ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!
የዑስማን ኢብኑ አፋን(ሸይኽ ደሊል) መስጅድና ደረሳ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ
የአካዉንት ስም:- ካሚል ነስሩ፣ ጀማል ሁሴንና ሚፍታ ኢብራሂም
ሂጅራ ባንክ 1004952340001
ዘምዘም ባንክ 0037167820101
ንግድ ባንክ 1000441008833
አቢሲኒያ ባንክ 80756569
🔠🔠🔠 4️⃣4️⃣4️⃣
ከረመዳን በፊት ከናይልሳት በተጨማሪ በኢትዮሳት ስርጭት ለመጀመር እንችል ዘንድ የሁላችሁንም ትብብር እንሻለን።
በ 444 የንግድ ባንክ አካውንታችን የቻሉትን ድጋፍ በማድረግ አጋር ይሁኑ!
🤍 CBE የሂሳብ ቁጥር 444 የአካውንቱ ባለቤት ibnu Masoud islamic Center
@Nesihatv
ጣፋጭ አቀራር #25
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
/channel/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
ዉዷ እህቴ ፈትዋዉን እራስሽ መልሺ!
አላህ በቁርአኑ ያዘዘዉ የሂጃብ ድንጋጌና አላማዉ ማለትም [... ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (ሱረቱል አህዛብ 59)] የሚለዉ መመርያ አሁን አንቺ ያደረግሽዉ ፀጉርሽን ድብን አርገሽ ሸፍነሽ ሌላዉን የሰዉነት አካል እንደፈለክሽ ልቅ ማድረግሽ ትእዛዙን መፈፀምሽና ጥበቃዉን የምታገኚ ይመስልሻል?
ለምን ነብዩ ሙሀመድ(ﷺ) ከነብሳቹ፣ ከልጃቹና ከቤተሰባቹ በላይ ትወዳላቹ ብላ ለጠየቀች አንዲት ወገን አጥጋቢ መልስ!
Читать полностью…ትላንት ከሌለንበት ዓለም ምንም ሳይቸግረውና ሳይከብደው፡ ከፈሳሽ ውሀ ከ(sperm cell) በሶስት ጨለማዎች ውስጥ (በሆድ፣ በማህጸንና በእንግዴ ልጅ) የፈጠረንና ያስገኘን አላህ፡ ዛሬ ካለንበት መቃብር ውስጥ ዳግም ነፍስን በመዝራት ለመቀስቀስ ምንም ሊከብደው እንደማይችል በመግለጽ ያስረዳል፡፡ የሌለን ነገር በማስገኘት መፍጠር የቻለ አላህ፡ እንዴት ያለን ነገር ነፍስ በመዝራት መመለስ ያቅተዋል? እያለን ነው፡፡ ቀጣዮቹን ቁርኣናዊ አንቀጾች እንመልከታቸው፡-
" وَقَالُوا أَإِذَا كُنَّا عِظَامًا وَرُفَاتًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ خَلْقًا جَدِيدًا * قُلْ كُونُوا حِجَارَةً أَوْ حَدِيدًا * أَوْ خَلْقًا مِمَّا يَكْبُرُ فِي صُدُورِكُمْ فَسَيَقُولُونَ مَنْ يُعِيدُنَا قُلِ الَّذِي فَطَرَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ فَسَيُنْغِضُونَ إِلَيْكَ رُءُوسَهُمْ وَيَقُولُونَ مَتَى هُوَ قُلْ عَسَى أَنْ يَكُونَ قَرِيبًا * يَوْمَ يَدْعُوكُمْ فَتَسْتَجِيبُونَ بِحَمْدِهِ وَتَظُنُّونَ إِنْ لَبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا " سورة الإسراء 52-49
"አሉም፦ እንዴት አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተንቀሳቃሾች ነን? በላቸው፦ደንጊያዎችን ወይም ብረትን ሁኑ፤ ወይም በልቦቻችሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረት (ሁኑ መቀስቀሳችሁ አይቀርም)፡፡ የሚመልሰንም ማነው? ይላሉ፤ ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው በላቸው፤ ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ እርሱም መቼ ነው ይላሉ፤ (እርሱ) ቅርብ ሊሆነን ይቻላል በላቸው። (እርሱም) የሚጠራችሁና (አላህን) አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት ጥቂትንም (ቀኖች) እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው (በላቸው)።" (ሱረቱል ኢስራእ 49-52)፡፡
ሌሎች እንደሚያስተምሩት ኢስላም ከሌሎች እምነት በኃላ የመጣ ነዉ? ነብዩ ሙሀመድ የእምነቱ መስራች ነዉ? አጠር ብላ ብዙ መልስ ያላት ተመልከቱት!
