መስከረም 22/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ዑራኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው
👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ ዕዝ ሱቱኤል.13፥39
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው ድርሳነ ዑራኤል ገፅ.26፥ምዕ 4
👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ምእመናን ሆይ
ላለው ይጨመርለታል
ለምን ይጨመርለታል ? ይመስለኛል ይህን የሚጠይቅ
መቼም ነግዶ የከሰረ ሰው የተናገረው ይመስላል
ላለው ይጨመርለታል ማለት ምን ማለት ነው ?
ንባቡን ለያዘ ትርጓሜ ይሰጠዋል
ትርጓሜ ለያዘ ምስጢር ይሰጠዋል
ምስጢሩን ለያዘ ተግባሩ ይሰጠዋል
ተግባሩን ለያዘ ፀጋ ይጨመርለታል
ፀጋው ለተጨማለት መንግስተ ሰማያት ይጨመርለታል
ማለት ነው።
ድንግልናን ለያዘ ንፅህና ይሰጠዋል
ንፅህናን ለያዘ የነፍስ ይሰጠዋል
የነፍሱን ለያዘ ወህደት ይሰጠዋል
ሀይማኖት ለያዘ ክብር ይሰጠዋል
ክብሩን ላገኘ የበለጠ የክብር ክብር ይሰጠዋል
ከሌለውማ የለውም አንድ ናት ያለችው
አንዷን ሃይማኖት ላጣ በአንዷ በሀይማኖት
የሚሰጠው ክብር ሁሉ ይወሰድበታልማለት ነው
ላለው ይሰጠዋል ማለት ይህ ነው
አዳም በገነት ሀይማኖት ነበረው
ልጅነት ተጨመረው በልጅነቱ አደገ
ሲያጣው ተወሰደበት
እንንደዚያ ነው ላለው ይሰጠዋል ማለት
ኑሮን እንዲጨመርልን ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
ጨለማ ሲበዛ ድንጋይ ይደበቃል፣
ከዋክብት ግን ይደምቃሉ፥
መከራ ሲበዛ ቅዱሳን ይገለጣሉ፣
ኃጥአን ግን ይደበቃሉ፦
ጨለማ ለኮከብ መድመቅያው ነው፣
ለድንጋይ ግን መደበቅያ ነው።
መከራ ለክርስቲያን መድመቅያው እና መብዣው ነው።
ክርስቲያንን የሚያበዛው መከራ ነው።
ክርስቲያንን የሚያሳንሰው ኃጢአት ነው።
ከ በደል ከኃጢአት ክርስቶስ ይጠብቀን🙏
#መስከረም_19
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ #ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት የወጣበት መታሰቢያው ነው፣ የከበረ #ገዳማዊ_ቂርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው እና የኢትዮጵያ ንጉሥ የናዖድ ልጅ የከበረችና #የተባረከች_ሮማነ_ወርቅ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘአርማንያ
መስከረም ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት የወጣበት መታሰቢያው ነው።
ይህም በንጉሥ ድርጣድስ ዘመን በአርማንያ አገር ራሱን ባሪያ አድርጎ ይኖር ነበር። ይህም ንጉሥ ከሀዲ ነበርና ዕጣን ሊዐሳርግ ወደ ጣዖቱ ቤት ሲገባ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጠርቶ ለአማልክት ዕጣን እንዲአሳርግ አዘዘው። ቅዱሱ ግን የንጉሡን ትእዛዝ አልሰማም ስለዚህም እጅግ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ከዚህም በኃላ ጥልቅ ከሆነ ጉድጓድ ውስጥ ጣለው በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ።
በንጉሡ አዳራሽ አቅራቢያም አንዲት አሮጊት ነበረች እርሷም እንጀራ እየጋገርሽ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በውስጡ ከአለበት ጉድጓድ ሁል ጊዜ ጣይለት የሚላትን ራእይ አየች። ይችም አሮጊት እንዲህ እያደረገች እንጀራንም እየጣለችለት እስከ ዐሥራ አምስት ዓመት ፍጻሜ ኖረች።
በዚያም ወራት ይህ ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሎችንና ቅድስት አርሴማን ገድሎ ሥጋቸውም በተራራ ላይ ተጣለ። ሰይጣንም በንጉሥ ድርጣድስ ላይ ተጫነ እግዚአብሔርም የተፈጥሮ መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች ብዙዎቹን ሰይጣን ተጫነባቸው በቤተ መንግሥት ውስጥ ታላቅ ኀዘንና ጭንቀት ሆነ።
የንጉሡ እኅት ግን በሌሊት ራእይ ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ ውስጥ ካላወጣችሁት አለዚያ አትድኑም እንደሚላት ሰውን አየች ለወገኖቿም ነገረቻቸውና እንርሱም ሒደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን ከጎድጓድ አወጡት በዚያን ጊዜም ቅዱሳት ደናግልን ሥጋቸውን ገንዞ በመልካም ቦታ አኖራቸው ከዚያም በኃላ ንጉሡንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም ረወሳቸው። ዜናውም ሁሉ በዕረፍቱ ታኅሣሥ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቂርቆስ_ገዳማዊ
በዚህችም ቀን በሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ዘመን የሆነ የከበረ ገዳማዊ ቂርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
ይህም ቅዱስ ሰው ከከሀዲው ንጉሥ ከመርቅያን በሸሸ ጊዜ በከፍተኛ ተራራ ላይ በብቸኛነት ተቀመጠ በውስጡም አራዊት የኖሩበታል ምግቡንም ከእግዚአብሔር ለመነ አጋዘንም በየሦስት ቀን ወደርሱ እንድትመጣ ወተቷንም እንዲጠጣ አዘዘለት በእንዲህ ያለ ሥራም ዐሥር ዓመታት ኖረ።
የተረገመ ሰይጣን ግን በተጋድሎው በቀና ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ፈተና ሊፈትነው ጀመረ ያስፈራው ዘንድ በጥቁር ባሪያ አምሳል የሚመጣበት ጊዜ አለ ደግሞም በብዙ ሠራዊትና በፈረሰኞች አምሳል ሁነው ይዘው ያሥሩታል በጅራፍም ገርፈው በእግሮቹ ይጎትቱታል ሰይጣናት እንደሆኑ በአወቀ ጊዜ በመስቀል ምልክት በላያቸው ሲአማትብ ያን ጊዜ ሸሹ።
በአንዲትም ዕለት በሌሊት ሲሰግድ በታላቅ ከይሱ አምሳል በአንገቱ ላይ ተንጠለጠለና በፊቱ ውስጥ ሊተነፍስበት ፈለገ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ርዳታን ለመነ መልአኩን ልኮ አዳነው።
የዕረፍቱም ጊዜ ሱቀርብ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ሒዶ ሥራውን ሁሉ ነገረው ከዚህም በኃላ ወደ በዓቱ ተመለሰ ሊቀ ጳጳሳቱም መገነዣውን እንዲያዘጋጁ ሦስት ኤጲስቆጶሳትን ወደርሱ ላከ ወደ በዓቱም በሔዱ ጊዜ ታሞ አገኙት ነፍሱም ከሥጋው በምትወጣ ጊዜ ለመነገር የማይቻል ታላቅ ክብርን ተመለከቱ በበዓቱም ውስጥ ቀበሩት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ሮማነ_ወርቅ
በዚህችም ቀን የከበረችና የተባረከች ሮማነ ወርቅ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።
ይህቺ ቅድስት እናት ኢትዮጵያዊት ናት። የንጉሥ ልጅ ስትሆን አባቷ አፄ ናዖድ እናቷ ደግሞ እሌኒ (ወለተ ማርያም) ይባላሉ። ወንድሟ ደግሞ አፄ ልብነ ድንግል ይባላሉ።
በቤተ መንግስት ውስጥ ብታድግም መንፈሳዊነቷ የገዳም ያህል ነበር። መጾምና መጸለይን የምትወድ ድኆችንና ችግረኞችን የምትጐበኝ እና ከተባረከ ትዳሯም ቅዱስ ላዕከ ማርያምን አፍርታለች። አብያተ ክርስቲያናትን ከማነጽ ባለፈ የነዳያን እናትም ነበረች። በክርስትናዋ ፈጣሪዋን ደስ አሰኝታ በዚህ ቀን ዐርፋለች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)
የ8ኛው ሺ እመቤት ፦
ቅድስት ፀበለ ማርያም መስከረም 18 ዓመታዊ በዓሏ ነው፦
ንህድ ክብርት እናታችን ቅድስት ፀበለ ማርያም ባለ ብዙ ገብረ ተአምረኛ ስዕለት ሰሚ የሆነች በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኖረች በ8ኛው ሺ የተገለጠች ኢትዮጰያዊት ፃድቅ ናት።
