kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው  ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።

ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014 

inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+"+ ዕረፍት +"+

=>ነቢየ ጽድቅ: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ:: 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና::

*በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና (ዜና. 21:16) ሰውነቱ ደከመ:: በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ዳዊት በሰማይ +"+

=>በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል:: ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው::

*በነገረ ማርያም ትምሕርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው::
*እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ:: ክብሩ ታላቅ ነውና::

<< በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል >>

=>አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን:: በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን::

✞✞✞ ታኅሣሥ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
3.አባ ሳሙኤል ጻድቅ
4.አባ ስምዖን ጻድቅ
5.አባ ገብርኤል ጻድቅ
6.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
3.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ

=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88:20)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም እንዴትዋላችሁ ለገና የሚቀርብ ግጥም ካላችሁ ላኩልኝ እባካችሁ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Amen Kale hiwet yasemalen🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ: የዋሕና ልበ አምላክ ቅዱስ #ዳዊት ንጉሥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✞✞✞

✞✞✞ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ ✞✞✞

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ: አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:20) ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን::

+እንደ አምላክ ልብ ኾኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል::

*አቤት አባታችን ዳዊት ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል* እንላለን::

+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግሥት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

+በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

+"+ ልደት +"+

=>ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ-በኃጢአት ተጸነስኩ" ይላል (መዝ. 50:5) አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው::

+ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል:: በዚያች በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል::

+"+ ዕድገት +"+

=>ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር:: ሕጸን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር:: አንበሳውን በጡጫ: ድቡን በእርግጫ: ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር:: በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል::

+"+ መቀባት +"+

+እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሗላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የኾነውን ቀብተህ አንግስልኝ" ቢለው ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም ገብቷል::

+በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ:: ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::
+በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ::

+"+ ዳዊትና ጐልያድ ++

=>ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እሥራኤልን ሲያስጨንቅ ለ40 ቀናት ቆይቶ ነበር:: ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል: በጠጠር ጥሎታል:: ከእሥራኤልም ሽሙጥን አርቁዋል:: ግን ቅዱሱ ብላቴና: ጐልያድ ደግሞ 6 ክንድ (3 ሜትር) የሚረዝም ሰው ነበር::

+"+ ስደት +"+

=>ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም:: ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ: ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ:: ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር::

+እርሱ ግን ለ18 ዓመታት በትእግስት ተሰደደ:: ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው:: በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የምትለውን ሕግ ፈጸማት:: (ማቴ. 7:45, መዝ. 16:4)

+"+ ንግሥና +"+

=>ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ:: ምን ጠላቱ ቢሆን 'የሳዖል ገዳይ ነኝ' ያለውን ተበቀለ:: ስለ ጠላቱም አለቀሰ:: 30 ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ7 ዓመታት በኬብሮን: ለ33 ዓመታት በኢየሩሳሌም (ጽዮን) ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቁዋል::

+በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጉዋል:: በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን: በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል::

+"+ ንስሃ +"+

=>ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው:: ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ት/ቤት ነው:: ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ: ኦርዮን አስገድሎ ነበር:: ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ::

+ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ አለቀሰ:: መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት:: ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ:: እግዚአብሔርም ንስሃውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው:: በንስሃ ለምትገኝ ጸጋም ምሳሌ ሆነ::

+"+ ነቢይነት +"+

=>በቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ (ምሥጢር የበዛለት) አልተገኘም:: 'ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ' ብሎ: ከዚያ ከስነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው::

+ስለ መላእክት: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል:: ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ: አስፍቶ ተናግሯል:: 150 ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል::

+ስለዚህም አበው:-
"አልቦ ምስጢር ወአልቦ ትንቢት:
ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት" ይላሉ::

+"+ መዝሙር +"+

=>ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው:: ለራሱ ባለ 10 አውታር : ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ 8 አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር:: 24 ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቁዋረጥ 288 መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር::

+ራሱም በፍጹም ተመስጦ: ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር:: "ቃልህ ለጉረሮየ ጣፋጭ ነው" እንዲል:: (መዝ. 118:103) የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው:: ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ::

"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል::

+"+ #ዳዊትና ጽዮን +"+

=>ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን አንጾ ጽላተ ኪዳኑን አመጣ:: ለአምላከ ያዕቆብ ማደሪያን ሊፈልግም ዐይኑ ከእንቅልፍ ተከለከለ:: (መዝ. 131:2) የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ "አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ - አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው" አለው::

*አያይዞም የምሥጢረ ሥጋዌን ነገር ቢገልጥለት "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ - እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ሲል ተናግሯል:: (መዝ. 131:6) የኪዳኑ ጽላት (ጽዮን) ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ: ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ::

*ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ:: ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና:: በጽዮን ፊት እየወደቀ: እየተነሳ: እየታጠቀ: እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው:: እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው:: (ሳሙ. 6:16)

