ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
✝️
እንኳን ለጌታችን እና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰለም የጤና እንዲሆንላችሁ ሁሉግራም ይመኝላችኋል!
መልካም ገና!
𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 @liyusportet
*በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ
*በሥጋ
ማርያም ጌታ ተነሳ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
*በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
+በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው::
<< ለድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ ከስግደት ጋር ይሁን !!! >>
=>የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን:: ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን::
=>ታሕሳስ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አማኑኤል አምላካችን
2.በዓለ ጌና ስቡሕ
3.ዕለተ ማርያም ድንግል
4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
=>+"+ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-
'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል::'
የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው:: +"+ (ማቴ. 1:20)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
ውድ ቤተሰቦቼ ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከእነ ሙሉ ቤተሰቦቻችሁ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የመተሳሰብ በዓል ያድርግልን!
መልካም የገና በዓል ይሁንልን/ ይሁንላችሁ!!!
✞እንኳን ለሰማዕቱ "አባ አብሳዲ" እና ለጻድቁ "አባ በግዑ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ✞
+"+ ቅዱስ አባ አብሳዲ +"+
=>ቅዱሱን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::
+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::
+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::
+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::
+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::
+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታችን "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:18) እንዳለው ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::
+"+ ቅዱስ አባ አብሳዲ +"+
=>ቅዱሱ ሰማዕት ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ : በ3ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: እንደርሱ በቅድስና ያጌጠ ባልንጀራም ነበረው:: ስሙም ቅዱስ አላኒቆስ ነበር::
+እኒህ ክርስቲያኖች በዚያ የመከራ ዘመን ግራ ቀኝ ሳይሉ ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቀው ተምረዋል:: በጐውን ጐዳና አጽንተው በመገኘታቸውም መንፈስ ቅዱስ 2ቱንም በአንዴ ለእረኝነት ጠራቸው::