የእመቤታችንን የድንግል ማርምን ስም የተሸከመች ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሀ ሰው ተመስሎ ቢለምናት ቁራሽ እንጀራ ሰጥታ ያበላች አብራማዊት እናት ናት።
ከፆምና ከስግደቷ የተነሳ በወገባዋ ያለው ጠፍር ሰንሰለት ስጋዋን ቢቆራርጠው ሰው እንዳያውቅባት መሬት ቆፍራ ስጋዋን የቀበረች በእንባዋ ብዛት መሬቱ ቢርስ በደረቅ አፈር የለወሰች በራሷ ላይ የጨከነች ሰማይት ናት።
የቅድስና ማዕዛዋ አርያም የሚሸት ሱራፌልና ኩሩቤል ሊሸከሙት ያልቻሉትን የድንግል ማርያምን ልጅ አማኑኤል በደሀ ተመስሎ የዲንጋይ መወርወሪያ ያህል በጀርባዋ የተሸከመች ከጀርባዋም ሲወርድ ፀበል ያፈለቀላት ናት።
በዋሻው እንደ ሊባኖስ ዝግባ ቀጥ ብላ ስትፀልይ ነብሮች መጥተው እግሮቿን ይልሱላት ነበር እንደ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ከባህር ገብታ ትለምን ትፀልያላች ከክብሯም የተነሳ በገነት ያሉ ነፍሳት የሕይወት ፍሬ ፤ የገነት ፍሬ ይሏታል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ስሜን የተሸከምሽ ፀበለ ማርያም ሆይ ብላ አቅፋ ስማታለች።
ከጫጉላ ቤት እንደ ገብረ ክርስቶስ ወጥታ መንናላችና ለሰማያዊ ሙሽራ ለክርስቶስ ታጭታለችና መናኝ ናት በራሷ ላይ ጨክናለችና ሰማይት ናት የክርስቶስ ወንጌል ከአባ ቶማስ በሚገባ ተምራለችና ሐዋሪያዊት ናት ።
በረከቷ በሁላችንም ይደርና እንኳን ፀበሏን እምነቷን ያገኘ ስሟን የጠራ የለመነው ይደረግለታል ምስሏን ከቤቱ ያስገባ ከጭንቀት ትጠብቀዋለች ለመካኖች ልጅ ለእሙማን ፈውስ ከአይን ጥቅሻ ፈጥና የምትሰማ ስለት ሰሚ ተአምረኛ እናት ናት በዓለም ሁሉ ዝናዋ እየተሰማ ነው በየፀበል ቤቱ በየገዳማቱ ስሟ የታወቀ ሆነ።
የታመማችው ለምኗት ለተቸገራችው ተማፀኗት ፀሎታችውን ለመስማት የሴኮንዶች ቁርጥራጭ እንኳን አይቀድሟትም
ይህን በጥንቃቄ የተሳለ ምስሏን ያሰሩት ወለተ መድህን ከፈረሳይ ሀገር እና ኪዳነ ቃል ከኢትዮጰያ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግዲያ ቅድስት ፀበለ ማርያምን በሚገባ የሚገልፃትን ምስሏን ያሰሩ ባለታሪኮች ሆነዋል።
እስቲ በዕለተ ቀኗ እናታችን ቅድስት ፀበለ ማርያም በረከቷ ከቤታችን ይገባ ዘንድ ከበረከቱ ተሳተፉ።
❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ስለ ቅድስት እሌኒ በዐርኬው ላይ
✍“ሰላም ለእሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወሰዳ ለዘሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ አንግዳ ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ”
❖ የመንፈስ ቅዱስ ምክር በወሰዳት ጊዜ ኤልዳ ወደ ተባለች የሕይወት ምድር የኼደች ለኾነች ለዕሌኒ ሰላምታ ይገባል፤ በአደባባይዋ ፊት መስቀልን በመንካት የዳነውን በድን በበረሓ ወድቀኽ የተገኘኽ አንተ እንግዳ ከወዴት ነኽ አለችው በማለት መስቀሉ ከወጣ በኋላ ስለተደረገላት ተአምር ጽፏል፡፡
✍"ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኀኒት ኀይልነ ወጸወንነ"
ምንጭ
✍ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
☞መስከረም 16 ድንጋይ ጎርሶ የኖረ የአባ አጋቶን የዕረፍቱ መታሰቢያው ነው፡፡
☞ ይህን ቅዱስ ታላቅ ጻድቅ
ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ30
ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል:: ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት "ክምረ ክምር
ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ ደግነቱ አርምሞው ትሩፋቱ ከመነገር
በላይ ነው:: በነበረበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት
ነው::
☞ታላቁ ገዳማዊ አባት አጋቶን የታላቁ መቃርዮስ ቅዱስ የመንፈስ ልጅ ነው::
ገዳመ አስቄጥስ እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን ስታፈራ ይህ አባት ቅድሚያውን
ይይዛል:: ምንም በብዛት የሚታወቀው በአርምሞው (በዝምታው) ቢሆንም ባለ
ብዙ ትሩፋት አባት ነው:: የሚገርመው የቀደሙ አባቶቻችን የፈለገውን ያህል
መናኝ ቢሆኑም የሰው ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም:: "ሊሠራ የማይወድ አይብላ"
የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ መሠረት አድርገው ከተጋድሎ በተረፈቻቸው ሰዓት
ሥራ ይሠራሉ:: አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ምናኔ ሥራ መፍታት አይደለምና
ሰሌን ዕንቅብ ሠፌድ የመሳሰለውን ይሠፋሉ:: ታላቁ አባ አጋቶንም በአንደበቱ
ድንጋይ ጐርሶ በእግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንቅቦችን ይሠፋ ነበር::
☞ ቅዱሱ
የሰፋውን ወደ ገበያ ይወጣል በጠየቁትም ዋጋ ሽጦት አንዲት ቂጣ ይገዛል::
የተረፈውን ገንዘብ ግን እዚያው ለነዳያን አካፍሎት ይመጣል እንጂ ወደ ገዳሙ
አይመልሰውም::
☞አንድ ቀን እንደልማዱ የሠፋቸውን እንቅቦች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሔድ
መንገድ
ላይ አንድ የኔ ቢጤ ወድቆ ያገኛል:: እንደ ደረሰም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ
ይለምነዋል:: አባ አጋቶን ከእንቅቦቹ ውጪ ምንም ነገር አልነበረውምና "እንቅቡን
እንካ" አለው:: ነዳዩ ግን ወይ የሚበላ ካልሆነም ገንዘብ እንደሚፈልግ
ይነግረዋል:: ወዲያው ደግሞ "የምትሠጠኝ ነገር ከሌለህ ለምን ወደ ገበያ
ተሸክመህ አትወስደኝም?" አለው:: የነዳዩ አካል እጅግ የቆሳሰለ በመሆኑ
እንኩዋን ሊሸከሙት ሊያዩትም የሚከብድ ነበር:: ጻድቁ ግን ደስ እያለው
ያለማመንታት አንስቶ ተሸከመው:: ከረጅም መንገድ በኋላ ከገበያ በመድረሳቸው
አውርዶ ከጐኑ አስቀመጠው:: ያ ነዳይ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ቢለምንም
የሚዘከረው አጣ:: አባ አጋቶን አንዷን እንቅብ ሲሸጥ "ስጠኝ?" ይለዋል::
ጻድቁም ይሠጠዋል:: እንዲህ "ስጠኝ" እያለ የእንቅቦችን ዋጋ ያ ነዳይ
ወሰደበት:: አባ አጋቶን ግን ምንም ቂጣ ባይገዛም በሆነው ነገር አልተከፋምና
ሊሔድ ሲነሳ ነዳዩ "ወደ ቦታየ ተሸክመህ መልሰኝ" አለው:: አባቶቻችን
ትእግስታቸው ጥግ የለውምና ጐንበስ ብሎ በፍቅር አንስቶት አዘሎት ሔደ::
ካነሳበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ይወርድለት ዘንድ ጻድቁ ቆመ:: ነዳዩ ግን አልወርድም
አለ:: ትንሽ ቆይቶ ግን ለቀቀው ሊያየው ዞር ቢል መሬት ላይ የለም:: ቀና ሲል
ግን ያየውን ነገር ማመን አልቻለምና ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ:: ነዳይ መስሎ
እንዲያ ሲፈትነው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበርና ክንፎቹን
ዘርግቶ በብርሃን ተከቦ በግርማ ታየው ከወደቀበትም አነሳው:: "ወዳጄ አጋቶን!
ፍሬህ ትእግስትህ ደግነትህ ግሩም ነውና ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎት
ተሰወረው:: ጻድቁም በደስታ ወደ በዓቱ ሔደ::
☞የጻድቁ የአባ አጋቶን የጸሎቱ በረከት አይለየን
+በበረሀው ጉያ ውስጥ ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ
+15-1-2017
ምእመናን ሆይ
ሰዎች በሌሎች ስለተገፉ ስለተነቀፉ ስለተሰደቡ ብቻ
ንዑዳን ክቡራን ናቸው ብላችሁ እንዳታስቡ
ታዲያ ንዑዳን ክቡራን መባላቸው እንደምንድን ነው ?
