kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1940

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወደ ንጉሡም በገቡ ጊዜ ከእነርሱ ቡራኬ ተቀበለ ቁስላቸውንም ሳመ እጅግም አከበራቸው ብዙ ገንዘብም ሰጣቸው እነርሱ ግን ለቤተ ክርስቲያን ከሚሆን ንዋየ ቅድሳት በቀር ምንም ምን አልተቀበሉም ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶ ወደየሀገራቸው በሰላም አሰናበታቸው። አባ ኖብም ወደ ቦታው ተመልሶ አረፈና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_23

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ሦስት በዚች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ #የጠቢቡ_ሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ #አባ_ኖብ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢየ_ጽድቅ_ቅዱስ_ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)

ሰኔ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

የዚህ የሰሎሞንም የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ነው ዳዊትም ሕግ ተላልፎ ከእሷ ጋራ ስለ መበደሉ ባሏንም ስለ ማስገደሉ ጌታ በገሠጸው ጊዜ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ጌታም ንጹሕ ስለሆነ ንስሓው ይቅር አለው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሷን አገባትና ሰሎሞንን ወለደችው ንጉሥ ዳዊትም ከእርሱ በኋላ ልጅዋ ሰሎሞን እንዲነግሥና በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ ቃል ገባላት።

እንዲህም ሆነ ሰሎሞን ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አዶንያስ እነግሣለሁ ብሎ ተነሣ ምክሩም ሁሉ ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ አብያታር ጋር ሆነ። እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት። አዶንያስም በሮጌል ምድር ምንጭ አጠገብ ባለ በኤልቲ ዘዘኤልቲ ላይ ፍየሎችን በጎችንና ላሞችን አርዶ የንጉሥ አሽከሮች የሆኑ የይሁዳ አርበኞችን ሁሉና የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ ጠራ።

ከዚህም በኋላ አዶንያስ ይህን እንዳደረገ ለቤርሳቤህ በነገሩዋት ጊዜ ወደ ንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ገብታ ለንጉሡ ሰገደች ንጉሥ ዳዊትም ምን ሆንሽ አላት። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል ብለህ ለእኔ ለባርያህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም አንተ ማልክልኝ እነሆ ዛሬ አዶንያስ ነገሠ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አንተ ግን አላወቅህም አለችው።

ከንጉሥም ጋራ ገና ስትነጋገር ነቢዩ ናታን መጣ ለንጉሡም ናታን መጣ ብለው ነገሩት። ወደ ንጉሡም ገባ በምድር ላይም በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ነቢዩ ናታንም ከእኔ ቀጥሎ አዶንያስ ይንገሥ በዙፋኔም ላይ ይቀመጥ ያልክ አንተ ነህን ዛሬ ወርዶ በጎችንና ብዙ ፍየሎችን አርዶ የሠራዊቱ አለቆችንና የንጉሥ አሽክሮችን ሁሉ ካህኑ አብያታርንም ጠርቷልና በፊቱም ይበላሉ ይጠጣሉ አንዶንያስ ሽህ ዓመት ያንግሥህ ይሉታል አለው።

ዳዊትም መልሶ ቤርሳቤህን ጥርዋት አለና ጠሩዋት ገብታም በንጉሡ ፊት ቆመች። በእግዚአብሔር ፊት እንደማልኩልሽ አሁንም በዚች ቀን እንደዚሁ እንዳደርግ ሰውነቴን ከመከራዬ ሁሉ ያዳናት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕያው ነው ብሎ ማለ። ቤርሳቤህም አንገቷን ደፍታ በግምባርዋ በመሬት ወድቃ ለንጉሡ ሰገደች ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ኑር አለች።

ንጉሥ ዳዊትም የዮዳሄ ልጅ ብንያስንና ካህኑ ሳዶቅን ነቢዩ ናታንንም ግራዝማቹንና ቀኝ አዝማቹን ጥሩልኝ አለ። ንጉሡም ከእናንተ ጋራ የጌታችሁ አሽከሮችን ይዛችሁ ልጄ ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን አውርዱት። በዚያም ነቢዩ ናታንና ካህኑ ሳዶቅ ቀብታችሁ በእስራኤል ላይ አንግሡት አላቸው።

ቀንደ መለከት ንፉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ በሉ። ተከትላችሁትም ውጡ ገብቶም በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ እርሱም ስለ እኔ ፈንታ ይንገሥ በሁለቱ ነገድና በዐሥሩ ነገድ ይነግሥ ዘንድ እኔ አዝዣለሁ። ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ ቀርነ ቅብዑን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው ቀንደ መለከትንም ነፉ ሕዝቡም ሁሉ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ አሉ ሕዝቡም ሁሉ ተከትለውት ወጡ ከበሮም መቱ ታላቅ ደስታም አደረጉ ከድምፃቸውም የተነሣ ምድሪቱ ተናወጸች።

ሰሎሞንም በመንግሥት ዙፋን ተቀመጠ። የንጉሡም አሽከሮች ጌታቸው ንጉሡ ዳዊትን ሊአመሰግኑ ገቡ። እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርገው ዙፋኑንም ከዙፋንህ ይልቅ የበለጠ ያድርገው አሉት። ንጉሡም በዐልጋው ሆኖ ሰገደ። እንዲህም አለ ዐይኖቼ ሲያዩ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ልጅን ለኔ ለባርያው ዛሬ የሰጠ የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አለ። ዳዊትም የሚሞትበት ወራት በደረሰ ጊዜ ልጁ ሰሎሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው። እኔ ሰው ሁሉ በሚሔድበት በሞት ጐዳና እሔዳለሁ አንተ ግን ጽና ብልህ ሰውም ሁን።

በሕጉ ጸንተህ ትኖር ዘንድ የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ትእዛዙን ጠብቅ እኔ እንዳዘዝሁህ እንዴት እንደምታደርግ ታውቅ ዘንድ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ትእዛዙንና ሕጉን ፍርዱንም ጠብቅ ልጆችህ ሕጌን ቢጠብቁ በፊቴም በፍጹም ልቡናቸው በፍጹም ሰውነታቸው በዕውነት ጸንተው ቢኖሩ ከእስራኤል ዙፋን ላይ ሰው አይጠፋብህም ብሎ እግዚአብሔር ለእኔ የነገረኝ ቃሉን ያጸና ዘንድ ጠብቅ ብሎ አዘዘው።

ዳግመኛም በኢዮአብና በሳሚ ወልደ ጌራ ላይ በቀል እንዲአደርግ አዘዘው እነርሱ እጅግ የከፉና ብዙ ክፋት የሠሩ ነበሩና። ከዳዊት ዕረፍትም በኋላ ሰሎሞን በዚያ መሥዋዕትን ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ወደ ገባዖን ሔደ ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና ሰሎሞንም በገባዖን በዚያው መሠዊያ ውስጥ ሽህ መሥዋዕትን ሠዋ። እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት በሕልም ተገለጠለት ለአንተ እሰጥህ ዘንድ ልብህ ያሰበውን ልመናን ለምን አለው።

ሰሎሞንም በቅንነትና በእውነት በንጹሕ ልቡናም ከአንተ ጋራ በፊትህ ጸንቶ እንደኖረ ከአባቴ ከዳዊት ጋራ ታላቅ ቸርነትን አድርገሃል በዚችም ቀን ልጁን በዙፋኑ ላይ ታስቀምጠው ዘንድ ይህን ታላቁን ቸርነት አጽንተህለታል አለው። አሁንም አቤቱ አንተ ፈጣሪዬ ስለ አባቴ ስለ ዳዊት ፈንታ እኔን ባሪያህን አነገሥኸኝ እኔም መግቢያዬንና መውጫዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።

እኔ ባሪያህ ግን የማይቈጠር ብዙ ሕዝብ በሆነ በመረጥከው ወገንህ መካከል አለሁ። ለዚህ ለብዙ ወገንህ መፍረድ የሚችል የለምና ሰምቶ ለወገኖችህ በእውነት ፍርድን ይፈርድ ዘንድ ከክፉ ነገርም ለይቶ በጎውን ነገር ያውቅ ዘንድ ለባሪያህ ዕውቀትን ስጠው። ሰሎሞን ይህንን ነገር ለምኖታልና ይህ ነገር እግዚአብሔርን በፊቱ ደስ አሰኘው። እግዚአብሔርም ይህንን ነገር ከእኔ ለምነሃልና ለአንተም ብዙ ዘመንንና ባለጸግነትን አልለመንህምና ጠላቶችህንም አጥፋልኝ ብለህ አልለመንህምና ነገር ግን ፍርድ መስማትን ታውቅ ዘንድ ለምነሃልና እነሆ እንዳልህ አደረግሁልህ።

እነሆ ከአንተ አስቀድሞ እንዳልነበረ ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ እንዳይነሣ አድርጌ ብልህና አስተዋይ ልቡናን ሰጠሁህ። ሰው በመንግሥቱ እንዳንተ እንዳልሆነ አድርጌ ያልለመንኸኝን ባለጠግነትንና ክብርንም በዘመንህ ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።

ሰሎሞንም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እውነተኛ ሕልም እንደ ሆነ ዐወቀ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በጽዮንም በእግዚአብሔር ታቦተ ሕግ አንጻር ባለ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የሰላም መሥዋዕትን አቀረበ ለሰዎቹና ለሱም ታላቅ ግብዣ አደረገ።

በዚያን ጊዜም ሁለት አመንዝራ ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው በፊቱ ቆሙ አንዲቱም ሴት ጌታዬ ስማኝ እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን በአንድ ቦታም ወለድን እኔ በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች በአንድነትም እንኖራለን በዚያም ቤት ከሁለታችን በቀር ከኛ ጋራ ማንም አልነበረም። በላዩ ላይ ተጭናዋለችና የዚያች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ።

በሌሊት እኩሌታም ተነሥታ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወስዳ በብብቷ አስተኛችው። የሞተውን ልጅዋንም በአጠገቤ አስተኛችው። ልጄን አጠባ ዘንድ በጧት በነቃሁ ጊዜም ያንን የሞተ ልጅ አገኘሁ በነጋም ጊዜ አየሁት እነሆ የወለድሁት ልጄ አይደለም አለች።

ያቺ ሁለተኛዋ ሴትም አይደለም ይህ ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው እንጂ ያንቺ ልጅ አይደለም ያንቺስ የሞተው ነው አለች። በንጉሡም ፊት እንዲህ ተባባሉ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ማስቀደስ እየቻልን ሳናስቀድስ በቤታችን ብንጸልይ ጉዳቱ ምንድን ነው?

“ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳንኼድ በቤታችን ኾነን መጸለይ እንችላለን” የሚ ሉ ሰዎች አሉ፡፡

ሰው ሆይ! ራስህን አታስት! እርግጥ ነው, አንድ ክርስቲያን በቤቱ ውስጥ መጸለይ _ ይችላል፡፡ ነገር ግን _ ጸሎቱ በቤተ ክርስቲያን እንደሚደረገው ጸሎት በፍጹም እኩል አይኾንም፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩት ጸሎት በአንድነት ኾነው የሚያደርሱት እንደዚሁም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው እየጮኹ ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር የሚሰቅሉ ብዙ ሰዎች ናቸውና ያሉት፡፡ ብቻህን በቤትህ ኾነህ የምታደርሰው ጸሎት ከወንድም እኅቶችህ ጋር በአንድ ነት በቤተ ክርስቲያን ኾነህ የምትጸልየውን ያህል በእግዚአብሔር ዘንድ የመሰማት ኃይል የለውምና፡፡ ለምን ቢሉ በቤትህ ውስጥ ካለው ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ከፍ ያለ አንድነት፣ የፍቅር ገመድ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የካህናት ጸሎት አለና፡፡

ካህናት በፊታችን ይቆማሉ፡፡ ስለዚህ የሕዝቡ ጸሎት ደካማ ቢኾን እንኳን ከእነርሱ ኃያል ጸሎት ጋር ይዋሐዳል፣ ወደ ሰማያትም ያርጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከውኅኒ ቤት ነጻ የወጣው በቤተ ክርስቲያን ስለ ተደረገለት ጸሎት ነው፡፡ … እንግዲህ ንገረኝ! የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ለሐዋርያው ጴጥሮስ እንኳን አስፈላጊው ከነበረ፣

እንደዚህ ያለ የእምነት ዓምድ የኾነውን ቅዱስ ከወኅኒ እንዲወጣ ካደረገው ለምን እንደዚህ ያለውን ኃይል ትንቃለህ? ለዚህ የምታመጣው አመክንዮስ እንደ ምን ያለ አመክንዮ ነው?

ሰዎች በአንድነት ኾነው ሲጸልዩ እግዚአብሔር እንዲራራ ምሕረቱም እንዲያበዛ እንደሚያደርጉት እርሱ እግዚአብሔር ራሱ የተናገረውን አድምጥ፤ ለነቢዩ ዮናስ እንዲህ ብሎታልና፡- “ከመቶ ሃያ ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” (ዮና.4፡11)፡፡

የሕዝቡን ቍጥር ጠቅሶ የተናገረው እንዲሁ ለከንቱ አይደለም፤ በአንድነት የሚደርስ ጸሎት እጅግ ኃያል እንደ ኾነ ታውቅ ዘንድ ነው እንጂ።


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዘማሪ አይደፈር ጋሻው
በእለተ ቀኗ ሼር አድርጉት ዝማሬውን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

'ደናግል ሆይ የሰማያዊ አርአያና ምሳሌ የሆነችው የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ። እርሷ ለክርስቶስ እናት ለመሆን በምንም የምታንስ አልነበረችም'

የሚለው ቅዱስ አትናትዮስ ሐዋርያዊ ስለ ድንግሊቱ ህይወት እንዲህ ይላል:-

👉እግዚአብሔርን ዳኛው እንዲሆንላት ትጸልይ ነበር እንጂ በወንዶች መታየትን አትሻም ነበር።

👉ከቤት ለመውጣት አትቸኩልም ነበር።

👉በህዝባዊ ስፍራዎች የሚያውቃት ሰው አልነበረም።

👉ማር እንደምትሠራ ንብ በቤትዋ ውስጥ ብቻ መቆየትን ትመርጥ ነበር።

👉በቤቷ የቀረውን ሁሉ ለድሆች በቸርነት ትሰጥ ነበር።

👉ቃላትዋ ጥንቃቄ የተሞሉ ነበሩ ድምጽዋም የተመጠነ ነበር።

👉 ጮኻ አትናገርም ነበር።

👉ማንም ላይ ክፉ ነገርን አልተናገረችም።
ክፉ ወሬን ለመስማትም አትፈቅድም ነበር'

👉'ተፈሥሒ ፡ባሕታዊት፡ እንተ ፡ኃጣእኪ መምሰለ'

('የሚመስልሽ ያጣሽው ብቸኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ')

👉እያልን የምናመሰግናት ይህቺ ድንግል ከእድሜ አቻዎችዋ በተለየ በፍጹም ጭምትነት የምትኖር ቅድስት ነበረች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዳግመኛም በዚህች ዕለት በቂሣርያው በቅዱስ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ፡- ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም ‹‹የልጆቼ ነው አልሰጥም›› አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡
የእመቤታችን ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ባስልዮስ ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሏም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ የከበረች ሥዕሏ ከተቀመጠበት ምሰሶ ሥር ጸበል ፈለቀና በዚኽም ብዙዎች ተፈወሱ፡፡ ይህም የተፈጸመው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት ዕለት በሰኔ 21 ቀን ነው፡፡ የብርሃን እናቱ የእመቤታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሊቁ አባ ዮሐንስ ዘደማስቆ የገብርኤልን አንደበት እንዲህ አድርጎ ይቃኛል:-

'ገብርኤል በሰማያት እንዲህ አለ:-

👉 በከፍታዎች የሚኖር እርሱ ማንም ሊመረምረው የማይቻለው እርሱ እንዴት ሊወለድ ይችላል?

👉 ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነው እርሱ እንዴት በአንዲት ድንግል ማህፀን ሊወሰን ይችላል?

👉ስድስት ክንፍ ያላቸው ኪሩቤልና ሱራፌል ሊያዩት የማይቻላቸው እርሱ የፍጥረቱን ስጋ ሊለብስ እንደምን ወደደ?

👉እዚህ መቆሜ ስለ ምንድር ነው ወደ ባርያይቱ ሔጄ ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ

👉ንጽህት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ

👉 የሕይወት እናት ሆይ ደስ ይበልሽ ልበላት እንጂ'

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† ✝✝እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝

†††✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝

††† ✝በዓለ ሕንጸታ✝ †††

††† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ) /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::

በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::

በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::

ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: (ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::)

ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::

ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::

እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::

¤ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::

††† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::

††† ሰኔ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
3.ቅዱሳን ሐዋርያት
4.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

††† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ሒዶ ወደ ኢያሪኮ ገባ የዚያች አገር ሰዎችም ጌታችን እነሆ እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት። ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውኃው ምንጭ ጨመረው እንዲህም አላቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ አጣፈጥሁት። ከዚያች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ኤልሳዕ እንደተናገረ ያ ውኃ ጣፋጭ ሆነ።

ከዚያም አገር ወደ ቤተል ወጣ ሲወጣም ከከተማው ሲወጡ ታናናሽ ልጆችን በጎዳና አገኘ እነርሱም አንተ ራሰ በራ ውጣ ውጣ እያሉ ይዘባበቱበት ጀመር። ወደ ኋላው ተመልሶ በአያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ረገማቸው የዚያን ጊዜ ሁለት ድቦች ከዱር ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለት ልጆችን ገደሉ።

ከነቢያት ልጆች አንዲት ሴት ነበረች ወደ ኤልሳዕም ጮኸች ባሪያህ ባሌ ሞተ ባሌ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ ባለዕዳ ሁለቱን ልጆቼን ወስዶ ይገዛቸው ዘንድ መጣ አለችው። ኤልሳዕም አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ በቤትሽስ ምን አለሽ አላት ዘይት ካለበት ማሰሮ በቀር ለእኔ ለባሪያህ ምንም የለኝም አለችው።

