ቅድስት ኪዳነ ምህረት
እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" ከመረጥዃቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
መዝ. ፹፱፥፫ /89፥3/
❤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር አምላካችን በተለያዩ ጊዜያት ከመረጣቸው ከወዳጆቹና ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በየዘመናቱ ቃል ኪዳን ፈጽሟል
❤ በየካቲት ፲፮ (16) ቀንም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የማይጠፋ የዘላለም ቃል ኪዳንን አደረገ
❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በሚማፀኑ፣ መታሰቢያዋን በሚያደርጉ፣ ለችግረኞች ለሚራሩና በስሟ ቤተክርስቲያንን ለሚያንጹ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ ለእናቱ ቃል ኪዳን ገባ
➻ እኛም ይህንን ዕለት ኪዳነ ምህረት እያልን እናከብረዋለን
❤ በቤተክርስቲያናችንም ይህ ታላቅ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፣ ቃል ኪዳኑም ይታወሳል
አምላካችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይክፈለን። የእመቤታችን አማላጅነትም አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ተዋህዶ
#ድንግል
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
ተወዳጆች ሆይ
ሹመትም አይኑራችሁ እውቀትም አይኑራችሁ
ጤናም አይኑራችሁ ሀብትም አይኑራችሁ
ማርያም ስላለችልን ብቻ ደስ ሊለን ይገባል።
እሷ ስላለችን ይበቃናል ።
የ አክል ሐይማኖት ዘአልቦ ጥልቀት ወእምነት
በ ቅድስት ድንግል ከመ ይዕቲ ወላዲተ አምላክ
✅ ዘአልቦ ጥልቀት አለ
ጥርጥር የሌለበት ሐይማኖት ለምንም ነገር ይበቃል።
ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ ማመን ለሁሉም ይበቃል
ለልብስ ይበቃል ክርስቶስን እንለብሳለን
ለምግብ ይበቃል የህይወት እንጀራ ልጇን እንበላለን።
ለጥበቃ ይበቃል መልካም እረኛ ልጅ አላትና በእሷ ይጠብቀናል ።
ስለዚህ ምንም የሚጎልብን ነገር የለም
ሰው ማርያምን ከወደደ የሚያጣው ነገር የለም ።
✅ መለመን ያለብን
የእናትህን ፍቅር ጨምርልን ብለን ነው
መፀለይ ካለብን እሷን ነው
በኃጢአት የመረረው ህይወታችን ሊጣፍጥ የሚችለው
ጥዕምተ ስም ማርያም በልቡናችን ያደረች እንደሆነ ነው
✅ እሷ ስታድርብን
መራራው ንቅል ንቅል ንቅል እያለ ይጠፋል
መራራውን ህይወታችን
መራራውን ኃጢአታችን
በእናቱ በጣፈጠው ሥሟ ነቅሎ ይጣልልን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕
ወዳጄ ሆይ
👉ባልንጀራህን በቁጣ ገንፍለህ ልትመታዉ ትችላለህ
👉ልብሱንም ልትቀድበት ትችላለህ
👉የከፋው ቅጣት የምትቀበለው ግን አንተው ራስህ ነህ
👉ምክንያቱም በቡጢ ብትመታዉ ሥጋውን ነዉ
👉አንተ ግን የምትጎዳው ነፍስህን ነዉ።
👉የባልንጀራህን ልብስ ልትቀድበት ትችል ይሆናል
👉አንተ ግን ከሁለት የምትተረትራት የገዛ ነፍስህን ነወ።
👉ባልንጀራህን ብትመታዉ ሥጋዉን ነዉ
👉አንተ ግን የምትጎዳው ነፍስህን ስለ ኾነ ሥቃይህም የነፍሰ ነዉ።
የ💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💕 አማላጅነት አይለየን !!!
ሰላም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በአክብሮት እንጠይቃለን ተሰውረው የሚኖሩ አባቶች እንዲሕ ብለዋል የመጨረሻ ዘመን ስለሆነ ዛሬ እንጠራ ነገ እንጠራ ስለማናዉቅ ንሰሀ ግቡና ታጥባችሁ ጠብቁኝ ብለዋል።ቢያንስ (ለ10ሰው) አስተላልፉ ሳታስተላልፉ ብትቀሩ በድንግል ማርያም ስም የተወገዛችሁ(የተረገማችሁ ) ሁኑ?
