jibc_aastu | Unsorted

Telegram-канал jibc_aastu - Ahava 4 Solace

249

#Represent_Jesus!! #Counseling_Team!! If u have any request,questions or comment, u can put here @aastuecsfcounselingBot

Subscribe to a channel

Ahava 4 Solace

#በትግርኛ የተዘመረ መዝሙር!!
📟📟 Size :3.4Mb 📟📟
#Shared by Tesfu
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot
👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

We would like to thank all of you for participating and following the challenges...bless you!!

አሁን ደግሞ በተለያየ ቋንቋ የክርስቶስን ትንሳኤ የሚገልፁ ፎቶዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል

ከላይ ካሉት ምስሎች አንደኛውን መርጠን
#Profile_Picture በማድረግ አንድም #ቻሌንጁን እንቀላቀል በዚያውም ወዳጆቻችን ወደ ቻናላችን እንጋብዛቸዉ!!...

በዚህ ዉስጥ ያልተካተቱ በተወለዳችሁበት ቋንቋ ኢየሱስ ተነስቷል ሚለዉን
@J0hnny_710 ላይ ብትልኩልን እላይ ባሉት መልክ አዘጋጅተን እንለቃቸዋለን!!

መልካም የትንሳኤ በዓል !!

መልዕክት እና ሐሳቦቻችሁን በነዚህ ሊንኮች ላኩልን

@J0hnny_710 @wushiy @emuti77

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በወላይትኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በትግርኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በከፊኛ (የቦንጋ ቋንቋ)

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በኢንግሊዘኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በአማርኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

Singer - Hana Tekle

ካህን በገዛ ደምህ አዳንከኝ
ካህን በገዛ ቁስልህ አተረፍከኝ
ከፍለህ አቋደስከኝ ህይወትህን
ቆርሰህ አካፈልከኝ ነፍስህን
ከዚህ የጨመረ ምን ፍቅር ይኖራል
ከዚህ ደርዝ ያለፈ ምን መውደድ ይገኛል
መስዋዕት ከመሆን ከመሞት የባሰ
ለነፍስ ነፍስ ከማጣት ከማለፍ ያለፈ

ብልህ የመውደድ ጥልቅ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ባንተ ፍቅር ብቻ

በቃል ብቻ በአንደበትህ መች ወደድከኝ
በግብር እንጂ በእውነት ትርጉም ያፈቀርከኝ
ፍቅርን አሳየኸኝ ራስህን ለቅቀህ
ሆነህ ከነፍስ ውጪ በፍቃድህ ተገድለህ
ቅን ደጉ ታመምህ የዋህ ስቃይ ገባህ
ፍቅር ተገድልህ ህይወቴ እንዲገባ

ብልህ የመውደድ ጥግ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
ህይወቴ ተርፎልኝ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ብልህ የመውደድ ጥልቅ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ባንተ ፍቅር ብቻ

ልታድነኝ ልታተርፈኝ ወደህ የሄድክበት
የሞትህ ነው ያልተገባህ በደም ያለፍክበት
ከሞትም የስቃይ በእንጨት ተንጠልጥለህ
ጻድቅ ያለኀጥያትህ ከአባይ መሃል ውለህ

ቅን ደጉ ታመምህ የዋህ ስቃይ ገባህ
ፍቅር ተገደልህ ህይወቴ እንዲገባ
ብልህ የመውደድ ጥግ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ስቃይ ብቻ
በህማምህ ብቻ
ብልህ የመውደድ ጥልቅ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ

ምልህ አይገልጽህም ዘመኔም ያንስሃል
ለፈሰሰው ደምህ ምኔስ ይክስሀል
እንዲያው ዝም ብዬ ቤዛዬ እልሀለሁ
በቀረልኝ እድሜ ሳመልክህ ኖራለው
አዜምልሃለሁ

ቤዛዬ እልሀለሁ ቤዛዬ እልሀለሁ
ቤዝወት ባንተ ያየሁ
አዳኜ እልሀለሁ አዳኜ እልሀለሁ
ድነት ባንተ ያገኘሁ..


@JIBC_AASTU @JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_23

🎶Singer - Yoseph Bekele
📃Title - መስቀልህ ስር
⌛️Size - 7.8 MB


@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

ሻሎም!!!
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!