+"+ ክብረ ዳዊት +"+

=>እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጉዋል:: ሰሎሞንና ሕዝቅያስን (ነገሥታቱን) ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው::*የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት:: (ማቴ. 1:1) ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና:: እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል:: (ራዕ. 22:16)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 22/2016 #ብስራተ_ገብርኤል (የለዉጥ በአል)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመስግንበት በዚህ እለት አብሣሪዉ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ለእናታችንና ለእመቤታችን ወላዲተ አምላክ #ማርያም ደስ የሚያሰኘዉን #ብስራት ያበሠረበት አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ይኽም በአል የለዉጥ በአል ነዉ የብስራት በአል የተከናወነዉ መጋቢት 29 ቀን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ እለቱ እሁድ ነበር ይህ እለት ፆም ላይ ስለሚዉል የእመቤታችን ወዳጅ #ቅዱስ_ደቅስዮስ ከልደት አስቀድሞ ታህሳስ 22 ቀን እንዲከበር በማድረጉ ተቀባይነት ኖሮት እለቱ #ብሥራተ_ገብርኤል ተብሎ ቢከበርም ጥንተ ብሥራቱ ግን በአለ ፅንሰት ያዉ ከመጋቢት 29 አይወጣም

☞ሰላም ለኪ እያለ
☞ሰላም ለኪ እያለ
☞ሀር እና ወርቁን ስታስማማ
☞የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
☞ተሰማ የመላኩ ድምፅ ተሰማ
☞ውሃ ሰትቀጂ ክንፉን እያማታ
☞ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
☞ከሞጎስሽ ብዛት ሲታጠቅ ሲፈታ
☞አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ

👉እመቤታችን #ድንግል_ማርያም በቤተ ዮሴፍ ሳላች ለቤተ መቅደስ መጋረጃ የሚሆን ወርቁን ከሐር ጋር እያስተባበረች ትፈትል ነበር፡፡

👉ከዕለታት ባንደኛው ቀን በናዝሬት ክፍል በሚገኝ ጉድጓድ ውሃ ልትቀዳ በሄደች ጊዜ የመላዕክት አለቃ #ቅዱስ_ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ #እግዚአብሔር ያከበረሽ ንጽሕት ቅድስት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እሱ #እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና በሱም ዘንድ መወደድን ባለሟልነትን አገኘሽ ከሴቶቹ ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽና አላት

👉እመቤታችን #ማርያም ይህን በሰማች ጊዜ ማን እንደተናገራት ለማወቅ ግራ ቀኝ ተመለከተች ነገር ግን ምንም ያየችው ነገር ሰለሌለ ፍርሃት አደረባትና ገንቦዋን ትታ ወደ ቤቷ ተመለሰች እንደ ልማዷም #ሐርና_ወርቁን እያስተባበረች ትፈትል ጀመር

👉ዳግመኛም በግልፅ መጥቶ #ማርያም ሆይ አትፍሪ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት አግኝተሻልና #የእግዚአብሔር ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ትፀንሻለሽ አላት

👉 #ማርያምም ለቅዱስ #ገብርኤል ስትመልስ እኔ ወንድ የማላውቅ ስሆን ይህ እንዴት ይሆንልኛል አለችው

👉 #ቅዱስ_ገብርኤልም አንቺ የምትወልጂው ሴቶች እንደሚወልዱት አይደለም #መንፈስ_ቅዱስ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል እንጂ ካንቺ የሚወለደው ቅዱስ ነው

👉እሷም #የእግዚአብሔር አገልጋዩ እኔ እንሆ አለሁ ሰውነቴም በእጁ የተያዘች ናትና እሱ የወደደውን በኔ ላይ ያድርግ ብላ ለመላኩ መለሰችለት

👉ይህንንም ምክንያት አድርጎ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካላዊ #ቃል ከላይ ከሦስትነቱ ሳይጎድል ከታችም ዐራተኛ ሳይታከልበት በፍጹም አካሉ ወርዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን ሕፃናትን የፈጠረ እሱ ቀዳማዊው አካላዊ ቃል በግዕዘ ሕፃናት #በማኅፀኗ_ተቀረፀ

👉ወንጌላዊ ዮሐንስ በማይመረመር #ተዋሕዶ ባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ #ቃል_ሥጋ ሆነ ብሎ እንደተናገረ መፅሐፍም እንዳረጋገጠ የሁለቱን ተዋህዶ ሊመረምሩት ፈፅሞ አይቻልም

👉(ድርሳነ ገብርኤል ዘ መጋቢት)