+ዽዽስና ከዚህ በፊት እንደ ተመለከትነው እዳ (ኃላፊነት) እንጂ ምድራዊ ክብርን ማጋበሻ መንገድ: ወይም የሥጋ ድሎትን መፍጠሪያ ዙፋን አይደለም:: ያም ሆኖ ምርጫው የመንፈስ ቅዱስ ሲሆን ደስ ያሰኛል::
+በእርግጥም የክርስቶስን መንጋ እንደሚገባ መምራትና በለመለመው የወንጌል መስክ ማሰማራት የሚያስገኘው ክብር በሰማያት ታላቅ ነው:: ያም ቢሆን ግን ከብዙ መከራ በሁዋላ እንጂ እንዲሁ በዋዛ አይደለም:: የእግአብሔር ጸጋውና መንግስቱ ያለ መከራ አትገኝምና::
+ቅዱሳኑ አባ አብሳዲና አባ አላኒቆስም ይህንን ኃላፊነት የተረዱ ነበርና ታጥቀው ሥራቸውን ጀመሩ:: እንደ ሐዋርያት ሥርዓትም ያላመነውን ማሳመን: ያመነውን በሃይማኖቱ ማጽናት: የጸናውን ደግሞ ለምሥጢራተ ቅድሳት (ሥጋ ወደሙ) ማብቃት የዘወትር ተግባራቸው ነበር::
+ቅዱሳኑ በዚህ ተጋድሏቸው ሳሉ ዜናቸው በየቦታው ተሰማ:: ነገር ግን ይህ ዝናቸው የወለደው መከራን ነበር:: በጊዜው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል ብሎ ነበር::
+ለክፋቱ እንዲመቸው በየሃገሩ ጨካኝ መኮንኖችን ሾመ:: በምድረ ግብጽም 2 ገዢዎችን ሲያኖር አንዱ አርያኖስ (በሁዋላ አምኖ ሰማዕት ሆኗል): 2ኛው ደግሞ ሔርሜኔዎስ ይባላሉ::
+እነዚህ መኩዋንንት ግብጽን ለ2 ተካፍለው: በሥራቸው ገዥዎችን ሹመው በግፍ ተግባራቸው ክርስቲያኖችን ይቀጡ ገቡ:: የስቃይ ተራው ደግሞ የ2ቱ ቅዱሳን (አባ አብሳዲና አባ አላኒቆስ) ነበርና ተከሰሱ::
+ለፍርድ ይቀርቡ ዘንድም አርያኖስ በማዘዙ ወታደሮች መጡ:: ነገሮችን አስቀድሞ የሚያውቀው ቅዱስ አብሳዲም ምንም ስለ ክርስቶስ ለመሞት ቢቸኩልም መንጋውን እንዲሁ ሊበትን ግን አልወደደም::
+ስለዚህም ወታደሮችን "እባካችሁ ሕዝቡን ልሰናበት : አንድ ቀን ታገሱኝ" አላቸው:: ወታደሮቹ ከፊቱ የሚታየው ግርማው ደንቁዋቸው ነበርና ፈቀዱለት:: ቅዱሱም ከሕይወቱ የቀረችውን 24 ሰዓት ይጠቀምባት ዘንድ ምዕመናን ልጆቹን ሁሉ ጠራ::
+ቅዳሴ ቀድሶ : ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ፈትቶ ለሁሉም አቀበላቸው:: (በጊዜው የማይቆርብ ክርስቲያን አልነበረምና)
+ከቅዳሴ መልስም የተፈጠረውን ሁሉ ነግሮ ወደ ክርስቶስ ሊሔድ እንደ ናፈቀ ነገራቸው:: ሊያስቀሩት እንደማይችሉ ሲረዱ ፈጽመው አዘኑ:: እርሱም በቀናችው እምነት እስከ ሞት ድረስ እንዲጸኑ አስተምሯቸው ከባልንጀራው ቅዱስ አላኒቆስ ጋር በወታደሮች እጅ ወደቀ::
+እነርሱም ቅዱሳኑን ወስደው በመኮንኑ አርያኖስ ፊት ለፍርድ አቀረቧቸው:: አርያኖስም የአባ አብሳዲ የፊቱ ግርማ ቢስበው ላለመግደል ወስኖ ሊያባብለው ወሰነ:: "አንተ ክቡር ሰው ነሕና ለንጉሡ ታዘዝ : ለጣዖትንም እጠን" አለው::
+ቅዱስ አላኒቆስ ግን "ክብሬ ክርስቶስ ነውና ፈጣሪየን በምንም ነገር አልለውጠውም" ሲል እቅጩን ነገረው:: እንደማያሳምነው ሲረዳም ከአባ አላኒቆስ ጋር ያሰቃዩአቸው ዘንድ አዘዘ::
+በምስክርነት አደባባይም በመንኮራኩር (አካልን የሚበጣጥስ ተሽከርካሪ ብረት ነው) አበራዩአቸው:: እግዚአብሔር ግን አዳናቸው:: እንደ ገና እሳት አስነድደው እዚያ ውስጥ ጨመሯቸው:: እሳቱም ግን ሊበላቸው አልቻለም::
+በመጨረሻም መኮንኑ አንገታቸው ይሰየፍ ዘንድ አዘዘ:: ከመሰየፋቸው በፊትም ቅዱሳኑ ጸሎትን አደረሱ:: አባ አብሳዲ ነጭ የቅዳሴ ልብሱን ለብሶ: ወደ ሰይፍ ቀረበ:: ወታደሮች ደግሞ ሁለቱን ቅዱሳን እንደታዘዙት ሰየፏቸው:: በክብርም ዐረፉ::
+"+ አባ በግዑ ጻድቅ +"+
=>እኒህ አባት በመካከለኛው ዘመን የሃገራችን ታሪክ ሰፊ ቦታን ይዘው ይገኛሉ:: ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በደብረ ሐይቅ ነው:: ጻድቁ ብዙ ጊዜ የሁዋለኛው ዘመን ሙሴ ጸሊም ይባላሉ:: ብዙ የሕወታቸው ጐዳና ተመሳሳይ ነው::
