kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

፲፱ እ እሱም ጥቂት ቆዩ እሰጣችሁአለሁ አላቸውና ሕፃኑንም በትከሻው ተሸክሞ አምጥቶ ቀድሞ በታየውና የልጁንም መወለድ በነገረው በም ሥዋዑ ላይ አስቀመጠው።

፳ ፥ በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ገብርኤል መጣና በክንፉ ተሸክሞ ጲግ ወደምትባል ወደሲና

በርሃ ወሰደው።

፳፩ ሕፃኑም ይህ መልአክ ከአራዊት አፍ እየጠበቀው አደገ እኛን ከሚገፋን ጠላታቹ እንዲሁ ያድነን ሰውነታችንንም ከጠላታችን ከሰይጣን ወጥመድ ይጠብቅልን።

♥️ ፳፪ እሱ እንደ አንበሳ እያናሩ ከእኛ የሚውጠውኃ ያሻልና የጸሉቱ ኃይል #በጥምቀት_የተወልድን_ሁላችንንም_ይጠብቀን_አሜን።🌹♥️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹♥️ #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሀይማኖትና_አቡነ_ኤወስጣቴዎስ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮዽያ ታሪክ ዕንቁ ሓዋርያት፣ የሀይማኖት አርበኛ ከዋክብት ናቸው።

ኢትዮዽያዊው ሐዋርያ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው። አባታችን አቡነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ተወልደው ያደጉት በኤርትራ ክፍለ ሀገር ውስጥ ነው። አባታችን በ፲፪፷፭ ዓ/ም ገደማ ከአባታቸው ክርስቶስ ሞዓና ከእናታቸው ሥነ ሕይወት ተወለዱ። የጻድቁ የመጀመሪያ ስም "ማዕቀበ እግዚእ (ለጌታ የተጠበቀ) ነበር። ኤዎስጣቴዎስ የተባሉት በኋላ ነው። (አቡነ ተክለ ሀይማኖት የመጀመርያ ስም ፍስሃ ጽዮን እንደ ነበር ልብ ይለዋል)።

አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ገና ከልጅነታቸው መንፈሰ እግዚአብሔር ያደረባቸው ስለሆኑ ለዚህ ዓለም ግድ አልነበራቸውም። ከቤተ ክርስቲያን መገብት መምህራን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምረው ዲቁና ተቀብለው በነቅንነትና በቅድስና ሲያገለግሉ አበው ደግማዊ እስጢፋኖስ ብለው ይጠሩአቸው ነበር። ጻድቁ ገና በወጣትነት እድሜአቸው ምናኔን መርጠው፡ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ይተጉ ጀመር። እንዲህ ባለ ሕይወት ሳሉ አንድ ቀን ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ መጣ። በዘባነ ኪሩብ፡ በግርማ ቢያዩት ደነገጡ። ጌታ ግን ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ገና ከእናትህ ማሕጸን መርጬሃለሁ። ከኢትዮዽያ እስከ አርማንያም ሐዋርያ ትሆን ዘንድ ሹሜሃለሁ። ሐዋርያው ቅ/ ጳውሎስን ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ብሎ በጠራው አጠራር ጠራቸው። የሐዋ. ፱፥ ፲፭። ዘኪያከ ሰምዐ ኪያየ ሰምዐ (አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ አለ ብሏቸው ባርኩዋቸው ዐረገ። የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል እንዲል ሉቃ. ፲፥ ፲፯።

ጻድቁ አባታችን ስለ ቸር ስጦታው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ቅስናን ተቀብለው እንደ ሐዋርያት ቅዱስ ወንጌልን መስተማር ጀመሩ። ስም ዝናቸው ፈጥኖ በመላ ሀገሪቱ ተሰማ። በየቦታው እየተዘዋወዞሩ አሕዛብን አሳምነው እያጠመቁ፣ ያመነውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እያጸኑ፣ ገዳማው ሕይወትን እያስፋፉ ኖሩ። በታላቁ ገዳማቸው በርካታ አርድእትን አስተምረው አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ አባታችን ቀደሚት ሰንበት ልክ እንደ ሰንበት ክርስቲያን (እሁድ ሰንበት) እንዲትከበር እስከ ስደት ድረስ ከፍተኛ ተገድሎ አድርገዋል። ዓላማቸውንም ኣሰክተዋል።

በመጨረሻ ሕይወታቸውም በገዳማቸው ላይ ደቀ መዝሙራቸው አባ አብሳዲን ሹመው ለአዲስ በወቅቱ በነበረው ችግር ለስደት ተነሱ። ልጆቻቸው በገደማቸው እንዲጸነ መክረው ተወሰኑትን አስከትለው ወደ አርማንያ ተጓዙ። በመንገድም ወደ ባሕረ ኢያሪኮ ሲደርሱ የሚሻገሩበት መርከብ አጡ። ድንቅ አባት ናቸውና በእምነት አጽፋቸውን (መጎናጸፊያቸውን አውልቀው ባሕሩ ላይ ጣሉት። በትእምርተ መስቀል አማትበው ተቀመጡበት። ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው መጎናጸፊያ ላይ ከበው ተቀመጡ። ከሰማይም ጌታችን ወርዶ በመካከላቸው ቆመ። ቅ/ሚካኤል በቀኝ ቅ/ገብርኤልም በግራ ቆሙ። ጻድቁ ደግሞ ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው ይተረጉሙላቸውም ጀመሩ። በመካከል ግን አንዱ ደቀ መዝሙራቸው (የማነ ብርሃን የተባለ) በቅኔ ቤት በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጥሞ ሞተ። ጻድቁ አባታችን ከሰጠመበት አውጥተው ከሞት አስነስተውታል። በዚህም ምክንያት "ዘአደወ ባሕረ'' (ማዕበልን የተሻገረ) ተብለዋል። አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ለዘመናት ቅ/ወንጌልን ሰብከው፣ ሕይወተ ገዳምን አስፋፍተው፣ ብዙ ተአምራትን ሠርተው ከዚህ ዓለም በክብር አልፈዋል።