Читать полностью…ህዳር 13/2017 #አምላካችን_እግዚአብሔር_አብ
#አእላፋት_መላእክት
#መልአኩ_ቅዱስ_ሩፋኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ኅዳር 13 በዚህች ቀን #የአእላፋት_መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ #ለዓለሙ_ሁሉ_የሚማልዱ ናቸው እንኳን ለአመታዊ ክብረ በአላቸው አደረሰን
👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ
👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም_መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ
👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ #ረቂቃን_መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ
👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው ሁለተኛም #የእግዚአብሔር_ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ
👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስኪዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉር እንደ ብዝት ነጭ ነው ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል #የእልፍ_እልፍ_መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መፃሕፍትን ገለጠ
👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ #የሰማይ_ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ #ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ
👉ማቴዎስም እነሆ መላእክትም ሊያገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ #ቅዱሳን_መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል
👉ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም_መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው
👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ #ቅዱሳን_መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ
👉የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓርጋቸውን ደረጃ እንዲህ ብለው ተናገሩ #መላእክት_አጋዕዝት ሥልጣናት #ኃይላት_መናብርት መኳንንት ሊቃናት #ኪሩቤል_ሱራፌል ብለው ተናገሩ
👉 #የእልፍ_አእላፋት_መላእክት ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የሚዉለዉ የጦቢትን አይን ያበራ ተራዳኢዉ መልአክ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃዉ ተራዳኢነቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ጊዜዉ ያላችሁ የበአሉ መታሠቢያ #በደብረ_ሲና_ቅዱስ
#እግዚአብሔር_አብ ቤተክርስቲያን አዲሱ ገበያ በድምቀት ይከበራል የበረከቱ ተሣታፊ ሁኑ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ጻዲቁ ንጉሥ በእደ ማርያም ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን በእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የጠበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንችላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
ከገድላት አንደበት
ህዳር 11/2017 #እናታችን_ቅድስት_ሐና
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅድስት #ሐና ስም ለምናመሰግንበት #ለቅድስት_ሐና አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉በዚህ ዕለት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያቱ እንዲሁም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች #የቅድስት_ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው
👉ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ #አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት
👉ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት #ከአረጋዊ_ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል #ማርያምን ያገለገለቻት ናት
👉ሶፍያም ለባል ተድራ #ለመጥመቁ_ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ይችንም #ቅድስት_ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ፃድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን #ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ #ለቅድስት_ሐና የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው
👉የዚችንም #የቅድስት_ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና #ከሴቶች_ሁሉ_የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ፀጋ ባልተገባት ነበር
👉ይህችም #ፃድቅት_ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በፀሎት ትተጋና ትማልድ ነበር #እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ናት
👉ስለዚህም ይህን ታላቅ ፀጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷ እና ረድኤቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ "አሜን"✝️ 💒 ✝️
ተወዳጆች ሆይ
እግዚአብሔር ትዝ ብሎት ሚያለቅስ አለ ?
ክርስቶስ ትዝ ብሎት ሚያለቅስ አለ ?
የሚያለቅሰውን ሰው እዩት
ሆዱ ሲነካ ያለቅሳል
ሹመቱ ሲነሳ ያለቅሳል
ለገዛ ኃጢአቱ ያለቅሳል
ለዘሩ ሲሆን ይብከነከናል
አንድ የነኵት ለት ማለት ነው
መጀመርያ ለእግዚአብሔር
አርብ እንኳ እንባው መጥቶት አያውቅም
ሲርበው ሲታመም ሲብሰው ሲገፋ ብቻ
እስኪ አሁን ማያለቅስ ማን አለ ?
መጀመርያ ሰው የሚያለቅሰው ለምንድን ነው ?