ሔደሽ ከጎረቤትሽ ሁሉ የሸክላ ዕቃና ባዶ ዕቃዎችን ተዋሺ አታሳንሺ። ወደ ቤትሽም ገብተሽ በአንቺና በልጆችሽ ላይ ደጁን ዝጊ በዚያ በሸክላ ዕቃም ዘይቱን ገልብጪው የመላውንም አንሥተሽ አኑሪው አላት። እርሷም ወደ ቤቷ ገብታ በልጆቿና በእሷ ደጃፏን ዘጋች እነርሱ ያቀርቡላት ነበር እርሷም እየቀዳች ትገለብጥ ነበር። ከዚህ በኋላ ልጆቿን ዳግመኛ የሸክላ ዕቃ አቅርቡልኝ አለቻቸው የሸክላ ዕቃ ሁሉ አለቀ የለም አሏት ከዚህ በኋላ ያም ዘይት ተገታ።

እርሷም ሒዳ ለእግዚአብሔር ነቢይ ነገረችው አልሳዕም ሒጂ ይህን ዘይት ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈዪ የቀረውን ዘይት ግን የልጆችሽን ሰውነትና ያንቺን ሰውነት አድኚበት አላት።

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ በአንዲቱ ቀን ወደ ሱማን ሔደ በዚያም አገር አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች ወደዚያ ከመሔድ ውሎ አድሮ ነበርና እህል ይበላ ዘንድ አቆመችው። ያቺም ሴት ባሏን እነሆ ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ ቅዱስ ነው ዘወትር በእኛ ዘንድ እያለፈ ይሔዳል። ትንሽ እልፍኝ እንሥራለት አልጋም እንዘርጋለት መብራት የሚበራበት መቅረዝንና ወንበርን ጠረጴዛንም እናዘጋጅለት ወደ እኛም በመጣ ጊዜ በዚያ ይደር አለችው።

ከዚህም በኋላ በአንዲቱ ቀን ወደዚያ ገብቶ በእልፍኙ አደረ። ደቀ መዝሙሩ ግያዝንም ያቺን የሱማን ሴት ጥራት አለውና ጠራት እርሷም መጥታ በኤልሳዕ ፊት ቆመች። እነሆ ይህን ሁሉ ክብር አከበርሽኝ ምን ላድርግልሽ ከንጉሥ ዘንድ ከአለቃም ዘንድ ቢሆን ጉዳይ እንዳለሽ ንገሪኝ በላት አለው እርሷም እኔስ በወገኖቼ መካከል እኖራለሁ አለችው። ምን ላድርግላት አለ ደቀ መዝሙሩ ግያዝም ልጅ የላትም ባሏም ሽማግሌ ነውና የሚታዘንላት ሴት ናት አለው። ደግሞ ጥራት አለው በጠራትም ጊዜ መጥታ በደጃፍ ቆመች። ኤልሳዕም የዛሬ ዓመት እንደዛሬ ልጅ ትወልጃለሽ አላት እኔን አገልጋይህን ጌታዬ አታሰቅቀኝ አለችው።

ከዚህም በኋላ ያቺ ሴት ፀንሳ ኤልሳዕ በነገራት ቀን በዓመቱ ወንድ ልጅን ወለደች። ያም ልጅ አድጎ ከአባቱ ጋራ ወደ አዝመራው መጣ። አባቱን ራሴን ራሴን አለው የሕፃኑም አባት ብላቴናውን ወደ እናቱ አስገባው አለው። ብላቴናውም ያንን ልጅ ወደ እናቱ አስገባው እናቱም እስከ ቀትር በጉልበቷ ላይ አስተኛችው።

ከዚህም በኋላ በሞተ ጊዜ አውጥታ በእግዚአብሔር ነቢይ ዐልጋ ላይ አስተኛችው ዘግታበትም ወጣች። ባሏንም ጠርታ ወደ እግዚአብሔር ነቢይ እሔዳለሁና አንድ አህያና ከብላቴኖች አንድ ብላቴና ስደድልኝ አለችው። ባሏም መባቻ ያይደለ ቅዳሜ ያይደለ ዛሬ ለምን ትሔጃለሽ አላት እጅ እነሣው ዘንድ እሔዳለሁ አለችው። አህያውንም ጫኑላት አገልጋይዋንም ተነሥ እንሒድ ባልኩህ ጊዜ መሔድን አትከልክለኝ ና ተከተለኝና ወደ እግዚአብሔር ነቢይ ወደ ቀርሜሎስ እንሒድ አለችውና ሔደች።

ኤልሳዕም ያቺን ሴት ስትመጣ በአያት ጊዜ ብላቴናው ግያዝን ያቺ ሴት ሱማናዊቷ ሴት ናት። አሁንም ሩጠህ ሒደህ ተቀበላት ደኅና ነሽን ባልሽስ ደኅና ነውን ልጅሽስ ደኅና ነውን በላት አለው እርሷም ደኅና አለችው። ወደ ኤልሳዕም ዘንድ ወደ ተራራው ደርሳ እግሩን ያዘችው ግያዝም ሊከለክላት መጣ ኤልሳዕም ሰውነቷ አዝናለችና ተዋት እግዚአብሔር ግን ነገሩን ሠውሮኛልና አልነገረኝም አለው። አታሰቅቀኝ ያልኩህ አይደለምን በውኑ እኔ ከአንተ ከጌታዬ ልጅን የለመንኩት መለመን አለን አለችው።

አልሳዕም ግያዝን ወገብህን ታጠቅ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሒድ ሰውም ብታገኝ እንዴትነህ አትበለው እንዴት ነህ ቢልህም አትመልስለት በትሬንም በሕፃኑ ግንባር ላይ አስቀምጣት አለው። የዚያም ሕፃን እናት እንዳልተውህ ሕያው እግዚአብሔርን በረከትህን አለችው ኤልሳዕም ተነሥቶ አብሮአት ሔደ። ግያዝም በፊታቸው ይሔድ ነበር ሩጦም ቀደማቸው በትሩንም በዚያ ልጅ ግንባር ላይ ጣላት ነገር ግን አልሰማውም አልተናገረውም ግያዝም ተመልሶ ኤልሳዕን ተቀብሎ ያ ልጅ አልተነሣም አለው።

ኤልሳዕም ወደ ቤት ገብቶ ሕፃኑን ሙቶ በዐልጋ ላይ ተኝቶ አገኘው በሁለታቸውም ላይ ደጃፉን ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ወደ ዐልጋውም ላይ ወጥቶ በዚያ ሕፃን ላይ ተኛ አፉን በአፉ ላይ ዐይኖቹን በዐይኖቹ ላይ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ በላዩ ላይ ተኛ የዚያም ልጅ ሰውነት ሞቀ።

ከዚህ በኋላ ተነሥቶ በቤቱ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ተመላለሰ ዳግመኛም ወጥቶ በዚያ ልጅ ላይ ተኛ እስከ ሰባት ጊዜ እንዲህ አደረገ ከዚያም በኋላ ያ ልጅ ዐይኑን ገለጠ ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ ያቺን ሱማናዊት ሴት ጥራት አለው።

ጠርቷትም ወደርሱ ገባች ኤልሳዕም እነሆ ልጅሽን ውሰጂ አላት እርሷም ከእግሩ ላይ ወድቃ ሰገደችለት ልጅዋንም ይዛ ወጣች። የሶርያ ሰው ንእማንም ወደርሱ በመጣ ጊዜ በዮርዳኖስ ውኃ ከለምጹ አዳነው ንእማንም ብዙ እጅ መንሻ ወርቅና ብር ልብሶችንም አመጣለት ከእርሱም ምንም ምን አልወሰደም።

ደቀ መዝሙሩ ግያዝም ተደፋፍሮ ንእማንን ተከተለው ምክንያትም ፈጥሮ ንእማንን እንዲህ አለው ከኤፍሬም አገር ከነቢያት ልጆች ሁለት ሰዎች መጥተውብኛልና አንድ መክሊት ብርና ሁለት ልብሶች ስጣቸው ብሎሃል አለው ንእማንም ሁለት መክሊቶችንና ሁለት ልብሶችን ሰጠው።

