ጣና ሐይቅን በያዟት በትር (ዘንግ) ተሻግረው መጡ። «አባ እንዴት መጡ?» ሲሏቸው «በዘንጌ» አሉ። ከዚያ በኋላ ቦታው «ዘንጌ» የሚለው አጥሮ «ዘጌ» ተብሎ ተጠራ።
ያችን ተሻግረው የመጡባትን ዘንግ ደግሞ ከሦስት ቆርጠው ተከሏት። አንዷን ቡና፣ አንዷን ሎሚ፣ አንዷን ጌሾ አድርጐ አጸደቀላቸው። እስከ ዛሬ ድረስ ዘጌ ገዳማትና በዙሪያው ከእነዚህ ከሦስቱ አጽዋት በቀር ሌላ ምንም ነገር ለመተዳደሪያነት አይውልም።
ዛሬ የጻድቁ የአቡነ በትረ ማርያም በዓለ ዕረፍታቸው ነው። በረከታቸው ይድረሰን።
1⃣ የሙሉ ሰውነት መገለጫ ያልሆነው የቱ ነው ?
ሀ) ከተናቀ ነገር የከበረ ነገር ይወጣል ።
ለ) ሰዎች ብዙ ቢሉትም የማይደነቅ ነው ።
ሐ) ለእውነት ፈጥኖ የሚታዘዝ ።
መ) ሁሉም
ሠ) መልሥ የለም
2 ) ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ድንጋይ ሆነ
ግንበኞች የተባሉት እነማን ናቸው ?
ሀ) አጋንንት
ለ) አይሁድ
ሐ) መናፍስት
መ) ቅዱሳን
ሠ) መልስ የለም
🍀🍀🍀 በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት ሆነው እንሰራለን ።
🍀🍀መርጌታ ጌታቸው የባህል የህክምና የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
🍀-ለገበያ ለሃብት
🍀-ለመስተፋቅር
🍀-ገንዘብ አልበረክት ላላቹሁ
🍀-ገንዘብ ለተወሰደባቹሁ እንዲመለስ
🍀-የስራ እድል
🍀-ለትምህርት
🍀- ለገርጋሪ
🍀-ለአፍዝ አደንግዝ
🍀- ለመፍትሔ ስራይ
🍀- ለህመም
🍀- ለውጭ እድል
🍀- ጋኔን ለያዘው ሰው
🍀🍀ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ዛሬ ለሚገረግር እና እንቢይ (አልሸጥ )ለሚል ገብያ የሚሰራ ።
🍀ሆቴል
🍀ግሮሰሪ
🍀ሱቅ
🍀ጉልት
🍀ቡቲክ
🍀መጋዘን
🍀ማከፋፈያ ወዘተ.......ሲሆን
🍀🍀ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል ከተዘረዘሩት ውጭ ደውለው የአማክሩን።
ይደውሉ//0968839047
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 16- ‹‹ወንጌሉ ዘወርቅ›› የተባለ ታላቁ አባት አቡነ ዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አባታችን ሀገራቸው ሮም ሲሆን ወላጆቻቸውም ደጋግ ባለጸጋ የሆኑ ክርስቲያኖች ስለነበሩ ለመምህር ሰጥተው መጻሕፍትን እየተማሩ እንዲያድጉ አደረጓቸው፡፡ በኋላም ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራላቸው ዘንድ አባታቸውን ለመኑትና አሠራላቸው፡፡ ያንንም ወንጌል ዕለት ዕለት ያነቡት ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ወላጆቻቸው ቤት የሚያርፍ አንድን መነኩሴ እንዲወስዳቸው ለመኑትና ወደ ገዳሙ በስውር ይዟቸው ሄደ፡፡ የገዳሙ አበ ምኔትም ዮሐንስን አመነኮሷቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪታይ ድረስ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ አበ ምኔቱም ድካማቸውን እንዲቀንሱ ይመክሯቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በራእይ ወደ አባታቸው ቤት እንዲሄዱ አመላከታቸውና ለአበ ምኔቱ ነግረው ወደ ባለጸጋው አባታቸው ዘንድ ሄዱ፡፡ በመንገድ ላይም አንድ ነዳይ አገኙና ልብሳቸውን ቀይረውት የነዳዩን ልብስ ለብሰው ሄደው በአባታቸው ደጅ ማንም ሳያውቃቸው ለማኝ መስለው ተቀመጡ፡፡ በአባታቸው ደጅም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ የአባታቸው ባሪያዎች የሚጥሉትን ፍርፋሪ እየተመገቡ 7 ዓመት ተቀመጡ፡፡
እናታቸውም ከቤት በወጡ ጊዜ ሽታቸው እየከረፋቸው ትጨነቅ ነበር፡፡ ዕረፍታቸውም በቀረበ ጊዜ የታዘዘ መልአክ ለአቡነ ዮሐንስ ተገልጦላቸው የዕረፍታቸውን ጊዜ ነገራቸው፡፡ ወዲያውም ወደ እናታቸውም ሰው ልከው ስትመጣላቸው ልጇ መሆናቸውን ሳይነግሯት በሚሞቱ ሰዓት በዚያች በለበሷት እራፍ የነዳይ ጨርቅ ብቻ ጠቅልለው እንዲቀብሯቸው ነገሯት፡፡ ‹‹በሞትኩም ጊዜ ይህን መጽሐፍ በአስክሬኔ ላይ አንብቡልኝ›› ብለው የወርቅ ወንጌላቸውን ጠቅልለው ሰጧት፡፡ አባታቸውም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል ባየ ጊዜ ልጁ እንደሆነ ዐወቀና መሪር ዕንባን አለቀሰ፡፡ ሁሉም አብረው ተላቀሱ፡፡ የሮም ከተማ ሽማግሌዎችና ሕዝቡም ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ሰባት ቀን ሲሆናቸው ሐምሌ 16 ቀን ዐረፉ፡፡ እናታቸውም ባማሩና በተዋቡ ንጹሕ ጨርቆች እንዲገነዙ ስታደርግ ወዲያው ታመመች ነገር ግን አባታቸው በእራፊ ጨርቃቸው እንዲገንዟቸው ያዘዟቸውን አስታውሰው ቀድሞ በለበሱት እራፊ ጨርቅ ሲገንዟቸው ተመልሳ ዳነች፡፡ የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ገብርኤል
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ስቡህ_ከተባለ_በኃላ
@esate_yarade
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡
@esate_yarade
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።
@esate_yarade
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡
@esate_yarade
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
@esate_yarade
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
@esate_yarade
ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።
@esate_yarade
መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡
@esate_yarade
ዚቅ
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።
@esate_yarade
ወረብ
"ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
@esate_yarade
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።
@esate_yarade
ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።
@esate_yarade
ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/
@esate_yarade
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእሳት አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።
@esate_yarade
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።
@esate_yarade
ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/
@esate_yarade
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።
@esate_yarade
ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡
@esate_yarade
ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/
@esate_yarade
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡
@esate_yarade
ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡
@esate_yarade
ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ኢይኩን ሕፀተ /፪/
ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/
@esate_yarade
መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።
@esate_yarade
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡
@esate_yarade
መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።
@esate_yarade
ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።
@esate_yarade
ወረብ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/
@esate_yarade
ምልጣን፦
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ
አመላለስ:
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/
@esate_yarade
ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
@esate_yarade
እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ማ- አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡
@esate_yarade
አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/
@esate_yarade
ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/
👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@esate_yarade👈
👉@esate_yarade👈
👉@esate_yarade👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@esate_yarade
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
🌹#አባ_መቃርስ❤
☞ወር በገባ በ14 የአባታችን የአባ መቃርስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡
☞በልጅነቱ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እየተማረ አደገ፡፡☞የዓለምን ከንቱነት ተመልክቶ ዳግመኛም የኃጢአንንና የጻድቃን ዎጋቸው አይቶ ወደ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ከመነኮሰም በኃላ የ10ቀን መንገድ ተጉዞ ኩዕንትና
ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ላይ ደረሰ፡፡
☞በዚያም ኩዕንትን ወደ መልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል
በዚህም ተራራ ላይ ብቸኛ ነኝና ሰብስቦ የሚያገባልኝ የለም፡፡ ሥጋ አትብላ
ያለውስ የባልንጀራህን ሥጋ በሐሜት የምንበላው አይደለምን?ሌላ ምግብ
እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃልብሎ ከዚያች ዕለት ወዲህ ለምግቡ ቆቅ
የሚያጠምድ ሆኖ በእግዚአብሔር ፈቃድ በየቀኑ አንድ አንድ ቆቅ የሚያዙለት
ሆነ፡፡
☞በየቀኑም አንድ አንድ ቆቅ እየተመገበ ውኃ እየጠጣ ፈጣሪውን እያመሰገነ
በታላቅ ተጋድሎ ሆኖ የሰውን ፊት ሳያይና ከማንም ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን
ኖረ፡፡
☞ከቁስጥንጥንያ ከተማ የወጣ አንድ መነኩሴ ዋሻ ሲፈልግ አባ መቃርስ
ደግሞ ቆቅ ሲያጠምድ አየውና ለሐሜት ቸኩሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ሄደ
ለሊቀ ጳጳሳቱ"ቆቅ እያጠመደ ሥጋ የሚበላ መነኩሴ አገኘሁ፤ እርሱም በሕዝብ
ዘንድ ሊስነቅፈን ነው ብሎ ነገረው፡፡
☞ሊቀ ጳጳሳቱም ከአንድ ሌላ መነኩሴ ጋር ድጋሚ እንዲያረጋግጥላቸው
ላካአቸው፡፡ እነርሱም ገና ከበዓቱ ሳይደርሱ አባ መቃርስ ቆቅ ሊያጠምድ ሄደና
ያለወትሮው በአንዲት ወጥመድ ሦስት ቆቆችን ተያዙለት፡፡
☞ሌላ ጊዜ በቀን አንድ ብቻ ነበር የሚያዝለት ዛሬ ግን እግዚአብሔር
ለሚመጡት እንግዶችም ጭምር ሲያዘጋችላቸው ነው ያለወትሮም ዛሬ ሦስት
ሆነው የተያዙለት፡፡
]አባ መቃርስም ሁለቱን መነኮሳት ሲያያቸው ሁለት ተጨማሪ ሆነው የተያዙለት
ቆቆች የእንግዶቹ መሆናቸውን ዐውቆ ጌታችንን አመስገነው፡፡
☞እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ እስካቀረበላቸው ድረስ በመቃርስ ላይ
ይጠቋቆሙበት ነበር፡፡
☞አባ መቃርስም ምግብ አዘጋጅቶ ሲጨርስ የራሱን ድርሻ አንዷን ቆቅ አስቀርቶ
ሁለቱን ለእንግዶች አቀረበላቸው፡፡
☞እርሰሱም በልቶ ጨርሶ ቀና ሲል እንግዶቹን መነኮሳት እንዳልበሉ ተመልከተና
አባቶቼ ለምን አልበላችሁም?አላቸው፡፡
☞እነርሱም እኛ መነኮሳት ስለሆንን ሥጋ አንበላም አሉት፡፡ አባ መቃርስም እሺ
ተውት አላቸውና እነዚያን አብስሎ በገበታ ላይ ለምግብነት ያቀረበላቸውን ሁለት
ቆቆች ሦስት ጊዜ በእስትንፋሱ እፍ ቢልበባቸው ሕይወት ዘርተው በረሩና ወደ
