ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል ተቀብሎ ከፍዳ ከኩነኔ ያዳነን መድኃኔዓለም (የዓለም መድኃኒት) ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር፥ምስጋና፥ስግደት ለእርሱ ይገባል።
***ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ (መከራ) መስቀል፤
፩ኛ/ተኮርዖተ ርዕስ:-ራሱን በዘንግ መመታቱ፤፪ኛ/አክ ሊለ ሦክ:-የሾህ አክሊል ጎንጉነው ደፍተውበታል። ማር:፲፭፥፲፰።፫ኛ/ተአስሮ ድኅሪት:-እጆቹን ወደ ኋላ ጠፍረው አስረውታል።፬ኛ/ስትየ ሐሞት:-ተጠማሁ ባለ ጊዜ ሐሞት፥ከርቤና ወይን ቀላቅለው አቅርበውለ ታል።መዝ:፷፰፥፳፩፣ማቴ:፳፯፥፴፬፣ማር:፲፭፥፳፫፣ሉቃ:፳፫፥፴፮።ቀምሶ ተወው።፭ኛ/ወሪቀ ምራቅ:-ሐክታቸ ውን ከፊቱ ላይ ተፍተውበታል።ኢሳ:፶፥፮፣ማቴ:፳፯፥፳፱ ።፮ኛ/ተቀስፎ ዘባን:-ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆ ጠር ድረስ አምስት ሺ አምስት መቶ ጅራፍ ገርፈው ታል።ኢሳ:፶፥፮።፯ኛ/ጸዊረ መስቀል:-ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ከባድ መስቀል ተሸክሟል።ዮሐ:፲፱፥፲፯።፰ኛ/ ተጸፍዖ መልታህት:-ፊቱን በጥፊ መትተውታል። ማቴ:፳፮፥፷፰።ከ፱ - ፲፫ ያሉት ሳዶር፥አላዶር፥ዳናት፥ አዴራ፥ሮዳስ የተባሉት አምስቱ ቅንዋተ መሰቀል ናቸው።(አምስቱ ችንካሮች)።መዝ:፳፩፥፵፮።
***ሰባቱ አጽርሐ መስቀል፤(በመስቀል ላይ የተናገራ ቸው)።
፩ኛ/“ኤሎሄ፥ኤሎሄ ላማ ሰብቅታኒ፤አምላኬ፥አምላኬ ለምን ተውከኝ?”ብሏል።ማቴ:፳፯፥፵፮።እርሱ በተዋ ህዶ የከበረ የባህርይ አምላክ ሲሆን ስለ አዳም ተናግ ሮታል።አዳም በሲኦል የጸለየው ጸሎት ነው።
፪ኛ/“አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ፤” ብሏል።ከዚያ በፊት ነፍስ የምትሰጠው ለሲኦል ነበር፥ እርሱ ቀረላችሁ ሲል ነው።ሉቃ:፳፫፥፵፮።እርሱ ራሱ ዕሩይ ምስለ አብ ስለሆነ ነፍስን ይቀበላል።የሐዋ:፯፥ ፶፱።
፫ኛ/“እነሆ ልጅሽ፥እነኋት እናትህ፤”በማለት ድንግል ማርያምን የአደራ እናት አድርጎ ለቅዱስ ዮሐንሰ (በእ ርሱም በኩል ለቤተ ክርስቲያን)፥እርሱንም የአደራ ልጅ አድርጎ ለእርሷ አረካክቧል።እመቤታችን በሕይወ ታችን ተጠብቃ የምትኖር አምላካዊ አደራ ናት።ዮሐ: ፲፱፥፳፯።
፬ኛ/የሕይወት ውኃ እርሱ ”ተጠማሁ፤”ብሏል።ዮሐ:፲፱ ፥፳፰፣፬፥፲፬፣፮፥፴፭፤፩ኛ:ቆሮ:፲፩፥፬።
፭ኛ/ባለቀ ሰዓት ንስሐ የገባውን፥በቀኙ የተሰቀለውን ወንበዴ:-“ከአዳም ቀድመህ ገነት ትገባለህ፤”ብሎታል ።ሉቃ:፳፫፥፵፫።
፮ኛ/መከራ አጽንተው የሰቀሉትን ሁሉ ይቅር ብሎ “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላ ቸው፤”በሏል።አብ ይቅር አለ ማለት ከእርሱ ጋር በአን ድነት የሚመሰገኑ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ይቅር ብለዋል ማልት ነው፥በመለኮት አንድ ናቸውና።ሉቃ: ፳፫፥፴፬።
፯ኛ/በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅ ፀን የዕለት ፅንስ ሆኖ የጀመረውን የማዳን ሥራ በመ ስቀል ላይ በመፈጸሙ “ተፈጸመ፤”በሏል።ዮሐ:፲፱፥፴።
ቢያንስ ለ10 ሰዎች በመላክ ሰብስክራይብ እና ላይክ በማስደረግ አገልግሎቱን ያጠናክሩ።
https://kassdire.psee.ly/5zyxnm
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝
"✝" ግንቦት 26 "✝"
+*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+
=>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::
+እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::
+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
+ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
+አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
+በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
+በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
+ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
+ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
+በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
+ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
+ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
+እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
+ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
<< ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >>
=>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊
(ማቴ ፫:፫)
✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨
🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም።
⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።
🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን።
⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት።
🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ"
⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።
🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።
✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
🔗/channel/zikirekdusn
▶️ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
👉እያንዳንዱ ክርስቲያን ቅድስናን ለራሱ አስፈላጊ እና ማበረታቻ ማግኘት አለበት።
👉ያለ ተጋድሎና ቅድስናን ተስፋ ሳታደርጉ የምትኖሩ ከሆነ በስም ብቻ እንጂ በመሠረታዊነት ክርስቲያን ናችሁ።
👉ነገር ግን ያለ ቅድስና ማንም ጌታን አያየውም ማለትም ዘላለማዊ በረከትን አያገኙም።
👉 ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም መጣ የሚለው የታመነ ቃል ነው (1ጢሞ. 1፡15)።
👉እኛ ግን ኃጢአተኞች ሆነን ድነናል ብለን ካሰብን ራሳችንን እናስታለን።
👉ክርስቶስ እነዚያን ኃጢአተኞች ቅዱሳን የሚሆኑበትን መንገድ በመስጠት አዳናቸው።
ከቅዱሳን አንዱ እንዳስተማረው
ሰይጣን ሰበበኛ አድርጎናል!