🌹♥️ #የቅዱሳን_አባቶቻችን_በረከታቸው_ይደርብን🌹🌹

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ማርያም ብፅዕት ነሽ❤ በዘማሪት ሰላማዊት አዲሱ
➤ግጥም እና ዜማ /ዲ/ን መርሐ ጽድቅ/መሳይ ቢቂላ።
በቅርብ ቀን ➤በዘማህደር ሚዲያ➤ የቴሌግራም ቻናል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከይቅርታ ጋር የመስቀሉን ታሪክ የሚነግረኝ አለ ካላስቸገርኩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወንድሞች ልመርቃችሁ
ሱሪ ሳይሆን ረዥም ቀሚስ የምትለብስ፥ ሜካፕ የማትቀባ፥ ሰውነቷን ያልተበሳሳች ወይም ሰውነቷን ወንፊት ያላደረገች፥ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ጉባኤ የምትሄድ፥ ውስኪ ሳይሆን የቅዳሴ ጠበል የምትጠጣ፥ ስጋወደሙን የምትቀበል፥ ተሳዳቢ ሳይሆን መራቂ የሆነች ቤተሰቧን አክባሪና ታዛዥ፥ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በምታደርገው እንቅስቃሴና ንግግር ራሷን ያላረከሰች እጮኛ ይስጣችሁ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/DjBm_Zw_1ZM?si=RaujjO9FC617HwwA

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ዓመታዊ የተዓምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

"በዛቲ ዕለት #እግዚአብሔር ገብረ: በእደ ባስልዮስ መንክረ::"
(በዚህች ዕለት እግዚአብሔር በባስልዮስ እጅ ድንቅን አደረገ)

††† ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ †††

††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ #አርእስተ_ሊቃውንት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ነው:: አባቱ #ኤስድሮስ(ባስልዮስ የሚሉ አሉ): እናቱ ደግሞ #ኤሚሊያ ይባላሉ:: ባልና ሚስት ከተቀደሰ ትዳራቸው 5 ወንድና 1 ሴት ልጅን አፍርተዋል:: የሚገርመው ሴቷ ( #ቅድስት_ማቅሪና) ገዳማዊት ስትሆን 5ቱም ወንዶች ዻዻሳት መሆናቸው ነው::

የሁሉ የበላይ የሆነው ግን ቅዱስ ባስልዮስ ነው:: አባቶቻችን እንዳስተማሩን ቅዱሱ ሊቅ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ነው:: #ቅዱስ_ኤፍሬም ሶርያዊንም ያስተማረው እርሱ ነው:: ነገር ግን ቅርብ ጊዜ ከድረ ገጾች (websites) እየገለበጡ የሚጽፉ አንዳንድ ወንድሞች ይህንን የሚያፋልስ ነገር ጽፈው ተመልክተናል::

††† ቅዱስ ባስልዮስ
ገዳማዊ ጻድቅ:
ባለ ብዙ ምሥጢር ሊቅ:
የብዙ ምዕመናን አባት:
የቂሣርያ ሊቀ ዻዻሳት:
ባለ ብዙ ተአምራትና ከከዊነ እሳት (ከፍጹምነት) የደረሰ አባት ነው:: ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳያንን ሆስፒታል በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ያስገነባ እርሱ ነው::

እጅግ ብዙ ድርሰቶች አሉት:: መጽሐፈ ቅዳሴንም ዛሬ በምናውቀው መንገድ ያሰናሰለው እርሱ ነው:: ለምዕመናን የሚጠቅሙ ብዙ ሥርዓቶችን ሠርቶ: የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተርጉሟል:: ታዲያ ይህ ሊቅ: ቅዱስና ጻድቅ ሰው ብዙ ድንቆችን ሠርቷል:: ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዛሬ ይህኛውን ታስባለች::

በዘመኑ እዚያው #ቂሣርያ ውስጥ አንድ አገልጋይ (በዘመኑ አጠራር ባሪያ) ነበር:: የሚሠራው ደግሞ በሃገረ ገዥው ግቢ ውስጥ ነው:: ለሥራ ሲገባ የሰውየውን አንዲት ብቸኛ ልጅ ተመለከታት:: ቆንጆ ነበረችና በፍትወት ተለከፈ:: ጧት ማታ ሥራው እሷን ማየት ሆነ::

እንዳይጠይቃት ደረጃው አይመጥንምና ከባድ ፍርድ ይጠብቀዋል:: ነገሮች ከአቅሙ በላይ ሲሆኑበት በቀደመ ስሕተቱ ላይ ሌላ ከባድ ስሕተትን ጨመረ:: ወደ ጠንቅዋይ (መተተኛ) ቤት ሒዶ ሥራይ እንዲደረግለት ጠየቀ:: መተተኛው ግን "ይህንን ማድረግ የሚችል ሰይጣን ብቻ ስለሆነ ካልፈራህ ወደ እርሱ ልላክህ" አለው::

ያ ከንቱ ሰው "እሺ" አለ:: መተተኛው ቀጠለ "በል! ሌሊት 6 ሰዓት ሲሆን ወደ አሕዛብ መቃብር ሒድና ግራ እጅህን ወደ ላይ ዘርጋ:: ከዛ ይመጣልሃል" ብሎ ላከው:: አገልጋዩም የተባለውን ሲያደርግ ከአጋንንት አንዱ መጥቶ: ነጥቆ ወደ ጥልቁ: የሰይጣኖች አለቃ ወደ ሚገኝበት ወሰደው::

ጋኔኑ ሰውየውን አለው:- "አንተ የፈለከው እንዲፈጸም መጀመሪያ ክርስትናህን ካድ:: በክርታስም ላይ ክህደትህን ጽፈህ በፊርማህ ስጠኝ" አለው:: ያ ልቡ የታወረ ሰው እንደተባለው መጽሐፈ ክህደቱን ለሰይጣን ሰጠ:: ወዲያው ያ ያመጣው ወደ ቤቱ መለሰው::

በማግስቱ ጠዋት በሃገረ ገዥው ቤት ታላቅ ግርግር ሆነ:: ልጃቸው "ያን አገልጋይ ካላጋባችሁኝ ራሴን አጠፋለሁ" አለች:: ቢለምኗትም ልትሰማ አልቻለችም:: ወላጆቿ ግራ ስለተጋቡ ከምትሞት ብለው እያዘኑ ልጃቸውን ከአጋንንት ጋር ለተዛመደ ሰው ሰጡ::

