#አስቸኳይ_መልዕክት!
#ሼር_ይደረግ!
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።
ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኛሉ ሲሉ መረጃ ሰጭዎቻችን አድርሰውናል።
©ማኅበረቅዱሳን ብሮድካስት
.........ፍቅርን ብለሽ...!
፨፨፨///////፨፨፨ፍቅርን ብለሽ ብታቀረቅሪ፣ አንገትሽን ብትደፊ፣ ብትታዘዢ፣ ዝቅ ብትይ፣ እራስሽን ብትሰዊ፣ እራስሽን ብትሰጪ ምንም ክፋት የለውም። ክፋቱ ፍቅርን ብለሽ ባቀረቀርሽበት ስትረገጪ ነው፤ ፍቅርን ብለሽ እራስሽን በሰጠሽበት ስትሰቃዪ ነው፤ ፍቅርን ብለሽ ብትታዘዢ እንደባሪያ ስትቆጠሪ ነው። ሁሌም ያንቺ ፍቅር በመልካም ሃሳቦች፣ በቅን ተግባሮችና በበጎ ሁነቶች የተደገፈ ሊሆን ይችላል፣ የተቀባዩ ግን በበደልና በክፋት ከታገዘ፣ በጭካኔ ከተሞላ፣ ርህራሄ ከራቀው፣ ፍቅርን ካልታደለ ያንቺ ፍቅርን መምረጥ፣ በፍቅር መመላለስ፣ ፍቅርን ማለት አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም። ፍቅር እንዲገባው የሚፈልግ ሰው ይገባዋል፤ ካልፈለገ ግን ሊገባው ቀርቶ ምንም ለመረዳትና ለማስታወስ አይፈልግም።
.....✍️ጀግኒት..! ፍቅርን ብለሽ ፍቅርን አትግፊ፤ ያተረፍሽ መስሎሽ አታጉድይ፣ ያገኘሽ መስሎሽ አትጪ፤ ባንቺ ውስጥ ባለው ስሜት ብቻ እየተመራሽ አንቺን ብሎ ከመጣው አትሽሺ። በፍቃድሽ ሰዶ ማሳደድ ውስጥ አትግቢ። ለእውነተኛ ስሜትሽ፣ ለጥልቅ ፍቅርሽ ዋጋ ብትከፍይም፣ ብትሰቃይም፣ ብትወጪም ብትወርጂም ይህ ሁሉ መሱዓትነት ለፍቅርሽ ዋስተና፣ ላንቺም ደህንነት ጠበቃ ሊሆንሽ እንደማይችል አስታውሺ። ስትወጂው የማይወድሽን፣ ጊዜ ስትሰጪው ጊዜ የማይሰጥሽን፣ ስትከተይው የሚሸሽሽን፣ ስትደግፊው የሚጎዳሽን፣ ስታክሚው የሚያሳምምሽን እያሳደድሽ ተንከባካቢሽን፣ ውድ አፍቃሪሽን፣ ጠባቂሽን እንዳታጪ፣ በምላሹም ከረፈደ ወደማሳደድ እንዳትገቢ ተጠንቀቂ።
.....✍️ጀግናዬ..! የሚያለቅስልህ፣ የሚያስብልህ፣ የሚራራልህ እያለ ለሚስቅብህ፣ ለሚያፌዝብህ፣ ለሚቀልድብህ አታልቅስ። ላንተውን ጊዜን የሚያመቻች እያለ በትፍ ጊዜ ከሚያስታውስህ ጋር አትታገል። ፍቅርህን ከረገጠው ባላይ በፍቅር የሚያነግስህ አለ፤ መውደድህን ካኮሰሰው በላይ በፍቃዱ የሚንከባከብህ አለ። ለፍቅርህ ብለህ ብቻህን ዋጋ ብትከፍል፣ ብትሰበር፣ ብትጋጣ፣ ብትላላጥ፣ ብትገፋ፣ ብትረሳ እራስህን ታጣለህ እንጂ ፍቅርህን አታተርፍም፤ ማንነትህን ታሳንሳለህ እንጂ ለክብር አትበቃም፤ በስቃይ ትሞላለህ እንጂ ሰላምን አታገኝም። ዋጋ መክፈልህ ድጋፍ ይፈልጋል፤ መሱዓትነትህ አጋዥ መሶዓትነት ይጠበቅበታል። ብቻህን ጥረህ፣ ግረህ የእራስህን ቤት ልትገነባ ትችላለህ ነገር ግን ብቻህን ለፍተህና ደክመህ እኩልነት የሰፈነበት፣ በነፃነት የተሞላ፣ በፍቅር የታነፀ የጋራ ቤት መገንባት እንደማትችል አስታውስ። ቢያንስ የጋራ ጥረትና ልፋት ምሰሶውን ማቆሙ የግድ ነው።