👉አንዳንዶቻችን ለኃጢአታችን ተጠያቂ መሆናችንን ሳይቀር እስከመካድ በሚያደርስ ደረጃ "ሰይጣን አታለለኝ" በምትል ጥቅስ ራሳችንን ከጥፋተኝነት ነፃ ለማድረግ እንሞክራለን።
👉 በእውነቱ አሁን ላይ ሰው በኃጢአቱ እግዚአብሔርን ከማሳዘኑ በላይ የሚያስጨንቀው በሰዎች ዘንድ ምን ዓይነት ስም ይሰጠኝ ይሆን ብሎ ነው! በዚህም ለኃጢአቱ ሰይጣንን ተጠያቂ ያደርግና ራሱን ገሸሽ ያደርጋል።
👉ሰይጣን አስገድዶ የኃጢአትን ሸክም በአንተ ላይ አይጭንብህም!
👉 ኃጢአትን በልብህ ፀንሰህ በተግባር እንድትወልዳት ግን ውብ እና ማራኪ አስመስሎ ያቀርብልሃል!
👉ይህን የክፋት ግብዣ መቀበል ያለመቀበል ያንተ ድርሻ ነው!
👉 ግብዣውን ተቀብለህ ጋባዡን ብቻ ለስህተትህ ማጋፈጥ ፍትሐዊ አይደለም!
+++ ግንቦት 24 +++
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::
+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::
+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 14,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::
+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::
+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::
+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::
+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::
=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?
1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)
2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)
4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::
6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
ከቴሌግራም ከዝክረ ቅዱሳን ገጽ
©gigar negusse
ድንግል ማርያም ሆይ❤️
👉የአርያም እኅት ሁለተኛዋ ሰማይ ሆይ ሕዝቅኤል ካየው ሰረገላ አንቺ ትበልጫለሽ።
👉 ዳንኤል ካየው ኪሩቤልም ኮሚሽከሙት ዙፋን አንቺ ትበልጫለሽ።
👉 የጉስቁልናዬ ሽታ የሚከረፋ እንዳይሆንም ራሴን በሃይማኖት ዘይት አለዝቢው።
👉በልጅሽ ፈውስም ዐይኖቼን ኳይ። በልጅሽ ደምም ከንፈሮቼን ቅቢ። በእርሱ ምልክትም ፊቴን ባርኪ። በወንጌሉ ልጓምነትም ጉንጮቼን /አፌን/ ለጉሚ።
👉 ትእዛዞቹን ለመስማትም የጆሮዬን መስኮቶች ክፈቺ። በመስቀሉ ቀንበርም አንገቴን ጥመጅው።
👉የኃጢአቴን ሸክምም ከትከሻዬ አስወግጂ።
👉በጀርባዬም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከምሪ። በሰውነቴም ማስተዋልን አሳድሪ። እጆቼንም በንጽሕና ውኃ እጠቢ።
ቅዱስ ዳዊት ታላቅና ገናና የከበረ ንጉሥ ከመሆኑ የተነሣ መንግሥቱ የመሢሕ መንግሥት ምሳሌ ሆኗል፤ መሢሑም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ስም ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል። (ኢሳ 9፡7፣ ኤር 23፡5-6፣ ኤር 33፡14-17፣ ሕዝ 34፡23፣ ሆሴዕ 3፡5) በሐዲስ ኪዳንም ወንጌላዊያኑ ጌታችንን ‹‹የዳዊት ልጅ›› በማለት ነው መጀመሪያ ነገረ ልደቱን ማውሳት የጀመሩት፡፡ ማቴ 1፡1፡፡ ራሱ ጌታችንም ‹‹እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ›› ብሏል፡፡ ራእ 22፡16፡፡
ቅዱስ ዳዊት 7 ሀብታት የተሰጡት ጻድቅ አባት ነው፡፡ እነዚህም የተሰጡት ሀብታት፡- ሀብተ ክህነት፣ ሀብተ መንግሥት፣ ሀብተ መዊዕ (የማሸነፍ ሀብት)፣ ሀብተ ትንቢት፣ ሀብተ ኃይል፣ ሀብተ በገና (ዝማሬ) እና ሀብተ ፈውስ ናቸው። ቅዱስ ዳዊት 24 ሰዓት ሙሉ የእግዚአብሔር ምስጋና እንዳይቋረጥ መዘምራንን መድቦ እንዲያገለግሉ ያደርግ ነበር፡፡ ራሱም 10 አውታር ባለው በገና ሌት ተቀን በፍጹም ተመስጦ ያመሰግን ነበር፡፡ በመዝሙሩም አጋንንትን ያቃጥል ነበር፡፡ መዝሙረ ዳዊት በውስጡ የያዘው ሚሥጢር እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ አባቶቻችን ዛሬም በዱር በጫካ ሆነው መዝሙረ ዳዊትን አብዝተው ይደግማሉ፡፡ እንኳንስ የሰው ልጅ ይቅርና ‹‹መዝሙረ ዳዊትን›› ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም እግዚአብሔርን ለማመስገኛነት ተጠቅመውበታል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እድሜ ዘመኑን እግዚአብሔርን በማገልገልና በመፍራት ኖሮ በታኅሣሥ 23 ቀን በሰላም ዐርፎ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል፡፡ የቅዱስ ዳዊት ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
🌹#ነብዮ_ቅዱስ ዳዊት🌹