+ልክ ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ከኃጢአት ከሽፍትነት ሕይወት እንደ መጣው ሁሉ አባ በግዑም አስቸጋሪ ሰው እንደ ነበሩ ይነገርላቸዋል:: ከዚያ የከፋ የኃጢአት ኑሮ እግዚአብሔር ሲጠራቸው ግን ክሳደ ልቡናቸውን አላደነደኑም:: "እሺ" ብለው ንስሃ ገቡ እንጂ::
+ከዚያም በደብረ ሐይቅ (ወሎ) በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል:: ያዩ ሁሉም ፍጹም ያደንቁ ነበር:: ስትበላ: ስትጠጣ የኖረችውን ሰውነት ራሳቸውን ውሃ ለዘመናት በመከልከል ቀጥተዋታል:: ስለዚህም "ውሃ የማይጠጣው አባት" ይባሉም ነበር:: ጻድቁ ሲያርፉ ፈጣሪያቸው አክብሯቸዋል::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን አሠረ ፍኖታቸውን ይግለጽልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ታሕሳስ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አብሳዲ ሰማዕት
2.አባ አላኒቆስ ሰማዕት
3.አባ በግዑ ጻድቅ
4.አባ ፊልዾስ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ መድኃኔ አለም ቃል ኪዳን
ሲገባለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሁለተኛው ሊቀሰማዕት
አንተ ነህ ብሎታል ። በጣም የሚገርመው ቃል ኪዳን ደግሞ
የቅዱስ መርቆሬዎስን ስዕል አድኅኖ የያዘው ን ሰው የተወረረ ጦርም ሆነ ቀስት፤ የተተኮሰ ጥይትም ቢሆን አይነካውም ብሎ
መድኃኔ አለም ቃል ገብቶለታል። ገዳሙ ላይ ያለውም ስዕል
አድኅኖም ካህናት ማህሌት እና ሰዓታቱንሲያደርስ ፈረሱ ይንቀሳቀሳል። የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከቱ ይደርብን
*በክርስቶስ እጅ ተባርኩዋል
*ፈጣሪውን ፊት ለፊት አይቷል
*ሐዋርያትን አገልግሏል
*ከምሥጢር አባት ከዮሐንስ ወንጌላዊ እግር ተምሯል
*ስለ ክርስትና ለአንበሶች ተጥሎ በመገደሉ "ምጥው ለአንበሳ" ይባላል::+ቅዱስ አግናጥዮስ የተወለደው በክርስቶስ አምላካችን መዋዕለ ስብከት (በ30 ዓ/ም አካባቢ) እንደ ሆነ ይታመናል:: በትውፊትም በማቴ. 18:1 ላይ ያለው ሕጻን እርሱ ነው ይባላል::+ሐዋርያት ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ ሲጠይቁት አንድ ሕጻንን (አግናጥዮስን) ከመሃል አቁሞ "ካልተመለሳችሁ: እንደዚህም ሕጻንካልሆናችሁ ከቶውንም ወደ እግዚአብሔር መንግስት አትገቡም" ብሏቸዋል::
+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ሐዋርያት ለወንጌል ሲፋጠኑ ሕጻኑ ቅዱስ አግናጥዮስ እየተከተለ አገልግሏል: ተምሯል:: ኢየሩሳሌም በጥጦስ አስባስያኖስ ቄሣር በጠፋችበት ዓመት (በ70 ዓ/ም) ቅዱሱ የአንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሟል::
+ከዚህ በሁዋላም ለ2 እና 3 አሠርት ዓመታት ከወንጌላዊ ዮሐንስ ጋር አብሮ ወንጌልን ሰብኩዋል:: የዚህ ቅዱስ ተጋድሎ ጫፍ የደረሰው ከ100 ዓ/ም በሁዋላ ሁሉም ሐዋርያት ሰማዕት በመሆናቸውና ትልቁን ኃላፊነት እርሱ በመሸከሙ ነው:: የወቅቷን ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳኑ ቀሌምንጦስ ዘሮምና ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ ጋር ሆኖ እስከ ደም ጠብታ ጠብቁዋል::
+ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ አግናጥዮስ ለዘመናት ወንጌልን እየሰበከ በሕይወቱና በትምሕርቱ አስተማረ:: ብዙ መልእክቶችን (ድርሳናትንም) ጻፈ:: በመጨረሻው ግን በጠራብሎስ ቄሣር ተይዞ: በብረት ሰንሰለት ታስሮ: ከአንጾኪያ (ሶርያ) ወደ ሮም (ጣልያን) ተወሰደ::