👉ደስታን አብሳሪ ሊቀ መላዕክት #ቅዱስ_ገብርኤል በዚህ ሰዓት ጊዜ በማይሰጠው ረሀብ እና ጥም እንዲሁም በመረረ ሀዘን ውስጥ ላሉ ደስ የሚያሰኘውን የምስራች አሰማቸው መፅናናትን ስጣቸው ለኛም ለልጆችህ መልካሙን #የምስራች አሰማን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ መልአከ ሠላም #ቅዱስ_ኡራኤል ጥበቃው አይለየን እንዲሁም የእመቤታችን ማርያም ወዳጅ #ቅዱስ_ደቅስዮስ ረድኤት በረከቱ ይድረሰን ምልጃና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4.በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ከሐዋርያት ተልኮ ሒዶ በጐ ጐዳናን መራቸው:: (ሐዋ. 11:22)+ቅዱስ በርናባስ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ ከቅዱስ ዻውሎስጋር: ቀጥሎ ደግሞ ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ብዙ አሕጉራትን አስተምሯል:: ቆዽሮስም ሃገረ ስብከቱ ናት::

+ቅዱሱ ከብዙ ትጋት በሁዋላ በዚህች ቀን አረማውያንና አይሁድ ገድለውታል:: ቅዱስ ማርቆስም ገንዞ ቀብሮታል::
<< ስለርሱ መጽሐፍ "ደግ: መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ነው" ይላልና ክብር ይገባዋል !! >> (ሐዋ. 11:24)

+"+ አባ ይስሐቅ ጻድቅ +"+

=>ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ ነው:: መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ ነበረች:: እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር::

+የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል ማርያም ስዕል ፊት ይጸልይ: ይሰግድ: ያነባ ነበር:: እንዲህ ለ7 ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል እመ ብርሃን ልመናውን ሰማች::

+በዚህ ዕለትም ከፀሐይ 7 እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች:: ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው:: "ከ3 ቀናት በሁዋላ እመለሳለሁ" ብላም ተሠወረችው:: በ23ም ዐረፈ::
"በዛቲ ዕለት ሶበ ጸለየ ጥቡዐ::
ለይስሐቅ አስተርዓየቶ እም አይቆናሃ ወጺአ::
እምጸዳለ መብረቅ ጥቀ እንዘ ትጸድል ስብአ::" እንዳለ ደራሲ:: (አርኬ)

=>የእሥራኤል እረኛ ሥጋችንን ከመቅሰፍት: ነፍሳችንን ከገሃነመ እሳት ይጠብቅልን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ኖላዊ ሔር
2.ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ
3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

=>+"+ መልካም እረኛ እኔ ነኝ:: አብም እንደሚያውቀኝ: እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጐች አውቃለሁ:: የራሴም በጐች ያውቁኛል:: ነፍሴንም ስለ በጐች አኖራለሁ:: ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጐች አሉኝ:: እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል:: ድምጼን ይሰማሉ:: አንድም መንጋ ይሆናሉ:: +"+ (ዮሐ. 10:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🛑+++ወትረ ዝክረ ቅዱሳን+++🛑

=>የዩቱዩብ ቻነል<=
ZekereKedusan?si=7acGUCDCLO2Qxl37" rel="nofollow">https://youtube.com/@ZekereKedusan?si=7acGUCDCLO2Qxl37

=>የቴሌግራም ቻነል<=
/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

፩.ሚስጥረ ጥምቀት
፪.ሚስጥረ ሜሮን
፫.ሚስጥረ ቁርባን
፬.ሚስጥረ ንስሐ
፭.ሚስጥረ ክህነት
፮.ሚስጥረ ተክሊል
፯.ሚስጥረ ቀንዲል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4.በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ከሐዋርያት ተልኮ ሒዶ በጐ ጐዳናን መራቸው:: (ሐዋ. 11:22)+ቅዱስ በርናባስ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ ከቅዱስ ዻውሎስጋር: ቀጥሎ ደግሞ ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ብዙ አሕጉራትን አስተምሯል:: ቆዽሮስም ሃገረ ስብከቱ ናት::

+ቅዱሱ ከብዙ ትጋት በሁዋላ በዚህች ቀን አረማውያንና አይሁድ ገድለውታል:: ቅዱስ ማርቆስም ገንዞ ቀብሮታል::
<< ስለርሱ መጽሐፍ "ደግ: መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ነው" ይላልና ክብር ይገባዋል !! >> (ሐዋ. 11:24)

+"+ አባ ይስሐቅ ጻድቅ +"+

=>ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ ነው:: መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ ነበረች:: እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር::

+የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል ማርያም ስዕል ፊት ይጸልይ: ይሰግድ: ያነባ ነበር:: እንዲህ ለ7 ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል እመ ብርሃን ልመናውን ሰማች::

+በዚህ ዕለትም ከፀሐይ 7 እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች:: ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው:: "ከ3 ቀናት በሁዋላ እመለሳለሁ" ብላም ተሠወረችው:: በ23ም ዐረፈ::
"በዛቲ ዕለት ሶበ ጸለየ ጥቡዐ::
ለይስሐቅ አስተርዓየቶ እም አይቆናሃ ወጺአ::
እምጸዳለ መብረቅ ጥቀ እንዘ ትጸድል ስብአ::" እንዳለ ደራሲ:: (አርኬ)

