kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ድልዋኒ ክሙ ንበሩ ፤ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ።
                   ማቴ ፳፬፥፵፬
እርሶስ በእለተ ደብረ ዘይት የት ኖት ?
እነሆ በአይነቱ ለየት ያለ የወንጌል መርሐ ግብር በጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መጋቢት 28 እና 29 /2016 ዓ.ም የደብሩ ስብከተ ወንጌል ታላቅ ጉባኤን አሰናድቷል ፤ እርሶም ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ እንዲገኙልን ሲሉ የደብሩ ስብከተ ወንጌል በክርስቶስ ፍቅር ይጠይቋቸዋል ።


Profile እንዲሁም History በማድረግ በአጫጭር ቪዲዮም በፌስቡክ ፣ በቲክቶክ ፣ በቴሌግራም እና በማንኛውም የማኅበራዊ ሚዲያ ይህንን ታላቅ ጉባኤ ይቀስቅሱ 🙏🙏🙏

#Share # ያጋሩ
#ይቀስቅሱ

ፕሮፋይል በማድረግ እንቀስቅስ 🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/Yeimkea0_o4?si=AuKK9dB8XzZDl2gW

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی

https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⬇️⬇️⬇️⬇️
የጥንት ቅኔ
ንኢ ንኢ ጉባኤ ቃና ድመት፣
አምጣነ ተክዕወ ለኪ ልበ ተማሪ ወተት።
❤️❤️❤️❤️
ፍቺ
⬇️⬇️⬇️⬇️
ጉባኤ ቃና ድመት ነይ ነይ። የተማሪ ልብ ወተት ፈስሶልሻልና።

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
➡️የቅኔው አመሥጥሮ
✅የቅኔው ሠም
✅የቅኔው ወርቅ
✅የቅኔው መንገድ
✅የቅኔው ዘይቤ
✅የቅኔው መነሻ ወዘተ ለማወቅ
💠💠💠💠💠💠💠
ለጥያቄ  ከዚኽ በታች ባለው
አድራሻ ይጠይቁኝ
❤️❤️❤️❤️❤️
(
@GeezL73 )
መ/ር ጳውሎስ ብለው ያናግሩኝ።
+251915642585

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

ገብተው የቅኔ ጥበብን ይቅመሱ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/XgBra8rPCEw?si=rAAnpa8qqZEOpXh0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹#ወር በገባ በ24 #አባ_ኖብ ሰማዕት📕

✍️ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች።

♨••እንኳን ለአባታችን ለአባ ኖብ ሰማዕት ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል::
ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል::
በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣእመ ስብከቱም190,000{ ከመቶ ዘጠና ሺህ} በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል::
ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች::

➛የአባ ኖብ ሰማዕት በረከታቸው ይደርብን፤
➛ጸሎታቸው ይጠብቀን፤
➛ለመንግሥተ ሰማይ መሪ በትር ይሁነን፤
➛ድካማቸው ከጠላት እጅ ያድነን፣
➛የትዕግሥታቸው ሀይል ከእሳት ባሕር ያድነን።

#አባ_ኖብ_ገዳም_ጉዞ_4_ሰው_ነፃ_ትኬት_ይሸለማል።
ይሄን ሥጦታ ለማግኘት መጀመሪያ #ሼር_ማድረግ እና ቀጥሎ #በኮሜንት_መስጫው ላይ"#ቅዱስ_አባ_ኖብ"ብሎ መጻፍ ብቻ።
እኩለ ጾምን{በዓለ ደብረ ዘይትን}

የደርሶ መልስ ጉዞ የፊታችን እሁድ #መጋቢት_29/2016.
ሼር በማድረግ
የድህነት ምክንያት ሁኑ🙏

የአባታችንን ተጋድሎ የምንናገርበት በጸበል በቃልኪዳናቸው የምንድንበት ጊዜ ደረሰ መላእክት በነብር ተመስለው የሚጠብቁት ከደጁ ፍጹም ሰላምን የሚያፍሱበት ታላቁ የቃል ኪዳን ስፍራ ቅዱስ አባኖብ ገዳም

#ቃል_ኪዳናቸውም
:➛እጅግ የበዛ ለትውልድ የተሰጡ፣ለክርስቲያኖች የታደሉ ድንቅ አባት ያሰኛቸዋል።በገዳሙ በሚገኘው ገድላቸውም ይሄ ቃል-ኪዳናቸው ተጽፎ ይገኛል።
:➛ ስለ ስሜ ብለህ የተቀበልከውን መከራ እያሰበ ስምህን የጠራ ከመከራ አድነዋለው።
➛ገድልህን የጻፈ የኃጢአቱን ደብዳቤ እፍቅለታለው።
➛ገንዘቡን አበረክትለታለሁ፤
➛ለቤተ ክርስቲያንህም ስዕለት የተሳለ ቢኖር እኔ በምድር ላይ እባርከዋለሁ፤
➛በመንግሥተ ሰማያት እጥፍ እሰጠዋለሁ፤
➛በስምህ በማመን።ልጁን የሰየመውን ሁሉ እኔ እባርከዋለሁ ቤቱንም እባርካለሁ።
➛#ከጥፋትም_ሁሉ_አድነዋለሁ።
➛ሴቶች ሁሉ በሚወልዱበት ጊዜ ምጥ የሚጸናባቸው ቢሆን ስምህን።በጠሩ ጊዜ እኔ እሰማቸዋለሁ፤ከብቶችም ቢሆኑ በምጥ በተያዙ ጊዜ ባለቤቶቻቸው ስምህን ቢጠሩ ፈጥኜ እሰማቸዋለሁ፤
➛መልአኩ ሱርያልንም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለቤተ ክርስቲያንህ እንዲላላክ አደርገዋለሁ ብሎ ቃል ገብቶላቸዋል።

ስፍራው ከአዲስ አበባ 100ኪሎ ሜትር ርቀት #ባልሞላ በቅርብ ርቀት #ቡልጋ ምድር #ደብረ_ጽላልሽ ከተሰኘው ከተክለሃይማኖት የትውልድ ሀገር #ኢቲሳ የቃል ኪዳን ምድራቸው ከሆነ ደብረ ጽላልሽ አካባቢ የሚገኘው
➛#በበረከት፣#በቃል_ኪዳን፣#በፈውስ እና #በጸሎት #ሰሚነት #በስእለት_ደራሽነት፣#በልጅ_ሰጪነት፣#በእውር #አብሪነት የሚታወቀው የታላቁ #ሰማዕት_አባ_ኖብ_ዘታህታይ_ግብጽ ብቸኛ ገዳማቸው።

ታቦታቸው የሚገኝበት በስማቸው የፈለቀ ጸበል ያለበት ብዙዎችም ➛እውራን ያዩበት ከወገብ ህመም የተፈወሱበት
➛ከካንሰር
➛ከቆዳ ሕመም
➛ከእንቅርት
➛ ከጨጓራ
➛ ከወገብ ሕመም የዳኑበት።ከአጋንንት እስራት የተላቀቁበት ነው።
ሥራ ያጡ፣በጽኑ የተቸገሩ፣በልጅ እጦት የተሰቃዩ ሁሉ መፍትሄ ያገኙበት ገዳሙም በነብር እና ሚዳቋ የሚጠበቅ ታላቅ የበረከት ስፍራ ሲሆን።