ሁላችንም እንደምናውቀው ይኼ በዓል ከመብላትና መጠጣት ከፍ ያለ፣ ከመደሰት ያለፈ ትርጉም ያለዉ መሆኑ ነዉ። ይህ የጌታችን #ሞት_እና_ትንሳኤ እርሱ ከሙታን በኩር ሆኖ እኛን በፀጋዉ እና በመንፈሱ ሀይል ለራሳችን ሞተን ለርሱ ህያው እንድንሆን የተነሳንበት ስለሆነ ነቅተን ልናስተውል እና አብዝተን ልናመሰግን ይገባል።

#AHAVA_4_SOLACE ቤተሰቦቻችን ለአንድ #Challenge ልንጋብዛችሁ ወደናል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ስለመስቀሉ የተረዳችኋቸዉን መረዳቶች
👉 በፅሁፍ
👉 በስዕል
👉 በዝማሬ
👉 በፀሎት
👉 በገለፃ
👉 በፎቶግራፊ
.... በሌላ አማራጭ እያጋራችሁን(#Share) የመስቀሉን ስራ እና የሆነልንን በማዉራት ክርስቶስን እናልቀዉ!!

#መልዕክቶቻችሁን በነዚህ ሊንኮች ላኩልን
@JIBC_bot
@J0hnny_710
@emuti77
@wushiy
#ብሩካን_ናችሁ!!
@JIBC_AASTU

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_20

የጌታ እራት መልዕክት

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከስቅለቱ አንድ ቀን በፊት ካደረጋቸው ወሳኝ እና መልዕክት አዘል ድርጊቶች አንዱ ነው የጌታ እራት (The Last Supper)


ሉቃስ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና፦ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
²⁰ እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።

👉ይህ ስፍራ በክርስቶስ የማስታረቅ ስራ ላይ ወሳኝ የሆኑትን "ስጋውን" እና"ደሙን" በደንብ ገልፆታል

👉በኃጢአታችን ምክንያት ከእግዚአብሔር የተለየን እና ዕዳ የነበረብን፣ የሁላችን ኃጢያት ደመወዝ በመስቀሉ ላይ ክርስቶስ "በሥጋው" ተቀጥቶ እኛን ነፃ አወጣን። እግዚአብሔር ይመስገን!!!!!

❝እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥❞
—ኤፌሶን 2: 14-15

❝እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።❞
—ቆላስይስ 1: 21-22

👉በፊት ተስፋ ያልነበረን፣ በኃጢአት ጉልበት ስር የተገዛን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም አዲስን ኪዳን ተቀብለናል።
❝እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።❞
—ሉቃስ 22: 20

🙏የጌታ ስም የተባረከ ይሁን !!!🙏

ስለዚህ ከጌታ ጋር ያለንን ኪዳን በፀጋው ኃይል አጽንተን እና በሥጋው መቆረስ የተቀበልነውን ህይወት ጌታን በመውደድ እና በማፍቀር እንዲሁም በፍጹም መገዛት ለጌታ እንደሚገባ እንመላለስ!!!

#ኢየሱስ_ይመጣል!!!
#Meti_Tegegn
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_18

🔖Title-እንደ ሌባ
🎶Singer- ዶ/ር ደረጀ ከበደ
⌛️Size- 2.8 MB

--------------------------------------------

አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ

ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ

በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን

በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x)


እጅግ ፡ ከብዶት ፡ ነበረ ፡ መስቀሉ

አሸክመው ፡ ሲያስጨንቁት ፡ ዋሉ

ለዓለም ፡ ኃጢአት ፡ ኢየሱስ ፡ ተመታ

በመስቀል ፡ ሞት ፡ በእርባን ፡ እንዲፈታ (፪x)


የደሙ ፡ ላብ ፡ አለዋጋ ፡ አይደለም

የጐኑ ፡ ውኃ ፡ ለከንቱ ፡ አልፈሰሰም

ንጹህ ፡ ደሙ ፡ ለእንስሳት ፡ አይደለም

ክቡር ፡ ማንጻት ፡ አለው ፡ ለእኔም ፡ ለአንተም
(፪x)


አዝ፦ እንደ ፡ ሌባ ፡ እንደ ፡ ወንጀለኛ

ንጹህ ፡ አምላክ ፡ ሆነልን ፡ ስለእኛ

በጨለማ ፡ በድቅድቁ ፡ ሳለን

በእግዚአብሔር ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘን (፪x)

@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_17

🔦🔦 ግጥም 🔦🔦
📜ርዕስ፦ በርባን 📜

#Ermiyas (Pre-Engineering)
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_4
#Challenge_15

