ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
አነቃቂ የሚባሉ ሰዎች ዛሬ ትዳርን መጥፎ አድርጓ እየሰበኩ ነገ ደግሞ በግልፅ ከትዳር በተቀራኒ የሆነዉ እንትንን ያስተዋዉቁሀል ለማንኛዉም ቀድማቹ ንቁ!!!
ያለ ምንም ሸሪዓዊ ምክንያት እራስን ከትዳር ዓለም ማግለል ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱንና ማፈንገጥ እንደኾነ ተገልጾአል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡" (ሱረቱ-ሩም 30፡22)፡፡
/channel/islamictrueth
የሰዶማውያን(ተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት) በቀላሉ ቀጥሎ ያሉትን ግላዊና ማኃበራዊ ችግሮች ያስከትላል፡-
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
አንደኛ
ከተፈጥሮአዊ ማንነት መጣረስን፡- ይህን ተግባር ንጹህ ህሊና ያወግዘዋል፡፡ ስሜታችንም አይቀበለውም፡፡ በዚህ ስራ ላይ መገኘት ከተፈጥሮ ስርአት መውጣት ነው፡፡
/channel/islamictrueth
በግብረ ሰዶማዊነት አፀያፊ ተግባር የተገኙ ኢስላም ግደሉ ይላል!
عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " مَنْ وَجَدْتُمُوهُ يَعْمَلُ عَمَلَ قَوْمِ لُوطٍ فَاقْتُلُوا الْفَاعِلَ وَالْمَفْعُولَ بِهِ "
ከኢብኑ ዐባሥ እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) አሉ፦ «ማንም የሉጥ ሕዝብ የሚያደርጉት ድርጊት ሲያደርጉ ብታገኙ ሁለቱንም ግደሏቸው»። [ኢብኑ ማጃህ 2658]
ለተባለሻ የምድር ስርአት ብቸኛ መፍትሄ ያለዉ ኢስላም ጋር ነዉ!
/channel/islamictrueth
ስለ ግብረ-ሰዶም የኢስላም አቋም!
ክፍል አንድ
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የተወገዘ ኃጢአት መሆኑ፡-
1) ጌታ አላህ በባሪያዎቹ ላይ ከዋላቸው ከማይቆጠሩ ጸጋዎቹ የተወሰኑትን እያነሳ ሲያስታውሰን፡ አንደኛውን የገለጸው ‹‹ለኛ የትዳር አጋር የምትሆነን ሴትን›› ከኛው መፍጠሩን በመጠቆም ነው፡፡ ይህም ከአስደናቂ ምልክቶቹ መሆኑን አያይዞ ይነግረናል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ " سورة الروم 21
"ለናንተም፣ ከነፍሶቻችሁ (ከጐሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ።" (ሱረቱ-ሩም 30፡21)፡፡
"وَاللّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ أَفَبِالْبَاطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَتِ اللّهِ هُمْ يَكْفُرُونَ " سورة النحل 72
"አላህ ከነፍሶቻሁ (ከጐሶቻችሁ) ለናንተ ሚስቶችን አደረገ፤ ለናንተም ከሚስቶቻሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፤ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ፤ ታዲያ በውሸት (በጣዖት) ያምናሉን? በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን?" (ሱረቱ-ነሕል 16፡72)፡፡
"فَاطِرُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَمِنَ الْأَنْعَامِ أَزْوَاجًا يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ " سورة الشورى 11
"ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፤ ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሴቶችን፣ ከቤት እንሰሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፤ በርሱ (በማድረጉ) ያበዛችኋል፤ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 42፡11)፡፡
ከነዚህ ሶስት አንቀጾች በግልጽ የምንረዳው ነገር፡- ጌታ አላህ ለኛ ተጣማሪን (የትዳር አጋር) ያደረገልን ከሴቶች ጋር እንጂ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር አለመሆኑን ነው፡፡ ይህ የተቃራኒ ፆታ በጋብቻ መጣመር ከአላህ የሆነ ኒዕማ (ጸጋ) ከሆነ ከዛ በተቃራኒው ሆኖ መገኘት (ወንድ ከወንድ ወይም ሴት ከሴት ጋር) ደግሞ እርግማንና ቁጣ እንጂ ሌላ አይሆንም፡፡ በዚህም ሰበብ ተግባሩ ኃጢአት መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ይቀጥላል...
/channel/islamictrueth
"ዱዓእ" ማለት፡- የምትፈልገውን ነገር ሊሰጥህ፣ የምትመኘውን ነገር ሊያሳካልህ፣ ከምትጠላውና ከምትፈራው ነገር ሊጠብቅህ እንደሚችል አምነህ ለዚህ አካል የምታቀርበው ተማጽኖና ልመና ማለት ነው፡፡
አንድ ሙስሊም ዱዓእ አደረገ ማለት፡- የሚፈልገውን ነገር ከአላህ ለማግኘት፣ ከሚፈራው ነገር በአላህ ለመጥጠበቅ ጌታውን አላህን አጥብቆ ለመነ፣ ተማጸነ ማለት ነው፡፡ "ዱዓእ" ልብ ከምላስ ጋር በመጣመር ከሚፈጸሙ የዒባዳ ዘርፎች ውስጥ የሚመደብና ተቀዳሚ ተግባርም ነው፡፡
ዱዓእ በዱዓነቱ ብቻ ለባለቤቱ አጅር ያስገኛል፡፡ ሶላት የሰገደ በሶላቱ፣ ዘካት ያወጣ በዘካው፣ ሶደቃህ ያወጣ በሶደቃው አጅር እንደሚያገኘው፤ እጁን ወደ ላይ አንስቶ ያ አላህ! ያ ረቢ! የሚል ጌታውን የሚማጸን ባርያም የዱዓውን ምላሽ ወዲያው ቢያገኝ፤ ወይም ምላሹ ቢዘገይም በዱዓው ብቻ አጅርን ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ዱዓእ ዒባዳህ (አምልኮ) ነውና!፡፡
ከአቡ ሀይደር ትምህርት የተወሰደ!
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
ጥቂት ምክር ከኒካህ በፊት በሃራም ግንኙነት ውስጥ ለወደቅሽው እህቴ...
ቁጥር አንድ
አላህ ሲፈጥርሽ ውድ አድረጎ የፈጠረሽ ውዷ እህቴ ሆይ የሰው ልጅ ነሽና ማግባት፣ መውለድ፣ ወግ ማዕረግ ማየትን እንደምትመኚ አውቃለው፡፡ ይህን ውድ ምኞትም ኢስላም በምን መልኩ ማሳካት እንዳለብሽም መስመር ዘርግቶልሻል፡፡ ይህን ኢስላማዊ የትዳር ህይወት ለመቅመስ ባለሽ ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ በጠላፊዎች እና በተኩላዎች ወጥመድ ስር ልትወድቂ አይገባም፡፡ ከጌታሽ የተሰጠሸን ክብር በራስሽ እጅ ልታዋርጂ አይገባሽም፡፡
Abdulaziz Aliiy
#ዝሙትን_እንጠየፍ
/channel/islamictrueth
ዐሹራእ ደረሰ
በአቡ ሀይደር
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
#ዐሹራእ ምንድነው?
ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡
#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡
#ለምን ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡
#ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡
#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡
#መቼ እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ጁምዓ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ጁምዓ ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ሀሙስና ጁምዓ ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡
ሐ. ከ ሀሙስ-ቅዳሜ ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡
መ. ጁምዓና ቅዳሜ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
አላህ ይወፍቀን፡፡
#ስምንቱ የፆም ቀናት
አላህ ፆምን ያገራለትና የወፈቀው ሰው ደግሞ ከፈለገ በተከታታይ ለስምንት ቀናት መፆም ይችላል፡፡ እንዴት ካሉም፡-
ከሀሙስ-ቅዳሜ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐመረም 9ኛ 10ኛና 11ኛ ቀናት ስለሆኑ፡ ከዐሹራእ ፆም ጋር በተያያዘ መልኩ ይፆማሉ ማለት ነው፡፡
ሰኞ፡- ይህ 13ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡
ሰኞ -እሮብ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐረም 13ኛ 14ኛና 15ኛ ቀናት ናቸው፡፡ አያሙል-ቢድ በመባልም ይጠራሉ፡፡ የወሩን ሶስት ቀናት በነዚህ ቀናት መፆም በላጭ ነው፡፡
ሀሙስ፡- ይህ 16ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡
Click and Like ➤➤
http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
/channel/islamictrueth
አንቀጽ ላይ የአህሉል ኪታብ (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶችን ከሙሽሪኮቹ በመነጠል እነሱ ለሙስሊም ወንድ የተፈቀዱ መኾኑን ኻስ አድርጎ (ነጥሎ አውጥቶ) በመስፈርት ነግሮናል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"…ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡" (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡5)፡፡
በዚህ አንቀጽ መሠረት መጽሐፍ ከተሰጣቸው ሴቶች (አሕሉል ኪታብ) መካከል ዝሙተኛ ያልኾነችውን ማግባት እንደሚቻል የአላህ ቃል ይገልጻል፡፡ ‹‹ጥብቆቹም›› የሚለው ከዚና የተጠበቁ መኾናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
የሐንበሊያው መዝሀብ ሊቅ የኾኑት ኢብኑ-ቁዳማህ (541-620 ሂጅ) ረሒመሁላህ ሲናገሩ፡- ‹‹በባርነት ቀንበር ውስጥ ያልኾኑ በነጻነት የሚኖሩ የአህሉል ኪታብ ሴቶች ለትዳር ሐላል በመኾናቸው ጉዳይ ላይ በዑለሞች መሐል ምንም ልዩነት የለም›› ይላሉ፡፡ (አል-ሙግኒ 7/500)፡፡
5ኛ/ እነዚሁ የኢስላም ሊቃውንት የመጽሐፉ ባለቤት የኾኑ ሴቶችን ማግባት የተፈቀደ መኾኑን ሲገልጹ እግረ መንገዱንም መሟላት ያለበትንም መስፈርት አብረው አስቀምጠዋል፡፡ እነዚህም መስፈርቶች፡-
ሀ/ ከዝሙት ጥብቅ የኾነች
ለ/ ኢስላምን በሚዋጉ ከሀዲያን በሚገዙት ሀገር ነዋሪ ያልኾነች ከኾነ የሚለው ነው፡፡
ከዚሁም ጋር አያይዘው በዘመናችን እራሷን ከዝሙት የጠበቀች አህሉል ኪታብ ማግኘት አስቸጋሪ መኾኑን በመጥቀስ ደግሞም በትዳር ዓለም ፍቺ ቢከሰት በምድራዊ ህግና ስርአት መሠረት ልጆቹ ለሷ ተወስኖላት እሷም የሱን ልጆች ወደ ኩፍር ልትወስዳቸው ስለምትችል፣ ደግሞም ከአጅነቢ ወንዶች መቀላቀልና መሰል ሐራም ነገራትን ሃይማኖቷ ስለማይከለክላት በዚህ ሰበብ ከባለቤቷ አለመስማማቷን፣ ሃይማኖታዊ በዐል በሚደርስበት ጊዜ በቤቷ ከኢስላም ጋር የሚጻረሩ ሃይማኖታዊ ስርአቶችን ለመፈጸም ደፋ ቀና ስለምትል ሙስሊም ደግሞ በቤቱ ከአላህ ውጭ ማንም ሊመለክ መፍቀድ ስለሌለበት ይህ ሁሉ ችግር ባለበት ሁኔታ ላይ እነሱን ለትዳር አስቦ መሄዱ አግባብ እንዳልኾነ ይገልጻሉ፡፡ ሙስሊሙ ወደነሱ ከሄደ የኛዎቹንስ ማን ያግባቸው? የሚለው በራሱ ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ ስለዚህም ዲን ያላትን ይምረጥ የሚለው የሁሉም ስምምነት ነው፡፡
ሐሰን ኢብኑ ዐሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ይላል፡- "ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ‹‹የሚያጠራጥርህን ነገር ትተህ ወደማያጠራጥርህ ነገር ሂድ፡፡ እውነት መረጋጋት ሲኾን ሀሰት መጠራጠር ነውና›› የሚለውን ምክር ያዝኩኝ" [ቲርሚዚይ 2442፣ አሕመድ 1630፣ ኢብኑ ሒባን 722]፡፡
ኢማሙል-መናዊ ረሒመሁላህ ይህን ሐዲሥ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹መልካም ይሁን መጥፎ፣ ሐራም ይሁን ሐላል ለይተህ የማታውቀውን ነገር በመተው በመልካምነቱና በሐላልነቱ የማትጠራጠርበት ወደኾነው ነገር አዘንብል፡፡ ምክንያቱም እውነት የኾነን ነገር ልብ ይረጋጋበታል፡፡ ሐሰት ላይ ግን ልብ በጥርጣሬ ይዋልላል፡፡ ስለዚህም ነፍሲያህ በኾነ ጉዳይ ላይ ከተጠራጠረች ተወው የሙእሚን ነፍስ በእውነት ነገር ላይ ትረጋጋለች በሀሰት ላይ ደግሞ ትጠራጠራለችና፡፡›› [ፈይዱል ቀዲር 3/529]፡፡
6ኛ/ ሙስሊሟ እሕት ግን ከአህሉል ኪታብም ሆነ ከሙሽሪኮች (ጣኦታውያን) ወንዶችን ማግባት ያልተፈቀደላትን ሚስጥር ሲያብራሩ የኢስላም ሊቃውንቶች እንዲህ ይላሉ፡-