=>የእሥራኤል እረኛ ሥጋችንን ከመቅሰፍት: ነፍሳችንን ከገሃነመ እሳት ይጠብቅልን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ኖላዊ ሔር
2.ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ
3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

=>+"+ መልካም እረኛ እኔ ነኝ:: አብም እንደሚያውቀኝ: እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጐች አውቃለሁ:: የራሴም በጐች ያውቁኛል:: ነፍሴንም ስለ በጐች አኖራለሁ:: ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጐች አሉኝ:: እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል:: ድምጼን ይሰማሉ:: አንድም መንጋ ይሆናሉ:: +"+ (ዮሐ. 10:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Egzabher ymesgen endet walachu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው  ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።

ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014 

inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር "ቅዱስ ሐጌ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✞

+*" ቅዱስ ሐጌ ነቢይ "*+

=>ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር) : መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

+"ዘመነ ነቢያት" ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

+ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

+ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

+ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ዼጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው : ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

+ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት "15ቱ አበው ነቢያት" : "4ቱ ዐበይት ነቢያት" : "12ቱ ደቂቀ ነቢያት" ና "ካልአን ነቢያት" ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

=>"15ቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ
*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ
*አብርሃም
*ይስሐቅ
*ያዕቆብ
*ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::

=>"4ቱ ዐበይት ነቢያት"
*ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
*ቅዱስ ኤርምያስ *ቅዱስ ሕዝቅኤልና
*ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

=>"12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
*ቅዱስ ሆሴዕ
*አሞጽ
*ሚክያስ
*ዮናስ
*ናሆም
*አብድዩ
*ሶፎንያስ
*ሐጌ
*ኢዩኤል
*ዕንባቆም
*ዘካርያስና
*ሚልክያስ ናቸው::

=>"ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስና
*ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

=>ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ:: በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-

*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት):
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::

+ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

+ቅዱስ ሐጌ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ450 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸው::

=>"ሐጌ" ማለት መልአከ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መልእክተኛ) ማለት ነው:: አንዳንዴም "በዓል" ተብሎ ይተረጐማል:: ትውልዱ ከነገደ ጋድ ሲሆን አባቱ አግታ: እናቱ ሲን ይባላሉ::

+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከደኃርት (ከሁዋለኛው ዘመን ነቢያት) አንዱ ነው ይባላል:: ቁጥሩም ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+እሥራኤል ከተከፈለችበት ከመንግስተ ሮብዓም (ከክርስቶስ ልደት 931 ዓመታት በፊት) በሁዋላ 10ሩ ነገድ "እሥራኤል": 2ቱ ነገድ "ይሁዳ" ተብለው በሰሜንና በደቡብ አቅጣጫ ተለያዩ:: መናገሻቸውም ኢየሩሳሌምና ሰማርያ ሆኑ::

+ከዕለት ዕለት ግን የሁሉም ኃጢአት እየበዛ በመሔዱ እግዚአብሔር አዘነባቸው:: ለአሕዛብም አሳልፎ ሰጣቸው:: አስቀድሞ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ722 ዓመት የአሦሩ ንጉሥ ስልምናሶር መጥቶ ሰማርያን አጠፋት:: 10ሩን ነገድም በባርነት አሦር አወረዳቸው::

+ከዚህ ትምሕርት መውሰድ የተሳናቸው 2ቱ ነገድም ሊገሰጹ አልቻሉምና ተመሳሳይ ዕጣ ደረሰባቸው:: የእግዚአብሔርንና የነቢያቱን ድምጽ: ይልቁኑ የኤርምያስን ምክር አልሰሙምና ከክርስቶስ ልደት 586 ዓመታት በፊት ኃይለኛው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር መጣ::

+የሚገድለውን ገድሎ: ሕዝቡንም ማርኮ ወደ ፋርስ ባቢሎን ሲያወርዳቸው ኢየሩሳሌምን ምድረ በዳ አደረጋት:: (2ነገ. )

+እግዚአብሔርን የማይሰማ ሕዝብ ምን ጊዜም እጣ ፈንታው ይሔው ነው:: በተለይ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ቸርነት የበዛለት ሕዝብ እንዲህ አንገተ ደንዳና ሲሆን ይገርማል:: በእርግጥ ዛሬ እስራኤል ያይደለ ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮዽያ ናትና ከመሰል መከራ ለመራቅ ድምጹን መስማት ያስፈልጋል::

+ሕዝቡ ግን ፋርስ : ባቢሎን ወርደው መከራን ሲቀበሉ : ነቢያት ያሉት ሁሉ ሲፈጸምባቸው ተጸጸቱ:: ፈጣሪም ተስፋ እንዳይቆርጡ በዚያው ዳንኤልን የመሰሉ ነቢያትን አስነሳላቸው:: እነ ኤርምያስንም ከግብጽ ላከላቸው::

