islamictrueth | Unsorted

Telegram-канал islamictrueth - ኢስላማዊ እውነታ

11751

ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

Subscribe to a channel

ኢስላማዊ እውነታ

ሙስሊም ላልሆነ ግለሰብ ሩቃ ማድረግ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሙሉዉን ካዳመጣቹ ብቻ ነዉ የምትረዱት!

ዱዐ ባደርግ ቀደርን መመለስ ይችላል ወይ ብትባሉ አይችልም ነዉ መልሱ። ነገር ግን...

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የሀምሌ ወር የአዲስ አበባና አካባቢዋ የሶላት ወቅቶች

إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ [4:103]

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም!

በአቡ ሀይደር

1) ቅዳሜን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡

2) ጁምዓና ቅዳሜን ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡

3) ከ ጁምዓ-እሁድ ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡

4) ቅዳሜና እሁድ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
አላህ ይወፍቀን፡፡

#ስምንቱ የፆም ቀናት
አላህ ፆምን ያገራለትና የወፈቀው ሰው ደግሞ ከፈለገ በተከታታይ ለስምንት ቀናት መፆም ይችላል፡፡ እንዴት ካሉም፡-

ሀሙስ፡- ይህ 8 ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡

ከጁምዓ-እሁድ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐመረም 9ኛ 10ኛና 11ኛ ቀናት ስለሆኑ፡ ከዐሹራእ ፆም ጋር በተያያዘ መልኩ ይፆማሉ ማለት ነው፡

ሰኞ፡- ይህ 12ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡

ማክሰኞ -ሀሙስ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐረም 13ኛ 14ኛና 15ኛ ቀናት ናቸው፡፡ አያሙል-ቢድ በመባልም ይጠራሉ፡፡ የወሩን ሶስት ቀናት በነዚህ ቀናት መፆም በላጭ ነው፡፡

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ጨዋታ የህይወት ማጣፈጫ!

ከቤተሰብ ጋር መጫወት የባከነ ጊዜ አይደለም። ግንኙነትን ያጠነክራል፤ መተማመንን ይገነባል፤ ደስ የሚሉ ምርጥ ትዝታዎችን ይፈጥራል።

📌 ወደ መልካም ያመለከተ የሠሪውን አምሳያ ምንዳ ያገኛል!

#ሂዳያ_ተርቢያ #ተርቢያ

💫 @HidayaTerbiya 💫

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ለሀጅ ወይም ለዑምራ በምትሄዱበት ወቅት ህግጋቶችን ክንዋኔዎችን ከቁርአንና ከሀዲስ ብቻ ዉሰዱ። ከሸሪዐ ዉጪ የሚፈፅም በጣም ብዙ ስለምትመለከቱ እንዳትደናበሩ፣ እንዳትወዛገቡ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ነሲሀ ቲቪ በ "ሩጣንኛ" ቋንቋ ዳእዋን ሲያስተላልፍ ተመለከትኩ በየትኛዉ ቦታ የሚገኝ ነዉ? የሚያዉቅ ሰዉ ቢያስረዳን!

ለማንኛዉም ነሲሀ ቲቪ ለሁሉም!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የንግስና ተጋሪ የሌለዉ አምላክ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

❌ንፋስን አትሳደቡ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿الريحُ مِنْ رّوْحِ اللهِ، تأتِي بالرَّحْمَةِ، وتأتي بالعذابِ، فإذا رأيتُموها فلا تسبُّوها، واسألُوا اللهَ خيرَها، واستعيذُوا باللهِ مِنْ شرِّها﴾

“ንፋስ ከአላህ የሆነ መልዕክተኛ (ሰራዊት) ነች። እዝነትንም ይዛለች። ቅጣትንም ይዛለች። በተመለከታቿት ግዜ እትስደቧት። ከያዘችው መልካም ነገር አላህን ጠይቁት። ከያዘችው መጥፎ ነገር ደግሞ በአላህ ተጠበቁ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 3564