ሙስሊሞች በአላህና በመልክተኞቹ እንዲሁም በመጻሕፍቱ ሲያምኑ በተለይም በሙሳና በዒሳ ነቢይነት በተውራትና በኢንጂል የአላህ ቃልነት ባመኑ ጊዜ ጌታ አላህ ደግሞ የተውራትና ኢንጂል ተከታይ ነን የሚሉ የአህሉል-ኪታብ ከዝሙት ጥብቅ ሴቶችን ለትዳር ፈቀደላቸው፡፡ አሕሉል ኪታብ የኾኑ ወንዶች ግን በነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነት እና በቁርኣን አምላካዊ ቃልነት በካዱ ጊዜ እስኪያምኑ ድረስ የሙስሊም ሴቶችን በትዳር መጣመር እርም አደረገባቸው፡፡ ያመኑ ጌዜ ግን ሴቶቻቸው ለኛ ሐላል እንደኾኑት ሴቶቻችንም ለነሱ ሐላል ይኾናሉ ማለት ነው፡፡ ደግሞም በተጨማሪ ሌላው ምክንያት፡- በአብዝሐኛው ሴት በድክመቷ ሰበብ በባሏ ሥር ሆና ስትምመራ እንጂ ባሏን ስትመራ አይታይም፡፡ ስለዚህም ሙስሊሟ ሴት ለአህሉል ኪታብ ወንድ የተፈቀደች ብትኾን ኖሮ በዲኗ ተፈትና በባሏ የክህደት ዲን ውስጥ በወደቀች ነበር፡፡ (ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ፡ http://www.binbaz.org.sa/fatawa/1587 )፡፡
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሴት ልጅ ለአራት ነገራት ለትዳር ትፈለጋለች፡፡ ለንብረቷ፣ ለዘሯ፣ ለውበቷና ለዲኗ፡፡ አንተ ግን ዲን ያላትን ምረጥ፡፡ እንቢ ካልክም እጅህ አፈር አፋሽ ይሁን" [ቡኻሪይ 4802፣ ሙስሊም 1466]፡፡
አላህ ሙስሊም ወንዶችን በሙስሊሟ ሴት የሚብቃቁ፣ ሙስሊም ሴቶችንም በሙስሊሙ ወንድ የሚብቃቁ ያድርጋቸው፡፡
ወላሁ አዕለም (አላህ የበለጠውን እውነታ ዐዋቂ ነው)
ለተጨማሪ የኡስታዙን ትምህርት ለማግኘት
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን!
Click and like
በቴሌግራም
/channel/islamictrueth
በ BIP APP
https://channels.bip.ai/join/islamawieweneta
በወርድ ፕረስ
https://wincdaawa.wordpress.com
🍃አዲስ ወርና ዓመት
በ516 ዓ.ሂ የሞቱት ኢማም አልበጘዊ
መዕሪፈቱስሰሓበህ በተሰኘው መጽሃፋቸውና ሌሎችም ዐብዱላህ ኢብኑ ሂሻም ከተሰኘው ታቢዒ በትክከኛ ሰነድ የሚከተለውን ዱዓ ዘግበዋል
⛤" የነቢዩ ባልደረቦች ይህን ዱዓ ልክ እንደ ቁርኣን ይማሩት ነበር አዲስ ዓመት ወይም አዲስ ወር ሲገባ ( አላህ ሆይ: የደህንነት፣ የኢማንና የሰላም፣ ከሸይጣንም የምንጠበቅበት፣ የአላህንም ውዴታ የምናገኝበት ወር/ ዓመት አድርገው ) ይሉ ነበር
☞በዚህም መሰረት አዲስ ወርና ዓመት ሲገባ ይህንን ዱዓ ብናደርግ ተጠቃሚዎች እንሆናለን
( اللهم أدخله علينا بالأمن والإيمان والسلامة والإسلام وجوارٍ من الشيطان ورضوانٍ من الرحمن )
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ሙሐረም1/1/1445 ዓ. ሂ
/channel/ahmedadem
ከእርዳችን እሱ የሚያገኘው ጥቅም የለም!
لَن یَنَالَ ٱللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَاۤؤُهَا وَلَـٰكِن یَنَالُهُ ٱلتَّقۡوَىٰ مِنكُمۡۚ كَذَ ٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمۡ لِتُكَبِّرُوا۟ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمۡۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُحۡسِنِینَ
“አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡”
ኢደል አድሃ የአላህን ትዕዛዝ የምንፈፅምበት ከቤተሰቦቻችን ከዘመዶቻችን እንዲሁም ከምስኪኖች ጋር አብረን የምንደሰትበት በነብዩ ኢብራሂም የተጀመረ ድንቅ የመታዘዝ ተምሳሌታዊ ኢባዳን የምናከናውንበት በዓል ነው።
በድጋሚ እንኳን ለ1444ኛው አመተ ሂጅራ የኢድ አልአድሀ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ። የሰላምና የህብረት፣ የመተዛዘን የፍቅር በዓል ይሁንልን!
ሐጅን በአስር ደቂቃ በነሲሃ ቲቪ የተዘጋጀ
https://youtu.be/JeWN-oNkc_U
🌐 /channel/tahaahmed9
☝️ በራሪ ወረቀቱን በታተመበት መልኩ በሙሉ ማተም ለሚፈልጉ ከዚህ በላይ ያገኙታል።
👇 በተሻለ ጥራት በፒዲኤፍ ከታች ያገኙታል።
"ወደ መልካም አመላካች እንደሰሪው ነው።"
በማሰራጨት የምንዳው ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።
🌐 /channel/tahaahmed9
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት
(ክፍል–3)
የሶስተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስረኛው የዒድ ቀን ነው።
1⃣ ሚና ሲደርስ ወደ ጀምረተል—ዓቀባ በመሄድ "አላሁ አክበር " እያለ በማከታትል ሰባት ጠጠሮችን ይወረውራል።
2⃣ ሀድይ ወይም የመቃረቢያ መስዋእት ካለው ያርዳል።
3⃣ ፀጉሩን ይላጫል ወይም ያሳጥራል።
እነዚህን ተግባራት በመፈፀሙ የመጀመሪያ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል—አወል) ይከሰትለታል። በመሆኑም ከግብረ—ስጋ ግንኙነት ውጭ በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩ ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
4⃣ ወደ መካ መሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህ ማድረግ፦
ወደ መካ ይሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህን (የሐጅ ጠዎፍን) ያደርጋል። ሙተመቲዕ (በሐጅ ወራት ዑምራን ፈፅሞ በዚያው ጉዞ ሐጅን የሚያደርግ) የሆነና እንዲሁም ሙተመቲዕ ባይሆንም በመጀመሪያ የመግቢያ ጠዎፉን ሲያደርግ አሰከትሎ በሰፋና መርዎ መካከል ሰዕይ ያላደረገ ከነበረ የሐጅን ሰዕይ ያደርጋል።
በዚህ ተግባሩም ሁለተኛ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል አስ–ሳኒ) ይከሰታል። በመሆኑም የግብረ—ስጋ ግንኙነትን ጨምሮ ሌሎቹም በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩበት ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
5⃣ ወደ ሚና በመመለስ አስራ አንደኛውን ሌሊት በዚያ ያድራል።
ይቀጥላል…
ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ… አላህ ያግራልን!