ጫካ ሄዱ፡፡
☞እነዚያ መነኮሳትም እጅግ ደንግጠው ማረን ይቅር በለን ቅዱሱን
የእግዚአብሔር ሰው በከንቱ አምተንሀል ብለው እግሩ ሥር ሲወዱቁ
እግዚአብሔር የሁላችንን በደል ይቅር ይበለን አላቸው፡፡
☞ሁለቱ መነኮሳት ወደ ቁሰጥንጥንያ ተመልሰው ለሊቀ ጳጳሳቱ ለሕዝቡ ያዩትን
ነገር መሰከሩ፡፡
☞ሊቀ ጳጳሳ እጅግ ተደንቆ ወደ ንጉሡ ደብዳቤ ጽፎ በምድራችን ጻድቅ ሰው
ተገኝቷልና አንተም ና ሄደን በረከቱን እንቀበል ብሎ መልእክት ላከበት፡፡
☞ንጉሡም እሺ ብሎ ከሠራዊቱ ጋር ተነሥቶ ከካህናቱ ጋር ወደ አባ መቃርስ
ዘንድ ሄደ፡፡
☞ወደ ገዳሙም በቀረቡ ጊዜ አባ መቃርስን ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ
መልአክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሸክሞት ሲያርግ አዩት፡፡
☞እርሱም የእግዚአብሔር ቅዱስ ሰው ሆይ ባርከን የምንድንበትንም አንዲት
ቃል ንገረን አሉት፡፡
☞አባ መቃርስም ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁን ይከልከል፤ካህን ብዙ
ባይማር ትዕቢት መታጀር ባልመጣበት ነበር፡፡ መነኩሴም ትኅምርት ባያበዛ
ባልተመካ ነበር፡፡ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ እግዚአብሔር አድሮባች ይኑር
አላቸው፡፡
☞ይህንንም ከተናገራቸውና ከባረካቸው በኃላ ከአይናቸው ተሰወረ፡፡
©መዝገበ ቅዱሳን መጽሐፍ
☞የበረሀው መናኝ የአባታችን የአባ መቃርስ የጸሎታቸው በረከት አይለየን፡፡
📣📣📣 Big Discounts ‼️‼️📣📣 📣📣📣📣📣📣📣📣
❇️ Smart Watch Series 8
🚩2022 Model
🚩Model: W26+
📞📞0909143543
💦 ዋጋ፦ 3, 200 ብር
➡️ የልብ ምትን ይለካል
➡️ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን
➡ የደም ግፊትን ይለካል
➡️ ስፖርት ስንሰራ ይቆጥርልናል
➡️ ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
➡ ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
➡️ ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ይቻላል
➡️ ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚችሉበት
✔️Size: 44mm
✔️ Battery: 380mAh
✔️ Built-in: Mic+Speakers
✔️ Full Touch Screen, 1.75" Display
🌀 Bluetooth Calling
🌀 Notifications
🌀 Music & Camera Remote Control
🌀 Heart Rate Tracker
🌀 Monitor Blood Pressure
🌀 Magnetic pin charger
🌀 Charging time upto 2 to 3 hrs
📞📞0909143543
💦 ዋጋ፦ 3,2000 ብር
የሚፈለግ ያናግረኝ
ሐምሌ 13/2016 #እግዚአብሔር_አብ
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል እና ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምህረት #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃ የፃድቁ #አቡነ_ዘርአ_ብሩክ ፀሎት አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን እረድቶ ሰናክሬምንና 185,000 ሠራዊቱን በአንዲት ሌሊት የገደለበት ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አባ ሖር ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡
አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልንና ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም በሆነ ተአምር ረድቶታል፡፡ ከጌታችን ልደት 700 ዓመታት በፊት ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር፡፡ደጋጓቹ ነገሥታት ዳዊትና ሰሎሞን ካረፉ በኋላ የሕዝቅያስን ያህል ቅንና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሠም፡፡ ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት፡፡ ወደ አካባቢውም መጥቶ ከቦ አስጨነቀው፡፡ ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር፡፡የሠራዊቱም ብዛት ከ185,000 በላይ ነውና ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደማይችለው ዐውቆ መልእክተኛ ላከበት፡፡ ‹‹ግብር እገብርልሃለሁ፣የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ፣ ነገር ግን ሀገሬን አታጥፋ፣ ኢየሩሳሌምን አታቃጥል፣ ሕዝቤንም አትግደል›› ብሎ ለመነው፡፡ እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት፡፡ ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና በመናቅ አምላኩን እግዚአብሔርንም ተሳደበ፡፡ ‹‹ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው›› ሲል ላከበት፡፡ ሕዝቅያስም በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲሰደብ ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ። መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ፡፡ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና ‹‹ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ›› ብሎ ለነቢዩ ኢሳይያስ ነገረው፡፡ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን መልእክት ለንጉሥ ሕዝቅያስ ነገረው፡፡ በዚያችም ሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወርዶ የሰናክሬምን 185 ሺውንም የጦር ሠራዊት በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው አደረ፡፡ በለኪሶ የነበረው ሰናክሬምም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱን ሁሉ የአስከሬን ክምር ሆኖ አገኘው፡፡ በታላቅ ድንጋጤ ሆኖ ወደ ነነዌ በመሄድ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች በሰይፍ ገደሉት፡፡ትዕቢተኛው ሰናክሬምም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ። ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ሞገስና ረዳት ሆኖታልና የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት፣ እጅግ አከበሩትም፡፡ 1ኛ ነገ 18፡13፣ 19፡1፡፡
የሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልን!
+ + +
ሰማዕቱ አባ ሖር፡- አባቱ ስርያቆስ በምትባል አገር ይኖር የነበረ አንጥረኛ ነው፡፡ልጁን ሖርንም እግዚአብሔርን በመፍራት በሃይማኖት በምግባር አሳደገው፡፡ጎልማሳ በሆነም ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት ስለመጣ አባ ሖር በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ ፈርማ ወደምትባል አገር ሄደ፡፡ በዚያም በከሃዲው መኮንን ፊት ቀርቦ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ በጽኑ አሠቃየው፡፡ ጌታችንም ከሥቃዩ ፈውሶት ተነሣ፡፡ከሃዲ የነበረው መኮንንም ጌታችን ለአባ ሖር ያደረገለትን ታላቅ ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር በጌታችን አመነ፡፡እርሱም በማመኑ በሌላ መኮንን ዘንድ በተራው ብዙ ተሠቃይቶ ከነቤተሰቡ በሰማዕትነት ዐረፈና በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ይኽም ሌላኛው መኮንን አባ ሖርን ወደ እንዴና ላከው፡፡ በዚያም ከሃዲዎች በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ በመንኮራኩር አበራዩት፣ዘቅዝቀው ሰቅለው በእሳት በጋለ ብረት ደበደቡት፡፡ መኮንኑም አባ ሖርን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የከበረች ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ ቅዱስ አባ ሖር አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ የእርሱም ማኅበርተኞቹ
የሆኑ 127 ወንዶችና 20 ሴቶች አብረውት ተሰይፈው የድል አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡
የአባ ሖር ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን ረድቶ በትዕቢት እግዚአብሔርን የሰደበውን ንጉሥ ሰናክሬምንና 185,000 ሠራዊቱን በአንዲት ሌሊት ጨርሶ በመግደል ታላቅ ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አባ ሖር ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡
አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልንና ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም በሆነ ተአምር ረድቶታል፡፡ ከጌታችን ልደት 700 ዓመታት በፊት ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር፡፡ ደጋጓቹ ነገሥታት ዳዊትና ሰሎሞን ካረፉ በኋላ የሕዝቅያስን ያህል ቅንና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሠም፡፡ ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት፡፡ ወደ አካባቢውም መጥቶ ከቦ አስጨነቀው፡፡ ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር፡፡ የሠራዊቱም ብዛት ከ185,000 በላይ ነውና ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደማይችለው ዐውቆ መልእክተኛ ላከበት፡፡ ‹‹ግብር እገብርልሃለሁ፣ የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ፣ ነገር ግን ሀገሬን አታጥፋ፣ ኢየሩሳሌምን አታቃጥል፣ ሕዝቤንም አትግደል›› ብሎ ለመነው፡፡ እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት፡፡ ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና በመናቅ አምላኩን እግዚአብሔርንም ተሳደበ፡፡ ‹‹ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው›› ሲል ላከበት፡፡ ሕዝቅያስም በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲሰደብ ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ፡፡ መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና ‹‹ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ›› ብሎ ለነቢዩ ኢሳይያስ ነገረው፡፡ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን መልእክት ለንጉሥ ሕዝቅያስ ነገረው፡፡ በዚያችም ሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወርዶ የሰናክሬምን 185 ሺውንም የጦር ሠራዊት በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው አደረ፡፡ በለኪሶ የነበረው ሰናክሬምም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱን ሁሉ የአስከሬን ክምር ሆኖ አገኘው፡፡ በታላቅ ድንጋጤ ሆኖ ወደ ነነዌ በመሄድ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች በሰይፍ ገደሉት፡፡ ትዕቢተኛው ሰናክሬምም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ፡፡ ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ሞገስና ረዳት ሆኖታልና የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት፣ እጅግ አከበሩትም፡፡ 1ኛ ነገ 18፡13፣ 19፡1፡፡
የሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልን!
