ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
ኢስላምን በመሳደብ በቲክቶክ ታዋቂ የሆነ አንድ ክርስቲያን ኢስላም ወንድ ልጅን ቁጭ ብሎ እንዲሸና ያዛል ብሎ ተሳልቆ ነበር። ይህንን ጥናት ሲሰማ ምን ይል ይሆን?
/channel/islamictrueth
በኢስላም የገ*ደ*ለ ይ*ገ*ደ*ል የሚለዉ ህግ ጥቅሙ ምንድን ነዉ? ሌላ አማራጭ የለዉም?
የነዚህ ጥያቄ መልስ ከዚህ ቪዲዩ ታገኛላቹ!
/channel/islamictrueth
"ሻእባንን ለዑስማን ኢብኑ ዓፋን መስጂድ" በሚል ርዕስ ለአንድ ወር የሚቆይ የኡስማን ኢብኑ አፋን መስጅድ ግንባታ ለማስቀጠል ያለመ ፕሮግራም ይፋ ሆነ!
በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ በተለምዶ ሸህ ደሊል መስጂድ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የኡስማን ኢብኑ አፋን መስጅድ ግንባታ ለማስቀጠል ያለመ "ሻእባንን ለዑስማን ኢብኑ ዓፋን መስጂድ" በሚል ርዕስ ለአንድ ወር የሚቆይ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ይፋ መሆኑ ተገልጿል።
በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለጸው ማህበረሰቡ እንደ አቅሙ የሚሳተፍበት የ100,000፣ 50,000፣ የ25,000፣ 10,000 እና 5,000 የቦንድ ሰርተፊኬት ግዢ ይፋ መሆኑ ተገልጿል።
መርኅ ግብሩ ይፋ በሆነበት በዛሬው ዕለት በርካቶች ለራሳቸው እና ይህ ኸይር ስራ አያምልጣቸው ለሚሏቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ከ 5 ካርድ ጀምሮ እስከ 22 ካርድ ለማድረስ ወስዶዋል ተብሏል።
በዚህ ለአንድ ወር በሚቆየው ንቅናቄ የመስጂዱ አስተዳደር 11 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ እንዳቀደ ይፋ አድርጓል ተብሏል።
መላው ሙስሊም ማህበረሰብ በዚህ ኸይር ስራ ላይ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
የኡስማን ኢብኑ አፋን (ሼይኽ ደሊል ) መስጂድ የግንባታ ሂሳብ ቁጥሮች
አቢሲኒያ ባንክ 80756569
ሂጅራ ባንክ 1004952340001
ዘምዘም 0037167820101
ንግድ ባንክ 1000441008833
ካሚል ነሰሩ ና ጀማል ና ሚፍታ ኢብራሂም
ለበለጠ መረጃ
0911472317 ወይም
0911457872
አክሱም ላይ መስጅድ፣ የቀብር ቦታ የምንከለክለዉ በታሪክ የተቀመጠና የተደነገገ ስለሆነ ነዉ። ነገር ግን ጥላቻ አሊያም እምነት እየተገፋን ሳይሆን የክርስትና ማእከል ስለሆነቸዉ ላሉት ቄስ ወንድም ኢስሀቅ እሸቱ የሰጠዉን ቆንጆ መልስ ተጋበዙ።
ሰዉየዉ ሌላም ብዙ የዘባረቀ ሲሆን ወንድም ኢስሀቅ የመለሰበትን ሙሉ ቪዲዩ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ። ቻናሉን ሰብስክራይብ፣ ላይክ፣ ሼር ማድረጉም አትርሱ!
ኢስሃቅ እሸቱ [ ተክቢር ሚዲያ ]
➽ https://youtu.be/Rzf5wDBXisY
በኢስላም እግዛብሄር የሚለዉን ስያሜ መጠቀም አይፈቀድም!
/channel/islamictrueth
ያለ ሀይማኖት መዳን አይቻልም! ሀይማኖት አያስፈልግም ከሚሉ ወገኖች የተደረገ ዉይይት ቁ.2
/channel/islamictrueth
አላህን ከፍጡራኑ ጋር ማመሳሰል!
አጠር ያለ ማብራሪያ ይነበብ!