📌•••ወር በገባ በ23 የልብ አምላክ የነብዮ ንጉሠ እስራኤል ቅዱስ ዳዊት፡- ወርኃዊ መታሰብያው ነው #ዳዊት ማለት ‹‹ኅሩይ›› ማለት ነው። አንድም ‹‹ልበ አምላክ›› ማለት ነው። ሐዋ 13፡22፡፡ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ነው። አባቱ እሴይ እናቱ ሁብሊ ይባላሉ። ሁብሊ መልከ መልካም ሴት ነበረች። ከጎረቤታቸው ያለ ጎልማሳ መልኳን እያየ በሐጸ ዝሙት ተነደፈ። እሴይ የእሷም ፈቃድ እንደሆነ አውቆ መንገድ እሄዳለሁ ብሎ ስንቁን ይዞ ወጣ። የሄደ መስሎ ከዚያው ውሎ ሲመሽ በልብሱ ተሸፋፍኖ ድምጹን ለውጦ ያንን ሰው መስሎ ገብቶ ከእርሷ ጋር አድሮ ጎህ ሳይቀድ ወጥቶ ሄደ። ዳዊት በዚህ ዕለት ተጸንሷል። “እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝ 50፡5) ማለቱ ስለዚህ ነው። ቅዱሱም ተወልዶ ጉልበቱ ከጸና በኋላ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አድጓል።
ንጉሥ ሳኦል ከጌታ ፈቃድ በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሳሙኤልን ቅብዐ መንግስሥት እንዲቀባው አደረገ። 1ኛ ሳሙ 16፡1-13፡፡ ከዚህ በኋላ በረድኤተ እግዚአብሔር ጎልያድን በአንድ ጠጠር ገደለ። ግዳይ ጥሎ ሲመለስ ሴቶች “ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ” እያሉ እየዘፈኑ ተቀበሉት። ቅንዐት አድሮበት ነገር ግን አስቀድሞ ምሎለት ነበርና የመቶ ፍልስጤማውያንን ሸለፈት ተቀብሎ ልጁ ሜልኮልን ዳረለት። አንድ ቀን ሊገድሉት ሲማከሩ ሜልኮል ሰምታ ሽሽ አለችው። ሳዖልም ሶስት ሺህ ሠራዊት ይዞ ተከተለው፡፡ ከሠራዊቱ ተለይቶ ሰውነቱን ለመፈተሽ ዳዊት ካለበት ዋሻ ውስጥ ገባ። ጨለማ ነበርና ሰው መኖሩን አላወቀም። አቢሳ ዳዊትን ጠላትህን አሳልፎ ሰጥቶሀልና ልውደቅበት አለ። ተው ኦሪት ‹‹በእግዚአብሔር መሢሕ ላይ እጅህን አታንሳ›› ትላለችና አይሆንም አለው። እርሱ የልብሱን ዘርፍ በሰይፉ ቀዶ ያዘ። ሲወጣ ተከትሎ ወጥቶ “ንጉሥ ሆይ ዳዊት ቢያገኝህ አይምርህም የሚሉህን ለምን ትሰማለህ እነሆ ዛሬ አሳልፎ ሰጥቶኝ ነበር። ነገር ግን የልብስህን ዘርፍ ከመቅደዴ በቀር ምንም ምን እንዳላደረግሁህ አንተ ታውቃለህ” ብሎ ቅዳጁን አሳየው። ሳኦልም ድምጹን ከፍ አድርጎ በማልቀስ ‹‹ልጄ ዳዊት ሆይ! እኔ ክፉ በመለስሁልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግህልኝ አንተ ዛሬ አሳየኸኝ። ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ። አሁንም እነሆ! አንተ በእርግጥ ንጉሥ እንድትሆን የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ እንድትጸና እኔ ዐአውቃለሁ›› አለው፡፡ 1ኛ ሳሙ ም 24፡፡ ከዚህም በኋላ ዳዊት በነገሠ ጊዜ ለልጆቹ እንዲራራላቸው ሳኦል ቃል አስገብቶት ወደ ቤተ መንግሥቱ መለሰው። ዳዊት ግን በረሀ በረሀውን ሲዞር ቆይቷል።
በሐቅለ-ፋራን ሳለ ናባል የሚባል ባለጸጋ ድግስ ደግሶ በጎቹን አሸልቶ ሲያበላ ሲያጠጣ ብላቶኖቹ “ምሳ ላክልኝ ብለህ ላክበት” አሉት። “ተው አይሆንም ያለ እንደሆነ እጣላዋለሁ” አለችው። “ይህን ያህል ጊዜ አንዲት ጠቦት እንኳ ሳትነካ ከብቶቹን ጠብቀህለት እምቢ ይላልን ላክበት ግድ የለህም አሉት።” እንኪያስ ሔዳችሁ ንገሩት አለ። ሄደው ቢነግሩት “የማነው ዳዊት” ብሎ አልሰጥም አለ። ዳዊት ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ ሊጣላው ተነሳ። ሚስቱ አቤግያ ይህን ሰምታ 5 በግ አሳርዳ አሠርታ፣ 5ቱን አሰናድታ የበለስ የወይን ጥፍጥፍ 500 እንጀራ፣ 12 ጭነት ዱቄት አሲዛ ሄደች። ዳዊት ከመንገድ አገኛትና “ባልሽን ልታድኚው መጣሽን?” ብሎ ያመጣችውን ተቀብሏት ተመለሰ። ናባል ማታ ሰክሮ ነበርና አቤግያ ሳትነግረው አደረች። ሲነጋ ትናንት ዳዊት ሊጣላህ መጥቶ ነበር አለችው። ዳዊት ብሎ ደነገጠ። ልቡን አጥቶ ሰንብቶ በ10ኛው ቀን መልአኩ ቀስፎታል። እመቤታችንና ጌታችን ከአብራኳ አሉና እሷን ግን ኀዘኗን ከጨረሰች በኋላ ዳዊት ሚስት አድርጓታል። 1ኛ ሳሙ ም25፡፡
ከዚህ በኋላ ሳኦል ፍልስጤማውያን በጠላትነት ተነሱበትና ገጠማቸው። ከጠላቶቹ አንዱ ቀስቱን መርዝ ቀብቶ ጎኑን መታውና እንደ እሳት አቃጠለው። ሎሌውን ጠርቶ ገደልነው እንዳይሉ አንተ ጨርሰኝ” አለው። “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ባሪያህ ካንተ ጋር እሞታለሁ እንጂ እገድልሃለውን?” ብሎ እምቢ አለው። የገዛ ሠይፉን ከምድር ተክሎ ወደቀበት። ሌሎቹም እርሱን አይተው በገዛ ሠይፋቸው እየተወጉ ሞቱ። ዳዊት የርሱንና የልጁ የዮናታንን ሞት ሲሰማ አዘነ። ግጥም እየገጠመ አለቀሰላቸው። ከሳዖል ሞት በኋላ ዳዊት መንግሥቱን አጽንቶ ጽዮንን አቅንቶ ተቀመጠ። ታቦተ ጽዮንንም በዕልልታ በሆታ ወደከተማው አስገባ። የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን በታቦተ ጽዮን ፊት ሲዘምር አይታ በልቧ ናቀችው። ሲገባ ልትቀበለው ወጥታ “የእስራኤል ንጉሥ በባሪያዎቹ ቆነጃጅት ፊት ዕርቃኑን በመግለጹ ምን ይከብር?” ብላ በአሽሙር ዘለፈችው። በዚህ ቢያዝንባት መካን ሆና ሞታለች። “ሜልኮል እስከምትሞት ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር” እንዲል። 2ኛ ሳሙ ም6፡፡