+ደሙ እስኪፈስም ገረፉት:: ዛሬ በሮም ከተማ ግማሽ አካሉ ፈርሶ በሚታየው ስታዲየም (በአባቶቻችን አጠራር ተያጥሮን) እንዲገደል ተወሰነበት:: በወቅቱ ባደረገው ንግግርም ቄሣሩና ሕዝቡ ድፍረቱን አደነቁ:: በመጨረሻም ለአንበሳ እንዲሰጥ ተደርጐ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነ::
+" ቅድስት አስቴር "+
=>ይህቺ ቅድስት እናት:-
*እሥራኤል በባቢሎን ምርኮ ሳሉ የነበረች
*አባቷ አሚናዳብ ባለ መኖሩ በአጐቷ መርዶክዮስ እጅ ያደገች
*እጅግ ውብ በመሆኗ የአርጤክስስ ሚስት (ንግሥት) ለመሆን የበቃች
*ራሷን መስዋዕት አድርጋ ወገኖቿን አይሁድን ከሞት ያተረፈች
*ለመርዶክዮስ ክብርን: ለአማሌቃዊው ሐማ ደግሞ ስቅላትን ያስፈረደች እና
*እግዚአብሔር ሞገስ የሆናት እናት ናት::
*ዛሬ ዕረፍቷ ነው::
=>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን ባጸናበት ቅዱስ መንፈሱ እኛንም ያጽናን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ታሕሳስ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኃረያ
3.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያ
4.ቅድስት አስቴር
5.አባ ፊሎንጐስ ሊቀ ዻዻሳት
6.አባ ዻውሊ ጻድቅ
7.ጻድቃን ቅዱሳን ዘከዲህ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
2.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
3.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
4.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
5."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
=>+"+ ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ:- 'ንጉሥ ሆይ! በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ: ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው: ሕይወቴ በልመናዬ: ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ:: እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል: ለመደምሰስም ተሸጠናልና:: +"+ (አስቴር. 7:3)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
/channel/zikirekdusn
✝እንኳን አደረሰን።
ታኅሣሥ ፳፬፦
✝#ተክለሃይማኖት ሐዋርያ ምሥጢረ መለኮት ከሣቲ፤
ወጻድቃን #ዘከዲህ ኅዱራነ በአት አሐቲ፤
#አግናጥዮስ ብጹዕ በኃይለ ቃሉ ነሣቲ፤
#ጳውሎስ #ወፊሎንጎስ ባሕረ ጥበባት ጸባቲ፤
#አስቴር ጻድቅት #ወመርዶክዮስ አእኳቲ!
ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
#የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ምሳሌ 10፥7
❤ልደቱ ለአቡነ ተክለሐይማኖት❤
#ታህሳስ 24 በዚህች እለት በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስቅዱስ” ብለው ሥላሴን ያመሰገኑ ሐዋርያዊ መነኩሴ የወንጌል ገበሬ ሰዳዴ አጋንት የህሙማን ፈውስ የብዙዎች አባት የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ልደታቸው በታላቅ ክብር የሚከብርበት ታላቅ እለት ነው።💒
#የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው ፍጹም የሆነ ቃልኪዳናቸው አትለየን አሜን!!