✍️*ጣሀ አህመድ
🌐 /channel/tahaahmed9
አረፋህ ሊመን አረፈህ!
ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። የኢድ ሸመታም ሆነ የመዝናኛ እንዲሁ!
ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።
ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!
ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ
ጠዋት
ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!
ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአን፣ተህሊል፣ተህሚድ በአጠቃላይ በዚክር ማሳለፍ(አዝካረ ሰባህ ሳይረሳ)
ፀሀይ ስትወጣ የፀሃይ መውጣትን ሰላት እዛው ከመስገጃችን ሳንነሳ በመከወን ከረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሀጅ የማድረግን ምንዳ እንዲጎናጸፍ
ለቀን ኢባዳ ያግዘናል ብለን ካሰብን መጠነኛ እኝቅልፍ እንተኛ። ስንነሳ በትንሹ 4 ረክኣ ሰላተ ዱሃ እንስገድ!
ከሰአት
ከዝሁር ሰላት በኋላ ቁርዐናችንን እንቀራለን። የአረፋ ኹጥባ(ከመስጂደ ነሚራህ የሚተላለፈውን) መልእክት በጥብቅ መከታተል
ልባችንን ሊያረጥብ የሚችል መፅሐፍ ወይም ቪድዮ እየተመለከትን እራሳችንን እናርጥብ!
ከአስር በጥሎ እንዲሁ በቁርአን እና በዚክር መግሪብ 1 ሰአት አቅራቢያ እስኪቀረው ማሰለፍ!
የእለቱ ወሳኝ ሰአት ይህ ነው።
የተሰበረ የሚጠገንበት፤ የታመመ የሚፈወስበት፤ ተስፋ የቆረጠ ተስፋው ነፍስ ሚዘራበት ድንቅ ሰአት!
ዱኣ!!! ዱኣ ብቻ!
በዚህ ቀን ከእሳት ነፃ አለመባል ኪሳራ ነው። ምኞት ኖሮን ምኞታችንን ሳናሳካ መቅረት ቂልነት ነው!
ነገ አላህ አልመረጥንም እና እየተመለከታቸው ከሚኮፈስባቸው ጌታቸውን ለማላቅ በነጭ ተውበው ከአረህማን ድግስ ከሚታደሙት አልሆንም!
"አረፋ ተራራ ላይ መቆም ያልቻለ
አላህ ያሳወቀው ድንበር ላይ ይቁም
ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ያልቻለ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ይደር...ያቀርበዋልና!
ሚና ላይ እርዱን መከወን ያልቻለ
ምኞቱን ይረድ! ከፍ ይላልና።
ወደ ቤቱ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለ ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ይከጅል!" ኢብኑ ረጀብ
እርቅ ይበጀናል!
Huzeyfa Sultan
የሰዶማውያን(ተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት) በቀላሉ ቀጥሎ ያሉትን ግላዊና ማኃበራዊ ችግሮች ያስከትላል፡-
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
ሶስተኛ
ያልተፈቀደ ግንኙነት ከወንዶች ጋር ያንን አስቀያሚ ተግባር የለመደ ሰው ወደ ሴቶችም ሲመጣ ስሜቱን ማርካት የሚፈልገው ዘር ከሚገኝበት ቦታ ሳይሆን ከተወገዘው ሌላኛው ስፍራ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ብሉሹነት ነው፡፡
/channel/islamictrueth
የሰዶማውያን(ተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት) በቀላሉ ቀጥሎ ያሉትን ግላዊና ማኃበራዊ ችግሮች ያስከትላል፡-
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
ሁለተኛ
ወጣቱን አካል ማኮላሸትን፡- ወጣቶች ከወዲሁ እራሳቸውን ተጣማጃቸውን በመፈለግ በትዳር ካልታቀፉ፡ ለዚህ ተግባር በቀላሉ ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ ስሜታቸውም ያለ አግባብ ይባክናል፡፡
/channel/islamictrueth
በግብረ ሰዶማዉያን ላይ አላህ ያደረሰባቸዉ ቅጣት!
إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ
«እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው»፡፡ [54:34]
فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
«ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው»፡፡ [15:74]
وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
«በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት»፡፡ [7:84]
وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ
«በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናምን አዘነምንባቸው፤ የተስፈራሪዎቹም ዝናም ምንኛ ከፋ»፡፡ [26:173]
/channel/islamictrueth
ስለ ግብረ-ሰዶም የኢስላም አቋም!
ክፍል ሁለት
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የሉጥ ህዝቦች የጠፉበት ምክንያት ቁርአን እንዲህ አድርጓ ይተርክልናል!