Читать полностью…በፕሮቴስታንቱ (የጴንጤው) ዓለም እየደረሰ ያለ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራና የሥነ–ምግባር ዝቅጠት ያጋለጠ ቃለመጠየቅ
ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic
እራሳቸውን "ሐዋርያ" እና "ነብይ" እያሉ የሚጠሩ
የፕሮቴስታንቱ ዓለም ጉዶች በራሳቸው ስሜት እየተነዱ ከራሳቸው፣ከኪሳቸው አፍልቀውና አመንጭተው ጌታ ነገረን መልዕክት መጣልን እንዲህ ይሆንልሃል እንዲያ ይደረግልሃል ጠላትህ ተሰበረ፣ ቀንበር ተሰበረ፣ ተወጋ , ወጋሁት ወዘተ በማለት የዋሁንና ሞኙን ሕዝብ የህልም ዓለም ተስፋ በመስጠት ቁስሉን በመነካካትና ጎዶሎውን እየነገሩት ችግሩንና ብሶቱን በአዳራሽ በማይክራፎን ጮክ አድርገው እየነገሩት ስስ አንጀቱን እየሸነቆጡ ብሶቱን እያወሩለት እያስለቀሱት ሕዝቡን እያጭበረበሩና እያታለሉ እንዳለ የአደባባይ ምስጢር ነው ።
እነሆ ከዛ ሁሉ ቅጥፈት በኃላ የልባቸው ደርሶ የአማኙን ትዳር አፍርሰው ኪሱን አራቁተው የሺዎችን ነፍሳት ወደ ገደል ነድተው ሲያበቁ እንዲሁ እንደዋዛ በሚዲያ ብቅ ብለው በኩራት ተለጥጠውና ተኮፍሰው ከካሜራ ፊት ቁጭ ብለው ተሳስተን ነበር ዝም ብለን ነበር ስናወራ የነበረው ስብከቱም ስብከት ፈውሱም ፈውስ አልነበረም የውሸት ፈጠራ ነበር ብለው ሲያወሩ ከመስማት የበለጠ ምን ኪሳራ አለ?
ይህ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቴስታንቱ ዓለም ምዕመን የሞራል ዝቅጠትና የሞራል ኪሳራ ነው!
በጣም የሚገርመው ነገር ዛሬም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የራሳቸውን ቅዠት የሚቃዡና የፈጠራ ወሬ የሚያወሩ እንደ ሐዋርያ ዳንኤል አይነት መኖራቸው ነው።
ግርምቴን ደግሞ እጥፍ የሚያደርገው ደግሞ ዛሬም ድረስ የእነዚህ "ሐሰተኛ ነብይና ሐዋርያ" ነን ባዮች አድናቂና ተከታዮች አለመንቃታቸውና ዛሬም በፅኑ እንቅልፍ ውስጥ መሆናቸው ነው ።
እናንተ የሐሰተኛ ነብያትና ሐዋርያት መጫወቻ የሆናችሁ ፕሮቴስታንቶች ሆይ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁት መቼ ይሆን? እንዳታስተውሉስ አዚሙን ያደረገባችሁ ማን ይሁን?
ኑ ወደ ኢስላም ሰላማችሁን ታገኛላችሁና።
ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic https://www.facebook.com/profile.php?id=100064506050455&mibextid=ZbWKwL ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic
ሙስሊሞች ነብዩ ሙሀመድን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያመልካሉ ይባላል ለዚህ ምላሽ ብትሰጥ?
Читать полностью…አንባቢን ላለማድከም እንጂ በጉዳዩ ላይ ብዙ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ታዲያ የመጽሐፋቸውን መግቢያውንና መውጫውን በቅጡ ያልተረዱ ሰዎች፡ ከምን ተነስተው ነው ይህ አባባል የመድረክ ላይ ሙቀትና የጋለ ስሜት እንጂ መረጃ አልባ ነው ያሉት? ለነገሩ መሃይም አፉ እንደ መቀመጫው ነው፡ ንግግሩ ደግሞ እንደ ቆ*ሻ*ሻ*ው ነው አይደል የሚባለው?
5ኛ. በመጨረሻም ለነዚህ ልባቸው በጥ*ላ*ቻ ለታወረ ወገኖች የምንላቸው ነገር ቢኖር፡- ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንኳን ወላጆቻችን ዓለሙ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ቢቀርብ አላህ ዘንድ ካላቸው ደረጃ፡ አንድ እጁንም አይሞላም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ምድር ውበቷ፡ እሷንና በላይዋ ላይ ያሉትን የፈጠረውን አንድ አምላክ ስናመልክባት ነው፡፡ ይህ ትምሕርት ደግሞ እሳቸው ነቢይ ሆነው ባይላኩ ኖሮ መች ይገኝ ነበር?፡፡ እኛም በክህደት ጨለማ ተውጠን፡ በአምላክ ፈንታ ሰውን አምልከን፡ የክህደት ጉድጓድ ውስጥ በወደቅን ነበር፡፡ ዓለሙም በጨለመ ነበር፡፡ አልሐምዱ ሊላህ እሳቸውን ነቢይ አድርጎ ለላከልን አላህ፡፡
"ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰዉ፣ ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለዉም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎች ነዉ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 85)፡፡
ኢስላማዊ ዳእዋ በቴሌ ግራም ለመከታታል ሊንኩን ይጫኑት!