#share 👉የቴሌግራም ቻናላችን👇👇
...✍️ t.me/Asresee
...✍️ t.me/Asresee
ጥር 26/2016 #ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
"የቅዱሣኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ መዝ 115፥15"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለአረጋዊ_ዮሴፍ እና ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉አረጋዊዉ #ቅዱስ_ዮሴፍ በእርጅና ዘመኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምን ለመጠበቅ የተመረጠና በመፅሐፍ ቅዱስም ፃድቅ ተብሎ የተመሠከረለት ነዉ ማቴ 1፥19 ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን"
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ አባት አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝምተኝነትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"
📒➱የንስሐ ጸሎት🙇🥀🕯
➱ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ አዳምን ከሲኦል ፣ ኖህን ከውሃ ጥፋት ፣ ይስሃቅን ከመታረድ ፣ እስራኤልን ከፈርኦን ፣ ዳዊትን ካሳኦል ፣ ኤልያስን ከኤልዛቤል ፣ መርዶክዮስን ከሀማ ፣ ሰልስቱን ደቂቅን ከእቶን እሳት ፤ ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ባሪያህን ከመከራ ስጋ ከመካራ ነፍስ አድነኝ ። በዚህ አለም ስኖር ከርሃብ ፣ ከጥማት ፣ ከመሰደድ ፣ ከመንገላታት ፣ በኃይለኞችና በጨካኞች እጅ ከመውደቅ አድነኝ ፤ ለንሰሐ ሞት አብቃኝ ፤ የሗላ ቤቴን አሳምርልኝ ፤ ከዳግም ሞት አድነኝ አሜን!
አቤቱ አምላኬ ሆይ ኢዮብን ከቁስል ፣ አላዛርን ከመቃብር ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም ፣ ዮናስን ከአሳነባሪ ፣ ምናሴን ከብረት ቀፎ ፣ ሙሴን ከዳታንና ከአቤሮን ፣ አሮንን ከደቂቀ ቆሬ ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አድነኝ ፤ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ዳንኤልን አእፈ አናብስት ፣ ሶስናን ከእደ ረበናት ፣ ሎጥን ከሰዶምና ከገሞራ ፣ ዲቦራን ከሲሳራ ፣ ያእቆብን ከወንድሞቹ ፣ ሶምሶምን ከእርግውና ወደ ውርዝውና የመለስክ ፤ የበለአምን አህያ ያናገርክ እኔንም ባርያህን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ሰውረኝ ፤ በንፅህና ሆኜ ቅዱስ ስጋህን እና ክቡር ደምህን እየተቀበልኩኝ ለመኖር ፍቀድልኝ ከዚህ አለም እሾህና አሜኬላ አድነኝ አሜን!
አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሰባ ነገስታት ፣ ጦቢትን ከአይን ህመም ፣ ብሩክ ታዊትን ከአፍ ደራጎን ፣እግዚሃርያን ከመቶሎሚ ፣ የአትናስያን ሞት ወደ ህይወት የመለስክ ፣ በላኤሰብን የማርክ ፤ አክሊለ እሾህን ያጠለክ ፣ በቅድመ አይሁድ እስራትና ግርፋት ለአለም ቤዛነትን የተቀበልክ ፣ በፆረ መስቀል በፍኖተ አምስት ጊዜ የወደቅህ ፣ በፊትህም በኃላህም ምራቀ አይሁድን የተቀበልክ ፣ በቀራንዮ በእለተ አርብ ደምህን ያፈሰስክ ስጋህን የቆረስክ ፣ ህማማተ መስቀልን የተቀበልክ ፣ የእውሩን አይን ያበራክ ፣ ለምፃሙን ያነፃክ ፣ ጎባጣውን ያቀናክ ፣ ዲዳን ያናገርክ ፣ አንካሳን የፈታህ ፣ ባህርን ያናወፅክ ፣ ፴፰ አመት በአልጋ ቁራኝነት የነበረውን መፃጉን ያዳንክ ፣ ያመኑብህን የማትጥል ፣ ሰማይና ምድርን በቃልህ ያቆምክ ፣ መአልቱን በሌሊት በጋውን በክረት የምታፈራርቅ ፣ አካልህ የማይዳሰስ ቃልህ የማይገሰፅ ፣ መንግስትህ አያልፍ ፣ ከተሾምክ ያልተሻርክ የማትሻር ፣ ከተወለድክ የማታረጅ ያላረጀክ ፣ ከአለም በፊት የተገኘህ አለምን አሳልፈህ ለዘለአለም የምትኖር አልፋና ኡሜጋ ኤልሻዳይ አዶናይ ፀባኦት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከክፋት ወደ በጎነት መልሰኝ ፤ ሀይል መዊእ ለዳዊት የሰጠህ ለእኔም ስጠኝ እድሜ ለማቱሳላ ፣ ፅድቅ ለቅዱስ ላሊበላ የሰጠህ ለእኔም እድሜ ለንሰሐ ፅድቅ ለፍሰሀ ስጠኝ ፤ መልአከ ጠባቂዬን አበርታልኝ ከሰውና ከእግዚአብሔር የሚስማማ ምግባርን ስጠኝ ፤ በተወለድኩበት አገር ክፋን ነገር አታሳየኝ ፤ የመላእክት የሰማእታት የፃድቃን የነቢያት የሐዋርያትና የምእመናን የደብርን የገዳማትን የእፅነ የእንስሳትን የአእሩግን የህፃናትን የንጉስን የመስተጋድል ልመና ፀሎት የተቀበልክ አምላክ የእኔንም ልመና ፀሎት ስማኝ ተቀበለኝ ። "
""፩// እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
""፪// በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
""፫// ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
""፬// በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
""፭// በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
""፮ // ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።
መዝሙር ዳዊት ፳፪፥፩-፮🕯
መሐረኒ እመከራ ስጋ እመከራ ነፍስ ዓለም ለዓለም አሜን !!!
🕯🥺🕯🖤
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስም በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን የገደለው በዚሁ ዕለት ነው፡፡ (የዕረፍቱን ዕለት ኅዳር ሃያ አምስትን ይመለከቷል፡፡)
‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡
መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል፡፡
የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
መንግሥት ሰማያት ማለት ከትንሣኤ ሙታን ቡሃላ ፃድቃን የሚኖሩባት ሰማያዊት ሀገር ናት።
ገነት ማለት ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በደስታና በፍቅር የሚገናኝበት እስከ ትንሳኤ ሙታን የፃድቃን ነፍስ የምትቆይባት በሰማይ እና በምድር መካከል ያለች ቦታ ነች።
እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።
ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014
inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER
#ጊዜ …
👉👉 ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት ። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን ። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች ።
👉👉 ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ ሀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን ።
👉👉 በከረጢትዋ ውስጥ ያሉት ፈርጦች አንድ ባንድ ፣ አንዳንዴም ካንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ ።
👉👉 ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም ። ድህነት የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም ።
#_ምንጭ :- የተቆለፈበት ቁልፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ
💚@ t.me/Asresee
💛@ t.me/Asresee
❤@ t.me/Asresee
#እንኳን ለጌታችን #አማኑኤል_ክርስቶስ ዓመታዊ የታአምር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ/አደረሰን🙏🕯️
#አምላካችን ቅዱስ #አማኑኤል በዚህች ዕለት ተአምራትን በማድረግ (፯) እንጀራና በ(፪)ዓሣ ሴቶችና ህፃናት ሳይቆጠሩ አምስት_የገበያ ህዝብ አበርክቶ ያጠገበበት ዓመታዊ ክብረ በዓል መታሰቢያ ነው እንኳን አደረሰን ።
#በመጽሐፍ_ቅዱስ ላይ የተመዘገበው ይህ የጌታችን ተአምር በውስጡ ብዙ ምሥጢራትን የያዘ ነው እንጂ ስለ ሥጋዊ ምግብ ብቻ የተነገረ አይደለም ማቴ 14 ቁ13÷23
#የተመገቡትና የተቆጠሩት አምስት_ሺህ ወንዶች ብቻ ናቸው እንጂ ሴቶችና ሕጻናት አልተቆጠሩም ይህስ ለምን ነው ቢሉ ሴቶች በአደባባይ ሲበሉ በሃፍረት ዳር ዳር ስለሚሉ ነው ሕጻናት ደግሞ ከሚበሉት የሚፈረፍሩት ይበዛልና ነው