ብላችሁ ብትጠይቁ
ክርስቶስ ባስቀመጠልን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች
1ኛ ነቀፋው በእርሱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን
2ኛ የሚነቀፍበት የውሸት ሲሆን
ከእነዚህ ዉጭ በሆነ በሌላ ምክንያት
በሰዎች ዘንድ ቢነቀፍ ቢሰደድ ብፁእ አይደለም
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
++ የደመራው ምሥጢር ++
እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክትነት ነው፡፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ በታዘዘ ጊዜ የሞርያን ተራራ የመረጠው እግዚአብሔር በተራራው ላይ ካሳየው ብርሃን የተነሣ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ መስቀልም የድኅነታችን ምልክቶች ናቸው፡፡ የአሮንና የሙሴ በትሮች፣ የይስሐቅ ቤዛ የሚኾን በግ የተገኘባት ዕፀ ሳቤቅ ደግሞ የእመቤታችንና የመስቀል ምልክቶች ነበሩ፡፡ ወደ ፊት የምንወርሰው መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነው፤ እርሱን ደግሞ ያገኘነው ከመስቀል ላይ ነው፡፡
ጥንተ ጠላት ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ቅዱስ መስቀሉን አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡ በመሠረቱ ለሰይጣን ምሥጢሩ ስለማይገባው ነው እንጂ የመስቀሉ ትክክለኛ መቀበሪያ ሥፍራ የምእመናን ልቡና ነው፡፡ ቀራንዮ ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡
ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡ ይህች ሴት ቤቷ በሀብት፣ በንብረት ሞልቶ በነበረበት ጊዜና በገረድ፣ በደንገጡር በምትንቀሳቀስበት ወቅት ምን እንደ ሠራች አልተመዘገበላትም ነበር፤ ከክብሯ ወርዳ በተጣለችበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ለሚፈልገው ሥራ ምቹ ኾና ተገኘች፡፡ እርሷ በተጣለችበት ባዕድ አገር ውስጥ ኾና የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች፡፡
መስቀልና ደመራ እንዲህ ነበር የተገናኙት፡፡ ደመራው ለመስቀሉ መገኘት፣ መስቀሉም ለደመራው መሠራት ምክንያት ናቸው፡፡ በዚህ አንጻር መለኮትና ትስብእት በአንድነት መደመራቸው መስቀሉ እንዲሠራ ምክንያት ኾነዋል፡፡ አምላካችን ሥጋ ለብሶ ‹ክርስቶስ› በሚል የተዋሕዶ ስም ሲጠራ ለመከራ መዘጋጀቱን እንረዳለን፡፡ መስቀሉ የሥጋ ብቻ ነበረ፤ አሁን ግን መለኮትም በሥጋ ባሕርይ የመስቀሉ ተካፋይ ኾነ፡፡ ይህም የደመራው ውጤት ነው፡፡ መለኮት አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን መስቀል የተሸከመ ሥጋን ሲዋሐድ መስቀሉን አስወግዶ አልነበረም፡፡ ይኸው በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከምነው መስቀል ነው፡፡ ሥጋ ዓቅም አጥቶ መስቀሉን ከትከሻው ላይ ሳያወርድ ለዘመናት የተጓዘውን ጕዞ መለኮት ኀይል ኾኖት ድካሙን ሳይለቅ ኀያል፤ ኀይሉን ሳይለቅ ደካማ ኾነ፡፡ መስቀል ትርጕሙ መከራ ቢኾነም ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያመጣውና ሰው ሲያመጣው ግን ትርጕሙ ይለያያል፤ ሰው ያመጣው መስቀል ኹላችንን ለመከራ፣ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር መስቀል ግን መከራነቱ ለሰይጣን እንጂ ለእኛ ሕይወታችን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል ብሂል ዕፀ ሕይወት ብሂል፤ መስቀል ማለት የሕይወት ዛፍ ማለት ነው›› በማለት የመስቀልን ትርጕም ነግሮናል፡፡
አዳም ከገነት ሲወጣ በመላእክት እንዲጠበቅ የተደረገው የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ኹላችንም እንደ ተጎዳን በዕፀ ሕይወቱም ተጠቃሚዎች ኾነናል፤ አስቀድመን በአዳም መከራ እንደ ተባበርን አሁን ደግሞ በደስታው እንተባበራለን፡፡ ሞትም ሕይወትም አንድ አድርጎናል፡፡ የክርስቶስ መስቀል ኹሉንም በሕይወት አስተባብሯልና፡፡ በአንጻሩ ሰውና ዲያብሎስን ለያይቷል፡፡ የኀጢአት ቁራኝነትን አጥፍቷል፡፡ ጌታችን በማኅፀን ሲፀነስ ጀምሮ የእኛን መስቀል መሸከም ሲጀምር የእርሱ የኾነውን ለእኛ ስለ ሰጠን ከሰይጣን ጋር መለያየታችን በመስቀሉ ተረጋግጧል፡፡ የአምላካችን መስቀል ምልክቱ ደመራ መኾኑ የእኛን ወደ እርሱ መሰብሰብና የጠላታችንን መበተን የሚያረግጥልን ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወብየ ካልዓትኒ አባግዕ እለ ኢኮና እምዝንቱ ዐፀድ ወኪያሆንሂ ሀለወኒ አምጽኦን ዝየ፤ ከዚህ በረት ያልኾኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ላመጣቸው ይገባኛል›› በማለት ሊሰበስበን እንደ መጣ ነግሮናል /ዮሐ.፲፥፲፮/፡፡ መስቀሉ ፍጥረት አንድ ደመራ ኾኖ የተሠራበት ስለ ኾነ በደመራ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ኾነ፡፡
መስቀሉ አንድ ደመራ ያደረጋቸው ፍጥረታት
፩. ነቢያትና ሐዋርያት
ነቢያት የሚባሉት ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉ አባቶች ሲኾኑ፣ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የወንጌልን የምሥራች እንዲነግሩ የተላኩ አባቶች ደግሞ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የኾነ ነቢይ የለም እንጂ ነቢይ የኾነ ሐዋርያ አለ፡፡ ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣ በክብር እና በግብር የማይገናኙ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መንፈሰ ረድኤት የተሰጣቸው ነቢያት ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ ልደት ለማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ ሐዋርያት ግን ኹሉንም አንድ አድርገው ይዘዋል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› በማለት አጕልቶ የተናገረው /ዮሐ.፲፥፲፰/፡፡ ነቢያት በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን መንግሥት በመፈለግ ብዙ ደክመዋል፡፡
ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት፣ ሐዋርያትን በበጋ ገበሬ ይመስሏቸዋል፡፡ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ፣ ታቹ ውሃ ኾኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባም ሚስቱ ጨምቃ ያቆየችለትን ጐመን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፡፡ ነቢያትም በዚህ ዓለም በጣዖት አምላኪ ነገሥታት፣ በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ኖረው ሲሞቱም ሲዖል ይገባሉ እንጂ ገነትን አይወርሱም ነበር፡፡ የበጋ ገበሬ በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ከቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ ጠላው በማቶት፣ ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ሐዋርያትም ልጅነትን አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፤ በሔዱበት ኹሉ ተአምራትን እንዲያደርጉ፣ ልጅነትንም እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
እስኪ ከፍጠረታት እንማር
ሸረሪትን ተመልከቱ
ትደክማለች ትለፋለች
ከሴት ብልሀት ይልቅ የተከበረችው
እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ
ድሯን በግድግዳ ላይ ታድራለች
ነገር ግን ሥራዋ ልክ እንደኛ የሚጠቅም አይደለም
የማይጠቅም በመሆኑ የሚያከብራት የለም
ለራሳቸው ብቻ የሚደክው
ለራሳቸው ብቻ የሚለፉ ሰዎችም
ልክ እንደዚች ሸረሪት ናቸዉ ።
ለራሳቸው ብቻ የሚደክሙ የሚለፉ ሰዎች
እኛ ራስ ወዳድ የምንላቸው
ልክ እንደዚች ሸረሪት ናቸው
ሁሌም ከሌሎቹ ይለቅ ለራሳቸው ይደክማሉና
ሁሌም ከሌሎቹ ይልቅ ለራሳቸው ይለፉሉና
ለሌሎች የሚሰጡት ረብ(ጥቅም) የለምና።
በመረዳዳት እንኖር ዘንድ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
☞መሰከረም 15 የቀዳሚ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍለሰት ነው፡፡
☞ይኸውም ከ 300 ዓመታት በኃላ ጻድቁ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ከነገሠ በኃላ
ሃይማኖት በተመለሰች ጊዜ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው ባለበት አቅራቢያ
በገማልያል ቦታ ለሚኖር ሉክያኖስ ለተባለ አገልጋል ተገለጠለትና ስለ ሥጋው
ነገረው፡፡
☞ሉክያኖስም ወደ ኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ሄዶ ተናገረ፡፡ ኤጴስ ቆጶሳት፤ካህናትና
ዲያቆናት ሁሉ መጥተው ሥጋውን ቆፍረው ሲያወጡት በአካባቢው ታላቅ
ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ አካባቢውንም እጅግ በጎ መዓዛ ሞላው ፡፡ ከሥጋውም እጅግ
ብዙ ተአምራት ተገለጠ፡፡ በሽተኞች ተፈወሱ ደንቆሮዎችን እንዲሰሙ አደረገ፡፡
ዕውራሮችን አበራ፡፡ ይህ የሆነው በዚች በመስከረም 15 ቀን ነው፡፡
☞በቅዱስ ወንጌል ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን ያዩታል
የተባለው በእርሱ ተፈጸመ፡፡ በሥጋው ሕያው ሆኖ እያለ በዓይቹ የተመለከተ ይህ
እስጢፋኖስ ነው፡፡
☞ከጥንት ጀምሮ የነበረ የአብን ልጅ በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ ግርማ
በአርያም የተመለከተ የቃልንም መኖር ያስተዋለ ይህ እስጢፋኖስ ነው፡፡ ይህን
አይቶም አልፈራም፡፡ በፍጹም ደስታ ጮኸ እንጂ፡፡ ሁሉ በላይ እንሆ እኔ ዛሬ
ሰማያት ሁሉ ተከፍተው የእግዚአብሔር ልጅም ከፍጥረታት ሁሉ በላይ በታላቅ
ክብር በቀኝ ተቀምጦ አየሁት ያለ ይህ እስጢፋኖስ ነው፡፡
