አንድ ቀን እንደልማዷ ማርያም እንተ ዕፍረት ነጭ ሐር ለብሳ፣ አጊጣና ተኳኩላ ፊቷን በመስታወት አይታ ውድ ሽቱ ተቀባች፡፡ ጉንጮቿ ቀያዮች፣ ዓይኖቿ የተዋቡ ሆነው ደም ግባቷ በጣም አማራት፡፡ እንደዚህ እየተመለከተች አንድ ሰዓት ያህል ቆየች፡፡ ከዚህ በኋላ መልካም አሳብ በእርሷ ላይ አድሮ እንዲህ አለች፡- ‹‹ይህን ሁሉ ታስወግድ ዘንድ መልኬንም ትለውጥ ዘንድ ሞት ትመጣ የለምን? ይህ መልካም ሽታ ወደ ትልነትና ወደ መሽተት ይለወጣል፡፡ ይህስ ብርታት ፍጻሜው ጉስቁልናና ድካም አይለምን? ሊቀርቡኝ የሚወዱትስ የሚርቁኝ አይደሉምን? እንደዚህስ ከሆነ ዘለዓለም ከጥፋትና ከኩነኔ በቀር እንግዲህ ምን አገኛለሁ? የዚህን ዓለም ገንዘብ ብገዛ፣ ብነዳ ከድካም በዐይኖቼም ዕንባን ከማፍሰስ የሚያድነኝ ይኖራልን? ወይስ ይህ ሁሉ ከሞት ያድነኝ ዘንድ ይችላልን? ነፍሴ ሆይ! እንግዲህ ሁሉን ለሚገዛ ጌታ ምን ትመልሻለሽ? ከእውነተኛው ፈራጅ ዘንድ በአንቺ ላይ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ እንዴት ትሆኛለሽ? ነፍሴ ሆይ! ንስሐ በሌለበት፣ ነፍስ የተናቀች በምትሆንበት ጩኸት፣ ልቅሶና ጩኸት ባለበት ቦታ የሚረዳሽ ማነው? ነጭ ሐርና ኅብሩ ልዩ ልዩ የሆነ ልብስ በመልበስ ደስ የምትሰኝ ሥጋዬ ሆይ በክብር ባለቤት በእግዚአብሔርና በመላእክቱ ፊት ራቁትሽን በቆምሽ ጊዜ እንዴት ትሆኛለሽ? ነፍሴ ሆይ! በዚህ ዓለም የተደሰትሽው ምን ይጠቅምሻል?…›› እያለች ራሷን መመርመር ጀመረች፡፡ መድኃኒት ታገኝ ዘንድም የአመለከታትን አታውቅም፡፡
ከዚህ በኋላ በማመን ጸንታ እንዲህ ብላ አሰበች፡- ‹‹ስለ ኃጥአን ወደዚህ ዓለም የመጣ ስለ እነርሱ በመካከላቸው እንደሰው የተመላለሰ ይህ አይደለምን? የኃጢአተኛን መመለሱን ነው እንጂ ሞቱን አልሻም ያለስ እርሱ አይደለምን? ነፍሴ ሆይ ምሕረትስ ቅርብ ናት ባለመድኃኒትም የራቀ አይደለም ሌላ መድኃኒትሽን ተስፋ የምታደርጊበትስ አለን? መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዲቱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ሊፈልጋት የሚሔድ አይደለምን? ባገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከማታል፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሷ ደስ የሚሰኝ አይደለምን? እናንት ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ የሚል እርሱ መድኃኒት ክርስቶስ ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ ለምን እሰንፋለሁ? ለምንስ ንስሓ አልሻም? እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ወደ እርሱ ሄጄ ራሴን በፊቱ እክዳለሁ›› ብላ ካሰበች በኋላ ተጽናናችና በፍጥነት ተነስታ ግንዘቧን፣ የገዛችውን ወርቋንና ብሯን ሁሉ ሰበሰበች፡፡ ‹‹ምን አደርጋለሁ ይህን ገንዘብ ወስጄ ብሰጠው አይቀበልም እርሱ ፈጣሪ፣ ጌታና የዓለም መድኃኒት ነውና›› ብላ አሰበች፡፡ ከዚህ በኋላ ሽቱ ወደሚሸጥ ሰው ፍለጋ ሄደች፣ ያን ሰው ከጥንት ጀምሮ ታውቀው ነበርና ከእርሱ ዘንድ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቱን ገዛችና በደስታ ስትሄድ እነሆ ሰይጣን በወርቅ ያጌጠች ሴት መስሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ የዚህን ዓለም ምኞት እያጣፈጠ ይነግራት ጀመር፡፡ መብላትን፣ መጠጣትን፣ ያማረ ልብስ መልበስን፣ ሽቱ መቀባትን… ይህን ሁሉ ያሳስባት ጀመር፡፡ ጌታችንም በይቅርታው ብዛት የጠላት ዲያብሎስን ክፋት ገለጠላትና ‹‹ለበደልና ለኃጢአት ሥራ የተዘጋጀሁ አድርገኸኛልና ኃፍረትና ጉስቁልናንም በእኔ አምጥሃልና አንተ ሰይጣን ከእኔ ወግድ›› ብላ በቁርጥ ነገር መለሰችለት፡፡ ጠላት ዲያብሎስም የሃይማኖቷን ጽናት ባየ ጊዜ ከእርሷ ሸሽቶ ፈሪሳዊ ወደሚሆን ስምዖን ወደሚባል ሰው ዘንድ ሄዶ ልቡናውን ያውከው ጀመር፡፡ እርሱም ጌታን በቤቱ ማዕድ ይመገብ ዘንድ ጋብዞት ነበርና፡፡ በልቡናው ያደረው ክፉ ሰይጣንም እንዲህ ብሎ እንዲናገር አደረገው፡- ‹‹ይህስ ነቢይ ቢሆን ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደሆነች እንዴትስ እንደነበረች ኃጢአተኛ እንደነበረች አያውቅም ነበር?›› ብሎ እንዲያስብ አድረገው፡፡
ማርያም እንተ ዕፍረት ለጌታችን ያቀረበችው ልመናዋና ንስሓዋ ይህ ነው፡- ‹‹ማርያም እንተ ዕፍረትም ደጆቸ ተከፍተው አገኘች፣ ያለማፈር ገብታ በፍጹም እምነት ከእግዚአብሔር ወልድ ዘንድ ቀረበችና በስተኋላው ቆማ ልመናን አቀረበች፣ እያለቀሰችም በእንባዋ ታርሰው ጀመረች፣ በራስ ፀጉሯም ታብሰው እግሩንም ትስመውና ሽቱ ተቀባው ነበር፡፡ በልቅሶና በዕንባ ሆና እንዲህም እያለች ልመናን አቀረበች፡- ‹ነፍስንና ሥጋን የምታድን የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ሆይ! የሕይወት ምንጭ ሆይ! ሕይወቷን ወዳሳመርክላት ወደ አገልጋይህ ተመልከት፡፡ እኔ ግን አንተን በድያለሁ፣ እንደ እንስሳ ሆንሁ፣ እንደ እነርሱም የተቆጠርሁ ሆንሁ፣ ኃጢአኛና በደለኛ የምሆን እኔን አቤቱ ይቅር በለኝ፣ ማረኝ፣ ከኃጢአት ቀንበር በታች ሆኜ ለሰይጣን ተገዝቻለሁና ጌታዬ ሆይ! ከሰይጣን እጅ አድነኝ፣ የንስሐ ቀንበርንም እሸከም ዘንድ የበቃሁ አድርገኝ፣ የምሕረትህንም በር ክፈትልኝ፣ ጌታዬ ሆይ! ይቅርታህንና ሥርየትህን ተስፋ አድርጌ ወደ አንተ የመጣሁ ባሪያህን ተቀበለኝ› እያለች ፍጹም በተሰበረ ልብ ሆና ልመናን አቀረበች፡፡ ዳግመኛም ‹ነፍሴ ሆይ መድኃኒትሽን እንዴት አትሽም? እነሆ መድኃኒት ክርስቶስ በዚህ አለና ለምንስ ትዘገያለሽ? እነሆ የሕይወት ውኃ ምንጭ መጥቶልሻልና ከቆሻሻነትሽስ ለምን ቶሎ አትነጭም? ለደዌሽስ ፈውስን አትፈልጊምን?