#ጌታችን ያንን ሁሉ ሕዝብ በመንደር አጠገብ ሊመግባቸው ሲችል ለምን አርቆ ወደ ምድረ_በዳ ወሰዳቸው ከተባለ ስለ ሁለት ምክንያት ነው
#አንድም ‹‹ጥንት አባቶቻችሁን ከመንደር (ከግብጽ) አውጥቼ አርባ ዘመን ሙሉ መና የመገብኳቸው እኔ ነኝ አሁንም በሥልጣኔ በተአምራቴ መገብኳችሁ›› ሲላቸው ነው
#አንድም ጌታችን ተአምራቱን ከመንደር አጠገብ አድርጎት ቢሆን ኖሮ ሁልጊዜ ክፋትንና ጠማማ ነገርን ማሰብ ለአይሁድ ልማዳቸው ነውና ‹‹ፈጣን ፈጣን ደቀ መዛሙርቱን በጎን ወደ መንደር እየላከ ያስመጣው ነው›› ይሉት ነበር
#ስለሆነም ጌታችን ለጥርጥር ምክንያት እንዳይኖራቸው አድርጎ ነው ተአምራቱን የገለጠላቸው ጊዜውም አመሻሽ ላይ ነበርና ምሽት ላይ ያደረገበትም ምክንያት ጠዋት ላይ ቢሆን ኖሮ ‹‹የበላነው ሳይጎድል ነው ያበላን›› ብለው ከማመን ይርቁ ነበር
#በተጨማሪም በበረሃ ያውም በምሽት ሕዝቡን በውኃ አጠገብ በሣር ላይ አስቀምጧቸው መመገቡ ‹‹በፍጻሜው ዘመን በምቹ ስፍራ በመንግሥተ_ሰማያት መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ በውኃ በጥምቀት በሚገኝ ክብርም አከብራችኋለሁሲላቸው ነው
#ተአምራቱን ከውኃ ዳር ማድረጉ ‹‹መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው ሳር የበዛበት ቦታ ላይ ማድረጉም ‹‹መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው
#አምስቱ_እንጀራ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ማለትም የምሥጢረ ሥላሴ፣ የምሥጢረ ሥጋዌ፣ የምሥጢረ ጥምቀት፣ የምሥጢረ ቁርባንና የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ምሳሌዎች ናቸው፡፡
#ሁለቱ ዓሣ ደግሞ የፍቅረ_እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌዎች ናቸው ፍቅረ_እግዚአብሔር ማለት እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ነፍስና በፍጹም ሐሳብ መውደድ ነው ፍቅረ ቢጽ ደግሞ ባልንጀራን እንደራስ አድርጎ መውደድ ነው፡፡ አንድም ደግሞ እንጀራውና ዓሣው የቅዱስ #ሥጋውና የክቡር #ደሙ ምሳሌ ነው
#ቅዱስ_አማኑኤል ስለ አባቶቻችን ስለ ቅዱስ አብርሐም ስለ ይስሐቅ ስለ ያዕቆብ ብሎ በበረከት በረድኤት ይጎብኘን🙏 አሜን፫
#አምላካችን_ቅዱስ_አማኑኤል (፳፰)አባቴ ደግፈኝ እንዳልወድቅ 🙏❤️🕯️
†✝† እንኳን ለጌታችን አማኑኤል ክርስቶስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
✝ተአምረ እግዚእ✝
††† "ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል::
ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::
እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1 ነገሥት) እንደ ነበር ይታወቃል::
እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12)
እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)
††† ተአምራተ እግዚእ †††
††† ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: እያንዳንዱ ግን ቢጻፍ ዓለም ለራሷ ባልበቃች ነበር:: ከእነዚህ መካከልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በዚህ ዕለት በ7 እንጀራ እና በጥቂት ዓሣ ሴቶችና ሕፃናትን ሳይጨምር 4,000 ሰዎችን በቸርነቱ አበርክቶ አጥግቡዋል:: ደቀ መዛሙርቱም 7 ቅርጫት ማዕድ አንስተዋል::
ጌታችን በከሃሊነቱ የተራቡትን ሲያጠግብ እንዲሁ አይደለም:: በጊዜው የነበሩ አይሁድ ጠማሞች ነበሩና እነሱን ምላሽ በሚያሳጣ መንገድ ነበር እንጂ:: አይሁድ ላለማመን ብዙ ጥረት ነበራቸውና::
በዚህ ዕለትም እንጀራውን አበርክቶ ሲያበላቸው:-
1.ጊዜው አመሻሽ ላይ ነበር:: ምክንያት:- ጧት ላይ ቢሆን ከቤታችን የበላነው ሳይጐድል ብለው ከማመን ይርቁ ነበርና::
2.ከውሃ ዳር አድርጐታል:: መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::
3.ሳር የበዛበት ቦታ ላይ አድርጐታል:: ምክንያቱም መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::
4.ከከተማ አርቆ ምድረ በዳ ላይ አድርጐታል:: ያማ ባይሆን "ፈጣን: ፈጣን ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው እየገዙ አቀረቡለት" ባሉ ነበርና::
††† ለመድኃኒታችን ክርስቶስ አምልኮና ምስጋና ይሁን!
አማኑኤል አምላካችን ጣዕመ ፍቅሩን ያሳድርብን::
††† ጥር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት (ስለ ሃይማኖት 7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ, 7 አክሊል የወረደለት)
2.ቅዱስ አካውህ መነኮስ
3."800" ሰማዕታት
4.ቅዱስ ዮሴፍ አይሁዳዊ (የእመቤታችን ወዳጅ)
5.ቅድስት ሳቤላ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባቶቻችን አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
††† "ጌታ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ:- ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስከ አሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ:: በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም' አላቸው::
