kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1940

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ስለ ትጋት

👉 የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ትሆን ዘንድ በፈጣሪህ ታመን፤

👉 የጠላት ሰይጣን ወጥመድ ከአንተ ይቆረጥ ዘንድ ረኀብን አዘውትር፤

👉 ያለ ተግባር ነገር ከሚያበዛ ሰው ራቅ፤ እንደዚህ ያለውን ሰው ሥራውንም አትመነው፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት የተናቀ ነውና፡፡

👉ሕዋሳትህን ለእሳት አሳልፈህ እንዳትስጥበመከር ጊዜ አትተኛ፤ ባለፉት ኃጥኣን ላይ እንደ ጸና ፍትወት በአንተ ላይ እንዳይፀና የሰውነትህን ፍላጎት ገሥጸው ግራው።

👉ወይን ለሕሙማን ፈውስ እንደሆን እወቅ፤ ነገር ግን በተሠወረ ቦታ ዕርቃንህ እንዳይገለጥና እንዳታፍር ወይንን አትውደደው፡፡

👉ለሥጋህ ዕረፍትን አትስጠው፣ ሁል ጊዜ ኃጢኣት ከእርሱ ይወለዳልና፡ ፡

👉ጠላት መጥቶ ሀገርህን እንዳይዘርፍ መዛግብትህን እንዳይበረ በረብርህ ለሥጋህ.ዕረፍት የሚሆን በርን አትክፈት፡፡

👉ዕረፍትን ብትወድ ግን የሚረዳህ ረዳት አታገኝም ።

👉 ይልቁን ም የሚሰጥህ በሌለበት የሚያበድርም በታጣበት ጭንቅ ስዓት ስትደርስ የሚያሻህን እንዳታጣ ዘርህን በመልካሚቱ ምድር ላይ ዝራ፡፡

👉መብራትህን አብራ ማድጋህን በምሕረት ዘይት ሙላ፤ በብርሃናውያን መካከል ብርሃንህ እንዳይጠፋ፡፡

ርዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መልካም ሰው የሚሞተው

👉መልካም ሰው የሚሞተው ከክፉዎች ሞት ይወገድ ዘንድ ነው

👉ደጎች የሚሞቱት ወደ ሰማይ ( ጽድቅ) ሀገራቸው ይጠቀለሉ ዘንድ ነው ።

👉 አያችሁ እግዚአብሔር አምላክ
👉 አይደለም ህይወትን ሞትንም ሲመርጥ ደስተኝ ልንሆን ይገባል።

👉በእርግጥ የደጎች የመልካሞች ሞት ከባድ ነው

👉 ምክንያቱም የዚህች አለም ቁስል የሚቀንሰው እነዚህ ሰዎች ሲኖሩ ነው ።

👉እግዚአብሔር እራቅ እራቅ አድርጎ በጎ ሰዎችን ባያስቀምጥ ኑሮ
ምድራችን ትጨልም ነበረ።

👉ከባድ ነው የመልካም ሰው ሞት ግን አንዳንዴ እግዚአብሔር በፈቃዱ ሲዎስዳቸው እናያለን

👉ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ቢቆዩ የሚያዩትንና የሚሰሙትን መቋቋም ስለማይችሉ ነው።

👉ስለዚህ እግዚአብሔር ሥራየን እኔ እስራለሁ
ልጆቼን ግን አሳርፋለሁ ብሎ በጎዎችን የሚወስድበት ጊዜ አለ።

👉ሥለዚህ ፈቃዱ ገዥ ነው : ሀሳቡ ገዥ ነው ለፈቃዱ ህይወታችንን እንድንሰጥ እግዚኣብሔር ይርዳን።

መምህር ሳሙኤል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።

ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።

ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ኅልያን_ገዳማዊ

በዚህችም ቀን መስተጋድል አባ ኅልያን አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።

በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ አላት።

ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።

ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።

ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር።

የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።

ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።

ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይህንን ኃላፊ ዓለም ስለ መናቅና የሚመጣውን ዓለም ስለ መሻት

ራስን ስለ መሠዋት

👉የተወደድክ ወንድሜ ሆይ ይህቺን ዓለም መውደድ
-ልብን ታውካለች፤
- መንፈሳዊ ዓይንን ታጨልማለች ፤
-ከልዑል እግዚአብሔር ታርቃለችና ይህንን እወቅ፡፡


👉ወንድሜ ሆይ ፍቅረ ዓለምን ከአንተ ቆርጠህ ጣል፡፡

👉ለክፉ ምኞትህ ባርያ አትሁን፣ ሥጋን ለመብላት ወይንን ለመጠጣት አትሳሳ፡፡

👉በባሕርይህ ጾር ተቃጥለህ ድል እንዳትነሳና የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳትረሳ ለረኃብና ለጽምዕ ተገዛ እንጅ፡፡

👉 በጠላቶችህ እጅ እንዳትወድቅ በየጊዜውና በየሰዓቱ ወደ እርሱ ጸልይ፡፡

👉 ከስስትና ከንፍገት ራቅ፤ ሰማያዊ ዐይን ይገለጥልህ ዘንድ ለስማያዊ ነጽሮት ትበቃ ዘንድ ተጋድሎና ትጋትህን አስተውለህ ያዝ፡፡

👉ለኃጢኣትህ ሥርየትን ይሰጥህ ዘንድ በመኮንነ ጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እንባህን አፍስስ፡፡