› አለች፡፡ ዳግመኛም ‹ከንቱ ነገርን ስትመለከቱ የኖራችሁ ዐይኖቼ ሆይ! ጌታን ታዩ ዘንድ ተሰጣችሁ፤ ርኩስን የምትዳስሱ እጆቼ ሆይ! የሰማያዊ ጌታን እግር ትዳስሱ ዘንድ ሰጣችሁ፤ ኃጢአተኛ ነፍሴ ሆይ! እነሆ ፈጽሞ ከፍ ያለ ባለሟልነትን አገኘሽ፤ ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለሁ› እያለች ታላቅ ልቅሶን አለቀሰች፡፡ የጌታንም እግር ይዛ በእንባዋ እያራሰች በፀጉሯ ታብስ ጀመር፡፡ አስቀድማ በልቧ እንዲህ ብላ አስባለችና ‹በጌታ ፊት ባለሟልነትንስ ካገኘሁ ወደ እርሱ ዘንድ እንድቀርብ ያደርገኛል፡፡ በሥራዬም ክፋት ካበረረኝ ግን ዳግመኛ አልድንም› ብላ አስባ ነበር፡፡ ከጌታም ባለሟልነትን ባገኘች ጊዜ ጨክና በራሱ ላይ ሽቱውን ጨመረች፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋርም ልቅሶንና ልመናን አላቋረጠችም፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ በእርሷ ላይ እንደበዛ ባየ ጊዜ ጠላት ዲያብሎስ በእርሷ ላይ ታላቅ መቅናትን ቀናባት፡፡ ተቆጥቶም ወደ ስምዖን ተመልሶ ልቡን አወከው፡፡ ‹ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ኃጢአተኛ እንደሆነች ያውቅ ነበር› እንዲል አደረገው፡፡ ጌታችንም ስምዖንን ሁሉ ከእርሱ እንዳልተደበቀና ሀሳቡንም እንዳወቀበት እንዲረዳና እግዚአብሔርም በደለኞችን ማዳንና ከኃጢአታቸው ማንጻት እንደሚችል ያውቅ ዘንድ እንዲያስተውል አደረገው፡፡››
ማርያም እንተ ዕፍረት ወይም በሌላኛው ስሟ ማርያም እኅተ አልዓዛር ትባላለች፡፡ ጌታችን በቤታቸው ተገኝቶ ሳለ እኅቷ ማርታ ለአገልግሎት ስትደክም ማርያም ግን ከእግሩ ሥር ተቀምጣ ቅዱስ ቃሉን በመስማቷ ጌታችን ‹‹ማርያምስ የማይቀሟትን መልካም ዕድል መረጠች›› በማለት መስክሮላታል፡፡ ሉቃ 10፡38-42፡፡ ቀድሞ በዝሙት የኖረችበትን አስከፊ ሕይወት በመተው በቆራጥ ኅሊና ፍጹም ንስሓ ገብታ ገንዘቧን ሁሉ አውጥታ እጅግ ውድ የሆነውን ሽቱ ገዝታ ጌታችንን ስትቀባው ጌታችንም በፍጹም ንስሓዋ ተደስቶ ‹‹እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርሷ ያደረገችው ደግሞ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል›› በማለት አስደናቂ ትእዛዙን የሰጠላትና ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ወገን የደመራት ቅድስት ናት፡፡ ማቴ 26፡6፡፡
በዚኽ ክፍል ከ"በስመ አብ ጀምሮ እስከ መዝሙረ ዳዊት የንባብ ትምህርት በግእዝ ቋንቋ ይሰጣል"
ማስፈንጠሪያውን ተጭነው
/channel/+uzuZlTcUJp5kNGJk
ይማሩ
#ወር_በገባ_በ 4️⃣
#ነባቤ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ነው።
ጥበቃው አይለየን ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏❤
ከዚህም በኋላ ወደ ሕዝብ መካከል ወጣ እያለቀሰ ጸለየ እንዲህም አለ አቤቱ በጌትነትህ ክብር ፊት የረከሰች እፌን እንዴት እገልጣለሁ በኃጢአት ብዛት የጠቆረ ፊቴንስ እንዴት ቀና አደርጋለሁ ነገር ግን እንደ ይቅርታህ ገናናነት እንደ ቸርነትህም ብዛት ሕዝብህን ይቅር በል አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና በዚያንም ጊዜ ብዙ ዝናም ወረደ እርሱም ጸሎቱንና ንስሓውን እግዚአብሔር እንደ ተቀበለው ኃጢአቱንም እንደ ተወለት አወቀ።
ከዚህም በኋላ አስቀድሞ እንደሚሠራው ተግቶ መጸለዩንና መሰገዱን አላጐደለም ነፍሱንም ዳግመኛ በኃጢአት ውስጥ እንዳትወድቂ ተጠበቂ በማለት ይገሥጻት ነበር ከዚህም በኋላ ዕድሜውን አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ዕብሎይ_ገዳማዊ (የባሕታውያን አለቃ)
በዚህችም ዕለት የባሕታውያን አለቃ ኑሮው የመላእክትን ኑሮ የሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ የተገኘ የከበረ አባት ዕብሎይ አረፈ።
ቅዱስ አትናቴዎስም ከተሰደደበት በተመለሰ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ወደ አባ ባስልዮስ ዘንድ መጥቶ ሁለቱም በአቡቂር ቤተ ክርስቲያን አደሩ በግብጽ ገዳማት ስለሚኖሩ ቅዱሳን እርስ በርሳቸው ሊነጋገሩ ጀመሩ አባት ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ አባ ጳኵሚስ አለ ብሎ ተናገረ አባ ባስልዮስም አባ እንጦንዮስና አባ አሞኒ አሉ አለ በእንዲህ ያለ ነገርም ከእርሳቸው የሚልቀውን ሊረዱ ሽተው ሳሉ የካቲት አምስት ቀን በመንፈቀ ሌሊት አባ አትናቴዎስ ራዕይን አየ።
እስከ ሰማይ የምትደርስ ታላቅ ዛፍ ነበረች ቅርንጫፎቿም እስከ ባሕር ደርሰዋል ብዙ ሰዎችም ከቅርንጫፎቿ በታች ተጠልለዋል በመካከሏም ታቦት መሠዊያ አለ ከዚህም ራእይ የተነሣ እየተደነቀ ሳለ እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ይህን ያየኸውን ከባስልዮስ ጋር ተነጋገር እኔም እገልጥላችኋለሁ አለው።
እንዲህ ብሎ ተረጐመላቸው ያየሃት ዛፍ በግብጽ አውራጃዎች ውስጥ የሚሠራ ገዳም ነው ቅርንጫፎቿም መነኰሳት ናቸው መሠዊያውም መላእክት የሚጐበኙት የእግዚአብሔር ማደሪያ ይህ ርኵሳን መናፍስትን የሚሽር የሐዋርያት አለቃ የጴጥሮስ አምሳል የሆነ አባ ዕብሎይ ነው።
በእስክንድርያ የሚኖር አንድ የመቶ አለቃ የአባ ዕብሎይን ዜና ሰምቶ በረከቱን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዕብሎይ እንዲልከው ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስን ማለደው። እርሱም ከሰባት መነኰሳት ጋር ሰደደው እነርሱም አባ ኤስድሮስ፣ አባ ዮሐንስ፣ አባ ብሶይ፣ አባ አሞኒ፣ አባ ፊቅጦር፣ አባ አግሮኒኮስና አባ ካሉናስ ናቸው። በደረሱም ጊዜ አባ ዕብሎይ በደስታ ተቀበላቸው ከመነኰሳቱም ጋር የመጣው የመቶ አለቃ አንዲቷ ዐይኑ የታወረች ናት አባ ዕብሎይን በተሣለመው ጊዜ ዐይኑ ተከፈተች እርሱም በዓለም የሚያበራ ኮከብ ብሎ ተናገረ።
ዳግመኛም አባ ዕብሎይን ለመነው እንዲህም አለው ሚስቴ በለምጽ ደዌ ትጨነቃለች እርሷም በአስኬማህ የተማጸነች ናት እኔ ያገኘሁት ጸጋህ ለርሷም ይድረሳት። አባ ዕብሎይም በክብር ባለቤትም ጌታችን ስም ፈውስ ይሁንላት አለ ይህም ቃል ከአፉ እንደወጣ ድና ጤንነትን አገኘች።
በአንዲትም ዕለት አባ ዕብሎይ ከመነኰሳት መካከል ቁሞ ቤተ ክርስቲያን የምትሠራበትን ያስገነዝበን ዘንድ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይመጣልና አንዱም አንዱ ከእናንተ አይሒድ ከዚህ ይኑር እንጂ አላቸው።
ያን ጊዜም በዚያ ቦታ ብርሃን ወጣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበሩ ደቀ መዛሙርቱና ከመላእክቶቹ ጋር መጣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ የሚመሠረትበትንም አሳያቸው።