ደቀ መዛሙርቱም:- 'ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?' አሉት:: ጌታ ኢየሱስም:- 'ስንት እንጀራ አላችሁ?' አላቸው:: እነርሱም:- 'ሰባት: ጥቂትም ትንሽ ዓሣ' አሉት::
ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ:: ሰባቱንም እንጀራ: ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ:: ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ:: ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ:: ሁሉም በሉና ጠገቡ:: የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሱ:: የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ::" †††
(ማቴ. 15:32)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
ጥር 27/2016 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ
👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት
👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር
👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን በሚሰቀል ጊዜ የተገኙ እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግን ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አባታችን አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ጥር 26/2016 #ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
"የቅዱሣኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ መዝ 115፥15"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለአረጋዊ_ዮሴፍ እና ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉አረጋዊዉ #ቅዱስ_ዮሴፍ በእርጅና ዘመኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምን ለመጠበቅ የተመረጠና በመፅሐፍ ቅዱስም ፃድቅ ተብሎ የተመሠከረለት ነዉ ማቴ 1፥19 ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን"
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ አባት አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝምተኝነትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"
✅ ሜላት ✅
23 ሰው add ስላደረጉ በላኩልን አካውንት 2300 ብር ገቢ አድርገናል add ስላደረጉ እናመሰግናለን🎁🎁
🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🏪🏪
🌐🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁☄️
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን እንዲሁም መንፈሳዊ ቦታዎችን መጎብኘት የምትፈልጉ join በማለት ይቀላቀሉን ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።
/channel/meazahaymanot
Share
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥር 25-ከበሬ ጋር ተጠምደው በማረስ ሰማዕትነት የተቀበሉት አቡነ ሕፃን ሞዐ ልደታቸው ነው፡፡
+ የሮሙ ንጉሥ ልጅ ቅዱስ ስብስትያኖስ ምስክርነቱን ፈጽሞ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ ራሱን የሸጠው ቅዱስ ጴጥሮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም በቀድሞ ሕይወቱ ‹‹ርኅራኄ የሌለው፣ ንፉጉ ሰው›› እየተባለ እስከመጠራት ድረስ ለድኆች የማይራራ ባለጸጋ የነበረ ሲሆን በኋላም በተአምራት የምጽዋትን ጥቅም ዐውቆ ንብረቱን ሁሉ የመጸወተ ነው፡፡ ንብረቱንም ሁሉ መጽውቶ ለድኆች የሚሰጠው ቢያጣ ራሱን ሸጦ የጉልበት ሥራ በመሥራት የሚመጸውት ሆነ፡፡
+ ዳግመኛም ይህች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን የገደለባት ዕለት ናት፡፡
የሮሙ ንጉሥ ልጅ ሰማዕቱ ቅዱስ ስብስትያኖስ፡- አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡
ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይሰውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ እያሳረደ ክርስቲያኖችን አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል ጀመረ፡፡ በዘመኑም ሰማዕት የሆኑት የክርስቲያኖች ቁጥር ከ470,000 (አራት መቶ ሰባ ሺህ) በላይ ናቸው፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡
ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች ሰውነቱን አስነደፈው፡፡ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡
ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስገድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በአንደኛው ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ የቅዱስ ስብስትያኖስያኖስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ራሱን የሸጠው ቅዱስ ጴጥሮስ፡- ይኸውም ለድኆች ለመመጽወት ሲል ራሱን በገንዘብ የሸጠ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ አስቀድሞ ቀራጭ ነበር፡፡ እርሱም ልቡ የደነደነ ርኅራኄ የሌለው ንፉግ ሰው ነበር፡፡ የሚያውቁትም ሰዎች ሁሉ ‹‹ጨካኙ፣ ንፉጉ›› እያሉ ይጠሩት ነበር፡፡ የኃጢአተኛውን ሞት የማይሻ ጌታችንም ሊያስተምረው ፈልጎ አንድ የሚለምን ድኃ ሰው ወደ እርሱ ላከለት፡፡ ድኃውም ሰው ጴጥሮስን እየለመነው እያለ አገልጋዩ ከውስጥ እንጀራ ይዞ ሲወጣ ደረሰ፡፡ ጴጥሮስም አድርጎት የማያውቀውን ቶሎ ብሎ ቁራሽ እንጀራ ለዚያ ድኃ ጣለለትና ቶሎ ሂድልኝ አለው፡፡ እንጀራውንም የሰጠው ለድኃው ራርቶለት ሳይሆን ቶሎ ከፊቱ ዘወር እንዲልለትና ዳግመኛ መጥቶ እንዳይጠይቀው ነው፡፡ ምስኪኑም እንጀራውን ተቀብሎ ሄደ፡፡
ጴጥሮስም በዚያች ሌሊት ተኝቶ ሳለ በእጆቻቸው ሚዛን ይዘው መላእክተ ጽልመት የሰውን ኃጢአት እየመዘኑ በግራ በኩል ሲያስቀምጡ አየ፡፡ የጴጥሮስንም ኃጢአት በዚያው ሲያኖሩ አየ፡፡ መላእክተ ብርሃናትም በሚዛናቸው በቀኝ ባለው ሚዛን የሚያስቀምጡለት መልካም ነገር አጡበት፡፡ ከእነርሱም አንዱ መልአክ ጴጥሮስ ለድኃው የጣላትን እንጀራ አምጥቶ ‹‹ከዚህች እንጀራ በቀር ሌላ በጎ ሥራ አላገኘሁለትም›› አላቸው፡፡ ጴጥሮስም ይህንን ሕልም አይቶ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከተኛበት ተነሣ፡፡ ከዚህች ቀን ወዲህ ስለ ክፉ ሥራው ማዘንና መጸጸት ጀመረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ በኋላ እጅግ የሚራራ ሆነ፡፡ ያለውን ንብረቱን ሁሉ አውጥቶ ሸጦ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች መጸወተ፡፡ በመጨረሻም ለድኆች የሚሰጠው አንዳች ነገር ቢያጣ ራሱንም ሸጦ በጉልበቱ እየሠራ የሚያገኘውን ይመጸውታል፡፡ ይህ ሥራውም በብዙዎች ዘንድ ሲታወቅበት ውዳሴ ከንቱን ሸሽቶ ከአባ መቃርስ ገዳም አስቄጥስ ገባ፡፡ በዚያም መነኮሰና በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፡፡ እግዚአብሔርን ሲያገለግል ከኖረ በኋላ ፍጹም የሆነ ተጋድሎውን ፈጽሞ ዕለተ ዕረፍቱን ዐወቀ፡፡ ቀኑም ሲደርስ ቅዱሳንን ጠርቶ ተሰናበታቸውና በዚህች ዕለት ጥር 25 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ከበሬ ጋር ተጠምደው በማረስ ሰማዕትነት የተቀበሉት አቡነ ሕፃን ሞዐ ልደታቸው ነው፡፡ (የዕረፍታቸውን ዕለት ሐምሌ ሃያ አምስትን ይመለከቷል፡፡)
አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
/channel/zikirekdusn
†✝† እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††
††† ልደት †††
††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን
የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው::
እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ
እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ
ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ
አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን
መወለድ አብስሯቸዋል::
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን
በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን
በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት
ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::
††† ዕድገት †††
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል::
ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው
አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት:
ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ
እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ
ተቀብለዋል::
††† መጠራት †††
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት
ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት
በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ
ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን::
ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር
ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ
ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም::
ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው
እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::
††† አገልግሎት †††
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል
አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው
ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን
አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት::