👉እኛም ከዚህ በረከት ለመቀበል እና ቃል ኪዳን ለመሳተፍ በዚህ የአቢይ ጾም የበረከት ሳምንታት ከገዳሙ ጋር በመሆን ዘወትር እሁድ እሁድ የደርሶ መልስ ጉዞ ከጠቅላላ መስተንግዶ ጋር አዘጋጅቶላችኋል።

የፊታችን እሁድ በ29-07-2016ዓ.ም

👉#ከፒያሳ_ጊዮርጊስ

👉 #ከጀሞ_ሚካኤል

👉 #ከመገናኛ እና #ጣፎ_አደባባይ መነሻ ያደረገ ጉዞ አዘጋጅተናል።

☎️ #በ09_16_55_80_80

☎️ #በ09_06_34_55_55

በመደወል መመዝገብ ሲችሉ።

በአካል ቢሮአችን ቦሌ አለምነሽ ፕላዛ ቢ.ቁ#812 በመገኘት ትኬቱን መቁረጥ ይችላሉ።

#የጉዞ_ዋጋ_500ብር_ሲሆን

#የደርሶ_መልስ_ትራንስፖርት እና #መስተንግዶን ያካተተ ነው።

ትኬቱንም #በባንክ እና #በቴሌብር በማስገባት ዲጂታል ትኬቱን በእጅ ስልካችሁ ከነ ወንበር ቁጥራችሁ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን።

አዘጋጅ :➛ቤተ-ኤጲፋንዮስ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል

#ማሳሰቢያ:➛በጉዟችን የ40 ደቂቃ የእግር ጉዞ ያለው ሲሆን ይህንን ልታውቁ ይገባል።

#ቤተ_ኤጲፋንዮስ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/RqNl5FkU3ck?si=boQST35uJQznTn4V




ሰላም የተወደዳችህሁ የእግዚያብሄር ቤተሰቦች ይህ ከላይ የምትመለከቱት የሰመዕቷ አዲስ ዝማሬ 😍 እና መስምሩን የዘመረው ወንድማችን ቀድሞ በጎዳና ላይ የሚኖር ነበር እና አሁን ግን ያንን ታሪክ ሊቀይር ይህን የመሰለ ጥዑም ዝማሬ ይዞልን መቷል እና እኛም መዝሙሩን በማድመጥ ለውስጣችን ሰላም ለእርሱም ማበረታቻ ነውና ሁላችሁም እየገባችሁ እንድትመለከቱት በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን 🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዩቱዩብ ቻናል👇
https://youtu.be/OIOCAD82nxk?si=VMEi2GBRFE8w3lMi

የቲክቶክ ቻናል👇
zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1

የቴሌግራም ቻናል👇
/channel/zikirekdusn

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በነገራችን ላይ ማይኩን ሀቅም ያለው ገዝቶ መላክ ይችላል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው ‹‹ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም›› ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ ‹‹ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ›› ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡ አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ ሰላማን በአቃሊት ቅበረኝ ብለዋቸው በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ አቃሊት ወሰዷቸው፤ እዚያም ሐምሌ 28 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰባት አክሊላት አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ዐፅማቸውም ከተቀበረ ከ140 ዓመት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ በክብር መጥቶ ዐርፏል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መጋቢት_23

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መጋቢት ሃያ ሦስት በዚች ቀን #ታላቁ_ነቢይ_ዳንኤል አረፈ፣ የደብረ ሊባኖሱ #አቡነ_ፊሊጶስ ፍልሰተ ዐፅማቸው በክብር ተከናወነ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢዩ_ቅዱስ_ዳንኤል

መጋቢት ሃያ ሦስት በዚች ቀን የዮናኪር ሴት ልጁ የወለደችው ታላቅ ነቢይ ዳንኤል አረፈ። ናቡከደናጾርም ኢየሩሳሌምን በወረራት ጊዜ አባታቸው ዮናኪር አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ሦስቱን ልጆቹን የልጁን ልጅ ዳንኤልንም ወሰዳቸው ከእንርሱም ጋር ከእስራኤል ልጆች ብዙ ሰዎች ተማረኩ ።

ይህም ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም ልጅ ነው። ኢሳይያስ ለሕዝቅያስ ንጉሥ ትንቢት እንደተናገረ የቤተ መንግሥቱንና የቤተ እግዚአብሔርን ዕቃ ሁሉ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን ወሰደ።

ይህ ዳንኤል ያን ጊዜ በዕድሜው ታናሽ ነበር ፍጹም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ የእግዚአብሔር መንፈስም አድሮበት በባቢሎን አገር ትንቢት ሲናገር ኖረ።

ምርኮ በሆነ በአራተኛው ዓመት ናቡከደነጾር የምታስፈራ ራእይን አየ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ያቺን ሕልም ረሳት። በባቢሎን የሚኖሩትን ሁሉን ጥበበኞች ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ያቺን ራእይና ትርጓሜዋንም እንዲነግሩት ፈለገ እንርሱ ግን ያቺን ራእይና ትርጓሜዋን ሊያውቋት አልቻሉም።

የባቢሎንን ጥበበኞች ሁሉ እርሱንና ባልንጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅን ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። ዳንኤልም ይህን ነገር ሰምቶ የዘበኞችን አለቃ ስለ ምን እንዲህ ያለ ትእዛዝ ከንጉሥ ዘንድ ታዘዘ ብሎ ጠየቀው። እርሱም ንጉሥ ስለ አያት ራእይ ነው የባቢሎንና የግብጽ ጠቢባን ሁሉ እርሷን ራእዩን ትርጓሜዋንም ሊነግሩት አልተቻላቸውምና ብሎ መለሰለት።

ዳንኤልም የዘበኞቹን አለቃ እኔ ለንጉሥ ሕልሙን እንደምነግረውና ፍቺውንም እንደምተረጕምለት ስለ እኔ ንገርው እሊህንም ተዋቸው አለው ። ከዚህ በኋላም ዳንኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ባልንጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅም ከእርሱ ጋር የንጉሡን ሕልም ፍቺዋንም ይገለጥላቸው ዘንድ በአንድነት ማለዱ።

እግዚአብሔርም ገለጠላቸው ዳንኤልም ወደንጉሥ ገብቶ ሕልሙንና ፍችዋን ነገረው። ከእርሱ በኋላም ስለሚነሡ ነገሥታት ከእንርሱም ከየአንዳንዳቸው የሚሆነውንም ገለጠለት። የዳንኤል ቃል ናቡከደነጾርን ደስ አሰኘው በፊቱም ሰገደ ብዙ እጅ መንሻንም ሰጠው ታላቅ ክብርንም ሰጥቶ በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።

ከዚህም በኋላ ናቡከደነጾር ሌላ ሕልም አየ ያንንም ተረጐመለት እንዲህም ብሎ አስረዳው ስለታበይክ እግዚአብሔር ከሰው መካከል አውጥቶ ከአራዊት ጋራ በዱር ሰባት ዓመት ያኖርህ ዘንድ አለው። እንደ እንስሳም ሣር ትበላለህ ከሰባት ዓመትም በኋላ ወደ መንግሥትህ ይመልስሃል ፈ በማለት ይህም ተፈጸመበት።