☞የክርስቶስ ወዳጅ አባታችን ድንግሉ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሦስት
አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
☞አንደኛው ስለ ድንግልናው፤ሁለተኛ ሰለ ሰማዕትነቱ፤ሦስተኛው ሰለ
አገልግሎቱ ነው፡፡
☞ወንድሞቼ ሆይ ዛሬም እንለምን፤ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስም
በደላችንን ይቅር እንዲለን እናንጋጥ፡፡ ኃጢአታችንን እንዲደመሰስልን፤ ንጹሕ
ልብን ይሰጠን ዘንድ የሰማዕታት መጀመሪያ እንደተባለው እንደ ሊቀ ዲያቆናት
ቅዱስ እስጢፋኖስ የእኛንም የወንድሞቻችንም ኃጢአት እናስተሠርይ ዘንድ ትጉ፡፡
☞በዚህች ዕለትም በጥንቃቄ በዓሉን በየአመቱ በየወሩ በተለይም በሥጋው
ፍለሰትና በመሰከረም 15 ቀን እና በዕረፍቱ ቀን ጥር 1 ከመፃ ከኃጢአት ከሀሰት
በመራቆ እንደ መንፈሳዊ ታላቅ በዓል እንደ ትንሣኤ ዕለት አድርገን የተባረከች
የመታሰቢያውን ዕለት እናክብር፡፡
☞በዚህች የተከበረች ዕለት ሰውነታችንን በምስጋና በጸሎት በስግደት
በምጽዋት የሰማዕታት የመጀመሪያው አባታችን ቅዱስ እስጢፋኖስ የስጋው
ፍልሰት ተፈጽሞበታል እና፡፡
☞ሰለ ኃጢአት ይቅርታን ያደርግ ዘንድ በሰማዕታት መጀመሪያ በተመረጠው
በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት በመንግሥተ ሰማይ በድኅነት ወደብ ያሳድረን ዘንድ
በዓሉን እናድርግ፡፡
☞የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማለጅነት የቀዳሚ ሰማዕት
የቅዱስ እስጢፋኖስ የጸሎቱ በረከት አይለየን፡፡
☞(ገድለ ቀዲሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞14-1-2017
አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳም መነኮሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩአቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኮሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኮሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኮሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፡፡ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፡26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡
ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ ገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፣ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡
አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኃኔዓለምን ጽላት እንዲያወጣላቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኃኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጌታችንን እግር ያጠቡት አቡነ አብሳዲ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡
በጣና ደሴት ላይ ከሚገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ነው፡፡ ይህም አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንድ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡ ይህ ዋሻ ለብዙ ዘመናት አንድ ታላቅ አባት የጸሎት በዓት አድርገውት ‹‹አትማረኝ›› እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ያሳይ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ፣ አትማረኝ፣ አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?›› አሏቸው፡፡ ያም አባት ‹‹አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው ‹አትማረኝ› እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው›› በማለት መለሱላቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ‹‹እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው ‹ማረኝ› እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም ‹‹ማረኝ›› እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ ያሳይ ድንጋዩን እንደጀልባ ተጠቅመው እየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸው ያ አባት በውኃ ላይ በእግራቸው እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፤ እባክዎን እንደገና ያስተምሩኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ሐይቁን በእግራቸው እረገጡ እስኪሄዱ ድረስ ጽድቃቸው የተገለጠውን የእኚህን አባት መብቃት ተመልከተው ‹‹አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል›› ብለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የአቡነ ያሳይ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
መዝገበ ቅዱሳን
ምእመናን ሆይ
ቅድስት ድንግል ማርያም
የኖኅ የድኅነት ማደሪያ ፣
ሦስት ገዥዎች እነርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በውስጧ የከተሙባት የአብርሃም ድንኳን ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግታ የፍጥረቱ ሁሉ ንጉሥ የሚጠጋባት የያዕቆብ የእሳት መሰላል ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያደረባት የሙሴ የምስክር ድንኳን ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የኢያሱ የምስክር ሐውልት (የማዕዘን ድንጋይ) ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም ያበበችና የፈራች ባለርስቶች ያወቋት የአሮን በትርና ማዲጋ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሳሙኤል የረድኤት አለት ፣ በንጉሥ ቀኝ የምትቀመጥ የዳዊት ንግሥት ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም በኪሩቤል ክንፎች የምትጋረድ የሰሎሞን መቅደስ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሕዝቅኤል የተዘጋች የምሥራቅ በር ደጅ ናት።
ደጅ :- ማለት የምሕረት መግቢያ ማለት ነው።
ምሥራቅ :- ማለት የፀሐይ መውጫ ማለት ነው። መግቢያዎቹም :- ኮከቦች ናቸው።
እነዚህም ኮከቦት:- የጻድቃን ነፍስ ናቸው።
ቅድስት ድንግል ማርያም የነፍስ ሁሉ ምግብ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አዝመራ በውስጧ ያለባት
የዮሴፍ የስንዴ መዝገብ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የኢሳይያስ የተጠማች ምድር ናት።
የእመብርሃን አማላጅነት❤️ ረድኤት በረከት አይለየን🙏
እንኳን ለከቡነ ዘርዐ ቡርክ የመታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ
ረድኤት በረከቱ ይደርብንና በዚኽች ዕለት በወርሐዊ በዓሉ ታስቦ የሚውል ብፁዕና ቅዱስ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታምር ይህ ነው።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ደብረሳን በሚባል በአንድ አገር ተወልደ መድኅን በሚባል በእግዚአብሔር ሰው ቤት ተአምራትን አደረገ ክፉ ጠላቶች ብዙጊዜ ተነሱበት ብዙ ጊዜም በእግር ብረት አሰሩት ይህ ሰው አይወድህም በሃይማኖትህም አይመስልህም ብለው ከንጉሱ ጋር አጣሉት ንጉሡም ይህን ነገር ሰምቶ አሰረው ወደ ሩቅ አገር ወሰደው በዚያ እንዲያስቀምጡት አዘዘ የታዘዙትም ሰዎች ትእዛዙን ሰምተው አስረው ወስደው ለአስር ወራት ያህል በዚያ አስቀመጡት ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የሃይማኖቱንና በእርሱ መማፀኑን አይቶ ከእስራቱ ፈትቶ አወጣው በሩቅና በቅርብ ከተነሱበት ጠላቶቹ እጅም አዳነው ሌባ ከቤቱ ገብቶ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ በሰረቀበት ጊዜ ያሰው የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ እንዳያጠፋበት በወዳጁ በአባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ስም እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ጸሎቱንና ልመናውን ሰምቶ ያ ሌባ ርቆ እንዳይሄድ እጁንና እግሩን ያለ ማሰሪያ አሰረው ያም ሌባ በጫካ ውስጥ ሦስት ቀን ተቀመጠ ከዚህ በኋላ በሦስተኛው ቀን ያን ሌባ ሌላ ሰው አገኘውና እኒህን ልብሶች ከወዴት አመጣሀቸው ወዴትስ ትወስዳቸዋለህ ብሎ መረመረው ያም ሌባ ያመጣበትን ቦታና እግዚአብሔር ወደ ቤቱ እንዳይገባ ወደ ሌላ አገርም እንዳይሄድ በጻድቁ አባታችን ጸሎት አስሮ ሦስት ቀን በጫካ ውስጥ እንዳስቀመጠው ነገረው ይህም ሰው የሌባውን ነገር ሰምቶ ወደ ባለ ልብሱ ሂዶ ሌባውን እንዳገኘው ነገረው ሌባው የሠረቃቸው ልብሶቹን ባገኘ ጊዜ ደስ አለው ይህ ሁሉ ድንቅ ታምር የተደረገ በጻድቁ አባታችን ጸሎት እንደሆነ አወቀ ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ የፈለ ግዮን ግሽ ዓባይ ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ደብር ያሳተመው ገድለ ዘርዐ ብሩክ
(የተሰዋ - ይዌድስዋ)
ኤልያስ ሽታኹን
- - - - - -
ሰውነቱ ወልቋል።
ተንበረከከ አጥንቱ ከወለሉ ሲጋጭ ይሰማል።
የሚናገረው ነገር ጠፋበት።
ልጅነቱ ትዝ አለው። በጣም ጎበዝ ተናጋሪ ነበር። ዛሬ አፉን የፈታበት ቋንቋው ጠፋው።
ፀጉሩን እየጠቀለለ
"ብሬን ስጨርስ መጣሁ" አላት
ዝም አለችው።
"ደስታዬን ስጨርስ መጣሁ" አላት
ዝም።
"መልኬ ሲረገፍ መጣሁ
ጉልበቴን ስጨርስ መጣሁ
ጤናዬን ስጨርስ መጣሁ"
ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ!