የሉጥ (ዐለይሂ-ሰላም) ህዝቦች ነቢያቸውን በማስተባበልና ባለመቀበላቸው ከሀዲ ሆነዋል፡፡ ከክህደት የሚበልጥ ኃጢአት የለም፡፡ ከዚህ ክህደታቸው ጋር ደግሞ በተጨማሪ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በመፈጸማቸው አላህ አጥፍቷቸዋል፡፡ ይህም የሰዶምች ስራ (ግብረ-ሰዶም) የኃጢአት ተግባር ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ ነው፡፡ ቀጣዮቹ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾች ይህን ይገልጻሉ፡-
"ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አስቀያሚን ሥራ ትሰራላችሁን? በርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም። እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ፤ በውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ። የሕዝቦቹም መልስ (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው፣ እነሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም። እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው፣ ሚስቱ ብቻ ስትቀር፣ እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት ሆነች። በነርሱም ላይ (የእሳት) ዝናምን አዘነምንባቸው፤ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት።" (ሱረቱል አዕራፍ 7፡80-84)፡፡
"እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድን ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን? (አላቸው)፤ የሕዝቦቹም መልስ ከውነተኞቹ እንደ ኾንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።" (ሱረቱል ዐንከቡት 29፡28-29)፡፡
እስካልተናገረ ድረስ፡ በከባኢረ-ዙኑብ (በታላላቅ ኃጢአት) ኃጢአት ላይ መዘፈቁ፡ ከኢስላም አጥር አያስወጣውም፡፡
ኃጢአቱ በውስጡ ያለውን ኢማን ያዳክመዋል እንጂ፡ ኩፍር ውስጥ አይከተውም፡፡ በዚህ ተግባር ላይ ሁኖ ያለ ተውበት ቢሞትም እንኳ፡ ጉዳዩ ወደ አላህ የሚመለስ (አላህ ከፈለገ ሊምረው፣ ካልሆነም የኃጢአቱን ያህል ሊቀጣው) እንጂ እኛ የምንፈርድበት አይደለም፡፡
ግብረ-ሰዶም ከታላላቅ ኃጢአት ተርታ የሚመደብ እንጂ በራሱ ኩፍር የሆነ ተግባር አይደለም፡፡ ይህ አስቀያሚ ስራ ከአንድ ሙስሊም ላይ ቢገኝ እና ያ ሙስሊም ያለ ተውበት ቢሞት፡ የሰውየው ጉዳይ ወደ አላህ ይመለሳል እንጂ፡ ማንም ሰው እሱ የጀሀነም ነው ማለት አይችልም፡፡
ሰውየውን ሊያከፍረው የሚችለው ይህ አስቀያሚ ተግባር ሐላል ነው ብሎ ካመነ ወይም ከተናገረ ብቻ ነው፡፡ የዛኔ ስራው ላይ ባይገኝም በዚህ እምነቱ ብቻ ይከፍራል፡፡ ከዛ ውጪ ተግባሩ ኃጢአት መሆኑን ልቡ ያመነ ሙስሊም፡ በነፍሲያው ፍላጎት ኃጢአቱ ላይ ቢወድቅ ከፈረ አይባልም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
/channel/islamictrueth
ለዉዷ ሙስሊም እህቴ
ክፍል ሶስት
በሃራም ግንኙነትሽ መልካም ወንዶች ለመልካም ሴቶች የተገቡ ናቸው ሲል በቁርዓን ከተገለፁት ምድብ እራስሽን በፈቃድሽ አስወጥተሸል፡፡ ጥብቅ ሴት ብልቷን ብቻ የጠበቀች ሳይሆን እጮኛ፣ የወንድ ጓደኛ የሚባል ከኒካህ በፊት ፈፅሞ ያልያዘች ማለት ነው፡፡
فَانكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ
ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25)
ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ ኢብኑ አባስ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈጸሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ መሆኑን ሲገልፁ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ የሚለው ደግሞ ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ በዛው ማብራሪያቸው ላይም ሃሰነል በስሪ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) የወንድ ጓደኛ ማለት እንደሆነ መናገራቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ታዲያ እህቴ አንቺስ ከነዚህ ከጥብቆቹ ምድብ ወጥተሸ ከባለጌዎች ምድብ መመደብሽ እንደ ሙስሊም ሴትነትሽ ለህሊናሽ አይከብድሽም ??
Abdulaziz Aliiy
#ዝሙትን_እንጠየፍ
/channel/islamictrueth
ቁጥር ሁለት
ዉዷ እህቴ...
ሰዎች በየጥጋጥጉ በምሽት የሚፈፅሙት አስነዋሪ ተግባር ስትጠየፊ ኖረሽ አንቺም ሳታውቂው በተኩላዎች ወጥመድ ውስጥ ወድቀሽ ሰዎች በምሽት በየመንገዱ እና በየጥቃጥጉ የሚፈፅሙትን ጅንጀና እና የሃራም ግንኙነት አንቺም በኢንተርኔት መስኮት መፈጸም የለብሽም፡፡
በሰዎች ዘንድ እንኳን በየመንገዱ በየጭለማው የሚጀናጀኑ ሴት እና ወንዶች ሲታዩ እነዚህ ቤተሰብ አሰዳቢዎች ናቸው፣እከሊት እኮ የእነ እከሌ ልጅ ናት ፣ጥሩ ልጅ ነበረች ተበላሸች ሲባል ሁሌም ትሰሚያለሽ፡፡ ምናልባትም አንቺም ከዚህ መሰሉ አስቀየሚ ተግባር ሲፈፀም አይተሸ ተፀይፈሽ ተናግረሽ ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ ግን አንቺም ኒካህ አንድ ቀን አደርግልሻለው ላለሽ ሰው ጋር በየጭለማ ጥጋጥጉ የሚደረገው ጅንጀና በዘመናዊነት ተቀይሮ በኢንተርኔት መስኮት ብቅ ሲል አንቺም የዚህ የጥፋት ተግባር ተቀዳሚ ተሰላፊ ሆነሽ በሰዎች የጠላሽውን አስነዋሪ ተግባር ሰዎችም ሆነ ቤተሰቦሽን ሳያውቁ መኖሪያ ቤትሽ እየፈጸምሽው ትገኛለሽ፡፡ እህቴ ታዲያ መጀመሪያ ስትጸየፊ የነበረው ተግባር ጭለማውን ነበር ወይስ ተግባሩን ?? በኢንተርኔ መስኮትም በቀንም ሆነ በጨለማ አንቺም ከነሱ በባሰ ሁኔታ ይህን አስነዋሪ ተግባር እየፈጸምሽ ነው ፡፡ እናስ የምትጠየፊ የነበረው ምኑን ይሆን እህቴ??
Abdulaziz Aliiy
#ዝሙትን_እንጠየፍ
/channel/islamictrueth
በሰጋጅ ፊት ሰብሮ ማለፍ ምን ያህል ኃጢያት እንደሆነ ያውቃሉ?