እርሱም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ፍቅርንም ያጸኑ ዘንድ ልጆቹን ይመክራቸው ነበር እየመከራቸውም ፊቱ ተለውጦ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ሆነ ሁለመናውም እንደሚነድ እሳት ሆነ እነርሱም ፈሩ። እርሱም ልጆቼ አትፍሩ እነሆ እኔ እሰናበታችኋለሁ አላቸው። ይህንንም ብሎ ነፍሱ ተመሠጠች በጎ መዓዛም ሸተተ ወዲያውኑ ዐይኑ ተገለጠና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳኝ ነፍሴንም ወዳንተ ተቀበል አለ ይህንንም ብሎ አረፈ። የቀረውም ዜናው በጥቅምት ሃያ አምስት ቀን ተጽፎአል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)
የካቲት 3/2016 #ቅድስት_ባዕታ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ለምናመሰግንበት #ለክቡር_ሰንበት ለሰንበተ ክርስቲያን ለእናታችን ለአማላጃችን #ባዕታ_ማርያም ቤተ መቅደስ ለገባችበት ወርሐዊ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉" ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ " ( መዝ 45:4)
👉 #ባዕታ ማለት ባዕት ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን መግባት ማለት ነው ባዕታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታኅሣሥ 3 ቀን ወደ #ቤተ_መቅደስ የገባችበት እለትን በመሆኑ ወር በገባ በ3ኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ ቀን ነው
👉#ማርያም ማለት መርሕ ለመንግስተ ሠማያት ማለት ነው ወደ መንግስተ ሠማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው
👉 #ማርያም ማለት ፀጋ ወሀብት ማለት ነው ለሰው ልጆች ድህነት ምክንያት እንድትሆን ከአምላክ የተሰጠች ታላቅ ስጦታ ናትና
👉#ማርያም ማለት የሕያዋን እናት ማለት ነው
👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ልጅ በመሆኗ ቅዱስ እያቄምና ቅድስት ሃና #በቤተ_መቅደስ እንድታድግ ብለው በ3 ዓመቷ አምጥተዋት ለሊቀ ካህኑ ለዘካሪያስ አስረከቧት ነገር ግን ካህኑ ምን በልታ ታድጋለች ብሎ ቢጨነቅም መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሠማይ መናን እያወረደ እየመገበ 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች
👉እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም #እግዚአብሔርን እያመሰገነች ለመላእክት እያገለገለች ሐርና ወርቅን እያስማማች እየፈተለች በንፅህና በቅድስና #በቤተ_መቅደስ በምስጋና ኖራለች
👉እርሱ ጌታችን #ክርስቶስ መርጧታልና ልክ 15 ዓመት ሲሆናት ከሲዖል የታሰርነውን እኛን ለማዳን ሲል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ 9 ወር ከ5 ቀን በማህጸኗ አደረ ተወልዶ አደገ
👉በዚህ ምድር ሲኖር አዳኛችን #ክርስቶስ ወንጌልን አስተማረ ምሳሌ ሆነ መከራን ተቀበለ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ክቡር ደሙን አፈሰሰ ክቡር ሥጋውን ቆረሰ በእርሱ ሞት እኛን ነፃ አወጣን ክብርና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን ምስጋና ለድህነታችን ምክንያት ለሆነችው ለእናታችን #ባዕታ_ማርያም ይሁን
👉የእናታችን #ባዕታ_ማርያም ፍቅር በረከቷ ምልጃና ፀሎቷ ሁላችንንም ይጠብቀን ለሀገራችን ለህዝባችን ሠላሙን አንድነትን ይስጥልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የመልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ጥበቃዉ የአባታችን የፃድቁ አቡነ #ዜና_ማርቆስ ምልጃና ፀሎታቸዉ አይለየን የተባረከ የተቀደሠ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
☞የካቲት 2 የገዳማዊያን አለቃ ለሆነ ለአባ ጳውሊ የአመታዊ መታሰቢያ
አደረሳችሁ፡፡
☞አባ ጳዊሊ የማይቆጠር እጅግ ባለ ጸጋ የኾነ አባት በእስክድርያ ሀገር ነበረው፡፡
☞ጳውሊን ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጥቶ ብሉይ ሐዲስ እንዲሁም
ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ተምሮ በሕግ በሥርዐት አደገ፡፡
☞አባቱ ከሞተ በኃላ ጴጥሮስ የሚባል ወንድም ነበረውና የአባቴን ሀብት
አካፍለኝ ቢለው አንተ ሕፃን ነኽ ታባክነዋለህ እስክታድግ ድረስ ከእኔ ዘንድ
ይቀመጥልኽ እያለ እንቢ አለው፡፡
☞በዚህ ምክንያት ጳዉሊ ተቁጣና ተጣልተው ወደ ዳኛ ሲኼዱ የሞተ ሰው
ተሸክመው ሲኼዱ ሰዎችን አገኙ፡፡ ከሀዘንተኞቹ መካከል አንዱን ማን እንደ ሞተ
አባ ጳዉሊ ጠየቀ ያም ሰው ልጄ ሆይ አስተውል፡፡ ይህ የሞተው ሰው በወርቅ
በብር እጅግ ባለ ጸጋ የኾነ ኹል ጊዜ ደስ የሚለው ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን
በኅጢአት ማዕበል ውስጥ እያለ ዕራቁቱን ወደ መቃብር ወረደ ብሎ መለሰለት፡፡
አኹንም እኛ መቼ እንደ ምንሞት አናውቅምና ሰለ ነፍሳችን ልንታገል ይገባል፤
ገንዘብ ሥልጣን ኑሮት ይህን ዓለም የተወ የተመሰገ ነው፤ በቅዱሳን ሀገር ክብር
ይቀበላልና አለው፡፡
☞አባ ጳውሊ ይህን በሰማ ጊዜ ከልቡ ጮኸ የዚህ ኅላፊ ዓለም ገንዘብም ምን
ይጠቅመኛል አለ፡፡ እኔም ከጥቂት ቀን በኃላ ዕራቁቴን ትቼው እኼድ የለምን ና
ወንድሜ ወደ ቤታችን እንመለስ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህም ሰለ ገንዘብ ከአኔ ጋር
አልነጋገርም አለው፡፡
☞ከዚያም ፧ኃላ ከወንድሙ ሸሽቶ ከሀገሩ ወጣ፡፡ ከመቃብር ቤት ገብቶ 3ቀን
3ሌሊት መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አየማለደ ሰነበተ፡፡ ወንድሙ
ጴጥሮስ ሲፈልገው ሰንብቶ ሰላጣው አዘነ፡፡
☞ጳዉሊ ግን ያለ ፍርሀት በቃብር ቤት ሳለ በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር
መልአክ በምሥራቅ በምትገኝ በረሓ ወሰዶ የሰኔል ቆብ አልብሶት አሰቀመጠው፡፡
እሱም ማንም ሳያይ 80 ዓመት በዋሻ ውስጥ ኖረ፡፡
☞ምግቡንም ግማሽ እንጀራ ቁራ እየመጣለት ይመገብ ነበር፡፡
☞ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ቅድስናውን ዐውቆ እንጦንስ የዓለም ሰዎች
የአንዲቱን የእግር ጫማ የማይኾኑት በጸሎቱ ዓለም ተጠብቆ የሚኖር ከአንተ የ
2 ቀን ጉዳና ርቆ የሚገኝ ጻድቅ ሰው አለ ብሎ ገለጠለት፡፡
☞አባ እንጦስ የመጀመሪያው መናኝ ራሱ ብቻ እንደ ኾነ ያስብ ነበርና ይህን ቃል
በሰማ ጊዜ ፍለጋ ጀመረ፡፡ ከቅዱስ ጳውሊ ደርሶ በሩን አንኳኳ፡፡ እንጦስም ድምፅ
አሰምቶ ተናገረ ከፈተለት ገባ፡፡ መንፈሳዊ ሰላምታ ተሰጣጡና ጸለየው
ተቀመጡ፡፡
☞ አባ እንጦስም ሰምኽ ማነው አለው፡፡ አባ ጳውሊም እንዲት ሰሜን ሳተውቅ
መጣህ አለው፡፡
☞በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ገለጠለትና ገዳማዊ ጳውሊ እንዳየው ሰለ ተገባኝ
እኔ ብፁዕ ነኝ ብሎ ሰሙን ጠራው፡፡ ከዚያ ብዙ ተጨዋውተው ሲመሽ ያ ቁራ
ሙሉ እንጀራ ጣለለት፡፡ እሰከ በዋሻ 80 ዓመት ስኖር ግማሽ እንጀራ ነበር
የሚያመጣልኝ አሁን ያንተ መምጣት አውቆ አንድ እንጀራ አመጣልኝ ብሎ
የፈጣሪን ስራ አደነቀ፡፡
☞ከዚያም ሥጋ ወደሙን ከወዴት ትቀበላላኽ ብሎ አባ እንጦስ ሲይቀው
በየሳምንቱ ቅዳሜ እሑድ የእግዚአብሔር መላእክት ያቀብለኛል አለው፡፡
☞አባ ጳውሊም አስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሡ መነኮሳትን ግብር ነግሮት
ቁስጢንጢኖስ ለአባ አትናቴዎስ ሰጦት ለአንተ ያለበሰኽን ልብስ ይዘኻት ናና
ገንዘኝ ከዓለም የምወጣበት ጊዜ ቀርቧልና ብሎ አሰናበተው፡፡
☞ እሱም 2 ቀን መንገድ ኺዶ ሲመለስ የቡላንና የመላእክት ማህበራት ነፍሱን
ሲያሳርጉ አይቶ ይቺ የአባቴ ነፍስ ናት አለ፡፡ እንደ ደረሰም እጆቹ በመስቀል
ምልክት ተዘርግተው ጉልበቱ ተንበርክኮ አገኘው፡፡ ከዚያም በኃላ በዚያች ልብስ
ገነና ሥርዐተ ጸሎት ፈጽሞ ምን ላድርግ ሰ ሲል ( አንበሶች መጥተው እጅ
ነሡትና አዘንብለው እግሩን ላሱ፡፡ አንበሶቹ ሰላምታ ከሰጡት በኃላ መቃብሩን
ቆፍረው ቀበሩት፡፡ አባ እንጦስ ወደ ባዓቱ ተመለሰ፡፡ የአባ ጳውሊን ልብሱን
(ዐጽፋንም) ለአባ አትናቴዎስ ልኮለት በዓመቱ ሦስቴ የልደት፤የጥምቀት የትንሳኤ
ለት ይለብሳት ነበር፡፡ ሙትም አሠነስቶባታል፡፡ የአባ ጳውሊ የዕረፍቱ መታሰቢያ
የካቲት 2 ነው፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ ☞በመ/ር ዐይነ ኩሉ ከተጻ
ፈው (መድበ ታሪክ መጻፍ) የተወሰደ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞1-6-2016
"በሌሎች ላይ መፍረድ የአንድ ሰው የትዕቢት ውጤት ነው፤ ትሑት ሰው ግን ሁሉ ሰው ያከብራል፤ከእርሱ የተሻሉ እንደሆኑ ያስባል። ''
(ቅዱስ ዕንባቆም)
ጥር 30/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ11፥11
👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው
👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች
1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው
👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን
👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ባለወልድ ማለት ወር በገባ በ29ኛው ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን የስሙም ትርጓሜ የወልድ በዓል ማለት ነው።
ይህም ጌታችን መድኃንታችን እየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስና የሰውን ልጅ ነጻ ለማውጣት ሲል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መጋቢት 29 የተጸነሰበትና ታህሳስ 29 የተወለደበት ቅዱስ ዕለት ስለሆነ በየ ወሩ ይታሰባል
.......
በአንድ መድረክ ላይ ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀልድ ቀልዶ ሁሉንም ታዳሚሚዎች በጣም ያስቃቸዋል ። ሁለተኛም ያንኑ ቀልድ ደገመዉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሳቁ ። ለሶስተኛ ጊዜ ያንኑ ቀልድ ደገመው ፤ በዚህን ጊዜ ግን ማንም አልሳቀም ነበር ። ይህን ያየዉ ቻርሊ ለታዳሚዎቹ እንዲህ አላቸው ።
"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ ካልሳቃችሁ ለምን ታዲያ በአንድ ችግር ደጋግማችሁ ትጨነቃላችሁ ።" ነበር ያላቸው ።
በዚህች አለም ላይ ምንም ዘላቂ ነገር የለም ችግራችንም ቢሆን !!!!!
......የእናቴ ልጅ-Tame........
✔ /channel/Asresee
✔ /channel/Asresee
✔ /channel/Asresee
እኅቷ ማርታ ደግሞ የምትኖረው ከኢየሩሳሌም 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በቢታንያ መንደር ነው፡፡ ጌታችንም ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣና ሲገባ በቤቷ ያርፍ ነበር፡፡ እርሷም በሚገባ ታስተናግደው ነበር፡፡ እንዴት የታደለች ናት!!! ጌታችን ከሞት ያስነሣው ወንድማቸው አልዓዛር ደግሞ ጌታችን ይወደው የነበረ የቢታንያ ሰው ነው፡፡ አልዓዛርና እኅቶቹ ጌታችን ካረገ በኋላ በቀድሞው መኖሪያቸው እንግዶችን እየተቀበሉ ቤታቸውንም የወንጌል መማሪያ አድርገው ተቀምጠው ነበር፡፡ ነገር ግን ክፉዎች አይሁድ በክርስቲያኖች ላይ ስደት በማስነሣታቸው በ35 ዓ.ም ላይ አልዓዛርንና ሁለቱን እኅቶቹን በቀዳዳ መርከብ ጭነው ወደ ባሕር ጣሏቸው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ሦስቱንም በተአምራት ሰጥመው ከመሞት አዳናቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ሲፕረስ ወደምትባል አገር ሄደው ኑሮአቸውን በዚያ ከመሠረቱ በኋላ አልዓዛር የመጀመሪያው የኪትዮን (ፈረንሳይ ውስጥ የምትገኝ ከተማ) ሊቀ ጳጳስ በመሆን እኅቶቹም እንደቀድሞው እያገለገሉ ክርስትናን ማስፋፋታቸውን ታሪካቸው ይናገራል፡፡
የቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን!