ዝም አለችው።
ከውስጡ አንድ ድምጽ ሰማ
"እድሜህን ሳትጨርስ መምጣትህ ነው ደስታዬ" አለችው።
ጭራሽ ከፋው።
ዝም ብላ አየችው።
ዝም ብሎ አያት።
ሳቀ።
የልጅነቱ የአብነት ተማሪ እያለ የነበረው ስም ትዝ አለው። "ቄሴ"
እየሳቀ አለቀሰ።
የማይቆረጠው ፀጉሩ ትከሻውን ነክቶታል።
በፊት ተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነበር ጃንጥላ የሚይዝበት እጁ አሁን
በሲጋራ የሚይዝበት ጠቁሯል።
ሱሪውን ዝቅ አርጎት ሊወልቅ ደርሷል።
ለሎቲ የተበሳው ጆሮው ተደፍኗል።
ቅዱስ ዳዊት ከጠላቶቼ የተነሳ አረጀሁ እንዳለ
ገና በወጣትነቱ አርጅቷል።
ፊቱ ላይ አጥንት አለ።
ራሱን አየው።
አፈረበት በራሱ።
ጥግ ላይ የተቀመጡት ሽማግሌ ጋ አይኑ ተጋጨ። በግንባራቸው ጠሩት።...
"ጉዴ ነው" አለ በውስጡ።
"አቤት አባቴ... እንኳን መጣህላት"
"ለማን"
"ለማርያም"
"ሰምተውኝ ነበር ማለት ነው አለ" ለራሱ
"ምን ዋጋ አለው ብለው ነው...አሁንማ ከረፈደ"
"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ፍቅሩ ለምን እንደማይቀንስ ታውቃለህ ?"
ዝም አላቸው።
"በፀጋ ስለሚያየን።
በዛሬ ማንነታችን ሳይሆን በፈጠረን ፀጋ ነው የሚያየን። በልጀነት ንጽህናችን በበፊቱ ቀናነታችን በትንንሹ አግልግሎታችን ነው የሚያየው። አይኑ እስከዛሬ ከፀጋችን ተነስቶ አያውቅም።"
ልቡንም ጆሮውንም ሰጣቸው።
"በኛ ተስፋ የማይቆርጠው የልጅነት ፀጋችንን ስለሚያውቅ ነው። ሌብነትህን ሳይሆን ልጅ ሆነህ የዘመርከውን ዘማዊነትህን ሳይሆን ድሮ ፀበል የቀዳኸውን ገዳይነትህን ሳይሆን ቤተመቅደስ መጥረግህን ነው የሚያየው። እግዚአብሔር ሰውን የሚያየው በፀጋው ነው።"
"እኔ ምን አለኝና ታዲያ ?"
ካንተ በላይ ያውቅሀል።
በፀጋህ ነው የሚያይህ ባሁኑ ኃጢያትህ አይደለም። እናት ልጇ ቢታሰር አትክደውም ልጅነቱን አስታውሳ ታዝናለች። ድሮኮ ተምሮ እንደዚህ ይሆንልኛል ብዬ ነበር የማስበው ብላ ልጅነቱን ነው የምታስታውስለት። አየህ እግዚአብሔር ልጅነታችን ጋ ነው አይኑም ልቡም።
ዕንባው ወረደ።
"ልጠይቅህ" አሉት
"ገብርኤል ማርያምን ከሰላምታ በፊት ምንድነው ያላት"
ይዌድስዋ ትዝ አለው።
"ፀጋን የሞላብሽ ሰላምታ ይገባሻል"
"ጎበዝ
ማርያምም ፀጋን የሞላባት መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ናት። ሁሉንም የምታየው በፀጋ ነው። እንኳን አንተን ለሚቃወሟት ሳይቀር ሩህሩህ ናት። ለምን በልጅነት ፀጋቸው ነው የምታውቃቸው። ክፋት አታውቅም ቂም አታውቅም ለምን ፀጋን የሞላባት ናት።"
ጉልበታቸው ስር ወደቀ።
እጣን እጣን ሸተተው።
(ተፈጸመ)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 21-ብዙኃን ማርያም (የእመቤታችን የበዓሏ መታሰቢያ ነው፡፡)
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አስቀድሞ ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው ቅዱስ ቆጵርያኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
+ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ድንግሊቱ ዮስቴናም በሰማዕትነት ያረፈችው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም ይህች ዕለት የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም አርዮስን አስተምረው ለመመለስ በኒቅያ የተሰበሰቡባት ዕለት ናት፡፡ የጉባኤውም ፍጻሜ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ኅዳር ዘጠኝ ነው፡፡
+ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት ነው፡፡ (የመስከረም ዓሥራ ሰባቱን ይመለከቷል፡፡)
+ ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ዮስቴና፡- ይኽም ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሃዲና ሥራየኛ ነበር፡፡ እንዲያውም ለሥራየኖች ሁሉ አለቃቸው ነበር፡፡ በዚህ በጥንቆላ ሥራው ከመመካቱ የተነሣ ‹‹ሥራይ በማድረግ የሚስተካከለኝ ካለ ልይ እስቲ…›› በማለት ወደ አንጾኪያ አገር ሄደ፡፡ ቆጵርያኖስም አንጾኪያ በገባ ጊዜ ወሬው ሁሉ በሀገሪቱ ተሰማ፡፡ በአንጾኪያ የሚኖር አንድ ወጣት በመልኳ እጅግ ውብ የሆነችውን ወጣት ዮስቴናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄድ እያያት እጅግ አድርጎ ወደዳት ነገር ግን እርሷ የክርስቶስ ሙሽራ ናትና እሺ ልትለው ስላልቻለች ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ገንዘብ በመስጠት፣ በጉልበት በማስፈራራት፣ በሥራይ ሥራ በእነዚህ ሁሉ ሊያገኛት ስላልቻለ ወጣቱ አሁን የቆጵርያኖስን ወደ ከተማው መምጣትና ዝናውን በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት ሄዶ ዮስቴናን እጅግ አድርጎ እንደወደዳትና ሊያገኛት እንዳልቻለ ነገረው፡፡
