ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጂ
👉 አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ ።
👉 ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ።
👉 ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም ።
👉 ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ ።
👉 ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም ፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ ።
👉 ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው ።
👉ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል ።
👉ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው ።
👉በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው ።
✍ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
/channel/silase
با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی
https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app
ሦስተኛው እሁድ ምኩራብ በመባል ሲታወቅ በየምኩራቦቻቸው ጌታ እየዞረ ማስተማሩንና ደውዮችንም መፈወሱን የሚያመለክት ንባብና የጌታን መዋዕለ ስብከት በአይሁድ ምኩራብ ውስጥ እንዴት እንደነበር ያሳየናል ። ኢየሱስም በየምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝም ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር 💚ማቴ💛9÷35❤️
/channel/silase
/channel/silase
††† እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሰለፍኮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ሰማዕቱ ሰለፍኮስ †††
††† ቅዱስ ሰለፍኮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ ክርስቲያን ወጣት ነው:: በወቅቱ ያ የጭንቅና የመከራ ዘመን ከመምጣቱ በፊት በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር አስጠራጦኒቃ የምትባል ደግ የሆነች ክርስቲያናዊት ወጣት አጭቶ ነበር::
በዕጮኝነት ዘመናቸው ጾምን: ጸሎትንና ንጽሕናን በመምረጣቸው ያየ ሁሉ ያደንቃቸው ነበር::
ታዲያ የሠርጋቸው ቀን እየቀረበ ሲመጣ ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ጀመረ::
ሁለቱ ንጹሐን ወጣት ክርስቲያኖች ተመካከሩና ወሰኑ:: በምክራቸውም መሠረት ሁለቱም ከነ ድንግልናቸው ሰማዕትነትን ለመቀበል ተዘጋጁ:: በዚች ዕለትም ስለ ቀናች ሃይማኖትና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በከ+ሃ+ዲው ንጉሥ ትዕዛዝ ቅዱስ ሰለፍኮስ በሰማዕትነት አልፏል::
††† ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት አምላከ ቅዱሳን ያድለን::
††† መጋቢት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሰለፍኮስ ሰማዕት
2.እናታችን ቅድስት ሣራ ጻድቅት (ግብፃዊት)
3.አባ ሕልያስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አፈ በረከት
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና
††† "ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና:: ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው:: አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ:: ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ:: እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው:: ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ::" †††
(1ቆሮ. 7:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ሦስተኛው እሁድ ምኩራብ በመባል ሲታወቅ በየምኩራቦቻቸው ጌታ እየዞረ ማስተማሩንና ደውዮችንም መፈወሱን የሚያመለክት ንባብና የጌታን መዋዕለ ስብከት በአይሁድ ምኩራብ ውስጥ እንዴት እንደነበር ያሳየናል ። ኢየሱስም በየምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝም ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር 💚ማቴ💛9÷35❤️
/channel/silase
/channel/silase