(ምንጭ፡- ገድለ ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት፣ ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 6-በዓለም ሁሉ ወንጌል በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ገድሏ እንዲነገር ጌታችን ያዘዘላት፣ ገድሏንና ድርሳኗን ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጻፈላት ባለ ሽቱዋ ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ቅድስት አትናስያና ሦስቱ ደናግል ልጆቿ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ከእነርሱም ጋር የከበሩ ቅዱሳን ዮሐንስና አቡቂር በሰማትነት ዐርፈዋል፡፡
+ የዓለም ሁሉ መምህር የሆነ አባ አቡሊዲስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ሥጋው ከባሕር ውስጥ በተአምራት የወጣበት ዕለት ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ፣ ቅዱስ አቡቂር፣ ቅድስት አትናስያና ሦስቱ ደናግል ልጆቿ፡- የቅድስት አትናስያ ልጆች ስማቸው ቴዎድራ፣ ቴዎፍና፣ ቴዎዶክስያ ይባላል፡፡ የስማቸውም ትርጓሜ በቅደም ተከተል ‹‹የእግዚአብሔር ስጦታ››፣ ‹‹የእግዚአብሔር ሃይማኖት›› እና ‹‹የእግዚአብሔር ምስጋና›› የሚል ነው፡፡ ቅዱስ አቡቂር ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር መነኮስ ነው፡፡ የከበረ ዮሐንስ ግን በንጉሥ ሠራዊት ውስጥ የሚያገለግል ነው፡፡ የእነርሱም ሀገራቸው እስክንድርያ ሲሆን የሚኖሩት ግን አንጾኪያ ነው፡፡ በዚያም እነዚህ ሦስት ቅዱሳት ደናግል ቴዎድራ፣ ቴዎፍና፣ ቴዎዶክስያ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቆመው የጌታችንን ክብር መሰከሩ፡፡ ንጉሡም ከወዴት እንደሆኑ በጠየቃቸው ጊዜ ከእስክንድርያ እንደሆኑ ሲነገሩት ወደዚያ ወስደው ያሠቃዩአቸው ዘንድ አዘዘ፡፡
እነዚህም ሦስት ቅዱሳት ደናግል እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ ዳግመኛ በመኮንኑ ፊት ቆመው የጌታችንን አምላክነት በመመስከር በጣዖት ማምለክን ረገሙ፡፡ በዚህም የተናደደው መኮንን ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው፡፡ በመጨረሻም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ እናታቸው የከበረች ቅድስት አትናስያም ደናግል ልጆቿን በጌታችን ስም ምስክር ሆነው በሰማዕትነት ከሞቱ ለሰማያዊው ሙሽራ ለክርስቶስ ሙሽሮቹ እንደሚሆኑ በመንገር ታጽናናቸው ነበር፡፡ ቅዱስ አቡቂርም በከበረች ሐዋርያዊት በቅድስት ቴክላ ላይ የደረሰውን መከራና ያገኘችውን ክብር ይገልጥላቸውና ያጽናናቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ወታደሮቹ ሦስቱን ቅዱሳት ደናግል ቴዎድራን፣ ቴዎፍናንና ቴዎዶክስያን በየተራ እያቀረቡ አንገታቸውን ሰየፏቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ ቀጥለውም ጭፍሮቹ እናታቸው ቅድስት አትናስያን፣ ቅዱስ አቡቂርንና ቅዱስ ዮሐንስን ሁሉንም በየተራ ሰየፏቸውና ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ምእመናንም ሥጋቸውን ወስደው የመከራው ዘመን እስከፈጸም ድረስ በክብር አስቀመጡት፡፡ በኋላም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ቅዱስ ሥጋቸውን በዚያ አኖሩ፡፡ ከቅዱሳኑም ሥጋ ብዙ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አቡነ አቡሊዲስ፡- ይኸውም ቅዱስ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ነው፡፡ ምግባር ሃይማኖቱ የቀና፣ ትሩፋት ተጋድሎው የሠመረ ነውና ከአባ አውክዮስ በኋላ በሮሜ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው፡፡ ብዙ አረማውያንንም የሚያስተምራቸውና የሚያጠምቃቸው ሆነ፡፡ ዜናውም በከሃዲው ንጉሥ በከላድያኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉሡም አቡነ አቡሊዲስን ይዞ በብዙ ግርፋትና ድብደባ አሠቃየው፡፡ ማሠቃየትም በሰለቸው ጊዜ በእግረቹ ውስጥ ታላቅ የሆነን ድንጋይ አሥሮ የካቲት 5 ቀን ወደ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ወረወረው፡፡
በማግሥቱም የካቲት 6 ቀን የአቡነ አቡሊዲስ ቅዱስ ሥጋው በውኃው ላይ ተንሳፎ ተገኘ፡፡ ታላቁም ድንጋይ በእግሮቹ ውስጥ እንደታሰረ ነበር፡፡ አንድ ምእመንም ወስዶ በክብር ከእርሱ ዘንድ አኖረው፡፡ የአቡነ አቡሊዲስም ዜናው በሮሜ አገር ሁሉ ስለተሰማ ንጉሡ ሥጋውን ሊያቃጥለው ፈልጎት ነበር ነገር ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አቡነ አቡሊዲስ ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ድርሳናትን ደርሷል፡፡ በተለይም ስለ አካላዊ ቃል ሥጋ መሆንና እግዚአብሔር የሚወደውን ስለመሥራት ብዙ ደርሷል፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ሕግ 38 መመሪያዎችን ሠርቷል፣ እነዚህም በሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት፡- ስለ ማርያም እንተ እፍረት (ባለ ሽቱዋ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ላይ ‹‹እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርሷ ያደረገችው ደግሞ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል›› በማለት ተናግሮላታል፡፡ ማቴ 26፡13፡፡ በቅድሚያ በወንጌሉ ላይ ስለ እርሷ የተጻፈውን ሙሉውን ክፍል መመልከቱ ተገቢ ነው፡- ‹‹ጌታ ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። አንዳንዶችም ይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው? ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤ እርስዋንም ነቀፏት። ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፡- ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች። ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም። የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል።›› ማር 14፡3-9፣ ማቴ 26፡6-13፣ ሉቃ 7፡36-50፣ ዮሐ 12፡3-8፡፡
የማርያም እንተ እፍረትን ገድሏንና ድርሳኗን የጻፈላት ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው፡፡ ገድሏ ላይ ስለ እርሷ የተጻፈውን ደግሞ ቀጥለን እንይ፡- ማርያም እንተ ዕፍረት ሁልጊዜ ከነጭ ሐር የተሠራ ልብስ የምትለብስ፣ ከሽቱ ሁሉ ይልቅ የሚበልጥ ውድ ሽቱን ትቀባ ነበር፡፡ በወርቅም ታጌጥና በክፉ ሥራ ሁሉ ጸንታ የምትኖር ሴት ነበረች፡፡ ጠላት ዲያብሎስም የዚህን ዓለም ጣዕም አጣፈጠላት፡፡ ነገር ግን ስለዚህች ሴትና ስለ ኃጥአን ሁሉ ጌታችን ከጌትነቱ ከፍታ ሳይለወጥ ከልዑል ዙፋኑ ወረደ፡፡ በሰዎች መካከልም ከእነርሱ እንደ አንዱ እየተመላለሰ አስተማረ፡፡
BenjaminMebrahtom-rj7dl" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@BenjaminMebrahtom-rj7dl
ዝሊንክ ብምንካእ ቤተሰብ ይኩኑ
የካቲት 4/2016 #ተአምር_ሠሪዋ_ስዕለ_ማርያም
#ወንጌላዊዉ_ቅዱስ_ዮሐንስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናቱ ስም ለምናመሰግንበት በዚህች ዕለት #ሉቃስ የሣላት ከጒንጯ ደም የሚፈስሳት ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል የምትታሰብበት በዓሏ ነው እንዲሁም የሐዋርያዉ የቅዱስ #ዮሐንስ ወንጌላዊዉ ወርሐዊ መታሰቢያዉ ሲሆን በረከት ረድኤቱ አይለየን
👉ይኸውም ከ829-842 ዓ.ም በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት #ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር
👉በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የአምላክ እናት #የቅድስት_ድንግል_ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡
👉የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፤ ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጒንጯ ላይ ወጋት ኾኖም ግን #በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡
👉ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሸሽተዋል ሴቲቱም ይኽነን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራትን አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት #ድንግል_ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ ዐደረች፤ በነጋታውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጒንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕሩ ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘችና አስቀመጠቻት።
👉ሥዕሏም በባሕሩ ላይ በመንሳፈፍ በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ #ፀሐይ ሲያበራ ተመለከቱ
👉ይኽም ተአምር ለተከታታይ ቀናቶች በመቀጠላቸው በዚያ የተቀደሰ ተራራ በምናኔ ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድ ላይ ተሰባስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል በላዩ ላይ ወደ ተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመውረድ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም #ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሷት አልተቻላቸውም፡፡
👉በዚያው የአይቮሪዮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው በተመሳሳይም ለአባ ገብርኤል እመቤታችን ተገልጣለት ወደ ባሕሩ ኺድ ማዕበሉንም ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለችን ፍቅርና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾኑ #ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡
👉ከዚያም በአቶስ ተራራ ያሉት መናንያን ኹሉ አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው እያመሰገኑ በማዕጠንታቸው ዕጣን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት #ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ ውስጥ በመግባት በናፍቆት ኾኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕር ዳርቻ ይዟት ወጣ እነርሱም በደስታ ኾነው እጅ ነሷት
👉ከዚያም ማክሰኞ በጠዋቱ ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ ላይ በሚያመሰግኑበት ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው ከዚያም የእመቤታችንን #ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡
👉ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ #የእመቤታችን_ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኟትም ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኟት እነርሱም መልሰው ቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኟት ነበር
👉ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን እኔን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ልጋርዳችሁ እንጂ #ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም አለችው
👉በዚህ ምክንያት #ሥዕሏ በነገረ መለኮት ሊቃውንት "አቃቢተ ኆኅት" (ደጃፍን የምትጠብቅ) Panagia Portaitissa ("She who resides by the door" or "Keeper of the gate" ትባላለች
👉መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት ለአምላክ እናት #ለእመቤታችን ክብር በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራት ወመንክራት ድንቅ ተአምር አድራጊዋን) የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አገቧት የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም “የአይቬሮኗ የአምላክ እናት” (the Iviron Theotokos) ስትባል በግሪክ “ፓርታኢቲሳ” Παναγία Πορταΐτισσα; ትባላለች
👉ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው #የእመቤታችን_ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መኼድን ጀመሩ ይኽ የተቀደሰ #ሥዕሏና ታሪኳም ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለሙ ኹሉ ላይ ተሰማ ዛሬም ምእመናን ይማፀኑበታል
👉ለአባ #ገብርኤል የተለመነች እና በረከቷን እንዳሳደረችበት ዛሬም የምልጃዋ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም አይለየን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ የሐዋርያዉ የቅዱስ #ዮሐንስ ምልጃና ፀሎት ከክፉ ሁሉ ነገር ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
(#መጋቤ_ሐዲስ_ዶክተር_ሮዳስ_ታደሰ_እንደጻፈው)
#የካቲት_3
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የካቲት ሦስት በዚችም ቀን #የቅዱስ_ኤፍሬም የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ ተጋዳይ የሆነ #መነኰስ_አባ_ያዕቆብ አረፈ፣ የባሕታውያን አለቃ ኑሮው የመላእክትን ኑሮ የሚመስል የከበረ #ቅዱስ_አባት_አባ_ዕብሎይ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ኤፍሬም_አፈ_በረከት
የካቲት ሦስት በዚችም ቀን የሶርያዊ ቅዱስ ኤፍሬም የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም ቅዱስ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው አባቱም ክብር ይግባውና የክርስቶስን አምልኮት የሚጠላ የጣዖት ካህን ነበር።
በዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሰችውና አነሳሥታ የንጽቢን ጳጳስ ወደሆነው ወደ አባ ያዕቆብ ወሰደችው እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው በእርሱም ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።
የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት አሕዛብን ተከራክሮ ይረታቸው ነበር። ኒቅያ በሚባል ከተማ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከአባ ያዕቆብ ጋራ ወደ ቅዱሳን ጉባኤው ሔደ።
ከሀ*ዲ*ው አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ ከዚህ ራእይም የተነሣ አደነቀ ይገልጽለትም ዘንድ ወደ ጌታ ጸለየ ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ።
ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወድዶ ወደ ቂሣርያ ሀገር ተጓዘ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በማእዘኑ በኩል ቆመ ቅዱስ ባስልዮስንም ወንጌልን ሊያነብ በወጣ ጊዜ ዋጋው ብዙ የሆነ ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ አየው። ሦስት ምልክቶችንም እሰኪያይ ድረስ ተጠራጠረ ምልክቶችም እኒህ ናቸው ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች ሁለተኛም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተዋሐስያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር። ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል ወጥቶ በምእመናን ላይ ያድር ነበር።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠራውና እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተለዋወጡ። በአስተርጓሚ ይነጋገሩ ጀመሩ። የየራሳቸውንም ቋንቋ ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመነው። በጸለየ ጊዜም ተገልጾላቸው ያለ አስተርጓሚ ተነጋገሩ።