እነርሱ ተጋብተው ኑሯቸውን ቀጠሉ:: ወላጆች ግን የአንድ ልጃቸውን ነገር እንዲህ በዋዛ ሊተውት አልወደዱምና ጾሙ: ጸለዩ: ተማለሉ:: በእንዲህ ሁኔታ ብዙ ዓመታት አለፉ:: ወላጆቿ ግን ተስፋ አልቆረጡምና እግዚአብሔር ሰይጣን የቀማትን ማስተዋል መለሰላት::

አንድ ቀንም ባሏን ጠርታ " #ቤተ_ክርስቲያን ተሳልመህ: ቆርበህ : ስመ እግዚአብሔር ጠርተህ: አማትበህስ ታውቃለህ?" አለችው:: እርሱም "በጭራሽ አላውቅም" አላት:: "ለምን?" ብትለው የሆነውን ነገር ሁሉ ዘርዝሮ ነገራት:: በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ምድር ከዳት::

ለረዥም ሰዓት አለቀሰች:: ከሰይጣን ጋር ተጋብታ የኖረች ያህል ስታስበው አንገፈገፋት:: ሰውነቷ ተስፋ ቆረጠ:: ወዲያው ግን በህሊናዋ አንድ ሐሳብ መጣላት:: "ያ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ከሰይጣን ባርነት ሊገላግለኝ ይቻለዋል" አለች:: ፈጥናም ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ሒዳ ከእግሩ ሥር ወድቃ አለቀሰች::

እርሱም "ልጄ ሆይ! አይዞሽ: በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ቀላል ነው:: ሒጂና ባልሺን አምጪው" አላት:: ሒዳ አመጣችው:: ቅዱሱም ያን ሰው "መዳን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰውየው መልሶ "ያቺን ደብዳቤ መመለስ የሚቻል ቢሆንማ እፈልግ ነበር" አለው:: ቅዱስ ባስልዮስም ሴቷን "ሒጂና ጸልይ: ከ40 ቀን በሁዋላ ትመጫለሽ" ብሎ አሰናበታት::

በሰይጣን ባርነት የተያዘውን ያን ሰው ግን ወደ ራሱ በዓት ወስዶ አስገባውና በ4 አቅጣጫ በመስቀል አተመው:: ትንሽ ምግብ ሰጥቶት "ከ3 ቀን በሁዋላ እመጣለሁ" ብሎት ሔደ:: ቅዱሱ ያለ ዕረፍት ይጋደልም ጀመር:: በ3ኛው ቀን መጥቶ "እንዴት ነህ?" አለው:: "አባቴ! አጋንንት አሰቃዩኝ" አለው:: "አይዞህ!" ብሎት ወጣ::

በ6ኛው ቀን መጥቶ "አሁንስ?" አለው:: "አባ! ስቃዩ ቀረልኝ: ግን ደብዳቤዋን እያሳዩ ያስፈራሩኛል" አለው:: "በርታ" ብሎት ሔደ:: በ9ኛው ቀን ተመልሶ "ደግሞ አሁንሳ?" አለው:: "አባቴ! ምስጋና ለፈጣሪህ! ከአካባቢው እየራቁ ነው" አለው::

እንዲህ በ3: በ3 ቀናት እየተመላለሰ ለ13 ጊዜ ጠየቀው:: በ39ኛው ቀን መጥቶ "ዛሬ ምን አየህ" ቢለው "አባ! አጋንንትን ከእግርህ በታች ስትረግጣቸው አየሁ" አለው:: ቅዱስ ባስልዮስ በ40ኛው ቀን ደወል ደውሎ መነኮሳት: ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ: ያን ሰው ከመሃል አቁሞ: "እግዚኦ በሉ" አላቸው::

ሕዝቡ እግዚኦታውን ሲፈጽሙ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ:: ቀና ሲሉ ያቺ የክህደት ደብዳቤ ሁሉ እያዩአት ከመካከላቸው ወደቀች:: በዚያች ቦታም ታላቅ እልልታና ሐሴት ተደረገ:: ቅዱሱ በጸሎቱ ለ40 ቀናት ከእንቅልፍና ከምግብ ተከልክሎ ያቺን ነፍስ ማረከ::

የሕዝቡንም ሃይማኖት አጸና:: በዚያውም ቅዳሴ ቀድሶ ሕዝቡን አቁርቦ አሰናበታቸው:: ባልና ሚስቱንም ባርኮ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ አሰናበታቸው:: ታላቁ ሊቅም ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 6 ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱስ ባስልዮስ እኛንም ከኃጢአት ማሠሪያ ፈትቶ ከአጋንንት ሤራ ይሰውረን:: ከሊቁም በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
2.አባ ይስሐቅ ባሕታዊ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† "እውነት እውነት እላቹሃለሁ:: በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል:: ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል:: እኔ ወደ አብ እሔዳለሁና:: አብም ስለ #ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ:: ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ::" †††
(ዮሐ. 14:12)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንት ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኤፌሶን †††

††† ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ያከበሩትን: እርሱም ያከበራቸውን ሰዎች 'ቅዱሳን' ትላለች:: ራሱ ባለቤቱ "ኩኑ ቅዱሳነ እስመ ቅዱስ አነ-እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" ብሏልና:: (ዼጥ. 1:15) እነዚህንም ቅዱሳን 'መላእክት: አበወ ብሊት: ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ጻድቃን: ሊቃውንት: ደናግል: መነኮሳት: ባሕታውያን' ወዘተ. ብለን: ክፍለ ዘመን ሰጥተን በአበው ሥርዓት እናስባለን::

ከእነዚህ ቅዱሳን መካከልም አንዱንና ትልቁን ቦታ ቅዱሳን ሊቃውንት ይወስዳሉ:: 'ሊቅ' ማለት 'ምሑር: የተማረ: ያመሰጠረ: ያራቀቀ: የተፈላሰፈ: በእውቀቱ የበለጠ: የበላይ: መሪ: ሹም: ዳኛ' . . . ወዘተ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል::

ወንጌል ላይም ጌታችን መድኃኔ ዓለም ኒቆዲሞስን "አንተ ሊቆሙ ለእሥራኤል-አንተ የእሥራኤል መምሕር (አለቃ) ነህ" ብሎታል:: (ዮሐ. 3:10) ስለዚህም 'ሊቃውንት' ማለት በእውቀት ከሁሉ በላይ የሆኑ እንደ ማለት ነው::