+ሕዝቡም (በተለይ "ትሩፋን" የተባሉት) "እግዚአብሔር ሆይ! 'ወሰብዓ ዓም ኃሊቆ' ባልከው ቃልህ : 70ው ዘመን ሲፈጸም ወደ አባቶቻችን ርስት ብትመልሰን መቅደስህን እናንጻለን:: በጐ ምግባርን እንይዛለን" ሲሉ ተሳሉ::

+ልመናን የሚሰማ ቸሩ ፈጣሪም እንደ ቃሉ 70ው ዘመን ሲፈጸም እሥራኤል በነ ኤርምያስ ባሮክና እና ሌሎችም አማካኝነት በኃይል: በድንቅና በተአምራት ከፋርስ ባቢሎን ወጡ:: በድል ተጉዘውም ወደ ርስታቸው ገቡ::

+የሰው ነገር አስቸጋሪ ነውና ከርስታቸው ከገቡ በሁዋላ ግን ስዕለታቸውን ሳይፈጽሙ ቀሩ:: በዚህ ጊዜም እንደ ዘወትሩ ይገሥጻቸው ዘንድ እግዚአብሔር ነቢያቱን ሐጌን : ዘካርያስንና ሚልክያስን አስነሳቸው::

+ሕዝቡ "እስመ ኢኮነ ጊዜሁ ለሐኒጽ - ለማነጽ ወቅቱ አልረዳንም" እያሉ ቤተ መቅደሱ ሳይታነጽ ዘመናት አለፉ:: የሚገርመው ግን ቤተ መቅደሱ ምድረ በዳ ሆኖ የራሳቸውን ቤት አሳምረው ያንጹ ነበር::

+በዚህ ጊዜ በመካከላቸው የነበረው ቅዱስ ሐጌ ዘለፋቸው::
"እምጊዜሁ ለክሙ ከመ አንትሙ ትንበሩ ውስተ ቤት ጥፉር: ወቤትየሰ ምዝቡር? - ቤቴ ፈርሶ ሳለ እናንተ ባማሩ ቤቶቻችሁ ልትኖሩ ጊዜው ነውን?" (ሐጌ. 1:4) አላቸው::

+አክሎም "ቃላችሁን አልፈጸማችሁምና በረከቴን ከእናንተ አርቃለሁ" አላቸው:: ተግሣጹን ከልብ የሰሙት ሕዝቡም በዘሩባቤል መሪነት 46 ዓመታት የፈጀውን ቤተ መቅደስን አንጸዋል::

+ቅዱስ ሐጌም በሕጉ እየኖረ: ትንቢትን እየተናገረ ዘመኑን ፈጽሟል:: በትውፊት ትምሕርትም ቅዱሱ የተወለደው በ500 ዓ/ዓ ሲሆን ያረፈው በ70 ዓመቱ በ5,070 ዓ/ዓ ነው:: ከክርስቶስ ልደት 430 ዓመታት በፊት ማለት ነው::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/GykURGKZVYs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንዴት ዋላችሁ በአል እንዴት ነበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/yX0xBzQezkw?si=vO2X-NCgQS1KQp7n

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ታኅሣሥ_23 ኃሳቡ የእግዚአብሔር ኃሳብ የሆነለት ሰው

🎚️እግዚአብሔር እንደልቤ ብሎ የጠራው የክብር ክብር፤ ውዳሴና ስግደትም የሚገባው በእስራኤላውያን ላይ ከንጉሱ ሳኦል ቀጥሎ 40 ዓመት የነገሰው ቅዱስ ዳዊት እረፍቱ ነው፡

🎚️ቅዱስ ዳዊት 7 ኃብታት መንፈስ ቅዱስ ሲኖሩት:-

1.ኃብተ ትንቢት
2.ኃብተ መንግስት
3.ኃብተ ክህነት
4.ኃብተ በገና (መዝሙር)
5.ኃብተ ፈውስ
6.ኃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ኃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ:

🎚️ጸሎቱና በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Hi shalom are you ok this group man?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

​​4. ከተጽኖው ጋር መቀጠል

በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ ለመድረሱን ያሳያል።

5. ሚስጥራዊነት

በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ሚስጥር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል።

ሚስጥሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት፤ የት እና ምን ያደርግ እንደነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል።

6. ኃላፊነትን አለመወጣት

ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፍ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን፤ የቤተሰብ፤ የማህበራዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መደረሱን ያሳያል።

7. የፀባይ መቀያየር

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፤ ቁጡ እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ።

ከላይ የጠቀስናቸው ዋና የሚባሉት የሱስ ምልክቶች ሲሆን እነዚህ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱስ መዘዞች ራሳቸውን ያጋልጣሉ።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
✅ t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
✅ t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+"+ ዕረፍት +"+