ከሰጋጁ ፊት ለፊት አቋርጦ የሚያልፈው ግለሠብ የድርጊቱን ኩነኔ ቢያውቀው ኑሮ አቋርጦ ከማለፍ ይልቅ ዐርባን ቢቆም ይሻለው ነበር(ይመርጥ ነበር።)" የሐዲሱ አስተላላፊው አቡንነድር "ዐርባን ቢቆም ይሻለው ነበር (ይመርጥ ነበር)" ካለ ቡኋላ ዐርባ ቀን ይበል ዐርባ ወር ይበል ዐርባ ዓመት ይበል አይበል አላስታውስም ሲል ተናገሯል። (ቡኻሪ 510 ላይ ዘግበውታል።)
በተጨማሪም ቡኻሪ 487 እና ሙስሊም 505 ላይ የሚከተለለውን ዘግበዋል:- "አቡ ሰዒድ አልኩድሪይ ከዕለታት በአንዱ ጁምዓ ከፊት ለፊቱ ግርዶሽ ከሚሆንለት ነገር ተጠግቶ እየሰገደ ሳለ ከአቢ ሙዐይጥ ነገድ የሆነ ወጣት ከፊት ለፊቱ ለማቋረጥ ሲፈልግ አቡ ሰዒድ ደረቱን በመግፋት አቀበው፤ ወጣቱም ሌላ አቋርጦ የሚሄድበት ክፍት ቦታ እንዳለ ዙሪያውን ቢቃኝም በአቡ ሰዒድ ፊት ለፊት አለም እንጂ ሌላ ክፍተት ያለው ማቋረጫ ሊያገኝ አልቻለም፤ ወጣቱ ተመልሶ በመምጣት ዳግመኛ ለማቋረጥ ሲሞክር አቡ ሰዒድ ከመጀመሪያው ይበልጥ በበረታ ሁኔታ ደረቱን በመግፋት ዐቀበው፤ በዚህ ድርጊቱ ውስጡ ቅሬታ እንዲያድር አደርጎበት መርዋን ዘንድ በመሄድ ስሞታውን አሰማ። አቡ ሰዒድም ከተወሰኑ ቆይታዎች ቡኋላ ከመርዋን ዘንድ ሲገባ "አባ ሰዒድ ሆይ! አንተና የወንድምህ ልጅ መካከል ምን ዓይነት ቅሬታ ተፈጠረ ?" ሲል ይጠይቀዋል። አቡ ሰዒድም የአሏህ መልክተኛ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) "አንዳችሁ ከሚጋርደው ግርዶሽ አጠገብ በመሆን እየሰገደ ሳለ ሰላቱን ለማቋረጥ አንድ ግለሠብ ቢመጣ ገፍተር ያድርገው፣ ገፍትሮትም ማቋረጡን ካላቆመ በኃይል ተጠቅሞ ከማቋረጥ ይመልሰው *እርሱ እኮ ሸይጧን ነው*" ማለታቸውን ስለሰማሁ ነው የገፈተርኩት በማለት መለሰለት።
ይህን ሐዲስ አስመልክቶ ( …*እርሱ እኮ ሸይጧን ነው*) የሚለውን የሚለው ሐረግ ኢማሙ ነወዊይ ረሒመሁሏሁ ሲያብራሩ( *እርሱ እኮ ሸይጧን ነው*) የሚለው ሐረግ ፍቺ ምን እንደሆነ አልቃዲ ሲገልጹ "እርሱ እኮ ሸይጧን ነው ሲገፈተር ከመመለስ አሸፈረኝ እንዲል ያደረገውና እንዲያቋርጥ የገፋፋው" ተብሏል። "እርሱ እኮ ሸይጧን ነው የሸይጧንን ተግባር የሚተገብር ምክኒያቱም ሸይጧን በጎ ተግባርን ከመተግበር በእጅጉ የራቀና ሱንናን ከመቀበል ዕብሪተኛ ነው"ም ተብሏል። በሌላም ዘገባ እንደተገለጸው ጥውንቱ ሸይጧን ነው ይህን እንዲተገብር የገፋፋው የሚልም ፍቺ ተሰጥቶታል። አሏህ ይበልጡን ያውቃል። [ ሸርሑ ሰሂህ ሙስሊም 4/167]
ነገር ግን የኢማሙ ግርዶ ለተከታዮቹም ግርዶ ይሆናል። ይህ ማለት ኢማሙ እያሰገደ በተከታዩች ላይ ማለፍ ይቻላል ለዚህም ማረስጃው:-
ኢብን ዑመር(ረ.ዐ) እንዳወሡት የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የኢድ ቀን የወጡ ጊዜ አጭር ጦር(አንካሴ) ከፊት ለፊታቸው እንዲተከል ያዙናል፡፡ እርሷን ፊት ለፊታቸው አድርገው በመቆም ያሰግዳሉ፡፡ ሰዎች ደግሞ ከኋላቸው ይሰለፋሉ፡፡ ለጉዙ ሲወጡም እንዲህ ያደርጉ ነበር። ከርሳቸው ቡኋላ(ፈለጋቸውን የተከተሉ) መሪዎችም ይህንኑ ፋና ይከተሉ ነበር፡፡ (ሶሂህ አል ቡኻሪ)
አቡ ጁሐይፋ እንዳስተላለፉት ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቡጥሀእ ዙህርን ሁለት "ረከዓ" ዐስርንም ሁለት "ረከዓ" አሰግደዋል፡፡ ከፊት ለፊታቸው አንካሴ ይተክሉ ነበር፡፡ ከፊት ለፊታቸው(አንካሴ ከተቸከለበት ውጭ ባለው ቦታ) ላይ ሴቶችና አህያዎች ያልፉ ነበር፡፡ (ሶሂህ አል ቡኻሪ)
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዙዎች ይህን ስህተት ሲፈፅሙ ይታያል! ይህን መልእክት በማስተላለፍ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንርዳቸው!
/channel/islamictrueth
#የአሹራ ቀን ፆም!
ለመልካም ስራ አስተዋሽ እንሁን
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾
“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1134
በሌላ ሀዲሳቸው (ﷺ)፦
﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾
“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
ጆይን፦ /channel/BuhariMuslimAmharic
ሙስሊም ወንድ ከሌላ እምነት ሴት ጋር፤ ሙስሊም ሴት ከሌላ እምነት ወንድ ጋር በትዳር መጣመር! በሸሪአ እይታ!
