ማብዛት። ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል
📗 ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ነቢዩ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡-
"በነዚህ ቀናት ውስጥ ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢልለሏህ)፤ ተክቢር (አላሁ አክበር)፤ ተሕሚድ (አል-ሐምዱ ሊላህ) ማለትን አብዙ" (አህመድ 7/224)
📗 ዐብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ወደ ገበያ በመውጣት በተክቢራ ሲያሞቁት ሰዎቹም እነሱን ተከትለው ተክቢራ ይሉ ነበር (ኢርዋዑል-ገሊል: አልባኒይ 651)
🗓️ በእነዚህ ቀናት እኔን አስታውሱባቸው ብለዋል አላህ፡-
🟢 ۞ "ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።" ۞ (📖 ሱረቱል-ሐጅ 28)
💬 "የታወቁ ቀኖች" የተባሉት እነዚሁ አሥርቱ ቀናት እንደሆኑ ሙፈሲሮች ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ አላህን በማንኛውም ጊዜ ማውሳትና ማወደስ ከመቻሉ ጋር በነዚህ ቀኖች አወድሱት ብሎ ቀኖቹን ለይቶ መጥቀሱ የተለየ ደረጃና ክብር እንዳላቸው ይጠቁማል
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
4️⃣ ተውበት ማብዛት፡-
🟢 ۞ "…ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።" ۞ (📖 ሱረቱል አሕዛብ 31)
5️⃣ መልካም ሥራዎችን ማብዛት፡-
በኢስላም የመልካም ሥራ በሮች ብዙ ናቸው፡፡ ተቆጥረው አይዘለቁም፡፡ ከኛ የሚጠበቀው ስራው ላይ ተሳታፊ መሆን ነው፡፡ ከቤተሰብ ጀምረን እሰከ ሩቅ ሰው ድረስ አቅማችን የቻለውን ያህል በመርዳት ወደ አላህ እንቃረብ።
6️⃣ ኡዱሕያ፡-
በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ ነው። ኡድሂያን ለማረድ ያቀደ ሰው የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን መቁረጥ የለበትም።
የኡድሑይያህ የእርድ ቀናት ከዒዱ ቀን ሶላት መጠናቀቅ ጀምሮ (የውሙ–ነሕር 10ኛው ቀን ማለት ነው) እስከ አያሙ–ተሽሪቅ የመጨረሻው ቀን (11፣ 12 እና 13ኛው ቀን ፀሀይ መግባት ድረስ) የሚቆይ ይሆናል
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
7️⃣ በዒባዳህ መጠናከር፡-
ነፍል (ትርፍ ግዴታ ያልሆኑ) ዒባዳዎችን ማብዛት ለምሳሌ ሱና ሶላቶችን ማብዛት፤ ቁርኣንን ማንበብና ማዳመጥ
8️⃣ ከሐራም መቆጠብ፡-
ከላይ የተጠቀሱት መልካም ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የአላህን ተውፊቅ ያላገኘ ሰው ቢያንስ ከወንጀል ይታቀብ። እሱም ትልቅ ተውፊቅ ነውና
በነዚህ ውድ ቀናቶች ከተጠቀሱት ውጪ ያሉትንም መልካም ስራዎች በሙሉ መስራት ምንዳው ላቅ ያለ ነው። ከመልካም ፈገግታ ጀምሮ በኸይር ስራ ሚዛን ላይ ሊያመዝንልንና ሊጠቅመን የሚችልን ነገር ከመተግበር ወደ ኋላ አንበል።
http://t.me/khalidzemen
ዛሬ ከሚሰጠዉ መግለጫ የበለጠ ሊያፅናናን፣ ሊያበረታታን የሚችል አስደማሚ መልእክት!
ሙእሚኖች ከሆናችሁ የበላዮች ናቸሁ
በሚል ርዕስ በነሲሓ ቲቪ ትላንት ምሽት የቀረበውን እጅግ መሳጭ ወቅታዊ ምክር!
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
🕌 በዕለተ ቅዳሜ ,በቀን 26/09/2015 EC ከመግሪብ በኃላ በላፍቶ ቢላል መስጂድ የተደረገ ልዩ ሙሀደራ።
ሼር በማድረግ እናዳርሰው
/channel/islamictrueth/4674
እነዚህ ሸሂድ ናቸዉ!
عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ : " مَنْ قُتِلَ دُونَ مَالِهِ فَهُوَ شَهِيدٌ، وَمَنْ قُتِلَ دُونَ أَهْلِهِ أَوْ دُونَ دَمِهِ أَوْ دُونَ دِينِهِ فَهُوَ شَهِيدٌ " .