/channel/islamictrueth
ለምን ፊዳከ አቢ ወኡምሚ ያረሱለላህ ትላላቹ? ነብይን መዉደድ እንጂ ማምለክ እንዴት ይቻላል? ተብሎ የዛሬ 8 አመት የተጠየቀ ጥያቄ ሰሞኑን ድጋሚ ተጠይቋል።
እንደተለመደዉ የኡስታዝ አቡ ሀይደር መልስ አቅርበናል!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ይህን ጽሁፍ እንዳዘጋጅ ሰበብ የሆንከኝ ወንድሜ አላህ ኸይር ጀዛህን ይክፈልህ፡፡ በ inbox በኩል፡ አንድ መሃይምነትና ጭፍን ጥላቻ የተቀላቀለበትን የካፊሮችን ጽሁፍ ለጥፎልኝ ምላሽ እንድሰጥበት ጠይቆኝ ነበር፡፡
ጽሁፉ ያተኮረው በነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ነው፡፡ ጭብጡም፡- ‹‹ለምን ለሳቸው ‹ፊዳከ አቢ ወኡሚ› ይባላሉ? ለምን በየቀኑ ‹ባለውለታዬ ሐቢብ ተምሳሌቴ፣ ስላንቱ ይሰዉ እናቴና አባቴ› በማለት ያስነብቡናል? ደግሞም ጉዳዩ መረጃ የሌለው የስሜት መገንፈልና የመድረክ ሞቅታ የወለደው ነው፡፡ ፊዳ ማለት መስዋእት ነውና፡ መስዋእት የሚገባው ደግሞ ለሕያው አምላክ ነው፡፡ ለእሳቸው መስዋእት ማቅረብ ደግሞ፡ እሳቸውን በአምላክ ቦታ ማስቀመጥ ነው፡፡ ለዚህ ነው ነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አምላክ አድርጋችሁ ይዛችኋል የምንለው፡፡››
ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል፡፡ የኛም መልስ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
1ኛ. በጽሁፉ ላይ እጅግ የከፋ ጥልቅ ጥ*ላ*ቻና ጭ*ፍ*ን መሃይምነት በጉልህ ይታያል፡፡ በተለይ የአካውንቱን ባለቤት ሙሉ ጽሁፍ ላነበበ ሰው አይደለም ለሙስሊም፡ ገለልተኛ ለሆነ ሰውና በንጹህ አእምሮው ለሚመዝን ሰው ለመስማት የሚሰቀጥጡ ስድቦችን ያገኛል፡፡ ይህም ችግሩ ከጸሀፊው ሳይሆን፡ ከተኮተኮተበት የትምህርት መሰረት ነው፡፡ ችግሩ ዛፉ ላይ ነው፡፡ አጠጥተው ያሳደጉት ውሀ የተመረዘ ነበር፡፡ ታዲያ ከፍሬው ምን መልካም ነገር እንጠብቃለን፡፡ ይህ አይነትና መሰል ስድቦች ደግሞ ለነሱ (ለካ*ፊ*ሮ*ች) አፍ መፍቻ ቋንቋ እስኪመስል ድረስ ተዋህዷቸዋል፡፡ ምን ያድርጉ ሁሌም የሚሰሙት ስብከት ‹‹የምላስ ወለምታ፣ የሐሜት አስከፊነት፣ ነገር ማዋሰድና አደጋው፣ የውሸት አደጋ›› እና መሰል ነገራትን ሳይሆን፡ ገደል ውስጥ የሚከቱ ትምህርቶችን ነው፡፡ ታዲያ የሚገርመን ባይሳደቡ ነው፡፡ እጅጉኑ የሚያስቀውና የሚያስገርመው፡ በዚያው ማንነታቸው ተመልሰው መጥተው ‹‹ክርስትና ፍቅር›› ናት! ይሉናል፡፡ እውነትም ፍቅር! ይኸው በተግባር አየነው እኮ! ለካ አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ብቻ አይደለም፡ ልብም ጭምር ይታያል፡፡ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል መጠቀሱ ተገቢ ነው፡-
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 118)፡፡
2ኛ. ወደ ነጥቡ ስንመለስ፡- ፊዳእ ማለት ቤዛ ማለት ነው፡፡ ይህም አንድን ነገር ለማስቀረትና ለማስተው በምትኩ የሚከፈል ክፍያ ይባላል፡፡ በዕዳ የተያዘ ሙስሊም ወንድምህን ከክስና ከእስር ነጻ ለማውጣት ለባለ መብቱ የገንዘቡን መጠን በመስጠት ወንድምህን ነጻ ብታወጣው ፊዳእ ሆንከው (ተበዤኸው) ይባላል፡፡ ይህንን ሀሳብ የሚገልጹ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችን በመጠኑ እንመልከት፡-
" وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ " سورة الصافات 107
"በታላቅ ዕርድም (መስዋእት) ተቤዠነው" (ሱረቱ-ሷፍፋት 107)፡፡