በዘመኑ የነበረው ነቢይ ቅዱስ ናታን ነው። እርሱም ሊጠይቀው መጥቶ ሳለ አዝኖ አየው። “ምን ሆነህ ታዝናለህ?” አለው። ቅዱስ ዳዊትም “እኔ በጽድ በዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬ ታቦተ ጽዮን በድንኳን ስትኖር ምነው አላዝን?” አለ። “ጠላት ጠፍቶልሀል፤ መንግሥትህም ጸንቶልሀል አታንጽምን?” አለው። “ያስ ቢሆን ያለፈቃደ እግዚአብሔር ይሆናልን?” አለ። ከዚህም በኋላ ሁለቱም ቀኖና ገቡ። የቤተ መቅደስ ነገር ለናታን ተገልጾለት “አንተ አይደለህም የምትሠራልኝ ከአብራክህ የተከፈለ ልጅህ ይሠራልኛል” ብሎታል። 2ኛ ሳሙ 7፡1-17፡፡ ለቅዱስ ዳዊት ግን የበለጠ የሥጋዌ ነገር ተገልጾለት “እነሆ በኤፍራታ ሰማነው” ብሏል። መዝ 131፡6፡፡
ኢዮአብና አቢሳ ጠላት ለመመለስ ታቦተ ጽዮንን አሲዘው ሠራዊት አስከትለው ወደ አራቦት ዘመቱ። ቅዱስ ዳዊት ግን ከከተማ ቀርቶ ነበር። በሰገነቱ ሲመላለስ ቤርሳቤህን በአፀደ ወይን ውስጥ ስትተጣጠብ አይቷት ፍቅረ ዝሙት አደረበት። “የማን ሚስት ናት?” አለ። “የኦርዮን” አሉት። ኦርዮን ዘምቶ ነበር። “የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ” (ዘጸ 20፡14-17) ያለውን ተላልፎ አስጠርቶ ደረሰባትና ጸነሰች። ጽንስ ያሳስትልኛል ብሎ እቦ ኦርዮንን አስጠርቶ ስለጦሩ ሁኔታ ከጠየቀው በኋላ “ወደቤትህ ሂድ” አለው። ኦርዮን ግን ድንኳን አስተክሎ ከዘበኞቹ ጋር አደረ። “አልመጣም” ብሎ ላከችበት። ዳግመኛም የሚያሰክር መጠጥ አጠጥቶ “ወደቤትህ ግባ” አለው። “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ታቦተ ጽዮን ተማርካ እስራኤላውያንም ዋዕየ ፀሐዩን ቁረ ሌሊቱን ታግሠው በሜዳ ሲሆኑ እኔ ቤቴ ገብቼ ተድላ ደስታ አደርግ ዘንድ ይገባልን?” ብሎ እምቢ አለ። በማግሥቱ “ኦርዮንን ፊት መሪ አድርጉት ጦሩ ሲበረታ ትታችሁት ሽሹ እሱ በዚያ ይሙት” የሚል ጽፎ አትሞ “ለኢዮአብ ስጠው” ብሎ ሰጠው። የዋህ ነውና የሞቱን ደብዳቤ ይዞ ሄዶ ሰጠው። ኢዮአብ እንደታዘዘው ኦርዮን ከፊት አሳልፈው ጦሩ ሲበረታ ተጠቃቅሰው ወደኋላ ሸሹ። እርሱ መለስ ብሎ “ምን ሆናችሁ?” ቢላቸው ጠላቶቹ ደርሰው ልብ ራሱን ብለው ገድለውታል።
ግንቦት 22/2016 #ቅዱስ_ዑራኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው
👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ (ዕዝ ሱቱኤል13፥39)
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው (ድርሳነ ዑራኤል ገጽ 26 ምዕ 4)
👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን "አሜን" ✝️ ⛪️ ✝️
ግንቦት 21/2016 #እናታችን_ማርያም_በደብረ_ምጥማቅ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት አመታዊ ክብረ በአል ነዉ
👉ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ
👉እርሷም በልጅዋ #የመለኮት_ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው #ለንግሥቷ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ
👉ሁለተኛ #ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል
👉ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ #መርቆሬዎስ ነው ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል ሁለተኛም ደግሞ ፃድቃን በአንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ
👉 #ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር
👉እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ #ቅድስት_ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳይኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል
👉እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ #ክርስቲያንም_እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ
👉ለአባቶቻችን የተለመነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ለኛም ትለመነን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን "አሜን"
👉#የዘርዐ_ያዕቆብ_እመቤት የፃድቃኔ ማርያም የቦታዋ በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
❗#ሚስጥረ_ላሴ ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴.1 ማን ፈጠረን?
መልስ 👉 ቅድስት ሥላሴ ።
🔵.2 ሥላሴ ስንት ናቸዉ?
መልስ 👉 አንድም ሶስትም ናቸዉ።
🔴.3 ሶስትነታቸዉ በምን በምን ነዉ?
መልስ 👉 በስም በአካል በግብር።
🔴.4 አንድነታቸዉስ በምንድነዉ?
መልስ 👉 በባህርይ በህልዉና በመለኮት በፈቃድ ሰዉን በመፍጠር አለምን በማሳለፍ በዘለአለማዊ ስልጣን!