ከዚህ በኋላም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው ከጥቂት ወራትም በኋላ ቅስና ሾመው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ተገለጡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ተጋደለ። አንዲት በወገን የከበረች ባለ ጸጋ ሴት ነበረች ራስዋንም ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ ጽፋ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አመጣች። አባቴ ሆይ በዚህ ክርታስ ውስጥ ያሉት ኃጢአቶቼ ይደመሰሱ ዘንድ ተናገር ብላ ለመነችው እርሱም እንዳልሺው ይሁንልሽ አላት፡፡
እርሷም ክርታሱን በገለጠች ጊዜ ከአንዲት ኃጢአትዋ በቀር ኃጢአቷ ሁሉ ተደምስሶ አገኘች ያችም ኃጢአት አስጨናቂና ታላቅ ኃጢአት ነበረች።
ባገኘቻትም ጊዜ ያቺን የቀረች ኃጢአቷን ያጠፋላት ዘንድ አልቅሳ ለመነችው እርሱም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒጂ እርሱ ይህችን የቀረች ኃጢአትሽን ያስተሠርይልሻል አላት። ወዲያውም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሔዳ ከርሷ የሆነውን ሁሉ ነገረችው ። እርሱም እንዲህ አላት ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሒጂ ግን ሙቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኝዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይህችን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመሰስልሻል።
ያቺም ሴት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ተመለሰች ሙቶ ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱትም አገኘችው ። ያንንም ክርታስ በአስክሬኑ ላይ ጣለችው ወዲያውኑም ተደመሰሰላት። ይህም ቅዱስ ኤፍሬም ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል በዘመኑም ዲዳን የሚባል አንድ ከሀ*ዲ ተነሣ ይህም አባት ኤፍሬም ተከራክሮ ረታው።
እጅግም ብዙ የሆኑ ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ከእርሳቸውም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴዋ ነው። አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሶአል ። መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው ወደ እግዚአብሔር ሔደ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ያዕቆብ_መነኰስ
በዚህች ቀን ተጋዳይ የሆነ መነኰስ አባ ያዕቆብ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ይህን ዓለም ትቶ መነኰሰና በአንዲት ዋሻ ውስጥ የሚኖር ሆነ ያለ ማቋረጥም በቀንና በሌሊት ሁልጊዜ ይጾማል ይጸልያል በመስገድም ይተጋ ነበር ከበዓቱም ወጥቶ ወደ መንደር አይገባም የሴት ፊትም አያይም እንዲህም ሁኖ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ።
ከዚህም በኋላ ዲያብሎስን ከሚከተሉት ክፉዎች ሰዎች ውስጥ ምክንያት ፈጥረው አንዲቷን አመንዝራ ሴት ወደርሱ እንድትገባ አደረጓት በገባችም ጊዜ የኃጢአትን ሥራ እያስታወሰች በፊቱ መጫወት ጀመረች ቅዱስ ያዕቆብም ገሠጻት በገሀነም እሳትም ዘላለም ሲቃጠሉ መኖርን አሳሰባት ደንግጣም ንስሓ ገባች እግዚአብሔርንም የምታገለግል ሆነች።
ሰይጣንም መፈታተኑን አልተወውም ከሀገር ታላላቆችም በአንዱ ሰው በሴት ልጁ ላይ አደረ የሚጥላትና የሚያንከባልላት ሆነ ወደ አባ ያዕቆብም ይወስዳት ዘንድ እርሱም ሊያድናት እንደሚችል አሳሰበው አባቷም ወደ አባ ያዕቆብ አደረሳትና በላይዋ ይጸልይ ዘንድ ለመነው እርሱም በላይዋ ሲጸልይ ዳነች አባቷም ያ ሰይጣን እንዳይመለስባት ብሎ ከታናሽ ብላቴና ወንድሟ ጋር ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ተዋት።
ከዚህም በኋላ ከእርሷ ጋር በኃጢአት እስከ ጣለው ድረስ እርሷን በማሳሰብ በሌሊትም በቀንም በዝሙት ጦር ሰይጣን ተዋጋው በኃጢአትም በወደቀ ጊዜ ስለ ርሷ እንደይገዱሉት ፈርቶ ኃጢአቱ እንዳይገለጥ ከወንድሟ ጋር ገደላት ሰይጣንም ደግሞ ቀቢጸ ተስፋ በልቡ አሳደረበት ወደ ዓለም ሊሔድ ከበዓቱ ወጣ።
የኃጢአተኛውን ሞት የማይወድ መሐሪ ይቅር ባይ እግዚአብሔርም። ጻድቅ የሆነ መነኰስ ወደርሱ ላከ በጐዳናው ሲጓዝ ተገናኘውና ሰላምታ ሰጠው እንዲህም ብሎ ጠየቀው ወንድሜ ሆይ ምን ሁነሃል አዝነህ ተክዘህ አይሃለሁና የደረሰብህስ ምንድን ነው? እርሱም የሆነውን ሁሉ ከዚያች ብላቴና ጋር በኃጢአት እንደ ወደቀና ከወንድሟ ጋር እንደገደላት ነገረው። ያ ጻድቅ መነኰስም አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ እግዚአብሔር መሐሪ ይቅር ባይ ምሕረቱ የበዛ ነውና አለው። ከዚህም በኋላ የጾም የጸሎት የስግደት ቀኖናን እንዲይዝ አዘዘው።
እርሱም ተመልሶ ከአንድ ፍርኩታ ውስጥ ገባ በውስጡም ራሱን እሥረኛ አደረገ በታላቅ ድካምና በብዙ ችግርም ላይ ታገሠ በመጾም በመጸለይ አብዝቶ በመስገድም ሁልጊዜ ይተጋል ከምድር የሚበቅል ሥርንም የሚመገብ ሆነ አብዝቶ እያዘነ እግዚአብሔር ይቀበለኝ ብዙ በደሌንስ ይተውልኝ ይሆን ይላል እንዲህም በመጸጸት እየተጋደለ ሠላሳ ዓመት ኖረ።
እግዚአብሔርም ንስሓውን እንደተቀበለለት ሊገልጥ ወዶ በሀገር ውስጥ ረኃብን አመጣ ለዚያች አገር ኤጲስቆጶስም በፍርኩታ ውስጥ ከሚኖር ከመነኰስ ያዕቆብ ጸሎት በቀር ይህ ረኃብ አያልፍም አለው።
በዚያንም ጊዜ ኤጲስቆጶሱ ከእርሱ ጋር ካህናቱንና የዚያችን አገር ሰዎች ይዞ ተነሣ ወደ ቅዱስ ያዕቆብም ደርሰው ስለ ርሳቸው ይጸልይ ዘንድ ለመኑት እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸውና ዝናምንም እንዲአወርድላቸው አባ ያዕቆብም እኔ እግዚአብሔርን በኃጢአቴ ያሳዘንሁት ኃጢአተኛና በደለኛ ሰው ነኝ አላቸው ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ እግዚአብሔር ያለውን ነገረው።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100094364178618&mibextid=98BtzZNkros8nYVe
Читать полностью…በቅድስት ቤተክርስትያናችን በየእለቱ የሚከበሩ በአላት
በ1----- ልደታ ማርያም፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ጻድቁ ኢዮብ፣ ነቢዩ ኤልያስ፣ሐዋርያው በርተሎሜዎስ፣ ቅድስት ሶስና፣ አባ ሚልኪ፣ቅዱስ መክሲሞስ
በ2.....ሐዋርያው ታዴዎስ፣ ሠለስቱ ምዕት፣ ቅድስት አትናስያ፣አቡነ እንድርያኖስ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ፣ አባ ጉባ
በ3......ባዕታ ማርያም፣ ቅዱስ ፋኑኤል፣ አባ ዜና ማርቆስ፣ አባሊባኖስ፣ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ
በ4.....ወልደ ነጎድጓድ፣ ሐዋርያው እንድርያስ፣ ጻድቁ መልከጼዴቅ፣አባ መቃርዮስ፣ ሰማዕቱ ፊቁጦር፣ አብርሃምወአጽብሐዮ
በ5......ጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነአሮን፣ አቡነ ዮሐኒ፣ አቡነ አሞኒ፣ አቡነ መልአክ ክርስቶስሐንስ
በ6......ግዝረተ ኢየሱስ፣ ቁስቋም ማርያም፣ ነቢዩ ኢያሱ፣ቅድስት አርሴማ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ፣ አቡነተጠምቀመድኅን
በ7......አጋዝዕተ ዓለም ሥላሴ፣ ስዕለተ ማርያም፣ ቅዱስዲዮስቆሮስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ቅድስት እኅተ ጴጥሮስ
በ8......አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል)፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴ፣ሐዋርያው ማትያስ፣ ካህኑ ዘካርያስ፣ አባ ኪሮስ፣ ቅድስትአመተክርስቶስ
በ9.......ሐዋርያው ቶማስ፣ ቅዱስ አትናትዮስ፣ አቡነ እስትንፋሰክርስቶስ፣ አቡነ ብጹዕ አምላክ፣ አቡነ ህልያና፣ አቡነ ፂዋወንጌል
በ10.....መስቀለ ኢየሱስ፣ ሐዋርያው ናትናኤል፣ ያዕቆብ ወልደእልፍዮስ፣ ጼዴንያ ማርያም፣ ሰማዕቱ ሠርጊስ
በ11.....ሐና ማርያም፣ ቅዱስ ኢያቄም፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ሰማዕቱፋሲለደስ፣ አቡነ ሐራ ድንግል፣ አባ አሌፍ፣ ቅድስት ታኦድራ፣ቅዱስ ገላውዴዎስ
በ12......ቅዱስ ሚካኤል፣ ሐዋርያው ማቴዎስ፣ ቅዱስ ዮሐንስአፈወርቅ፣ አባ ሳሙኤል፣ ቅድስት አፎሚያ፣ ቅዱስ ዲሜጥሮስ
በ13.....እግዚአብሔርአብ፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ እልፍ አእላፍመላእክት፣ አቡነ ዘርዐ ብሩክ፣ አቡነ ተንሳኢ ክርስቶስ
በ14......አቡነ አረጋዊ፣ አባ ጳኩሚስ፣ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፣አቡነ ተስፋ ጽዮን፣ ሰማዕቱ አብሮኮሮስ፣ አባ ዘሚካኤል፣ሙሴጸሊም