=>ነቢየ ጽድቅ: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ:: 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና::

*በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና (ዜና. 21:16) ሰውነቱ ደከመ:: በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ዳዊት በሰማይ +"+

=>በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል:: ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው::

*በነገረ ማርያም ትምሕርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው::
*እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ:: ክብሩ ታላቅ ነውና::

<< በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል >>

=>አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን:: በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን::

✞✞✞ ታኅሣሥ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
3.አባ ሳሙኤል ጻድቅ
4.አባ ስምዖን ጻድቅ
5.አባ ገብርኤል ጻድቅ
6.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
3.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ

=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88:20)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 22/2016 #ብስራተ_ገብርኤል (የለዉጥ በአል)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመስግንበት በዚህ እለት አብሣሪዉ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ለእናታችንና ለእመቤታችን ወላዲተ አምላክ #ማርያም ደስ የሚያሰኘዉን #ብስራት ያበሠረበት አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ይኽም በአል የለዉጥ በአል ነዉ የብስራት በአል የተከናወነዉ መጋቢት 29 ቀን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ እለቱ እሁድ ነበር ይህ እለት ፆም ላይ ስለሚዉል የእመቤታችን ወዳጅ #ቅዱስ_ደቅስዮስ ከልደት አስቀድሞ ታህሳስ 22 ቀን እንዲከበር በማድረጉ ተቀባይነት ኖሮት እለቱ #ብሥራተ_ገብርኤል ተብሎ ቢከበርም ጥንተ ብሥራቱ ግን በአለ ፅንሰት ያዉ ከመጋቢት 29 አይወጣም

☞ሰላም ለኪ እያለ
☞ሰላም ለኪ እያለ
☞ሀር እና ወርቁን ስታስማማ
☞የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
☞ተሰማ የመላኩ ድምፅ ተሰማ
☞ውሃ ሰትቀጂ ክንፉን እያማታ
☞ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
☞ከሞጎስሽ ብዛት ሲታጠቅ ሲፈታ
☞አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ

👉እመቤታችን #ድንግል_ማርያም በቤተ ዮሴፍ ሳላች ለቤተ መቅደስ መጋረጃ የሚሆን ወርቁን ከሐር ጋር እያስተባበረች ትፈትል ነበር፡፡

👉ከዕለታት ባንደኛው ቀን በናዝሬት ክፍል በሚገኝ ጉድጓድ ውሃ ልትቀዳ በሄደች ጊዜ የመላዕክት አለቃ #ቅዱስ_ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ #እግዚአብሔር ያከበረሽ ንጽሕት ቅድስት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እሱ #እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና በሱም ዘንድ መወደድን ባለሟልነትን አገኘሽ ከሴቶቹ ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽና አላት

👉እመቤታችን #ማርያም ይህን በሰማች ጊዜ ማን እንደተናገራት ለማወቅ ግራ ቀኝ ተመለከተች ነገር ግን ምንም ያየችው ነገር ሰለሌለ ፍርሃት አደረባትና ገንቦዋን ትታ ወደ ቤቷ ተመለሰች እንደ ልማዷም #ሐርና_ወርቁን እያስተባበረች ትፈትል ጀመር

👉ዳግመኛም በግልፅ መጥቶ #ማርያም ሆይ አትፍሪ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት አግኝተሻልና #የእግዚአብሔር ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ትፀንሻለሽ አላት

👉 #ማርያምም ለቅዱስ #ገብርኤል ስትመልስ እኔ ወንድ የማላውቅ ስሆን ይህ እንዴት ይሆንልኛል አለችው

👉 #ቅዱስ_ገብርኤልም አንቺ የምትወልጂው ሴቶች እንደሚወልዱት አይደለም #መንፈስ_ቅዱስ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል እንጂ ካንቺ የሚወለደው ቅዱስ ነው

👉እሷም #የእግዚአብሔር አገልጋዩ እኔ እንሆ አለሁ ሰውነቴም በእጁ የተያዘች ናትና እሱ የወደደውን በኔ ላይ ያድርግ ብላ ለመላኩ መለሰችለት

👉ይህንንም ምክንያት አድርጎ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካላዊ #ቃል ከላይ ከሦስትነቱ ሳይጎድል ከታችም ዐራተኛ ሳይታከልበት በፍጹም አካሉ ወርዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን ሕፃናትን የፈጠረ እሱ ቀዳማዊው አካላዊ ቃል በግዕዘ ሕፃናት #በማኅፀኗ_ተቀረፀ

👉ወንጌላዊ ዮሐንስ በማይመረመር #ተዋሕዶ ባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ #ቃል_ሥጋ ሆነ ብሎ እንደተናገረ መፅሐፍም እንዳረጋገጠ የሁለቱን ተዋህዶ ሊመረምሩት ፈፅሞ አይቻልም