የአላህ መልእክተኛ ረሱል(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
አንድ ሰዉ ንብረቱን፣ ቤተሰቡን፣ ደሙንና ሀይማኖት በመከላከል እያለ ከሞተ ሸሂድ(ሰማእት) ነዉ። [አቡ ዳዉድ 4772 ዘግበዉታል አልባኒም ሶሂህ ብለዉታል]
/channel/islamictrueth
ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፣ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
Читать полностью…ቁርአናችን እስትንፋሳችን ነው። መስጂዳችን አይናችን ነው። እስትንፋሳችንን ለመቁረጥ ሞክራችኋል። መስጂዳችን አላህን ለመገዛት የምንሰባሰብበት የአምልኮ ስፍራችን ነው። የአምልኮ ስፍራችንን ደፍራችኋል።
#በመስጂዶች_ፍርስራሽ_የምትገነባዋ_ከተማ_ሸገር
#ሕገወጥ_አስተዳደር_እንጂ_ሕገወጥ_መስጂድ_የለም!
#ዓሳ_ያለ_ውሃ_ሙስሊም_ያለ_መስጂድ_መኖር_አይችሉም!
#መስጂዴን_አታፍርስ_ያፈረስከውንም_መልስ!
#Magaala-Diigama-Masjiidota-Irratti-Ijaaramtu-Shaggar
#Bulchiinsa-Seeran-Alaa-Malee-Masjidni-SeeranAlaa-HinJiru
#QurxummiinBishaanMalee-MuslimniMasjiidaMaleeJiraachuuHinDanda'an
#MasjiidakooHinDiiginKanDiigdesDeebisi
የአላህን እርዳታ ፈልጉ!
አቡ ሁረይራ(ረዲየላሁ አንሁ) እንዳወሱት ነቢዩ ሙሐመድ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
«ዲን ገር ነው፤ አንድ ሰው በሃይማኖቱ(ክንውን) ላይ ከአቅሙ በላይ ከተሸከመ በዚሁ ሁኔታ አይቀጥልም። ስለዚህ ጽንፈኛ አትሁኑ። ግን ወደ ፍጹምነት ለመቃረብ ስራችሁን በጥራት ለማከናወን ጥረት አድርጉ። ሸልማት የምታገኙ በመሆኑም ደስታ ይሰማችሁ። በጧትም ሆነ በማታ እንዲሁም በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ፀሉት በማድረግ ታገዙ። (የአላህን እርዳታ ፈልጉ)» [ሶሂህ ቡኻሪ]
/channel/islamictrueth
የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«መስጅድ የሁሉም ሙስሊም ቤት ነዉ።» [ሶሂህ ጃሚእ 6702]
/channel/islamictrueth
በንዴት ይሙቱ እንጂ የኢስላምን ስርጭትና የሙስሊሞችን ጥንካሬ መስጂዶችን በማፍረስ መግታት አይቻልም!
ዛሬ አንድ መስጂድ ቢፈርስ ወይም ቢቃጠል በምትኩ ሌላ ይሰራል! የአማኞች ልብ ላይም ብዙ መስጂዶች ይገነባሉ!
يُرِيدُونَ أَن يُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَيَأْبَى اللَّهُ إِلَّا أَن يُتِمَّ نُورَهُ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ [9:32]
ዑስታዝ አህመድ ሼይኸ አደም
/channel/islamictrueth
👆ዛሬ ላይ ህገወጥ ግንባታ ተብሎ የሚፈረሱ መስጅዶች በሌሎች እምነት ቦታዎች ላይ ቢሆን ኖሮ ...
Читать полностью…ስለ እናትህ ስለ እናቲሽ አንተና አንቺ እንዴት ነን? ከዚህ ታሪክ የኛን ቦታ እንመርምር!
እኔ አላምንም! እኔ አላምንም! እነሱ አንቺ ላይ ይሄንን ይፈፅማሉ ብዬ እናቴ!
ታላቁ ሼህ ካሊድ ራሺድ(አላህ ከእስር ነጃ ይበለውና) ይህንን ዘግናኝ ታሪክ እያለቀሰ ይተርክልናን!
/channel/islamictrueth
አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أحبُّ الأعمالِ إلى اللهِ ﷻ سُرُورٌ يدْخِلُهُ على مسلمٍ، أوْ يكْشِفُ عنهُ كُرْبَةً، أوْ يقْضِي عنهُ دَيْنًا، أوْ تَطْرُدُ عنهُ جُوعًا﴾
“አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ማለት በሙስሊም ወንድምህ ልብ ውስጥ ደስታን ማስገባት፣ ወይንም ከርሱ ያለበትን ጭንቅ ማስወገድ፣ ወይንም ብድሩን መክፈል፣ ወይንም ረሀቡን ማባረር (ማስወገድ) ናቸው።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 906
ጆይን፦ /channel/BuhariMuslimAmharic
ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«ሶስት ነገሮች በመሀላ አስረግጨ
አወጋቹኋለሁና በልቦናቹሁ ያዟቸው።
★ የአንድ ሠው ገንዘብ በሰደቃ ምክንያት አይጎድልም።
★ በደል የደረሰበት ሰው ከታገሰ አላህ ክብርን ይጨምርለታል።
★ ሰውየው የልመና በር ከከፈተ አላህ የድህነትን በር ይከፈትበታል። [አህመድና ቲርሚዚ ዘግበዉታል]
/channel/islamictrueth
«አንድ ሙስሊም ከመናገሩ በፊት ቃላቱን መመዘን ይኖርበታል፣ ንግግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አወንታዊ እና አሉታዊ ውጤታቸውን ማጤን አለበት፣ ቃላቱን በትክክለኛ ሚዛን መዝኖ ሲያበቃ፣ ቃላቱ ለመልካም ሰበብ ከሆነ ይናገር፣ አሊያ ግን ሸርን የሚያስከትል እና ለሸር ሰበብ ከሆነ ክፋቱን ከሰዎች ሊከላከል ይገባል።» ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን
📚 ["ሸርሑ ኪታቢ አልፊተን ወል ሓዋዲስ" (ገጽ 239)]
/channel/islamictrueth
ማወቅና መረዳት ያለብን የእስልምና እውቀት!