ዘመነ ሊቃውንት ተብሎ የሚታወቀው ከ3ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 6ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ያለው ሲሆን በዚህ ዘመን እንደ እንቁ ያበሩ: ብርሃንነታቸው በሰው ፊት የበራ ብዙ አበው ተነስተዋል:: ቅዱሳን ሊቃውንት ከሌሎች ምሑራን ቢያንስ በእነዚህ ነገሮች ይለያሉ:-
1.እንደ ማንኛውም ሰው ከተማሩ በኋላ እውቀቱ ይባረክላቸው ዘንድ ጠዋት ማታ በጾምና በጸሎት ይጋደላሉ::
2.አብዛኞቹ ቅዱሳን ሊቃውንት ገዳማዊ ሕይወትን ጠንቅቀው ያውቃሉ::
3.ምሥጢር ቢሰወርባቸው ሱባኤ ይገባሉ እንጂ በደማዊ ጭንቅላት አይፈላሰፉም::
4.ፍጹም መናንያን በመሆናቸው ሃብተ መንፈስ ቅዱስ እንጂ የሚቀይሩት ልብስ እንኳ የላቸውም::
5.እያንዳንዷን የመጽሐፍ ቃል ከማስተማራቸው በፊት በተግባር ይኖሯታል::
6.እረኞች ናቸውና ዘወትር ለመንጋው ይራራሉ::
7.ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ግፍን ተቀብለዋል::
8.በኃይለ አጋንንት የመጡ መ* ና.* ፍ*. *ቃንን ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ለብሰው: መጻሕፍትን አልበው: ጥቅስ ጠቅሰው መክተዋል::
9.ምግብናቸውንም ፈጽመው ዛሬ በገነት ሐሴትን ያደርጋሉ::

††† የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምትቀበላቸው የቅዱሳን ጉባኤያት 3 ብቻ ናቸው::
1ኛ.በ325 (318) ዓ/ም በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ያደረጉትን
2ኛ.በ381 (373) ዓ/ም በቁስጥንጥንያ 150ው ሊቃውንት ያደረጉትን: እንዲሁም
3ኛ.በ431 (424) ዓ/ም በዚህች ቀን 200ው ሊቃውንት ያደረጓቸውን ጉባኤያት ትቀበላለች::
ይሕስ እንደ ምን ነውቢሉ:-
በወቅቱ ስመ ክፉ መ* ና* ፍ* ቅ* ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን 2 አካል: ባሕርይ ነው (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት)

ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ::

ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም በኤፌሶን ከተማ የመ***ና****ፍ*****ቃ***ኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 ቅዱሳን ሊቃውንት ተገኙ::

የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በኋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር(ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: ድንግል ማርያምም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::

የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::

ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም "ታኦዶኮስ (የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን የአምላክ እናት: ዘላለማዊት ድንግል: ፍጽምት: ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::

ጉባዔው ከተጠናቀቀ በኋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::

እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሂዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::

††† አምላከ ሊቃውንት ዛሬም ያሉንን አባቶች ይጠብቅልን: ያንቃልን:: ከቅዱሳን ሊቃውንት በረከትም አይለየን:: የእመ ብርሃን ፍቅሯንም ያሳድርብን::

††† መስከረም 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 200ው ሊቃውንት (በኤፌሶን የተሰበሰቡ)
2.ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
3.ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ
4.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
6.ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. ፳፥፳፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
C^O~h]5;j=>9B/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
zBW{"1sP

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
U{!pMMZrU;

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝️ የመስቀል መዝሙሮች ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውብ እና ማራኪ
ለስጦታ የሚሆኑ
ተገጣጣሚ ፍሪሞች
ይደውሉ ያሉበት እናደርሳለን
0963343853

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት እና ቅድስት ታኦድራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ፋሲለደስ ነው:: እንዲያውም ለዘመነ ሰማዕታት መሪና አስተማሪ እርሱ ነበር::
እስኪ በጥቂቱ ነገሩን ከሥሩ እንመልከተው::
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ (3ቱም): አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::

ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ /ሞተ/::

የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::

በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::

ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::

ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ከሃዲውም ይህንን ሲያይ የልብ ልብ ተሰማው:: ከድሮ ያሰበውንና ክርስቲያኖችን የማጥፋቱን እቅድ ሊፈጽም ምክንያት አገኘ::

አባ አጋግዮስ በሚባል መነኩሴ ምክንያት "አብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ: አብያተ ጣዖታት ይትረኀዋ-ቤተክርስቲያኖች ይዘጉ: ቤተ ጣዖቶችም ይከፈቱ" አለ:: አዽሎን: አርዳሚስ የሚባሉ ጣዖቶችንም አቆመ::

በዚህ አዋጅ ምክንያትም የክርስቲያኖች ሰቆቃ ጀመረ::
*ምድር በደም ታጠበች::
*ቅዱሳኑ ቀባሪ አጡ::
*እኩሉ ተገደለ: እኩሉ ተቃጠለ: እኩሉ ታሠረ: እኩሉም ተሰደደ:: በዚህ ጊዜ 'መራሔ ትሩፋት' ቅዱስ ፋሲለደስ ለሰማዕትነት ይበቁ ዘንድ ስለ ራሱና ስለ ወገኖቹ ጸለየ::
ቅዱስ ሚካኤልም በግርማ ወርዶ ቅዱሱን ወደ ሰማይ አወጣው:: ከቅዱሳን ጋር በገነት አስተዋውቆት: ክብረ ሰማዕታትን አሳይቶት: ከጌታ ዘንድ አስባርኮት: ከሕይወት ውሃ ምንጭም አጥምቆ መለሰው::ቅዱስ ፋሲለደስም ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ በንጉሡ ፊት ቆመ::

ንጉሡ ፈራ: እርሱ ግን በፈጣሪው ስም መሞት እንደሚፈልግ ነገረው:: ሊያባብለው ሞከረ: አልተሳካም እንጂ:: ከዚያም አስሮ ወደ አፍራቅያ (አፍሪካ) ላከው:: መጽሩስ የሚባል መኮንንም ቅዱሱን አሰቃየው::