👉(ድርሳነ ገብርኤል ዘ መጋቢት)

👉ደስታን አብሳሪ ሊቀ መላዕክት #ቅዱስ_ገብርኤል በዚህ ሰዓት ጊዜ በማይሰጠው ረሀብ እና ጥም እንዲሁም በመረረ ሀዘን ውስጥ ላሉ ደስ የሚያሰኘውን የምስራች አሰማቸው መፅናናትን ስጣቸው ለኛም ለልጆችህ መልካሙን #የምስራች አሰማን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ መልአከ ሠላም #ቅዱስ_ኡራኤል ጥበቃው አይለየን እንዲሁም የእመቤታችን ማርያም ወዳጅ #ቅዱስ_ደቅስዮስ ረድኤት በረከቱ ይድረሰን ምልጃና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

​​በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?

ፖርኖግራፊ ቃሉ የተገኘው πορνογραφία (pornographia) ከሚል የግሪክ ቃል ሲሆን በጥንት ጊዜ የቃሉ ትርጉም ስለ ሴተኛ አዳሪ ግልጽ በሆነ መንገድ የሚያትት ማናቸውም አይነት የስነ ፁህፍ ወይም የስነ ጥበብ ስራ ማለት ነው።

ነገር ግን በአሁኑ ዘመን ይህ ከጽሁፍ እና ስዕል ወደ ቪዲዮ ምስል ማደጉን እናያለን። ማንኛውም የወሲብን ስሜት የሚቀሰቅሱ ወሲባዊ ታሪኮች፣ ፊልሞች፤ ፎቶግራፎች እንዲሁም የቃላት ልውውጥ ፖርኖግራፊ ይባላል።

በአሁኑ ወቅት ሰዎች ፖርኖግራፊ ለማየት ለዚህ ከተዘጋጁ ልዩ ድህረ ገፆች ባሻገር ለዚህ አላማ ባልተዘጋጁ የማህበረሰብ መገናኛ ድህረ ገፆች ማለትም ቴሌግራም ፣ ትዊተር፣ ፌስቡክ የመሳሰሉትን በመጠቀም ለፖርኖግራፊ ሱስ ተጋላጭ ይሆናሉ።

በዘመናችንም ፖርኖግራፊ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል መሆኑም ሱሱ እንደወረሽኝ እንዲዛመት አድርጎታል። ፖርኖግራፊ ሰዎችን በቀላሉ ሱሰኛ የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን ሲጋራ፣ ጫት እና የተለያዩ ዕፆች ሊያደርሱት ከሚችሉት ጉዳት በላይ ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በግልጽ ለማየት ተችሏል።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
✅ t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
✅ t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
✅ t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞ እንኳን "ለኖላዊ ሔር ክርስቶስ" : ለቅዱሳን "በርናባስ ሐዋርያ" እና "አባ ይስሐቅ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

+*" ኖላዊ ሔር "*+

=>እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው::

+ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር:: ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር: ሱባኤ ይቆጠር: ምሳሌም ይመሰል ገባ::

+ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ:: ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት / ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል::

+ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል:: እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል::

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች:: ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች:: መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10:1) ነው:: "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው::

+ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል:: ከአባታችን አዳም ስህተት በሁዋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው:: እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ: ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር::

+ኤዶም ገነት የለመለመች: ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና:: አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር:: ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ::

+እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ:: ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው:: ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ:: ከሴት ኄኖስ: ከኄኖስ: ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ::

+ከኖኅም በሴም ከአብርሃም: ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ:: ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ:: እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም::

+ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን: የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው:: "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ:: (መዝ. 79:1)

+ጩኸቱም ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል ማርያም ተወለደ:: በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ:: መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው::

+ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5:36, ዮሐ. 10:8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ:: እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ. 10:7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ::

+እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ. 10:11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል:: በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት: መንጋው (በጐቹ) ከሁዋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው::

+መድኃኒታችን ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን: በመራቆቱ የጸጋ ልብስን: በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ:: የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ:: ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ. 1:1, ዮሐ. 1:2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን::

+በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን: ሐዋርያትን (ዮሐ. 21:15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ. 20:28) ካህናትን (ማቴ. 18:18) ሾመልን:: እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ:: እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም: ኃላፊነቱም አለባቸው:: (ማቴ. 28:19)

+*" ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ "*+

=>ቅዱሱ ሐዋርያ ስሙ ሲጠራ ሞገስ አለው:: የቅዱሱ ሰው የመጀመሪያ ስሙ ዮሴፍ ሲሆን በርናባስ ያለው መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው:: ትርጉሙም "ወልደ ኑዛዜ-የመጽናናት ልጅ" እንደ ማለት ነው::