ለሴት ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለወንድ ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለዝሙት ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለዚያ እየየ ሌሊቱን ሙሉ ያለቅሳል
ጣዖት ነው ያሁሉ ነገር
ለገንዘብ ነው ስናለቅስ የኖርነው
ለኩራታችን ነው ስናለቅስ የኖርነው
ለደስታችን ነው ስናለቅስ የኖርነው
የእግዚአብሔር ፍቅር ተለወጠ ያቀረ ጎደልን በሉ
ክርስቶስን እያሰብን እንድናለቅስ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
ህዳር 10/2017 #መስቀለ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ቅዱስ እፀ መስቀል ለተገኘበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉እውራንን የሚያበራው ድውያንን የሚፈውሰው ሰላመ #እግዚአብሔርን ያገኘንበት የድህነታችን አርማ ሀይላችን የምንመካበት የምንድንበት ቅዱስ #እፀ_መስቀላችን ነው
👉የድህነታችን አርማ የሆነውን ቅዱስ #እፀ_መስቀል አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ቀበሩት ለዘመናት የቆሻሻ ክምር በመጣል መስቀሉ እዲሰወር አደረጉ
👉በ 320 ዓ.ም የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት #ቅድስት_እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ከ አረማዊ እምነት ወደ ክርስትና እንዲመለስ ስለት ተሳለች በስለቷ መሰረት ልጇ ወደ ክርስትና አምነት ከተመለሰ #የጌታችን_ኢየሱስን_መስቀል ለማግኘት በተሳለችው ስለት መሰረት መስከረም 16 ደመራ ደምራ እጣን በውስጡ ጨምራ አበራች
👉በዚህም ወቅት ጢሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ ወደ ምድር ሰግዶ በዘመኑ ከነበሩት ብዙ የቆሻሻ ክምር ተራራዎች የጌታችን #ቅዱስ_እፀ_መስቀል ወዳለበት ተራራ አመለከተ
👉 #ቅድስት_አሌኒም መስከረም 17 ቁፋሮውን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን ቅዱስ እፀ መስቀሉ ተገኘ።
👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመስቀሉ መታሰቢያ ክብረ በአል በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ህዳር 9/2017 #ፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው
👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው
👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል
👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል
👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች
👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ #መልክአ_መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ፀሎት በፀለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ
👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል
👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ፃድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️💒✝️
ወጣትነትን ለቅድስና ህይወት
(youth for aholy life)💠💠
በዚህ ገፅ በሃይማኖታችን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሥርዓት መሰረት መንፈሳዊ አስተምሮ እናስተላለፍበት። የምናውቀውን ለማያውቀው ማሳወቅ፤ መንፈሳዊ ትምህርት ማሰራጨት አንዱ ነፍስ የማዳን ስራ ነውና።
ትናትናን አሳልፎ ዛሬን ከሀጢአታችን በንሰሐ እንድንመለስ ተጨማሪ እድሜ የሰጠን እግዚአብሔር ምንሰጠው ስጦታ ምስጋና ነውና ይክበር ይመስገን🙏
ተወዳጆች
ድንግል ማርያምን የያዘ ሰው የክርስቶስ በግ ነው ።
ምልክት የሌለው የላባ ነው ማለት
ምልክቲቱ ድንግል ማርያም ናትና
ድንግል ማርያም የሌለቻቸው ሰዎች የዲያብሎስ ናቸው ።
የክርስቶስ በጎች አይደሉም አንዱ ምልክታችን መስቀል ነው።
መስቀል የላቸውም አያምኑትም ይክዱታል።
ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ።
እኔ ከክርስቶስ መስቀል በቀር በምንም ባንዳች አልመካም ።
ተወዳጆች
ሥላሴን ስማቸውን ውደዱ
ሥላሴ ተመስገን ሥላሴ ተመስገን ሥላሴ ተመስገን በሉ
ለሰይጣን ከዚህ በላይ ጦር የለውም
ቀኑን ሙሉ ዝምብላችሁ ሥላሴ ተመስገን በሉ
ተመስገን ካላችሁ ዲያቢሎስ እንዴ
ይሄን ሁሉ እያረኵት አይመረውም እንዴ ብሎ
እኛን ማሰልቸት ሲያቅተው እራሱ ስልችቶ ይሄዳል
ሥላሴ ተመሰገን በሉ
የእናት አማላጅ ስለሰጠን
ስጋወ ደሙን ስለሰጠን
የሰማይ በር ስለከፈተልን
በንስኃ ስለሳበን
አንድ ልጁን ስለሰጠን
ሥላሴ ተመሥገን በሉ
ሰማይን ማን አፀናው ?