➖➖➖➖➖➖➖➖

👆 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️Telegeram

📞 Whatsup

👤Facebook 

📸Instagram

💬X

🎥buharimuslimamharic?si=mVyabo_ffqR2LTWK">Youtube

🎵buhari.muslim.amh?_t=ZM-8xIqYuJ3u7E&_r=1">Tik tok

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የአብዛኛዉ ሰዉ የሞት ሰበብ አይን ነዉ መድሀኒቱ ደግሞ ቁርአን። ሩቃ ለማድረግ ደግሞ እነ ፋቲሀ፣ ቁልሁወላሁ አሀድ፣ ቁል አኡዙ ቢረቢናስ(ፈለቅ) በቂ ናቸዉ። ከሩቃ አድራጊዎች ሁሉ በላጭ ራሳችን የምናደርገዉ ነዉ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የኢስላምን ባንዲራ ከፍ ያደረገ መስሏቹ በገንዘብ የደገፋቹት ሙነሺድ ሙአዝ ኡስታዝ ዋሂድን ፔንጤ ነህ መች ሰለምክ ብሎት አከፈረዉ።

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

እንኳን ለ 1446ኛው የዒዱል አድሐ በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ። ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የዐረፋ ቀን


ቢስሚላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ


🗓️ የዙልሒጃ 9ኛው የዐረፋ ቀን ነገ ሀሙ ላይ ይውላል


ከሌሎች ቀናት ይበልጥ ለምላሽ በጣም ቅርብ የሆነው የዱዓ ወቅት የዐረፋ ቀን ነው፡፡ ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀንም የለም። ስለዚህ ይህን አጋጣሚ ዱዓእ በማድረግና ወደአላህ በመጠጋት ተጠቀሙበት


🗓️ በዚህ 9ኛው የዐረፋ ቀን መጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል


🗓️ ለዛሬ ልዩ ስለሆነው ዐረፋ ቀን እናኛለን፡-


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


🌕 ሓጅ አድራጊዎች ያለ ፆም በዐረፋ ተራራ ላይ ከእኩለ-ቀን (ዙህር) አንስቶ መግሪብ እስኪደርስ ይቆያሉ፣ በዱዓም ጌታቸውን ይማጸናሉ፡፡ ጌታቸውም ወደነሱ ይቀርባል። አላህም በተከበሩት መላእክት ላይ የሚኮራበት፣ ባሮቹ የሚሰሩትን ስራ የሚወድበትና የሚቀበልበት ቀን ነው


📗ረሱል ﷺ በዐረፋ ምሽት ላይ አላህ ዐረፋ ላይ ወደቆሙት ሰዎች እያመላከተ “ወደባሮቼ ተመለከቱ ጸጉራቸው የተንጨባረረና አቧራ የለበሱ ሆነው ወደኔ መጥተዋል፡፡” እያለ በመላእክቱ ላይ ይኮራል ብለዋል


🍏 ሓጅ ያላደረጉት ደግሞ ቀኑን በፆምና በተለያየ ዒዳባህ ያሳልፉታል። በዚያም ቀን ብዙዎች በክፉ ተግባራቸው እሳት የተገባቸው፣ በአላህ ቸርነት ከእሳት ነጻ ይባላሉ።


📗ረሱል (ﷺ) ከዐረፋ ቀን ይበልጥ በዚያ ቀን ሸይጣን እጅግ አንሶ፣ እጅግ በጣም የሚርቅበት፣ እጅግ የሚዋረድበትና እጅግ የሚበሳጭበት ቀን የለም፡፡ ይህም የሚሆነው የአላህ እዝነት በመወረዱ፣ አላህም ሰዎችን ከሰሯቸው ትልልቅ ወንጀሎች ይቅር በማለቱ ነው፡፡ ብለዋል፡፡


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


🗓️ ይህ የዐረፋ ቀን ከሌሎች ቀናት ከሚለይባቸው ውስጥ፡-


1️⃣ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን መሆኑ፡-


📗 እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

"ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን የለም”። (ሙስሊም)


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


2️⃣ ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ በዚህ ቀን መሆኑ:–


🌕 በማንኛውም ቀንና ለሊት፣ በማንኛውም ስፍራና ሁኔታ ወደ አላህ የሚደረገው ዱዓ በሩ ክፍት ነው። ተመላሽነት የለውም፣ ሆኖም በዐረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓ ግን ከየትኛውም የተሻለ ነው


📗 ከዐብዱላህ ኢብኑ አምሩ ኢብኑል–ዓስ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

"ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓእ ነው፡፡ እኔና ከበፊቴ የነበሩት ነቢያት ከተናገርነው ቃላት ሁሉ በላጩ፡-

‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏሁ፣ ወሕደሁ፣ ላ-ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ፣ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር›› የሚለው ነው"

(ቲርሚዚይ 3585፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3274)


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


3️⃣ ፆሙ የሁለት አመት ኃጢአት ያስምራል፡-


📗 አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

"የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል”። (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው)


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


4️⃣ የሙስሊሞች ዒድ መሆኑ፡-


📗 ዑቅበተ ኢብኑ ዐሚር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

"የዐረፋ ቀን፣ የእርዱ ቀን፣ ቀጣዮቹም 3ቱ ቀናት የኛ ዒዳችን ነው”። (ሶሒሑል ጃሚዕ 8192)


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


5️⃣ ለአምስት ቀናት የሚቆየው ተክቢራም የሚጀምረው በዚሁ በዐረፋ በዘጠነኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ ነው


🌕 በዚሁ ቀን ከፈርድ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ አስተግፊሩላህ እንበልና ከዛም አላሁመ አንተ–ሰላም ...... ካልን በኋላ በቀጥታ ወደ ተክቢሩ በመግባት፡-

🗣 "አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር። ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ" እንበል


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


6️⃣ ዲኑ የተሟላበት ቀን መሆኑ፡-


🟢 ۞ "…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ…" ۞ (📖 ሱረቱል ማኢዳህ 5:3)


🍏 ይህ አንቀጽ የወረደው በዙል ሒጃ ወር፣ የመሰናበቻው ሐጅ በ 9ኛው ቀን፣ በዕለተ ጁምዓ በዐረፋ ተራራ ላይ ነበር


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


🌕 ከዐረፋ በፊት ዱዓ ለማድረግ የምትፈልጉት ሃሳብና ጉዳዮችን መዝግቡ፡፡ በቃላቹ በሸመደዳቹት ቁርአናዊ እና ነቢያዊ ዱዓዎች ዱዓዎች ዱዓእ አድርጉ፡፡ በቃል ካልሸመደዳቹ ጽፋቹ ታገዙ።


ስም እየጠራቹህ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለወንድም፣ ለወዳጅ መልካም የሆኑ ዱዓዎችን አርርጉላቸው፡፡ ምክንያቱም፡- በድብቅ ለወንድሙ ዱዓ ላደረገ ሰው መላኢካ፡- “ያደረክለት አምሳያ ላንተም ይሁን፡፡” ይለዋል፡፡


ለምድራዊው ሕይወትና ለወዲያኛው ዘላለማዊ ዓለም በሚጠቅም ነገር መልካም ዱዓእ አድርጉ፡፡ መልካም በሆኑት የአላህ ስሞች ዱዓእ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ፡- እጅግ አዛኝ የሆንከው አላህ ሆይ! እዘንልኝ፡፡ እጅግ በጣም መሐሪ የሆነከው አላህ ሆይ! ማረኝ፡፡


አንድን ዱዓእ ለብዙ ጊዜያት እየደጋገሙ ያድርጉ፡፡ አላህ በዱዓእ ላይ የሙጥኝ መባልን ሐያእ ያደርጋል፡፡ ዱዓእ ሲያደርጉ ልቦናዎን ወደ አንድ ቦታ ይሰብስቡና ወደአላህ ይቅረቡ፡፡


🔹🔹🔹🔸🔸🔸


📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ፣ "ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)" ይላሉ ነብዩ ﷺ


➡ ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen


⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪ ⚪

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ አቡ ሀይደር እየሱስን ተሳድበዋል። እፎይ ጥያቄ ስለጠየቀ ለምን ተንጫጫቹና ለመሰል ጥያቄዎች ወንድም ኢሳቅ በብቃት መልሷል አዳምጡት!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሰዎች በመንገድ ላይ እየዘፈኑና ሲሄዱ አንተ ግን...

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የምሰጠዉ ርዕስ አጣዉ! አዳምጡት ትደሰታላቹ።

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ለሀጅና ለዑምራ ከሚሄዱ አማኞች ከሚሰሩት ትልቅ ስህተቶች አንዱ መቃመ ኢብራሂምን የመተሻሸትና የመሳም ድርጊት ነዉ። ይህ ተግባር በዲን ያልታዘዘና የተወገዘ ነዉና ልንጠነቀቅ ይገባል። ዑምራም ሆነ ሀጅን በእዉቀት እንፈፅም!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሰዉ የሚድነዉ በምንድን ነዉ ተብላቹ ብትጠየቁ ይህንን መልሱ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የአሹራ ቀን ለምን ይጾማል?