+ + +
ሰማዕቱ አባ ሖር፡- አባቱ ስርያቆስ በምትባል አገር ይኖር የነበረ አንጥረኛ ነው፡፡ ልጁን ሖርንም እግዚአብሔርን በመፍራት በሃይማኖት በምግባር አሳደገው፡፡ ጎልማሳ በሆነም ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት ስለመጣ አባ ሖር በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ ፈርማ ወደምትባል አገር ሄደ፡፡ በዚያም በከሃዲው መኮንን ፊት ቀርቦ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ በጽኑ አሠቃየው፡፡ ጌታችንም ከሥቃዩ ፈውሶት ተነሣ፡፡
ከሃዲ የነበረው መኮንንም ጌታችን ለአባ ሖር ያደረገለትን ታላቅ ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር በጌታችን አመነ፡፡ እርሱም በማመኑ በሌላ መኮንን ዘንድ በተራው ብዙ ተሠቃይቶ ከነቤተሰቡ በሰማዕትነት ዐረፈና በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ይኽም ሌላኛው መኮንን አባ ሖርን ወደ እንዴና ላከው፡፡ በዚያም ከሃዲዎች በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ በመንኮራኩር አበራዩት፣ ዘቅዝቀው ሰቅለው በእሳት በጋለ ብረት ደበደቡት፡፡ መኮንኑም አባ ሖርን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የከበረች ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ ቅዱስ አባ ሖር አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ የእርሱም ማኅበርተኞቹ የሆኑ 127 ወንዶችና 20 ሴቶች አብረውት ተሰይፈው የድል አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡
የአባ ሖር ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
ሰይጣን መንፈሳዊ ህይወትን ለመኖር ወስነህ ስትጀምር በእነዚህ ሁለት ሀሳቦች ይዋጋሃል።
1,
👉አንተ ለዚህ ህይወት እንደማትሆን እና መቼም እንደማትለወጥ ሹክ ይልሃል ይህን የሚያደርገው የሚገርመው ተስፋ ቆርጠህ የምታደርገውን ሩጫ እንድታቆም ነው።
👉 የሚገርመው ግን መለወጥ ባትጀመር ኖሮ ሰይጣን አትለወጥም አይልህም።
2,
👉ገና ከመጀመርህ የደረስክ እና ለመፈፀም ጥቂት የቀረ አስመስሎ ያሳየሃል።
👉ብዙ ርቀት እንደሄድክ አስበህ እንደ ጥንቸሏ ተዘናግተህ እንድትተኛ እና የፅድቅን ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው ትዕቢት እስረኛ እንድትሆን ያደርገሃል አሁንም ሰይጣን ደርሰሃል እያለ ሲክብህ ገና እግርህን ለማንሳት የምትጣጠር እንደሆን በደንብ ያውቀዋል።
👉 ጀማሪ ስትሆን ሰይጣን አትችልም ብሎ ተስፋ በማስቆረጥ ወይም ደርሰሃል እያለ ልክ በማመስገን ወጥመድ ውስጥ ሊጥልህ ይሞክራል።
👉በሰይጣን እንዳትታለል የእርሱን ሀሳብ አንስተውልምና
2 ቆሮ ምእራፍ 2:11
ሊቀቅ 7 ቀን ነዉ የቀረዉ አሪፍ ስራ ነዉ ከ75dollar በላይ ነዉ የሚሰጠዉ ሞክሩት
Your referral link: /channel/avagoldcoin_bot.?start=15f7b82a631018626949
ክርስትና ባጭር ቃል ፍፁም ፍቅር ነው
ፍቅር የልብ ሀሳብን ይገዛል ዱላ ግን ጉልበትን ይገዛል ።
ክርስቲያን ሁልጊዜ በልቡ ፍቅር አለ
ፍቅር ፍፁም ቅዱስ እርህራሄ ነው
ስንቶቻችን ነን ክርስቲያን መባል የተገባን
የስም ሳይሆን የተግባር ?
ጥያቄ
1 ቀኑን ሙሉ እግዚአብሄርን❤️ በመፍራት ኑሩ ሲል ምን ማለት ነው ?
