ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
አላህ(ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአን ዉስጥ ነብዩ(ﷺ) ምን ብሎ ነዉ ያወደሳቸዉ?
/channel/islamictrueth
ረመዳን ከመሆኑ ጋር ብታዳምጡት የበለጠ አጅር የምታገኙበት። አቀራሩም ስለሚያምር የምትረኩበት ስለሆነ ለማበረታትና ለቀጣይ ስራዎች ይመጣ ዘንድ ከምንጩ ከራሱ ከዩትዩብ ቻናሉ እናዳምጥ!!!
Читать полностью…ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሚፈፀሙ ተደጋጋሚ ሁለት ስህተቶች 2 ደቂቃ ብቻ
/channel/islamictrueth
🌙 ረመዳን ሙባረክ🌙
የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ ነገ ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ይሆናል።
ፆሙ የሰላም፣ የአፊያ፣ የኢባዳ ያድርግልን!
/channel/islamictrueth
አላህ ለፆመኞች የሚሰጠዉ ምንዳ እኔ ነኝ የምከፍለዉ ነዉ ያለዉ። ማለትም ቁጥሩንም ምን እንደሆነም አልተናገረም!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
አንድ ቤንጤ ሙስሊም ሳይሆን ሙስሊም ነበርኩኝ ማለት ይችላል። ይህን የፈቀደዉ መፀሀፍ ቅዱስ ነዉ!
/channel/islamictrueth
ፆማችን ሆነ ሌላ መልካም ስራችን ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለዉ...
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
በረመዳን ሰይጣኖች የሚታሰሩ ከሆነ መጥፎ ስራዎችና ወንጀሎች ለምን አይቆሙም ለሚለዉ ጥያቄ የተሰጠ በቂ መልስ!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
በሁሉም ለሊቶች የሚገኝ በረከት!
ልብ ይበሉ ሀዲሱን በደንብ ደግማቹ አንብቡት በሁሉም ለሊቶች የሚገኝ ነዉ እሺ።
ሶሒሕ መሆኑ ሁሉም ሙስሊሞች የሚስማሙበት ኪታብ ውስጥ ቡኻሪ እና ሙስሊም ውስጥ ደግሞ [ አላህ በየሌሊቱ የሌሊቱ መጨረሻ 1/3ኛ ሲቀር ወደ ቅርቧ ሰማይ ወርዶ "ማነው የሚለመነኝ? እሺ የምለው ፤ ማነው የሚጠይቀኝ? የምሰጠው ፤ ማነው ኢስቲግፋር የሚያደርግ? የምምረው ] እንደሚል ነቢዩ (- ﷺ -) ተናግረዋል።
/channel/islamictrueth
የዱንያንና የአኼራን ጉዳይ መልካም ነገር መጠየቅ የፈለገ ይሄን ዱአ ያድርግ!
/channel/islamictrueth
የሙስሊሞች ጀነት መብላት፣ መጠጣትና ግንኙነት መፈፀም ነዉ ለሚሉ ሰዎች የተሰጠ አጭር ማብራሪያ!
/channel/islamictrueth
ፆም ማለት ገበያን ማጨናነቅ፣ ቤትን ማጨናነቅ ማለት አይደለም!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
ልባቸው በጥ*ላ*ቻ ለታወረ ወገኖች የምንላቸው ነገር ቢኖር፡- ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንኳን ወላጆቻችን ዓለሙ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ቢቀርብ አላህ ዘንድ ካላቸው ደረጃ አንድ እጁንም አይሞላም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ምድር ውበቷ እሷንና በላይዋ ላይ ያሉትን የፈጠረውን አንድ አምላክ ስናመልክባት ነው፡፡ ይህ ትምሕርት ደግሞ እሳቸው ነቢይ ሆነው ባይላኩ ኖሮ መች ይገኝ ነበር?፡፡ እኛም በክህደት ጨለማ ተውጠን በአምላክ ፈንታ ሰውን አምልከን የክህደት ጉድጓድ ውስጥ በወደቅን ነበር፡፡ ዓለሙም በጨለመ ነበር፡፡ አልሐምዱ ሊላህ እሳቸውን ነቢይ አድርጎ ለላከልን አላህ፡፡
"ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰዉ፣ ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለዉም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎች ነዉ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 85)፡፡
ከኡስታዝ አቡ ሀይደር ከበፊት ፁሁፉ የተወሰደ!