እርሱ የሁሉ የበላይ ሲሆን ስለ ክርስቶስ ሁሉን ተወ:: አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት: በምጣድ ላይ ጠበሱት: አበራዩት: በወፍጮም ፈጩት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሁሉን ታገሰ:: ሁለት ጊዜ ገድለውት ከሞት ተነሳ:: በተአምራቱ ምክንያትም ከከተማው ሕዝብ ግማሹ ያህል ከአሕዛባዊነት ተመልሶ ሰማዕት ሆነ::

በመጨረሻም በዚህ ዕለት አንገቱን ሲቆርጡት ደምና ወተት ፈሶታል:: መላእክትም እርሱን ለመቀበል ዐየሩን ሞልተውታል:: ከልዑላኑ ወገንም የቅዱስ ፋሲለደስን ሚስትና ልጆችንጨምሮ አንድም የተረፈ የለም:: ሁሉም በሰማዕትነት አልፈዋል::

††† እናታችን ቅድስት ታኦድራ †††

††† ይህች ቅድስት እናታችን የትእግስት እመቤት ናት:: ትእግስቷ: ደግነቷ ፈጽሞ ይደነቃል:: ታሪኳ ደግሞ በሆነ መንገድ ከቅድስት እንባ መሪና ጋር ይገናኛል::

ቅድስት ታኦድራ ግብጻዊት ስትሆን ተወልዳ ያደገችው በእስክንድርያ ነው:: ከሕጻንነቷ ጀምራ ቅን ነበረች:: ምንም እንኳ የምናኔ ሰው ብትሆንም ወላጆቿ ያመጡላትን ባል 'እሺ' ብላ አገባች:: ለተወሰነ ጊዜም በሥጋ ወደሙ ተወስነው ከባሏ ጋር በሥርዓቱ ኖሩ::

ለቤተ ክርስቲያን ከነበራት ፍቅር የተነሳ ጠዋት ማታ ትገሰግስ ነበር:: አንድ ቀን ግን መንገድ ላይ የሆነ ፈተና ጠበቃት::ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ተግባር ይፈልጋት የነበረ አንድ ጐረምሳ ድንገት ያዛት:: ታገለችው: ግን ከአቅሟ በላይ ነበር:: ጮኸች:የሚሰማትም አልነበረም:: ሰውየው የሚፈልገውን ፈጽሞ: ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ይህንን መቻል ለአንዲት ንጽሕት ወጣት ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ መረዳቱ አይከብድም::

እጅግ መጥፎ ሰው: በቀለኛም ለመሆን ከዚህ በላይ ምክንያት አይኖርም:: ቅድስቷ ግን ከወደቀችበት ተነስታ መሪር እንባን አለቀሰች:: ሕመሟን ችላ ወደ ቤቷ ላትመለስ ወደ በርሃ ተጓዘች:: ወደ ገዳም ገብታ በወንድ ስም 'አባ ቴዎድሮስ' ተብላ መነኮሰች:: በአካባቢው የሴቶች ገዳም አልነበረም::

የሚገርመው በገዳም ውስጥ ሆና ያንን ጨካኝ ሰው ይቅር አለችው:: ቀጥላም ስለ እርሱ ኃጢአት ንስሃን ወስዳ ከባዱን ቀኖና ተሸከመችለት:: ይሔ ነው እንግዲህ ሕይወተ ቅዱሳን ማለት: ራስን አሳልፎ ለጠላት መስጠት:: (ዮሐ. 15:13) ፈተናዋ ግን ቀጠለ::

ወንድ መስለዋት 'በአካባቢው ከምትገኝ ሴት ጸንሰሻል' ብለው ከገዳም አባረሯት:: ያልወለደቺውንም ልጅ ታሳድግ ዘንድ ሰጧት:: አሁንም በአኮቴት ተቀብላ ለ7 ዓመታት በደረቅ በርሃ ተሰቃየች:: ልጁንም አሳደገች:: ከዚያም ከባድ ንስሃ ሰጥተው ተቀበሏት:: ቅድስት ታኦድራ እንዲህ ስትጋደል ኑራ በዚህች ቀን ዐርፋለች:: በዕረፍቷም ቀን ክብሯ ተገልጧል::

††† ቸር አምላክ የቅዱሳኑን ትእግስትና መንኖ ጥሪት አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† መስከረም 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
2.ቅድስት ታኦድራ እናታችን
3.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ሐዋርያዊ (ሐዋ. 10ን ያንብቡ)
4.ቅድስት በነፍዝዝ ሰማዕት
5."3ቱ" ገበሬዎች ሰማዕታት (ሱርስ: አጤኬዎስና መስተሐድራ)

✝ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጎች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/XAGRrK3DZGI?si=VHtGEk87qMha4sfn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♥️🌹 #እንኳን_አደረሳችኹ🌹♥️

🌹♥️ #አንድ_አምላክ_በሚሆን_በአብና_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስም_ስም_አምነን_መለየት_በእንድነት_አንድነትም_በመለየት_ከዓለም_አስቀድሞ_በሦስትነቱ_የነበረ።♥️🌹

፪፤ ሰማይን በከዋክብት የጋረደው ምድርንም ልምላሚዎችን አብቅሎ የሚአለብሳት መሠረቷን በንፋስ አውታር ያጸናው።

፫ የተዋረደውን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ደኃውንም የሚያበለጽግ ከኛ ዘንድ ለሱ ምስጋና

የሚገባው ለኛም ከእሱ ይቅርታ መለመን የሚገባን።

፩፡ በመስከረም ፲፱ ቀን የሚነበብ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን ይህ ነው እንላለን ልመናው ከአገልጋዩ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

፭፤ ከአብያ ቤት ከሚያገለግሉት ወገን የሚሆን ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር ሚስቱም ከአሮን ወገን ናት ። ስሟም ኤልሳቤጥ ይባላል

፮፤ ሁለቱም ደጋጎች ነበሩ በእግዚአብሔር በፍጹም ትእዛዙ በሕጉም ጸንተው ይኖሩ ነበር።

፯ ንጹሖች ነበሩ ልጅ አልነበራቸውም ኤልሳቤጥ መካን ነበረችና በዕድሜአቸውም አርጅተው ነበር። ዘካርያስ ልጅ ስጠኝ እያለ ወደ እግዚአብሔር ሲለምን ይኖር ነበር። ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ካህናቱ እንደ ደለመዱት በሰሞኑ የክህነት ሥራ በሚሠራበት ጊዜ።