ሀ) ከጥዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት
ለ) 24 ሰዓት ሙሉ
ሐ) ዕድሜያችሁን ሙሉ
መ) መልስ የለም
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 16- ‹‹ወንጌሉ ዘወርቅ›› የተባለ ታላቁ አባት አቡነ ዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አባታችን ሀገራቸው ሮም ሲሆን ወላጆቻቸውም ደጋግ ባለጸጋ የሆኑ ክርስቲያኖች ስለነበሩ ለመምህር ሰጥተው መጻሕፍትን እየተማሩ እንዲያድጉ አደረጓቸው፡፡ በኋላም ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራላቸው ዘንድ አባታቸውን ለመኑትና አሠራላቸው፡፡ ያንንም ወንጌል ዕለት ዕለት ያነቡት ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ወላጆቻቸው ቤት የሚያርፍ አንድን መነኩሴ እንዲወስዳቸው ለመኑትና ወደ ገዳሙ በስውር ይዟቸው ሄደ፡፡ የገዳሙ አበ ምኔትም ዮሐንስን አመነኮሷቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪታይ ድረስ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ አበ ምኔቱም ድካማቸውን እንዲቀንሱ ይመክሯቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በራእይ ወደ አባታቸው ቤት እንዲሄዱ አመላከታቸውና ለአበ ምኔቱ ነግረው ወደ ባለጸጋው አባታቸው ዘንድ ሄዱ፡፡ በመንገድ ላይም አንድ ነዳይ አገኙና ልብሳቸውን ቀይረውት የነዳዩን ልብስ ለብሰው ሄደው በአባታቸው ደጅ ማንም ሳያውቃቸው ለማኝ መስለው ተቀመጡ፡፡ በአባታቸው ደጅም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ የአባታቸው ባሪያዎች የሚጥሉትን ፍርፋሪ እየተመገቡ 7 ዓመት ተቀመጡ፡፡
እናታቸውም ከቤት በወጡ ጊዜ ሽታቸው እየከረፋቸው ትጨነቅ ነበር፡፡ ዕረፍታቸውም በቀረበ ጊዜ የታዘዘ መልአክ ለአቡነ ዮሐንስ ተገልጦላቸው የዕረፍታቸውን ጊዜ ነገራቸው፡፡ ወዲያውም ወደ እናታቸውም ሰው ልከው ስትመጣላቸው ልጇ መሆናቸውን ሳይነግሯት በሚሞቱ ሰዓት በዚያች በለበሷት እራፍ የነዳይ ጨርቅ ብቻ ጠቅልለው እንዲቀብሯቸው ነገሯት፡፡ ‹‹በሞትኩም ጊዜ ይህን መጽሐፍ በአስክሬኔ ላይ አንብቡልኝ›› ብለው የወርቅ ወንጌላቸውን ጠቅልለው ሰጧት፡፡ አባታቸውም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል ባየ ጊዜ ልጁ እንደሆነ ዐወቀና መሪር ዕንባን አለቀሰ፡፡ ሁሉም አብረው ተላቀሱ፡፡ የሮም ከተማ ሽማግሌዎችና ሕዝቡም ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ሰባት ቀን ሲሆናቸው ሐምሌ 16 ቀን ዐረፉ፡፡ እናታቸውም ባማሩና በተዋቡ ንጹሕ ጨርቆች እንዲገነዙ ስታደርግ ወዲያው ታመመች ነገር ግን አባታቸው በእራፊ ጨርቃቸው እንዲገንዟቸው ያዘዟቸውን አስታውሰው ቀድሞ በለበሱት እራፊ ጨርቅ ሲገንዟቸው ተመልሳ ዳነች፡፡ የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስርአተ ዋዜማ ዘሀምሌ ቅዱስ ገብርኤል
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ዋዜማ በ1-
ሃሌ ሉያ እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት፤እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐት፤ ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ኢይምፃአ ሞተ ላህም ወኢብድብድ በሰብእ፤ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ ኢይኩን ሕፀተ ማይ ወኢአባረ አክል፤ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ፤ወልደ አንጌቤናይት
@esate_yarade
@esate_yarade
አመላለስ፦
ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ/2/
አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናይት/4/
@esate_yarade
@esate_yarade
ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
ሰአል ለነ ሕፃን ቅዱሱ ለእግዚአብሔር ሰአል ለነ ሕፃን
@esate_yarade
@esate_yarade
እግዚአብሔር ነግሰ፦
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ ደምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት፤ኢፈርሕዎ ለሞት ቅዱሳን
@esate_yarade
@esate_yarade
ይትባረክ፦
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ ወስምዖሙ አጥፍዑ ኃይለ እሳት ወቦዑ መንግሥተ ሰማያት
@esate_yarade
@esate_yarade
ስቡውኒ፦
ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናይት አጽምዑ መንግስተ ወኮኑ ሰማዕት ሕፃን ወእሙ
@esate_yarade
@esate_yarade
ሰላም፦
እንዘ ሕፃን አዕበዮ እግዚአብሔር ፣ወፈነዎ ብሔረ ጽልመት፤ ኢያውዓዮ ውኂዘ እሳት፤ለሕጻን ሀቦ ሞገሰ፤ሖረ ወገብዓ በሰላም
👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@esate_yarade👈
👉@esate_yarade👈
👉@esate_yarade👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@esate_yarade
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
-ቃልህ መረቅ ነው ይጠግናል
-ቃልህ መቀነት ነው የልብን ወገብ ያጠብቃል
-ቃልህ የሚያንፅ ነው ትዳርን ይሰራል
-ቃልህ የፍቅር እሳት ነው ቤትን ያሞቃል