ናቡከደነጾር ከሞተ በኋላ መልአክ በግድግዳ ላይ የጻፋትን ለልጁ ለብልጣሶር ተረጐመለት በቤተ እግዚአብሔር ዕቃ በጠጣ ጊዜ ጽሑፉ የተቆጠረ የተመጠነ የተመዘነ እንደሆነ ትርጓሜውም ዙፋኑንና መንግሥቱን እግዚአብሔር ለሌላ የሰጠው መሆኑን ገለጠለት። እንዲህም አለው ቢመዝንህ ጐደሎ ሆነህ አገኘህ መንግሥትህንም ለፋርስ አሳልፎ ሰጠ ትንቢቱም ተፈጸመች።

እግዚአብሔርም እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚነግሡትን ነገሥታት በራእይ አሳየው የሐሳዊ መሲሕንም መገለጥ አሳየው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርነቱን ክብር ልዕልናውን ጌትነቱን አሳየው። የክበር ባለቤት ክርስቶስን ወደ ዓለም መምጣቱን ትንቢት ተናገረ ሱባኤዎችንም ወሰነ እንዚያ ሱባኤዎችም በተፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ።

ክርስቶስ ይመጣል ይገድሉታልም ለኢየሩሳሌምም መዳኛዋ ይሆናታል ብሎ ትንቢት እንደ ተናገረ። የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ቤተ መቅደስም እንደሚፈርስ የተናገረው ትንቢት ሁሉ ተፈጸመ።

በባቢሎን አገርም ቤል የሚባል ጣ*ዖ*ት ነበረ ምግብንም ሁልጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚፈጅ ቻል ዐሥራ ሁለት መስፈሪያ ስንዴ አርባ በግ ሰባት ፊቀን የወይን ጠጅ እያወጣጡ ይሰጡት ነበር። ንጉሡም ሁልጊዜ ይሰግድለታል ቤል ጣ*ዖ*ት*ም ከንጉሡ ቤት የሚሰጡትን የሚበላና የሚጠጣ ይመስለው ነበር ።

ንጉሡም ዳንኤልን ለቤል የማትሰግድ ለምንድን ነው አለው። ዳንኤልም ንጉሡን እኔስ ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ፍጥረቱንም ሁሉ በሕያውነት ለሚያኖር አምላክ እንጂ የሰው እጅ ለሠራው ጣ*ዖ*ት አልሰግድም አለው።

ንጉሡም ቤል ሕያው ያልሆነ ይመስላሃልን በየነጋታው እንዲበላ እንዲጠጣ አታይምን አለው። ዳንኤልም በንጉሡ ሳቀበት ንጉሥ ሆይ ይበላል ይጠጣል እያሉ አያታሉህ ይህ ውስጡ ጭቃ ላዩ ናስ ነው ምንም ምን አይበላም አይጠጣም አለው። ንጉሡም ተቆጣ የ*ጣ*ዖ*ቱን*ም ካህናት ጠራቸው እውነት ነውን ቤል አምላክ አይበላም አይጠጣምን አላቸው። ሁልጊዜ የምንሰጠውን በዕውነት ይበላል ይጠጣል አሉት።

ከዚህም በኋላ በመሸ ጊዜ ከጣ*ዖ*ቱ ዘንድ መብሉንና መጠጡን ሁሉ ንጉሡ እየተመለከተ ካህናቱ አስቀምጠው ወጡ። የጣ*ዖ*ቱ ካህናትም ከወጡ በኋላ ዳንኤል አመድ አምጡ ብሎ አዘዘ አመጡለትም። ንጉሡም ከዚያ ሁኖ እያየ በጣዖቱ ቤት ውስጥ ነሰነሰው። ንጉሡም በቁልፉ ከዳንኤል ጋር በአንድነት ቈለፉት አተሙትም ወደ ማደሪያቸውም ሔዱ። የጣ*ዖ*ቱ ካህናት ግን ከምድር በታች ውስጥ ለውስጥ መግቢያ ቀዳዳ ነበራቸው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ በሌሊት በዚያ ገብተው በሉ ጠጡ በመጡበትም ተመለሱ።

በማግሥቱም ንጉሡ መጥቶ የጣ*ዖ*ቱ*ን ቤት ከፈተ ራሱ ከአኖረው መብሎች ምንም አላገኘም ንጉሥም ቤል ሆይ ፈጣሪዬ ዳንኤልን ያሳፈርከው አንተ ገናና ነህ ብሎ ጮኸ። ዳንኤልም ሳቀ ለንጉሡም የወንዶችና የሴቶችን የልጆችንም ፍለጋቸውን በአመድ ላይ አሳየው። ንጉሡም የጣዖቱን ካህናት ይዞ መረመራቸው እነርሱም ውስጥ ለውስጥ ተሠውረው የሚገቡበትንና የሚወጡበትን ለንጉሡ አሳዩት። ያን ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ የጣ*ዖ*ቱ*ን ካህናት ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ገደላቸው ጣ*ዖ*ቱ*ን,ም ለዳንኤል ሰጠው። ዳንኤልም ሰበረው ምኲራቡንም አፈረሰ።

ከዚህ በኋላ ደግሞ የባቢሎን ሰዎች የሚአመልኩትና የሚሰግዱለት ታላቅ ዘንዶ ነበር ንጉሡም ዳንኤልን ይህንንስ አምላክ አይደለም ትለዋለህን እነሆ ሕያው ነው ይበላል ይጠጣል ናስ ነው ትለው ዘንድ አትችልምና ስገድለት እንጂ አለው።

ደንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔስ በሕያውነት ከሚኖር ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም ግን ያለ ሰይፍና ያለ በትር ይህን ከይሲ እገድለው ዘንድ አሰነሰብተኝ አለው። ንጉሥም አሰናበትኩህ አለው።

ዳንኤልም ጠጉርና አደሮ ማር ወስዶ እንደ እንቁላልም አድበልብሎ በእሳት አጋለው በሞራም ጠቅልሎ ለከይሲው አጐረሰው በዋጠውም ጊዜ ሆዱ ተሰንጥቆ ሞተ ዳንኤልም የባቢሎን ሰዎች ሆይ አምላካችሁን ተመልከቱ አላቸው።

የባቢሎን ሰዎችም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ ወደ ንጉሡም ተሰብስበው አይሁዳዊው ዳንኤል ነግሦአልን እነሆ ቤልን ሰበረው ካህናቶቹንም ገደላቸው ከዚያም ደግሞ ዘንዶውን ገደለው አሁን እርሱን ዳንኤልን እንድንገድለው ካልሰጠህን አንተን ቤተ ሰብህንም እንገድላለን አሉት።

ንጉሡንም እጅግ በአስጨነቁት ጊዜ ስለ ዳንኤል አዘነ ግን ዳንኤልን ሰጣቸው እነርሱም በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት በዚያም ሰባት ቀን ኖረ። ከረኀብ ጽናትም የተነሣ እንዲበሉት በሌላ ጊዜ የሚሰጧቸውን በእነዚያ ቀኖች ምንም ምን አልሰጧቸውም ነበር።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† እንኳን ለታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ዳንኤል †††

††† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ጴጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

††† ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት: አራቱ ዐበይት ነቢያት: አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ::

††† "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ
*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ
*አብርሃም
*ይስሐቅ
*ያዕቆብ
*ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::

††† "አራቱ ዐበይት ነቢያት"
*ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
*ቅዱስ ኤርምያስ
*ቅዱስ ሕዝቅኤልና
*ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

††† "አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት"
*ቅዱስ ሆሴዕ
*አሞጽ
*ሚክያስ
*ዮናስ
*ናሆም
*አብድዩ
*ሶፎንያስ
*ሐጌ
*ኢዩኤል
*ዕንባቆም
*ዘካርያስና
*ሚልክያስ ናቸው::

††† "ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስና
*ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

††† ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)ና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

††† በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት):
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::
ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ600 ዓመታት አካባቢ ከይሁዳ ነገሥታት ዘር ተወለደ:: ገና በሕፃንነቱ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ : ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን ሲያወርዳቸው አብሮ ወርዷል::

ከሕፃንነቱ ጀምሮ በአምላኩ ፍቅር የታሠረ : ከሦስቱ ጓደኞቹ (አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል) ጋር ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በዘመኑ እንደርሱ ያለ መተርጉመ-ሕልም አልተገኘምና ለወገኖቹ ሞገሳቸው ነበር::

ኃይለኛውን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ጨምሮ የባቢሎንና ፋርስ ነገሥታት ያከብሩት : ይወዱትም ነበር::

ቅዱስ ዳንኤል በጥበብና በሃይማኖት የአሕዛብን አማልክት ድል ነስቷል:: አሕዛብ በተንኮል ወደ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ቢያስጥሉት እግዚአብሔር የአናብስቱን አፍ ዘግቷል:: ዕንባቆምንም አምጥቶ መግቦታል::

ቅዱስ ዳንኤል የብሉይ ኪዳኑ "አቡቀለምሲስ" ይባላል:: ስለ ጌታችን የማዳን ሥራና ስለ ዳግም ምጽዐቱ በግልጥ ተናግሯል:: ሐረገ ትንቢቱም 12 ምዕራፍ ነው:: የዘመኑ አይሁድ ክርስቶስ ገና አልተወለደም ለማለት ዳንኤልን ጠልተውታል::

ታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል እስራኤል ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ አብሯቸው አልመጣም:: ከ70 ዓመታት በላይ በጸጋ ትንቢት ኑሮ እዛው ባቢሎን ውስጥ አርፏል::

††† ፈጣሪ ከበረከቱ ለሁላችን ያድለን::

††† በዚህች ቀን ክፉዎች አይሁድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይገድሉ ዘንድ በቤተ ቀያፋ መከሩ::

††† እርሱ ቸሩ አምላክ ከክፉ መካሪዎች ይሠውረን::

††† መጋቢት 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል (የስሙ ትርጓሜ- እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው::)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.አባ ሳሙኤል
6.አባ ስምዖን
7.አባ ገብርኤል

††† "የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ:: ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጉድጓድ ጣሉት . . . ድንጋይም አምጥተው በጉድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙት . . . በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሳ . . . ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኀዘን ቃል ጠራው . . . ዳንኤልም ንጉሡን . . . በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና . . . አምላኬ መልዐኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ:: አንዳችም አልጐዱኝም አለው . . . ዳንኤልም ከጉድጓድ ወጣ:: በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም::" ††† (ዳን. ፮፥፲፮-፳፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🍀 መሪጌታ መንግስቱ በብዙዎቹ የተመሰከረለት የባህል ህክምና በኢትዮጽያ : ይደውሉ ☎ 0913467282☎️ ፩ 🍀ለሀበት (ሀብት ማግኛ) : ፪ 🍀ለእቁብ ( እጣ እንዲወጣ)
፫ 🍀ለመስተፋቅር( የሚወዱትን ሰው አግብቶ ለመኖር
፬ 🍀ለስንፈተ ወሲብ (ብልቱ ለሚልፈሰፈስበት
፭ 🍀🍀የውጭ እድል ለተዘጋበት
፮ 🍀🍀 ለገቢያ ( ገበያ እንዲኖረን )
፯ 🍀🍀 ለትዳር እንቢ ላላቹሁ
፰ 🍀🍀 ለአይነ ጥላ
፱ 🍀🍀ለስልጣን
፲🍀🍀ገንዘብ አልበረክት ላላችሁ
፲፩🍀🍀ለግርማ ሞገስ
፲፪🍀🍀ገንዘባቹሁን የተወሰደባቹሁ እንዲመለስላቹሁ የሚያደርግ
፲፫🍀🍀አፍዝ አደንግዝ
፲፬🍀🍀ለትዳር የሚሆን ኮኮብ ቆጠራ
፲፭🍀ለሁሉ መስተፍቅር
፲፮🍀🍀ለድምፅ
፲፰🍀🍀ለብልት
፲፰🍀🍀ለውጭ እድል
፲፱🍀🍀 ለሰላቢ
፳🍀🍀ለደም ግፊት
፳፩🍀🍀ለመካንነት
፳፪🍀🍀 ለህመም
፳፫🍀🍀ኢቃማ ሳይኖራቹሁ ለምትንቀሳቀሱ እንዳትያዙ የሚያደርግ
፳፬🍀🍀ለቁማር
፳፭🍀🍀ለጥይት መከላከያ ወይም ጥይት እዳይመታ የሚያደርግ
፳፮🍀እፀ መሰዉር
ከምንሰጣቸዉ
በትንሹ ይህን ይመስላል
🍀 🍀በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር ውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን
🍀🍀ለጥያቄ ይደውሉልን

🇪🇹 0913467282
በimo አና Telegram ማውራት ለምትፈልጉ በውስጥ ያመስመር ያውሩኝ
ግሩፑን ይቀላቀሉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ቅድሚያ ለአባት"

ከመፅሀፍ ቅዱስ ውጭ ያሉ መፀሀፍቶ መፅሀፍ ቅዱስን ሸፍነውታል ወይም ጋርደውታል
መፅሀፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተሰጠን የፍቅር ደብዳቤ ነው ማለቱ ደስ የሚል አገላለፅ ይመሥለኛል፡፡ ይሄን የፍቅር ደብዳቤ(መፅሐፍቅዱስ)
እንዳናነብ ወይም በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን እንዳንሰማ የመፅሀፍ ቅዱስ ልጆች በሚባሉ መፅሀፍት የመሸፈን ሁኔታ ይታይበታል፡፡

"አባት" ቁጭ ብሎ "ልጅ" ቆሟል ልጅ የአባቱን ፊት ሸፍኖአል በአሁን ጊዜ "ልጅ" እኔ ልታይ እኔ ልታይ በማለት ላይ ይገኛል::
በየመምህራኖቻችን አፍ አብዛኛውን ጊዜ ስለ "ልጁ" ብቻ መሰበክ ስለ "ልጁ" ማንነት መናገር ይዘወተራል አባትን እየረሳነው ነው