If love endured that ancient cross
How precious is my Saviour’s blood
The beauty of heaven wrapped in my shame
The image of love upon death’s frame

If having my heart was worth the pain
What joy could You see beyond the grave
If love found my soul worth dying for

How wonderful
How glorious
My Saviour’s scars
Victorious
My chains are gone
My debt is paid
From death to life
And grace to grace

If heaven now owns that vacant tomb
How great is the hope that lives inYou
The passion that tore
Through hell like a rose
The promise that rolled back
Death and its stone

If freedom is worth the life You raised
Oh where is my sin where is my shame
If love paid it all to have my heart

When I see that cross I see freedom
When I see that grave I’ll see Jesus
And from death to life
I will sing Your praise
In the wonder of Your grace

How my soul will sing Your praise
In the wonder of Your grace
How my soul will sing Your praise

@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥21 (አዲሱ መ.ት)

ዮሐንስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት።
²⁹ ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።


#ወንጌል_ለእግዚአብሔር_መስራት_ሳይሆን_እግዚአብሔር_የሰራዉን_በእምነት_መቀበል_ነዉ!!

@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

We would like to thank all of you for participating and following the challenges...bless you!!

አሁን ደግሞ በተለያየ ቋንቋ የክርስቶስን ትንሳኤ የሚገልፁ ፎቶዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል

ከላይ ካሉት ምስሎች አንደኛውን መርጠን #Profile_Picture በማድረግ አንድም #ቻሌንጁን እንቀላቀል በዚያውም ወዳጆቻችን ወደ ቻናላችን እንጋብዛቸዉ!!...

በዚህ ዉስጥ ያልተካተቱ በተወለዳችሁበት ቋንቋ ኢየሱስ ተነስቷል ሚለዉን @J0hnny_710 ላይ ብትልኩልን እላይ ባሉት መልክ አዘጋጅተን እንለቃቸዋለን!!

መልካም የትንሳኤ በዓል !!

መልዕክት እና ሐሳቦቻችሁን በነዚህ ሊንኮች ላኩልን

@J0hnny_710 @wushiy @emuti77

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በሲዳሚኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በአፋን_ኦሮሞ (ኦሮሚኛ)

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በአደርኛ (የሐረር ቋንቋ)

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በጉራጊኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በቤንችኛ (የሚዛን አካባቢ/ የቤንቺ ማጂ ቋንቋ)

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#ኢየሱስ_ተነስቷል Challenge
#በአገዉኛ

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_24

#For_Profile_Picture_2


Join the challenge by changing your profile pictures

We will continue posting other photos....

Stay tuned 😊

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_22

#For_Profile_Picture_1


Join the challenge by changing your profile pictures

We will continue posting other photos....

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_21

Singer - Tesfaye Gabiso


@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_19

John 3 (NLT)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ "For God so loved the world that he gave his only Son, so that everyone who believes in him will not perish but have eternal life.
¹⁷ God did not send his Son into the world to condemn it, but to save it.

The #REGENERATED life

#Spirit_born

“And the Lord God formed a man's body from the dust of the ground and breathed into it the breath of life.
— Gen 2:7 (NLT)

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከውሃ እና ከአፈር ከሰራው በሗላ የሂወትን እስትንፋሱን እፍ ሲልበት ነፍስ ዘራ።

" Lord and giver of life "

✔The breathe of God is his spirit and who generates man from clay.
✔It is the spirit of God who generates and who sustain each of us in life.

— Gen 3 (NLT)

-ነገር ግን የሰው ልጅ በሰራው ሀጢያት ምክንያት እግዚአብሔር ካስቀመጠው ስፍራ ተባረረ ሞትንም እንደ እርግማን ተቀበለ ። ይህም እርግማን ትውልድን እየተከተለ የትውልዱም ሀጢያት እጅግ እየበዛ ሄደ። እግዚአብሔርም ደግሞ የሰው ልጅን ከሃጢአት ባርነት ነፃ ሊያወጣ የሞትንም እርግማን ሊሰብር በምትኩም የዘላለም ሕይወት ሊሰጠን አንድያ ልጁን ሰዋልን።

ልጁም ወደ ምድር መጣ ስለእኛ የበግ መስዕዋት ሊሆን ተገረፈ ፣ ተሰቀለ ፣ ሞተ በሶስተኛውም ቀን ተነሳ።

— Eph 2: 1-5 (NLT)

✔We must be resurrected from the dead and born again into new life .
🔺️ Regeneration🔺️:—The new birth, the new creation,the resurrected life is the sovereign work of God the holy spirit. Left to our selves we would never turn to God .