በ15.....ቅዱስ ቂርቆስ፣ አቡነ ቆራይ፣ ቅድስት ለባሲተክርስቶስ፣አቡነ ያሳይ፣ አቡነ ተስፋ ሐዋርያ፣ አባ ሚናት
በ16......ኪዳነምሕረት፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ፣ ቅድስት እየሉጣ፣ሰማዕቱ ጊጋር፣ አባ ጽሕማ፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ አባጳውሊ
በ17......ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ያዕቆብ ወልደዘብዴዎስ፣ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ አቡነ ገሪማ፣ ቅዱስ ሚናስ፣ ጽላተሙሴ
በ18......ሐዋርያው ፊልጶስ፣ አቡነ ዮስጣጤዎስ፣ ቅዱስማርያዕቆብ፣ሰማዕቱ ሮማኖስ፣ ሊቁ ቅዱስ አባ ዳንኤል፣ አቡነአኖርዮስ፣ማዕቀበ አልፋ
በ19......ቅዱስ ገብርኤል፣ ሠለስቱ ደቂቅ፣ ቅዱስ ይምርሐነክርስቶስ፣ቅዱስ ሐርቤ (ገ/ማርያም)፣ አብየ እግዚእ፣ አቡነ ጸጋኢየሱስ፣አቡነ እናዝጊ
በ20.....ነቢዩ ኤልሳዕ፣ ሕንጸታ ቤተክርስቲያን፣ ቅዱስ ዮሐንስአንፂር፣ ቅድስት ወለተ ሰማዕት
በ21......እመቤታችንድንግል ማርያም፣ ነቢዩ ኢዩኤል፣ አቡነበትረ ማርያም፣ ቅድስት ሔራኒ፣ ጻድቁ ቆጵርያኖስ
በ22.......ቅዱስ ዑራኤል፣ ወንጌላዊው ሉቃስ፣ አባ ደቅስዮስ፣ብስራተ ገብርኤል፣ ሰማዕቱ ቶኮሎስ፣ ሰማዕቱ ቅዱስ ማሩና
በ23.......ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ልበ አምላክ ዳዊት፣ ጠቢቡሰለሞን፣ሰማዕቱ ቅዱስ ቤድራቶስ
በ24......24ቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)፣ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፣ ቅድስት አስቴርእስራኤላዊት፣ አባ ሙሴጸሊም፣ አቡነ መርቆርዮስ፣ አባ ኖብ፣ ቅድስት ወለተ ሙሴ፣አቡነ ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብጽ
በ25......ነቢዩ ዮናስ፣ ሰማዕቱ መርቆርዮስ፣ አቡነ አቢብ፣ ሕጻንሰሎሜ፣ አባ ሕጻን ሞዐ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ከማ
በ26......ነቢዩ ሆሴዕ፣ አረጋዊ ዮሴፍ፣ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፣ቶማስ ዘህንደኬ፣ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ)፣ አቡነሐብተማርያም፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ፣ አቡነ ሰበነ ድንግል
በ27.....መድኃኒዓለም፣ ርዕሰ አበው ሔኖክ፣ ቅዱስ ያዕቆብዘስሩግ፣ ቅዱስ ያዕቆብ ዘአርማንያ፣ አባ ጽጌ ድንግል፣ አቡነመብዐ ጽዮን (ተክለ ማርያም)፣ አቡነ ተክለ አዶናይ፣ አቡነ ተክለሐዋርያ
በ28.....አማኑኤል፣ አብርሐም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ አባይምአታ፣ አባ ሊቃኖስ፣ ቅድስት አመተ ክርስቶስ፣ አመተጊዮርጊስ
በ29......ባዕለ ወልድ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ አቡነ መዝርዐተክርስቶስ፣ አባ አፍጼ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ
በ30......መጥምቁ ዮሐንስ፣ ወንጌላዊው ማርቆስ፣ ቅድስትማርያም ክብራ፣ አቡነ አሮን ዘገሊላ
የቅዱሳን በረከት አይለየን::
#ወር_በገባ_በ ❷ #የእመቤታችን_ወዳጅ_የቅዳሴ_ማርያም_ደራሲ_የአባ_ሕርያቆስ_ወርሐዊ_መታሰቢያው ነው፡፡
ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ይሰውረን።🙏❤
++ለሚጸልይ ሰው ብዙ ሥርዓት አለው(1)++
መጽሐፈ ምዕዳን{የሰባቱ መነኮሳት መጽሐፍ}
.....የሚደገመውን ጸሎት በፍርሓት መድገም ነው፡፡ ሲደገምም ምሥጢሩን እያስተዋሉ ቀለሙ እንዳይነጥብ አድርጎ ሳይቸኩሉ ቀስ ብሎ ሳይጮሁ ለራስ እንዲሰማ አድርጎ መድገም ነው:: “ወኢትኈጕዕ ሶበ ትጼሊ-በምትጸልይበት ጊዜ አትቸኩል" እንዳለ ሲራክ 7:10። ሕዋሳትን ሰብስቦ ነው፡፡ አብዝታችሁ አትጸልዩ ብሏል፡፡ ማብዛት ከመሰልቸት መሰልቸት ከመተው ያደርሳልና፡፡ “ግብርኒ ዘአልቦ ምጣኔ ገዐር ውእቱ ወለገዐርኒ ይተልዎ ዝንጋዔ ወዝንጋዔኒ ያመጽእ ሐኬተ- ስጸልይ መጠን የሌለው ሥራ ጩኸት ነው፤ ጩኸትም መዘንጋትን ያመጣል ፤መዘንጋትም ስንፍናን ያመጣል " እንዳለ፡፡ ጩሃችሁ አትጸልዩ አለ “ኢትክላህ በህቁ አላ ዘምር በመጠን- ፈጽመህ አትጩኽ በመጠን ሆነህ አመስግንህ እንጂ" እንዳሉ ፫፻::
††† እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ150ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት †††
††† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲኾን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::
ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::
ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::
አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::
ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
††† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ (ዘፀ. 32:13): በምጽዋትም ማሰብ (ማቴ. 10:41) ይገባል::
††† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን!
††† የካቲት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."150"ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት (በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መ+ና+ፍ+ቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ381 ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
*ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
*ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም)
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
3.ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ (ንጉሠ ቁስጥንጥንያ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. 20:28)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ጥር 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ
#ፅንሰት_ልደት_ትንሣኤ_
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የከበረ #መልአክ_የቅዱስ_ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት የከበረዉን #ትንሣኤውን የገለጠበት ወርሐዊ መታሰቢያ ነዉ
👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ #ምፅአቱን የምንጠባበቅበት እለትም ጭምር ነዉ
👉በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል
👉ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ
👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች
👉መልአኩም እንዲህ አላት #ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል
👉 #እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም
👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል
👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ #የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።
👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው
👉ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ #በቅድስት_ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ በህቱም ድንግልና ታህሣሥ ሀያ ዘጠኝ ቀን ተወለደ
👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና
👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #በሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና
👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን #ሙታንና_ሕያዋን ደስ አላቸው
👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" ✝️💒✝️