በአብዛኞቻችን አማኞች በእጃችን ያለው "ልጁ" ነው "አባቱ" የለንም😞

እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው አባት በህይወት አለ ቦታ እንስጠው ለማለት ነው t.me/enweye

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 22/2016 #ቅዱስ_ዑራኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል መታሰቢያ ወርሐዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው

👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ (ዕዝ ሱቱኤል13፥39)

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው (ድርሳነ ዑራኤል ገጽ 26 ምዕ 4)

👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን "አሜን" የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ ⛪️ ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ትኬቱን ለማግኝት
+251985047611

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 26/2016 #ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም

"የቅዱሣኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ መዝ 115፥15"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለአረጋዊ_ቅዱስ_ዮሴፍ እና ለፃድቁ #አቡነ_ሐብተ_ማርያም ወርሐዊ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

👉አረጋዊዉ #ቅዱስ_ዮሴፍ በእርጅና ዘመኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምን ለመጠበቅ የተመረጠና በመፅሐፍ ቅዱስም ፃድቅ ተብሎ የተመሠከረለት ነዉ ማቴ 1፥19 ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን"

👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር

👉ግን የበቃ አባት አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች

👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር

👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል

👉ፃድቁ አባታችን በዝምተኝነትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል

👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል

👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውድ meki,,,,,,, እንኳን ደስ አሎዎት
የደረሶት ሽልማት መጠን :- 15,000 ብር
ነው

ሽልማት መቀበያ ቀን ሊያልቅ 1 ቀን ነዉ የቀረዉ

❇️ሽልማትዎን ለመቀበል ዋናው ግሩፕ ላይ ከ100 ሰዉ በላይ አድ ያድርጉ።

🎁 አድ ማድረጊያ ግሩፕ 👇
🏻👇🏻👇🏻
/channel/telebirr_one
/channel/telebirr_one
/channel/telebirr_one
🟢አድ አድርገዉ ሲጨርሱ
#የባንክ አካዉንት ይላኩልን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለዘመነ ሐጋይ (በጋ) የመጨረሻ ዕለትና ለሐዋርያው ቅዱስ አንሲፎሮስ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን ስነ ፍጥረት የፈጠረ ለሰው ልጆች ጥቅም ነው:: ጌታ አዝማናትን : ወሮችን : ሳምንታትን : ቀኖችንና ሰዓታትን ፈጥሮ : ወስኖ ሰጥቶናል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት እንደ መሆኗ ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ይፈፀማል::

በራሷ የዘመን ቀመር ስሌት መሠረትም አንድ ዓመት በአራት ወቅቶች ይከፈላል:: አባታችን ሊቁ ቅዱስ ያሬድም እነዚህን ወቅቶች መሠረት አድርጎ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::

እነዚሕ አዝማናት (ወቅቶች):-
1.ዘመነ ክረምት (ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25)
2.ዘመነ መፀው (ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25)
3.ዘመነ ሐጋይ (ከታኅሣሥ 26 እስከ መጋቢት 25)
4.ዘመነ ፀደይ (ከመጋቢት 26 እስከ ሰኔ 25) መሆናቸው ይታወቃል::

ዘመነ ሐጋይ (በጋን) የባረከ አምላክ ዘመነ ፀደይ (መከርን) እንዲባርክልን : የንስሐ ጊዜም እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን::

††† ቅዱስ አንሲፎሮስ †††

††† በዚህች ዕለት ጌታችንን በሃገረ ናይን የተከተለ : ከዋለበት ውሎ : ካደረበት ያደረ : ከሰባ ሁለቱ አርድእት የተቆጠረ ሐዋርያው ቅዱስ አንሲፎሮስ አርፏል::

††† ዳግመኛ በዚህ ዕለት አይሁድ ለመጨረሻ ጊዜ ጌታችንን ሊገድሉት ተስማሙ:: ይሁዳም በ30 ብር ይሸጠው ዘንድ ከአይሁድ ጋር ተዋዋለ::

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታውና ምሕረቱ ከሁላችን ጋር ይሁን::

††† መጋቢት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አንሲፎሮስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ: ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዘመናትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን:: እርሱም . . . ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ::" †††
(ዕብ. ፩፥፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Old telegram groups መሸጥ ለምትፈልጉ

Old telegram ግሩፖች ያላችሁ( be 2022 Ena keza betach balew amete mihret create yetederge )  የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም የGroup ሜምበር 1 ሰው ቢሆንም በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን ነው።  ግን የተከፈተበት አመተ ምህረቱን ነው የምፈልገው  ቢያንስ አንድ አመት የቆየ መሆን አለበት



ቢያንስ አንድ አመት የቆየ እና ትንሽ ሜምበር ያለው ግሩፕ (ከ1 ሜምበር ጀምሮም ይቻላል) ያላችሁ ሰዎች እና መሸጥ የምትፈልጉ inbox ላይ አናግሩኝ🙏 በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን።

Yetekefetebet year bekoye kutr birrum bezaw lk ychemral

It's not a scam it is real ከናንተም ከምታውቁትም ሰው የማትፈልጉትን በመሸጥ ብሮን ይቀበሉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی

https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††

††† ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው::

ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው::

††† ልደት †††

††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::

መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት::

1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2ኛ. በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል::

ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

ስድስት ክንፍ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*ስድስት ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

ተአምራት

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

ዕረፍት

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

=>ይህች ዕለት ለጽንሰታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡
††† አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባታችን በረከትን ይክፈለን::

††† መጋቢት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (ጽንሰቱ)
2.ቅዱሳን እግዚእ ኃረያና ጸጋ ዘአብ
3.ቅዱስ አባ መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አጋቢጦስ ጻድቅ
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ

††† "በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል::" †††
(ምሳሌ ፲፥፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †✝†

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††

††† ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው::

ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው::

††† ልደት †††

††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::

መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት::

1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2ኛ. በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል::

ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

ስድስት ክንፍ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*ስድስት ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

ተአምራት

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

ዕረፍት

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

=>ይህች ዕለት ለጽንሰታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡
††† አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባታችን በረከትን ይክፈለን::

††† መጋቢት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (ጽንሰቱ)
2.ቅዱሳን እግዚእ ኃረያና ጸጋ ዘአብ
3.ቅዱስ አባ መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አጋቢጦስ ጻድቅ
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ

††† "በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል::" †††
(ምሳሌ ፲፥፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችሗለን!+

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቤተሰብ እንደምን አላችሁ ሰላማችሁ ይብዛና ለበረከት የኮሰበር መንበረ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ማይክራፎን ለመግዛት የ100ብር ቻሌንጅ አድርገን ሁለት ባለ ገመድ ማይክራፎን እንግዛ በእግዚአብሔር ስም ከበረከቱ እንሳተፍ እኔ 100 ብር ችያለሁ