✔ታዲያ spirit born (born again) ለመሆን የሰው ልጅ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ማመን አለበት ።

“For people can't come to me unless the Father who sent me draws them to me, and at the last day I will raise them from the dead.”
— John 6:44 (NLT)

#What_does_spirit_born_means?

✔We are not good enough for the kingdom to enter .

“Jesus replied, "I assure you, unless you are born again, you can never see the Kingdom of God."”
— John 3:3 (NLT)

🔸️ዳግም ልደት🔸️ ፦ በክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በማመን በሞቱ ለስጋችን ሞተን ፣ አዳማዊ ማንነታችንን ገድለን በትንሳኤው ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት አገኘን ።

#ዳግም_ልደት_ምን_አስገኘልን?

“For God has reserved a priceless inheritance for his children. It is kept in heaven for you, pure and undefiled, beyond the reach of change and decay.”
— 1Pet 1:4 (NLT)

✔የዘላለም ሕይወት እና ተስፋ

የማይለወጥ
የማይጠፋ
የማይበለሽ............ ርስት ተሰጠን።

❤ስለዚህ ደስ ይበላችሁ አዳኝ ከሰማይ ወደ ምድር መጣ። ክብር እያለው ክብሩን ጣለ😔 አይሁዶች በንጉስ ቤት🤴 የሚጠብቁት ኢየሱስ ስለ እኔ እና ስለ እናንተ ሲል በበጎች🐑 በረት በግርግም ውስጥ ተወለደ ። ደምግባቱን አጥቶ ደምግባትን ሰጠን ። ባደገም ጊዜ ፃፎች እና ፈሪሳውያን አሳደዱት ፣ ሊገድሉት ከሰሱት ። ኢየሱስን በጅራፍ ገረፍት በአደባባይ መስቀል አሸክመው አንገላቱት በጎልጎታ እርቃኑን ሰቀሉት ኢየሱስ ታመመ ፣ ደከመ ሞተ።❣❣❣

ነገር ግን ሁሉን የሚቻለው ንጉሥ በሶስተኛው ቀን ሞትና የሞትን መውጊያ ድል አድርጎ ተነሳ።😁✊
ብዙዎች ሞተው ቀርተዋል ኢየሱስ ግን ሞትን አሸንፏል እርሱ ሕያው ነው።💪
ስለ እኔ ፣ ስለ እናንተ ደግሞም በአለም ላሉት ሁሉ ኢየሱስ የነፍስ ዋጋ ከፍሎ ወደ ዘላለማዊው ቤቱ አፈለሰን ስሙ ይባረክ።🙏🙏


#Yididiya
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_17

#የቄዳር_ወንዝ

ይህ የቄዳር ወንዝ ታሪኩ ብዙ ትርክቱም ጥልቅ ነዉ። ንጉሡ ዳዊት በልጁ አቤሴሎም በደረሰበት መከዳት በዚህ ወንዝ ተሻግሮ ነበር ወደ ኮረብታው በባዶ እግሩ የወጣዉ። ከእርሱ ስር የተገኘዉ የናዝሬቱ ኢየሱስም ተመሳሳይ #ክህደት ባስጠጋዉ ወዳጁ ይሁዳ ከዚህ ወንዝ ማዶ ካለ የአትክልት ቦታ ላይ ነበር የተከዳዉ።

#ክህደት ያሳምማል!! በተለይ ባቀረቡት እና አምነዉ ወዳጅ ባደረጉት ሰዉ ሲሆን ደግሞ ከማመም አልፎ ያቆስላል። ይህን ክህደት ተከትሎ ወደ ጊዜዉ ሊቀ ካህን ሐና ቀጥሎም ሊቀ ካህን ቀያፋ ጋር ወሰዱት። እንዴት ቢቀኑ ነዉ እኚህ ሊቀ ካህናት በዚህ ድንቅ ሊቀ ካህን ላይ ይሙት ሲሉ የፈረዱት?! "መፅሀፍትን አታስተዉሉምና ትስታላችሁ።" የሚለዉ ቃል ለእኛ ነዉ አሉሳ!!....ለነገሩ እንኳንስ ተሞኙ ተሞኝተዉ የወሰኑት ዉሳኔ ለእኛ ደህንነት ወደ ሚሆን እዉነት ኢየሱስን ገፈተረዉ።