ኤልሳዕም ግያዝ ያደረገውን አውቆ ረገመው የንእማንም ለምጽ ገንዘብ ወዳጅ በሆነው በግያዝ ላይ ተመለሰ። በሰማርያም ረኃብ ጸና ከሶርያ ሰዎች የተነሳ የአህያ መንጋጋ በአምሳ ወቄት ብር እስቲለወጥ ድረስ ኵስሐ ርግብም የድርጎ አራተኛ በአምስት ብር እስቲሸመት ድረስ በሀገራቸው የሶርያ ሰዎች ሰፍረው ተቀመጡ። በዚህ ነቢይ ጸሎትም በአንዲት ቀን ረኃቡ ተለወጠ ጥጋብም ሆነ። በዘመኑም ብዙ ድንቆችና ተአምራቶችን አደረገ በሞተም ጊዜ በመቃብር ውስጥ አኖሩት በዚያም ወራት የሞአብ ሰዎች አገራቸውን ከበቡ። ይቀብሩም ዘንድ ሌላ ሰውን አመጡ አደጋ ጣዮችንም በአዩ ጊዜ የዚያን ሰው ሬሳ በኤልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት የዚያም ሰው ሬሳ በኤልሳዕ ዐፅም ላይ ወረደ የኤልሳዕንም ዐፅም በነካው ጊዜ ያ በድን ድኖ በእግሮቹ ቆመ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ሰኔ 20 ቀንከእመቤታችን ድንግልማርያም ከ33ቱ በዓለት አንዱ ለሆነው
ሕንጸተ ቤተክርስቲያ ለእግዝትነ ማርያም(የእመቤታችን ድንግል ማርያ ቅዳሴ
ቤቷ የከበረበት በዓል ነው እና እንኳን አደረሳችሁ፡፡ ይህ እንዴት ነው ቢሉ፡፡
☞ጌታ በዐረገ በ8ኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆ ጎዳና ኢየሱስ ክርስቶስ
በመብረቅ አስደንግጦ ለምን ታሳድደኛለኽ ሲል ባነገረው መሠረት በ42ዓ/ም
ገደማ በክርስቶስ አምኖና ምርጥ ዕቃ ተብሎ የክርስትና ሃይማኖት ዋና አስተማሪ
ኾነ፡፡
☞ባመነ በ11ዓመቱ እመቤታችን ባረገች በ 4ዓመቱ በ53ዓ/ም በ2ኛው
ሐዋርያዊ ጉዞው ከበርናባስ ጋር የኬልቄዶን ዕጣ በምትኾን በቂሳርያ ወደ
ፊልጵስዪስ ገብተው አሰተማሩ፡፡ ሕዝቦችም አምነው ተጠመቁ፡፡
☞ከእንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትኺዱ አላቸው፡፡ የለመድነውን
ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡ እነሱም ነገሩ ደግ እንደ ኾነ
ዐውቀው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩበት፡፡
☞እሱም ከዮሐንስ ጋራ ነበር፡፡ ዮሐንስም ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምክር
በቀር ምንም የምታደርጉት የለም አላቸው፡፡
☞ሰለዚህ ያመኑትን ይዛችኹ አንድ ሱባዔ ጽሙ፡፡ እኛም እንጾማለን ብለው
ላኩባቸው፡፡ በሱባዔው ማለቂያ ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን
ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስም ጴጥሮስን ለምን እንደ
ሰበሰበን ጠይቀኽ ንገረን አለው፡፡
☞ጴጥሮስም በምሴተ ሐሙስ የጠየኸው አንተ ነኽና ጠይቀው አለው፡፡
☞ዮሐንስም ጌታዬ ስለምን ሰበሰብኸን አለው፡፡
☞ጌታም በእናቴ ስም ቤተክርስቲያን እሰከ አጽናፈ ዓለም እንዲሠራ ፈቃዴ ነውና
አሠራሩን ላሳያችኹ ሥርዐት ላስተምራችሁ ነው አላቸው፡፡
☞ከዚያም ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ድንጋዮች
አቅርቦ ጥቃቅን የነበሩትን ታላቅ አድርጎ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፡፡
☞ከዚህ በኀላ ሥራ ጀመሩ፡፡ እንደ ሰም ለመለመላቸው በእጃቸው ላይ እየተሳበ
ቁመቱን 14 ወርዱ 12 ክንድ አድርገው በሦስት ክፍል ሠርተውለታል በዚች
በሰኔ 20ቀን ሠርተው ጨረሱ፡፡
☞በነጋታው ሠኔ 21 ቀን ሰማያዊ ጽዋዕ እና ሰማያዊ ኅብስት ወረደላቸው፡፡
☞እመቤታችንን ታቦት ሐዋርያትን ልኡካን አድርጎ ጌታ ዐቢይ ካህን ኹኖ ቀድሶ
አቁርቧቸዋል፡፡
☞ጌታም እናንተ ከዛሬ ጀምሮ እንዲህ አድርጉ ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ አርሳይሮስ
ብሎ የዓለም ፖትርያርክ አድርጎ ሾመውና ወደ ሰማይ አረገ፡፡
☞ቤተ መቅደሱ የተሰራበት 3ቱ ድንጋይ የሥላሴ ምሳሌ ነው፡፡
☞ይህም በዓል ከእመቤታችን ከ33በዓላት አንዱ ነው፡፡
☞ጌታም በዚህ ቀን ሥጋዬን ደሜን የተቀበለውን ኅጢአቱን ይቅር እለዋለኹ
ብሎ ለእመቤታችን ቃል ገብቶላታል፡፡
☞የጹሁፍ ምንጭ☞(መድብለ ታሪክ መጽሐፍ )
☞እኛም የስላሴ ህንጻዎች ንስሀ ገብተን ቅዱስ ስጋው ክብሩ ደሙን ተቀብለን
መንግሥቱን ለመውረስ ያብቃን፡፡
☞የጌታ ቸርነት የእናቱ የእናታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞19-10-2015

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዳግመኛም እስኪርዪንን አቀረቡት ዳክስም ለራስህ እዘን በክፉ አሟሟትም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እንዲያሠቃዩት እንዲሰቅሉትና ሥጋውን እንዲሰነጥቁት አዘዘ ወታደሮችም ተረከቡትና በጽኑ ሥቃይ አሠቃዩት በትዕግሥቱም በአሸነፋቸው ጊዜ ለመኰንኑ ነገሩት በረኃብና በጽምዕ ይሞት ዘንድ በግንድ ውስጥ አሥረው በባዶ ቤት እንዲዘጉበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።

ደግመው ዲያቆን ቢልፍዮስን አቀረቡት መኰንን ዳክስም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ አለው ባልሰማውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ ሥጋውን ሠነጣጥቀው በከተማው አደባባይ ጐተቱት እንጨት ተክለውም ቍልቍል ሰቀሉት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ ከሃይማኖቱም ባልተናወጸ ጊዜ በረኃብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስጥ አሥረው በላዩ መዝጊያ ሠርተው ዘጉበት።

በየዕለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ሆነው ይጐበኙት ነበር ጳሔን የተባለው የሰኔ ወር በባተ በሠላሳ ጴጥሮስ ነፍሱን ሰጠ።እርሱንም አውጥተው ደጁን በሌሎቹ ላይ ዘጉ። የከበረ አርጌንዮስም ከአምስት ቀን በኋላ አረፈ እርሱን አውጥተው በቀሩት ላይ ደጁን ዘጉ። ብፁዕ አስኪርዮንም ከዐሥራ ሁለት ቀን በኋላ አረፈ። እርሱንም አውጥተው በቅዱስ ቢልፍዮስ ላይ ደጃፍ ሠርተው ዘጉበት እርሱም የሚያርፍበት ቀን ስትደርስ ወንድሞቼ ታገሡኝ በዚች ሌሊት እወጣለሁና አላቸው። ከዐሥራ ዘጠኝ ቀን በኋላም በዚያች ሌሊት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtube.com/channel/UCAe0Vv9bIkCTTkeilxcUoYQ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አረፈዳችሁ እስኪ ሁላችሁም ቢሆን ይህንን መንፈሳዊ ቻናል እና ሌሎችን ሰብስክራይብ በማድረግ መንፈሳዊ ቻናሎቻን እንዲስፋፉ እናድርግ እንደሆነ ካለን ላይ የሚቀነስብን ነገር የለም።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክርስትያን ነህን?

ወዳጄ ሆይ ክርስቲያን ነህን እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈለገ ግብር አታውለዉ።

እጅን የሰጠህ እንደትሰረቀበት ሳይሆን ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት፣ በጎ ምግባር እንድትሠራበት ለጸሎት እንድትነሳበት፣ የወደቁትን እንድታነሳበት ነው ።

ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬ እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታዳምጥበት ነው።

አንደበትን የሰጠህ እንደትሰድብበትና እንደትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት እንደታመሰግንበት፣ እንድትመክርበት ነው።

እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን ወደ በጎ ስራ እንድትፋጠንበት ነው።

ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው።

ፈቲውን የሰጠህ እንደታመነዘርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው።

ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን እውነትነትን ታውቅበት ዘንድ ነዉ።

ገንዘብና ጉልበትን የሚሰጠን ሰማያዊ ቤታችን እንድንሰራበት ነው።......

እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ንጉሡም ሰይፍን አምጡ ደኅነኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ስጧት አለችው ያቺ ሴት ግን አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእሷም አይሁን አለች።

ንጉሡም መግደልስ አትግደሉት እሱን ለእሷ ስጧት ላለችው ለዚች ሴት ደኅነኛውን ሕፃን ስጧት እርስዋ እናቱ ናትና አለ። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ የፈረደውን ይህን ፍርድ ሰምተው ቅን ፍርድን ይፈርድ ዘንድ የእግዚአብሔር ጥበቡ በሱ ላይ እንዳለ አይተዋልና በንጉሡ ፊት ፈሩ።

ከዚህም በኋላ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዘመን በሆነ ጊዜ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሊያንፅ ጀመረ።

በዐሥራ አንደኛውም ዘመነ መንግሥቱ ወሩ ባዕድ በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱንና ሥርዓቱን ሁሉ ፈጸመ በሰባት ዓመትም ውስጥ ሠራው የራሱንም ቤት በዐሥራ ሦስት ዓመት ሠርቶ ጨረሰ። ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት በሃያ ዘመን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያመጣት ዘንድ ያን ጊዜ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆች የአባቶቻቸውንም ቤት አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው።

የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን በሰባተኛው ወር በጥቅምት ተሰበሰቡ። የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ ካህናቱም ታቦትዋንና የምስክሩን ድንኳን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያለ ንዋየ ቅድሳቱንም ሁሉ ተሸከሙ። ንጉሡና እስራኤል ሁሉ በታቦትዋ ፊት ሥፍር ቍጥር የሌላቸው በጎችና ላሞችን ይሠዉ ነበር። ካህናቱም ታቦቷን ከኪሩቤል ክንፎች በታች በቤቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ቦታዋ አገቧት።