††† እንኳን ለ40 ቅዱሳን እና ለታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ †††
††† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚሕች ዕለት አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::
በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል::
በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2 ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት በዚችው ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::
††† ከቅዱሳን አባቶቻችን የስደት በረከት ፈጣሪ አይለየን::
††† አርባ ሐራ ሰማይ †††
††† አርብዐ ሐራ ሰማይ ማለት በዘመነ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሰማዕትነትን የተቀበሉ 40 ጭፍሮች ናቸው:: "ሐራ ሰማይ" የተባሉት በምድር ሲሠሩት የቆዩትን የውትድርና ሥራ ትተው የክርስቶስ (የሰማያዊው ንጉሥ) ጭፍራ ለመሆን በመብቃቸው ነው::
አርባው ባልንጀሮች ወጣትና ጐበዝ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በእርግጥ እነርሱ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት አልነበረም:: ነገር ግን ሰማዕትነት የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ : የእድሜ : የጾታ : የዘር . . . ልዩነት አያግደውምና እነዚህ ወጣቶች ለዚህ ክብር በቅተዋል::
ነገሩ እንደዚህ ነው:-
በ330ዎቹ አካባቢ የዓለም ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አንዱን መኮንኑን ወደ ቂሣርያ አካባቢ ይልከዋል:: የተላከው አካባቢውን ለማስተዳደር ሲሆን ቦታው ስብስጥያ (ሴባስቲ) ይሰኛል::
መኮንኑ ክርስቲያኖችን እንዲንከባከብ ጥብቅ ትዕዛዝ ከንጉሡ ቢሰጠውም ፍቅረ ጣዖት በልቡ የነበረበት ሰው ነውና ክርስቲያኖችን ይጨቁን : ያሰቃይ : ይገድል : አብያተ ክርስቲያናትን ያፈርስ ገባ::
በጊዜው ይህንን የተመለከቱት 40ው ጭፍሮች በአንድነት መክረው መኮንኑን ገሠጹት:: ስመ ክርስቶስንም ሰበኩለት:: እርሱም በፈንታው 40ውን አስሮ ብዙ አሰቃያቸው::
በመጨረሻ ግን 40ውንም የበረዶ ግግር አስቆፍሮ: ከነ ሕይወታቸው እስከ አንገታቸው ቀብሮ : ለ39 ቀናት ያለ ምግብ በጽኑ ስቃይ አቆያቸው:: በ40ኛው ቀን ግን ከ40ው አንዱ "ይህን ሁሉ መከራ የምቀበል ለምኔ ነው?" ብሎ "አውጡኝ!" እያለ ጮኸ::
ክርስቶስን አስክደው ወደ ውሽባ ቤት (ሻወር ቤት) ሲያስገቡት ፈጥኖ ሞተ:: በነፍስም በሥጋም ተጐዳ:: ነገር ግን ከአረማውያን ወታደሮች አንዱ "እኔን አስገቡኝ" ስላለ እንደገና 40 ሆኑ::
በዚህች ዕለትም 40ውን ጭን ጭናቸውን በመጅ እየሰበሩ ሲገድሏቸው ቅዱሳን መላእክት በአክሊል ከልለው : በዝማሬ አጅበው ወደ ገነት ወስደዋቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም በጊዜው ነበርና ገድላቸውን ጽፎ ውዳሴ ደርሶላቸዋል:: ቤተ ክርስቲያናቸውንም አንጾ የካቲት 16 ቀን እንዲቀደስ አድርጉዋል::
ብጹዕ አባታችን አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ በቅዱሳኑ ላይ የሆነውን ነገርና ሥልጣነ እግዚአብሔርን እያደነቀ እንዲህ ሲል ተናግሯል::
"ኦ አውጻኢሁ ለዘእንተ ውስጥ:: (በውስጥ ያለውን የምታስወጣ)"
"ወአባኢሁ ለዘእንተ አፍአ:: (በውጪ ያለውንም የምታስገባ)"
"ወይእዜኒ ስማዕ አውያቶሙ ለሕዝብከ እለ ይጼውዑከ በጽድቅ:: (እንግዲህ በእውነት የሚጠሩህን የወገኖችህን ጩኸት /ልመና/ ስማ)" ((ቅዳሴ ማርያም ቁ.146))
ስለዚህ በውስጥ ያለን አንታበይ:: ያለንበት የእኛ አይደለምና:: እንዳንወድቅም እንጠንቀቅ:: ብዙዎቹ የቆሙ ሲመስላቸው ወድቀዋልና:: ያሉ ሲመስላቸውም ወጥተዋልና::
በውጪ ያለንም ተስፋ አንቁረጥ:: ወደ ሁዋላም አንበል:: ወደ ቤቱ ሊመልሰን : በክብሩ ማደሪያ ሊያኖረን የታመነ አምላክ አለንና::
††† ቸሩ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ገብቶ ከመውጣት : አግኝቶ ከማጣት ይሠውረን:: ከሰማዕታቱ በረከትም አይለየን::
††† መጋቢት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ-ስደቱ)
2.ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ
3.40 ቅዱሳን ሰማዕታት (ከሃገረ ስብስጥያ)
4.ቅዱስ ዲዮናስዮስ (ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
††† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" †††
(ማቴ. 5:10)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝
ፍፁሞ አትችሉም #ድንቅ የሕይወት ቃል#lovesong#hymnfortheweekend#mezmur #donkeytube#l...