መቼም በፈጣሪና በፍጡር መካከል መመሳሰልና አንድነት ሊኖር እንደማይችል ማንኛውም ንፁህ አዕምሮ ያረጋግጣል።
ለዚህ ማስረጃነት ከሚጠቀሱት አንቀፆች መካከል፦
[ ليس كمثله شئ وهو السميع البصير ﴾ [الشورى: 11]
☞ «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚዉና ተመልካቹ ነው። [አሽ-ሹራ 11] አሚሙና
ولم يكن له كفوا أحد ، الاخلاص: 4]
☞ «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም። [አል-ኢኽላስ 4]
(هل تعلم له سميا ) [مريم: 65]
☞ «ለርሱ በስሙ ወደር ታውቃለህን?» [መርየም 65]
➢ ታላቁ ሰሓቢይ ኢብኑ ዓብ-ባስ (ረ.ዐ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ:-
« هل تعلم للرب مثلا أو شبيها ؟!»
“ለጌታ አምሳያ ወይም ቢጤን ታውቃለህን [ተፍሲሩ'ጥ-ጦበሪ” (18/226)]
ስለዚህ የጌታ መጠሪያዎችና መገለጫዎች አንዳንዴ ከፍጡራን ስያሜዎችና ባህሪያት ጋር በቃላት ደረጃ ቢገጥሙ እንኳ በይዘት ግን ፍፁም አይመሳሰሉም፤ ጌታ በጌታነቱ ከፍጡራን መለያዎች የጠራና በስሞቹም ይሁን በባህሪያቱ ተጋሪ የሌለው ብቸኛ ነውና!
ታዲያ “ማመሳሰል” የሚባለው ባህሪያቱን ከፍጡራን ጋር በሁኔታ ማዛመድ እንጂ አላህና መልዕክተኛው ያፀደቁትን መቀበል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።
➢ አል-ኢማም አት-ቲርሚዚይ (279 ዓ.ሂ) እንደሚያስተላልፉት ታዋቂው አል-ኢማም ኢስሓሃቅ ኢብኑ ራሀወይህ እንዲህ ብለዋል፦
«إنما يكون التشبيه إذا قال: يد كيد أو مثل يد، أو سمع كسمع أو مثل شمع. فإذا قال: سمع كسمع أو مثل شمع فهذا التشبيه، وأما إذا قال- كما قال الله تعالى-: يد، وسمع، وبصر، ولا يقول: كيف، ولا يقول: مثل شمع ولا تسمع، فهذا لا يكون تشبيها.
«ማመሳሰል የሚሆነው “እንዲህ ያልለ ወይም ይሄ አይነት እጅ”፣ “እንዲህ ያልለ ወይም ይሄ አይነት መስማት” ሲባል ነው፤ ነገር ግን አላህ እንደተናገረው “እጅ፣ መስማት፣ ማየት” ብሎ “እንዴት” ካላለ፣ “እንዲህ አይነት፣ እንዲያ ያለ መስማት..” ካላለ ማመሳሰል አይሆንም!» [ሱነኑ'ት-ቲርሚዚይ”፤ ኪታቡዝ-ዘካህ፤ ከሐዲሥ ቁጥር (662) ቀጥሎ]
አዎን! የቁርኣን ገለፃን የተከተለን ሰው ማውገዝ በተዘዋዋሪ ቁርኣንን ራሱን ማውገዝ እንደሆነ ማስታወስ ያሻል!
የአማኞች ጋሻ ከሚለው ከሼይኽ ኤልያስ አህመድ መፀሀፍ የተወሰደ!
/channel/islamictrueth
ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ! እና ከዚህ አደጋ ለመዳን መጠቀም ያለባቹ መፍትሄዎች!
1) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት
መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!!
[ቡኻሪና ሙስሊም]
2) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]
3) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4) ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ
እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው
ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን
ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ
እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡
ወንድም እህቶች ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጉ፡፡ ወቅቱን ጠብቃቹ እንድትሰግድ የሚያግዛቹሁን ብልሃትም ተጠቀሙ!
1) በጊዜ ተኛ! የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) ቡኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
2) ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር
ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ
የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ
ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
3) ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ
ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ
ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም
እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ
የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
4) ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት
ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ
ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
5) በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ!
6) በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር
ካለህም እሰየው!
ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች በማስተላለፍ ከዚህ አደጋ ይታደጎቸው!
#መሀመድ አህመድ
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በፌስቡክ ለመከታተል
Www.fb.com/islamictrueth
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
አላህ ለከሀዲያን ልባቸዉን ከዘጋባቸዉ በኃላ ለምን ይቀጣቸዋል?