ጌታ አላህ ለነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐለይሂ-ሰላም) ልጁን ኢስማዒልን (ዐለይሂ-ሰላም) እንዲያርደው በህልሙ በማሳየት ትእዛዝን ይሰጠዋል፡፡ ኢብራሂምም የጌታውን ትእዛዝ ለልጁ ባሳወቀው ጊዜ፡ ኢስማዒልም ለአላህ ትእዛዝ ፈቃደኛ ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ አባት የመጀመሪያ ልጁን ለማረድ፡ ልጅም ለመታረድ በዝግጅት ላይ ሳሉ፡ ‹ኢብራሂም ሆይ!› የሚልን ጥሪ ይሰማሉ፡፡ ኢብራሂምም ህልሙንም በተግባር በማረጋገጡ፡ ለጌታውም ትእዛዝ እጅ በመስጠቱ፡ ፈተናውን ማለፉ ይነገረውና ልጁን እንዳያርድ በመከልከል በምትኩ እጅግ የደለበ የበግ ሙክት ቤዛ ሆኖ ይሰጠዋል፡፡ በተጨማሪም በሚስቱ በሳረት በኩል ኢስሐቅንም እንደሚወልድ ብስራት ይደርሰዋል፡፡(ሱረቱ-ሷፍፋት 101-113)፡፡
አሁን የሆነው ነገር፡ በኢስማዒል ምትክ በጉ ቤዛ ሆነ፡ ታረደ ነው እንጂ፡ አላህ ለኢብራሂም መስዋእትን አቀረበ እንላለን እንዴ? አላህ እንታዘዘው ዘንድ መስዋእትን የምናቀርብለት አምላክ እንጂ፡ እራሱ መስዋእት የሚያቀርብ አይደለም፡፡
" يُبَصَّرُونَهُمْ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ " سورة المعارج 11
"ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል አመጠኛው ከዚያ ቀን ስቃይ፣ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል።" (ሱረቱል መዓሪጅ 11)፡፡
በዕለተ ቂያማህ በፍርዱ ቀን፡ አመጠኛ (ከሀዲ) የሆነ ሰው፡ ቤተሰቦቹ በሱ ቦታ ቤዛ ሁነው፡ እነሱ የሱን ኃጢአትና ቅጣት ተሸክመው ቢቀጡና፡ እሱ ነፍሱን ቢያድን እንደሚመኝ ጌታ አላህ ይነግረናል፡፡ ያ ማለት ግን ሰውየው ቤተሰቡን መስዋእት አድርጎ ያቀርባል ማለት አይደለም፡፡ በሁለቱም ቦታዎች የገባው የዐረብኛ ቃል ግን ‹ፊዳእ› መሆኑን ልብ በሉ፡፡
ታዲያ አንድ ሙስሊም ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‹‹ፊዳከ አቢ ወኡምሚ›› (አባቴም እናቴም ለእርስዎ ይሰዉሎት) ቢል፡ ትርጉሙ ምንድነው ካሉ፡- የእርሶን ክፋት አያሳየኝ፣ እንዲሁም አያሰማኝ፡፡ የእርሶን መጥፎ ነገር ከምሰማ በምትኩ እናቴና አባቴ ለእርስዎ ቤዛ ይሁንልዎ ማለት ነው፡፡ እንግዲያውስ ይህ ለሳቸው ያለን ፍቅር፡ ያቃጠላቸው ካ*ፊ*ሮ*ች መልክቱን ሳያውቁና በአግባቡ ጠይቀውም ሳይረዱ ይህ ለእሳቸው መስዋእት ማቅረብ ነው! ይሉናል፡፡ በክርስትና አስተሳሰብ ተመልክታችሁት ከሆነ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ እውነታውና እንደ ኢስላም ከሆነ ግን ስህተት ነው፡፡ የፊትን ትክክለኛ ገጽታ ለማወቅ በተስተካከለ መስታወት እንጂ በተሰነጠቀና በቆሸሸ መስታወት መመልከቱ አግባብ አይደለም፡፡ ውጤቱ ጥሩ ስለማይሆን፡፡
3ኛ. እኛ ነቢዩ ሙሐመድንም ሆነ ዒሳን (ዐለይሂማ-ሰላም) አናመልክም፡፡ ሁለቱም የአላህ ፍጥረቶችና ባሪያዎች ስለሆኑ አምልኮ አይገባቸውም፡፡ እንዲሁም መላእክትን አናመልክም፡፡ በስማቸው ቀናትን መድበን፡ ጅብሪል ድረስልኝ፣ ሚካኢል እርዳኝ፣ እገሌ ተከተለኝ፣ እንትና ጥበቃህ አይለየኝ የመሳሰሉትን ሁሉ አንጠቀምም፡፡ ጥበቃውንና እርዳታውን፣ መከተሉንና ማገዙን ለመላእክት፣ ለጻድቃን፣ ለሰማእታትና ለቅዱሳን ከሰጠናቸው፡ ታዲያ አላህ ምን ቀረው? በጣም የሚገርመው በዚህ አይነት የተሳሳተ አምልኮ ውስጥ የተዘፈቀ ሰው፡ ተመልሶ ሙስሊሙን ሌላ ታመልካላችሁ ማለቱ ነው፡፡ ሰው እራሱን በከንቱ አምልኮ ተብትቦ፡ ከተተበተበበት ገመድ ሳይላቀቅ፡ ሌላውን በሌለበት ጥፋት መክሰስ ምን የሚሉት ድፍረት ነው?
ለኡስታዝ ሙሀመድ ከድር የቀረበ ከባድ ጥያቄና መልሱ... በጓዳና የዳእዋ ስራ ላይ የገጠሞት ትልቁ ፈተና ምንድን ነዉ?
Читать полностью…★ ተሻጋሪ ሀሳብ
ጉዳዩ ከተጀመረ አይቀር…‼
===================
(ለምን ይህን ቁም ነገር ተረባርበን አንሠራም?)