በአቡ ሀይደር
ሰፊ ርእስ ሰፊ ትንተና ይፈልጋልና በትእግስት ሙሉዉን ያንብቡት!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን(አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
1ኛ) ጋብቻ የጌታ አላህ ትእዛዝ፣ የነቢያት ሱንና እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሕይወት ፈለግ ነው፡፡ አላህ ትዳር የሌላቸውን ሰዎች እንድናጋባቸው ትእዛዝን ሰጥቷል፡፡ ለጊዜው ችግረኞች ቢኾኑ ከሱ በኾነ ቸርነት እንደሚያብቃቃቸውም ቃልን ገብቶላቸዋል፡፡ ቀደምት ነቢያትንም በትዳር እንዲጣመሩ በማድረግ የነቢያት ሱንና መኾኑንንም አበክሮ ነግሮናል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)…" (ሱረቱ-ኑር 24፡32)፡፡
"ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል…" (ሱረቱ-ረዕድ 13፡38)፡፡
2ኛ) የጋብቻ ዓላማው፡- እራስን ሐራም ከኾነው ዝሙት በመከላከል በህጋዊ መንገድ ትዳርን መስርቶ የነፍሲያን እርካታ ለመጎናጸፍ፣ በምድር ላይ ቀጣይነት ያለው አላህን የሚያመልክ ትውልድ ለመተካት ነው፡፡ በተለይ ዝሙትን ለመሸሽ እና ለመራቅ ብሎ ትዳርን የሚፈልግ ሰው፤ ችግረኛም ቢኾን እንኳ አላህ እንደሚያብቃቃው በቁርኣኑ ረሱላችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ደግሞ በሐዲሣቸው ነግረውናል፡፡ በተቃራኒው ያለ ምንም ሸሪዓዊ ምክንያት እራስን ከትዳር ዓለም ማግለል ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱንና ማፈንገጥ እንደኾነ ተገልጾአል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡" (ሱረቱ-ሩም 30፡22)፡፡
"ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡" (ሱረቱ-ኑር 24፡32)፡፡
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሶስት ሰዎች አላህ ሊያግዛቸው የተገባ ነው…..ከዝሙት መጥጠበቅን ፈልጎ ትዳር የመሰረተን" (ሶሒሑ ቲርሚዚ 1655)፡፡
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- ሶስት ሰዎች ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሚስቶች ቤት ስለ መልክተኛው ዒባዳህ አፈጻጸም ለመጠየቅ መጡ፡፡ በተነገራቸውም ጊዜ ‹‹እሳቸው ያለፈውም የሚመጣውም ስህተት ተምሮላቸው ሳለ እንዲህ ከኾኑ እኛ ከሳቸው አንጻር ታዲያ የት ነው ያለነው!›› በማለት ሥራቸውን አቅለው ተመለከቱት፡፡ ከዚያም ከሶስቱ አንደኛው፡- ‹‹ከአሁን በኋላ ሁሌም ለሊት ተነስቼ እሰግዳለሁ በፍጹም አላርፍም›› አለ፡፡ ሌላኛውም፡- ‹‹ሁሌም ቀኑን እጾማለሁ በፍጹም አላፈጥርም!›› ሲል ሶስተኛውም በበኩሉ፡- ‹‹እኔም ሴቶችን እርቃለሁ መቼም አላገባም!›› ይላል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጡና፡- ‹‹እንደዚህ እንደዚህ ያላችሁት እናንተ ናችሁን? በጌታዬ ይሁንብኝ! አላህን በመፍራትና እሱን በመጠንቀቅ እኔ በላጫችሁ ነኝ፡፡ ኾኖም አንዳንዴ እጾማለሁ ደግሞም አፈጥራለሁ፣ ከለሊቱ ክፍል ተነስቼ ለጌታዬ እሰግዳለሁ ደግሞም አርፋለሁ፣ አላህ የፈቀደልኝንም ሚስቶችን አገባለሁ፡፡ ከኔ ሱንና የጠላ ሰው ከኔ አይደለም!›› አሏቸው›› (ቡኻሪይ 5063፣ ሙስሊም 1401)፡፡
3ኛ) ጋብቻ ሃይማኖታዊ ብይኑ ሱንና ሙአከድ (እጅግ ተወዳጅ የኾነ) ነው፡፡ ዋጂብ አይደለም፡፡ የትዳር ጣጣዎችን መሸፈን እየቻለ ስሜት የሚያስቸግረው በኾነ ሰው ላይ ግን ዋጂብ እንደኾነ የኢስላም ሊቃውንት ይገልጻሉ፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ ‹‹በስሜት መቸገር ምክንያት ሐራም ላይ የሚወድቅ ከኾነ እራሱን ከሐራም መጠበቅ ግዳጅ ስለሚኾንበት አማራጩ ደግሞ ቶሎ ትዳር መመስረት ከኾነ ለዚህ ሰው ትዳር ዋጂብ ይኾናል ማለት ነው›› በማለት ይገልጻሉ፡፡ ትዳር በመሠረቱ ግን የተወደደ ተግባር እንጂ ግዳጅ አይደለም፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፡- "እናንተ የወጣት ስብስቦች ሆይ! ከናንተ ውስጥ የትዳርን ጣጣ የሚችል ካለ ቶሎ ያግባ፡፡ እሱ (ትዳሩ) አይንን ለመስበር ብልትንም ከዝሙት ለመከላከል ይረዳልና፡፡ ጣጣውን መሸፈን ያልቻለ ደግሞ በፆም ላይ ይበርታ፡፡ እሱ (ፆሙ) ስሜቱን ያቀዘቅዝለታልና" (ቡኻሪይ 5066፣ ሙስሊም 1400)፡፡
4) አንድ ሙስሊም የኾነ ወንድ ለትዳር የሚፈልጋት ሴት ሙስሊም መኾኗ በተለይም ኢማኗ ጠንካራ የኾነ ዲነኛ ሴት ማግባቱ እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡ ቤቱንም ሆነ ልጆቹን በአላህ ዲን ላይ ሰበብ በመኾን ትጠብቅለታለችና፡፡ በተጨማሪም አላህና መልክተኛው ባዘዙት መሠረት የባሏን ሐቅ ለመወጣት ትጥራለች፡፡ በተጨማሪም ብዙ ወላድ እና ተወዳጅ የኾነችውን ማግባት ተመራጭ ነው፡፡ የቤተሰቧን እና የዘመዶቿን ሁኔታ በመጠየቅ እናቷ ብዙ የወለዱ ከኾነ ወይም ከታላላቅ እሕቶቿ መውለድ በመነሳት ወላድ መኾነዋን በአመዛኙ ማወቅ ይቻላል፡፡ ወይንም ከዚህ በፊት ትዳር ይዛ ከነበር በዛ ማወቅ ይቻላል፡፡ ዋናው የአላህ ፈቃድና ውሳኔ ከመኾኑ ጋር ማለት ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"(በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡ ከአጋሪው (ጌታ) ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ እነዚያ (አጋሪዎች) ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡220)፡፡
"…የከሓዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ…" (ሱረቱል ሙምተሒናህ 60፡10)፡፡
መዕቀል ኢብኑ የሳር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ባሏን ወዳድና ልጆችን ወልላድ የኾነችዋን አግቡ፡፡ እኔ በናንተ ሰበብ ብዛት ያለው ተከታይ ይኖረኛልና " (አቡ ዳዉድ 2050፣ ነሳኢ 3227)፡፡
በነዚህ አንቀጽ መሠረት በአላህ የሚጋሩ የኾኑ ሙሽሪኮች እንዲሁም ከሀዲያኖች ጋር ሴቶቻቸውን ማግባትም ኾነ የጋብቻ ቃል-ኪዳን መያዝ ሴቶቻችንን ለነሱ መዳር ሐራም መኾኑን በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ አያይዞም በአላህ ያመነች ሙስሊም ሴት በባርነት ቀንበር ውስጥ እንኳ ብትኾን በአላህ ካጋራችው ውብና ቆንጆዋ ሙሽሪክ ሴት እጅግ የምትበልጥ እንደኾነች በጌታ አላህ ተመስክሮላታል፡፡ ምክንያቱም ሙሽሪኮች የሚጣሩት ወደ ጀሀነም እሳት ነውና፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡ በዚህ ሙሽሪክ በሚለው ጥቅላዊ ቃል ውስጥ ጣኦት አምላኪዎች ብቻ ሳይሆኑ አይሁዶችና ክርስቲያችም ይካተታሉ፡፡ እነሱም ዑዘይርን እና የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂማ-ሰላም) የአላህ ልጅ ናቸው በማለት ስለሚያሻርኩ ማለት ነው፡፡ ኾኖም በሌላ
ዒድ ሙባረክ
እንኳን ለ1444ኛው የዒደል አድሀ(ዓረፋ) በዐል በሰላም አደረሰን ኢዱ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ ያድርግልን!!!