-ቃልህ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነው ጥምን ይቆርጣል
-ቃልህ ዘይት ነው ያለመልማል
-ቃልህ ብርሃን ነው ጨለማን ያርቃል
-ቃልህ የእውቀት መሠረት ነው ህፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን ረድቶ በትዕቢት እግዚአብሔርን የሰደበውን ንጉሥ ሰናክሬምንና 185,000 ሠራዊቱን በአንዲት ሌሊት ጨርሶ በመግደል ታላቅ ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አባ ሖር ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡
አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልንና ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም በሆነ ተአምር ረድቶታል፡፡ ከጌታችን ልደት 700 ዓመታት በፊት ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር፡፡ ደጋጓቹ ነገሥታት ዳዊትና ሰሎሞን ካረፉ በኋላ የሕዝቅያስን ያህል ቅንና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሠም፡፡ ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት፡፡ ወደ አካባቢውም መጥቶ ከቦ አስጨነቀው፡፡ ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር፡፡ የሠራዊቱም ብዛት ከ185,000 በላይ ነውና ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደማይችለው ዐውቆ መልእክተኛ ላከበት፡፡ ‹‹ግብር እገብርልሃለሁ፣ የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ፣ ነገር ግን ሀገሬን አታጥፋ፣ ኢየሩሳሌምን አታቃጥል፣ ሕዝቤንም አትግደል›› ብሎ ለመነው፡፡ እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት፡፡ ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና በመናቅ አምላኩን እግዚአብሔርንም ተሳደበ፡፡ ‹‹ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው›› ሲል ላከበት፡፡ ሕዝቅያስም በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲሰደብ ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ፡፡ መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና ‹‹ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ›› ብሎ ለነቢዩ ኢሳይያስ ነገረው፡፡ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን መልእክት ለንጉሥ ሕዝቅያስ ነገረው፡፡ በዚያችም ሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወርዶ የሰናክሬምን 185 ሺውንም የጦር ሠራዊት በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው አደረ፡፡ በለኪሶ የነበረው ሰናክሬምም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱን ሁሉ የአስከሬን ክምር ሆኖ አገኘው፡፡ በታላቅ ድንጋጤ ሆኖ ወደ ነነዌ በመሄድ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች በሰይፍ ገደሉት፡፡ ትዕቢተኛው ሰናክሬምም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ፡፡ ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ሞገስና ረዳት ሆኖታልና የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት፣ እጅግ አከበሩትም፡፡ 1ኛ ነገ 18፡13፣ 19፡1፡፡
የሊቀ መልአክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነቱ ለሁላችን ለጥምቀት ልጆች ይደረግልን!
+ + +
ሰማዕቱ አባ ሖር፡- አባቱ ስርያቆስ በምትባል አገር ይኖር የነበረ አንጥረኛ ነው፡፡ ልጁን ሖርንም እግዚአብሔርን በመፍራት በሃይማኖት በምግባር አሳደገው፡፡ ጎልማሳ በሆነም ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት ስለመጣ አባ ሖር በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ ፈርማ ወደምትባል አገር ሄደ፡፡ በዚያም በከሃዲው መኮንን ፊት ቀርቦ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ በጽኑ አሠቃየው፡፡ ጌታችንም ከሥቃዩ ፈውሶት ተነሣ፡፡
ከሃዲ የነበረው መኮንንም ጌታችን ለአባ ሖር ያደረገለትን ታላቅ ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር በጌታችን አመነ፡፡ እርሱም በማመኑ በሌላ መኮንን ዘንድ በተራው ብዙ ተሠቃይቶ ከነቤተሰቡ በሰማዕትነት ዐረፈና በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ይኽም ሌላኛው መኮንን አባ ሖርን ወደ እንዴና ላከው፡፡ በዚያም ከሃዲዎች በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ በመንኮራኩር አበራዩት፣ ዘቅዝቀው ሰቅለው በእሳት በጋለ ብረት ደበደቡት፡፡ መኮንኑም አባ ሖርን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የከበረች ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ ቅዱስ አባ ሖር አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ የእርሱም ማኅበርተኞቹ የሆኑ 127 ወንዶችና 20 ሴቶች አብረውት ተሰይፈው የድል አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡
የአባ ሖር ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
አወ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ❤️
👉 አንተ ሰው ትፈልጋለህ
-ልቡ ንፁህ የሆነውን
-ሀሳቡ የተቃናውን
-ማግኘት የማይለውጠውን
-ይቅርታ አድራጊውን
-ለእውነት ተቆርቋሪውን
-ተለሳልሶ የማይናደፈውን
-ለፍቅር ዋጋ የሚከፍለውን
-አድሮ የማይቀለውን
- በየወንዙ አቋሙን የማይለወጠውን
- ለጥፋቱ ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት የሚወስደውን
-ለቆዳው ሳይሆን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን
- የሃይማኖት አባቶችን የሚያከብረውን
-ለመታዘዝ ራሱን ያዘጋጃውን
- ክስና ክርክርን የናቀውን
-በገርነት የሚያዳምጠውን
- ትጋትና ትዕግስት የያዘውን
-ለመንገዱ ግብ ያለውን ሰው
አወ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ❤️ አንተ ትፈልጋለህ።
👉እኛግን አንተ እንደምትወደው ሰው አልሆንምና እባክህ የሚለውጠውን ሀይልህን ከላይ ከአርያም ላክልን ።
👉በብዙ ነገር እንመካለን ግን ሁሉም የጉም ስፍር ነው
አለ ግን የለም የሚያስብል ነው
-ገንዘብ አለ ደሰታ ግን የለም
-ጤና አለ እርካታ ግን የለም
-ሁከት አለ ማረፍ ግን የለም
-መብሉ አለ የምግብ አዕምሮቱ ግን የለም
-ትዳሩ አለ ፍቅሩ ግን የለም
👉አወ አለ ግን የለም ማለት እንዴት አድካሚ ነው።
አንተ ጌታየ እግዚአብሔርን ❤️ ግን በማንነትህ ብቻ ታሳርፋለህና
የምስጋና ነዶ ዙፋንህን ይክበበው ።
አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏
መምህር ሳሙኤል ❤️
ስለ ስስት
👉ፍሬን ዘር ይቀድመዋል፤ ፍርሃትን መገዛት ይቀድመዋል፤ ሆዱን የማይሞላም ፍትወቱን ያደክመዋል::
👉መብልን የሚያበዛ ፍትወትን ያበዛል:: የአሕዛብ ቀዳሚያቸው አማሌቅ እንደሆነ፥ የፍትወት መጀመሪያም ስስት ነው፡፡
👉የእንጨትብዛት እሳትን ያነሣሣዋል፤ የመብል ብዛት ፍትወትን ይቀሰቅሰዋል፡፡
👉 እሳት ሲጠፋ አመድ ይሆናል፤ መብልን የሚቀንሳትም ፍትወቱን ያጠፋታል፡፡
👉መብልን መውደድ ፍትወትን ስባ መርታ ታመጣለች ፤ በመጎምጀት የበሉት ከገነት ወጥተዋልና፡፡
👉መብልን ማብዛት ከባድ እንቅልፍን ያመጣል፧ የማያንቀላፉ ትሎችን (ፍትወታት እኩያትን) ያሳድጋቸዋል፡፡
👉የማይጠግብ ሆድ ውርደትን የፈለገ ነው፡፡
👉 የላመ የጣፈጠ መብልን መመኘት ልቡናን ያሰጥመዋል፡፡
👉 በቀናች ሃይማኖት ጸንቶ የሚጾም ሰው በጸሎቱ አየር ላይ እንደሚበርር እንድ ንስር ጸጉር ነው።
👉ጥጋብ ግን ዕምቀ ዕመቃት ያወርደዋል፡፡
👉የንጋት ደመና ፀሐይን ይሸፍነዋል መብልን ማብዛት ልቡናን
ይጋርደዋል።
👉የዛን መስታወት ፊትን ያጠቁረዋል ጥጋብም አስተዋዩን ያደነቁረዋል፡፡
👉ጭንጫ መሬት እሾህን ያበቅላል! የስስታም ሰው ልብም ክፋትን ይወልዳል።
👉የደነደነ ሰው በጸለቱ የከፋ ነው፤ የስስታም ሰው እውቀትም ክፋት ነው::
👉የስስታም ሰው ዓይን የመሸተኞችን ቤት ይመለከታል፤ ትጉሕ ግን የጥበብን ቃል ይፈልጋል፡፡
👉ሰፊ መረብ ጎተራን ይሞላል፤ የስስታም ሆድ ግን እስኪቀደድ አይሞላም፡፡
👉ደካማ ሥጋህን አትራራለት፤ አንተ ከተንከባከብኸው በአንተ ላይ በጠላትነት ይነሣብሃልና! የተለጎመ ፈረስ እንደሚታዘዝ ሥጋችንም ከገራነው ታዛዥ ይሆናል፤ ፈጽሞም አይናወጽም፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
ሐምሌ 11/2016 #ቅድስት_ሐና
#ቅዱስ_ያሬድ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለቅዱሣኑ #ለቅድስት_ሐና እና #ለቅዱስ_ያሬድ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉ቅዱስ ያሬድ #ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን ክብራችን ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን?
👉አንደበቱ ጣፋጭ ልቡናው #የቅድስና_ማሕደር ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ
👉 #ቅዱስ_ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ሙሉ አካሏ ነው ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ
👉 #ቅዱስ_ያሬድ በሕፃንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ #እግዚአብሔር ምንም ትምሕርት ባይገባው ፆምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር
👉ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ #ማይ_ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና
👉ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር
👉ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ #ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት
👉ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ #ቅዱስ_ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላታል
👉 #ቅዱስ_ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት አምስት ያሕል መጻሕፍትን ፅፏል በጣና ቂርቆስ በዙር አንባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋት እንደ መላእክት በተባሕትዎ ኑሯል በተወለደ በ71 አመቱ ተሰዉሯል የአባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ #ቅድስት_ሐና እንዲሁም #ከቅዱስ_ያሬድ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️