||
✍ ኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር ሰሞኑን ዓለም ገና አካባቢ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ ባደረገው የንፅፅር ዳዕዋው ቪድዮ ላይ አስተውላችሁ ከሆነ ከጀርባው ሞንታሪቦ የተጫነባት አንድት ያሪስ የቤት መኪና ትታያለች። (ምናልባት ቪድዮውን ያላያችሁ ካላችሁ፦ /channel/MuradTadesse/33650)
ይህቺ መኪና የኪራይ መኪና ነበረች። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወንድሞቻችን ለኡስታዙ የዳዕዋ ሥራ ትሆነው ዘንድ ተከራይተውለት ነው። ቀስ በቀስ ያከራየውም ወንድም ሙስሊም ስለነበር ኪራይዋን ቀነሰለት። ይህቺን መኪና ሌሎችም ወንድምና እህቶች ተረባርበው ለግሉ ለማድረግና ባለቤቷም ከመደበኛ መሸጫ ዋጋዋ ቀንሶ ቢሸጥለትም ዋጋውን ግን ጨርሶ መክፈል አልተቻለም።
አስቡት! በብዙዎቻችን ላይ ግደታ የተደረገውን የኢስላም ዳዕዋ ኃላፊነት ጫንቃው ላይ ተሸክሞ ሰበብ እያደረሰ ላለ ሰው ይህ ኡማ ሚሊዮን ባለሃብቶች እያሉት ይህቺን እንኳ መኪና እንኳ ለእንዲህ አይነት ሰው የግሉ ማድረግ አልቻለም። በርግጥ ብዙዎቻችሁ ይህን ስለማታውቁ እንጂ ሐቂቃ ይሄን የሰማ ባለሃብት ካሉት በርካታ መኪናዎች መካከል አንዱን እንደሚሰጠው አስባለሁ፤ ኢንሻ አላህ።
እንደዛ የሚያደርግ ጀግና ካለ ያሳውቀኝ። ከሌለም እኛው ተረባርበን በአላህ ፈቃድ ተጋግዘን መግዛት እንችላለን።
የሚገርማችሁ ለዚህ የዳዕዋ ሥራው ይሆነው ዘንድ አንድት ኸይር ፈላጊ እህታችን ትልቅ ሞንታሪቦ ገዝታለት ነበር። ግን ያኛውን ሞንታሪቦ ይህቺኛዋን መኪና መሸከም ስለማትችል ቤት ውስጥ ተቀምጧል። እኛ ግን አይደለም ትልቁን ሞንታሪቦ መሸከም የሚችለውን ይህቺንም አሟልተን ገዝተን የግሉ ማድረግ አልቻልንም።
ባለፈ የሆነ የተጀመረ ነገር ነበር። ግን ግብ ሳይመታ ተቋረጠ። በአሁኑ ግን በአላህ ፈቃድ የተሻለ ነገር ገዝተን የዳዕዋ ሥራውን ማገዝ አለብን።
አፋችን ዳዕዋ ማድረግ ባይችል እንኳ በገንዘባችን ዳዕዋ በማድረግ በዳዕዋ ሥራው ላይ አሻራችንን እናሳርፍ።
የመንገድ ላይና የገበያ ላይ ዳዕዋ የነቢያት መሠረታዊ ጥሪ ነው። ሲጀመር ዳዕዋ ማለት ሙስሊሙ ላልሆኑ ወገኖች የሚደረገው ነው። ሙስሊም ለሆነውማ ምክርና ተግሳፅ ነው የሚያስፈልገው።
በሉ! አነሰ በዛ ሳንል እንረባረብና የተሻለ ኸይር ነገር እንሥራ። ብዙዎች ለባጢል ስንት እየተረባረቡና በቢሊዮን በጀት እየመደቡ፤ እኛ ለሐቅ መቶዎችንና ሺዎችን ማውጣት አይሳነንም። ቀሪውን አላህ በበረካው ይሞላዋል።
በነገራችን ላይ ይህቺ መኪና እንደ ልብ ክፍለ ሃገር ድረስ ሩቅና ፒስታ መንገድ በመጓዝ የዳዕዋ ሥራን ለማስሄድ አትሆንም። እንበራታና ትልቁን ሞንታሪቦና ጀኔሬተርም ጭምር አብሮ ለመያዝ አመች የሆነ መኪና እንግዛ። ይህ ኡስታዝ ከበርካታ አመታት በፊት ጀምሮ በንፅፅር ዳዕዋ የተሰማራና አሁን ለምናውቃቸው ለብዙዎችም ፋና ወጊ የሆነ ነው።
ይህ ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም። ሲቀጥል መኪና የምንገዛለት ለምቾቱና ለቅንጦት ሳይሆን፤ የተሰማራበት ዳዕዋ ስለሚያስገድድም ጭምር ነው።
እንዲህ አይነት ወንድሞችና ኡስታዞች ቤታቸው ውስጥ በሰላም ኖረው እንደኛ ህይዎታቸውን ከቤተሰባቸው ጋር መምራት ጠፍቷቸው አይደለም። ግን አላህ ስለመረጣቸው የብዙዎችን ግልምጫና መሰል ጫና ተቋቁመው የአላህን ጥሪ ላልሰማ ለማሰማት ደፋ ቀና እያሉ ነውና፤ አላህ በመልካም ነገር ላይ ተረባረቡ ስላለን እኛም አላህ የመረጠን እንሆን ዘንድ ገንዘባችን ለዚህ እገዛ በማዋል ከአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን።
በሉ! የት አላችሁ? ኸይር ፈላጊዎች ተሽቀዳደሙ።
√ የአካውንት ስም፦ Muhammed Khedr Essa
√ የኢትዮጵ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000258086857
√ የዘምዘም ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 000 19768 20101
√ የሂጅራ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000771510001
የምትልኩበትን ደረሰኝ ኮመንት ላይ ወይም በውስጥ መስመር t.me/Murad_Tadesse ላይ ብትልኩልኝ ለሌሎችም ለኸይር ማነሳሻ አደርገዋለሁ።
አላህ ይጨምርላችሁ!
ይህን የኸይር ሥራ ዘመቻ ለሌሎችም በማሰራጨት ከምንዳው ተካፋይ እንሁን!
ኢንሻ አላህ እናሳካዋለን‼
ለሰው ልጆች ሁሉ የተደረገ ጥሪ
“ከሙዕሚን ወንድሙ የዱንያን ጭንቀት የገላገለ ሰው አላህ (ሱ.ወ) ከቂያማ ቀን ጭንቀት እርሱን ይገላግለዋል” ነብዩ መሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
በባዩሽ መስጅድ የዲን ትምህርትን ጨምሮ ቁርኣንን በመሀፈዝ ፣ በኡስታዝነትና በኢማምነት እያገለገለ የሚገኘው ኡስታዝ ኸሊፋ በርታ በኮልፌ የገበያ ማዕከል በደረሰው የእሳት አደጋ በመጋዘናቸው ውስጥ የነበረ ግምቱ 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ውድመት ደርሶበታል።
ወንድማችን የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከመሆኑም በተጨማሪ አብዛኛው ንብረት በዕዳ የገባ በመሆኑ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ወንድማችንን ከጭንቀት ለመፈረጅ የበኩላችንን ድጋፍ እናደርግ ዘንድ እንጠይቃለን።
የአካውንት ስም:- ከሊፋ በርታ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000230579548
አዋሽ ባንክ:- 01425224548200
ዳሽን ባንክ:- 2920310294311
አቢሲኒያ ባንክ:-47469767
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:- 1000068036805
በአንድ ጳጳስና ኢማም የተደረግ ዉይይት። ክሪስማስና ሌሎች በዐላት ላይ መሳተፍ ያለዉ አደገኝነት ተገልፆል በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሙሉዉን አዳምጡት!