የ ሥላሴ ስም
ምድርን ማን አፀናት ?
መላእክትን ማን አፀናቸው ?
ፍጥረታትን ማን አፀናቸው ?
ለሁሉ ነገራችሁ የሥላሴን ሥም ተጠቀሙ
የሥላሴ በረከት እረድኤት አይለየን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
ተፃፈ ፦ በ ዲ/ን ዑራኤል
እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" ከመረጥዃቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
መዝ. ፹፱፥፫ /89፥3/
❤️ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር አምላካችን በተለያዩ ጊዜያት ከመረጣቸው ከወዳጆቹና ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በየዘመናቱ ቃል ኪዳን ፈጽሟል
❤️ በየካቲት ፲፮ (16) ቀንም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የማይጠፋ የዘላለም ቃል ኪዳንን አደረገ
❤️ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በሚማፀኑ፣ መታሰቢያዋን በሚያደርጉ፣ ለችግረኞች ለሚራሩና በስሟ ቤተክርስቲያንን ለሚያንጹ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ ለእናቱ ቃል ኪዳን ገባ
➻ እኛም ይህንን ዕለት ኪዳነ ምህረት እያልን እናከብረዋለን
❤️ በቤተክርስቲያናችንም ይህ ታላቅ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፣ ቃል ኪዳኑም ይታወሳል
አምላካችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይክፈለን። የእመቤታችን አማላጅነትም አይለየን። /channel/Tewahedomender
ህዳር 16/2017 #እናታችን_ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት
"ከመረጥኋቸዉ ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግኹ"መዝ.88፥3
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን
👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው
👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት
👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ
👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል
👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ.9፥16
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የአበዉ ነብያት ረድኤት በረከት አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
🖌 ሦስት ዓመት ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነት የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዛሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ሲሆን በኅዳር 15 ቀን ተወልዷል፡፡
🖌 ዛሬ ኅዳር 15 የልደቱ መታሰቢያ ቀን በቤተክርስቲያናችን ታስቦ ይውላል። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃልኪዳኑን ሰቶታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን አሜን።
#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ህዳር 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ
" ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል ማቴ.10፥42 "
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው
👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ
👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል
👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #መልአክ_በክንፉ_ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ
👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል
👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል
👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል
👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል
👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች
👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሣኑን ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ያድለን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕
👉ራሱ ጌታችን ተሰዉቶ በመሠዉያዉ (በጻሕሉ ) ላይ ሁኖ
👉 ካህኑ ቁሞ ለመሥዋዕት በቀረበው ላይ ሲጸልይ
👉ምእመናን በሙሉ በከበረዉ ደሙ ፈሳሽነት ነጽተዉ ስታይ
👉አሁንም በሰዎች መኻከልና በምድር ላይ እንደቆምህ አድርገህ ታስባለህን?
👉ይልቁንስ በተቃራኒው ወደ ሰማየ ሰማያት ወጥተህ ፣
👉ምድራዊ አስተሳሰብን ኹሉ ከሕሊናህ አሽቀንጥረህ ጥለህ
👉 በመንፈስና በርቱዕ ሕሊና ሰማያዉያን ነገሮችን አታስብምን?
👉ወዮ! እንደምን ይረቅ?
እንደምን ይደንቅ?
ለሰዎች የተደረገው የእግዚአብሔር ቸርነት
እንደምን ያለ ቸርነት ነዉ?
የቅዱሳን አማላጅነት አይለየን !!!
ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ አዳዲ ማርያም🙏
መነሻ ቀን በ21
የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ አዳዲ ማርያም
መነሻ ቦታ ፣፣ አስኮ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
በእለቱ የ ፀበል መጠመቅ የፀሎት ፕሮግራም የተለያዩ ሰባኪ መምርሀን ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ ።
ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 600 ብር ብቻ።
ስልክ 09-91-11-96-29
09-25-49-26-34 ይደውሉልን
ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር🙏🙏
ተወዳጆች ሆይ
የሰው ስህተት የሚለቅም እሱ ሰይጣን ነው።
እኩይ ፍልስጣ የሚባል ሰይጣን አለ
✅ የሰይጣንም ድርሻ ድርሻ አለው
የሚያሰርቀው ሰይጣንሌላ ነው
የሚያዘሙተው ሰይጣን ሌላ ነው
የሚያጣላው ሰይጣን ሌላ ነው
✅ እኩይ ፍልስጣ
ደሞ የሰውን ክፋቱ ሁልጊዜ ነው የሚመዘገብ
✅ ለምሳሌ
እኔ ዝክር ስዘክር አይመዘግብም
የሰርቅኩ ዕለት ሰርቋል እያለ ይፅፋል
ዛሬ ስፀለይ አደረኩ ነገ ተኝቼ አደርኩ ተኝቷል ብሎ ይጽፋል
በፍፁም አንድ መልካም ነገር አይመዘግብም
ሁልጊዜ ክፋት የሚመዘገብ ሰው እኩይ ፍልስጣ ይባላል ።
በ ነገራችን እቤትም በሰላም ማትኖሩት ለዚህ ነው ።
መልካም መልካሙን ብትቆጥሩ ምን አለ ።
እግዚአብሔር መልካም መልካሙን ቆጥሮ ነው
ክፉ ክፉን ቆጥሮ ነው የሚያድነን ?
✅ መልስ
መልካሙን ቆጥሮ ነው
✅ እግዚአብሔር
እገሌ አርብ ሰርቋል ሰርቃለች የሚለውን ሳይሆን
ሐሙስ ዘክሯል ዘክራለች የሚለውን ነው የሚያየው
✅ አባቶቻችን እንደሚሉት
ሰይጣን ሰውን ለማጥፋት ምክንያት እንደሚፈልግ
እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ምክንያት ይፈልጋል።
✅ ምክንያት ከመፈለጉ የተነሳ
ጠጅ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል
በሬ እረዱ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል።
በግ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል ።
ወርቅ ብላቸው ስንቱ ይሳከለታል ብሎ
ቀዝቃዛ ዉኃ ሰጣችሁ ዳኑ አለ
ሰውን ለማዳን ወርዶ እስከዚህ ድረስ ዋጋ ይከፍላል ።
✅ ስለዚህ እግዚአብሔር
መንግስተ ሰማያትን ያህል ሀገር
በቀዝቃዛ ውኃ ሽጣት ይላሉ ሊቃውንቱ
ክፍትን ከመመዝገብ ፈጣሪ አምላክ ይጠብቀን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ጻዲቁ ንጉሥ በእደ ማርያም ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን በእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የጠበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንችላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
ከገድላት አንደበት
ወገኖቼ
ስንፀልይ እንዲህ እንላለን አደል ?
አቤቱ ወደፈተና አታግባን እንላለን
ምን ማለት ይመስላችኋል ?
ፈተና ማለት መከራ ፈርቶ ሃይማኖትን መካድ ነው ይላሉ።
ስለዚህ
ወደ ፈተና አታግባን ማለት ?
መከራ ፈርቼ ሃይማኖቴን ከምክድበት ቀን ሰውረኝ ማለት ነው ።
እግዚአብሔር
ረኃብ ፈርተን
በሽታ ፈርተን
ጦርነት ፈርተን
ሰይፍ ፈርተን
ክርስቶስን ከመካድ ይሰውረን 🙏
ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ
ያለ መጽሐፍ ለዚህ ነው
እዚህ ዉስጥ አሁን ሁላችንም ጀግና ጀግና እንሽታለን
ችግር የደረሰበት ቀን ግን ሰው ደካማ ነው ወገኖቼ
ሰዉ አፈር ነው ሰው ትቢያ ነው
ሁላችንም እንደነግጣለን
ፈርተን ከመካድ ይሰውረን
የሃይማኖት ብርታት ያድለን አሜን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
ተወዳጆች ሆይ
እየጾመ የማይሰጥ ሰው
ቆጠበ እንጂ ጾመ አይባልም
የቁርሱ ለምፅዋት መሆን አለበት።
እኛ ለቤት መጥረጊያ ያደረግነው ሽሚዝ
ለሌላ ሰው የጌጥ ልብስ ይሆነዋል ።
እኛ ምሳ በልተን ጥሬ እንቆረጥማለን
ሌላ ጌጥ ያምረናል ያንን ለድሆች መራራት አለብን።
ያ ነው ጾም ማለት ያ ነው ደግነት ማለት
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
ተወዳጆች ሆይ
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉ
መጨረሻው ያማረ ነው ይላል ሲራክ
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉ
መጨረሻው ያማረ ነው
እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰው
ግን ጀምሮ ነው የሚቀረው
ወዲያው ነው ሁሉም ነገር
ታይቶ ነው መጥፋት ነው ልክ እንደ ዕፀ ከንቱ
ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለው ሰው ግን
👉እሾህ ቢወጋው ነቅሎ ይሄዳል
👉እንቅፋት ቢመታው አንክሶ ይደረሳል
👉ቢሰበር እግሩን ጠምጥም ካሰበው ይደረሳል
👉እግዚአብሔርን መፍራት በልቡናው ያለው ሰው
እግዚአብሔርን ሳይፈሩ የጀመሩት ሥራ ግን
በጥሩ ፍጥንት ብንጀምረው
በተከናወነ አዕምሮ ብናከናውነው ብንጀምረው
በጣም ብዙ አእላፍን ይዘን ብንጀምረው
ይበላሻል።
እግዚአብሔርን መፍራት ይቀድማል።
እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምንማለት ይመስላችኋል ?