https://youtube.com/watch?v=TyDp6nRqXEg&si=4YujCM-z0dJQoHwd
አሜን አሜን አሜን 🥰🙏
እንኳን አብሮ አደረሰን 🥰🙏🙏 ቅዱስ ሚካኤል በችግራችሁ ግዜ አለሁ ይበላችሁ ከክፉ ይሰውራችሁ 🥰🙏🙏
/channel/silase
†✝† እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ድሜጥሮስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †✝†
†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†
†✝† ቅዱስ ድሜጥሮስ ድንግል †✝†
††† ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ: በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን እንዲያገባ ግድ አሉት::
ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48 ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል::
ቅዱስ ሚካኤልም ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ : ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር:: ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ: ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል::
ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና ተረድተው: "ማረን" ብለው በፍቅር የተለያዩት በዚሕ ዕለት ነው::
ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ (Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መ+ና+ፍ+ቃ+ንንም አውግዟል::
ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው::
††† አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ያሳድርብን:: ጸጋ በረከቱን ደግሞ ያትረፍርፍልን::
††† መጋቢት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት (ደንግልናው የተገለጠበት)
2.ቅድስት ልዕልተ ወይን
3.ቅዱስ መላዚ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት (ጠንቁዋዩን በለዓምን የገሰጸበትና አህያዋን እንድትናገር ያደረገበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
††† "ሥጋዊ ፈቃዳቸውን የሚሠሩ ሁሉ እነርሱ በላይኛው ዓለም የሞቱ ናቸው:: ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ድል ከነሳችሁት ለዘለዓለም በሕይወት ትኖራላችሁ:: የእግዚአብሔር መንፈስ የሚወደውን ሥራ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው::" †††
(ሮሜ. 8:13)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝
🔶Notcoin?
✅ዛሬ በደንብ ላብራራላችሁ Notcoin አሁን ላይ በጣም ሰው ጋር እየደረሰ ነው እናንተም እየሰራችሁ ነው ግን አብዛኞቻችሁ ያልገባችሁ ነገር ብዙ አለ ከእነሱ በጥቂቱ በ tap tap ብቻ እያሳደጋችሁ ነው ይሄ ደግሞ በጣም አሰልቺ ነው ስለዚህ አሁን የምነግራችሁን ነገር አድርጉ✅😎
✅ Earn የሚለው ውስጥ በመግባት ቀላል task መርጣችሁ መስራት ደግሞ በአንድ በtask ከ 100,000 በላይ Coin በላይ ታገኛላችሁ 😎
✅Boost የሚለው ውስጥ በመግባት multi tap ማሳደግ ቢያንስ እስከ level 5 energy limit ማሳደግ ቢያንስ ከ 3000 በላይ ዋናው ነገር ግን Autotap የሚለውን ቀድማችሁ ማብራት ከሁሉም በፊት
✅ደግሞ በብዙ account እየገባችሁ ብትሰሩ ጥሩ ይመስለኛል
✅ደግሞ ያልጀመራችሁ በጣም ቀላል ነው Start አድርጉና play የሚለውን በመንካት ከላይ ያለውን step ተከትላችሁ መስራት
✅አድስ ጀማሪዎች የኛን Squad ተቀላቀሉ
/channel/notcoin_bot?start=r_617538_25560679
/channel/notcoin_bot?start=r_617538_25560679
✅ደግሞ ብዙዎቻችሁ እንደማየው ከ 100,000 አላለፋችሁም ግን በ1 ደቂቃ መግባት ይቻላል earn የሚለው ውስጥ ገብታችሁ Task ስሩ ከዛ በደንብ ከሰራችሁ ዛሬ ብቻ ከ 500k በላይ ታስክ አለ ባገኛችሁት 🔶Boost ውስጥ ገብታችሁ በጥንቃቄ
✅AUTO TAP
✅MULTI TAP
✅ENERGY LIMIT ግዙ
ያልጀመራችሁ ደግሞ በዚህ Link እየገባችሁ ቦቱን Start በማለት እና Squadችን በመቀላቀል ጀምሩ😎
/channel/notcoin_bot?start=r_617538_25560679
/channel/notcoin_bot?start=r_617538_25560679
⚠️Squadችን Join ያላደረጋችሁ Join አድርጉ😎🙏
መጋቢት 16/2016 #ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን
👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው
👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት
👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ
👉"ከመረጥሁት ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ፣89፦3
👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል
👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ፣9፣16