መደገፍ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ @Woladite11 ፈቃዳችሁን አሳውቀኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔርም መልአኩን ወደ እንባቆም ላከው እርሱም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለአጫጅዎች ምሳ ተሸክም ሲሔድ በራስ ጠጉሩ ተሸከመው። ወስዶም ዳንኤል በአለበት ጉድጓድ ውስጥ አኖረው። ዳንኤልም ተመግቦ እግዚአብሔርን አመሰገነው በዕንባቆምም ቃል ተረጋጋ በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የላከው መልአክ ወደ አገሩ ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አደረሰው።

በሰባተኛዪቱ ቀንም ስለ ዳንኤል እያለቀሰ ንጉሡ ወደ ጕድጓድ መጣ ዳንኤል ሙቶ አንበሶች የበሉት መስሎት ነበርና። ወደ ጕድጓዱም ሲመለከት ዳንኤልን አየው አንበሶችም እንደ ድመቶች እግሮቹን እየላሱ ከእግሮቹ በታች እጥፍጥፍ ብለው ተኝተው ነበር።

ንጉሡም እግሮቹን እስከሚልሱ እንደ ድመቶች አንበሶችን ያገረመለትና ያሰገዛለት የዳንኤል አምላክ ታላቅ ነው ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ። በዚያን ጊዜ ዳንኤልን ከጕድጓድ እንዲያወጡት እነዚያንም የዳንኤልን ጠላቶች ይዘው ለአንበሶች ወደ ጕድጓድ እንዲጥሉአቸው ንጉሥ አዘዘ ወዲያው እነዚያ አንበሶች በንጉሡ ፊት በሏቸው።

ዳንኤልም የእስራኤል ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም እስከ ሚመለሱበት ጊዜ በባቢሎን ኖረ እርሷም ሰባ ዘመን ናት ከዚያም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ፊሊጶስ_ዘደብረ_ሊባኖስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የአቡነ ፊሊጶስ ፍልሰተ ዐፅማቸው በክብር ተከናወነ፡፡ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሊጶስ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኩሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- ‹‹ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ ‹ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?› አሉት፡፡ እርሱም ‹ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ› አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ ‹አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ› አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡

አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም ‹ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?› አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም ‹ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት ‹ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል› ብሎኛል› ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር፡፡››
ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኮሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ ‹‹ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኩስና ይገባዋል›› አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኩስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡

በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡ አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ ‹‹ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች›› ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 አንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡

የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ ‹ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት› ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን ‹‹ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው›› ብለው መክረውት ‹‹እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት›› ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡ በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 23/2016 #ቅዱስ_ጊዮርጊስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት እና በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሐረገ ወይን ፀሐይ ማለት ነው ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 20 ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤኤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል አባቱ ዞሮንቶስ አንስጣስዮስ ይባላል ከልዳ መኳንንት ተሹሞ ይኖር ነበር እናቱ ቴዎብስታ አቅሌስያ ትባላለች ማርታና እስያ ተብለዉ የሚጠሩ እህቶች ነበሩት

👉10 አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው በጦር ሃይልም አሰለጠነው 20 ዓመት ሲሞላዉ የ15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ #እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ #ቅዱስ_ጊዮርጊስም ወደ ቤሩት ሄደ

👉በቤሩት ደራጎን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ #እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል

👉ወደ ፋርስ ሲመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገስታትን ሰብስቦ ጣኦታት ሰብስቦ ሲሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖት ቀናዒ ነውና ከቤተ መንግስቱ ገብቶ #እኔ_ክርስትያን_ነኝ_በኢየሱስ_ክርስቶስ አምናለሁ አለው

👉እርሱንም ማንነቱ ከተረዳ በኋላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው #ቅዱስ_ጊዮርጊስም ሹመት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬን #ኢየሱስ_ክርስቶስን አልክድም አለ በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት

👉እርሱ ግን ይህን ከሀዲ እስካስፈራው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ በማለት #እግዚአብሔርን ለመነና እንደ ጸሎቱ ተደረገለት በእምነቱ ጽናት ሰው ሊሸከመዉ የማይቻለውን መከራ የተቀበለ #ቅዱስ_ሰማእት ነው

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሰማእቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የኢትዮጵያ ጠባቂ ሰማእቱ ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሀገራችንን ህዝባችንን ጌታ ይጠብቅ ዘንድ በምልጃህ አስበን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ ተራ የማይደርሰው ተጠማቂ +

"ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው ሰውዬውም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት" ዮሐ.5:5-7

ይህንን ጥያቄና መልስ ሳይ በሽተኛውን ማናገር ያምረኝና እንዲህ በል ይለኛል :-

አንተ በሽተኛ ግድ የለህም የተጠየቅከውን ብቻ መልስ:: እመነኝ ጠያቂህ ተራ ጠያቂ አይደለም:: የሚጠይቅህ ሲያደርቁህ እንደኖሩት ሌሎች አሰልቺ ጠያቂዎች አይደለም:: ጥያቄውም የሌሎችን ሰዎች ዓይነት ጥያቄ አይደለም:: ከፊትህ የቆመው የመጠመቂያውን ውኃ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሞላውን ውኃ የፈጠረ አምላክ ነው::

"ወደ መጠመቂያው የሚያኖረኝ ሰው የለኝም" አልክን? የተጠየቅከውን መልስ እንጂ! ወደ መጠመቂያው መግባት ትወድዳለህን? ብሎ ማን ጠየቀህ? የጠየቀህ ማን እንደሆነ ባታውቅ እንኩዋን ጥያቄውን እንኳን በደንብ ስማ እንጂ!

ሰው የለኝም አትበለው : ስለመጠመቂያው ወረፋ አትንገረው : ስንት ሰው ቀድሞህ እንደዳነ አትቁጠርለት:: የጠየቀህ ግልፅ ጥያቄ ነው::

ልትድን ትወዳለህን?

እግዚአብሔር ፊት ስለ ችግርህ ክብደት ለምን ታወራለህ? ምን እንደሌለህማ እሱም ያውቃል:: አዎን እድን ዘንድ በለው:: ችግርህን ትተህ የምትፈልገውን ንገረው:: የችግርህ መወሳሰብና ሥር መስደድ ለእሱ የሚከብድ አይደለምና መዳን እንደምትሻ ብቻ በእምነት ንገረው የሚል ተግሣፅ በበሽተኛው በኩል ወደ እኛ ደረሰ::

🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌

መጻጉዕ (በሽተኛው) ቤተ ሳይዳ ከመጣ 38 ዓመት ሆነው:: ዳዊትና ሰሎሞን 40 40 ዓመት ነግሠው እንኳን ብዙ የምሬት ቅኔ ተቀኝተዋል:: ይህ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ አርባ ዓመት ሊሞላው ሲል ምንኛ ተንገሽግሾ ይሆን?