ቆጵርያኖስም ያንን ወጣት ‹‹እኔ የልብህን እፈጽምልሃለሁ አትዘን›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ቆጵርያኖስ ድንግሊቱን ዮስቴናን እንዲያመጧት በሥራዩ የአጋንንትን ሠራዊት ላካቸው፡፡ እነዚያ በሥራይ ወደ እርሷ የተላኩ አጋንንትም ወደ ድንግሊቱ ዮስቴና በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም ምክንያቱም እርሷ ዮስቴና በጾም በጸሎቷ የጸናች ናትና ከጸሎቷ የተነሣ አጋንንቱ ተቃጠሉ፡፡ ቆጵርያኖስ በሥራዩ ኃይል ዮስቴናን ያመጡለት ዘንድ ደጋግሞ ላካቸው ነገር ግን አጋንንቱ ቅድስት ዮስቴናን በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም፡፡ ከዚም በኋላ ቆጵርያኖስ ሁሉንም አጋንንት ጠርቶ ‹‹ድንግል ዮስቴናን ይዛችሁ ካላመጣችሁልኝ እኔ ከእናንተ ተለይቼ ክርስቲያን እሆናለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሰይጣናት አለቃ ቆጵርያኖስን ሊሸነግለው አሰበና ከሰይጣናት ውስጥ አንዱን ሰይጣን በዮስቴና ተመስሎ ለቆጵርያኖስ እንዲታየው አደረገ፡፡ ሰይጣኑም አለቃው እንዳዘዘው እንዲሁ አድርጎ (ዮስቴናን መስሎ) ተዘጋጀ፡፡
ሰይጣኑም ለቆጵርያኖስ ‹‹እነሆ አሁን ዮስቴና መጥታለች›› አለው፡፡ ቆጵርያኖስም እውነት ዮስቴና የመጣች መስሎት እጅግ ደስ ብሎት ሊቀበላት ተነሣ፡፡ በዮስቴና አርአያ የተመሰለውንም ምትሀት ባየ ጊዜ ‹‹የሴቶች እመቤት ዮስቴና ሆይ! መምጣትሽ መልካም ሆነ›› አላት፡፡ ቆጵርያኖስም የቅድስት ዮስቴናን ስሟን መጥራት በጀመረ ጊዜ በእርሷ የተመሰለው ሰይጣን እንደጢስ በኖ ጠፋ፡፡
ቆጵርያኖስም በዚህ ጊዜ የሽንገላው ምክንያት ምትሐቱ ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ዐወቀ፣ አስተዋለ፡፡ በልቡም እንዲህ አለ፡- ‹‹ስሟን በጠሩበት ቦታ አጋንንት እንደጢስ የሚበኑ ከሆነ በቅድስት ዮስቴና ፊት ሊቆሙ ሊሸነግሏትስ እንዴት ይቻላቸዋል?›› አለ፡፡ ይህንንም ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠላቸው፡፡ ሄዶም ቅድስት ዮስቴናን አገኛትና ሰገደላት፡፡ እርሷም ሃይማኖትን አስተማረችውና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ሄዶ ንስሓ ገብቶ ተምሮ አምኖ ተጠመቀ፡፡ የምንኩስና ልብስንም ለበሰ፡፡ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ዲቁና ሾመው፡፡ አገልግሎቱንና መንፈሳዊ ተጋድሎውንም ባየ ጊዜ ዳግመኛም ቅስና ሾመው፡፡ ቆጵርያኖስም በተጋድሎና በአገልግሎት ከኖረ በጎ ምግባሩ፣ ሃይማኖት፣ ትሩፋቱ ከፍ ባለ ጊዜ በምዕራባዊቷ ግዛት ኤጲስ ቆጶስነት ተሾመ፡፡ ቅድስት ዮስቴናንም ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት፡፡
በግርጣግና የቅዱሳን ስብሰባ በሆነ ጊዜ ቅዱስ ቆጵርያኖስ ከጉባው አባላት አንዱ ነበር፡፡ ከብዙ ወራት በኋላም ከሃዲው ንጉሥ ዳኬዎስም ስለ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ስለ ቅድስት ዮስቴና ሰማ፡፡ ንጉሡም ወደ እርሱ አስመጣቸውና የክብርን ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣኦት እንዲሰግዱ አዘዛቸው፡፡ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ቅድስት ዮስቴና ግን የጌታችንን አምላክነት ክብር በመመስከር ጣዖታቱን ረገሙበት፡፡ ንጉሡም እነርሱ ክርስቶስን በማመን እስከመጨረሻው ድረስ መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ልዩ ልዩ በሆኑ ጽኑ ሥቃዮች እጅግ አድርጎ አሠቃያቸው፡፡ በመጨረሻም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የቅዱስ ቆጵርያኖስን የቅድስት ዮስቴናን እንዲሁም የሌሎች ሦስት ወንዶችን በየተራ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
@ ከገድላት አንደበት
/channel/catsdogs_game_bot/join?startapp=1060582070
Join Cats or Dogs and get some $FOOD daily rewards. More $FOOD - more loot🐈🦮
ምእመናን ሆይ
የሚጎዳን ሀብታችን አይደለም
የሚጎዳን ድህነታችን አይደለም
ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው
ክፋ ልብ ደግሞ በሀብት የሚመጣ አይደለም
ክፉ ልብ ሌሎቹ ክፉ ልቦችን ይወልዳል
ልክ እሳት እሳትን እንደሚወልድ
እንጨቶችን እንደሚበላ ሁሉ
ክፉ ልብም ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል ።
ተወዳጆች
ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር
በተፈጥሮ የሚገኙ አይደለም
ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ ነው እንጂ
መድኃኔዓለም መልካም ልብን ያድለን🙏
ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ወደሚጠብቀው አዳራሽ አመራ። በጭብጨባ ከተቀበሉት በኋላ ወደ መድረክ እንዲወጣ ተጋበዘ።
#በመጀመርያ የሚያምር ቀልድ ነገራቸው። አዳራሹ በፉጨት ተቀወጠ በሳቅ ደመቀ።
ከዚያም ያንኑ ቀልድ #ለሁለተኛ ጊዜ ደገመላቸው። ግማሾቹ ሳቁ፤ ግማሾቹ ደግሞ ግራ ተጋቡ....
#ለሶስተኛ ጊዜ አሁንም ያንኑ ቀልድ ደገመው። በዚህ ጊዜ ግን አንድም የሚስቅ ሰው አልነበረም።
ያኔ ቻርሊ በጣም ደስ አለው። ከዛም የሚከተለውን ንግግር ተናገረ.....
"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ እንደማትስቁ ሁሉ ስለምን በአንድ ነገር ደጋግማችሁ ታለቅሳላችሁ?
ህይወትኮ እጅግ ውብ ናት። ዛሬ በህይወት ካላችሁ ነጋችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ።
በትላንት ውስጥ ስላጣችሁት ነገር አታስቡ ዛሬን ብቻ በህይወት በመኖራችሁ ፈጣሪን አመስግኑ።
ዛሬ ጠንካራ ከሆናችሁ ነጋችሁ የተዋበ ይሆናል፤ ነጋችሁ የሚጥም ይሆናል። አሁንም አሁንም አሁንም በህይወት መኖራችሁን ብቻ እያያችሁ ፈጣሪን አመስግኑ!"