ኪሩቤል በታቦትዋ ቦታ ላይ ክንፋቸውን ጋርደዋልና ኪሩቤልም በስተላይ በኩል በቅድስተ ቅዱሳን ላይ ታቦትዋን ጋርደዋት ነበር። ከቅድስተ ቅዱሳንም ጋራ የተያያዙ ነበሩ። ቅዱሳን ኪሩቤል ከፍ ብለው ከቅድስተ ቅዱሳኑ አንጻር ላይ ሁነው ያያሉ በውጭ ግን አይታይም ነበር። ከግብጽ አገር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ጋራ ቃል ኪዳን ከገባባቸው ሙሴም በዚያ በኮሬብ ከአኖራቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ አልነበረም።

ከዚህ በኋላ ካህናቱ ከቤተ መቅደስ በወጡ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ሁሉ ብርሃን መላው። የእግዚአብሔር ብርሃን በማደሪያው ቤተ መቅደስ መልቷልና ከብርሃኑ መገለጥ የተነሣ ካህናቱ ሥራቸውን መሥራትና ከፊቱ መቆም ተሳናቸው።

ያን ጊዜ ሰሎሞን እግዚአብሔር በደመና ውስጥ እኖራለሁ ብሏል። እኔም ለዘላለም የምትኖርበት ማደሪያህ ቤተ መቅደስን በእውነት ሠራሁልህ አለ። ንጉሡም ፊቱን መልሶ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መረቃቸው ወደ እግዚአብሔርም ረዥም ጸሎትን ጸለየ። ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ልመና ወደ እግዚአብሔር ለምኖ በጨረሰ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ከሰገደበት እጆቹንም ከዘረጋበት ከመሠዊያው ፊት ተነሣ።

ቆሞም የእስራኤልን ማኅበር እንደተናገረው ሁሉ ለወገኖቹ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጣቸው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ብሎ በታላቅ ቃል መረቃቸው። ከዚህ በኋላ ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕትን ሠዉ።

ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት የሠዋቸው ሃያ ሁለት ሽህ ላሞችና አንድ መቶ ሃያ ሽህ በጎች ናቸው ንጉሡ ሰሎሞንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ያንጊዜ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለቤተ መቅደስ ቅዳሴ ቤት አደረጉ።

ቀድሞ በገባዖን እንደታየው ዳግመኛ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ታየው በፊቴ የለመንኸኝ ልመናህንና ጸሎትህን ሰማሁ። እንደ ልመናህም ሁሉ አደረግሁልህ ስሜ በዚያ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖር ዘንድ የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ አከበርሁት ልቡናዬም ዐይኖቼም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ጸንተው ይኖራሉ አለው። ሰሎሞንም አርባ ዘመን ነገሠ ከመንገሡም በፊት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ መላ ዕድሜውም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነበር በሰላም አረፈ።

ይህም ጥበብ የተሰጠው ንጉሥ ሰሎሞን ጥቅም ያላቸው ብዙዎች መጻሕፍትን ደርሶአል። እሊህም ትንቢትና ትምህርት ያለባቸው ምሳሌዎችና መኃልዮች ናቸው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ኖብ

በዚህችም ቀን ደግሞ በክብር ባለቤት ክርስቶስ የታመነ አባ ኖብ አረፈ። ይህም ቅዱስ መነኰስ በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ የሚጋደል ጽሙድ ነበር።

ዲዮቅልጥያኖስም ብዙዎች ሰማዕታትን ሊአሠቃይና ደማቸውን ሊያፈስስ በጀመረ ጊዜ በአንዲት ቀን ሰማንያ ሰማዕታትን አቅርቦ ደማቸውን አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ አባ ኖብን አስታወሱት የእንዴናው ገዥ ወደሆነው ወደ አርያኖስ አቀረቡት። እርሱም ለአማልክት ዕጠን ሠዋ ይህንንም የምንኵስና ልብስ ከላይህ አውጥተህ ጣል አለው።

አባ ኖብም ይህ ሥራ ከቶ ከእኔ ዘንድ አይደረግም የክብር ባለቤት ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስንም አልተውም የረከሱ ጣዖታትንም አላመልክም አለ። መኰንኑም በየራሱ በሆነ ሥቃይ እጅግ አሠቃየው ያም አባ ኖብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ኃይል ታግሦ ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ ወደ አምስቱ አህጉር ሰደደው በዚያም በጉድጓድ ውስጥ ጣሉት በውስጡም ጌታችን ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍቶ ደግ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን እስከሾመው ድረስ ሰባት ዓመት ኖረ።

ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን ሁሉ ፈትተው ወደርሱ እንዲአቀርቧቸውና ከእርሳቸው እንዲባረክ ወደ አገሮች ሁሉ ደብዳቤዎችን ላከ። ለመልእክተኞችም እንዲህ አላቸው ሁሉንም ወደ እኔ ማድረስ ካልተቻላችሁ እጆቻቸውን በራሴ ላይ ጭነው ይባርኩኝ ዘንድ ክብር ያላቸውን ታላላቆችንና መምህራኑን አምጡአቸው።

ከእነርሱም ውስጥ የታወቁ አህናህ ከተባለ አገር አባ ዘካርያስ ከፍዩም መክሲሞስ ከሀገረ ድኂን አጋብዮስ ከሀገረ በላኦስ አባ ኖብ ናቸው የንጉሥ መልእክተኞችም በየአገሮች ሁሉ እየዞሩ የታሠሩ ቅዱሳንን ከእሥር ያወጡአቸው ነበር እነርሱም ደስ ይላቸው ነበር የተመሰገነ እግዚአብሔርንም ያመሰግኑት ነበር ይዘምሩለትም ነበር።

የንጉሥ መልእክተኛም አባ ኖብን ከአምስቱ አገሮች ፈልጎ የአገሩ አንጻር ወደ ሆነች ወደ ሀገረ በሰላ ወሰደው። በዚያም የብረት ልብስ ለብሶ ተቀምጦ ነበር የንጉሡ መልእከተኛም አገኘውና ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ እንዴናውም እስከ ደረሱ በመርከብ ተሳፈሩ ክርስቲያኖችም ተሰበሰቡ ከውስጣቸውም አራት ኤጲስቆጶሳት ነበሩ አባ ኖብንም ያለ ውዴታው ቅስና ሾሙትና የቊርባን ቅዳሴን ቀደሰ።

በቅዳሴውም ፍጻሜ ቅድሳት ለቅዱሳን ብሎ ጮኸ ይህም ማለት ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ከሥጋው ከደሙ ይቀበል ማለት ነው በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ ንስሐ የገቡትን ኃጢአታቸውን ይቅር ሲላቸው አየው ሥጋውንና ደሙንም ከአቀበላቸው በኋላ ወደ ንጉሡ ለመሔድ ተዘጋጁ ቍጥራቸውም ሰባ ሁለት ነበር ሠላሳ ሰባት ሠረገላም አዘጋጅተውላቸው እየአንዳንዳቸው በሠረገላው ተቀመጡ።

በአለፉም ጊዜ የደናግል ገዳማት ካሉበት ደረሱ ደናግሉም ወጥተው ተቀበሏቸው ቍጥራቸው ሰባት መቶ ነበር ከእነርሱ ጋራም እስከሚሰበሰቡ በቅዱሳን ፊት ይዘምሩ ነበር።

ወደ ንጉሡ ከተማም በደረሱ ጊዜ ወደ ንጉሡ ከመግባታቸው በፊት በውኃ ያጥቧቸውና አዳዲስ ልብሶችን ያለብሷቸው ጀመሩ እንዲሁም ለሁሉ አደረጉ ቅዱስ አባ ኖብ ግን አልታጠበም ልብሱንም አልለወጠም ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ድንግልናችሁን ያለጊዜው ያጠፋችሁ ደናግል ሆይ ወዮላችሁ።

የሚያቃጥላችሁ የእሳት ፍም አለና፡፡

ያለጊዜው የሰውን ልጆች ታሳስቱ ዘንድ ጸጉራችሁን የምትታሸሙ (የምትሠሩ) ሴቶች ወዮላችሁ፡፡ እስከ ራስ ጠጉራችሁ የሚበላችሁ የእሳት ፍም አለና፡፡

ልጄ ክርስቶስን የምት ጠሉት (የማትቀበሉ) የቃሉን ትእዛዝም ትምህርቱንም የማትጠብቁ ወዮላችሁ። በኋለኛው ዘመን በሰማይ የእሳት ጎርፍ አለባችሁ፤ ወደ እርሱም ትገባላችሁ፤ በጎስቋሎች ማኀተምም ትዘጋላችሁ፡፡

ሰንበቶቼን የማታከብሩ፣ ቃሌንም የማትሰሙ ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ፡፡ በሰይፌ አጭዳችኋለሁ፤ በመአቴም አፈርድባችኋለሁ፤ ሕማምን፣ ጥፋትን፣ረኀብን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡

እርስ በእርሳችሁም ትተላለቃላችሁ፤ በሚነድድ እሳትም እቀጣችኋለሁ፡፡

ዳግመኛም እግዚአብሔር ቀን በፀሐይ ብርሃን ትሄዳላችሁ፡፡

ዐይኔ የማይመለከታችሁ ይመስላችኋልን?" ነገር ግን ዐይኔ ያያችኋል ጆሮዬም ይሰማችኋል፡፡

ከእጆቼ የምታመልጡበት የላችሁምና። ወደ ተራሮች፣ ወደ ኮረብቶች፣ ወደ ጉድጓዶች፣ ወደ ፍርኩታዎች፣ ወደ ሳሮች፣ ወደ ጫካዎች ብትሸሹም ከእጄ የምታመልጡበት መንገድ የለም፡፡