ልብ በሉ ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ይህ በሽተኛ በአልጋው ላይ ነበረ:: እረኞች ከብዙ መላእክት ጋር ሲዘምሩ እሱ የአንድን መልአክ መውረድና ውኃውን ማናወጥ እየጠበቀ ስድስተኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር:: ጌታችን የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ደርሶ ወደ መጠመቂያው ሥፍራ ሲመጣም ይህ ሰው አልጋው ላይ ነው:: መጠመቂያዋን 38 ዓመት በተስፋ ሲጠብቅ ቆይቶ ሳይጠመቅባት ቀረ::

ጌታ ሆይ የማይደርሰኝን ወረፋ ከመጠበቅ አድነኝ:: እንድፈወስበት ባልፈቀድክበት ሥፍራ ዕድሜዬን እንዳልጨርስ ጠብቀኝ::

ወደ ሐዲስ ኪዳንዋ ቤተ ሳይዳ ወደ ቤተክርስቲያን ከመጣሁ ብዙ ዘመን አስቆጠርኩኝ:: ግን እስካሁንም ድረስ ከኃጢአት አልጋ ላይ አልወረድሁም:: መነሣት እፈልጋለሁ ግን አቃተኝ:: ልቤ እንጂ እግሬ ጸንቶ መቆም አልቻለም::

ፈረቃ የሌለብህን የሕይወት ውኃ አንተን ሊጠጡ ሲመጡ በዓይኔ እየተቀበልኩ ብዙዎች ጠጥተውህ ሲድኑ በዓይኔ እየሸኘሁ አልጋዬ ላይ ቀረሁ::

እኔ እንደተኛሁ ስንቱ ቀድሞኝ እንደዳነ ባየህልኝ:: ከእኔ በኁዋላ መጥተውስ ከእኔ በፊት ስንቶች ዳኑ?
ስንቱ ከኃጢአት አልጋ በንስሓ ተነሥቶ ያንተን ሥጋና ደም ተቀብሎ ተፈወሰ?

የቤተ ሳይዳው ሐኪም ሆይ ወደ አንጋፋው በሽተኛህ ወደ ጽኑዕ ሕመምተኛህ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ይሆን? ያን ሕመምተኛ "ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበረ" አውቀህ ያናገርከው ሆይ እኔን የምታናግረኝ መቼ ይሆን? እኔስ ብዙ ዘመን እንደሆነኝ አታውቅምን? ሰው የለኝም : ልብ የለኝም : ኃይል የለኝም : አቅም የለኝም ብዬ ብሶቴን የምነግርህ መቼ ይሆን?

"ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ" ዮሐ.5:8-9

አንተ ተነሥ ብለኸው የማይነሣ ማን ነው? እንኳንስ ከአልጋ ከመቃብርም ተነሥ ያልከው ይነሣ የለምን?
ግዴለህም እኔንም ተነሥ በለኝ:: ተነሥ ኃይልን ልበስ ያልከኝ እንደሆነ እንኳንስ "ሸክሜም ቀሊል ነው" ያልከው አንተ ያዘዝከኝ የራሴን ሸክም ቀርቶ የወንድሜን ሸክምም ተሸክሜ የአንተን ሕግ እፈጽማለሁ:: (ገላ. 6:2)

🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌

"ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ... ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፡ አለው" ይላል::

በሽተኛው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ እንደሔደ ሳነብ አንድ ነገር ልቤን አስጨነቀው:: ይህ ሰውዬ 38 ዓመት ሙሉ የኖረው በቤተ ሳይዳ ነው:: ክርስቶስ ድንገት ፈውሶት ሒድ ሲለው እሺ ብሎ ከዚያ መጠመቂያ ሥፍራ ከወጣ በኁዋላ ወዴት ሔደ?

የሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛው ሆይ እውነት ወዴት ሔድህ? ከመጠመቂያው መውጣትህን ሰምተን አድንቀናል:: ከዚያስ ወዴት ሔድክ? ዙሪያ ገባው አልተለወጠብህም? መንገድስ አልጠፋብህም?
ወደ ዘመዶች ቤት ሔድክ እንዳልል "ሰው የለኝም" ስትል ሰምቼሃለሁ::

አልጋህንስ የት አደረስካት? መቼም ሰባብረህ እንደማትጥላት የታወቀ ነው:: አልጋ ለታመመ ብቻ ሳይሆን ለጤነኛም ያስፈልጋልና አራት እግር እያላት ጥላህ ያልሔደችውን ዘመድህን መቼም በክብር ማስቀመጥህ አይቀርም::

ለማንኛውም እዚያው ምዕራፍ ላይ ኢየሱስ ይህንን በሽተኛ ዳግም በመቅደስ አገኘው ይላል:: ዮሐ. 5:14 ጌታ ከመጠመቂያ ቦታ አድኖ ያስነሣውን ሰው በመቅደስ ቆሞ አገኘው:: ይህ በሽተኛ እግሩ ሲጸናለት የሔደው ወደ ፈጣሪ ደጅ መሆኑ ያስመሰግነዋል::

ጌታ በመጠጥ ቤት ቢያገኘው ኖሮ ያሳዝን ነበር:: እግርህን ያጸናሁልህ ለዚህ ነው ወይ ብሎ ባዘነበት ነበር:: አሁን ግን ያዳነው ጌታ በመቅደስ አግኝቶት "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" አለው::

ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ክርስቶስ አንተንስ አላዳነህም? "ኸረ እኔ ሽባ ሆኜ አላውቅም:: ማንም እኔን ከአልጋ አላስነሣኝም ትለኝ እንደሆን እመነኝ ክርስቶስ እንደ አንተ ያዳነውስ የለም:: እርሱ እኔና አንተን ተነሡ ብሎ ያስነሣን ከ38 ሳይሆን ከዘላለም የሲኦልና የኃጢአት አልጋ ነው::

እኛን የፈወሰን አልጋችንን አሸክሞ ሳይሆን እሱ ራሱ እኛን ከነአልጋችን ተሸክሞን ነው:: ካላመንከኝ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠይቀው "እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ" ሲልህ ትሰማዋለህ:: ኢሳ. 53:12 የእኛን በደል ተሸክሞ ጀርባው ምን ያህል እንደ ቆሰለ ባየህ:: ይህንስ ጀርባዬን ታያለህ የተባለውን ሙሴን ብትጠይቀው ሳይሻል አይቀርም::

ያዳነህ አምላክ አንተንስ የት ነው የሚያገኝህ? እንደዚህ ሰውዬ መቅደስ ያገኝህ ይሆን?

የትም ቢያገኝህ ግን ቃሉ አንድ ነው "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት የሚብስ ምን ሊመጣ ነው? ካልክስ እሱን ከማየት ይሠውረኝ ብትል ይሻልሃል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 10 2014 ዓ.ም. ተጻፈ
ባሕር ዳር ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በእግዚያብሄር ስም ቅዱስ ገብርኤል ብለህ አስተባብርልኝ7000027456591 ንብ ባንክ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✍ “መጻጉዕ” የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት ✍

የዐቢይ ጾም አራተኛው ሳምንት መጻጉዕ በመባል ይታወቃል፡፡ "መጻጉዕ" ማለት ትርጓሜው በቁሙ ሲፈታ "ጐበጠጠ" ማለት ነው፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(1948)። "መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ" ገጽ 605

መጻጉዕ የስያሜው ዋና ታሪክ፥ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ በምትባለው ቦታ አምስት መመላለሻ የነበራት አንዲት መጠመቂያ ሥፍራ ነበረች። በዚህች ሥፍራ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ስለታመመ አንድ ሰው የሚተርክ ነው። በአጠቃላይ ይህች ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የማዳኑ ጉዳይ ጎልቶ የሚነገርበት ነው፡፡ ይህንንም እንደሚከተለው እንመለከተዋለን።