፰ የሚያጥንበት ጊዜ ደርሶ ወደቤተ መቅደስ ገባ ሕዝቡም ዕጣን በሚያጥንበት ጊዜ በውጭ

ሁነው በሙሉ ይጸልዩ ነበር።

፱ የአግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ ምሥዋዕ በቀኝ በኩል ታየው ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ

መፍራትና መንቀጥቀጥም አደረበት መልአኩም ለዘካርያስ ጸሎተህ ተሰምቷልና አይዞህ

አትፍራ አለው።

፲ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ደስ የምትሰኝበትም ስለሆነ ስሙን ዮሐንስ ትለዋለህ።

፲፩፤ በተወለደም ጊዜ ብዙ ሰዎች ደስ ይላቸዋል በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ይሆናልና። ፲፪፤ የሚያሰክር ወይንም አይጠጣም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ይመላበታልና።

፲፫፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካቸው ይመልሳቸዋል ወድፊትም በመንፈስ ቅዱስ ይቃኛል በኤልያስም ኃይል ይጓዛል።

፲፬፤ ዘካርያስም ለመልአክ ይህ ነገር እንዲደረግ በምን አውቀዋለሁ እኔ ሽማግሌ ነኝ የሚስቴም የሕፃንነቷ ወራት አልፏል አለው።

፲፭ መልአኩም ይኸን የምሥራች እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ የተላክሁ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም እኔ ገብርኤል ነኝ ብሎ መለሰለት

፲፮፤ ይህ እስኪፈጸም ድረስ ድዳ ሁነህ መናገር ይሳንሀል በጊዜው የሚፈጸመውን ነገሬን አለ

መንከኝምና እንዲሁም ድዳ ሆኖ ኖረ።

፲፯፤ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ የዚህ የካህን ልብ የመልአኩን ቃል ለምን ተጠራጠረ ከሽማግሌ ከአብርሃም የይስሐቅን መወለድ የሚናገር የኦሪትን መጽሐፍ ሲያውቅ በእምነት በመጽናቱ ዕድሜው መቶ ዓመት ከሆነ በኋላ ሚስቱም ፈጽማ አርጅታ ሳለ እንድትወልድ የሚናገር ኦሪትን የአሕዛብ ሐዋርያ የሚሆን ነገሩ የሚያስደስት ጳውሎስ እንደተናገረ ሽማግሌ መሆኑን ሲያውቅ አብርሃም አመነ እንጅ አልተጠራጠረም ብሎ እንደተናገረ ሙቀት ልምላሜ ተለይቶት እንዳለ እያወቀ ዕድሜው መቶ ዘመን ነበርና ሣራም ሙቀት ልምላሜ እንደተለያት እያወቀ።

፲፰፤ እግዚአብሔር የነገረውን ተስፋ ይቀራል ብሎ አልተጠራጠረም። ዳግመኛም ልጅህን ይስሐቅን ሠዋልኝ ብሎ በነገረው ጊዜ ከይስሐቅ ስም የሚያስጠራ ልጅ ይወለድልሐል ብሎ ከነገረው በኋላ ተጠራጥሮ ለመሠዋት ቸል አላለም።

፲፱፤ ይስሐቅን ይሠዋው ዘንድ በልቡ ቆረጠ እንጅ ከዚህም አንቀጽ በሌላ ቦታ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ እንዲያስነሣለት አምኖ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋው ወሰደው። ሰዋልኝ ብሎ ለፈተና በነገረው ጊዜ ተስፋ ያናገረለትን እሱን ለመሠዋት አቀረበው እግዚአብሔር እሱን ማስነሣት እንዲቻለው አምኖ።
🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️
🌹♥️🌹♥️🌹♥️ #ምዕራፍ_፪♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️
♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️🌹♥️
፩ ዳግመኛ ሐዋርያ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል አባታችን አብርሃም በሥራው የከበረ አይደለምን ልጁን ይስሐቅን ወደ ምሥዋዑ ባቀረበው ጊዜ።

፪ በልቡ የተጠራጠረ ይህ ካህን የሕዝብ መሪ ተብሏል ። በካህን መመራትን የሚሹ ወገኖቹን ልባቸውን እንደምን ያጠራጥረው ይሆን።

፫ አስቀድሞ ልጅ የከለከለው ኋላም ሊሰጠው የወደደው መንሣት የሚቻለው ሊሰጠው የወደደ

እግዚአብሔር አንድ አይደለምን አሁንስ መስጠት አይችልምን? እግዚአብሔር የወደደውን

ሁሉ ማድረግ ይችላል መግደልና ማዳን መግረፍና ይቅር ማለት ማዋረድና ማክበር ይችላል። ፬ ወደቀደመ ነገራችን እንመለስ ከዚህ በኋላ ሚስቱ ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች።

፭ በስምንተኛው ቀን ዘመዶቿ እናቱን የልጁን ስም ማን ተብሎ ይጠራ ብለው ጠየቋት። እሷም ምንአልባት መናገር ይችል እንደሆነ አባቱን ጠይቁት አለቻቸው።

፮ በጠየቁትም ጊዜ የሚጽፍበት ብራና ይሰጡት ዘንድ በእጁ ጠቅሶ አሳያቸው የሚጽፍበት ብራናም በሰጡት ጊዜ አንደበቱ ፈቶለት ዮሐንስ ሲባል ብሎ ተናገረ።

፯ ዳግመኛም የቀድሞውን በማስተዋል አሁን የምንነግራችሁን ስሙ። በውሣጣዊ አሳባችሁም

አስተያየት የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን የተወደደ ዜናውን ተመልከቱ። እጅግ

የሚወደድ የሚለምኑትንም የሚጎበኛቸው።

፰፤ ከነገሩም መልካምነት (ጣፋጭነት) የተነሣ ሊጠገብ የማይቻል የነፍስና የሥጋ ጥቅም ነውና ። በመታገሣችን የመጻሕፍትንም ቃል በማመናችን ተስፋችንን እናገኝ ዘንድ የተጻፈው ሁሉ ለኛ ምክርና ተግሣፅ ተጻፈ ብሎ አመስጋኝ ጳውሎስ እንደተናገረ።