👉 ከቅዱሳን ጋር ዘለዓለማዊ ዕረፍትን ገንዘብ ታደርግ ዘንድ በአጭር ዘመንህ ዕረፍትን አትውደድ።

👉ክፉዎች መናፍስት ከአንተ እንዲርቁ የምትሻ ከሆነ መዝሙራትን ከመጸለይ አትስነፍ፡፡

👉የጨለማው አበጋዞች ምሕረት የሌላቸው አጋንንት ከአንተ ይርቁ ዘንድ ለፈጠረህ እግዚአብሔር ጸልይ።

👉በአልአዛር ማዕድ እንድትቀመጥ ራስህን ድኻ አድርግ።

👉 ለአንተ ሲል ራሱን ለሠዋ አምላክ ራስህን ሠዋ በግርምት ዕለት ወደ ሰርጉ ጠርቶ ያደርስሃልና፡፡

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 9-አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ እራሳቸው ተዘቅዝቀው ባሕር ውስጥ መቆም የጀመሩበት እና ከዘጠኝ ዓመት በኃላ ጌታችን ተገልጦላቸው "ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ና ከባሕሩ ውስጥ ውጣ" በማለት ከባሕር ካወጣቸው በኋላ ለአባታችን ቃልኪዳኑን ያጸናበት ዕለት ነው፡፡
+ የአምስቱ አሕጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ የቆጵሮሱ ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ከታኦድሮስም ጋራ ሦስት ሴቶችና እርሱን ያሠቃዩት የነበሩት ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ በጌታችን አምነው መስክር ሆነው ዐረፉ፡፡
+ መሥተጋድል አባ ኅልያን ዕረፍቱ ነው፡፡
+ የግብፃዊው የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡
+ ከአባ ኤሲ ጋራ በሰማዕትነት ያረፉ 5504 ሰማዕታት መታሲቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት፡- ዲዮቅልጥያኖስ በካደና ጣዖታትን ባመለከ ጊዜ ምእመናንን ያስሩና ይገድሉ ዘንድ መኳንንቱን ሁሉ ወደ አገሮች ሁሉ ላከ፡፡ ስሙ ፍላጦስ የሚባል መኮንንም ወደ አፍራቅያ አገር ላከው፡፡ በዚያም ለክርስቲያኖስ ወገን መምህር የሆነውን ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ እርሱ አስጠርቶ ለጣዖታት እንዲሠዋ አዘዘው፡፡ ቅዱሱም ‹‹ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ለእውነተኛው አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የምሠዋው እንጂ በሰው እጅ ለተሠሩና ለረከሱ ጣዖታት አልገዛም›› አለው፡፡ መኮንኑም ይህንን ኃይለ ቃል ከቅዱስ ቴዎድሮስ አንደበት በሰማ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ለ40 ቀን በፍርፋትና በስቅላት፣ በእሥራትና በመንኮራኩር እንዲያሠቃዩት አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም ለ40 ቀን በእጅጉ ካሠቃዩት በኋላ በመጨረሻ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብርን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ ታኦድሮስ፡- ይኽንንም ቅዱስ ክርስቲያን በመሆኑ ይልቁንም የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ በመሆኑ ብቻ በመኳንንቶቹ በሉክያኖስና በድግናንዮስ ዘንድ ከሰሱት፡፡ መኳንንቱም ወደ እነርሱ አስቀርበው በመረመሩት ጊዜ ቅዱስ ታኦድሮስም በጌታችን ታመነ፡፡ እነርሱም እየደበደቡት ለጣዖት እንዲሠዋ ባስገደዱት ጊዜ ቅዱሱ ከወደቀበት እየተዳኸ ሄዶ ጣዖቱን ረገጠውና ከመንበሩ ላይ ገልብጦ ጣለው፡፡ መኳንንቶቹም የሚያመልኩትን ስላቃለለባቸው በዚህ ተቆጥተው ቅዱስ ታኦድሮስን በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ፣ ጨውና ኮምጣጤ ነክረው ፋቁት፡፡ እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበር፡፡ የሚናገርበትንም ምላሱን ቆረጡት፡፡ አንዲትም ሴት የተቆረጠች ምላሱን አንሥታ ሆዱ ላይ ቢያደርጋት በተአምራት ተዘርግታ አፉ ውስጥ ገባችና እንደቀድሞው ሆነች፡፡ አንዲት ነጭ ርግብ መጥታ በቅዱሱ ላይ ስትዞር ሌላም ሶሪት ወፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች፡፡ በዚህም ጊዜ መኮንኑ ሉክያኖስ በጌታችን አመነ፡፡
ድግናንዮስ ግን ተቆጥቶ ቅዱስ ታኦድሮስን ይከተሉት የነበሩትን ሦስት ሴቶች በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ ቅዱስ ታኦድሮስም ነፍሱን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ወፏ በርረው ሄዱ፡፡ ሉክዮስም ድግናንዮስን የክርስቲያኖች ሃይማኖት የቀናችና እውነትም እንደሆነች መከረው፡፡ እርሱም የተመለከታቸውን ተአምራት አስተውሎና የጓደኛውን ምክር ሰምቶ በጌታችን አመነ፡፡
ከዚህም በኋላ ሉክያኖስና ድግናንዮስ ከቆሮንቶስ አገር ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄዱ፡፡ በዚያም ሌላኛው መኮንን ክርስቲያኖችን ሲያሠቃይ ሉክያኖስ ከጓደኛው ተሠውሮ በመሄድ በመኮንኑ ፊት የጌታችንን ክብር በመመስከር የጣዖታቱን መንበር ገለበጠው፡፡ መኮንኑም ራሱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረውና እርሱም በተራው በመኮንኑ ፊት ቀርቦ ጣዖታቱን በመርገም የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ አሁንም ከሃዲው መኮንን የድግናንዮስን ራስ በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ የክብር አክሊልንም ተቀበለ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
መሥተጋድል አባ ኅልያን፡- የዚህም ቅዱስ አገሩ ዐይነ ፀሐይ ይባላል፡፡ አባቱ ዲስጣ እናቱ ካልሞና ይባላሉ፡፡ ኅልያንም በወጣትነት የተመሰገነ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለት ከዐረብ አገልጋዮች የሆነች ሴት መጥታ የጆሮ ጉትቻ ከሠራላት በኋላ ዋጋውን ቢጠይቃት ‹‹ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም›› አለችው፡፡ እርሱም ይህንን በሰማ ጊዜ ‹‹አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ›› ብሎ ገሠጻት፡፡ ከዚህም በኋላ የነፍሱን ድኅነት አስቦ ገንዘቡን ለእናቱ ሰጥቶ ራቅ ወዳለ ገዳም ይሄድ ዘንድ ተነሣ፡፡ እግዚአብሔርም መንገዱን አቅንቶለት ረጅሙን መንገድ አቅርቦለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻ በአንዲት ቀን ደረሰ፡፡
በዚያም ቆሞ ሳለ ነጭ ልብስ የለበሱና እንደፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኮዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለትና ከእነርሱ ጋራ ወሰዱት፡፡ ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት፡፡ በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ፡፡ ቅዱስ ኅልያንም ሰግዶ ቀና ሲል እነርሱን አጣቸው፡፡ በመለየቱም አዝኖ አለቀሰ፡፡ በዚያም በአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየተገመበ ልብሱም ቅጠል ሆኖ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ፡፡ ወደ ዋሻዎችም ለመሄድ ባሰበ ጊዜ የሰጡት በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር፡፡
ሰይጣንም መልካም ተጋድሎውን ስላየ ቀናበትና በፈተና ሊጥለው በማሰብ በሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ዘንድ ሄዶ ‹‹እዚህ ቦታ የተሠወረ ገንዘብ አለ፣ ጠባቂውም አባ ኅልያን ነው፣ እርሱን ከያዛችሁት ያለበትን ያሳያችኋል›› አላቸው፡፡ ሰዎቹንም እየመራ አመጣቸውና ከወንዝ ማዶ በደረሱ ጊዜ መሻገሪያ አጡ፡፡ ውኃም እጅግ ተጠምተው ነበርና ሰይጣንም ወደ አባ ኅልያን በመሄድ ‹‹ውኃ ተጠምተውና መሻገሪያ አጥተው ተቸግረው ሳለ ውኃ የማታጠጣቸው ለምንድነው? አለው፡፡ እርሱም ሲሄድ ሰዎቹ የሚይዙት መስሎት ነበር፡፡ አባ ኅልያን ሄዶ ውኃ ቀድቶ አጠጣቸው፡፡ እነርሱም ባዩት ጊዜ ምንም የሌለው ድኃ መሆኑን ዐውቀው ተውት፡፡ ሰይጣንም ተንኮሉ ስለከሸፈበትና ስላፈረ ዳግመኛ በደጋግ በሆኑ መነኮሴዎች ተመስሎ አባ ኅልያንን ሊያስተው ወደ በዓቱ ሄደ፡፡ ቅዱሱም በብርሃን መስቀሉ ባማተበ ጊዜ እንደትቢያ በነው ጠፉ፡፡
የአባ ኅልያንም የዕረፍቱ ሰዓት በቀረበ ጊዜ እነዚያ መጀመሪያ የተገለጡለት ሦስት ሰዎች ዳግመኛ ተገለጡለትና ገድሉን ጻፉለት፡፡ ቅዱሱ ባረፈም ጊዜ በክብር ቀበሩት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+++
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡- አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሐምሌ 8/2016 #ፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ
#ፃድቁ_አባ_ብሶይ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ ከምታስባቸዉ ቅዱሣኖች መካከል #ፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ እና #አባ_ብሶይ ለአመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያቸዉ እንኳን አደረሰን

👉የፃድቁን ስም የሚጠራ ክቡር ነው በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል #አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው

👉ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻህፍትንና ትህርምትን ተምረዋል ወንድማቸው #ታላቁ_ቴዎዶስዮስ በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው አሕጉር አቁዋርጠው ወደ ግብፅ #ገዳመ_አስቄጥስ መጡ

👉እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ የቅኖች ትውልድ ይባረካል እንዳለ ቅዱስ ዳዊት #አቡነ_ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል

👉 #ቅዱስ_በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው ለምን ጌታ ሆይ በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል

👉አንድ ቀን #ፃድቁ_ለቅዱስ_በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ ሱባዔ ገብተው ፍጹም አልቅሰው ከጌታም አማልደው የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብፅ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ

👉ፃድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው ሙታኑን አስነስተው ንስሃ ሰጥተው ገዳሙን የፃድቃን ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል #ፃድቁ_እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር

👉ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና በየቀኑ ይጐበኛቸው ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር

👉በመጨረሻም #ጌታ አእላፍ መላእክትን ፃድቃን ሰማዕታትን ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ

👉ቅዱስ ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው በበገናው እየደረደረላቸው ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች #ጌታችንም ታቅፎ ስሞ ይዟቸው አረገ

👉ሥጋቸውን አባ ባውማ ቀበሩት #የአቡነ_ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ ፅሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም

👉የፃድቁ አባታችን #ፀሎት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን"

👉እንዲሁም በዚህ እለት ከዋክብተ ገዳም ፃድቁ #አባ_ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸዉ ነዉ እንኳን አደረሰን

👉በረከት #በፃድቅ ራስ ላይ ነው የኃጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል #የፃድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው ምሳ.10፥7

👉እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና
👉ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና
👉ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል
👉ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ
👉በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ
👉የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል
👉አንደበቱም ፍርድን ይናገራል
👉የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው
👉በእርምጃውም አይሰናከልም መዝ.36 28-31

👉በዚህ እለት የሚታሰቡ #አባ_ብሶይ ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን ፀሎታቸዉ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtube.com/shorts/qtwxMWnVwW0?si=QxjlMp5XTG2ybSXk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"የአብርሃም በረከት..." (ገላ. 3፥14)
***
"ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤" (መዝ. 105፥9-11)
***
አብርሃም በእግዚአብሔር አምኖ በመታመኑ በእምነት ለሚገኝ ጽድቅ መታወቂያ ሆኖ እንደሚኖር ሐዋርያው ጳውሎስ ይናገራል። (ገላ. 3፥8)
በእምነት የሚሆን ጽድቅ ማለትም የትውልድ እና የራስ ክንውን ትምክህት የሌለበት (ፊል. 3፥4-6)፣ የእግዚአብሔርን ኃያልነት እና ቸርነት በማሰብ የሚኖሩት ጽድቅ ነው።
ይህ ጽድቅ በኋላ ሉተርና ተከታዮቹ ቅዱስ ጳውሎስን ሲተረጉሙ እንደሚሉት በእግዚአብሔር ሕግ ከመኖር እና መልካም ሥራ ከመሥራት ጋር የሚቃረን አይደለም። እርሱ በማያወላዳ ሁኔታ "እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ፤" ብሎ አስተምሯልና። (ሮሜ 3፥31) በዚህች ትምክህት እና ራስን ከሌሎች ልዩ አድርጎ የማየት ፈሪሳዊ ኃጢአት ባልነካት፣ ራሷን አንድያ ልጅን ለእግዚአብሔር በእምነት እስከመስጠት በደረሰች የአብርሃም ሕይወት በኩል ለአሕዛብ ሁሉ የምትተርፍ ተስፋ ተገኘች። ይህችውም " የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፤” የምትል ለዘላለም የጸናች የእግዚአብሔር ጽድቅ (ኪዳን) ናት። (ዘፍጥ. 12፥3)
የሐዋርያውን ልቡና በምሥጢር የገዛች ሌላም ለአብርሃም የተነገረች ተስፋ አለች፦ "በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና፤" የምትል። (ዘፍጥ. 21፥12) ሐዋርያው ይህን በሥጋ ከአብርሃም ስለተወለደው ስለ ክርስቶስ ይተረጉማል፤ እስራኤልን ከአሕዛብ የሚለየው ሕገ ኦሪት ጊዜያዊ እና በመልእክተኛ የተሰጠ መሆኑን አስታውሶ የሚቀድመውን የአብርሃም ተስፋ (ወንጌልን) ፍጻሜ አድርጎ ያቀርባል፦ “እንግዲህ ሕግ ምንድር ነው? ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ።” (ገላ. 3፥16-19) ለአብርሃም የተሰጠው ተስፋ ከኦሪት ሕግ የቀደመ እና እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሁሉ ያለልዩነት የሚጸድቁበት በመሆኑ ለአይሁድም ለአሕዛብም መዳን የጋራ መነሻ ያደርገዋል። ሥላሴን በቤቱ ያስተናገደው አብርሃም የተስፋ አባት ነው። የእግዚአብሔር ወዳጅ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ የትምህርቱ መሠረት ነው። ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ሥላሴን ያስተናገደበት በዓሉን ዛሬ ታከብርለታለች። በረከቱ ትድረሰን፤ እምነቱም ትደርብን። አሜን።
©በረከት አዝመራው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አደረሳችሁ
💐💒ሐምሌ 7- እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም እናምናለን አሜን አሜን አሜን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሐምሌ 7-ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጡለት፣ በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው፡፡ የይስሐቅንም መወለድ አበሠሩት፡፡
💐💒አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ከመጽሐፈ ሰዓታት ውጭ 12ሺ ድርሰቶችን የደረሰ ፈላስፋም ጻዲቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም ሲሆን ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ነው፡፡
💐💒 ንስጥሮስን አውግዘው ሃይማኖትን አጽንተው ሲመለሱ መርከበኞች ‹‹ሊቀ ጳጳሳቱ በሚሳፈሩበት መርከብ አትሳፈርም›› ብለው ቢከለክሏቸው ሊቀ ጳጳሳቱን እጅ ከነሡ በኋላ ብሩህ ደመና ጠቅሰው በደመና ተጭነው የሄዱት የባሕታውያን አለቃ መስተጋድል አባ ሲኖዳ ዕረፍታቸው ነው፡፡
💐💒 የዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀመዝሙር የነበረውና ጌታችን "እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ..." ብሎ በምሳሌ ያስተማረበት አቡነ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ዕረፍቱ ነው፡፡
💐💒 አባ መቃቢስ፣ አባ ጊዮርጊስና አባ አግራጥስ መታሰቢያ በዓላቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡

💐💒‎"ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ ዘፍጥረት 12:2."
💐💒 ቅድስት ሥላሴ💐💒
ሥላሴ የሚለው ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት ሦስትነት ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም /አንድነት ሦስትነት/ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሦስትነታቸው በስም በአካል በግብር፤ አንድነታቸው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ ነው፡፡

1. 💐💒የሥላሴ ሦስትነት

ሀ.💐💒 የስም ሦስትነት ፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ . . .›› ማቴ. 28፥19
ለ. 💐💒የአካል ሦስትነት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው፡፡ (ሃይማኖተ አበው) አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው፡፡ ገጽ ማለት ደግሞ ፊት ነው፡፡ መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለ ነው፡፡ አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ ነቢዩ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው፡፡›› መዝ. 33፥15 ‹‹እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም›› መዝ. 118፥73 ኢሳይያስም ‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፡- ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት ›› ብሏል ኢሳ. 66፥1 ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር ዘፍ.18፥1-4 ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ማቴ. 3፥16-17
ሐ.💐💒 የግብር ሦስትነት፡- የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡ አብ ቢወልድ ቢያሠርጽ እንጅ እንደ ወልድ አይወለድም እንደመንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ ወልድም ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ መንፈስ ቅዱስም ቢሠርጽ እንጅ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ ወልድ አይወለድም፡፡ አብን ወላዲ አሥራጺ ወልድን ተወላዲ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደሉም አንድ ናቸው፡፡ ጌታ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹እኔ እና አብ አንድ ነን›› ብሏል፡፡ ዮሐ. 10፥30 አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኢይልህቅ አብ እም ወልዱ ወልድኒ ኢይልህቅ እምመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢይንዕስ እምወልድ ወወልድኒ ኢይንዕስ እምአቡሁ›› ብሏል፡፡ ይህ ማለት ሦስት አምላክ ማለት አይደለም፡፡ አንድ አምላክ ይባላሉ አንጂ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም‹‹ወመለኮትሰ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› ብሏል፡፡