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች
ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን
ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ
ተነቃቅቶ ነበር::
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ
መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን:
መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን
(ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል::
††† ገዳማዊ ሕይወት †††
††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን
ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል::
እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት
አገልግለዋል::
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት:
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ
ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26
ዓመታት አገልግለዋል::
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ
(ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት
ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን
በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::
††† ስድስት ክንፍ †††
ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት
ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ
መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
ከወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው
ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ
ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ
ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም
ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት
የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ
ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት
ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና
ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል
ማርያም ፈጥና ደርሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ
አሳረገቻቸው::
††† በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ
ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
††† ተአምራት †††
የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት
የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን
መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ
ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን
ታሥሯልና::
††† ዕረፍት †††
††† ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን
ሆነው: መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን
አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው
ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል
ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10
ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
††† በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት
የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሠበሩንና በአንድ እግራቸው
ለ7 ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ታስባለች::
††† ጥር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅድስት ማርያ ግብጻዊት
3.ታላቁ አባ ቢፋ
4.አባ አብሳዲ ቀሲስ
5.ቅዱሳን ጻድቃነ ሐውዚን
††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ (ዘክብራን ገብርኤል-ጣና)
2.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ
3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
4.ቅዱስ ሙሴ ጸሊም
5.ቅዱስ አጋቢጦስ
6.ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማይ
††† "በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር :
አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት :
ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ
ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . .
የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ
የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(፪ቆሮ ፲፩፥፳፫)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
መንግስተ ሰማያት ማለት ከትንሣኤ ሙታን ቡኋላ ፃድቃን የሚኖሩባት ሠማያዊት ሀገር ናት።
ገነት ማለት ሰው ከ እግዚአብሔር ጋር በደስታ እነ በፍቅር የሚገናኝበት እስከ ትንሳኤ ሙታን የፃድቃን ነፋስ የምትቆይባት በሰማይ እና በምድር መካከል ያለች ቦታ ነች።
በህፃናትና በሴቶች ላይ የተለመደ የ አይነናስ ጥቃት ነው።
1.ቶሎ መበሳጨት
2.ግኡዝ ነገር ማስታወክ
3.ግኡዝ ነገር ከሰውነት መውጣት
4.ቁርአን ሲቀራ ደስ የማይል ስሜት መሰማት
5.ጥፍርን ከንፈርን ማኘክ
እነኚህ ከጥቂት ምልክቶች ውስጥ በትንሹ ናቸው💡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
/channel/Qallbdoc
ህክምና ለማግኘት👇
/channel/freeeeeeeeeeeere
👆
🌿❤️ ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ ማለት🌿❤️
《የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን ለዚህች ታላቅ ክብረ በዓሏ አደረሳችሁ አደረሰን!!!
🌿❤️ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
🌿❤️ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡
🌿❤️ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
... 🌿❤️ የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡
🌿❤️ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡
🌿❤️ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡
🌿❤️ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡
🌿❤️ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
🌿❤️ አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ♥#አስተርእዮ__ማርያም♥ ተብሏል፡፡
🌿❤️ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡
🌿❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡
💟ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ 《ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ》ነገረቻቸው፡፡
💟ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡
🌿❤️ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡
🌿❤️ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡
🌿❤️ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
💟እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡
🌿❤️ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡
🌿❤️ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን አሜን ።
❤️💜💚💛💙❤️💙💚💜❤️
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
❤️💜💚💛💙❤️
/channel/DIYAKONAE
/channel/zikirekdusn
†✝† እንኳን ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ: እና ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †††
††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነው::
በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ዽዽስናን ሹሞ 2 መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::
ከሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን እንሳተፍ ዘንድ ጊዜ ካለን ቅዱስ ዻውሎስ ለልጁ ጢሞቴዎስ ከላካቸው መልዕክቶች ጥቂት እናንብብ::
††† ቴዎዶስዮስ †††
††† በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ሰማዕታትም: ጻድቃንም: ሊቃውንትም: ነገሥታትም ተጠርተውበታልና:: ዛሬ የምናከብረውም ቴዎዶስዮስ ዘየዓቢ (ታላቁ) የሚባል ሲሆን ይህን የምንለው ከትንሹ ቴዎዶስዮስ (የልጅ ልጁ ነው) ለመለየት ነው::
ታላቁ ቴዎዶስዮስ በሮም የነገሠው በ370 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን ከነ ቤተሰቡ ክርስቲያን ነበር:: እነዚህ ነገሮቹ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን እንዲታሰብ አድርጐታል:-
1.በዓለም ታሪክ ክርስትና በሮም ግዛት ሁሉ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን አውጇል::
2.የቤተክርስቲያንን ትልቁን 2ኛ ጉባኤ ቁስጥንጥንያን በ381 (373) ዓ/ም አሰናድቷል::
3.ከበጐነቱ የተነሳ የተቀደሱ ልጆችን አፍርቷል:: ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ: ቅዱስ አኖሬዎስ: ቅዱስ አርቃዴዎስ እና ቅድሰት ታኦድራ ልጆቹ ሲሆኑ አቡነ ኪሮስ ትንሽ ወንድሙ ናቸው::
ጻድቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በ390 ዓ/ም አካባቢ ዐርፏል::
††† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ጥር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጢሞቴዎስ (ሐዋርያና ሰማዕት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር)
2.ቅዱስ ጌርሎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
4.ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ (ዘቁስጥንጥንያ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.አባ ሳሙኤል
6.አባ ስምዖን
7.አባ ገብርኤል
††† "መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ዻውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ::
ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ." †††
(1ጢሞ. 1:1)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††