#በኤፍራታ_ምድር
በኤፍራታ ምድር በቤተልሔም/2/
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም/2/
ብርሐናዊው ኮከብ ከሠማይ ዝቅ አለ/2/
ፍጥረትም ዘመረ ሀሌሉያ እያለ/2/
መንጋውን በለሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሠሙ ታላቅ የምስራች
በመላዕክት ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
ድንገትም በሠማይ ሠራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሠላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሠው
ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሣለሙት
ከእናቱ ጋር ሆነው በግርግም አገኙት
የመላዕክትን ዜማ እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ
በመዝሙር ቢሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሠዎች የድህነት ምልክት
/channel/mezmur_store
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
✝✞✝ እንኩዋን ለቅዱስ "አምላካችን አማኑኤል" : "ዕለተ ማርያም" እና "ዕለተ ጌና ስቡሕ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞
+*" ቅዱስ አማኑኤል "*+
=>የክርስትና ሃይማኖት እጅግ ብዙ ምሥጢራትን ያካትታል:: ታላቅ መዝገብ ነውና:: ሰዎች እናልፋለን:: ዓለምም ታረጃለች እንጂ ምሥጢረ ክርስትና አያረጅም:: እዚህ ቦታ ላይ ይጠናቀቃልም አይባልም::
+"አማኑኤል" የሚለውን ስም መረዳት የሚቻለው በአንድ መንገድ : እርሱም ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን ጠንቅቆ በመማር ነው:: ምሥጢራት ደግሞ በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::
+እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር: ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::
+ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::
+ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::
+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ባለቤቱ ያውቃል::
+እግዚአብሔር በሁዋለኛው ዘመን ሰው የሆነበት ምሥጢር እኛን ለማዳን ቢሆንም ይሔው ተግባሩ ዓለም ሳይፈጠር ያሰበው እንጂ በአዳም ውድቀት ምክንያት ድንገት የታሰበ አይደለም::
+እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው::
+ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር:: ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር: ሱባኤ ይቆጠር: ምሳሌም ይመሰል ገባ::
+ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ:: ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት / ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል::
+ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል:: እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል:: መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል::
+"አማኑኤል" የሚለው ቃል ከእብራይስጥ ልሳን (ከጽርዕ የሚሉም አሉ) በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ" እንደ ማለት ነው:: (ኢሳ. 7:14, ማቴ. 1:22) ምሥጢሩ ግን ከዚህ የሠፋ ነው::
+"አማኑኤል" ማለት "እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋን: ከነፍሳችን ነፍስን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ እኛን መሰለን" ማለት ነው:: በሌላ አነጋገርም "አምላክ ሰው ሆነ: ሰውም አምላክ ሆነ" እንደ ማለት ነው::
+ይሕንን ሲያደንቁ ቅዱሳን ሊቃውንት "ወዝንቱ ስም ዓቢይ: ወኢይደሉ ፈሊጦቶ-ይህ ስም ታላቅ ነው:: ወደ ሁለት ሊከፍሉት (ሊለዩት) አይገባም" ብለው ምሥጢረ ተዋሕዶን አስረድተዋል:: (ሃይ. አበ. ዘሳዊሮስ)
+ስለዚህም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ እኛን ያድን ዘንድ በተለየ አካሉና በከዊነ ቃልነቱ ፍጹም የድንግል ማርያምን ሥጋ ተዋሕዶ የሰውነትንም: የአምላክነቱንም ሥራ ሠርቶ አድኖናል::
+በማሕጸነ ድንግል ከተቀረጸባት ደቂቃ ጀምሮም ፍጹም ተዋሕዶን ፈጽሟልና መቼም መች አምላክም: ሰውም ነው እንጂ ወደ ሁለትነት: ማለትም አምላክን ለብቻ: ሰውን ለብቻ አናደርግም::
+ስለዚህም ዛሬም: ዘወትርም እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደው ሥጋችን በዘባነ ኪሩብ ሲሠለስና ሲቀደስ ይኖራል:: እርሱ ጌታችን እስከዚህ ድረስ ወዶናልና::
+ፈጣሪያች በሦስትነቱ:- ሥላሴ (አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ): በአንድነቱ:- እግዚአብሔር: ኤልሻዳይ: አልፋ: ወዖ: ቤጣ: የውጣ: ኦሜጋ . . . እያልን እንደምንጠራው ሁሉ በሥጋዌው ምክንያት:- አማኑኤል: መድኃኔ ዓለም: ኢየሱስ: ክርስቶስ እያልን እንጠራዋለን::
+*" ዕለተ ጌና "*+