እስልምና ሚዛናዊ ሃይማኖት ነው!
እስልምና ከመጠን በላይ አለማክረርና አለማካበድን እንዲሁም ከደረጃ በታች አለመውረድና አለመለስለስን መለያው አድርጎ የተደነገገ ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ መለያው በሁሉም ሃይማኖታዊና አምልኮአዊ መርሆቹ ውስጥ ጎልቶ ይንፀባረቃል፡፡
አላህ(ሱ.ወ.) ለመልእክተኛው(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሰሀቦችም ሆነ ለምእመናን ሚዛናዊ ይሆኑ ዘንድ በማስገንዘብ አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡ ይህም በሁለት መንገዶች ሊገለፅ ይችላል፡-
1) በሃይማኖት ጎዳና ላይ በመፅናትና በልብ ውስጥ ለአላህ ሕግጋቶች ከፍተኛ ቦታ በመስጠት።
2) ከድንበር አላፊነትና ከጠርዘኝነት በመከልከል ናቸው፡፡
ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል:-
«እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ከአንተ ጋር ያመኑትም(ቀጥ ይበሉ)፤ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡» (ሁድ 112)
ጌታችን በዚህ አንቀፅ ለማለት የፈለገው በእውነት ላይ በመፅናት ብዙም ሳታካብዱና አላስፈላጊ ነገሮችን በመጨማመር ድንበር አላፊ ሳትሆን ለዚሁ እየታገልክ ኑር ነው፡፡
የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በአንድ ወቅት የእምነት ባልደረባቸውን(ሰሀባቸውን) ስለ ሐጅ ተግባራት ሲያስተምሩት፤ ያለፉት ህዝቦች ለጥፋት ሊዳረጉ የቻሉት ድንበር በማለፍ መሆኑን በማውሳት፤ ሰሀቢው ከማካበድ ተግባር እንዲቆጠብ አስገንዝበውታል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት:-
«አደራችሁን! በሃይማኖት ውስጥ ማካበድን ተጠንቀቁ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ለጥፋት የዳረጋቸው ማካበድ ነው፡፡» (ኢብን ማጃህ 3029)
ለዚህ ነው የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «አደራችሁን አቅማችሁ በሚፈቅደው ተግባር ላይ ብቻ ተሰማሩ» ያሉት (አል ቡኻሪ 1100)
የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተልዕኮዋቸውን ትክክለኛ ገፅታ ቁልጭ ባለ ቃል ገልፀዋል፡፡ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተላኩት ለሰዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር ለማሸከም ሳይሆን፤ ገራገርና በጥበብ የተሞላ ዕውቀት ለማስጨበጥ ነው፡፡ መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል:-
አላህ «አጨናናቂ ወይም አጣባቢ አድርጎ አላከኝም ነገር ግን አግራሪና አስተማሪ አድርጎ ልኮኛል፡፡» (ሙስሊም 1478)
የፔጃችን መልእክት "አታከብዱ ተብሎ የተጠቀሰው መልእክት አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት አደለም። ስህተት ላይ መሆናቸውን አይተህ ተው ይሄ አይባልም ይሄ ማለት ዲኑ አይፈቅድም ብለህ ስትላቸው አታካብድ ይላሉ፤ ይሄ ስህተት ነው! መረጃ እስከመጣልን ድረስ መተግበር ግዴታ ነው። ማካበድ የተባለው ዲኑ ያላጠበቀውን ነገር መረጃ ጠንካራ በሌለበት ጉዳይ ላይ እንደ ግዴታ አድርጎ ማውራቱ ነው ማካበድ የተባለው።"
ከ Www.newmuslim-guide.com የተወሰደ
tiktok.com/@sadamsuleyman
/channel/islamictrueth
ምን አይነት መታደል ነዉ የቲምን ማስደሰትና ደስታቸዉን በአይን ማየት! ያረቢ ወፍቀን!
Читать полностью…