/channel/islamictrueth
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት
(ክፍል–4/ የመጨረሻው ክፍል)
የአራተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ አንደኛው ቀን ነው።
1️⃣ በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል። የመጀመሪያው ከዚያም መካከለኛው ከዚያም ጀምረተል–ዓቀባ ላይ እያንዳንዱ ጉድጓድ ላይ ሰባት ሰባት ጠጠሮችን በማከታትል እና እያንዳነዱን ጠጠር በሚወረውርበት ጊዜ "አላሁ አክበር " በማለት ይሆናል። ጠጠር የመወርወር ተግባሩ የሚሆነው ጸሐይ ከአናት ከተዘነበለች በኋላ ነው። ከዚያ በፊት መወርወሩ አይፈቀድም።
ከመጀመሪያው እና መካከለኛው የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓድ በኋላ ዱዓእ ለማድረግ መቆም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
2️⃣ አስራ ሁለተኛውን ለሊት ሚና ውስጥ ያድራል።
የአምስተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሁለተኛው ቀን ነው።
1️⃣ በአራተኛው እለት እንዳደረገው ሁሉ በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
2️⃣ ተቻኩሎ በአስራ ሁለተኛው ቀን ከሚና መውጣት ከፈለገ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይወጣል ወይም እስከ አስራ ሶስተኛው ቀን መዘግየት ከፈለገ በዚያው ያድራል።
የስድስተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሶስተኛው ቀን ነው።
የዚህ እለት ተግባር ሚና ላይ የዘገዩትን ሰዎች ብቻ ነው የሚመለከተው።
1️⃣ ከዚህ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት በፈፀመው መሰረት በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
2️⃣ ከዚያ በኋላ ሚናን ለቆ ይወጣል።
የመጨረሻው ስራ ጠዋፈል—ወዳዕ (የመሰናበቻ ጠዎፍ) ይሆናል። እርሱም ወደ ሀገሩ ሊመለስ ሲል የሚያደርገው ነው።
ተፈፀመ
አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 /channel/tahaahmed9
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት
(ክፍል–2)
የሁለተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር ዘጠነኛው የዓረፋ–ቀን ነው።
1️⃣ ፀሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ዓረፋ ይጓዛል። የዙህርና የዓስርን ሰላቶች ሁለት ሁለት ረከዓ በማድርግ አሳጥሮ እንዲሁም አስቀድሞ በዙሁር ሰላት ወቅት ይሰግዳል። ፀሐይ ከአናት ከመዘንበሎ በፊት እዚያ ከደረሰና ከገራለት የሰላቱ እና የኹጥባው ስነ–ስርአት እሰኪጠናቀቅ ነሚራ በምትባለው አሁን መስጂድ በተሰራበት ቦታ ያርፋል።
2️⃣ ከሰላት በኋላ ፀሐይ እሰክትጠልቅ ያለውን ጊዜ ለዚክር እንዲሁም ወደ ቂብላ አቅጣጫ በመዞር እጆችን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመዘርጋት ለሚፈፅመው የዱዓእ ስነ–ስርአት ያውለዎል።
3️⃣ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሙዝደሊፋ ያቀናል። መግሪብን ሶስት ዒሻን ሁለት ረከዓ አድርጎ እዚያ ሲደርሰ ይሰግዳል። ጎህ እሰከሚቀድ ድረስም ለሊቱን በዚያው ያሳልፋል።
4️⃣ ጎህ ከቀደደ በኋላ የፈጅር ሰላትን ይሰግዳል ከዚያ በኋላ በደንብ መንጋቱ እስኪታወቅ ድረስ ያለውን ጊዜ ለዚክር እና ዱዓእ ያውለዎል።
5️⃣ ከዚያም ፀሐይ ከመውጣቶ በፊት ወደ ሚና ጉዞ ይጀምራል።
ይቀጥላል…
ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ… አላህ ያግራልን!
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 /channel/tahaahmed9
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት
ይህ የሐጅን ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት የሚያብራራ አጭር ጽሁፍ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል–ዑስይሚን ተዘጋጅቶ ወደ አማርኛ ተመልሶ የተሰራጨ ነው።
በአላህ ፍቃድ የየእለቱን የሐጅ ተግባር ከዚህ ቀጥሎ ከፋፍለን እናቀርባለን:–
(ክፍል–1)
የመጀሪያው ቀን ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን የውመ አት–ተርዊያ በመባል የሚታወቀው ነው።
1️⃣ ለሐጅ ኢህራም ወይም ኒያ ማድረግ
በመካ ከተማ እና በዙሪያዎ ያለ ሰው ካለበት ቦታ ታጥቦ፣ (አካሉን) ሽቶ ተቀብቶ፣ የኢህራም ልብሱን ለብሶ እና "ለበይከ ሀጀን፤ ለበይከ አላሁመ ለበይክ፤ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለከ" በማለት ኢህራም(ኒያ) ያደርጋል። ከዚህ ቀን በፊት መካ ያልመጣና ከሚቃት ክልል ውጪ ለሀጅ ወይም ዑምራ የሚመጣ ሰው የሚቃት ክልሉን ያለ ኢህራም(ኒያ) ማለፍ የለበትም።* 2️⃣ *ወደ ሚና መጓዝ*
ወደ ሚና ይጓዛል እዚያም የዘጠነኛው ቀን ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ ይቆያል። የስምንተኛውን ቀን የዙሁርን፣ የዓስርን፣ የመግሪብን እና የዒሻን እንዲሁም የዘጠነኛውን ቀን ፈጅር ሰላቶች በየወቅታቸው እና አራት አራት ረከዓ የሆኑትን የዙህር የዓስርና የዒሻእ ሰላቶች ሁለት ሁለት ረከዓ በማድረግ አሳጥሮ ይሰግዳል።
ይቀጥላል…
ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ
አላህ ያግራልን!
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 /channel/tahaahmed9