/channel/islamictrueth
ቃሪእ ሰኢድ ግርማ ሱረቱ-ቃፍ القارئ سعيد جرما سورة ق
https://youtube.com/watch?v=CpQQ7hSaxEU&si=aP1U-oIcqD3ho4jl
ያለ ሶላት ፆም፣ ሀጅ፣ ዘካና ሌላ መልካም ስራዎች ዋጋ የላቸዉም። በእለተ ቂያማ ከተዉሂድ በኃላ የሰዉ ልጅ የሚጠየቀዉ በሶላቱ ነዉ። ሶላቱ ካማራ መልካም ሆነለት።
/channel/islamictrueth
አዛኑ እስከሚጨርስ ድረስ የሚጠጡ ፆም መያዧዉ የአዛኑ መጨረሻ ብለዉ በማሰብ(በመጠርጠር) ለሚሉ የተሰጠ መልስ!
በሼይኸ ሱሌይማን አሩሀይሊ
ይሄ ስህተት ነዉ ከፊል አላዋቂዎች አሶላቱ ኸይሩ ሚነ ነዉም እስከሚል ድረስ የሚጠጡ የሚበሉ አሉ ከፊሎቹ ደግሞ አዛን ብሎ እስኪጨርስ ድረስ ይሄ ስህተት ነዉ። ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ብሉ ጠጡ ኢብን ኡሚ መክቱም አዛን እስከሚያደርግ ድረስ ብለዋል።
አዛን ወሰን አድርገዋል
አዛን ከበፊቱ አይነት አይደለም። ግዴታዉ አዛን ሲል ቶሎ መያዝ ማቆም ነዉ። አዛን እያለ
ሶስት ሁኔታዎች መብላት መጠጣት ይቻላል።
1ኛ) አዛን እያለ ዉሀ መጠጣት ፈልገህ እቃዉን አንስተሃል አዛን አድራጊዉ አሏህ አክበር አለ ጠጣ ጉዳይን እስክትሞላ ድረስ።
2ኛ) አዛን አድራጊዉ አዛን ካለ አፍህ ዉስጥ የጓረስከዉ ካለ ማዉጣት ግዴታ አይሆንብህም ዋጠዉ ፆምህ ትክክል ነዉ አልሀምዱሊላህ።
3ኛ) መድሀኒት አንስተህ አዛን አድራጊዉ አዛን ካለ መድኃኒት መውሰዱ ግድ ከኾነ ዉሰድ። መድሀኒት መዉሰድ እረስተህ አዛን ሲቃረብ ወደ ፍሪጅ ሄድክ ከፍሪጁ ወድሀኒቱን አወጣህ መድሀኒት መዉሰድ ፈለክ ከዚያ ቡሃላ ዉሀ መጠጣት ፈለክ ከዚያ ቡሃላ አዛን ሊል መድሀኒቱን ዉሰድ ዉሀ ጠጣ ፆምህ ትክክል ይሆናል ከዚህ ዉጭ ያለ አይፈቀድም።
Copy
/channel/islamictrueth
ጫት ለመተው ላሰበ ሰው እንደ ረመዳን አጋዥ አያገኝም። ረመዳንን መጠቀም ብልሀት ነው። ከተራዊህ መልስ ደሞ ሱስ እንዳይረብሸው መተኛት ይችላል።
ብዙ ሰዎች ጋር የሚተገበር የጾምን አላማ የሳተ አጿጻጿም👉 ለሊት እየቃሙ ቀን መተኛት ነው። ይህ ወሩን የ ኢባዳ ሳይሆን የመቃሚያ ወር ያስመስለዋል። ምንም ሳናሽሞነሙነው ጫት ለሰው ልጅ ጎጂ ነው። ጎጂ ሆኖ ደግሞ ሀላል የለም። የሱሰኞች ሁሉ ራስን ማታለያ ቃላቶች "መተው እችላለሁ" "ባልቅም ግዴለኝም" "ሁለት እንጨት ለጨዋታ/ለሙድ ብቻ ነው" የሚሉት ናቸው። ይህ ማለት denial የሱሰኝነት ምልክት ነው። እያንዳንዱ ሰው ለጫት ባወጣው ገንዘብ አላህ ይጠይቀዋል። ምንም ሸክ የለውም። የጫት ሱስ አደገኝነቱ ከህጻን እስከአዋቂ፣ የተማረ ያልተማረ፣ ከኸለፍ እስከ ሰለፍ፣ ሴት ወንድ ሁሉንም ማጥቃቱ ነው።
ባንድ ወቅት በረመዳን ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ላስተምር ሄጄ አንድ ወንድም ላፈጠርህ ብሎ ያዘኝ። ብዙም ስለማላውቀው ሳቅማማ የሱ ጓደኛ የሆነ ሷሂቤን ነግሮት ካላመጣሀው ብሎት ይዞኝ ሄደ። ለፊጥራ ስገባ ግን የተዘጋጀውን ምግብ አይቼ ድግስ መስሎኝ ነበር። ሆኖም ለኛው ነበር። አፍጥረን ስንጨርስ ልጁ "አንተኮ ባለውለታየ ነህ" አለኝ። እኔም ገርሞኝ "እንዴት የትስ ተገናኝተን" አልኩት። እሱም ባንድ ወቅት ጅማ ዩኒቨርስቲ ልጆችን ስትመክር "ሰባት ሰአት ላይ ቆጪ ጫት ተራ ልትገዙ እየሄዳችሁ ነቢ (ሰአወ) በህይወት ኑሮ መንገድ ላይ አግኝተው ስምህን ጠርተው "የት እየሄድክ ነው ? ቢሉህ ምን ብለህ ትመልሳለህ? ስትል ደነገጥኩ። ከዛ በፊት በጫት ህይወቴ ምስቅልቅል ያለ ነበር። ከዛ ንግግር በኋላ ጫትን ተውኩ ተውኩ። ዱንያ ሁሉ አማረችልኝ አለኝ።