🔵.5 የስም ሦስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ።
🔴.6 የአካል ሦስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ
👉ለአብ ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለወልድም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ።
🔵.7 የግብር ሦስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ነዉ።
🔴.8 አብ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 አባት።
🔵.9 ወልድ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 ልጅ።
🔴.10 መንፈስ ቅዱስ ማለትስ?
መልስ 👉 ሰራፂ
🔵.11 ከማን የሰረፀ?
መልስ 👉 አብን አክሎ ወልድን መስሎ ከአብ የተገኘ ወይም የሰረፀ።
❗ሚስጥረ_ሥላሴ አይመረመርም ጥልቅና ሰፊ ነዉ ከረጅሙ በአጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ከመለኮታዊ ስፋቱ የገለፀልን የአቦቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን አሜን❗
🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
#ግንቦት_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የማርያና የማርታ ወንድም #ጻድቅ_አልዓዛር አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ዮሐንስ
ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ደግ የተማረም ነበር። ከልጅነቱም ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ነበር። ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። የትሩፋቱና የዕውቀቱም ዜና በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ እግዚአብሔርም በዘመኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን አጸና።
ይህ አባት በተሾመበት ወራት ደግ ምእመን አንስጣስዮስ የሚባል ንጉሥ ነበር። በአንጾኪያም የከበረ አባት አባ ሳዊሮስ ነበረ እርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲህ ብሎ በመልእክቱ ውስጥ ጻፈ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶው በኋላ እንደ አባቶቻችን እንደ አባ ድሜጥሮስና እንደ አባ ዲዮስቆሮስ እምነት ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ ያለ መለያየትና ያለ መጨመር አንዲት ባሕርይ አለችው።
አባ ዮሐንስም መልእክቱን ተቀበለው ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ተለያይተው የነበሩ ሕዋሳትም ተመልሰው አንድ ስለ ሆኑ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት።
ከዚህም በኋላ ለመልእክቱ መልስ አባ ዮሐንስ ለአባ ሳዊሮስ እንዲህ ብሎ ጻፈለት። ይኸውም ስለ መለኮትና ትስብእት የአንድ ባሕርይ ህልውና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ያለ መለያየት ያለ መቀላቀልና ያለ መለወጥ ሁለት ያይደለ የሰውን ባሕርይ ከመለኮቱ ባሕርይ ጋራ አንድ አድርጎ በመዋሐድ ሰው ስለ መሆኑ።
ጌታችንንም የሚከፋፍሉትን ወይም ተጨመረበት የሚሉትን ወይም ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚሉትን በመለኮቱ ባሕርይ መከራ ተቀበለ የሚሉትን አወ**ገዘ። የቀናች ሃይማኖትስ ይቺ ናት እግዚአብሔር ከእኛ በነሣው ሥጋ ስለ እኛ መከራ እንደ ተቀበለ እናውቃለን እኮን። ይቺም የሚጓዝባት የማይሳሳትባትና የማይደናቀፍባት የሕይወት መንገድ ናት አለ።
አባ ሳዊሮስም ይቺን የአባ ዮሐንስን መልእክት በአነበባት ጊዜ በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በአንጾኪያ አገርም ሰበከባት ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመካከላቸው ሰላም ፍቅርና ስምምነት ሆነ። ይህም አባት ሕዝቡን እያስተማረ ዐሥራ አንድ ዓመት ኑሮ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቅ_አልዓዛር
በዚችም ዕለት የማርያና የማርታ ወንድም ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኃኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ።
አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ በሰላም በፍቅር አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
ከሞት መኃል ነጥቀሽ
ነፍስን ዘራሽብኝ
ሀጢአተኛ ሳለው
ሰው አርገሽ አቆምሽኝ
ሀዘን መከራየ
ታሪክ ሁኖ ቀረ
ኑሮየ በሙሉ
በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝
+✝" አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ "✝+
=>እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
+ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
+ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::
+ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::
+የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
+ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
*በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
*በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም::
+በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ:
2.ስለ ምናኔሕ:
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ:
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ:
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ:
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ:
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
+"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
+ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}
=>አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ❤️ እንዲህ ያስተምረናል።
👉ማር ያልቀመሰውን የማርን ጣፋጭነት በቃላት መግለጽ እንደማይቻል
👉 እኛም ራሳችን ወደ ጌታ ቸርነት በኛ ቸርነት ዘልቆ መግባት ካልቻልን
👉 የእግዚአብሄርን ቸርነት በማስተማር መንገድ በግልፅ መግለጽ አይቻልም። የራሱን ልምድ.
ቅዱስ ሰሎዋን ዘ አቶናዊ ❤️ ደግሞ እንዲህ ያስተምረናል።
👉ብዙ ባለጠጎች እና ኃያላን ሰዎች ጌታን ወይም እጅግ ንፁህ እናቱን ለማየት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፣
👉 ነገር ግን እግዚአብሔር በሀብት አይገለጥም፣
👉ነገር ግን በትሑት ልብ... እያንዳንዱ ድሀ ሰው ትሑት መሆን እና እግዚአብሔርን ማወቅ ይችላል።
👉 እግዚአብሔርን ለማወቅ ገንዘብም ሆነ ስም አያስፈልገውም ነገር ግን ትህትና ብቻ ነው።
👉 የቱንም ያህል ብንማር እንደ ትእዛዙ እስካልኖርን ድረስ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም፤
👉 እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በሳይንስ አያውቅም።
👉 ብዙ ፈላስፎች እና የተማሩ ሰዎች አምላክ መኖሩን ወደ ማመን መጡ, ነገር ግን እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር.