=>ከሳምንታት በፊት ጀምረን የክርስቶስን የማዳን ሥራ ለመገንዘብ እየሞከርን ቆይተናል:: በተለይ ታኅሳስ 7 ቀን "ስብከት" በሚል ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት መነገሩን: ምሳሌ መመሰሉን: ሱባኤ መቆጠሩን ተመልክተን ነበር::
+ቀጥለን ደግሞ ታኅሳስ 14 ቀን "ብርሃን" በሚል አምላካችን እንደ ምን ባለ ጥበቡ ብርሃኑን እንደ ሰጠን: አንድም ወደን ወደ ጨለማ በገባን ጌዜ ሥጋችንን ተዋሕዶ ብርሃን እንደ ሆነልን ለማየት ሞክረናል::
+ታኅሳስ 21 ቀን ደግሞ በበደላችን ምክንያት የነፍሳችንን እረኛ አጥተን ነበር:: ለእኛው በደል እርሱ ክሶ ድጋሚ መልካም እረኛችን ሆኖ በሥጋ ማርያም መለገለጡን አየን:: የዛሬው በዓል ዕለተ ጌና ደግሞ ማሠሪያው ነው::
+"ጌና" ማለት በቁሙ "ዕለተ ልደት ስቡሕ: ማለትም አምላክ ሰው የሆነበት ምስጉን ቀን" እንደ ማለት ነው:: ይህ ቀን ሁሌም በየዓመቱ "አማኑኤል (ጌና)" እየተባለ ይከበራል:: ምክንያቱ ደግሞ ጌታ የተጸነሰ መጋቢት 29 ቀን በመሆኑና ከዚህ ቀን 9 ወር ከ5 ቀናት ብንጨምር ይህ ዕለት ታሕሳስ 29 ቀን ይመጣል::
+ነገር ግን በ4ኛው ዓመት ዘመነ ዮሐንስ ዻጉሜን 6 ስትሆን 9 ወር ከ6 ቀን ስለሚሆን ቀኑን እንዳይለቅ በዘመነ ዮሐንስ ዕለተ ልደቱ ለክርስቶስ ታሕሳስ 28 ቀን ይከበራል:: ያም ሆኖ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሳስ 28ን አክብረናል ብለን 29ን አንተወውም:: እርሱም ይከበራል::
+በዚያው ልክ ደግሞ በ3ቱ አዝማናት (በማቴዎስ: በማርቆስና በሉቃስ) ልደቱ በ29 ነው ብለን 28ን አንሽረውም:: "ጌና-አማኑኤል-ዕለተ ማርያም" እያልን እናከብረዋለን እንጂ:: ብዙ ጊዜም በተለምዶ በዓለ ልደትን "ጌና" በማለት ፈንታ "ገና" የምንል ብዙዎች አለን::
+ግን አበው ባቆዩልን ትውፊት "ጌና" ልደቱን የሚመለከት ሲሆን "ገና" ግን ባሕላዊ ጨዋታውን የሚመለከት ቃል ነው::
+*" ዕለተ ማርያም "*+
=>ዳግመኛ ይህ ቀን ዕለተ ማርያም ይባላል:: "ማርያም" የሚለው ቃል ብዙ ትርጉምን ያዘለ የእናታችንና የእመቤታችን: የተስፋችንና መመኪያችን: የድንግል እመ ብርሃን ስም ነው::
+ክርስቶስ ተጸነሰ-ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ: የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር: ምስጋና: ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል:: መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና::
+ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት) ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል:-
*በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
*በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
*በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ::
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
=>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🛑+++ወትረ ዝክረ ቅዱሳን+++🛑
=>የዩቱዩብ ቻነል<=
ZekereKedusan?si=7acGUCDCLO2Qxl37" rel="nofollow">https://youtube.com/@ZekereKedusan?si=7acGUCDCLO2Qxl37
=>የቴሌግራም ቻነል<=
/channel/zikirekdusn
🌕🌖🌗"እንኳን ለታላቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን! አደረሳችሁ!"🌗🌖🌕
‹‹እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፡፡ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል፡፡ ማንም ከእነዚህ ከተናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋው አይጠፋበትም፤›› /ማቴ.፲፥፵-፵፪/
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ታኅሳስ24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት: ቅዱስ አግናጥዮስ እና ቅድስት አስቴር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱስ #ተክለ_ሃይማኖት ሐዋርያዊ "*+
*ልደት*
=>መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: #ጸጋ_ዘአብ ካህኑና #እግዚእ_ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
+በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው #ቅዱስ_ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::
+አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::
*ዕድገት*
=>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " #ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ #አባ_ጌርሎስ ተቀብለዋል::
*መጠራት*
=>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:
"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::
*አገልግሎት*
=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ ( #ጽላልሽ ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ #ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት::
1.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::
+ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት #ሐዲስ_ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::
*ገዳማዊ ሕይወት*
=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::
+እነዚህም በአቡነ #በጸሎተ_ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ #ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ #ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::
+በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ #ዞረሬ ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::
*ስድስት ክንፍ*
=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ #እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
+የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት #አባ_ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::
+ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
¤በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤በቤተ ልሔም ልደቱን
¤በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው #ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ፈጥና ደርሳ ጻድቁን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::
+በዚያም:-
¤የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤6 ክንፍ አብቅለው
¤የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
*ተአምራት*
=>የጻድቁ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::
+ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
*ዕረፍት*
=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24, በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
=>የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች :-
1.ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2.ፍስሐ ፅዮን
3.ሐዲስ ሐዋርያ
4.መምሕረ ትሩፋት
5.ካህነ ሠማይ
6.ምድራዊ መልዐክ
7.እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለስድስት ክንፍ)
8.ጻድቅ ገዳማዊ
9.ትሩፈ ምግባር
10.ሰማዕት
11.የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12.ፀሐይ ዘበፀጋ
13.የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14.ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15.መናኒ
16.ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)
=>እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:
+" ቅዱስ አግናጥዮስ "+
=>ይህ ቅዱስ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠገበ በመሆኑ በመላው ዓለም ዝነኛ ነው:: እርሱ:-
†
[ 🕊 የኢትዮጵያ ብርሃን 🕊 ]
✞ ታህሣስ ፳፬ ✞
† እንኩዋን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት : ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †
🕊
† ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት †
- አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት ፳፬, በ፩ ሺህ ፪ መቶ ፮ [1206] (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ ፳፬ [24] , በ፲፻፯ [1207] (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል::
"...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም።
ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር።
እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን [፳፪ [22] ዓመታት] ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው አልጠጣም"።
[ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ]
[ የኢቲሳ አንበሳ ፥ የኢትዮጵያ ብርሃን ፥ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐራሴ ወንጌል ፥ የጣኦታት ጠላት ፥ ጣኦታትን የሰባበሩ ፥ የአምላካቸውን ስም ያስከበሩ ፥ ሐዲስ ሐዋርያ በረከታቸው ይደርብን ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን፡፡ ]
† † †
💖 🕊 💖