#ወዳጆቼ ከተሰጠን ስጦታዎች ሁሉ ህይወታችን ይበልጣልና በህይወት ካላችሁ በነጋችሁ ላይ ለውጥ መፍጠር ትችላላችሁ።"
---------------------------------
አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን #አትርሱ🙏
----------------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደዚህ 👉 higherperspective1?_t=8pzIlA0L5PC&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8pzIlA0L5PC&_r=1 #tiktok አካውንታችን እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
መስቀሉን ያስወጣችው የእሌኒና የልጇ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ታሪክ
❖ ይኽ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የአባቱ ስም ቊንስጣ የእናቱ ስም እሌኒ ነው፤ ከሓዲው መክስምያኖስ በሮሜ በአንጾኪያ እና በግብጽ ነግሦ በነበረ ጊዜ አባቱ በራንጥያ ለሚባል ሀገር ንጉሥ ነበር፤ እሌኒ ከርሱ ቆስጠንጢኖስ ከወለደችው በኋላ አባቱ ቊንስጣ እነርሱን ሮሐ (ሶርያ) ላይ ትቷቸው ወደ በራንጥያ ተመለሰ፡፡
✍“ወይእቲ ነበረት እንዘ ተሐጽኖ ለወልዳ ወመሀረቶ ትምህርተ ክርስትና ወኮነት ዘትዘርዕ ውስተ ልቡ ምሕረተ ወሣሕለ ላዕለ ሕዝበ ክርስቲያን” ይላል፤ ርሷም ልጇን የክርስትና ትምህርትን አስተማረችው፤ ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው መልካም ዘርን ትዘራበት ነበር፡፡
❖ ከዚያም ቈስጠንጢኖስ አካለ መጠን ሲያደርስ ወደ አባቱ ሰደደችው፤ አባቱም የጥበቡን ብዛት አይቶ በመደሰት ከበታቹ መስፍን አድርጎት በመሾም በመንግሥቱ ሥራ ላይ ኹሉ ሥልጣንን ሰጥቶታል፤
✍“ወእምድኅረ ክልኤቱ ዓመት አዕረፈ አቡሁ ወተመጠወ ቈስጠንጢኖስ ኲሎ መንግሥተ ወገብረ ፍትሐ ርቱዐ” ይላል፤
❖ ከሁለት ዓመት በኋላ አባቱ በማረፉ ቈስጠንጢኖስ መንግሥቱን ኹሉ ተረክቦ የቀና ፍርድን የሚፈርድ ኾነ፤ ከርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ የሚያስወግድ ኾነ፤ በዚኽ ምክንያት ኹሉም ወደደው፤ ዝናውም በብዙ ሀገሮች ላይ ተሰማለት፡፡
❖ በአንጾኪያ ያሉ ክርስቲያኖችም የቈስጠንጢኖስን ፍርድ መጠንቀቁን፣ ድኻ መጠበቁን እየሰሙ ከከሓዲው ከመክስምያኖስ አገዛዝ እንዲያድናቸው የልብሰ ተክህኖውን ቅዳጅ፣ የመስቀሉን ስባሪ ይልኩለት ነበር፤ ርሱም ስለደረሰባቸው መከራ በእጅጉ እያዘነ እንዴት አድርጎ እንደሚያድናቸው ያስብ ነበር።
✍“ወእንዘ ይነብር ውስተ ዐውድ ወናሁ አስተርአዮ በመንፈቀ መዓልት መስቀል ዘሕብሩ አምሳለ ከዋክብት ወዲቤሁ ጽሑፍ በልሳነ ዮናኒ ኒኮስጣጣን ዘበትርጓሜሁ በዝንቱ ትመውዕ ጸረከ ወአንከረ ብርሃኖ ለመስቀል ሶበ ርእየ እንዘ ይከድኖ ለብርሃነ ፀሓይ” ይላል
❖ ከዕለታት ባንዳቸው በአደባባይ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ከቀኑ በስድስት ሰዓት ጊዜ ሕብሩ እንደከዋክብት የኾነ መስቀል በጸፍጸፈ ሰማይ ላይ ሲታየው፤ በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጽሑፍ ነበረው፤ ትርጓሜውም በዚኽ ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ ማለት ሲኾን፤ ርሱም የመስቀሉ ብርሃን የፀሓይን ብርሃን ሲሸፍነው አይቶ ተደንቋል፡፡
❖ ይኽነንም ያየውን ለሊቃውንቱ በጠየቃቸው ጊዜ አውስግንዮስ የሚባል ሕጽው በዚኽ መስቀል አምሳል ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ ማለት ነው ብሎ ተረጐመለት፤ መልአኩም ሌሊት በራእይ ታይቶት አስረዳው፤
✍“ወነቂሆ እምንዋሙ ጸንዐ ልቡ ወገብረ መስቀለ ዘወርቅ ወረሰዮ መልዕልተ አክሊለ መንግሥቱ ወአዘዞሙ ለኲሎሙ መኳንንቲሁ ወሐራሁ ከመ ይግበሩ መስቀለ በኲሉ ንዋየ ሐቅሎሙ” እንዲል
❖ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸናና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው፤ መኳንንቱንና ወታደሮቹን ኹሉ መስቀል አሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸውና እንዳላቸው አደረጉ፡፡
❖ ከዚያም በክርስቲያኖች ጠላት በከሓዲው መክስምያኖስ ላይ ዘመተበት፤ ከዚያም መክስምያኖስ ሰምቶ ጦሩን ይዞ መጣበት፤ በመክስምያኖስ ጦር ላይ ዐድረው ድል ያደርጉ የነበሩ አጋንንት በቈስጠንጢኖስ ጦር ላይ ያለውን ትእምርተ መስቀል ባዩ ጊዜ ተለይተውት በኼዱ ጊዜ ድል ተነሣ፤ ርሱም ከጥቂቶች ጋር ራሱን ለማዳን
✍“ወተጽዕኑ ዲበ ተንከተም ወተንከተምኒ ንህለ ወተሠጥመ መክስምያኖስ ምስለ ሰራዊቱ” ይላል ወደ ሮሜ ለመሻገር በድልድይ ላይ ሲወጡ ድልድዩ ፈርሶ ከሰራዊቱ ጋር ሰጥሟል፡፡
❖ ከዚያም በድል አድራጊነት ንጉሥ ቈስንጢኖስ ወደ ሮሜ በገባ ጊዜ ካህናቱ ሕዝቡ መብራት ይዘው፤
✍“መስቀል ኀይልን መስቀል ጽንዕነ መስቀል መዋዔ ጸር” እያሉ እየዘመሩ ተቀበሉት፤ ርሱም እናቱ ቅድስት እሌኒ እያስተማረች ያሳደገችው፤ በኋላም ምእመናን ይልኩለት የነበረው፤ በሰሌዳ ሰማይ ላይ የተመለከተው፤ አኹንም በአንጾኪያ ምእመናን ይዘው የተቀበሉትን አይቶ ትክክለኛውን ሃይማኖት በመረዳት ከሀገሩ ሶልጴጥሮስን አምጥቶ ተጠምቋል፡፡
❖ ከዚያም ዐዋጁን ባዋጅ በመመለስ “አብያተ ጣዖታት ይትዐጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ” (አብያተ ጣዖታት ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ) የሚል ታላቅ ትእዛዝን አዘዘ፤ የጌታችንንም መስቀል እንድታወጣ እናቱ እሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት።
❖ ይኽስ እንደምንድ ነው ቢሉ የጌታችን መስቀል ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሙት እያነሣ፣ ደዉይ እየፈወሰ ለክርስያኖች ታላቅ ክብር በመኾኑ፤ አይሁድ በዚኽ ቀንተው ጒድጓድ ቈፍረው በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ኹሉ ቤቱን የሚጠርግ ጒድፉን አምጥቶ እንዲያፈስስበት በማዘዛቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ ኾኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ300 ዓመታት ያኽል ተቀብሮ ኖረ፡፡
❖ ልጇ ቆስጠንጢኖስም በመስቀሉ ኀይል የክርስቲያኖች ጠላት የኾነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ በሶል ጴጥሮስ ተጠምቆ ክርስቲያን ኾነ፤ ርሷም ልጄ ክርስቲያን ከኾነ ኢየሩሳሌም ኼጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለኊ፤ የጌታዬ መስቀልን ከተቀበረበት አስወጣለኊ ብላ ስዕለት ተስላ ነበርና ያ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ፤ ለልጇ ነገረችው፤ ርሱም በደስታ ብዙዎች ሰራዊትን ስንቅ አስይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፤ በደረሰችም ጊዜ ሱባኤን አድርጋ የመስቀሉ ጠላቶችን በጽኑ እስራት አሰረቻቸው፤ በኋላም አሚኖስና ኪራኮስ የሚባሉ በዕድሜ የጠገቡ ሽማግሌዎችን ብትጠይቃቸው ሊነግሯት ፈቃደኛ አልኾኑምና በጽኑ እስራት ብታስጨንቃቸው፤ ታሪኩን ነገሯት፤ ቦታውንም ጠቈሟት፡፡
❖ ከዚያም በጸሎቷ ላይ ቅዱስ መልአክ ተገልጾላት በዕጣን ጢስ አማካይነት እንደምታገኘው ተረድታ፤ መስከረም 16 ደመራን አስደምራ በእሳት እንዲቃጠል አድርጋ እጅግ ብዙ ዕጣንን ብታስጨምር ጢሱ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ ካለበት ቦታ ላይ ተተክሎ ሰገደ፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይኽነን ድንቅ ታሪክ ይዞ
✍"ሰገደ ጢስ ኀበ አንጻረ መስቀል ሰገደ ጢስ ወባረከ" እያለ አመስግኗል፡፡
❖ ርሷም ፈጣሪዋ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ አመስግና ቊፏሮውን ከመስከረም 17 ጀምሮ እስከ መጋቢት 10 ድረስ እንዲቈፈር አስደርጋለች፤ በቊፋሮው ወቅትም የፈያታዊ ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም መስቀል ቢገኙም ዕውር አላበሩም፣ ሕሙማንን አልፈወሱም፡፡
❖ ከዚያም መጋቢት 10, በ327 ዓ.ም. ጌታችን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀሉ ተገኘ፤ በዚኽ ጊዜ ከሕሙማን ላይ ቢያደርጉት ኹሉንም ፈወሳቸው፣ ዕዉራን በሩ፣ ሙታንም ተነሡ፡፡ ከዚኹም ጋር የተወጋበት ጦሩ፣ የተቸነከረባቸው ቅንዋት ኹሉ ተገኝተዋል፤ ርሷም በፈረሷ ልጓም ላይ የመስቀል ምልክትን አስቀርጻበታለች፡፡
❖ ርሷም ጌታችን ተአምራት በሠራባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናትን በማሠራት፤ በተለይም በጎልጎታ የተሠራው ቤተ ክርስቲያን መስከረም 17 ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን በተገኙበት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተከብሯልና፡፡ ርሷም ለድኾችና ለጦም አዳሪዎች ብዙ መልካም ነገርን በማድረግ ግንቦት 9 በሰላም ዐርፋለች፡፡
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌺 መልካም 🌺🌻
🌻🌻 በዓል! 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻💐💐💐🌻🌻
🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
/channel/+Qf1iLKbD_bljNjg0
ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡ ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡
፪. ሙታንና ሕያዋን
አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡
፫. ጻድቃንና ኀጥአን
የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡ የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
ኪዳነ ምህረት
እንኳን ለወርሃዊው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳን መታሰቢያ /ኪዳነ ምህረት/ በሰላም አደረሰን !!!