👉እግዚአብሔር እንዳለ ማመን እና እሱን ማወቅ ሌላ ነገር ነው።
👉 አንድ ሰው እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ ካወቀ፣ ነፍሱ ቀንና ሌሊት ለእግዚአብሔር ባለው ፍቅር ትቃጠላለች፣
👉ነፍሱም ከማንኛውም ምድራዊ ነገር ጋር ልትታሰር አትችልም።
ፈጣሪ እግዚአብሔር ❤️ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
https://youtube.com/channel/UCAe0Vv9bIkCTTkeilxcUoYQ
እባካችሁን አሁን online ያላቹህ ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉልን
ግንቦት 24/9/2016 #ጌታችን_ከእናቱ_ጋር_ስደት
#ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ግንቦት 24 በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም_ከዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብፅ ምድር ተጓዘ
👉ግንቦት ሃያ አራት በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር ወንጌላዊ እንዳለ #የእግዚአብሔር_መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ምድር ሽሽ ተመለስ ብዬ እስከምነግርህም በዚያው ኑር
👉የጌታችንም ወደ ግብፅ መምጣት ሰለ ሁለት ሥራዎች ነው አንዱ ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንደአይችል ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ ሁለተኛው የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ፀጋውን እንዲያገኙ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት እነሆ #አግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ
👉የክብር ባለቤት #ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ በመጀመሪያም የደረሱበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል አልተቀበሏቸውም በዚያም የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች
👉ከዚያም በገምኑዲ መንገድ ተጉዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ የክብር ባለቤት #ጌታችንም_ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረከዝ ቅርጽ ተባለ
👉ጌታችንም እመቤታችን #ድንግል_ማርያምን እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ ስሙም ደብረ #ምጥማቅ ይባላል አላት
👉ከዚያም ወደ ፀሐይ መግቢያ ወዳለ ባሕር ሔዱ የአስቄጥስንም በረሀ ዱር ከሩቅ አዩ ጌታም በላዩ ባረከ እናቱንም #እናቴ_ማርያም ሆይ በዚህ ዱር ውስጥ ብዙዎች ሰዎች መነኰሳትን ሁነው በገድልም ተፀምደው በመላእክት አምሳል ያገለግሉኛል
👉ከዚያም በፀሐይ መውጫ በኲል ወደአለ ተራራ ሔዱ #ዮሴፍም የሚመረኰዘው በትር በእጁ ነበር ጌታችንም ይህ ቦታ የሚያቃጥል በረሀ ነውና እንቀመጥ አለ
👉 #ጌታችንም የዮሴፍን በትር አንሥቶ ሰበራት ጥቃቅን ስብርባሪዎች አድርጎ በዚያ ቦታ ተከላቸው በከበሩ እጆቹ ጉድጓድ ማሰ መዓዛው #የሚጣፍጥ_ውኃ ፈልቆ ፈሰሰ ከእዚያ ውኃም በመሐል እጁ እየዘገነ የተከላቸውን ስብርባሪዎች አጠጣቸው
👉ወዲያውኑ በቀሉ አድገውም ታላላቅ ዛፎች ሆኑ ከእርሳቸውም ጣፋጭ ሽታ ሸተተ እርሱም ከሽቱዎች ሁሉ እጅግ የሚጣፍጥ ነው በለሳንም ብሎ ጠራቸው እናቱን ድንግል እመቤታችንንም እናቴ ሆይ ይህ የተከልኩት በለሳን እስከ ዓለም ፍጻሜ ከዚህ ይኖራል #የክርስትና_ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሚጠመቁ ከእርሱ ቅባት ይገኛል አላት የዚያም ስም መጠሪያ ነው
👉ከዚያም #ብህንሳ ወደሚባል አገር ሔዱ ትርጓሜው ቤተ ኢየሱስ ወደሚባልም ቦታ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስም በሽታውን ደዌውን ሁሉ የሚፈውስ የጒድጓድ ውኃ አደረገ
👉ሁለተኛም በአንዲት የጕድጓድ ውኃ ምልክትን በየዓመቱ አደረገ ይኸውም ከቀኑ እኲሌታ በማዕጠንትና በጸሎት ጊዜ #ለእግዚአብሔር በዚያች የውኃ ጕድጓድ ዕጣንን ሲያሳርጉ የከበረ የወንጌል ንባብም ሲፈጸም በዚያች ጉድጓድ ውስጥ ያለ ውኃ ወደ ላይ ወጥቶ እስከ ጉድጓዱ አፍ ይደርሳል
👉ከእርሱም ይባረካሉ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ወደ ቦታው ይመለሳል ውኃው ከነበረበት እስከ ደረሰበት ይሰፍሩታል ሃያ ክንድ የሆነ እንደሆነ #የጥጋብ_ዘመን ይሆናል ዐሥራ ሰባት ክንድ ከሆነ ግን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ይሆናል
👉ከዚያም ወደ #እስሙናይን አገር ሔዱ በዚያ ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ እነርሱም ስሙ አፍሎን ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጡ በዚያም የእንጨት ዛፎች አሉ ለጌታችንም ሰገዱ እስከ ዛሬም እንደ ሰገዱ ናቸው ከዚያም ወደ #ደብረ_ቍስቋም ሔደው በውስጧ ስድስት ወር ተቀመጡ በዚያም በሽታን ሁሉ የሚያድን የጉድጓድ ውኃ አደረገ
👉ጌታችንም የፈቀደውን በግብጽ የሚኖርበት ወራት በፈጸመ ጊዜ ይኸውም ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው ኄሮድስም ከሞተ በኋላ #ከእግዚአብሔር_የታዘዘ_መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ተመለስ አለው
👉ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ #የቅዱስ_ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች
👉ከዚያም ጌታችን የተከለው #የክርስትና_ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው
👉በጌታችን መመለስም ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ያለው የኦዝያን ትንቢት ተፈጸመ ስለዚህም #ተአምራትን_በግብጽ ድንቅ ሥራንም #በጣኔዎስ_በረሀ ያደረገ በማለት እየዘመርን በዚች ዕለት መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ስለ እኛ ለተሰደደ #ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ምሕረቱ ለዘለዓለም ይሁንልን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ አባታችን #ተክለሃይማኖት እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ፀሎት ልመናቸዉ ለዘለዓለም ይጠብቀን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
نات کوین رایگان میخوای این رباتو از دست نده😍💪
با استارت این ربات 100k نات کوین رایگان دریافت کن
/channel/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId472409434
እግዚአብሔርም ለነቢዩ ናታን ተገለጸለት። ናታን ከል ለብሶ ከል ጠምጥሞ ጦር ይዞ ሄደ። ዳዊት “ነቢየ እግዚአብሔር አመጣጥህ በደኅና ነውን?” አለው። “የምነግርህ አለኝ” አለው። “መቶ በጎች ያሉት ሰው ነበር። ከአንዲት በግ ሌላ ምንም ምን የሌለው ጎረቤት ነበረው። መንገድ ሲሄድ አደራ ሰጥቶት ሄደ፡፡ ያ ሰው እንግዳ ቢመጣበት መቶ በጎቹን አስቀምጦ የእርሱን አንዲት በግ አርዶ እንግዳውን ሸኘበት። እርሱንም ለሰው እንዳይነግርብኝ ብሎ ገደለው። በዚህ እግዚአብሔር አዝኗል” አለው። ዳዊትም ይህን ጊዜ “ይህን የሚያደርግ በከተማዬ ካለ ሞት ይገባዋል” አለ። ነቢዩም ወዲያው “ንጉሥ ሆይ! ይህን ሁሉ ያደረግህ አንተ ነህ፣ በራስህ ፈረድህ ባለጸጋ የተባልህ አንተ ደኃ የተባለ ኦርዮን ነው። መቶ በጎች የተባሉ አሥሩ ዕቁባቶችህ ናቸው። አንዲት በግ የተባለች ቤርሳቤህ ናት። እንግዳ የተባለ ፈቃደ ሥጋ ነው። ፈቃደ ሥጋህ ቢነሳብህ 10ሩ ዕቁባቶችህን አስቀምጠህ ከቤርሳቤህ ደረስህ። ኦርዮንንም አስገደልከው። በዚህ እግዚአብሔር አዝኗል” አለው። ይህንንም ሲሰማ ዳዊት ልዋል ልደር ሳይል ዕለቱን ጉድጓድ አስምሶ ማቅ ለብሶ ሱባኤ ይዞ ሌት ተቀን ተንስቅስቆ አለቀሰ፡፡ እግዚአብሔርም ጥንቱን መርጦታልና ጸሎቱን ሰማው። ነቢዩ ናታን ዳግመኛ መጥቶ “በነፍስህ ምሬሀለሁ ብሎሀል። በሥጋህ ግን ኃጢአት ያለፍዳ አይነጻምና ለሦስት ወር ልጅህ መንግሥትህን ይነጥቅሀል፤ ዕቁባቶችን ይቀማሀል” አለው። ዳዊትም “ይህ እንዲሆን በምን ዐውቃለሁ?” አለ። “የሚወለደው ሕፃን ይሞታል፣ እርሷን ግን አግባት ወንድ ልጅ ትወልድልሀለች ስሙን ሰሎሞን ትለዋለህ” አለው። ቀን ከሌት አብዝቶ ያለቅስ ነበርና ከዕንባው ብዛት የተነሣ መሬቱ እርሶ ሠርዶ አብቅሎ ሰውነቱን ተብትቦ ይዞት ነበር። ብላቴኖቹ ቆርጠው አወጡት።
ከዚህም በኋላ ሕፃኑ ተወልዶ ታመመ። “እኔን በነፍሴ እንደማረኝ ሕፃኑንም በሥጋው ይማረው” ብሎ ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ ያለቅስ ጀመር። ሕፃኑ ሞተ፤ ከወደቀበት ተነስቶ ተጣጥቦ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ ማዕድ ቀረበ። ከምሳ መልስ “ታመመ ስንልህ ማዘንህ ሞተ ስንልህ እንዲህ ማድረግህ ስለምንድር ነው?” አሉት። “ውኃ ከፈሰሰ ይታፈሳልን? እንዲሁ ወደርሱ እንሄዳለን እንጂ እርሱ ወደኛ አይመጣም” ብሏቸዋል። ጌታ የተናገረው አይቀርምና ቅዱስ ዳዊት ፍዳን ሊቀበል ሰይጣን የበኵር ልጁ አምኖንን በእኅቱ በትዕማር ፍቅር እንዲያድርበት አደረገ። ኢዮናዳብ የሚባል የአጎቱ ልጅ ሰውነቱ ከስቶ ፊቱ ገርጥቶ ቢያየው “አንተ የንጉሥ ልጅ ሆነህ ምን ያከሳሀል?” አለው። “ፈርቼ እንጂ እኅቴ ትዕማርን ወድጃታለሁ” አለው። “ታመምሁ ብለህ ተኛና አባትህ ሊጠይቅህ መጥቶ ልጄ ብላ ሲልህ በትዕማር እጅ ቢሆን ኖሮ ሁለት ሦስት እንጎቻ በበላሁ ነበር በለው ያዝልሀል” አለው። እርሱም እንደመከረው አደረገ፡፡ ዳዊትም ትዕማርን አስጠርቶ እንድታሰናዳለት አዘዛት። “እኅቴ አንቺን ብዬ እንጂ እህል የሚያቀርብልኝማ መቼ አጣሁ” ብሎ ያዛት። እርሷም “ወንድሜ ይህን አታድርገው እኔን የተናቀች የተጠላች ታደርገኛለህ፣ አንተም ከሰነፎች እንደ አንዱ ትቆጠራለህ” አለቸው። አምኖን ግን በግድ አስነወራት። ወዲያውም ፊት ከወደዳት መውደድ ይልቅ ኋላ የጠላት መጥላት በለጠና ‹‹ውጪልኝ›› አላት። “ከቀደመው የአሁኑ ክፋትህ ይከፋል ተወኝ” አለችው። ብላቴናውን ጠርቶ አስወጥቶ እንዲዘጋባት አደረገ። እርሷም የለበሰችውን ባለህብር ልብስ ቀዳ አመድ ነስንሳ እያለቀሰች ስትሄድ ወንድሟ አቤሴሎም አገኛት። ያስነወራት አምኖን መሆኑን ዐውቆ “ወንድምሽ ነውና አትግለጪበት” ብሎ አጽናንቶ ዳዊት በከተማ ያሠራው ቤት ነበርና ከዚያ አስቀመጣት።
ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም ድግስ ደግሶ ዳዊትን ጠራው። “አስቀድመህ ብትነግረኝ መልካም ነበረ አሁን ግን እኔ ስመጣ መኳንንቱ፣ መሳፍንቱ ወይዛዝርቱ ስለሚከተሉኝ ይበዛብሃል አይሆንም” አለው። “ያም ባይሆን ታላቅ ወንድሜ አምኖን ይገኝልኝ” አለ። እርሱም ‹‹ይሂድልህ›› አለው። ከዚህ በኋላ አምኖን በልቶ ሲጠግብ፤ ጠጥቶ ሲሰክር አቤሴሎም ብላቴኖቹን አዝዞ አስገደለውና እርሱ ወደናቱ ሀገር ጌድሶር ሸሸ። ዳዊት ለልጁ ለአምኖን አለቀሰለት። ከሁለት ዓመት በኋላ አምኖንን እየረሳ አቤሴሎምን እያስታወሰ ሄደ። ቢትወደዱ ኢዮአብ ይህን ዐውቆ አንዲት ቴቁሄያዊት ልኮ አስታረቀው። አቤሴሎም ከአባቱ ጋር ከታረቀ በኋላ በሠረገላ ሆኖ እስራኤልን “ምን ዳኛ አለና ይፈርድላችኋል? እኔማ ይህችን መንግሥት ጥቂት ጊዜ ባገኛት ቀን በፀሐይ ሌሊት በመብራት ፈርጄ ኢየሩሳሌምን አቀናት ነበር” ሲል ሰንብቶ ዳዊትን ለምኖ ሥርዓተ መንግሥት አስወጥቶ ሁለት መቶ መኳንንት ይዞ ‹‹አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ›› እያለ ነጋሪት አስጎሠመ። ዳዊት ይህን ሰምቶ “ኑ ከኢየሩሳሌም እንሽሽ” አለ። ኢዮአብና አቢሳ ግን ‹‹እንዋጋለን›› አሉት። ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ጌታ ልጅህ መንግሥትህን ይነጥቅሀል፣ እዋጋለሁ አትበል ብሎኛል አይሆንም›› ብሎ ተራ ልብስ ለብሶ ተራ ጫማ ተጫምቶ ከከተማው ወጥቶ ሦስት ወራት በጫካ ሲያዝን ኖሯል። ከሦስት ወር በኋላ አቤሴሎም ሲዋጋ ሞተ። ዳዊት ወደ ቤተ መንግሥቱ ቢመለስ ዓሥሩ ዕቁባቶቹን ልጁ አርክሷቸው ተገኘ። እርሱም እስከ ፍጻሜ ዘመኑ ሳይደርስባቸው ቀርቷል።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዳዊት ብዙ ጊዜ ቆይቶ “የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ›› ያለው ቃል ተፈጽሞለት ልጁ ሰሎሞንን በዙፋኑ አስቀምጦ በነገሠ በ40 ዘመኑ በሰላም ዐርፏል። 1ኛ ነገ 2፡12-14፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነሐሴ 13 ቀን ተጸነሰ፣ በሚያዝያ 6 ቀን በይሁዳ በቤተልሔም ሀገር ተወልደ። 1ኛ ሳሙ 16፡10-11፡፡ እረኛና ብላቴና የነበረ ቢሆንም የፍልስጤማውያኑን ኃያል ሰው ጎልያድን በ12 ዓመቱ 5 ጠጠርን ከወንዝ ለቅሞ በወንጭፍ ወርውሮ ገድሏል፡፡ 1ኛ ሳሙ 12፡45-51፡፡ ንጉሥ ሳዖል በጌልቦአ ተራራ በራሱ እጅ ከሞተ በኋላ አስቀድሞ በይሁዳ 7 ዓመት በመላው እስራኤል 33 ዓመት ነግሡዋል፡፡ 2ኛ ሳሙ 2፡4፤ 5፡1-5፡፡ ‹‹እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል” (1ኛ ሳሙ 13፡14) ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠና ነገረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ዳግም ምጽዓትን፣ ነገረ ማርያምን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ በስፋትና በጥልቀት የተናገረ የብሉይ ኪዳን ‹‹ወንጌላዊ›› የተባለ ቅዱስ ነቢይ ነው። “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ…” እያለ የጌታችንን መከራ መስቀል በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 21 (22)፡ 16-18፡፡
“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”፣ “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ…” እያለ የጌታችንን ዕርገቱንና ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል፡፡ መዝ 46(47)፡4-5፣ መዝ 49(50)፡ 1-5፡፡ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እያለ የእመቤታችንን ክብር አይቶ በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 44(45)፡9፡፡
ልብ አምላክ ዳዊት እንዲህ ይዘምራል ።
👉 አቤቱ፥ በቍጣኽ አትቅሠፈኝ ፥ በመዓትኽም አትገሥጸኝ።
👉ድውይ ነኝና አቤቱ ፥ ማረኝ፤ ዐጥንቶቼ ታውከዋልና ፥ ፈውሰኝ።
👉 ነፍሴም እጅግ ታወከች፤ አንተም ኣቤቱ ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው፧
👉 አቤቱ : ተመለስ ነፍሴንም አድናት ፥ ስለ ቸርነትኽም አድነኝ።
👉በሞት የሚያስብኽ የለምና ፥ በሲኦልም የሚያመሰግንኽ ማን ነው፧
👉 በጭንቀቴ ደክሜያለኹ፣ ሌሊቱን ዅሉ ዐልጋዬን ዐጥባለኹ ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለኹ።
👉 ዐይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ዅሉ የተነሣ አረጀኹ።
👉ዐመፃን የምታደርጉ ዅሉ ፥ ከእኔ ራቁ ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቷልና።
👉እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
👉ጠላቶቼ ዅሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቍሉ፤ ወደ ዃላቸው ይመለሱ ፥ በፍጥነትም
እግዚአብሔር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
ግንቦት 21/2016 #እናታችን_ማርያም_በደብረ_ምጥማቅ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት አመታዊ ክብረ በአል ነዉ
👉ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ
👉እርሷም በልጅዋ #የመለኮት_ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው #ለንግሥቷ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ
👉ሁለተኛ #ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል
👉ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ #መርቆሬዎስ ነው ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል ሁለተኛም ደግሞ ፃድቃን በአንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ
👉 #ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር
👉እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ #ቅድስት_ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳይኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል
👉እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ #ክርስቲያንም_እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ
👉ለአባቶቻችን የተለመነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ለኛም ትለመነን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን "አሜን"
👉#የዘርዐ_ያዕቆብ_እመቤት የፃድቃኔ ማርያም የቦታዋ በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️