Читать полностью…የጁምዓ ሰደቃችንን ለሙሃጅሪን መስጅድ
አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበርካትሁ
ከወራት በፊት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የሙሃጅሪን መስጅድ ግንባታን በገንዘብ እጥረት ምክንያት በመቆሙ ግንባታውን ለማስጀመር ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የድጋፍ ጥሪ አቅርበን ነበር፡፡
ለረጅም ግዜ ተቋርጦ የነበረውን ግንባታ ለማስቀጠልም ከአምስት ሚሊየን አራት መቶ ሺህ ብር (5.4 ሚሊዮን ብር) በላይ እንደሚስፈልግም ገልጸን ነበር፡፡
በድጋፍ ጥሪው መሰረት አንድ ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ገዳማ ድጋፍ በመገኘቱ ግንባታው ከቆመ ከበርካታ ወራት በኋላ ዳግም ማስጀመር በመቻሉ በዝናብና በፀሐይ ብዛት አደጋ ላይ ሊወድቅ የነበረውን መስጅድ መታደግ ተችሏል፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ እንኳን ደስ አለን፡፡ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ በሙሉ ሁላችሁንም አላህ ኸይር ይመንዳችሁ።
በተገኘው ገንዘብም ጣራው ቆርቆሮ መልበስ በመቻሉ፣ የብሎኬት ድርደራ፣ ልስን፣ አሸንዳ ሥራ፣ የፍሳሽ ማስወገጃና ሌሎች መሰረታዊ ስራዎች መሰራታቸው መስጅዱን ከአዳጋ መከላከል ተችሏል፡፡
የመስጅዱ ግንባታ ምን ላይ እንደደረሰም በቪድዮና በፎቶ አስደግፈን ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ በተለያየ የሚድያ አማራጭ ለቀነዋል፡፡
ይሁን እንጅ የፊኒሽንግ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ማለትም በር፣ መስኮት፣ የወለል ስራና የመሳሰሉ በርካታ ሥራዎች አሁንም ስለሚቀሩና የተሰበሰበው ገንዘብ በማለቁ ግንባታው አሁንም ዳግም ሊቆም መሆኑ አሳስቦናል፣ አስጨንቆናልም፡፡
በመሆኑም የሙስሊም ወንድም እህቶችን ድጋፍ ድጋሜ መጠየቅ የግድ ሆኖብናል፡፡
ስለዚህ ሁላችሁም የተለመደ ትብብራችሁን ታደረጉልን ዘንድ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጥሪ እያቀረብን ለምታደርጉልን መልካም ትብብር ሁሉ አላህ ኸይር ጀዛችሁን እንዲከፍላችሁ የዘውትር ዱዓችን ነው፡፡
ለሙሃጅር መስጅድ ግንባታ ለምታደርጉት የገንዘብ፣ የሐሳብና ሌሎች ድጋፎች ከወዲሁ በአላህ ስም እናመሰግናለን፡፡
ግንባታውን ለማጠናቀቅ ቀሪ የገንዘብ መጠን ቢያንስ አራት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የግንባታ ባለሙያዎች አሳውቀውናል፡፡ በመሆኑም በገንዘብ ከመደገፍ ባለፈ መስኮት፣ በርና ሌሎች ቁሳቁሶችንም ገዝቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
ጥሬ ገንዘብ ማስገባት ለምትፈልጉና በሞባይል ባንኪንግ ለምታስተላልፉልን- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታችን
የሚከተለው ነው፡፡
-1000287521034 -ሙሃጂሪን መስጂድ
-ማንኛውም ጥያቄና አስተያየት ማድረስ ከፈለጉ የግንባታው አስተባባሪ ስልክ ቁጥር፡-
o ሸህ ሙስጠፋ ጀማል- 0910153147 የግንባታው አስተባባሪ
o ሲራጅ ሰይድ- 0941039736 የቀድሞ ተማሪዎች አስተባባሪ
o ሃሚድ አሊ- 0930619002 የቀድሞ ተማሪዎች አስተባባሪ
o ኡስታዝ ኑረዲን አብደላህ- 0913330123 የአሁኑ የዲላ ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አስተባባሪ(አሚር)
ታህሳስ 12/2016 ዓ.ል ኢትዮጵያ
ልክ የሌለዉ ቀልድ አንዱን ለሞት አንዱን ለ14 አመት እስር ዳረገ!
ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ አንደኛዉ በፌስቡክ ጓደኛዉ መንገድ ላይ ሽንቱን ሲሸና ይፖስታል። ፎቶ የተለቀቀበት ግለሰብ እንደሚበቀለዉ ይዝትና ከ3 ቀናት በኃላ ጓደኛዉ ሲሻ ሲያጨስ የሚያሳይ ፎቶ ይለቅበታል። ይህ የተቀቀበት ሰዉ ወደቤቱ ሲመለስ ሚስት እንዴት ሲሻ እንደጀመረ ስታፋጠዉ የት እንዳየችዉ ሲጠይቃት በፌስቡክ እንደሆነ ይነግራታል። ከዛም ጓደኛዉን ደብድቦ ገደለዉ። ምንጭ:- ብስራት ሬዲዩ
የማያምር ቀልድና በቀል ለከባድ አደጋ ይዳርጋልና እናስተዉል!
اَللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ.
Читать полностью…አሳሳቢዉ የሴት እህቶቻችን ልቅ የሆነ አለባበስ በተመለከተ የተደረገ ወሳኝ መልእክት!
Читать полностью…እህቴ ያጠለቀችዉ ቀሚሱ ከማጠሩ መወጣጠሩ የሆነ፤ ከመሳሳቱ የተነሳ የዉስጥ ቅርፅ የሚያሳይ የሆነ ቀሚስ ለብሳ እየወጣች እረ ተይ የሚል ወላጅ፣ ወንድም፣ ባል መካሪ እንዴት ታጣለች? እንዴት ሙስሊሟ እህቴ ከዝሙተኞች አለባበስ በባሰ መልኩ ለብሳ ትወጣለች?
Читать полностью…እናንተ በዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሰላም ላይ ወሰንን አልፋችሁ፡ ከአላህ ባርነት ወደ ልጅነት፣ ከነቢይነትና መልክተኝነት ወደ አምላክነት እንዳሸጋገራችሁትና በዚሁ ስራችሁም ኩፍር (ክህደት) ውስጥ እንደገባችሁት፡ እኛም በነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ከፍቅርና ከውዴታ የተነሳ ወሰን አልፈን እንዳንሳሳት፡ ከነፍሳችን በላይ ለኛ የሚራሩት ታላቁ ነቢይ እንዲህ አሉን፡-
عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، سَمِعَ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، يَقُولُ عَلَى المِنْبَرِ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: «لاَ تُطْرُونِي، كَمَا أَطْرَتْ النَّصَارَى ابْنَ مَرْيَمَ، فَإِنَّمَا أَنَا عَبْدُهُ، فَقُولُوا عَبْدُ اللَّهِ، وَرَسُولُهُ» البخاري 3445
ዐብዱላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ዑመር ኢብኑል-ኸጣብን (ረዲየላሁ ዐንሁ) በሚንበር ላይ ሁኖ እንዲህ ሲል ሰማው፡- ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፡- "ክርስቲያኖች ዒሳን ያለ ደረጃው ከፍ እንዳረጉት እኔንም ከፍ እንዳታረጉኝ፡፡ እኔ የአላህ ባሪያው ነኝና የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ"›› (ቡኻሪይ)፡፡
4ኛ. ትንሽ ያሳቀኝ ደግሞ ይህ ነው፡፡ ፊዳከ የምትለው በመድረክ ሞቅታ የተፈበረከች እንጂ ምንም ማስረጃ የላትም፡፡ በርግጥ ጥያቄው ከሙስሊም ቢመጣ ምነው እስከዛሬ የት ነበርክ? ያስብላል፡፡ ግን የራሱን መጽሐፍ እንኳ በወጉ ካላነበበ ሰው መገኘቱ ብዙም እንዳልገረም አድርጎኛል፡፡ ለማንኛውም የዚህን ቃል መሰረት ከየት እንደሆነ ማወቁ ለሙስሊሞች ጠቃሚ በመሆኑ እንመልከተው፡-
ሀ. ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)
ይህን ቃል ከተጠቀሙት ሰዎች የመጀመሪያው ታላቁ ነቢይ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እራሳቸው ናቸው፡፡ በእሁድ ዘመቻ ወቅት ሰዕድ ኢብኑ ማሊክን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አሉት፡-
عَنْ عَلِيٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ: مَا سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ جَمَعَ أَبَوَيْهِ لِأَحَدٍ إِلَّا لِسَعْدِ بْنِ مَالِكٍ، فَإِنِّي سَمِعْتُهُ يَقُولُ يَوْمَ أُحُدٍ: «يَا سَعْدُ ارْمِ فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي» رواه البخاري 4059 ومسلم 2411
ዐሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- "የአላህ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወላጆቻቸውን (አባትና እናት) በመሰብሰብ ለሰዕድ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉት ለማንም ሲሉ አልሰማኋቸውም፡፡ እኔ የእሑድ (ዘመቻ) ቀን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፡- ‹‹ሰዕድ ሆይ! (በጠላት ላይ በትርህን) ወርውር፡፡ እናቴና አባቴ ፊዳእ ይሁኑልህ››" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ጉዳዩ የፍቅርን ደረጃ ለመግለጽ እንጂ መስዋእት ለማቅረብ አለመሆኑን ይበልጥ የምንረዳው፡ የአላህ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ይህን በተናገሩ ጊዜ፡ ሁለቱም ወላጆቻቸው በህይወት አልነበሩም፡፡ ታዲያ ፊዳከ ማለት ፍቅርን ለመግለጽ እንጂ መስዋእት ለማቅረብ ነውን? ነገሩ አንድን ከሶስት መለየት ላልቻለ አእምሮ ይሄ ለመረዳት ቢከብደው የሚደንቅ አይደለም፡፡
ለ. አቡ በክር አስ-ሲዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ)፡-
ከነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ የኸሊፋነቱን ቦታ በመያዝ ኡምማውን የመሩት አቡ በክር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት ነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሚንበር ላይ ይቀመጡና፡- ‹‹አላህ ባሪያውን፡- ከፈለገ የዚህ ዓለምን ጌጦች የፈለገውን ያህል ሊሸልመው፣ ወይንም አላህ ዘንድ ያለውን ሊሰጠው አማረጠው፡፡ (ያ ባሪያም) አላህ ዘንድ ያለውን መረጠ›› ሲሉ፡ አቡበክር (ረዲየላሁ ዐንሁ) በጣም አለቀሱ፡፡ እንዲህም አሉ፡- ‹‹አባቶቻችንና እናቶቻችን ለርሶ ፊዳእ (ቤዛ) ይሁንልዎት›› ለካ ያ የአላህ ባሪያ የተባለውና ምርጫ የተሰጠው ነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መሆናቸው ለአቡበክር ተገልጾላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም የሳቸው መለየት ስላላስቻላቸው ‹‹በርሶ ምትክ አባቶቻችንና እናቶቻችን ፊዳእ ይሁንልዎት›› አሉ፡፡ (ቡኻሪይ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚይ)፡፡ የዚህን ሙሉ ቃል በዐረብኛ ለሚፈልግ ሰው ደግሞ ይኸው፡-
عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ جَلَسَ عَلَى المِنْبَرِ فَقَالَ: «إِنَّ عَبْدًا خَيَّرَهُ اللَّهُ بَيْنَ أَنْ يُؤْتِيَهُ مِنْ زَهْرَةِ الدُّنْيَا مَا شَاءَ، وَبَيْنَ مَا عِنْدَهُ، فَاخْتَارَ مَا عِنْدَهُ» فَبَكَى أَبُو بَكْرٍ وَقَالَ: فَدَيْنَاكَ بِآبَائِنَا وَأُمَّهَاتِنَا، فَعَجِبْنَا لَهُ، وَقَالَ النَّاسُ: انْظُرُوا إِلَى هَذَا الشَّيْخِ، يُخْبِرُ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ عَبْدٍ خَيَّرَهُ اللَّهُ [ص:58] بَيْنَ أَنْ يُؤْتِيَهُ مِنْ زَهْرَةِ الدُّنْيَا، وَبَيْنَ مَا عِنْدَهُ، وَهُوَ يَقُولُ: فَدَيْنَاكَ بِآبَائِنَا وَأُمَّهَاتِنَا، فَكَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ هُوَ المُخَيَّرَ، وَكَانَ أَبُو بَكْرٍ هُوَ أَعْلَمَنَا بِهِ، وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنَّ مِنْ أَمَنِّ النَّاسِ عَلَيَّ فِي صُحْبَتِهِ وَمَالِهِ أَبَا بَكْرٍ، وَلَوْ كُنْتُ مُتَّخِذًا خَلِيلًا مِنْ أُمَّتِي لاَتَّخَذْتُ أَبَا بَكْرٍ، إِلَّا خُلَّةَ الإِسْلاَمِ، لاَ يَبْقَيَنَّ فِي المَسْجِدِ خَوْخَةٌ إِلَّا خَوْخَةُ أَبِي بَكْرٍ» البخاري 3904 ومسلم 2382 والترمذي.
ሐ. አባ ጠልሓህ (አል-አንሷሪይ)፡-
የአላህ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከባለቤታቸው ሶፊያህ ቢንት ሑየይ (ረዲላሁ ዐንሃ) ጋር በአንድ ግመል ተፈናጠው ወደ አንድ ጉዞ እየተጓዙ ሳለ፡ የአላህ ቀደር ይሆንና እሳቸውና ባለቤታቸው ከግመሉ ላይ ይወድቃሉ፡፡ አባ ጠልሐም በድንገት ተወርውሮ ከራሱ ግመል ላይ ይወርድና በፍጥነት ወደ መልክተኛው በመምጣት፡- ‹‹አላህ እኔን ለርሶ ፊዳእ (ቤዛ) ያርገኝ፡፡ ምን የተጎዱት ነገር አልለ? ሲላቸው፡ እሳቸውም፡- እኔ ምንም አልሆንኩም፡ ግን እሷን አደራ ተጎድታ ከሆነ›› ብለው መለሱለት፡፡ (ቡኻሪይ 6185)፡፡
ተማራማሪዎች ለማግኘት ጊዜ ይፈጅባቸዋል እንጂ ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው! ይህ ደግሞ የነብዩ ሙሀመድ(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግር ነዉ።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما أنْزَلَ اللَّهُ داءً إلّا أنْزَلَ له شِفاءً.﴾
“አላህ አንድን በሽታ ከሰማይ አያወርድም። ለሷ የሚሆን መዳኛ አብሮ ቢያወርድላት እንጂ።” 📚 [ቡኻሪ ዘግበውታል 5678]
ዑስታዝ አቡ ሀይደር በሀላባ ዞን አንድ መስጅድ ከነመድረሳ ለማሰራት ከጥቂት አህለህ ኸይሮች ጋር በ11 ሚሊዩን ብር ስራዉ ከተጀመረና 4 ሚሊዩን ብር ካዋጡ በኃላ ከዚህ በላይ መቀጠል እንደማይችሉ አስታዉቀዋል። መስጅዱ እዚህ ደረጃ ደርሶ አላቋርጥም ብዬ ይህንን ኸይር ስራ ወደእናንተ አቅርቤዋለዉ ብሏል።
በዚህ ኸይር ስራ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ሙስሊም ወንድም እህቶች ቀጥታ ኡስታዝ አቡ ሀይደርን በዚህ ቁጥር 0911 10 32 31 የምታገኙት ሲሆን በተጨማሪ ከዚህ ስር በተጠቀሱ ባንኮች ብሩን ገቢ ማድረግ ትችላላቹ።
የአካዉንቱ ስም
SADIK MOHAMMED AHMED
የኢትዩጲያ ንግድ ባንክ
1000425034638
ዘምዘም ባንክ
0014688820101
ሂጅራ ባንክ
116229
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
1011300008645
አቢሲኒያ ባንክ
83047178
ዳሽን ባንክ
2900714650011
አዋሽ ባንክ
01425212425200