አራት ደቂቃ ብቻ ከአጥጋቢ መልስ ጋር!
/channel/islamictrueth
ሴት ልጅ የወር አበባና ምጥ የምታየዉ ከሀዋ ለወረሰችዉ ሀጢያት ነዉ የሚለዉ አባባል በኢስላም አይሰራም!
/channel/islamictrueth
በአላህ መኖር የማያምን አስተማሪ በተማሪዉ ተዋረደ!
/channel/islamictrueth
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أتاكم شهرُ رمضانَ شهرٌ مباركٌ فرض اللهُ عليكم صيامَه، تفتحُ أبوابُ السماءِ، وتغلقُ فيه أبوابُ الجحيمِ، وتغلُّ فيه مردةُ الشياطينِ، للهِ فيه ليلةٌ خيرٌ من ألفِ شهرٍ من حرمَ خيرَها فقد حُرِم.﴾
“የረመዳን ወር መጣላችሁ፤ የተባረከው ወር። አላህ በናንተ ላይ እንድትፆሙ ግዴታ ያደረገባችሁ፤ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት፣ ሸይጣኖች የሚታሰሩበት። በዚህ ወር ውስጥ ከአንድ ሺህ ሌሊት ብልጫ ያላት ሌሊት አለች፤ የሷን መልካም ነገር የተነፈገ በርግጥም መልካም ከሆነ ነገር ተንፍጓል።” [📚 ነሳዒ ዘግበውታል: 4/129]
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
ረመዳን የሚገርም ማሰልጠኛ ማእከል ነዉ!
#ረመዳን
#Remedan
/channel/islamictrueth
ረመዳን የመጀመሪያ ቀን መሆኑን ያበሰረ(የተናገረ) አላህ ከጀሀነም እሳት ነፃ ይለዋል ብለዉ ረሱል(ﷺ) ተናግረዋል እየተባለ ብዙ ሰዉ ሼር አድርጓታል። ይህንን በተመለከተ ኡስታዝ አቡ ሀይደር ከአመታት በፊት የሰጠዉን መልእክት አዳምጡት ሼርም አድርጉት።
/channel/islamictrueth
የአክሱም ትምህርት ቤቶች ህግ ማዉጣት እየቻለ ለምን ተፅኖ ይፈጠርበታል?
ሰዉየዉ ሌላም ብዙ የዘባረቀ ሲሆን ወንድም ኢስሀቅ የመለሰበትን ሙሉ ቪዲዩ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ። ቻናሉን ሰብስክራይብ፣ ላይክ፣ ሼር ማድረግም አትርሱ!
ኢስሃቅ እሸቱ [ ተክቢር ሚዲያ ]
➽ https://youtu.be/Rzf5wDBXisY
ረሱል(ﷺ) ወህይ ማየት የጀመሩት በጅብሪል(ዐ.ሰ) አማካኝነት ኢቅራእ የሚለዉ ቃል የወረደ ቀን አይደለም!
/channel/islamictrueth
ቁርአን ለመንፈሳዊና ለአካላዊ በሽታ መድሀኒትና መከለከያ ለመሆኑ በሶስት ምክንያቶች እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን!
/channel/islamictrueth
ማጥመምና ልብን መዝጋት ከአላህ ዘንድ እንደ ቅጣት የሚመጣዉ መጀመሪያ ከኛ ዘንድ እንቢተኝነት ሲኖር ነዉ!
/channel/islamictrueth
ሰይጣን ወደ ሰዉ ልጅ ገብቶ ከአላህ እራሱን እንዲቆርጥ ከሚጠቀምባቸዉ ዘዴና መፍትሄ!
/channel/islamictrueth
ይጠቅሙኛል፣ ይጎዱኛል የሚሏቸዉ አካላቶች እራሳቸዉ ፈላጊዎች ናቸዉ!
/channel/islamictrueth
አላህ ወደኔ ስትመጡ አንድ ነገር ይዛቹ ኑ ብሏል!
/channel/islamictrueth
የልጅ እናት የሆንሽ እህቴ ይሄ ችግር አንቺ ላይ የለም?
/channel/islamictrueth
መፀሀፍ ቅዱስ ከቁርአን ቀድሞ ስለወረደ የመፀሀፍ ቅዱስ እውነተኝነት ያሳያል?
የአምስት ደቂቃ መልስ ከአቡ ሀይደር
/channel/islamictrueth