እና እስቲ በዚህ ረመዳን ይህንን የአለም ጤና ድርጅትም ሆነ FDA "ከ ሀሽሾች አንዱ" ያሉትን ቅጠል፣ ሙስሊሙን አለም የቲም ብኩን አድርጎ ያስቀረ የተረገመ ቅጠል፣ የሰውን ግብ ዝቅ ያደረገ፣ ቤተሰብን የበተነ፣ ጤናን ያቃወሰ፣ ወጣቱን ከንቱ አድርጎ ያስቀረ ነጃሳን ለመተው ነይቱ።
አላህ ይርዳችሁ።
Kha Abate
ሴት ልጅ ሽቶ ተቀብታ አደባባይ ትዉጣ ይላሉ ሌላም ሀራም ነገር ይፈቅዳሉ። እነማን ካላቹ ሙሉ ቪዲዩ ተመልከቱ!
/channel/islamictrueth
የሰመረ ህይወትን ሰዎች እንዳይመሩ የሚያደርጋቸዉ ነገር...
/channel/islamictrueth
የሙስሊሞች አንድነት ላይ ጉጉት ይኑርህ!
ልብ ይበሉ ይህ መልእክት የዛሬ 8 አመት የተሰጠ ምክር ነዉና ከጭፍን ጥላቻ ወጥታቹ አዳምጡት!
/channel/islamictrueth
⚠️⚠️ የጎረቤት ሐቅ!
ከአቡ ሁረይራ (📿) ተይዞ: ለነቢዩ (📿) እንዲህ አልኳቸው፦
﴿يا رَسولَ اللهِ ! إنَّ فلانةَ تقومُ اللَّيلَ وتَصومُ النَّهارَ وتفعلُ، وتصدَّقُ، وتُؤذي جيرانَها بلِسانِها؟ فقال رسولُ اللهِ 📿 لا خَيرَ فيها، هيَ من أهلِ النّارِ.﴾
“አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እከሊት ሌሊት ሰላት በመቆም ታሳልፋለች፣ ቀን ትፆማለች እንዲሁም ሰደቃ ታደርጋለች። ነገር ግን ‘በምላሷ ጎረቤቷን በነገር ታስቸግራለች።’ ረሱል (🤍) አሉ፦ መልካም የሆነ ነገር የላትም። እሷ የእሳት ነች።”
📚 ቡኻሪ አልአዳቡል ሙፍረድ ላይ ዘግበውታል: 119
▪️▪️▪️▪️🔸🔸▪️▪️▪️▪️
✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
📱፦ https://bit.ly/486xnrS
📱፦ https://bit.ly/41zEZkk
📱፦ https://bit.ly/4arMbTx
📱፦ https://bit.ly/41tIUPv
📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh
በዘንድሮ ረመዳን ምን ለማድረግ ወሰናቹ?
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
ረመዳን የአላህ ታዛዥና ባሪያዉ መሆናችንን የምናሳይበትና የምንገልፅበት ነዉ!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
ረመዳን ወሩን ሙሉ እዝነት፣ ምህረትና ከእሳት ነፃ የምንባልበት እንጂ በቀናት የተከፋፈለ አይደለም!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
አላህን በቋንቋህ ለምን የግድ አረብኛ ይሁን አልተባልክም!
/channel/islamictrueth
ገበያ ላይ ጠፍቶ የነበረዉ የኡስታዝ አቡ ሀይደር ቀዷዕ ወል- ቀደር (ቅድመ ዉሳኔ) እና በሰዉ ነፃ ፍቃድ ዙርያ የተዘጋጀ ጥናታዊ ፁሁፍ መፀሀፍ አሁን በገበያ ላይ ይገኛል።
/channel/islamictrueth