💐💒 ምሳሌም፡- ፀሐይ ክበብ ሙቀት ብርሃን፤ እሳትም ነበልባል ፍሕም ሙቀት አላቸው፡፡ ነገር ግን አንድ ፀሐይ አንድ እሳት ቢባሉ እንጅ ሦስት ፀሐይ ሦስት እሳት አይባሉም፡፡

እንዲሁ ሥላሴም በአካል በግብር በስም ሦስት ቢባሉም ቅሉ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡
2. 💐💒የሥላሴ አንድነት

ሥላሴ በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ አንድ ናቸው፡፡

የህልውና አንድነታቸው፡- በአብ ልቡናነት ወልድ መንፈስ ቅዱስም ያስባሉ፤ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስም ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ ወልድም ህልዋን ሆነው ይተነፍሳሉ፡፡ ‹‹አሐዱ ህላዌሆሙ ለሥላሴ እንዘ ይሄልው በበአካላቲሆሙ ወዕሩያን እሙንቱ በህልውና አብኒ ልቦሙ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድኒ ቃሎሙ ለአብ ወለመንፈስ ቅዱስ፣ ወመንፈስ ቅዱስ,ኒ እስትንፋሶሙ ለአብ ወለወልድ›› አንዲል ሃይማኖተ አበው

ቅድስት የሚል የሴት ቅጽል የተቀጸለላቸው ባሕርያቸው ታይቶ ነው፡፡

- 💐💒 ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንዲገኝ ይህም ዓለም ከሥላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና፤

- 💐💒 እናት ለልጇ የሚያሻውን አስባ እንድታቀርብለት ሥላሴም ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድመው ያዘጋጁለታል ይሰጡታልም፡፡ ማቴ. 6፥32

- 💐💒 አንድም እናት ልጇ ቢያስቀይማት ፈጽማ እንዳትጣላው ሥላሴም ሠርቀው አመንዝረው ቢበድሏቸው ንስሓ ገብተው ቀኖና ይዘው ቢለምኗቸው ይቅር ይላሉና፡፡ማቴ. 6፥14

💐💒 ሥላሴ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ካለመኖር ወደመኖር አምጥተው የፈጠሩ ሕማም ድካም የማይሰማቸው በሞት የማይለወጡ ገዥ ፈጣሪ ናቸው፡፡ ሥላሴ እንደዛሬ ሁሉ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ባሕርያቸው ባሕርያቸውን ሲያመሰግን ይኖር ነበር ኋላ ግን ሰውና መላእክትን ስማቸውን ለመቀደስ ክብራቸውን ለመውረስ ፈጠሩ፡፡ ሌላውን ግን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ፈጥረውታል፡፡

💐💒 የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳም እና ሔዋን በገነት 7 ዓመት ከ1ወር ከ17 ቀን በገነት ኖረው በዕፀ በለስ ምክንያት ከገነት ወጥተው በምድረ ኤልዳ ተቀመጡ፡፡ ኩፋ. 5፥6 ሥላሴም ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት›› ብለዋቸው ወልደው ተዋልደው በዙ፡፡ የእነሱ ዐሥረኛ ትውልድ ኖኅ ይባላል፡፡ በዘመኑ የሰው ልጆች ምድርን በኃጢአት አረከሷት፡፡ ሥላሴ ኖኅንና 7 ቤተሰቦቹን አስቀርተው ሌላውን የሰው ዘር በንፍር ውኃ አጠፉት፡፡ ዘፍ. 7 እና 8 ከዚህ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Eskahun guadegnochachu ehen group ayakutim kalwekut sheare argulachew /channel/chiffonhawassa

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሐምሌ_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን #የነቢዩ_ዕዝራ ዕርገት ሆነ፣ #ቅድስት_ንስተሮኒን አረፈች፣ ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት #ገድለኛዋ_ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፣ የገርአልታው #አቡነ_አብርሃም መታቢያቸው ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዕዝራ_ነቢይ

ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ እርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን የዕዝራ ዕርገት ሆነ። ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጽፍ ነበረ እርሱም ከሌዊ ወገን ነበረ። ከእግዚአብሔርም ጋራ ግሩም የሆነ ነገርን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ ምድርን በፈጠርካት ጊዜ አዳምን ታስገኝ ዘንድ አዘዝካት አስገኘችውም።

ሁለተኛው የጥፋት ውኃ በጊዜው እንደ መጣና ሁሉን እንዳጠፋ ተናገረ ኖኅ አብርሃምና ዳዊት እንዴት እንደ ተመረጡ ደግሞ ተናገረ። ዳግመኛም ነፍስ ከሥጋዋ እንደምትወጣና ሰባት ቀኖች እንደምትዞር ከዚያም በኋላ እንደ ሥራዋ ወደተዘጋጀላት ቦታዋ እንደምትገባ ተናገረ።

ከዚያም ስለ ፍርድ ቀን ተናገረ። ከእግዚአብሔር ከጌትነቱ ብርሃን በቀር ፀሐይና ጨረቃ መብራትና ብርሃንም እንደሌሉ ተናገረ። ዳግመኛም በልቧ እጅግ በምትጨነቅ በምታዝንና በምትተክዝ ሴት አምሳል ጽዮንን አያት ልብሶቿም የተቀደዱ ነበሩ ልጇም ወደ ጫጕላው ቤት በገባበት ቀን እንደሞተ ነገረችው። ከዚህም በኋላ እርሷን ከማየቱ የተነሣ ፈርቶ በድንጋፄ እስከ ወደቀ ድረስ ፊቷ በድንገት እንደ መብረቅ በራ።

ደግሞም ዐሥራ ሁለት ክንፎችና ሦስት ራሶች ያሉት ንስር ከባሕር ሲወጣ ከክንፎቹም ውስጥ ራሶች ሲወጡ አየ እኒህም በየዘመናቸው ገዝተው የጠፉ ነገሥታት ናቸው። ደግሞም ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መወለድ ተናገረ እንዲህም አለ። አንበሳ እያገሣ ከበረሀ ወጣ በሰው አንደበትም ሲናገር ንስሩንም ሲገሥጸው ሰማሁት አለ።

ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። በሌሊት ታላቅ ነፋስ ከባሕር ሲወጣ አየሁ ከማዕበሉ የተነሣ ባሕሩ ይታወክ ነበር ነፋሱም እንደ ሰው አምሳል ሁኖ ከባሕር ሲወጣ አየሁ። ደግሞም ከብዙ ኃይልና ክብር ጋር በሰማይ ደመና ማረጉን በአብ ቀኝ መቀመጡንም አይቶ ተናገረ።

ዳግመኛም በፈሳሹ ማዶ ያኖራቸው ዘጠኙ ነገድ እንደሚሰበሰቡ ተናገረ። ከዚህም በኋላ የነቢያት መጻሕፍትና የአባቶችን ትውልድ የያዙ መጻሕፍት ተደምስሰው መጥፋታቸውን በአሰበ ጊዜ ወደ በረሀ ገብቶ በጾምና በጸሎት ምሕላ ያዘ። ከእርሱም ጋር አምስት ጠቢባን ጸሐፊዎችን ወሰደ።

ከዕንጨቱም አንጻር ቃል ጠርቶት ዕዝራ አፍህን ክፈት ብሎ ኅብሩ እሳት የሚመስል ውኃን የተመላ ጽዋን ሰጠው። ያንንም ጽዋ ጠጣ ያን ጊዜም ልቡናው ጥበብን አገሣ። ተገልጾለትም መጻሕፍትን ሁሉ ሰበሰበ ለእነዚያም ሰዎች ልዑል አምላክ ዕውቀትን ሰጣቸው። መጻሕፍትንም ሁሉ በየተራቸው ጻፉ። በዚያም አርባ ቀን ኖሩ እነዚያ ግን ቀን ቀን ይጽፋሉ ማታ ማታም ይመገባሉ እርሱ ግን ቀን ይጽፋል ማታም ዝም አይልም በእነዚያ አርባ ቀኖችም ሁሉ መጻሕፍት ተጻፉ።

ከዚህም በኋላ ልዑል እንዲህ ሲል ተናገረው የዕውቀት ምሥጢር የጥበብም ምሥጢር እንደ ፈሳሽ ውኃም ያለ ዕውቀት ላላቸው ታስተምራቸው ዘንድ ይህን ተመልከት እንዳለውም አደረገ። በአራተኛውም ዘመን ከሚቈጠሩ ከብዙ ሱባዔ በአምስተኛው ሱባዔ ይህ ዓለም ከተፈጠረ ከአምስት ሺ ዘመን በኋላ ጨረቃ ሠርቅ አድርጋ ጨለማዋን ባጣች በአሥረኛው ቀን በሦስተኛው ወር በዘጠና አንድ እንደእርሱ ያሉ ደጋግ ሰዎች ወዳሉበት ዕዝራን ወሰዱት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ንስተሮኒን_ዘኢየሩሳሌም

በዚህችም ዕለት ቅድስት ንስተሮኒን አረፈች። እርሷም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ውስጥ ነበረች። እርሷም አስቀድማ ኃጢአተኛ ነበረች ከዚያም በኋላ ንስሓ ገብታ ወደ እግዚአብሔር በተቃጠለ ልብ ተመለሰች የሥጋን ፍላጐቶች ሁሉ ናቀች እመምኔት እስከ ሆነች ድረስ በበጎ ሥራ ሁሉ ትሩፋትንና ተጋድሎን አበዛች።

እኅቶችም ከገድል ብዛትና ምግብን ከመተው የተነሣ ሥጋዋ እንዳለቀ አይተው ሥጋሽን እንድትረጂ ጥቂት እህል በወጥ ብዪ አሏት። አብዝተውም ግድ ባሏት ጊዜ ልጆቼ ሆይ ወደ ቀድሞ ልማዴ እንዳልመለስ ጥቂት ወጥ ስለመብላት አትድከሙ ስለዚህ ወጥ አልበላም አለቻቸው። ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መርቄሎስ_ሐዋርያ

በዚህችም ዕለት ጳውሎስ የተባለ ቅዱስ መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ ነው። እርሱም ሐዋርያትን አገልግሎአቸዋል። ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር ሔደ። የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን መልእክቶች አደረሰ በመከራውም ጊዜ አገለገለው። ከእርሱም ጋር መከራ ተቀበለ ከእርሱም አልተለየም።

ወደ ሮሜ አገርም ከርሱ ጋር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን አስተማረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ከአረማውያን ብዙዎቹን መለሳቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው።

የሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ አቅርቦ ጠየቀው እርሱም ለሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ አመነ ደግሞም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ።

ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት። ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዴት ሁነህ መሞት ትሻለህ በምን አይነት ሞት ልግደልህ ንገረኝ አለው። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰ እኔ ሕይወት በሆነ በክርስቶስ ስም መሞት እሻለሁ አንተ ግን በፈለግኸው ዓይነት ግደለኝ ፈጥነህም ወደ ፈለግኸው አድርሰኝ።

ያን ጊዜም ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ቴዎዳስያ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት ገድለኛዋ ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፡፡ ከእርሷ ጋርም ሁለት መኳንንቶችና አሥራ ሁለት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።

ይህም እንዲህ ነው ይቺ ቅድስት ልጇ አብሮኮሮንዮስን ክርስቲያን ነው ብለው እንደወነጀሉትና ለሞት እስቲደርስ ጽኑዕ ሥቃይን እንዳሠቃዩት ሰማች። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያች ሌሊት ተገለጠለት ከሥቃዩም አዳነው ያለ ምንም ጉዳት ጤናማ ሆነ።

እኒህ ሁለቱ መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች ከእናቱ ጋር በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ እንዲህ ብለውም ጮኹ እኛ በአብሮኮሮንዮስ አምላክ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀበሉ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🎤ሐይማኖት ላለው በልቡ ላለው ለፀናለት ሰው ሁሉ ይቻላል።

👉ሐይማኖት ማነው ሲባል ባጭር ቃል
👉ሐይማኖት እግዚአብሔር ነው

🎤ሐይማኖት ላለው ሰው  ሁሉ ይቻላል  ማለት

👉እግዚአብሔር ❤️  ላለው ሰው ሁሉ ይቻላል ማለት ነው
👉በልቡ በሁለንተናው እግዚአብሔር ላለው  ሰው ሁሉ አለው

🎤በዚህ አለም ሁለት አይነት ሰዎች አሉ ይላል❤️  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

1ኛ ደሀ ናቸው ሀብታም የሆኑ ይመስላቸዋ
2ኛ  ሀብታም ናቸው ደሀ የሆኑ ይመስላቸዋል

ሁለት ሰዎች አሉ ለድሆችም ድህነታቸውን
ለባለፀጎችም ባለፀጋነታቸውን ልናስረዳቸው ይገባል ይላል ።

1ኛ ደሀ ሁነው ሀብታም የሆኑ የሚመሰላቸው የሚባሉት

👉ልብስ ለብሰው ከፀጋ እግዚአብሔር የተራቆቱ
👉ምግብ እየበሉ ነፍሳቸው የተራበች
👉ሰው እየገደሉ ነፍሳቸው ግን የደከመች
👉በዘመድ ብዛት የታጀቡ  ከሰራዊተ መላእክት እና ከቅዱሳን አንድነት የተለዩ
👉በልዩ ልዩ መንገድ የተዋቡ  ነፍሳቸው ግን ከቁራ የጠቆረች የጨለመች የከረፋች የከፋች
👉እንዲህ አይነት ሰዎች አሉ ያወቅን ይመስላቸዋል ግን አያውቁም
👉ለነዚህ ሰዎች አልቅሱላቸው

🎤ባማሩ በተሸለሙ በተጋረዱ ቤቶች ይኖራሉ።

👉በሰማይ ቤት ግን ስደተኞች ናቸው
👉እንደህ አይነት ሰዎች ፍፁም የተዋረዱ ናቸውና
👉 ድህነታቸውን ንገሩአቸው በጊዜ ባለፀጋ እንዲሆኑ


2ኛ ሀብታም ሁነው ደሀ የሆኑ የሚመሰላቸው አሉ

👉መልክ የላቸውም በትህርምት የጎሰቆሉ ናቸው  ሰማያዊ መልክ ግን አላቸው
👉ልብስ የላቸውም ክርስቶስን ግን የለበሱ ናቸው
👉ምግብ የላቸውም  ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን የበሉ ናቸው
👉ቤት የላቸውም የብርሃን ቤት  ግን አላቸው
👉ዘመድ የላቸውም ቅዱሳን መላእክት ግን ሊረዱአቸው ይፋጠናሉ
👉ለነዚህ ሰዎች እልል በሉላቸው

🎤ሰውነቱን ላስጨነቃት ለገሰፃት ሰው 

👉በእውነት ለዚህ ሰው ምስጋና ይገባዋል ይላል ነብዩ ኢሳያስ

ስለዚህ ❤️እግዚአብሔር ያለው ሰው ሁሉ አለው

- ጥበብ አለው
- እውቀት አለው
- ጤና አለው
- ሀገር አለው
- ብቻውን ሁሉ ሁኖ ከሰራዊት ሁሉ አሽናፊ ነው

ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሐምሌ 3/2016 #ቅድስት_ባዕታ
#መልአኩ_ቅዱስ_ፋኑኤል
#ፃድቁ_ዜና_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን በቅዱሳኑ ስም ለምናማሰግንበት ለእናታችን ለአማላጃችን ለወላዲተ ቃል #ባዕታ_ማርያም ቤተ መቅደስ ለገባችበት ወርሐዊ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን

" ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ " ( መዝ 45:4)

👉 #ባዕታ ማለት ባዕት ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን መግባት ማለት ነው ባዕታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታኅሣሥ 3 ቀን ወደ #ቤተ_መቅደስ የገባችበት እለትን በመሆኑ ወር በገባ በ3ኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ ቀን ነው

👉#ማርያም ማለት መርሕ ለመንግስተ ሠማያት ማለት ነው ወደ መንግስተ ሠማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው

👉 #ማርያም ማለት ፀጋ ወሀብት ማለት ነው ለሰው ልጆች ድህነት ምክንያት እንድትሆን ከአምላክ የተሰጠች ታላቅ ስጦታ ናትና

👉#ማርያም ማለት የሕያዋን እናት ማለት ነው

👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ልጅ በመሆኗ ቅዱስ እያቄምና ቅድስት ሃና #በቤተ_መቅደስ እንድታድግ ብለው በ3 ዓመቷ አምጥተዋት ለሊቀ ካህኑ ለዘካሪያስ አስረከቧት ነገር ግን ካህኑ ምን በልታ ታድጋለች ብሎ ቢጨነቅም መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሠማይ መናን እያወረደ እየመገበ 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች

👉እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም #እግዚአብሔርን እያመሰገነች ለመላእክት እያገለገለች ሐርና ወርቅን እያስማማች እየፈተለች በንፅህና በቅድስና #በቤተ_መቅደስ በምስጋና ኖራለች

👉እርሱ ጌታችን #ክርስቶስ መርጧታልና ልክ 15 ዓመት ሲሆናት ከሲዖል የታሰርነውን እኛን ለማዳን ሲል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ 9 ወር ከ5 ቀን በማህጸኗ አደረ ተወልዶ አደገ

👉በዚህ ምድር ሲኖር አዳኛችን #ክርስቶስ ወንጌልን አስተማረ ምሳሌ ሆነ መከራን ተቀበለ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ክቡር ደሙን አፈሰሰ ክቡር ሥጋውን ቆረሰ በእርሱ ሞት እኛን ነፃ አወጣን ክብርና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን ምስጋና ለድህነታችን ምክንያት ለሆነችው ለእናታችን #ባዕታ_ማርያም ይሁን

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሀገራችን ሠላሙን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይስጥልን

👉ምስጋናና ክብር ሞቶ ላዳነን በትንሣኤዉ ለአከበረን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ይሁን የቅዱሳን #አበዉ_ሐዋርያት ፀሎት ከክፉ ነገር ይጠብቀን

👉የእናታችን #ባዕታ_ማርያም ፍቅር በረከቷ ምልጃና ፀሎቷ ሁላችንንም ይጠብቀን ለሀገራችን ለህዝባችን ሠላሙን አንድነትን ይስጥልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የመልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ጥበቃዉ የአባታችን #ዜና_ማርቆስ ፀሎትና ምልጃ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/NkSlK8R7GXE?si=cD8MUeFkHyhusoQS

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/major/start?startapp=623043698

👑Help me to become best of the best in @Major and get some Stars!
15⭐️ invite bonus for you
50⭐️ if you are Premium Major

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 10-ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀለዮጳ) ዕረፍቱ ነው፡፡
+ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ልደታቸው ነው፡፡
+ በውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቆሞ ሲጋደል የኖረውና መላእክትም ይጎበኙትና ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት እንደነበር ስንክሳሩ በስም የጠቀሰው አባ ብስንዳ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ቅድስት ቴዎና በሰማዕትነት ዐረፈች፡፡ ይኽችውም ቅድስት ከሐዋርያው ስምዖን ቀለዮጳ ጋር በሰማዕትነት ያረፈች ናት፡፡
ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ፡- ሐዋርያው ናትናኤል በሌላኛው ስሙ ስምዖን እየተባለም ይጠራል፡፡ ናትናኤል ብሎ የሰየመው ጌታችን ነው፡፡ የተወለደው በናዝሬት ቃና ዘገሊላ ሲሆን ከነገደ ብንያም ነው፡፡ የትውልድ ዘመኑ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ሄሮድስ ዕድሜአቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ የቤተልሔም እልፍ ሕፃናትን በሚያስፈጅበት ጊዜ የናትናኤል እናቱ ከበለስ ሥር ደብቃ አትርፋዋለች፡፡ ሐዋርያው ፊሊጶስ ናትናኤልን ጠርቶት ወደ ጌታችን ካመጣው በኋላ ናትናኤል ጌታችንን ‹‹ወዴት ታውቀኛለህ?›› ሲለው ጌታችንም ‹‹ፊሊጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ሥር ሳለህ ዐውቅሃለሁ›› በማለት ከሕፃንነቱ ጀምሮ የጠበቀው አምላኩ እርሱ መሆኑን ነግሮታል፡፡ ቅዱስ አውግስጢኖስ ናትናኤል ምሁረ ኦሪት እንደነበር ጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም ፊሊጶስ ሲጠራው ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር አይወጣም›› በማለት የነቢያትን ቃል የጠቀሰው የመጻሕፍትን ቃል በማወቁ ነው፡፡ ዮሐ 11፡44-52፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል በባቦሎን፣ በሶርያ፣ በግብፅና በኑቢያ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ብዙውን የአገልግሎት ጊዜውን ያሳለፈው በሰሜን አፍሪካ ነው፡፡ በግብፅ ሲያስተምር አማኞች በመብዛታቸው አረማውያን ቀኑበትና በሐሰት ‹‹ሕዝቡ የማይፈልገውን ሃይማኖት ያስተምራል›› ብለው በከንቱ ከሰሱትና ከንጉሡ ፊት ለፍርድ አቅርበው በሐሰተኞች አስመስክረው ሐምሌ 10 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በክብር ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጅቷል፡፡ የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ጻዲቁ አቡነ ሳሙኤል፡- እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት በቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው ‹‹እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናቸውን ‹‹ሳሙኤል›› አሉት፡፡ ትርጓሜውም ‹‹እግዚአብሔር ጸለቴን ሰማኝ›› ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሕፃንነት ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኩሰውታል፡፡ የአባታችን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ:-ከገድላት አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👉ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ትሑት ሁን፤

👉ባለጸጋ ትሆን ዘንድ ድኻ ሁን፤

👉ትጠግብ ዘንድ ረኃብን ውደዳት::

👉ጤነኛ ትሆን ዘንድ የመብል ሽክምን አቅልል፤

👉ትከብር ዘንድ ተዋረድ፣ ደስ ይልህ ዘንድ አልቅስ ፤

👉ትኖር ዘንድ ሙት፤ ትበራ ዘንድ ትጋ፡፡

👉ትድን ዘንድ በማስተዋል ጸልይ፡፡

👉ኃጢኣትህን ይቅር ይልህ ዘንድ አብዝተህ ጹም::

👉ታገኝ ዘንድ ፈልግ፤ ታተርፍ ዘንድ ለመነገድ ተፋጠን::

👉 ስጥ ይሰጡሃል፤

👉ባዕለ ጸጋ ትሆን ዘንድ በብርሃናውያን መንገድ ትመላለስ ዘንድ መስቀልህን ተሸከም፤

👉ሥጋህን ጥላት ነፍስህን አንጻት።

ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሐምሌ_9

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ታውድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መስተጋድል #አባ_ኅልያን አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡

መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡

አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡

አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን "ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው" ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል።

አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን በዚህች ዕለት ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ "ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ" በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ" ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ "አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ" ስትላቸው "እግዚአብሔር ይፍታሽ" ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡

ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ (ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡) ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)

ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር።

ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።

ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም። መኰንኑም በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ ይምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው አለው።

መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ታውድሮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን ከቆጵሮስ አገር ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ አረፉ።

ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውረው ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ምንጭ፦ ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ፤ከገድላት አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተጠንቀቁ እንጂ አትፍሩ!

አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሃገር ጉዞ ሲደርግ አንድ እጅግ አጥፊ የሆነ አውሎ ነፋስ ወደ እሱ አገር አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ኃይል አውሎ ነፋሱን አስቁሞ፣ “ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ፡፡ ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንዳማታጠፋ ቃል ካልገባህ አታልፍም አለው” አውሎ ነፋሱም፣ “በእርግጥ ነው ወደዚያ አቅጠጫ ነው የምሄደው፤ ነገር ግን የአንተን ሃገር ሕዝብ በፍጹም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለሁ” አለው፡፡

ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካታዎቹ እንደሞቱ ሰማ፡፡ በጣም በመቆጣት አውሎ ነፋሱን ተከታትሎ ደረሰበትና፣ “ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድን ነው ብዙ ሰው የገደልከው?” አለው፡፡ አውሎ ነፋሱም እዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩኝ እንጂ የሃገርህን ህዝብ አንዱንም አልነካሁም፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ነፋስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው”፡፡

አንዳንዴ በሃገራችን ከሚከሰተው ችግር ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከት፣ የሚወርሰን ፍርሃት፣ የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽና የፍርሃትና የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉ የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአአምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፋን፡፡

አንባቢዎቼ በወቅቱ በደረሰብን አስጊ ሁኔታ ስለራሳችንና ስለቤተሰቦቻችን የማሰባችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምክንያት የለሽ ፍርሃት ከመተራመስና ራስን ለከፋ ነገር ከማጋለጥ እንጠበቅ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ንስሐ ገብተን ፣ ቅዱስ ቁርባንን ተቀብለን እንዘጋጅ

ፈጣሪ እናንተንና የእናንተ የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅላችሁ፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ስለ ካህናት

👉 በመዝ.104: 5 «ወኢጎደገ ይስሐጦሙ ሰብአ ወገሠጸ ነገሥት በእንቲአሆሙ ወኢትግሥሡ መሲሐንየ ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ /

👉 የቀባኋቸውን አትዳስሱ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ ብሎ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፡፡

👉ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ» ተብሎ ተጽፎአል፡፡

👉እግዚአብሔር የሾምኳቸውን አትዳስሱ ሲል ኃጢአተኞቹንና ክፉ ግብር የሚሠሩትን ለይቶ አይደለም።

👉«የቀባኋቸውን» አለ እንጂ እነ አባ እገሌን እንዲህ ያሉትን እያለ እየመረጠ አይደለም፡፡

👉ካህናትንም በደል ቢሠሩ ከሾማቸው ከእግዚአብሔር በቀር ማንም ሊፈርድባቸጡና ሊያቃልላቸው አይገባውም::

👉 ይህንን ማድረግም ለእግዚአብሔር ከራሱ በላይ «አውቅልሃለሁ» ባይነት ነው::

👉 ስለዚህ ምእመናን በካህናት ላይ ክፉ ግብርን ቢያዩ እንዲያቃልሏቸው አልተፈቀደላቸውም፡፡

👉ይልቁን እግዚአብሔር በሾመው ላይ እኔ ምን ተገብቶኝ ብለው በትሕትና ሊሰበሰቡና በጸሎት ሊተጉ ይገባቸዋል፡፡

👉 ከተቻላቸውም ራስን ዝቅ ከማድረግ ጋር «ምነው አባቴ?» ብለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ዲያቆን ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በረከታቸው ይቅርታቸው ረድኤታቸው ይደርብንና አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምራት ይህ ነው።

ወረብ በሚባል አገር አንድ ሰው ነበረ ያም ሰው በሥራው ሁሉ ቸር ደግ ነበረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስን ይወዳቸው ነበረ ከዕለታት ባንዲት ቀን በበዓላቸው ሲሄድ ሽፍቶች ይገድሉት ዘንድ ተነሱበት ።

ያም ሰው ትገድሉኝ ዘንድ የወደዳችሁ ምን አደረኳችሁ እነዝያም ሽፍቶች እኛስ በዚህ መንገድ የሚሄደውን ሁሉ እንገድላለን አሉት ይህንን በተናገሩ ጊዜ ያ ሰው ፈራ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወደ በዓላችሁ ስሄድ እንዳይገድሉኝ ከነዚህ ሽፍ ቶች አድኑኝ ብሎ ጸለየ (ለመነ) ሥጋየን ሊገድሉት ወደዋልና ።

እንደዚህ እያለ ሳለ ያንን ሰው ይረዳው ዘንድ እነሆ አንበሳ መጣ ወዲያና ወዲህ ተመልክቶ አንበሳው ዘሎ የሽፍቶችን አለቃ አንገቱን ያዘው አጥንቱን በተነው ሰውነቱን ሁሉ አደቀቀው የሬሳው ምልክቱን አጠፋው ከሱ ጋራ የነበሩትም ያንን አንበሳ አይተው ፈሩ ደነገጡ ከዚያ ሰው ከእግሩ በታች ሰገዱ ወዲያና ወዲህ ተመለከቱ።

ይቅር በለን በደላችንን አስተሥርይልን አሉት ባንተ ላይ ክፉ ነገርን እንደተናገርን መጠን አንበሳ ለይቶ አባታችንን ገድሎታልና ከንግዲህ ወዲህ በአምላክህ ተማፅነናል ክፉ መሥራትን ከሚወዱ ሰዎች ሁሉ እንዳንተ ያድነን ዘንድ ።
ያም ሰው በዚህ ተአምራትን ያደረጉ ጌቶቼ ይምሩዋችኋል ።

ያ ሰው ይቅር ባላቸው ጊዜ ይህን ነገር ከሰሙ በኋላ ደስ እያላቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ ። ወዳጆቼ የወንጌልን ምርኮ አስተውሉ ተመልከቱ አእምሮ ከሌላቸው የበረሀ እንስሶች የሥላሴ ጠላቶች አውቀዋልና ያንን ሰው ከቀትለ ፈያት አድናችኋልና እንደዚሁ ሁሉ ሁላችንን ከገጸ ሞትና ከቀስት አድኑን።
የሥሉስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው ትደርብን!
+ + +

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/smDEv9Ue2YM?si=xutx5OP3qyeZr2jF

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#_ሐምሌ_7_የአብርሃሙ_ሥላሴ_ዝክራቸው_ሜቄዶንያ_ነው!

እሑድ ሐምሌ 7 ሜቄዶንያ አረጋውያንንና ሕሙማንን እንዘክራለን

#_ዝክሩ_የሚጀምረው_ጠዋት_3_ሰዓት_ነው!

ሼር በማድረግ መልእክቱን አዳርሱልን!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሐምሌ 7 እሑድ ሥላሴን ሦስት በሬ አርደን በሜቄዶንያ ለሚኖሩት ለአረጋውያንና ለአእምሮ ሕሙማን በሰፊው እንዘክራለን።

የሥላሴን በረከት ለመሳተፍ የምትመጡ ወዳጆቻችን እባኳችሁ በመቄዶንያ ለሚኖሩት ለአረጋውያንና ለአእምሮ ሕሙማን ለክረምት ለብርዱ የሚሆናቸውን ብርድ ልብስ ይዛችሁልን ኑ።

የአንዱ ብርድ ልብስ ዋጋ 1000 /አንድ ሺ/ ብር ነው። ከቻላችሁ ብርድ ልብሱን ገዝታችሁ ማምጣት፤ ካልቻላችሁ ለሜቄዶንያ ለድርጅት የአንድ ብርድ ልብስ ዋጋ ቢሮ ሄዳችሁ መስጠት ትችላላችሁ።

❤ ባለፈው ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዝክር ብርድ ልብስ ቃል የገባችሁልን ይዛችሁልን ኑ!

❤ እንዲሁም ቤታችሁ የማትጠቀሙበትን ልብሶች እና ጫማዎችን ይዛችሁልን ኑ።

❤ የበረታችሁ ደግሞ ለአዋቂዎች የሚሆን ዳይፐር ይዛችሁልን ኑ!