ያገኙት ሲሳለቁበት አንዳንዱም ሲያጣፉት ያደላቸዉ በዝምታዉ ዉስጥ የሚጮኸዉን ንፅህናዉን ሲሰሙ ለብዙሃኑ ግን "በድካሙ ፍሬዉን ያያል።"-(ኢሳ 53:11-12)(emphasised) የሚለዉ የመፅሀፍ ቃል እንዴት ተሰወረባቸው? እየገፈተሩ ወስደዉ ለነሱ የሚሞተዉን እነርሱን በሚገድለዉ በርባን ለወጡት! ልቅሶዉ ሳያሳሳቸዉ ፤ ሕመሙ ትርጉም ሳይሰጣቸዉ ፤ በጣሩ ተሳለቁ ፤ በመቃተቱ አስካኩ!!.....
🗞ግን ለምን ወዳጄ ይህን ሁሉ ታገሰ?
🗞 ስለምንስ የኔ ዉድ በፈጠራቸው እንዲያ ተሰቃየ?
🗞 ምን ገዶት በእጁ ስራ እጅ ጥፊን ተቀበለ?
🗞 ምን ቢጨንቀዉ ነዉ የስቃይን ፅዋ ያለ አንዳች ማማረር የተጎነጨዉ?
🗞 ለነርሱ ከሆነ የሚሞተዉ ካልተረዱት ለምን 'አይናቸዉን ላፈር' ብሎ ከመጣበት አልተመለሰም?

#ዉዴ በስቃዩ መሃል የእኛን ስቃይ ማስቀረቱ እየታየዉ በልቡ ደስታ የአካሉን ስቃይ ታገሰ።
#የኔ_ዉድ በለቅሶዉ የእኛን ለቅሶዉ ማስቀረቱ እየታየዉ የስቃዩን ለቅሶ በደስታ አነባ።
#ዉዴ በጣሩ ከሞት ጣር ነፃ አወጣን!!

🧩ታዲያ ምላሻችን ምን ይሁን?
" በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።"(2ኛቆሮሰዎች 5:15)
መልካም የትንሳኤ በዓል!!


#Tagicho
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_5
#Challenge_16

"መዉደዱ በሥጋው መቆረስ ደመቀ፣ ለእኛ ያለዉ ፍቅሩ በደሙ መፍሰስ ታተመ።
በቁስሉ ዉስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጨባበጥን ፣ በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ፡ በምድር ለሰው ልጁ ስምረት ኾነ!"

የተቆረሱ ነፍሶች፣ ሰለሞን አበበ

@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_4
#Challenge_14

#ክፍል_፪

#የመማፀኛ_ከተማዬ_ዘልዬ_የማመልጥበት
#ካሳዳጅ_ከአስጨናቂዎቼ_ተሸሽጌ_ምገባበት
#ኢየሱስ_በተባለው_ድንቅ_ስም
#ነብሴ_አርፋለች_ከምንም
#እርሱ_የከፈለውን_ዋጋ_አልፎ_ማነዉ_እኔን_ሚነካ
#በደም_የከፈለውን_ዋጋ_ደፍሮ_ማነዉ_እኔን_ሚነካ

የመዝሙሩ ቀጣዩ ቁጥር ከላይ ያለውን ይመስላል።
መፅሐፍት ሁሉ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያወራሉ ሲባል ግራ የሚገባው ሰዉ ካለ ይሄ መዝሙር በዚህኛው ቁጥሩ የብሉይ ኪዳንን ስርዓት ጠቅሶ የኢየሱስን #ይቅርታነት / ቤዛነት ያወሳል።

ከላይ ያለዉ ታሪክ (ማለትም የመማፀኛ ከተማ የሚለዉ ማለት ነዉ) እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ካዘጋጀላቸዉ የመዳን መንገድ ዉስጥ አንደኛው ነዉ።

#በዘኁልቁ 35 ቁጥር 6 ጀምሮ ስለ መማፀኛ ከተሞች ይናገራል። ይኸዉም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ለሌዋውያን 48 ከተሞችን እንዲሰጡኣቸዉ አዘዘ። ይሄም ብዙ ከሆነ ነገድ ብዙ ከተማ ጥቂት ከሆነዉ ደግሞ ጥቂት እንዲሰጣቸዉ ነዉ። ከሚሰጧቸው 48 ከተሞች መሃከል 6ቱ ከተሞች ለሕዝቡ #የመማፀኛ ከተማ ሆነዉ እንዲያገለግሉ የሚመረጡ ናቸዉ። እኚህ ከተሞች 3ቱ ከዮርዳኖስ ወዲህ እና የተቀሩት ሶስቱ በከነዓን ከተማ የሚሆኑ ናቸዉ።