እግዚ አብሔርን ማክበር ለእግዚአብሔር መጠንቀቅ ማለት ነው።
እግዚአብሔርን እንድንፈራ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
ርዕሰሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
1) ሰላማዊ ሰው ማን ነው ።
ሀ ሰውን ያልበደለ
ለ የበደሉትን ይቅር የማይል
ሐ እንደ ክርስቶስ ዝም ብሎ የማይወድ
መ ቂመኛ የሆነ
2) ኃጢአት ማለት ምን ማለት ነው ?
ተወዳጆቹ
ሰላማዊ ሰው ማነው ካላችሁኝ
ሰውን ያልበደለ ሰው ነው
በሰው ቂም የማይቋጥር
እንዴት ብየ ቂም ይጥፋልኝ ? ልንል እንችላለን
የበደለኝ የበደለችኝ ብዙ ነው ልንል እንችላለን
እግዚአብሔር ላንተ ስንት ነገር ትቶልሀል ነው መልሱ
እግዚአብሔር የ30 ዓመት በደል ከተወልህ
አንተ የአንድ ቀን የሁለት ቀን የ3ት ቀን
የህትህን የወንድምህን በደል ለምን አተወውም
እግዚአብሔር ይሄን ሁሉ እዳ ትቶልህ የል
ሰርቀህ ዝም
ዘሙተህ ዝም
አመንዝረህ ዝም
ተሳድበህ ዝም
ደብድበህ ዝም
እግዚአብሔር ይሄን ሁሉ ዝም ብሎ አይቶሀል
ምን አለ የበደሉንን ይቅር ብንል ?
የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
ተፃፈ : - በ ዲ/ን ዑራኤል
ህዳር 8/2017 #አርባእቱ_እንስሳ_ሱራፌል_ወኪሩቤኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳን መላእክቱ ስም ለምናመሰግንበት ለአርባእቱ እንስሳ ሱራፌል ወ ኪሩቤል አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ #የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው ስለ እሳቸውም ወንጌልን የፃፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው
👉የፊተኛው #አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም #ላም ይመስላል ሦስተኛውም #የሰው_መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር #ንስር ይመስላል
👉የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም
👉ሁለተኛውም ስለ እርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ #እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ #ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት
👉የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
👉ነቢዩ ዳዊትም #በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም #በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወፃት አለ ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል
👉በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው #የአንዱም_ፊቱ_አራት ነው ክንፉም አራት ነው
👉እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም #እሳት_ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል
👉ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ #መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው
👉ለዚያ ለተገደለው #በግ ኃይልን፣ ባለ ፀግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ
👉በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ #ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ በእውነት ይገባዋል እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ
👉ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ #አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ #እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገፀ #ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል ገፀ #አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገፀ #ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገፀ #ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና
👉ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን ስለ አለሙ #በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና
👉አርባእቱ እንስሳ #ሱራፌልና_ኪሩቤል በምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቁልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️