"ለድሆች ስጥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ" ማር 10፥21

ሐምሌ 5-11-16 ዓ.ም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Yene kiros aklil
Siwrd kerama
Atleyayubt
Be wengel alama ,
Yezarews slt esey esey
Albet krstos. ,,
Balbetu adrobt ,,
Be tansh ento ,,
Enatunm merat ,,
Yesost amt esan,,

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/major/start?startapp=623043698

👑Help me to become best of the best in @Major and get some Stars!
75⭐️ invite bonus for you
200⭐️ if you are Premium Major

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አደረሰን!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶቻችን ሐዋርያትን ሰማዕትነት በተቀበሉበት ቀናት በዓላት ሰይማ ታከብራቸዋለች፡፡ እንዲሁም በስማቸው የተሰየመውን ጾም በመጾም አሠረ ፍኖታቸውን ይከተሉ ዘንድ ምእመናንን ታሳስባለች፡፡ በሐምሌ ፭ ቀን ደግሞ የደጋጎቹን ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስን በዓል ታደርጋለች፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን በዓል መደረጉ በአንድ ቀን ሰማዕትነት በመቀበላቸው ነው፡፡

ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አመራረጣቸው በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የጥሪው መንገድ ግን ይለያይ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት የተመረጠው ጌታችን በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ሆኖ ዓሣ ለማጥመድ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ወደ እነርሱም ቀርቦ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ (ማቴ.፬፥፲፰‐፳)

በአንጻሩ የቅዱስ ጳውሎስ አመራረጥ ደግሞ በተአምር ነው፤ ይኸውም እንዲህ ነው፡፡ በቀደመ ስሙ ሳውል ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያን አሳዳጅ ነበር፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ ሲወገር የተስማማ የገዳዮቹንም ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (የሐዋ. ፯፥፶፰-፷)

ቅዱስ መጽሐፍ “ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወህኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር፡፡ . . . ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው እየዛተ . . .” እንዲል፡፡ (የሐዋ.፰፥፫፤፱፥፩) በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከሊቁ ካህናቱ ዘንድ የፈቃድ ደብዳቤ ጠየቀ፡፡ ይህን ዓላማውን ለማስፈጸም ወደ ደማስቆ ሲጓዝ በርሱ ዙሪያ ከሰማይ መብረቅ ወረደ፤ ዐይኖቹም ታወሩ፤ ወደ ምድርም ወደቀ፡፡

በዚያም ሳለ “ሳውል ሳውል፥ ስለምን ታሳድደኛለህ” የሚለውን ድምፅ ሰማ፡፡ ያነጋገረው ሳውል የሚያሳድደው ጌታ ነበር፡፡ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብኻል” አለው፡፡ ከዚያም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ፡፡ ሦስት ቀንም ሳይበላ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡ ሐናንያ የተባለው ከደቀ መዛሙርት ወገን የሆነ ወደ እርሱ ዘንድ ቀርቦ ጸለየለት፤ ዐይኖቹም ተፈወሱ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፡፡ (የሐዋ.፱፥፩‐፲፰)

ቅዱስ ጳውሎስ በወቅቱ ስለሆነው ነገር ለቆሮንቶስ ምእመናን ሲተረክላቸው “ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ፡፡ እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ” እንዲል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፱)

የቤተ ሰብ ሕይወታቸው
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ቤተ ሰቦቹ ደግሞ በቅፍርናሆም ይኖሩ ነበር፡፡ የኦሪት መጻሕፍትን ያልተማረ ከዝቅተኛው የማኅበረሰብ ክፍል የተገኘ ሰው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፬፥፲፫) ጳውሎስ ደግሞ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ተወለደ፡፡ ከአይሁድ ወገን ከብንያም ወገን ነበር፡፡ (ፊል.፫፥፭) በጠርሴስም ሳለ በገማልያል እግር ሥር የኦሪት ትምህርቱን ተማረ፤ በትምህርቱም የተመሰከረለት ነበር፤ (የሐዋ.፳፪፥፫፤፳፮፥፳፬) ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔር መንግሥት ለተማሩትም ላልተማሩትም፣ ለባለጸጎችም ለድሆችም የተዘጋጀ መሆኑን ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ባለ ትዳር ነበር፡፡ አማቱም ታማ በነበር ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤቷ ገብቶ እንደፈወሳት በወንጌል ተጽፏል፡፡ (ማቴ.፰፥፲፬‐፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ድንግል ነበር፡፡ “ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና ነገር ግን፥ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ፡፡ ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፡- እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ነገር ግን፥ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” በማለት ለቆሮንቶስ ምእመናን ጽፏል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፯፥፯‐፱) ቤተ ክርስቲያን እንደ ጴጥሮስ ያገቡ እንደ ጳውሎስ ያሉ ደናግላንን ይዛ የምትገኘው ጌታችን ሁሉንም ወደ እርሱ ስለጠራ ነው፡፡

የስማቸው መለወጥ
ቅዱስ ጴጥሮስ የዮና ልጅ ስምዖን ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፭) ነገር ግን ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “እናንተስ ማን ትሉታላችሁ” ብሎ ሲጠይቃቸው ሐዋርያው ተነሣና፡- “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም” በማለት ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፡፡ (ማቴ.፲፮፥፲፯—፲፰)

ጳውሎስን ደግሞ ጌታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠራው በመጀመሪያ ስሙ ሳውል ብሎ ጠራው፤ በምስክርነቱ ጊዜ ደግሞ “ጳውሎስ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና፥ አይዞህ አለው፡፡” (የሐዋ.፳፫፥፲፩)

አገልግሎታቸው
የቅዱስ ጴጥሮስ አገልግሎቱ በአብዛኛው ሕግ ለተጻፈላቸው፣ ነቢያት ለተላኩላቸው፣ መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ግርዛት ለተሰጣቸው ለአይሁድ ነበር፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት የነበረው በአሕዛብ መካከል ነበር፡፡ ይህንንም ሲመሰክር “ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቷልና፡፡” ብሏል፡፡ (ገላ.፪፥፯‐፰) እንዲያውም በአንድ ወቅት ጳውሎስና በርናባስን አይሁድ ትምህርታቸውን በተቃወሟቸው ጊዜ “እነሆ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን እንዲሁ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና” ብለው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፲፫፥፵፮—፵፯)

በበዓለ ኀምሳ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ ጴጥሮስና ዮሐንስ በትምህርታቸው በኢየሩሳሌም ለነበሩ ነፍሳት ደረሱ፡፡ በአንድ ቀን ብቻ ሦስት ሺህ ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ፡፡ (የሐዋ.፪) ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ “ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” በማለት ስለተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መስክሯል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፲፬፥፲፰) ሁለቱም ሐዋርያት በምእመናን ላይ እጃቸውን በመጫን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ያሳድሩ ነበር፡፡ (የሐዋ.፰፥፲፬፤፲፱፥፭‐፮)

በአገልግሎታቸው ድንቅ ተአምራትን ፈጽመዋል፡፡ ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡፡ “እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር፡፡” (የሐዋ.፲፱፥፲፩—፲፪) በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አገልጋይን ከሞተች፤ አጥበውም በሰገነት ከአኖሯት በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ካለበት ተጠርቶ ከጸለየ በኋላ ጣቢታ ሆይ ተነሽ ሲላት ዐይኖቿን እንደከፈተች ተጽፏል፡፡ (የሐዋ.፱፥፴፮—፵፪) በተመሳሳይ ቅዱስ ጳውሎስ አውጤኪስ የሚባል ከሦስተኛ ደርብ ወደ ታች ወድቆ የሞተን ጎልማሳ እንዲነሣ አድርጓል፡፡ (የሐዋ.፳፥፯—፲፪)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/DNLw7ydHUto

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/major/start?startapp=623043698

👑Help me to become best of the best in @Major and get some Stars!
15⭐️ invite bonus for you
50⭐️ if you are Premium Major

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

[🗒]
✅እባክዎትbetenaመጀመርያ አድ ያድርጉአድ ሳያደርጉ በፍጹም ሽልማት🎁 አይደርሱትም ከታች link አለ እሱ በመንካት ወደ ግሩፕ አስገባቸዋል ከዛ አድ አደረጉና ሽልማታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ ከዛ አካውንት ቁጥሩ ከታች ፃፉልን ግሩፕ ላይ አድ ያድርጉ ይሽለሙ🎁🎁🎁🎁🎁

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk
/channel/+VLw0zJgLeoAwOWZk

Читать полностью…
Subscribe to a channel