በአቡ ሀይደር

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፤ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡

ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ኒዕማህን ደብቅ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

🌙 ከረመዳን ቀጥሎ በላጩ ፆም!

ከአቡ ሁረይራ (💚) ተይዞ፡ ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أفضلُ الصِّيامِ بعدَ رمضانَ شَهْرُ اللَّهِ المُحرَّمُ﴾

“ከረመዳን በመቀጠል በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ወር ፆም ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1123



ማስታወሻ፦ የሙሀረም ወር ፆም በኢትዮጵያ ካላንደር አቆጣጠር አርብ ሰኔ 27 ላይ ይሆናል። ከበፊቱ ወይም ከበስተኋላው ያለውን አንድ ቀን ጨምሮ መፆም መዘንጋት የለበትም።

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️Telegeram

📞 Whatsup

👤Facebook 

📸Instagram

💬X

🎥buharimuslimamharic?si=mVyabo_ffqR2LTWK">Youtube

🎵buhari.muslim.amh?_t=ZM-8xIqYuJ3u7E&_r=1">Tik tok

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

የኤሌትሪክን መኖር ያመንክበት ሎጂክ የአላህ መኖር ያሳምንሀል!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ሑጃጆችን መዘየር

🔅ከሐጅ የተመለሰን ሰው መዘየር የሚፈቀድና ከዲን ጋር የሚጋጭ ነገር ካልተቀላቀለበት የሚበረታታም ተግባር ጭምር ነው።
የግድ የሚታረድ ነገር ሳይያዝ አይኬድም መባል የለበትም።
🔅ዘመድ፣ ጓደኛ እና ጎረቤት አቅም ካላቸው ጉራ፣ ፉክክርና ብክነትን በማያስከትል መልኩ ከሐጅ የመጣን ሰው ደግሰው ቢቀበሉ ወይም ቢዘይሩ ችግር አይኖረውም።
🔅የአላህ መልዕክተኛ ﷺ "አላህ በሰጣችሁ ሃብት -ያለ ጉራና ብክነት- ብሉ፣ ጠጡ፣ ልበሱ፣ ሰደቃም አውጡ" ብለዋል።
                            📚ሱነን አንነሳኢይ: 2559

🔅ከሐጅ የተመለሰን ሰው ደግሶ መቀበል፤ እሱም የሚዘይሩትን ሰዎች ደግሶ መመገብ እንደሚችል (ይህን ማድረግ እንደሚወደድ) ቀደምት የፊቅህ ሊቃውንት ገልጸዋል።

🔅ከሐጅ የተመለሰን ሰው ሲያገኙና ሲዘይሩ "አላህ ሐጅህን ይቀበልህ/ሽ" ወዘተ የሚል ዱዓእ ማድረግ ይቻላል።

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል-መዓድ

🌐 /channel/ahmedadem

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ለእስራኤል ወዳጅ ክርስቲያኖች በሙሉ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ልጆችን የጠዋትና ማታ እንዲሁም ሌሎች ዚክሮችን ማስተማር ልክ እንደ መንፈሳዊ ክትባት ነው፤ ከማይታዩ አደጋዎች ሁሉ ይጠብቃቸዋል።

💫 @HidayaTerbiya

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

በዛሬዉ እለት ሆነ በቀሩት 3 ቀናት የኡዱሂያ እርድ የምትፈፅሙ ምእመናን በሙሉ!

لَن يَنَالَ اللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَاؤُهَا وَلَٰكِن يَنَالُهُ التَّقْوَىٰ مِنكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمْ لِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ ۗ وَبَشِّرِ الْمُحْسِنِينَ

«አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» [ሱረቱል ሀጅ: 37]

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ኢድና ጁምዐ ሲገጣጠም እንዴት ነዉ መስገድ ያለብን ለሚለዉ የተሰጠ መልስ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል!

አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐ «የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

ያስታውሱ ዛሬ ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን (የውሙ አት–ተርዊያ) ሑጃጆች የሐጅ ስራቸውን የሚጀምሩበት እለት ነው።

የነገው ዘጠነኛው ቀን የውሙ ዓረፋ ነው። ሑጃጆች በዓረፋ ምድር የሚቆሙበት ለነሱም ይሁን ለሌላው ሙስሊም ማህበረ–ሰብ እጅግ ልዩ የዒባዳ ቀን ነው።

በጾም፣ በዚክር በተለይ ተክቢራ እና ዱዓእ እንድንጠቀምበት ልንተዋወስ እና አንዳችን ሌለኛውን ሊያበረታታ ይገባል።
የነገውን ቀን ጾም በተመለከተ ከላይ በጠቀስነው ሀዲስ ላይ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያለፈውን እና የመጪውን አመት ወንጀል ያሰምራል ማለታቸው ይህን እለት በጉጉት እንድነጠብቀው ያደርጋል።

ከጾም ውጪ በዚህ ቀን ልዩ በሆነ መልኩ ልናደርጋቸው የሚወደዱ ነገሮችን በተመለከተ በተከታይ ጽሁፎች ኢንሻ አላህ ለመጠቆም እሞክራለሁ።

ወደ መልካም አመላካች እንደ ሰሪው ምንዳ አለው!!

ለሌሎችም መልእክቱን እናስተላልፍ

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
/channel/tahaahmed9

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

በስልክ ዳዕዋ ሊደረግልኝ ተደወለልኝ ግን...

ዛሬ በጠዋቱ በስልኬ ላይ አንድ ድምፁ አዛዉንት የሆነ ግለሰብ
ሰዉዬዉ:- ፍቃደኛ ከሆንክ ስለ መፀሀፍ ቅዱስ ተስፋ ሰጪ አንቀፅ ላነብልህ ነበር ፍቃደኛ ከሆንክ አለኝ።
እኔ:- ስለ መፀሀፍ ቅዱስ አልኩት?
ሰዉዬዉ:- አዎ ጌታዬ አለኝ።
እኔ:- ፍጡርን ጌታዬ ማለት አይከብድም አልኩት?
ሰዉዬዉ:- ከአክብሮት ነዉ እንጂ ከእየሱስ እኩል እያሰብኩህ አይደለም አለኝ።
እኔ:- ስህተትህ ከዚህ ይጀምራል አልኩት። በነገራችን ላይ ከየትኛዉ መፀሀፍ ቅዱስ ነዉ የምታነብልኝ አልኩት?
እሱ:- መፀሀፍ ቅዱስ አንድ ብቻ ነዉ አለኝ።
እኔ:- አይ ተሳስተሀል የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ፣ የፕሮቴስታንት አለ አንተ ከየትኛዉ ነህ አልኩት?
እሱ:- እኔ የማምነዉ በ66ቱ ነዉ አለኝ።
እኔ:- አየህ መፀሀፉ አንድ ብቻ አይደለም አልኩት።
እሱ:- ያልተበረዘዉ ያልተከለሰዉ 66ቱ አለኝ።
እኔ:- ከሱ መፀሀፍ ላይ ብዙ ስህተቶቹን ላሳይህ እችላለዉ አልኩት።
እሱ:- እኔ ለመከራከር አልነበረም የደወልኩት አለኝ።
እኔ:- ፋራ አገኘዉ ብለህ ዝም ብለህ ልተሰብከኝ ነበር አልኩት? ለምትናገረዉና ለምታምንበት መፀሀፍ ማወቅ ነበረብህ።
እሱ:- አይ በቃ መልካም ጊዜ ይሁንልህ ብሎ ስልኩን ሊዘገዉ ሲል
እኔ:- ጋሼ ይልቁኑ እኔ የሰዎች ቃል የሌለበት፣ መሰረዝ፣ መደለዝ ወደ ሌለበት ቁርአን እጠራዎታለዉ። አላህ ቀጥተኛዉን መንገድ ይምራቹ ብዬ ሊሰብኩኝ በደወሉ አዛዉንት እኔ በዳእዋ መለስኳቸዉ እላቹሀለዉ።

ለማንኛዉም ከመሠረታዊ የአቂዳ ትምህርት በተጨማሪ የንፅፅር ትምህርቶችን እንማር። እኛ የሀቅ እምነት ይዘን የባጢል ሰዎች እኛን ሊሰብኩን እድል መስጠት የለብንም!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…

ኢስላማዊ እውነታ

ልጅ ካለህ ካለሽ ይሄ ምክር ወሳኝ ነዉ!

/channel/islamictrueth

Читать полностью…
Subscribe to a channel