እኔ ድህነትንም ሀብትንም እሰጣለሁ፤ እኔ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፡፡ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፡፡ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፡፡ “ትሑታን፣ የዋኀን፣ ሰላምን ደኅንነትን የሚያደርጉ ከእኔ ጋር ለዘለዓለሙ ይኖራሉ" አለ፡፡

ርቱዓ ሃይማኖት ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†††✝ እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †††

†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ✝ቅዱስ ዻውሎስ የዋህ ✝†††

††† በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ዻውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ዻውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

የዋህ ዻውሊ ከሕጻንነቱ ጀምሮ መጻሕፍትን የተማረ: ግን ደግሞ ትዕቢት: ቁጣና ቂምን የማያውቅ ገራገር ሰው ነው:: እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ ቤተሰቦቹ ሚስት አግባ አሉት:: እርሱ ባያስብበትም ወገኖቹን ላለማሳዘን አገባ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ያገባት ሴት በጣም ቆንጆ በዚያም ላይ ክፉ ነበረች:: የዋህ ዻውሊ ክፋቷን ሁሉ ታግሶ ለበርካታ ዓመታት አብሮ ኖረ:: ልጆችንም አፈሩ::

አሁንም ግን እርሷ ከክፋቷ ልትታገስ አልቻለችም:: ይባስ ብሎ ዻውሊ በሌለበት ከሌሎች ወንዶች ጋር ትዘሙት ያዘች:: የዋሁ ሰው ይሕንኑ ያውቃል ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ዝም ብሎ በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ለነገሩስ እሱ ያርሳል: ይቆፍራል: ነዳያንን ያበላል: እንግዳ ይቀበላል እንጂ ክፋትን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም::

አንድ ቀን ግን ለሥራ ወደ በርሃ ወጥቶ አንድ ግሩም ዜና ሰማ:: "አባ እንጦንስ ምንኩስና የሚባል ሕይወተ መላእክትን ጀምሯል: ደቀ መዛሙርትንም ይቀበላል" አሉት:: ግን ሚስትና ልጆች አሉትና ምን ያደርጋል?

የዋህ ዻውሊ ሙሉ ቀን ሢሠራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን የጠበቀው ሌላ ነው:: ሚስቱ በራሱ መኝታ ላይ ከአገልጋይ እረኛው ጋር ራቁታቸውን አገኛቸው:: ልብ በሉልኝ በትክሻው ሞፈርና ምሳር: መጥረቢያም ይዟል:: እርሱ ግን ክፉን አላሰበም:: ጥሩ ልብስ አንስቶ ሁለቱንም አለበሳቸው::
እንዲሕም አላቸው:- "ከዚሕ በሁዋላ እኔ አልመለስም:: ሀብት ንብረቴን ውረሱ: በደስታም ኑሩ:: የልጆቼን ነገር ግን አደራ" ብሏቸው ተነሳ::

በእጁ ምንም አልያዘም:: በትከሻው ያለችውን ብጣሽ ጨርቅ ይዞ ወደ በርሀ ተጉዋዘ:: አባ እንጦንስም ተቀብለው አስተምረው አመነኮሱት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ራስን ዝቅ በማድረግ: በመታዘዝ አገለገለ:: ጾም: ጸሎትና ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት::

እያለ እያለ ከብቅዐት ማዕርግ ደረሰ:: ምዕመናንም ሆነ መነኮሳት ሊጠይቁት ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይመለከት ነበርና ስለነሱ ሲያለቅስ ቅንድቡ ተላጠ:: ሰውነቱም አለቀ:: አንድ ቀን ጋኔን የያዘውን ሰው ፈውስ ብለው አመጡለት:: እርሱ ግን በአጋንንት ላይ ሥልጣን እያለው በትሕትና ተጠግቶ ጋኔኑን "አባ እንጦንስን ከምጠራብህ ቀስ ብለህ ውጣ" አለው:: ጋኔኑ ግን የፈራው መስሎት በትዕቢት "እንጦንስ ማነው?"አለው::

ያን ጊዜ የዋህ ዻውሊ እንደ እሳት ከጋለ ድንጋይ ላይ ቁሞ "ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው:: ይሕ ጋኔን ካልወጣ አልወርድም" አለ:: ወዲያው በዘንዶ አምሳል ከሴትዮዋ ወጥቶ እየጮኸ ወደ ቀይ ባሕር ገባ::ቅዱስ ዻውሊ የዋሕም እንዲሕ በቅድስና ተመላልሶ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

" የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር: ደስታ: ሰላም: ትእግስት: ቸርነት: በጐነት: እምነት: የውሃት: ራስን መግዛት ነው:: እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም:: የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ::" (ገላ. 5:22)

††† ሰኔ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ
2.ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ (ሰማዕታት)
3.ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት (እናታቸው)
4.አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ (ሰማዕታት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
††† አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን: በጐነትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: †††

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ ፳፩/21 [በዓለ እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ ወጢሞቴዎስ ወተዝካረ ተአምር ዘቶማስ ወአባ ከላድያኖስ]

#የዕለቱ_ግጻዌ

✞ ምስባክ ዘነግህ
ወንሰግድ ውስተ መካን ኃበ ቆመ እግረ እግዚእነ።
ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ።
አንተ ወታቦተ መቅደስከ፣
ትርጉም:-
እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።
አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥
አንተና የመቅደስህ ታቦት።
(መዝሙር ፻፴፩ ÷ ፯ /131÷7)

✝ ወንጌል ዘነግህ
ሉቃስ ፩ ÷ ፴፱ - ፶፯ /1÷39-57
፴፱
ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥

ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
፵፩
ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
፵፪
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
፵፫
የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
፵፬
እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
፵፭
ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
፵፮
ማርያምም እንዲህ አለች።
፵፯
ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
፵፰
የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
፵፱
ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።

ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
፶፩
በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
፶፪
ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
፶፫
የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
፶፬-፶፭
ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
፶፮
ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።

✞ መልእክታት፦
፩. ኤፌሶን ፪፥፲፫-ፍጻሜ /2፥13-ፍጻሜ
፪. ፩ኛ ጴጥ ፪፥፬-፲፩ /2፥4-11
፫. የሐዋ/ሥራ ፩፥፲፪-፲፭ /1፥12-15

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል÷
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሐወክ÷
ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ።
ትርጉም:-
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።
(መዝሙር ፵፭ ፣ ፬-፭ /45÷4-5)

✝. ወንጌል ዘቅዳሴ
ማቴዎስ ፲፮ ÷ ፲፫ - ፳ /16÷13-20
፲፫
ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
፲፬
እነርሱም። አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
፲፭
እርሱም። እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
፲፮
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
፲፯
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
፲፰
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
፲፱
የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

+ ቅዳሴ - ዘእግዚእነ (ነአኲተከ)

የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከተ ልመናዋና አማላጅነቷ አይለየን። አሜን!
______________________

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 21-ለአዳም ዘር ሁሉ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ከተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ከነገረችው በኋላ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገች፡፡
+ አስቀድሞ ከከሃዲውና ከጨካኑ መኮንን ከአርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ አንዱ የነበረው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጢሞቴዎስ ተጋድሎውን በድል ፈጸመ፡፡
+ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረዷት ሴት ላይ ላደረገው ታላቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ፡፡
+ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ያጠመቀውና በኋላም ዲቁናና ቅስና የሾመው አባ ከላድያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም አባ ሜልዮስ ባረፈ ጊዜ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 4ኛ የሆነ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፡- ይህም ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከምስር የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ እርሱም አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ጣዖትን እንዲያመልክ የሚያዝ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ በግዛቱ ሁሉ በተነበበ ጊዜ ይህ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን የአዋጅ ደብዳቤ ቀደደው፡፡ ደብዳቤውን ከቀደደው በኋላ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ‹‹ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም›› ብሎ መሰከረ፡፡
የንጉሡ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል የሆነው መኰንን ይህንን የቅዱስ ጢሞቲዎስን ድፍረት በተመለከተ ጊዜ ይዞ ክፉኛ አስደበደበው፡፡ ዳግመኛም ሰውነቱ ሁሉ እስኪደቅ ድረስ እንዲደበድቡት አዘዘ ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ ፈውሰው፡፡ ከሥቃዩም ድኖ ፍጹም ጤነኛ ሆኖ አደረና በቀጣዩ ቀን ወደ መኰንኑ ቀርቦ አሁንም በድጋሚ ‹‹ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ ሰውነቱንም በመጋዝ ቆራርጦና ሰነጣጥቆ ሰቀለው፡፡ በብረት ምጣድም አድርጎ ሥጋው እንደ ሰም እስኪቀልጥ ድረስ በእሳት አበሰለው፡፡ ከከተማ ውጪም አውጥቶ ጣለው፡፡ አሁንም ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ ፈወሰውና ወደ መኰንኑ ተመልሶ ሄዶ ‹‹ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ ድጋሚ መሰከረ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው በዙያው የነበሩ በጣም ብዙ አሕዛብ በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀዳጅ አደረገው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + +
የእመቤታችን ዓመታዊ በዓልና በዓለም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ስለመታነጻቸው፡- ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጲስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፡፡
እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና በርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው፡፡ አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ፡፡ ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ፡፡
ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታነጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው፡፡ ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው፡፡ የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት፡፡›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14፡፡ እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡ እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡ ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፡፡ እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸው ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር፡፡
ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ያዕቆብ ዘስሩግ እንዲህ ሲል ይዘመራል:-