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
የማህተብ ትርጉም
1.☑ቀይ ክር ======የጌታችን ደም ምሳሌ ለማስታወስ እናስራለን
2.☑ጥቁር ክር======የሀዘናችን ምሳሌ ለማስታወስ እናስራለን
3.☑ነጭ ክር=======የሰላምና የፍቅሩን የትንሣኤ ሙታን የመላእክት ምሳሌ ለማስታወስ እናስራለን
4.☑የእንጨት መስቀል====ስለ እኛ ኃጢያትና እርግማን በመስቀል ላይ ጌታችን መሰቀሉን ነው
5.☑የነሀስ መስቀል=====ስለ እኛ ምራቅ መተፍቱ መረገጡ መገረፉ ስለ እኛ ጌታችን መቁሰሉ ነው
6.☑የብር መስቀል======= ስለ እኛ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ብር መሸጡ ነው
7.☑የወርቅ መስቀል====== የጌታ ክብሩን ንውስነቱን የሁሉ ገዥ አምላክ መሆኑን
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳውያን ለመሆናችን ለመመስከር እናስራለን
ማህተቤን አልበጥስም
@silase
@silase
Ze....... Te........:
Ze....... Te........:
https://youtu.be/GkZN-AKkpRc
https://youtu.be/6EfEADWj0s8
ዘሚካኤል:
https://youtube.com/@-BeteLewiMedia?si=3H3K52YSgwum9WnR
ወንድም እህቶቼ ይህን መንፈሳዊ ዩቲዩብ subscribe እና like በማረግ እና በማስደረግ እንድታበረታቱኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ 🙏🙏🙏
፡
አንዳንድ ጊዜ ቀድመን 'ባጣናቸው ሰዎች ምክንያት እና የኛ በነበረች እያንዳንዷ ነገር ዛሬ ላይ ጊዜ ሰጥተን ስንብሰከሰክ እንውላለን! ለምን? በትውስታና በትዝታ ውስጥ ትርፋችን ሐዘን ከሆነ ያለው ምን ይረባናል??? እኛ ጊዜ 'ሰተን ምናስበው ፍጥረት እኮ እሱ እንደኛ ለኛ ላያስብ ይችላል፤ በሱ ልቦናም ተሰርዘን ፣ተረስተን ሊሆን ይችላል፤ ታዲያ ሐዘንን ለማስታወስ ብቻ ምስሉን ካስቀመጥነው እየደጋገመ በየጊዚያቱ መብሰልሰላችን የማይቀር ነው!!!
ደግሞም አብዝተን በትላንት ውስጥ ምንኖርና ትላንት በተከሰተብን ሁነት ፍራቻ ነጋችንን ቆልፈን ከተቀመጥን አዲስ ነገር መች መጥቶ ሊጎበኘን ነው??? ምን አልባት እኮ ካጣነው በላይ የተሻለ ነገር ለኛ ተሰናድቶ መሻታችንን እየጠበቀ ሊሆን ይችላል።
በትላንት ብቻ 'ሚኖር ትላንት ላይ ይቆማል!!!
.....የእናቴ ልጅ-Tame.....
@ t.me/Asresee
@ t.me/Asresee
@ t.me/Asresee
AIRPODS PRO
2nd Generation
USA🇺🇸
🎵 Brand New
🛎️With ORIGINAL Cable
🛎️With BoX and extra buds
ORIGINAL AIRPODS PRO PACKED
ONLY 1350 BIRR Fixed
🚗 Free Delivery around adis abeba
📞0939923298
†✝† እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ድሜጥሮስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †✝†
†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†
†✝† ቅዱስ ድሜጥሮስ ድንግል †✝†
††† ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ: በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን እንዲያገባ ግድ አሉት::
ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48 ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል::
ቅዱስ ሚካኤልም ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ : ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር:: ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ: ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል::
ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና ተረድተው: "ማረን" ብለው በፍቅር የተለያዩት በዚሕ ዕለት ነው::
ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ (Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መ+ና+ፍ+ቃ+ንንም አውግዟል::
ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው::
††† አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ያሳድርብን:: ጸጋ በረከቱን ደግሞ ያትረፍርፍልን::
††† መጋቢት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት (ደንግልናው የተገለጠበት)
2.ቅድስት ልዕልተ ወይን
3.ቅዱስ መላዚ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት (ጠንቁዋዩን በለዓምን የገሰጸበትና አህያዋን እንድትናገር ያደረገበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
††† "ሥጋዊ ፈቃዳቸውን የሚሠሩ ሁሉ እነርሱ በላይኛው ዓለም የሞቱ ናቸው:: ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ድል ከነሳችሁት ለዘለዓለም በሕይወት ትኖራላችሁ:: የእግዚአብሔር መንፈስ የሚወደውን ሥራ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው::" †††
(ሮሜ. 8:13)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