መጻጉዕ

በዚህ በአራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ በሽታዎች ያሏቸውን ሰዎች ፈውስ እንደሰጣቸው ይሰበክበታል። በተለይም ለእነዚህ በሽተኞች ጌታችን ፈውስን ያደረገላቸው በሰንበት በመሆኑ፤ በሰንበት መልካም ሥራን መሥራትን፤ የታመመ መጠየቅን፤ ያዘነ ማጽናናትን፤ የደከመ መርዳትን፤ የነፍስ ረኀብ ያለበትን በቃለ እግዚአብሔር ማበርታትን እና ተመሳሳይ ሥራዎችን መሥራት ተገቢ እንደሆነም ይሰበክበታል። የሰንበት ቀን የተቀደሰች ዕለት ናትና በሰንበት ክርስቲያኖችን በጎ ሥራ መሥራትን ለሕይወታቸው ተገቢውን መንገድ የምናሳይበት እንጂ የግል ሥራ የምንሠራበት አለመሆኑም ይሰበክበታል።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት፣ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ሲፈውስ ሳለ፤ ከዕለታት አንድ ቀን በቤተሳይዳ በምትገኘው መጠመቂያ ሕሙማንን ሲጎበኝ ከነዚያም መካከል ሠላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ በሕመም ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘ መጻጉዕ የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው የህመሙ ዘመን ስለረዘመ ዘመዶቹ ሁሉ እየሰለቹ የማስታመሙን ነገር ችላ ብለው የጣሉት ሰው ነበር። ህመምተኛው ዘመዶቹ በተውት በቤተሳይዳ መጠመቂያ ጠበል አጠገብ ተኝቶ ነበር፡፡ ቤተሳይዳ አምስት መመላለሻ ነበራት፡፡ በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፣ ሰውነታቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ በቤተሳይዳ አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያዪቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማንኛውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሀን ከሠላሳ ስምንት ዓመታት ጀምሮ የታመመ ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን ተኝቶ እንደኖረ አውቆ አዘነለትና “ልትድን ትወዳለህን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኋላ በሰንበት ፈውሶኛል ብሎ ለአይሁድ ምስክር ይሆን ነበርና ዝም ብሎ አድኖት ቢሆን ኖሮ፤ እኔ ሳልጠይቀው ራሱ ወዶ አዳነኝ እንጂ እኔ መቼ ጠየቅሁት እንዳይል አስቀድሞ ጠየቀው። እርሱም ውኃው በተናወጠ ጊዜ መጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም በማለት መልስ ሰጠ፡፡ ፀበሉን አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ መጠመቂያው ወርዶ ውኃውን ድንገት ሲያናውፀው፤ ቀድሞ ወደ ጠበሉ የገባ ይድን ስለነበር፤ መልሱ የሚያመለክተው ከሁሉ ቀድሞ እኔን ተሸክሞ ወደ ፀበል ሊያስገባኝ የሚችል ዘመድ ስለሌለኝ እንዴት እድናለሁ ነበር። ነገር ግን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም መድኃኒት በመሆኑ ወዲያው " ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ”ሲለው ወዲያውም ሰውዬው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ /ዮሐ.፭፥፰/ ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ፡፡ ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው፤ ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልሀም አሉት፡፡ እርሱ ግን ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። በሌላ ጊዜ ጌታችን ሲያገኘው "እነሆ! ድነሃል ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ዕወቅ" በአለው ጊዜ ይህ ሰው ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት በኋላ ከተጣበቀበት አልጋ ያላቀቀውን አምላክ ረስቶ ለአይሁድ ሊጠቁመው ሮጦ ሄደ፡፡ እንዳሰበውም ነገራቸው እነሱም ሊያሳድዱት ሊገሉትም ይሹ ነበር።

በዚህች ሳምንት በተደረገልን መልካም ሥራ እያመሰገን የታመሙትን፣ የታሰሩትን፣ በችግር የወደቁትን መጎብኘት የተጣላ በማስታረቅ ወዘተ... ይህን የመሰለውን በጎ ሥራ ሁሉ መሥራት ይገባናል፡፡ በአጠቃላይ በዚህች ዕለት ነፍስን የማዳን ሰውን ከችግሩ የማላቀቅ፣ መንፈሳዊ ዕርዳታ የመርዳት ግዴታ አለብን፡፡ ዛሬስ እግዚአብሔር ላደረገልን መልካም ነገር ተገቢውን መልካም ምላሽ የመለሰን ስንቶቻችን እንሆን? ራሳችንን ልንመለከት ይገባናል፡፡ ለለመኑት ፈውስን ሰጥቶ በጐ ምላሽ እንዲሰጡ ያጸናቸው እግዚአብሔር አምላክ እኛንም ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

አምላኩሰ ለአዳም ለዕረፍት ሰንበተ ሠርዓ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ ወይቤሎሙ ኢየሱስ አነኒ እገብር አንትሙኒ እመኑ ለግብርየ ወይቤሎሙ አነ ዉእቱ እግዚአ ለሰንበት እግዚአ ዉእቱ ለሰንበት ወልድ ዋህድ ወይቤሎሙ ብዉህ ሊተ እኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር እስብክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ

ትርጉም። የአዳም ፈጣሪ ለዕረፍት ሰንበትን ሠራ። አይሁድም በማን ሥልጣን ይህን ታደርጋለህ አሉት፤ እርሱም እኔ እሠራለሁ እናንተም ሥራዬን እመኑ አላቸው፡፡ የሰንበት ጌታ እኔ ነኝ፤ የሰንበት ጌታዋ የአብ አንድያ ልጁ ነው። በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር እል፤ ነጻነትን እሰብክ፤ የዕውራንን ዐይን አበራ ዘንድ አባቴ ልኮኛል አላቸው።

በዚህች መጻጉዕ በተባለች ሳምንት እሑድ ጌታችን በዚህች ምድር ሲመላለስ የፈጸመውን የፈውስ ሥራ የሚያስረዱ የሚነበቡት ምንባባት (የቅዳሴ ምንባባት) የሚከተሉት ናቸው፡፡

ምንባባተ መጻጉዕ

መልዕክታት

➢ ገላ ፭፥ ፩-ፍጻ

➢ ያዕ. ፭፥ ፲፬-ፍጻ

ግብረ ሐዋርያት

➢ የሐዋ.ሥራ ፫፥፩-10

ምስባክ
መዝ ፵፩፥ ፫-፬
" እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ። ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ:: አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፡!"

➢ ትርጉም፡

"እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል። እኔስ አቤቱ ማረኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት አልሁ።"

ወንጌል
ዮሐ ፩፥ ፩
ቅዳሴ

➢ ቅዳሴ ዘእግዚእነ

ምንጭ :- ኢ.ኦ.ተ.ቤ ቴቪ

ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ( አዳማ - ኢትዮጵያ)
መጋቢት 21/ 2016 ዓ.ም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/notcoin_bot?start=rp_35961041
🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift
🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium @PremiumBot

Читать полностью…
Subscribe to a channel