'በተባረከው ማሕፀንሽ ውስጥ የእሳት ነበልባል አደረ፤ ሱራፌል ይህን ነበልባል ቢያዩት ይንቀጠቀጣሉ።

አለማትን ያበጃጀው ህያው እሳት በአንቺ ውስጥ ተዳፈነ።

ይህ እሳት የጣዖት አምልኮን የሚያጠፋ 9 ወር የተከደነ እሳት ነው።

በምድር ሁሉ የበቀሉትን እሾኾች ሊያጠፋ የሚቻለው እሳት በማህፀንሽ ውስጥ ሞላ'

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይህም ነቢይ በአራት ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ እሊህም ኢዮራም፣ አካዝያስ፣ ኢዩና፣ ዮአስ ናቸው የትንቢቱም ዘመን ከሀምሳ ዓመት በላይ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ከመምጣቱ አስቀድሞ ትንቢት ተናገረ ከዚህ በኋላም በሰለም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ ልመናዋ በረከቷም ወንዶችና ሴቶች ባሮቿ ከሆን ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር፣ በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ በዚች ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው፣ ከገልገላ አውራጃ አለሙት ከምትባል ቦታ የሆነው የሳፋጥ ልጅ #ታላቁ_ነቢይ_ኤልሳዕ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)

ሰኔ ሃያ በዚች ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው። አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው። አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው። የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው። ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ። ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው። ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች። ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ። ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው። ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው። ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ። ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ። ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል። በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው። ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል። ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው። የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት። ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት።›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14። እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው።

ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ። እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ።

ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል። በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል። ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም። እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸውን ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር።

ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት። ሐዋ 20፡28። በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰው ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል። ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነብዩ_ኤልሳዕ

በዚህችም ዕለት ከገልገላ አውራጃ አለሙት ከምትባል ቦታ የሆነው የሳፋጥ ልጅ ታላቁ ነቢይ ኤልሳዕ አረፈ። የዚህም ነቢይ መጠራቱ እንዲህ ኾነ ኤልያስ አልፎ ሲሔድ የሳፋጥ ልጅ ኤልሳዕን በፊቱ ዐሥራ ሁለት ጥምድ አስጠምዶ ሲያሳርስ አገኘው እርሱም በነዚያ የተሾመ ነበር ኤልያስም ሔዶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት።

ኤልሳዕም ጥማዱን ትቶ ኤልያስን ተከተለው ኤልሳዕም አባቴ እወድሃለሁ አንተንም እከተላሉሁ አለው ኤልያስም ብላቴናዬ አድርጌሃለሁና ተመለስ አለው። እርሱም ኤልያስን ከመከተል ተመለሰ ዐሥራ ሁለቱንም ጥምድ በሬዎች ወስዶ አረደ በላመ ፈጅ ጋኖችም ቀቅሎ ለሕዝቡ አቀረበላቸው እነርሱም በሉ ኤልያስንም ተከትሎት ሔደ ብላቴናውም ሆነ።

ብዙ ዘመናትም ሲያገለግለው ኖረ። ኤልያስም በሚያርግበት ጊዜ ኤልሳዕን ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ አለው ኤልሳዕም በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ሆኖ ይደርብኝ አለው።

ኤልያስም ኤልሳዕን ድንቅ ነገርን ለመንከኝ ነገር ግን ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ብታየኝ ይደርብህ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ባታየኝ ግን አይሆንልህም አለው።

ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ፈረስና የእሳት ሠረገላ መጣ ወደ መካከላቸውም ገብቶ አራራቃቸው ኤልያስም በመነዋወጥና በጥቅል ነፋስ እንደዚህ ወደ ሰማይ ዐረገ። ኤልሳዕም አይቶ የእስራኤል ኃይላቸውና ጽንዓታቸው አባ አባ ብሎ ጮኸ። ከዚህ በኋላም ዳግመኛ አላየውም ልብሶቹንም ከሁለት አድርጎ ከፈላቸው። ኤልያስም ለኤልሳዕ መጠምጠሚያውን ጣለለት በኤልሳዕ ራስ ላይም ወረደ ኤልሳዕም ተመልሶ በዮርዳኖስ ባሕር ዳር ቆመ። በራሱ ላይ የወረደች የኤልያስንም መጠምጠሚያ ይዞ ውኃውን መታባት ውኃውም አልተከፈለም የኤልያስ ፈጣሪ ወዴት ነው ይህስ እንዴት ነው አለ ከዚህ በኋላም ውኃውን መታው ውኃውም ተከፍሎ ወዲያና ወዲህ ቆመ ኤልሳዕም ተሻገረ።

በዚህም ኤልሳዕ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በዕጥፍ እንደተቀበለ ታወቀ። ኤልያስ የወንዙን ውኃ እንድ ጊዜ ከፈለ። ኤልሳዕ ግን ሁለት ጊዜ ከፈለ ኤልያስ አንድ ምውት አስነሣ ኤልሳዕ ግን ሁለት ምውት አስነሣ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የቆብ አባት ድሜጥሮስም እንዲህ ያመሰግናታል:-

ሰማይ ታላቅ ነው ቢሉ ካንችጋር አይተካከልም ሰማይንና ምድርን የሞላው በማህፀንሽ ሞልቷልና።

ሰዎች ከአንቺ ይልቅ ምድርን ታላቅ ናት ቢሉኝ ምድርም የእግሩ መረገጫ ብቻ ናት እላቸዋለሁ።

'የኖህ መርከብ ነሽ' ይሉሻል ፤ የኖህመርከብ ግን ያዳነችው ኖህን እና ቤተሰቦቹ ነው። በአንች ግን ዓለም ዳነ።

ታቦት ነሽ ይሉሻል። ታቦቱ የያዘው በእግዚኣብሄር ጣቶች የተጻፉ ሁለት ጽላትን ነበር።

አንች ግን የአለማትን ጌታ በኃይሉ ቃል ፀነስሽው'።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ሰኔ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን #ሐዲስ_ጊዮርጊስ ሰማዕት ሆነ፣ ሰማዕት በመሆን #አባ_ብሶይ_አኖብ አረፈ፣ አምስቱ #ቅዱሳን_አርሶፎኒስ_ጴጥሮስ_አስኪርዩን_አርጌንዮስና_ቢልፍዮስ በሰማዕትነት ሞቱ

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሐዲስ_ጊዮርጊስ_ሰማዕት

ሰኔ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ሐዲስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ሆነ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስላም ነበር ከግብጽ ደቡብ ድምራ ከሚባል አገር ክርስቲያን ሴት አግብቶ ከእርሷም ሦስት ልጆችን ወለደ ከሦስቱም አንዱ ይህ ቅዱስ ነው።

ከእናቱም ጋራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔድ ነበር ቅዱስ ቍርባንንም ይቀበል ዘንድ እናቱን ለመናት እርሷም ማንም የክርስትናን ጥምቀት ሳይጠመቅና ንጹሕ ሳይሆን ቍርባን ሊቀበል አይችልም አለችው።

ከዚህ በኋላም ከተረፈ መሥዋዕቱ ሰጠችው በጎረሳትም ጊዜ ጣዕሟ በአፉ ውስጥ እንደ ማር ሆነ የዚች የቁራሿ ጣዕም በአፌ ውስጥ እንዲህ የሆነ የዋናው የቍርባኑ ኅብስት ጣዕም ምን ያህል ይሆን ብሎ በልቡ አሰበ ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ።

በአደገም ጊዜ ክርስቲያን ሴት አገባ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ መፈለጉንም ነገራት እርሷም ወደ ሌላ ሀገር ሒዶ የክርስትናን ጥምቀት እንዲጠመቅ መከረችው እርሱም ወደ ሌላ አገር ሔዶ ተጠመቀ ስሙንም ለውጦ ጊዮርጊስ ተባለ። እስላሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ከዚያም አምልጦ ላፍጥ ወደሚባል አገር ሸሸ በዚያም ሦስት ዓመት ኖረ።

ወሬውም በተገለጠ ጊዜ ቀጡር ወደ ሚባል አገር ሒዶ የልዳዊው ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገሩ ድምራ ተመለሰ እስላሞችም ሰሙ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት የመኰንኑም ሚስት ክርስቲያን ነበረች ለመኰንኑም አታሠቃየው አለችው መኰንኑም አሥሮ በወህኒ ቤት ዘጋበት።

እስላሞችም ተሰበሰቡ የወህኒ ቤቱንም ደጅ ሰብረው ታላቅ ግርፋት ገረፉት አካላቱንም ቆራርጠው በሕይወትና በሞት መካከል ጣሉት ። ሲነጋም ክርስቲያኖች የሞተ መስሏቸዋልና ሊቀብሩት መጡ ነገር ግን በሕይወት አገኙት።