❤ እግዚአብሔር በየጊዜው በመንገዱ ከፀኑ ፣ በጽድቅ ከተመላለሱ ቅዱሳን ጋር ቃል ኪዳን እንደገባ መጻሕፍት ያስተምሩናል
❤ ቃል ኪዳን ትርጓሜውም "ውል፣ ስምምነት" ማለት ነው
❤ የዛሬው በዓልም ለእናቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን የገባላት ዕለት መታሰቢያ ነው
❤ ይህም ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ እየሄደ በምትጸልይበት በአንዱ ቀን የካቲት ፩፮ ተፈፀመ
❤ ስሟን ለሚጠራ፣ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውሃ ለሚሰጥ ከልጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች
❤ ስሟን የጠራ ሲባል፦
➻ በጸሎቱ በእርሷ የተደረገለትን የአምላክ ቸርነት እያሰበ ዘወትር በእምነት ፀንቶ በጎ ምግባርን እየፈጸመ የሚኖር ማለት ነው
❤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ዘወትር ጸንቶ የሚኖር ነውና ላመነው ሁሉ ይሆንለታል
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ለእኛም ይሁንልን። በበጎ ምግባር እንድንኖር ይርዳን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#ቅዱሳን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
#ግእዝ_geez_ገጽ
ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ
እንኳን ለቅዱስ ሚናስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!
✝️ ቅዱስ ሚናስ ከደጋግ ክርስቲያን ቤተሰቦች የተገኘ በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የነበር ቅዱስ ነው
✝️ ቅዱስ ሚናስ የስሙ ትርጓሜ "ታማኝና ብሩክ" ማለት ሲሆን እንደ ስሙም ለክርስቶስ ታምኖ የኖረ ጻድቅ ነው
✝️ በልጅነቱ ቤተሰቦቹ ሲሞቱ የወረሰውን ሀብትና ንብረት ለድሆች አካፍሎ መነነ
✝️ በገዳምም በርትቶ አምላኩን ማምለክና ማመስገንን አጥብቆ ቀጠለ
✝️ በዘመኑ በነበሩ የጣኦት አምላኪዎች ተይዞ ለጣኦታት አልሰግድም በማለቱ በ፳፬ ዓመቱ መስዋዕትነትን ተቀበለ
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ምልጃና በረከት ይደርብን። እኛንም ለመንግሥቱ የቀናን ያድርገን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
መስከረም 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው
👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ
👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል
👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ #ኢትዮዽያ መጡ
👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል
👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል
👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል
👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች
👉ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም አስራ አምስት ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን
👉ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል #ፃድቅን_በፃድቅ_ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ.10 ቁ.41
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሣን አባቶቻችን #የአቡነ_አረጋዊ እና የመናኙ ፃድቅ የቅዱስ #ገብረ_ክርስቶስን በረከታቸዉን ያሣድርብን ፀሎታቸዉ ልመናቸው ሀገራችንን ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 14-ዓለምን ንቀው ከመመንኮሳቸው በፊት የቀዳማዊው ንጉሥ የዓምደ ጽዮን ልጅ የነበሩና ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ የተሻገሩት የማንዳባው አቡነ ያሳይ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አምሳ ዓመት በዓምድ ላይ ቆሞ ሲጸልይ የኖረው አቡነ አጋቶን ዘአምድ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት እጆቻቸው እንደፋና እያበሩ ለጣና ሐይቅ ገዳማት በመብራትነት ያገለግሉ የነበሩት ኢትዮጵዊው አቡነ ጴጥሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ አጋቶን ዘአምድ፡- ከደቡባዊ ግብጽ የተገኘ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ አባቱ መጥራ እናቱ ማርያ ይባላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምሮ በቅስና ሲያገለግል ከኖረ በኋላ መርዩጥ ወደምትባል አገር ሄደ፡፡ ከዚያም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ቅዱስ መልአክ በመነኩሴ አምሳል ተገልጦ ወደ መቃርስ ገዳም አስቄጥስ አስገባውና መነኮሰ፡፡ በዚያም አረጋዊያን መነኮሳትን እነ አባ ገዐርጊን እያገለገለ ሥጋው ከቆዳው እስኪጣበቅ ድረስ እየጾመ ያለምንም ምንጣፍ ይተኛ ነበር፡፡ ሁልጊዜም የአባ ስምዖን ዘአምድን ገድል ያነብ ስለነበር ከገዳሙ ተሰናብቶ ወጥቶ ዓምድ ሠርቶ በላዩ ወጥቶ ለ50 ዓመት ቆሞ ሲጸልይ የኖረ ታላቅ አባት ነው፡፡ ጋኔን እያደረባቸው ቅዱሳን ተገለጡልኝ የሚሉ አሳቾችን ወደ እርሱ እያስመጣቸው በውስጣቸው ያደረውን ጋኔን ያወጣላቸው ነበር፡፡ አባ አጋቶን በመላእክት አምሳል ሆነው መልካም ዝማሬን እየዘመሩ ሰይጣናት ተገልጠውለት ሳለ አማትቦ ድል አድርጓቸዋል፡፡ ይህም ጻድቅ እስከ 35 ዓመቱ በዓለም እየኖረ እግዚአብሔርን አገለገለ፤ ለ15 ዓመታት በገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፤ ቀሪውን 50ውን ዓመት ደግሞ በዓምድ ላይ ተተክሎ በጸሎት ሲያመሰግን ኖረ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትን በማድረግና ወንጌልን በማስተማር ብዙ ካገለገለ በኋላ በ100 ዓመቱ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈና ቅድስት ነፍሱን አስረከበ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ፡- አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ የተባሉት ጻድቅ ትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ቡልጋ ልዩ ስሙ ደብረ ጽላልሽ ነው፡፡ ጻድቁ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ለ48 ዓመታት የቅዱስ ገላውዲዮስን ቤተ ክርስቲያን ሲያጥኑ ኖረዋል፡፡ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ ሊቃኖስ እጆቻቸው እያበሩ ለገዳሙ መብራትነት ይጠቀሙባቸው እንደነበረው ሁሉ የአቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊም እጆቻቸው እንደፋና እያበራ ለጣና ሐይቅ ገዳማት በመብራትነት ያገለግል ነበር፡፡ ጻድቁ ለ31 ዓመታት ከመላእክት ጋር እየተነጋገሩ የኖሩ ሲሆን መናም ከሰማይ እያወረዱ መነኮሳቱን ይመግቡ ነበር፡፡ ድውያንን በመፈወስ፣ ሙታንን በማንሣት ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገራችን ዞረው በማስተማር እግዚብሔርን ሲያገለግሉ ኖረው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈው ቅድስት ነፍሳቸውን ቅዱሳን መላእክት በክብር ተቀብለዋታል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፡- አቡነ ያሳይ ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እነዚህም ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› የተባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ ናቸው፡፡ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኮሷቸው መነኮሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት፡፡
አቡነ መድኃኒነ እነዚህንም ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኮሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፤ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ አንዱ ዛሬ በዓላታቸውን የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ናቸው፡፡
ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በገሃድ ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሎቸአውን በዚያ ፈጸሙ፡፡
ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ሐሤቶሙ ለመላእክት፡፡
የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ለሊሁ ዓለሞሙ ወለሊሁ ተድላሆሙ ወለሊሁ ሀገሮሙ እንዲል፡፡ አንድም ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት የሚነግሩ መላእክት ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት ፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ብለው አመስግነውት ፤ በጣዕም ላይ ጣዕም ፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋልና አንድም የመላእክት ደስታቸው የምትሆኝ ጌታን የወለድሺው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እያዩ ደስ ይላቸዋልና ሐሴቶሙ ለመላእክት አለ፡፡
ተፈሥሒ ኦ ድንግል ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡
የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ኦ ድንግል አምሳል ወትንቢት ፤ ዘነቢያት እንዲል፡፡
ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡
እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ፤ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ሆኗልና፡፡ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡
ተፈሥሒ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍሥሓ ኩሉ ዓለም፡፡
የሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን የመልአኩን ቃል ፤ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ እንደ ዘካሪያስ ሳትጠራጠሪ አምነሻልና ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ሰብአ ፊንቆን ተወክፍዎ ፤ ወእለሰ ተወክፍዎ ወሀቦሙ ሥልጣነ እንዲል ፍሥሐ ኩሉ ዓለም ያለውን ለመልአክ ቢቀጥሉ ምስጋናው ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ነውና ቃል ላለው ቢቀጽሉ ወነዋ ተወልደ ፍሥሐ ዘይከውን ፣ ለክሙ ለኩሉ ዓለም ይለዋልና፡፡
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም።
ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::