#አገልግሎታቸው??
ማንም ሰዉ ሰዉን ቢገድል፣ የሟቹ ደም መላሽ ገዳዩ ገድሎ እንዲበቀል ሕጉ ይፈቅድለታል(ሠዉየዉ ምናልባት ሳያዉቅ ይሆናል የገደለዉ🤔) -- ዘኁልቁ 35፥ 19። እንግዲህ ማንም ሰዉ ይሄን ጥፋት ቢያጠፋ "Automatically" የመሰንበት ነፃነቱን ይነጠቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ሕግ ሰጠ ይኸዉም ማንም ሰዉን የገደለ ሰዉ ተሸሽጎ የሚያመልጥበትን እና የሚሰነብትበትን ዕድል አዘጋጀ-- #የመማፀኛ_ከተማ!! ማንም ጥፋተኛ ወደዚህ ከተማ ሮጦ ዘሎ ቢገባ አሳዳጆቹ ምንም ሊያደርጉበት አይችሉም።

#ግን_ይኼ_የሚቆየዉ_የወቅቱ_ሊቀካህን_በሕይወት_እስካለ_ብቻ_ነዉ! 🙆🙆 ዘኁልቁ 35፥28

👌 እንግዲህ ይኼን ታሪክ ወስደዉ ነዉ ከኢየሱስ ጋር ያገናኙት እነዚህ እህቶች።
🎇 የዕብራውያን ፀሃፊ በመልዕክቱ 7ኛዉ ምዕራፍ 24ተኛዉ ቁጥር ላይ የኢየሱስ ክህነት የማይሻር እና የዘላለም እንደሆነ ያሳየናል። ይኼም ማለት ማንም በኢየሱስ ቢሆን ከሚከሰዉ ኩነኔ፣ ከሚያሳድደዉ ሞት እና የሞት ፍርሃት ተዘልሎ ይኖራል ማለት ነዉ። የዚህኛው የመማፀኛ ከተማ መልክ ሊቀ-ካህኑ ይሞት ይሆን ተብሎ የማይሰጋለት መሆኑ ነዉ!!💪
👉 እርሱ ሮጦ ለገባበት #ይቅርታው ፣ አምልጦ ለመጣበት #መዘለያዉ ፣ ሸሽቶ ለገባበት የዘላለም #መሸሸጊያዉ ነዉ!!

💗 ለእርሱ ክብር እና ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን!!

#ይቀጥላል...


#Tagicho
@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…

Ahava 4 Solace

#Day_4
#Challenge_13
The trial of Jesus before crucifixion

The night of Jesus’ arrest, He was brought before Annas, Caiaphas, and an assembly of religious leaders called the Sanhedrin (John 18:19-24  Matthew 26:57).
After this He was taken before Pilate, the Roman Governor (John 18:28), sent off to Herod (Luke 23:7), and returned to Pilate (Luke 23:11-12), who finally sentenced Him to death.

There were six parts to Jesus’ trial: three stages in a religious court and three stages before a Roman court. Jesus was tried before Annas, the former high priest; Caiaphas, the current high priest; and the Sanhedrin. He was charged in these “ecclesiastical” trials with blasphemy, claiming to be the Son of God, the Messiah.

The trials before Jewish authorities, the religious trials, showed the degree to which the Jewish leaders hated Him because they carelessly disregarded many of their own laws.

There were several illegalities involved in these trials from the perspective of Jewish law:


(1) No trial was to be held during feast time.
(2) Each member of the court was to vote individually to convict or acquit, but Jesus was convicted by acclamation.
(3) If the death penalty was given, a night must pass before the sentence was carried out; however, only a few hours passed before Jesus was placed on the Cross.
(4) The Jews had no authority to execute anyone.
(5) No trial was to be held at night, but this trial was held before dawn.
(6) The accused was to be given counsel or representation, but Jesus had none.
(7) The accused was not to be asked self-incriminating questions, but Jesus was asked if He was the Christ.


From GotQuestions.org


@JIBC_AASTU
@JIBC_bot

Читать полностью…
Subscribe to a channel