ከዚህም በኋላ እስላሞች ተሰብስበው ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኛ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተን እንገድልሃለን አሉት የመዛሕዝም ልጅ የከበረ ጊዮርጊስም ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም የፈለጋችሁትን አድርጉ አላቸው። እጅግም ተቆጡ በመርከብ ምሰሶ ላይም ሰቅለው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት መኰንኑም ከስቅላት አውርደው በእሥር ቤት እንዲአሥሩት አዘዘ እንደዚሁም አደረጉ።

ሚስቱም ታጽናናውና እንዲታገሥ ታደርገው ነበር ሰይጣንም እንዳያስተውና የደከመበትን ዋጋ እንዳያጣ በልቡ ወደ ክርስቶስ ያስብ ዘንድ ትመክረው ነበር። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና አረጋጋው አበረታታውም ከሰማዕታትም ጋራ እንደ ተቈጠረ በማግሥቱም ራሱን በሰይፍ እንደሚቆርጡት ነገረው። በነጋም ጊዜ እስላሞች ወደ መኰንኑ ተሰብስብው ጊዮርጊስን ይሰጣቸው ዘንድ ፈለጉ መኰንኑም የወደዱትን ያደርጉበት ዘንድ እንዲሰጧቸው አዘዘ።

ከዚህም በኋላ ከእሥር ቤት አወጡት ድምራ በምትባል አገር በከበረ የመላእክት አለቃ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ከዚህ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሌሊት በሥጋው ላይ እሳትን አነደዱ እሳቱም በላዩ እየነደደ ምንም ምን አልነካውም ወስደውም በገቢያ ውስጥ ጣሉት ከዚያም አንሥተው በባሕር ውስጥ ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ ደሴቱ ወደብ ዳር ደረሰ እናቱም ጠብቃው ነበረና ወስዳ ገነዘችው ለጥቂት ወራትም በቤቷ ውስጥ ሸሸገችው።

ከዚህም በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅና ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ብሶይ_አኖብ

ዳግመኛም በዚች ዕለት ሰማዕት በመሆን አባ ብሶይ አኖብ አረፈ፡፡ ትርጓሜውም የጠራ ወርቅ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ ከድምያጥ አውራጃ ስሟ ባኖስ ከሚባል አገር ከአቅራብ መኰንን ከቆጵርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ ከከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ልጆች ወገን ነበር።በዚህም ቅዱስ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። ቅዱሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊቱ ታመነ።

ወደ አንዴናውም ወሰዱት በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁሞ በጌታችን ታመነ አርያኖስም በእርሱ ላይ ተቆጣ ለአማልክትም ሠዋ አለው አልታዘዘለትም ሥቃዩንም አልፈራም መኰንኑም ወስዶ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ ወደሚገድሉበት ቦታም ሊወስዱት አወጡት ብዙ ሕዝብም ይከተሉት ነበር እነሆ ከዚያም የአርያኖስ መኰንን አንበሶች ነበሩ። የሚጠብቃቸውም ሰው ነበር እነርሱም በብረት ሰንሰለት ታሥረው ነበር ከእነርሱም አንዱ አንበሳ የብረት ሰንሰለቱን በጥሶ ሩጦ ወደ ቅዱሱ ደረሰ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱሱን በአንበሳው ጀርባ ላይ አወጣውና ዐይነ ፀሐይ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሰው በረረበት ቅዱሱ ግን ዐይኑን ሸፍኖ ስለ ነበረ ወዴት እንዳለ አላወቀም በዚያም ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_አርሶፎኒስ_ጴጥሮስ_አስኪርዩን_አርጌንዮስና_ቢልፍዮስ

በዚችም ቀን አምስት ጭፍሮች በሰማዕትነት ሞቱ እሊህም አርሶፎኒስ፣ ጴጥሮስ፣ አስኪርዩን፣ አርጌንዮስና ቢልፍዮስ በዲዮስጲልዪስም ቅጽር ውስጥ ይኖሩ ነበር። መኰንኑም ለጣዖታት እንዲሠዉ በአስገደዳቸው ጊዜ እኛስ የንጉሣችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ እንፈጽማለን ለእርሱም እንሠዋለን አሉት መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ በአንድ ቤት ውስጥም እንዲዘጉባቸውና እስከ ሁለት ቀን እህል ውኃ እንዳይሰጧቸው አዘዘ።

ከዚያም በኋላ እንዲያመጧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ ለአማልክት ሠዉ አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል እኛስ ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ እንሠዋለን ለረከሱ አጋንንት ግን አንሠዋም አሉት። አንገታቸውንም አሥረው ወደ ሌላ አገር ይወስዱአቸው ዘንድ አዘዘ።አርጌንዮስም ወንድሞቹን እኔ እውነትን እነግራችኋለሁ የእግዚአብሔር መልአክ አምስታችንንም በስማችን ሲጠራን ሰምቼዋለሁና አላቸው።

ዳክስ ወደሚባል መኰንንም በአደረሷቸው ጊዜ መኰንኑ አስቀድሞ አርሶፎኒስን ወስዶ ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ በአለውም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው በከተማ ውስጥ እንዲጐትቱትና እንዲአዞሩት አዘዘ። በመለሱትም ጊዜ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ፊቱን እንዲአጠወልጉት አዘዘ ሁለተኛም እስከ ሚጨነቅ ድረስ በሠረገላ ውስጥ አሥረው ቍልቍል ሰቀሉት ሃይማኖቱንም ጠብቆ ክብር ይግባውና ለጌታችን ነፍሱን ሰጠ።

ሁለተኛም ጴጥሮስን አቀረቡት ዳክስም ለአማልክት ሠዋ አለው ትእዛዙንም ባልተቀበለው ጊዜ እንዲአሠቃዩትና እንጨት ተክለው ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሁለተኛም ምድሩን ቆፍረው ከትከሻው በታች ቀብረው በቅሎዎችን በላዩ እንዲነዱበት አዘዘ ይህንንም እግዚአብሔር እየረዳው ታገሠ ከጉድጓዱም በእወጡት ጊዜ ከሥቃዩ ብዛት የተነሣ ሥጋው ጠወለገ መናገርም ተሣነው በግንድ ውስጥም አሥረው ጣሉት ።

ከዚህም በኋላ አርጌንዮስን እቀረቡት ዳክስም ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ያለ መብልና መጠጥም በተበሳ ግንድ ውስጥ አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክርስትያን ነህን?

ወዳጄ ሆይ ክርስቲያን ነህን እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈለገ ግብር አታውለዉ።

እጅን የሰጠህ እንደትሰረቀበት ሳይሆን ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት፣ በጎ ምግባር እንድትሠራበት ለጸሎት እንድትነሳበት፣ የወደቁትን እንድታነሳበት ነው ።

ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬ እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታዳምጥበት ነው።

አንደበትን የሰጠህ እንደትሰድብበትና እንደትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት እንደታመሰግንበት፣ እንድትመክርበት ነው።

እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን ወደ በጎ ስራ እንድትፋጠንበት ነው።

ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው።

ፈቲውን የሰጠህ እንደታመነዘርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው።

ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን እውነትነትን ታውቅበት ዘንድ ነዉ።

ገንዘብና ጉልበትን የሚሰጠን ሰማያዊ ቤታችን እንድንሰራበት ነው።......

እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝✝ እንኩዋን ለሐዲስ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝

✝ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ ✝

=>ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በሁዋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ (ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::

+እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው::

+እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::

+ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው::
ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::

+አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በሁዋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ:: አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::

+ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው #መንፈስ_ቅዱስ አናግሯቸው "#ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::

+በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: (እንዲሕ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው!!!)

+ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን #ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::

+በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::

=>ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

=>ሰኔ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት
2.አባ ብሶይ አኖብ ሰማዕት (በአንበሳ ጀርባ ላይ የተቀመጠ አባት)
3.ቅዱሳን "5ቱ" ጭፍሮች (በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች)
4.አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

=>+"+ ስለዚሕ #ወንድሞቼ_ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: +"+ (1ቆሮ. 10:14-18)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት አባ ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ድምያኖስ †††

††† አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር::

አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል::

በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው::

የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ::

የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል::

ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል::

ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ::
1.ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል::

2.በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር (በመልዕክት) አስተምረዋል::

3.በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል::

4.ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር (መልዕክት) በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል::

ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል::

††† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን::

††† ሰኔ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ

††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. ፳፥፳፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እኛም የበደሉልልን ይቅር እንደምንል
አቤቱ ይቅር በለን


ይህ የአባታችን ሆይ ፀሎታችን ነው

ቅዱስ ኤፍሬም ❤️እንድንማር የሚያስተምረን ይህ ነው።


በዚህ አለም ሳለን እርስ በርሳችን የማንዋ ወደድ ከሆነ ከባድ ይሆንብናል።

ከጠላቶቻችን ጋር ፈጥነን የማንታረቅ ከሆነ ያ አስቀየምናቸውንም ወገኖች ይቅርታቸውን የማናገኝ ከሆነ አንዱ ሌላውን የሚኮንን ከሆነ ይቅርም ካላልነው ችግር ይፈጥርብናል።

በሚመጣውም ዓለም ዘላለማዊ ህይወትን አናገኝም።

ሰማያዊዉ አባታችን ኃጢአታችንን ይቅር አይለንም።


ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ❤️

Читать полностью…
Subscribe to a channel