፱ የዘካርያስን ልጅ ዮሐንስን ወደምድረ በዳ ነጥቆ እንደወሰደው ነስሑ እያለ በማስተማር ለእስራኤል እስኪገለጥ ድረስም እየጎበኘው እንደኖረ መንግሥተ ሰማያት ልትሰጥ ቀርባለች እያለ እስኪያስተምር ሲጐበኘው እንደኖረ ሰምተናል።

፲፤ የነገሩ ምክንያት ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከማርያም ከተወለደ ጀምሮ

ሁለት ዓመት ከሆነው በኋላ የጥበብ ሰዎች ኮከብ እየመራቸው ከምሥራቅ መጡ። ያንንም

ኮከብ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ይመራው ነበር።

፲፩ ፣ የተወለደው የዓለም መድኃኒት ንጉሥ ወዴት አለ እያሉ ከፈረስና ከሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ።

፲፪ ይኸንም በሰማ ጊዜ ሄሮድስ ደነገጠ ።፡የጥበብ ሰዎችንም የአመጣጣቸውን ነገር በቆይታ ጠየቃቸው የመጡበትም ምክንያት ስለተወለደው ንጉሥ መሆኑን ነገሩት።

፲፫ ሄሮድስም እኔም መጥቸ እሰግድለታለሁና ተመልሳችሁ ንገሩኝ አላቸው።

፲፬ ከዚህም በኋላ ሄዱ ከዋሻውም በደረሱ ጊዜ ያኮከብ እየመሪቸው መሄዱን ትቶ በመካከላቸው ቆመ።

፲፭ ወደዋሻውም በገቡ ጊዜ ዮሴፍንና ሕፃኑን ከእናቱ ጋር አገኙዋቸው።

፲፭ ወደዋሻውም በገቡ ጊዜ ዮሴፍንና ሕፃኑን ከእናቱ ጋር አገኙዋቸው።

፲፮ ሰገዱለት እጅ መንሻ አድርገው ወርቅና ከርቤ ዕጣን ገበሩለት። ወርቁን ስለመንግሥቱ ዕጣኑን ስለ አምላክነቱ ከርቤውንም የእኛን ነፍስ ምረት ለማጥፋት ስለእኛ በፈቃዱ ስለተቀ በለው ስለ ሞቱ መሪርነት።

፲፯፤ ወደቀድሞ ነገራችን እንመለስ ከዚህ በኋላ የምሥጢር መልአክ ገብርኤልም በዚች ሌሊት ተገልጾላቸው። በሌላ ጐዳና እንዲሄዱ እንጂ ወደሄሮድስ እንዳይመለሱ ነገራቸው። በሌላ ጐዳና ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

፲፰፤ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ተቁጣና የሁለት ዓመት ከዚያም የሚያንስ ዕድሜ ያላቸውን ሕፃናት ፍጁ ብሎ አዘዛቸው። የታዘዙ ጭፍሮችም ሂደው ልጅህን ስጠን እንግደለው አሉት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለአበው #ቅዱሳን_ኤዎስጣቴዎስ_አኖሬዎስና_ማር_ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ማር_ያዕቆብ_ግብጻዊ +"+

=>በግብጽ ገዳማት ውስጥ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተነስተው ካበሩ ቅዱሳን አንዱ ማር ያዕቆብ ነው:: ቅዱሱ ከተባረከ ቤተሰብ ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ ገና በልጅነቱ ከመምሕሩ ጋር መንኗል:: ከገድሉ ጽናት የተነሳ ሰይጣን በግልጽ ይፈታተነው ነበር::

+በተለይ ለ7 ዓመታት ያህል ይደበድበው: መሬት ላይ ይጐትተው: በጥፊ ይመታው ነበር:: እርሱ ግን በጸሎቱ መብረቅ አውርዶ አባርሮታል:: በበርሃው ምንም የሚበላ ነገር ባለ መኖሩ የዱር እንስሳትን ወተት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይጠጣ ነበር::

+ቅዱሱ ሰማዕት ለመሆን ሞክሮም ነበር:: ማር ያዕቆብ ገድሉና ተአምራቱ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ስሙ ከፍ ከፍ ብሏል:: እስኪ ጊዜውና እድሉ ካለዎት #መጽሐፈ_ስንክሳር ላይ የተጻፈውን ገድሉን እንዲያነቡ ልጋብዝዎት:: ጻድቁ ያረፈው በዚሁ ዕለት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹ ካሉበት ጉባኤ እንደ ምሕረቱ ታላቀነት ያድርሰን:: በረከታቸውንም ይሙላልን::

=>መስከረም 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
2.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
3.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
4.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
5.ቅድስት እሌኒ ንግሠት
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ መርቆሬዎስ ካልዕ (ሰማዕት)
8.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት
9.ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕት
10.አባ ፊልሞስ
11.ቅዱስ ሰልሖን ሰማዕት
12.ቅዱስ አክሳኤልስ ሰማዕት
13.ቅዱስ ይስሐቅ ሰማዕት
14.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀሲስ
15.ቅዱስ ነኪጣ ሰማዕት
16.አባ ፊላታውዎስ መንክራዊ
17.አባ ኖብ ባሕታዊ
18.አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
19."60" ሰማዕታት (ማሕበረ ቅዱስ አቦሊ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)

=>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም #ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም . . . መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝️✝️ አቢ ጠቅላላ ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ጥገና ✝️✝️
ንኳን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን
👉 ኦቭን
👉 ማይክሮዌቭ
👉 ምጣድ
👉 ስቶቮች
👉 የሻይ ቡና ማሽን
👉 መፍጫዎች
👉 የውሃ ማፍያዎች
👉 የውሀ ፓምፖች
👉 ጄነሬተር በአስተማማኝ ሁኔታ እንጠግናለን
ከቤትዎ ሳይወጡ ይደውሉ ያሉበት በመምጣት እንሰራለን
📞 0938152513
/channel/abi1888
/channel/electricianbolegerji
jo1888" rel="nofollow">http://www.tiktok.com/@jo1888
✝️✝️ መልካም የመስቀል በዓል ✝️✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/XAGRrK3DZGI?si=VHtGEk87qMha4sfn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝

✝ #መስከረም ፲፭ (15) ቀን።

✝ እንኳን #ለዲያቆናት_አለቃ_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለሥጋው_ፍልሰት ለመታሰብያ በዓል፣ ጠራው ከሚባል አገር ለሆኑ እግራቸው በውኃው ሳይርስ በእግራቸው በባሕር ላይ ሲራመዱ ለነበሩት ለከበረ #ለጻድቁ_ለአባ_ጴጥሮስ በዓለ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

የዲያቆናት አለቃ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው
ከዐረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ "እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ" አለ።

ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ። "በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ" እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።

ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።

በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።

ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።

ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ "የቅዱስ እስጡፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ" ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።

እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም ለተመሰገነና ለተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ እስጢፋኖስ ሥጋው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ | ዘማሪት ለምለም ከበደ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ሚካኤል ዋስ ጠበቃ ይሁንልን!🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኦ ፡ ዘነፃኅኮ ።

ኦ ፡ ዘነፃኅኮ ፡ ለዲያብሎስ ፡ በትዕቢቱ ።
ወምስለ ፡ ሚካኤል ፡ አልዐልኮ ፡ ለመንፈሰ ፡ ገብርኤል ፡ በተትሕቶቱ ።
እግዚአብሔር ፡ እምኵሉ ፡ እስመ ፡ ትሕትና ፡ ትፈቱ ።
መሀረኒ ፡ ሕገ ፡ ትሕትና ፡ ዘእምኀቤከ ፡ ፀአቱ ።
ትዕቢትሰ ፡ እምሰይጣን ፡ ውእቱ ።

ትርጕም በግጥም፦

ዲያብሎስን የጣልክ፥ ሥልጣኑን ቀምተኽ፥ ቢበዛ ትዕቢቱ፣
ከሚካኤል ጋራ፥ ገብርኤልን የሾምክ፥ በትሑትነቱ፤
እግዚአብሔር ከኹሉ፥ ትሕትና ነውና፥ የልብኽ መሻቱ፣
ከአንተ የሚመነጭ፥ ፍጹሕ ትሕትናን፥ አልምደኝ አቤቱ፤
የትዕቢት ሥራማ፥ ምንጩ ከሰይጣን ነው፥ ገሃነም ርስቱ።

© ምንጭ፦ ጠቢበ ጠቢባን፣ ተርጓሚ እና አዘጋጅ፦ ኤፍሬም የኔሰው፣ አታሚ፦ ጃጃው ማተሚያ ቤት፣ ፳፻፲፭ ዐ.ም፤ ገጽ ፷፪–፷፫።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
31r6lHo~

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
F!l3#dMFIUY?y\

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
pZ0hfWR;+Nj3

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
<4`P]?XP#Jdr="k

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

QQ建群100一个 做的来
/channel/+0y1E6icHKl00OTE9
GEi})GA<V/!AhA

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+LNbJmr7thGAxNjJk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ ✝✝✝

✝መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+" በዓለ ስዕለ አድኅኖ "+

✝ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ስዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ስዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ስዕል' ማለት ነው::

+ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ስዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ስዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል::

+እንዲያውም የመጀመሪያው ሰዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምስል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ስዕለ ኪሩብን እንዲስል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል::

+በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ስዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት(ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ስዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13)

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ የመጀመሪያው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ስዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል::

('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው)

+ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ስዕለ ስቅለቱን ሲስልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምስለ ፍቁር ወልዳን' ስሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል::

+ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና::

+" ጼዴንያ "+

+በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::

+ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የስዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር:: (እርሱ ምን ያድርግ! እኔም ብሆን ይህንኑ ነበር የማደርገው)

+ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: ይህቺ ክብርት ስዕለ አድኅኖ የአሁን መገኛ 4 መረጃዎች አሉ:-

1.ያለችው ኢትዮዽያ ውስጥ (ደብረ ዘመዳ በሚባል ገዳም) ነው:: የመጣችውም ከግማደ መስቀሉ ጋር ነው::
2.ያለችው በቀደመ ቦታዋ ነው::
3.የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ወስደዋታል::
4.በፈጣሪ ጥበብ ተሰውራለች::

+" ልደታ ለማርያም "+

+በግብጽ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ: ማለትም በአስቄጥስ ደብረ አባ መቃርስ የእመቤታችንን ዜና ሕይወት የሚናገር 1 መጽሐፍ አለ:: መጽሐፉ እንደሚለው እመ ብርሃን ድንግል ማርያም የተጸነሰችው ታሕሳስ 17 ቀን ነው:: በዚህ ሒሳብ መሠረት ደግሞ እመ አምላክ የተወለደችው መስከረም 10 ቀን ነው:: ዓለማቀፍ ትውፊቱ ግን ነሐሴ 7 ተጸንሳ: ግንቦት 1 ቀን መወለዷን ያሳያል::

+" ተቀጸል ጽጌ / አጼ መስቀል "+

+'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን: አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል:: በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው:: በወቅቱ ንጉሡ: ሠራዊቱ: ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር-መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል" እያለ ይዘምር ነበር::

+የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር:: ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል::

+" ንግሥተ ሳባ "+

+ይሕቺ ደግ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት:: በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች::

+ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች:: ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ምኒልክን ወልዳለች:: ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች:: (ማቴ. 12:42) በስምም "ሳባ: አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍቷ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከስዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን::

+መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
2.በዓለ ስዕለ አድኅኖ
3.ቅዱስ እፀ መስቀል (ተቀጸል ጽጌ)
4.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5.ቅድስት ማርታ ዘጼዴንያ
6.ቅድስት ዮዲት ጥበበኛዋ
7.ንግስተ ሳባ / ማክዳ / አዜብ
8.ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት
9.አፄ ዳዊት ንጉሥ
10.ቅድስት አትናስያና 3 ልጆቿ

ወርኀዊ በዓላት

1 ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2 ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ
3 ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ
4ቅድስት እሌኒ ንግስት
5 ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ

++"+ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር:: ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? +"+ (ገላ. 3:1)

‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ›

Читать полностью…
Subscribe to a channel