+በምሥጢሩ ግን "ማሕደረ መንፈስ ቅዱስ-የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ" እንደ ማለት ያስተረጉማል:: ቅዱስ በርናባስ ምንም በትውልዱ እሥራኤላዊ ቢሆን ተወልዶ ያደገው በቆዽሮስ ነው:: እስከ ወጣትነት ጊዜውም የቆየው እዚያው ነው::

+የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የመሆኑ ዜና ሲሰማ ግን ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ መድኅን ክርስቶስን ተመለከተ:: ጌታውንም ሊከተል በልቡ ቆረጠ:: የፈጠረን ክርስቶስም እንዲረባ (እንዲጠቅም) አውቆ: ስሙን ቀይሮ አስከተለው:: ከ72ቱ አርድእትም ደመረው::

+ቅዱስ በርናባስ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ለ3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ቁጭ ብሎ ተማረ:: ተአምራቱንም ሁሉ ተመለከተ:: ከጌታ ዕርገት በሁዋላ 120ው ቤተሰብ በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩም አብሮ ይተጋ ነበር::

+በጊዜውም አበው ሐዋርያት በይሁዳ ፈንታ ከ12ቱ የሚቆጠረውን ሰው ለመምረጥ 2 ሰዎችን አቅርበው ነበርና አንዱ ይኸው ቅዱስ ነው:: እዚያውም ላይ ጌታችንን ከመጀመሪያው ጀምሮ ማገልገሉ ተመስክሮለታል:: (ሐዋ. 1:22)

+ስሙንም ኢዮስጦስ ብለውታል:: ባለ 3 ስም ነበርና:: በወቅቱም ዕጣ በቅዱስ ማትያስ ላይ ስለ ወደቀ በርናባስ ከ72ቱ አርድእት: ማትያስ ከ12ቱ ሐዋርያት ሆነው ቀጠሉ::

+ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ በርናባስ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በኃይል ያገለግል ጀመር:: የሐዋርያትን ዜና በሚናገር መጽሐፍ ላይ የተጻፉና ስለ ቅዱሱ ማንነት የሚናገሩ ክፍሎችን እንመልከት::

1.ቅዱሳን ሐዋርያት የእኔ የሚሉት ንብረት ሳይኖራቸው: ያላቸውን በጋራ እየተጠቀሙ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ነበር:: ያለውን ሁሉ ሸጦ በሐዋርያት እግር ላይ በማኖር ደግሞ ቀዳሚውን ሥፍራ ቅዱስ በርናባስ ይይዛል:: (ሐዋ. 4:36) በዚህም የዘመነ ሐዋርያት የመጀመሪያው መናኝ ተብሏል::

2.ልሳነ እፍረት (ብርሃነ ዓለም) ቅዱስ ዻውሎስ ባመነ ጊዜ ሐዋርያት ለማመን ተቸግረው ነበር:: የሆነውን ሁሉ አስረድቶ ቅዱስ ዻውሎስን ከሐዋርያት ጋር የቀላቀለው ይህ ቅዱስ ነው:: (ሐዋ. 9:26)

3.አንድ ቀን መንፈስ ቅዱስ "ፍልጥዎሙ ሊተ ለሳውል ወለበርናባስ - በርናባስና ሳውልን (ዻውሎስን) ለዩልኝ" በማለቱ ሐዋርያት ጾመው: ጸልየው: እጃቸው ከጫኑባቸው በሁዋላ ላአኩአቸው:: (ሐዋ. 13:1)

+እነርሱም ወንጌልን እየሰበኩ በየሃገሩ ዞሩ:: በሃገረ ልስጥራን መጻጉዕን ስለ ፈወሱ ሕዝቡ "እናምልካችሁ" ብለው የአማልክትን ስም አወጡላቸው:: 2ቱ ቅዱሳን ግን ይህንን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደው በጭንቅ አስተዋቸው:: መመለክ የብቻው የፈጣሪ ገንዘብ ነውና:: (ሐዋ. 14:8-18, ዘጸ. 20:1)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም እዴት ናችሁ 7ባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስ ካላችሁ ላኩልኝ

=>አምላከ ሐጌ ለቤቱ የምናስብበትን ዘመን ያምጣልን:: ከቅዱሱ ነቢይ በረከትም ይክፈለን::=>ታሕሳስ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሐጌ ነቢይ
2.አባ አውጋንዮስ
3.ታውፊና ንግሥት

=>ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት

=>+"+ 'ብሩ የእኔ ነው:: ወርቁም የእኔ ነው' ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር:: 'ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል' ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር:: በዚህም ሥፍራ ሰላምን እሰጣለሁ:: +"+ (ሐጌ. 2:9)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔር ይመስገን አሪፍ ነበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

fetari yesgen bealu des yel neberArif neber

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Endemn ameshachu beteseboch

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳንም አብሮ አደረሰን 🙏🙏🙏 የዓመት ሰው ይበለን 🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel