kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ #ታኅሣሥ ፲ (10) ቀን።

❤ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት #ለተላስስና_ለአልዓዛር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ከታናሽነቱ ጀምሮ ጃንደረባ ለሆነ #ለአባ_ጥዋሽ ለዕረፍት በዓል፣ ከቊጥስጥንጥንያ አገር ለከበሩ ሰዎች ልጅ ለሆነች #ለቅድስት_ሱርስት ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለነበረ #ለቅዱስ_አባ_ሳዊሮስ ከእስክንድርያ አገር ወጪ ወደሆነች ደብረ ዝጋግ ገዳም ሥጋው ለፈለሰበት በዓልና ለከበረ አባት ጻድቅ ኤጲስቆጶስ የስሙ ትርጓሜ የሕዝብ አሸናፊ ለሆነ #ለአባ_ኒቆላዎስ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ አገር ስልሣኛ ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ታውፋኔዎስ ዕረፍት፣ ከቅዱሳን #ከሜልዮስና_ከታውፍያ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ተላስስና_አልዓዛር፦ ይህም ተላስስ ከነነዌ አውራጃ ከባቢሎን ሰዎች ወገን ነው የፋርስ ንጉሥ ሳቦርም ይዞት "ለእሳት ስገድ ለአማልክትም ሠዋ" አለው ቅዱስ ተላስስም " እኔስ ለፈጣሪዬ እግዚአብሔር እሰግዳለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ እንጂ ለጣዖት አልሠዋም" አለው። ያስፈራውም ዘንድ የቅጣት መሣሪያዎችን አስመጣ እርሱ ግን አለሰፈራም መቶ ግርፋትም ለረዥም ጊዜ እንዲገርፋት አዘዘ ከዚህም በኋላ "ተላስስ ሆይ ከዚህ ሥቃይ እንድታርፍ ለአማልክት ሠዋ" አለው እርሱም "ፈጣሪዬ ስለሚጠብቀኝ ለእኔ ሥቃይህ አልታወቀኝም" አለው።

✝ በዚያንም ጊዜ ሁለት መቶ ጊዜ ገረፉት በዐይኖቹም ውስጥ የብረት ችንካሮችን ተከሉ መናገርም እስከሚሳነው በነሐስ መክደኛ ሸፍነው ደበደቡት ራሱንም በሰይፍ ቆረጡ። ከዚህም በኋላ አልዓዛርን አቀረቡት ንጉሥ ሳቦርም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ለረከሱ አማልክቶቹም መሠዋትን እምቢ ባለው ጊዜ ወዲያውኑ ወደ እሳት ወረወረው ያማረ ምስክነቱንም ፈጸመ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ቅዱሳን ተላስስና አልዓዛር ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ጥዋሽ፡- ይኽም ቅዱስ ከልጅነቱ ጀምሮ ድንግል ሆኖ በምንኵስና በታላቅ ተጋድሎ የኖረ ነው፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ እስክንድርያ ሲጓዝ በመንገድ ላይ አንዲት አይሁዳዊት ሴት ስታለቅስ አገኛትና ምን እንደሆነች ጠየቃት፡፡ እርሷም "ክርስቲያን መሆን እሻ ነበር" አለችው፡፡ አባ ጥዋሽ የነፍሱን ጥቅም አስቦ ሊተዋት ነበር ግን ሴቲቱ መዳን እየፈለገች ቢተዋት በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ በደል እንዳይሆንበት ከእርሱ ጋር ወሰዳትና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃት፡፡

❤ ከዚህም በኋላ አባ ጥዋሽ ከሴቲቱ ጋር ሆኖ በየገበያው ቦታ ሁሉ እየዞሩ ነለዳያን ይመጸውቱ ጀመር፡፡ የእስክንድርያ መነኰሳትም እርሷ ሚስቱ እንደሆነች አስበው በዚህ ተሰነካከሉበት፡፡ ይዘውትም ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ዮሐንስ ዘንድ አቀረቡት፡፡ አባ ዮሐንስም ሁለቱን ተያይተው እንዲታሰሩ አዘዙ፡፡ በዚያችም ሌሊት ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ዮሐንስ በሕልማቸው አባ ጥዋሽ የቆሰለ ጀርባውን እያሳያቸው "ያለበደሌ ለምን አቆሰልከኝ?" ሲላቸው ተመለከቱ፡፡ አባ ዮሐንስም በነቁ ጊዜ አባ ጥዋሽን አስመጥተው በግርፋት ብዛት የቆሰለ ጀመርባውንና ፍጹም ድንግል መሆኑን አይተው እጅግ አዝነው አለቀሱ፡፡ "ይቅር በለኝ" ብለው በፊቱ ወደቁ፡፡ ከዚያም አባ ጥዋሽን ያመጡትንና የደበደቡትን ሰዎች ከማዕረጋቸው አውርደው ለ3 ዓመታት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከመቀበል ከለከሏቸው፡፡ ካሳ ይሆነውም ዘንደ ለአባ ጥዋሽ ብዙ ገንዘብ ቢሰጡት እርሱ ግን ምንም ሳይቀበል ወደ በዓቱ ተመልሶ ሄዶ ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጥዋሽ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_ሱርስት፡- ይኽችም ቅድስት ከቁስጥንጥንያ አገር እጅግ ከከበሩ ወገኖች የአንዱ ልጅ ናት፡፡ ለአንድ ለከበረ ሰው ልጅ በታጨች ጊዜ አባቷን "አባቴ ሆይ! አስቀድሜ ወደ ቤተ መቅደስ ሄጄ እሰግድ ዘንድ ፍቀድልኝ በምመለስበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደፈቀደ ይሁን" አለችው፡፡ አባቷም "አስቀድመሽ ወደ ባልሽ ግቢ፣ ሰርግሽ ከተፈጸመ በኋላ ከእርሱ ጋር ወደ ወደድሽው ሄደሽ ስዕለትሽን ትፈጽሚያለሽ" አላት፡፡ እርሷም መልሳ "በድንግልናዬ ሳለሁ ወደዚያች የከበረች ቦታ ሄጄ ልጸልይ ለእግዚአብሔር ቃል ገብቻለሁና ቃሌን ብዋሽ ፈጣሪ በእኔ ላይ ይቆጣል" ስትለው አባቷ ከሚያገለግሏት ወንዶችና ሴቶች አሽከሮች ጋር ለምጽዋትም የምትሰጠው 300 የወርቅ ዲናር ሰጥቶ ላካት፡፡

❤ ቅድስት ሱርስትም እዚያ በደረሰች ጊዜ የከበሩ ቦታዎችን ሁሉ እየዞረች ተሳለመች፣ ወደ ግብጻውያን ገዳምም በደረሰች ጊዜ አንድ አረጋዊ መነኩሴ ማቅ ለብሶ አገኘችውና የልቧን ሀሳብ ሁሉ ማለትም ልትመነኩስ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ እርሱም "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሊሄዱ በተዘጋጁ ጊዜ ወደ ስውር ቦታ ገብታ ለወላጆቿ "እኔ ሰውነቴን ለእግዚአብሔር አቅርቤያለሁ አታገኙኝምና አትፈልጉኝ" ብላ ደብዳቤ ጻፈች፡፡ ደብዳቤውንም በልብሷ አሥራ ከዕቃ ውስጥ አኖረችው፡፡ ሰዎቹም ከእነርሱ ጋር አብራ የምትሄድ መስሏቸው ዕቃ ጭነው በቀደሟት ጊዜ አንዱን አገልጋይ ይዛ አስቀረችውና "ወደ ጎልጎታ ገብቼ ልጸልይ እሻለሁና" ብላ ምሥጢሯን እንዲጠብቅ ነገረችው፡፡

❤ ከዚህም በኋላ ወደዚያ ሽማግሌ መነኩሴ ዘንድ ተመልሳ የያዘችውን 300 የወርቅ ዲናር ለድኆችና ጦም አዳሪዎቸ እንዲያከፋፍለው ሰጠችውና ያመነኵሳት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ጽናቷን አይቶ ፈቃደ እግዚአብሔርም መሆኑን ዐውቆ ራሷን ላጭቶ የምንኩስና ልብስ አለበሳት፡፡ እርሷም እግዚአብሔር ወደፈቀደላት ወደ አንዲት ዋሻ ሄዳ በዚያ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረች፡፡ በዚህም ጊዜ ዕድሜዋ ገና 12 ዓመት የነበረ ቢሆንም የሰውን ፊት ሳታይ በዚያች ዋሻ ውስጥ ለ27 ዓመታት በተጋድሎ ኖረች፡፡

❤ ቃህራ ከሚባል አገር በገድል ሥራ የሚኖር ሲላስ የሚባል መነኰስ ነበር፡፡ በቀልሞን ዋሻ የሚኖር አንድ ጓደኛ መነኰስ አለውና ፋሲካ በደረሰ ጊዜ እርሱን ጎብኝቶ በረከት ለመቀበል ሄደ፡፡ በሄደም ጊዜ አላገኘውምና እርሱን ፍለጋ ተራራ ለተራራ ዞረ፡፡ በዚያም የእግር ዱካ አገኘና ዱካውን ተከትሎ በመሄድ መግቢያው ላይ ሲደርስ "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከኝ" አለ፡፡ ከውስጥም ያለው ድምጽ ስሙን ጠርቶት "ሲላስ ሆይ አንተ ካህን ነህና ልትባርከኝ ይገባል" አለው፡፡ ሲላስም ወደ ውስጥ እንደገባ ቅድስት ሱርስትን አገኛት፡፡ እርሷም ምሥጢሯን ሁሉ በዝርዝር ነገረችው፡፡ ወዲያውም በዚች ቀን ታኅሣሥ10 በሰላም ዐረፈች፡፡ ሲላስም በዚያች ዋሻ ውስጥ በክብር ገንዞ ቀበራት፡፡ ገድሏንም ጻፈላት፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሱርስት ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #የአንጾኪያ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት_የቅዱስ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿በአሚን ተአማኒ (ሰማዕተ ጽድቅ)
✿እስትንፋሰ ክርስቶስ ዘአስጋጅ
✿በድላም ወአርምያ
✿ወዘካርያስ ካህን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ካላበደ በቀር አንድ ባሪያ የጌታዉን ስም በግድየለሽነት ወይም በከንቱ አይጠራም፤ ታዲያ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔርን እንዲሁ በማይረባ ነገር ደጋግሞ መጥራቱ እንደ ምን ያለ ስንፍና ነው?

የወንጌል መጽሐፍን መውሰድ ስትፈልግ መጀመሪያ እጅህን ታጥበህ፣ ፈርተህና ተንቀጥቅጠህ አክብረህም ትቀበለዋለህ፤ታዲያ የወንጌሉን ጌታ በአንደበትህ በከንቱ ደጋግመህ ትጠረዋለህን?

የሰማይ ኃይላት ይህንን ስም እንደ ምን ባለ ፍርሐት፣ እንደ ምን ባለ ድንጋጤ፣ እንደ ምንስ ባለ መደነቅ ኾነው እንደሚጠሩት ልትማር ትወዳለህን? ነቢዩ እንዲህ ሲል ገልጾታል፡- “እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፡፡ አንዱም ለአንዱ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የጸባዖት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ኹሉ ከክብሩ ተሞልታለች' እያለ ይጮኽ ነበር” (ኢሳ.6፡1-3)፡፡

ሲያመሰግኑትና ሲያከብሩት እንኳን እንደ ምን ባለ ረዓድ፣ እንደ ምንም ባለ ፍርሐት ስሙን እንደሚጠሩ ታስተውላለህን?

አንተ ግን በጸሎትህና በልመናህ በፍርሐት፣ በአስተውሎትና ራስን በመግዛት ልታደርገው ሲገባህ እንዲሁ በግድየለሽነት ኾነህ ስሙን ትጠራለህ! አልፈህ ተርፈህም ይህን ስም ለመጥራት በፍጹም በማይገባ በመሐላ መኻከል የተለያዩ ዓይነት ርግማኖችን ለማስተላለፍ ትጠቀምበታለህ! ታዲያ እንዲህ ለማድረጋችን የፈለግነውን ያህል ምላሽ መስጠት ብንችል እንኳን ሊደረግልን የሚችል ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

አንድ ንግግር ዐዋቂ የኾነ የአሕዛብ ሰው በዚህ የስንፍና ልማድ ከመያዙ የተነሣ ሲኼድ የቀኝ ትከሻዉን ኹልጊዜ ያንቀሳቅስ ነበር ይባላል፡፡

በኹለቱም ትከሻዎቹ አንጻር ቢላዎችን በማኖርም አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቢላው እንዳይቈርጠው በመፍራት ይህን ልማድ ሊያስወግደው ችሏል! አንተም በአንደበትህ ላይ እንዲህ አድርግ፡፡

በቢላ ፈንታም የእግዚአብሔር ቅጣትን ፍርሐት አንጠልጥልበት፤ በእርግጠኝነትም ከዚህ ትሻሻላለህ! ምናልባት የማይቻል - በጭራሽ የማይቻል - መስሎ ሊታይህ ይችል ይኾናል፤ ለተጨነቁበትና ለተጉበት ጉዳዬም ብለው ለያዙት ግን ይቻላል፡፡


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ልብ አምላክ ዳዊት እንዲህ ይላል።

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤
እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል፡፡
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤
ሕያውም ያደርገዋል፤
በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፤
በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም፡፡
እግዚአብሔር አብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤
መኝታው ውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል፡፡»

መዝ ፡ - 140:1-3 ::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ታኅሣሥ 8 ቀን ተወለዱ። በዚህች ቀን ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ "ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን፤ ከጨለማ ወደ ብርርሃን ላወጣኸኝ" ብለው ፈጣርያቸውን አመስግነዋል። በ40ኛው ቀን የጌታ ሐዋርያት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ፊሊጶስና እንድርያስ ሆነው ጥር 17 ቀን ክርስትናን አቡነ ሙሴን አነሱዎቸው። በ3 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ለቤተ ከክርስቲያን ሰጧቸው። ቅዱስ ፋኑኤልና ቅዱስ ዮናኤል ሕብስት ሰማያዊ እያመጡ ይመግቧቸው ነበር። ከዚህ በኋላ መምህራቸው ዝክረ ጻድቅ ብሉያትንና ሐዲሳትን አስተማራቸው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ እጅ ዲቁና ተሾሙ።

❤ እመቤታችን ማርያምም ለብፁዓዊ ሙሴ ልፋፈ ጽድቅ፣ ሰኔ ጎልጎታን፣ ባርቶስና ራዕየ ማርያምን ሰታቸዋለች። ወገባቸውን ከጠጉር በተሰራ መታጠቂያ ይታጠቁ ነበር። አቡነ ዘበሰማያትም በጀመሩ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተውላቸው ከአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ጀምሮ ሁሉንም ቅዱሳን በግልጥ ያያሉ። ሲሰግዱ እንባቸው ደረታቸውና እግራቸውን እያራሰ በመሬት ይፈሳል። በዓለም ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲን አንጸዋል። የሕንፃ ሥራ ከመደመራቸው በፊት 40ቀን ይጾማሉ። ሁለቱ መላእክት ቅዱስ ፍርክኤልና ቅዱስ ፍናኤል እየረዷቸው መቅደስን ያንጻሉ። የዋሻ ቤተ መቅደስ ስራ ጎን ለጎን መስቀልና ሌሎች ንዋየ ቅዱሳት ይሰራሉ። የሚሰሯቸው መቅደሶች ከፊሉ የሚታዩ ምዕመናን የሚገለገሉባቸው ሲሆን የቀሩት የማይታዩ ስውራን የሚገለገሉበት ነው።

❤ አቡነ ሙሴ ጵጵስና የተሾሙት በ12ቱ ሐዋርያት በአንድነት ነው። ዘመናቸውን ሁሉ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በመሆን የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መንበር አጥነዋል። በድንግልናቸው በንጽሕናቸው የከበሩ 12ክንፍ የተጎናጸፉ ናቸው። ጥቂቶች ለማየት የታደሉትን ብሔረ ብፁዓን ሄደው አይተዋል።

❤ አቡነ ሙሴ በግብፅና በእስራኤል መካከል ሲካር በሚባል ቦታ ካገለገሉ በኋላ ጣዖታትን ለማሳፈር ወደ መቄዶንያ ሄደው ጣዖት አምላኪውን ንጉሥ ገሰጹት። ንጉሥ ተቆጥቶ አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ በብረት አስደብድቦ በብረት አልጋ ላይ አስተኝቶ እሳት አነደደባቸው። ቅዱስ ሚካኤልና ገብርኤል ግን ዳሰው ፈወሷቸው። በማግስቱ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢወስዷቸው ምንም እንዳልሆኑ ንጉሡ በማየቱ በንዴት ሰውነታቸውን በሰይፍ አስቆራረጠ። ከሰውነታቸው ደም፣ ውሃ፣ ወተትና መዓር ወጣ። ጌታችንም አድኗቸው በስምህ የተማፀነውን መልካም ነገር አደርግታለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው።

❤ በግብፅ አንስጣስዮስ ቴዎዶስዮስ ተብለው ሲነግሱ መላእክት የአባቱ የዳዊት መንግሥት ቅባት ቀቧቸው፤ የመንግሥት ልብስ አለበሷቸው፤ የመንግሥት ሥርዓትን ሁሉ ሰጧቸው። የጣዖታትን ቤት አፍርሱ ቤተ ክርስቲያንን ሥሩ በማለት ኅዳር12 አዋጅ ነጋሪን ላኩ። ጌታችን በግብፅ ተሶዶ ሳለ ለአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የተናገረው ትንቢት ተፈፀመ "ከልጅህ የሚወለድ በግብፅ ያሉትን ጣዖቶች አፍርሶ ሃይማኖትን ያጸናል" ብሎ ነበር። እዲሁም ቅድስት አርሴማ ሳትወለድ በስሟ የተሰየመውን ታቦት በግብፅ ያገኙና ያከበሩ ናቸው (ገድለ አርሴማ 7ኛ ተዓምር)።

❤ በግብፅ ደብረ ምጥማቅ ማርያም በመጀመሪያ ሰርተው የቀደሱት አቡነ ሙሴ ናቸው። በተጨማሪ ብዙ የህንጻ ቤተ ክረስቲያንና የዋሻ ቤተ ክረስቲያን አንጸዋል። እንደ ቅዱሳን ብዙ ድንቅ ተዓምር አድርገዋል። ለምሳሌ አውሬ ገድሏቸው ተጠራቅሞ የነበረ አፅም ላይ ጸልየው አራት ሺህ የሞቱ ሰዎችን ከሞት አስነስዋል። 40ዓመት በንግሥና ከቆዩ በኋላ ከብዙ ተከታዮቻቸው ጋር ወደ አስቄጥስ ገዳም በደመና ስጓዙ በበረሃው ተርበው ለወደቁት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ መና ወርዶላቸው መግበዋል አስቄጥስ ገዳም ሲደርሶ አቡነ መቃርስ ነበሩ የተቀበሏቸው፡፡ አቡነ ሙሴ በአስቄጥስ በአቡነ እንጦንስ ስም የመጀመርያውን ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ከፈፀሙ በኋላ አቡነ እንጦንስንና አቡነ መቃርስ በምንኵስና ልብስ፣ በመላእክት አስኬማ፣ በቅንዓት፣ በቀሚስና በቆብዕ ላይ ለ40ቀን ጸልየው ጥር22 ተክለማርያም ብለው ሰይመው አመነኰሷቸው። በዚያውም አቡነ መቃርስ ከበታቻቸው ብፁዓዊ ሙሴን ሾሙ። በአስቄጥስ ብዙ ተከታዮቻቸውን አመንኵሰው ቀድሞ ወደ ሰሯቸው ቤተ መቅደሶች ይልኳቸው ነበር። የቀሩት ደግሞ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አብረዋቸው መጥተዋል።

❤ የኢትዮጵያ የመጀመርያው ጳጳስ አቡነ ሰላማ በማረፋቸው ሁለቱ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ ጳጳስ እንዲልኩላቸው ከእጅ መንሻ ጋር ወደ ግብፅ ላኩ። አቡነ አትናቴዎስ ፈቃደ እግዚአብሔር ጠይቀው አቡነ ሙሴ ከአስቄጥስ ገዳም ለኢትዮጵያውያን አባት እዲሆኑ አቡነ ሚናስ ብለው ሾሙ። ከሦስት ሺህ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ቅርስ ይዘው አባታችን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ሕዝቡ በደስታ ተቀበሏቸው። ብዙ መጽሐፍትን ከአረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመው ጽፈዋል። ይጽፉበት የነበረው ብዕር አድሮ በማግስቱ ለምልሞ አብቦ ይገኛል። ቀለም ይበጠብጡበት የነበረው የቀንድ ዋንጫም ከመሬት ተጣብቆ ያገኙት ነበር። በእጃቸው ሲያላቅቁት ከመሬት ጠበል ይፈልቃል፣ በጠበሉም ህሙማንን ፈውሰውበታል።

❤ በኢትዮጵያ አምስት መቶ የዋሻ ቤተ ክስቲያን ያነጹ ሲሆን በአጠቃላይ በመላው ዓለም ከዐሥር ሺህ በላይ ቤተ ክርስቲያ ሰርተዋል፣ አንጸዋል (መለከት መጽሔት 2007 ዓ.ም)። በእንቁና በእብነ በረድ ከሰራቸው ቤተ ክርስቲያኖች መካከል በአራራት ደብር (ከምድር ጥፋት በኋላ የኖኅ መርከብ መጀመርያ ያረፈችበት) በጻድቁ ኖኅ ስም፣ አብርሃም ሥላሴን በድንኳኑ ባስተናገደበት ስፍራ በቅድስት ሥላሴ ስም፣ በሕንድ (በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ መቃብር ቦታ) በቅዱስ ቶማስ ስም፣ በአርማንያና በፋርስ (በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋውን ባሳረፉበት ቦታ) በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም።

❤ በኢትዮጵያ በአቡነ ሙሴ ከታነጹት ቤተ ክርስቲያ ውስጥ የተወሰኑት፦

1.የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ገዳም (ባለ ሰባት መቅደስ ፎቅ)፣ የረፍታቸው ቦታ፣ በትረ ሙሴያቸውና የእጅ መስቀላቸው ያለበት (ሰሜን ወሎ ዳውንት)

2.ደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ላይ በምሥራቅ በኩል ስውር ቤተ መቅደስ (ድርሳነ፡ራጉኤል)

3.አእማድ ቅድስት ሥላሴ ገዳም (መቄት) እንደ አቡነ አሮን መንክራዊ ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማይገባው፣

❤ በመጨረሻ ብጹዕ አቡነ ሙሴ በቤተ ሚናስ ቤተ መቅደስ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ ገዳም መሰከረም 4 በዕለተ እሁድ አረፋ። ወርሃዊ በዓላቸው ወር በገባ በ4 ነው። በተለይ ጋብቻን ሚቀድሱ፣ ክህነት የሚባርኩ፣ መናንያንን የሚያጸኑ አረጋዊን አባት ናቸው። ከአባታች አቡነ ሙሴ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ገዳም ያሳተመው መጽሔት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 8/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር

👉በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ #በቡነዳ_ገዳም ገቡ

👉በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ #ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ

👉ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም #ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል

👉ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ

👉ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው #ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል

👉ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሣሥ 8/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 7/2017 #አጋእዝተ_ዓለም_ቅድስት_ሥላሴ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው

👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው

👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ፣1፤2 ምሳ 30፤4

👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ፣ 2፤7

👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።

👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም

👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርፅ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረፀ ነው።

👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ.2፥7

👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው ኢዮ.26፥13

👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ (ቅድስት ሥላሴ) ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በረድኤት በበረከት ይጎብኙልን ይባርኩልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 7/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 7/2017 #ስብከተ_ነብያት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ታኅሣሥ ሰባት በዚህች ዕለት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ #በከበሩ_ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ሆነ ።

👉ይህች ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት #ስብከት ትባላለች ስብከት ማለት በቁሙ #የምስራች አዲስ ዜና መንገርን የሚመለከት ሲሆን ዋናው ምሥጢር ግን ከነገረ ድኅነት #ከመዳን_ትምሕርት ጋር የተገናኘ ነው።

👉በዚህ ዕለት (ሳምንት) ሁሉም #ነቢያት ከነ ትንቢታቸው ይታሰባሉ ዘመነ ስብከትም ከታሕሳስ 7 እስከ 13 ያለውን ይይዛል ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ #እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በላ

👉በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም #ተፈረደበት በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል #ቃል_ኪዳንን ሰጠው

👉ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ይቆጠር ጀመር ስለ #እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር ሱባኤ ይቆጠር ምሳሌም ይመሰል ተጀመረ

👉ከአዳም እስከ ሙሴ ዘመነ አበው ምሳሌያት ይበዛሉ ከሙሴ እስከ ዳዊት ዘመነ መሣፍንት ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ በዘመነ ነቢያት ነገሥት ግን ትንቢቶች ስለ #ክርስቶስና ስለ #ማደሪያ_እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል

👉 #ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በፆም በፆሎትና በትሕርምት ኑረዋል እንባቸውን አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል መድህን #ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል አድኖናል

👉ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር መፃዕያትን ለወደ ፊት የሚሆነውን የሚያውቅ ሰው ማለት ነው ሃብተ ትንቢት #የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በፀጋ ይሰጠዋል እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች #ቅዱሳን_ነቢያት በመባል ይታወቃሉ

👉ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምፅዓት ድረስ ፀጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ ሐዋ.11፥27 ቅዱሳን ነቢያት #ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ ይገስፃሉ

👉ከበጐ ሃይማኖታቸው ንፅሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል"እስመ በአንፅሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት #ለእግዚአብሔር ወተናፀሩ ገፀ በገፅ እንዳለ አባ ሕርያቆስ (ቅዳሴ ማርያም)

👉 የብዙ #ነቢያት ፍፃሜአቸው መከራን መቀበል ነው እውነትን ስለ ተናገሩ አንዳንዶቹ በእሳት አንዳንዶቹ በሰይፍ አንዳንዶቹ በመጋዝ ተፈትነዋል ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል

👉ስለዚህም መከራቸው #ለቤተ_ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ ሌሎች ደከሙ እናንተ በድካማቸው ገባችሁ ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል ዮሐ.4፥36

👉ነቢያት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል ሽተዋልም ብዙ ነቢያትና ፃድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ፈለጉ እንዳለ ጌታ በወንጌል ማቴ.13፥16 1ዼጥ.1፥10 ዛሬ ግን በሰማያት ፀጋ በዝቶላቸው ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ

👉 #ቅዱሳን_ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት 4ቱ ዐበይት ነቢያት 12ቱ ደቂቀ ነቢያት እና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ

👉15ቱ #አበው_ነቢያት ማለት፤ቅዱስ አዳም አባታችን፣ ሴት፣ ሔኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ኄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖህ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ሙሴ እና ሳሙኤል ናቸው

👉4ቱ #ዐበይት_ነቢያት ማለት ፤ ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል፣ ቅዱስ ኤርምያስ፣ ቅዱስ ሕዝቅኤልና፣ ቅዱስ ዳንኤል ናቸው

👉12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት ማለት፤ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ አብድዩ፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ኢዩኤል፣ ዕንባቆም፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው

👉 #ካልአን_ነቢያት ማለት፤ኢያሱ፣ ሶምሶን፣ ዮፍታሔ፣ ጌዴዎን፣ ዳዊት፣ ሰሎሞን፣ ኤልያስ እና ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው

👉 ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ የይሁዳ ኢየሩሳሌም፤የሰማርያ እሥራኤል፤የባቢሎን፤በምርኮ ጊዜ ተብለው ይጠራሉ

👉 #በዘመን_አከፋፈል ደግሞ፤ከአዳም እስከ ዮሴፍ የዘመነ አበው ነቢያት፤ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል የዘመነ መሳፍንት ነቢያት፤ ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት የዘመነ ነገሥት ነቢያት፤ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ የዘመነ ካህናት ነቢያት ተብለዉ ይጠራሉ

👉አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሣን #አባቶቻችን_ነብያት ረድኤት በረከት ያሣትፈን በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን የሠጣቸዉ ቃል ኪዳን በስጋም በነፍስም ዋስ ጠበቃ ይሁነን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 7/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ ሃያ ዓመትም ሲሆነው አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበውና ንጉሡም በአባቱ ፈንታ ምስፍና ሾመው አባቱ በዕድሜው ሸምግሎ ነበርና። ከጥቂት ወራትም በኋላ ጣዖታትን የማያመልኩ ክርስቲያኖችን ሁሉ ይገድል ዘንድ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ምልክትን ወደ እንጽና አገር መኰንን ደረሰ። መኰንኑም ክርስቲያኖችን እየፈለገ ወደ ሻው ከተማ ደረሰ ያን ጊዜ ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደሚአመልከው ክፉዎች ሰዎች ይህን ቅዱስ ፊቅጦርን ወነጀሉት ያን ጊዜም እንዲአመጡት አዘዘና በአመጡት ጊዜ ለጣዖታት እንዲሠዋ አስገደደው እምቢ በአለውም ጊዜ በወህኒ ቤት እንደመአሥሩት አዘዘ።

❤ በዚያም እያለ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሰማይ አወጣው የወህኒ ቤት ጠባቂዎችም በአጡት ጊዜ ተሸበሩ። ከሰባት ቀኖችም በኋላ አግኝተውት ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑ ግን ራራለትና ወደ ንጉሡ ሰደደው ንጉሡም እግዚአብሔርን ከማምለክ ይመልሰው ዘንድ በማባበል ብዙ ሽነገለው። መመለስም በተሳነው ጊዜ አውጣኪያኖስ ወደሚባል መኰንን ሰደደው። እንዲህም ብሎ አዘዘው "እንሆ ፊቅጦርን ወደአንተ ልኬዋለሁ ያንተን ምክር ከሰማ ለአማልክት ይሠዋ ካልሰማህ ግን ግደለው እንጂ አትራራለት"። አለው።

❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሊወስዱት እጆቹንና እግሮቹን አሠሩ በአፉም የብረት ልጓም አግብተው በመርከብ አሳፈሩት የእግዚአብሔርም መልአክ ወርዶ ከማሠሪያው ፈትቶ ወደ መኰንኑ አደረሰው ቅዱስ ፊቅጦርም መኰንኑንና ከሀዲውን ንጉሥ ሊረግም ጀመረ መኰንኑም ተቆጣ ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃይቶ በወህኒ ቤት አሠረው። በዚያም ሳለ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ተገለጠለትና ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙ በሽተኞችን የሚፈውስ ሆነ።

❤ መኰንኑም ይህን ሰምቶ ተቆጣ ወደርሱ አስመጣውና ይመለሰው ዘንድ ደግሞ ሸነገለው ቅዱስ ፊቅጦር ግን የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ በዚያንም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንዲጐትቱት ከዚያም ከውሽባ ቤት እሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨመሰሩት አዘዘ እንዲህም መልካም ተጋድሎውን ፈጸመ። ሥጋውን ግን ከዚያ ውሽባ ቤት አላወጡትም በመሰላል ወርደው በአማሩ ልብሶች ገንዘው በሽቱዎች አጣፈጡት እንጂ በላዩ ቤተ ክርስቲያንን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ፊቅጦር በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ5 ስንክሳር።


✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕት ዐመፃ። ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ። ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት"። መዝ 34፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 10፥11-ፍ.ም ወይም ገላ 3፥21-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 5፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥14-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥35-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ነቢዩ ናሆም የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለጸአተ_ነፍስከ እምነ ሥጋከ ዘተሰቅለ። #ለበድነ_ሥጋከ_ሰላም ዘመግነዘ ደመ ተጠብለለ። እንተ ነሣእከ #እንድርያስ_እምኀልከ_ኀይለ_አብ ኀይለ። ቃልከ ውስተ ኵሉ ሶበ መሀረ ወንጌለ። ሰይፈ ሃይማኖት ያርብሐዊ ነፍሰ ካሕድ ቀተለ"። ትርጉም፦ #ከተሰቀለው_ሥጋህ_ለተለየው_ነፍስህ_ሰላም እላለሁ፤ በደም መግነዝ ለተጠበለለው #የሥጋ_በድንህ_ሰላም_እላለሁ፤ #ከአብ_ኀይል_ከወልድ_ኀይልን_የተቀበልክ_ቅዱስ_እንድርያስ_ሆይ! አንደበትህ በኹሉም ወንጌልን በአስተማረ ጊዜ የሃይማኖት ሰይፍ ወታደር የክሕደትን ነፍስ ገደለ። #መልክዐ_ቅዱስ_እንድርያስ።

✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ረድአ_ኢየሱስ_ኬንያ። እንተ ሰበከ ወንጌሎ ወመሀርከ በኒቆምድያ። እዜምር ለከ ወእየብብ በሃሌ ሉያ። አንቅሐኒ እምኀኬትየ እንድርያስ ሐዋርያ። ከመ በእዴከ ነቅሐት እሙታን ልድያ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_4።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 3/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ፋኑኤል
#አቡነ_ዜና_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት እለት ነው የሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ፋኑኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው #የጻድቁ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአላቶቹ ረድኤት በረከት ያሣትፈን አሜን

👉በዚህም ቀን #የሊቀ_መላእክት_የቅዱስ_ፋኑኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነዉ ይህም ታላቅ መልአክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት እና አባት ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም #እግዚአብሔር አምላክ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ይማፀኑት ነበር

👉 #ለእግዚአብሔር ወንድ ልጅ ብንወልድ እርሱ ወጥቶ ወርዶ ያበላናል አንልም ያንተን ቤት ያገለግላል ሴትም ብትሆን ጋግራ ታብላን ፈትላ ታልብሰን አንልም ሀርና ወርቅ እየፈተለች መሶበ ወርቅ እየሰፋች #ቤተ_መቅደስን ታገለግላለች እንጂ ብለው ስዕለትንም ተስለው ነበር

👉ለአብርሀም እና ለሳራ ይስሐቅን ዘፍ.21፥1-8 ለሕልቃና እና ለሐና ነብዩ ሳሙኤልን 1ኛ ሳሙ.1፥1-21 የሰጠ አምላክ ዛሬም የእነዚህን ቅዱሳን እንባቸውንና ልመናቸውን ሰምቶ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰጣቸው

👉እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእናት እና አባቷ ቤት እስከ 3 ዓመት ድረስ ከቆየች በኋላ በስእለታቸው መሰረት ለቤተ መቅደስ ሰጡ ቤተ መቅደስ ከደረሱ በኋላ ስእለታቸውን ለሊቀ ካህኑ ለዘካርያስ በሰጡት ወቅት ሊቀ ካህኑ እና ሌሎች የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ካህናት የምግቧ ነገር እንዴት ሊሆን ነው ብለው እጅግ ተጨነቁ

👉በዚህ ወቅት ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ የሆነው መልዐኩ ቅዱስ ፋኑኤል ሰማያዊ ጽዋ አና ሰማያዊ ሕብስት ይዞ ረብቦ ታየ ሊቀ ካህኑ ዘካርያስ ለኔ የመጣ ነው ብሎ ወደ መልአኩ ጠጋ ሲል ያኔ ቅዱስ ፋኑኤል ወደ ላይ ከፍ አለ የሊቀ ካህኑ ምክትል የነበረው ስምኦንም ሲቀርብ መልአኩ አሁንም ከፍ አለ

👉ከዛም ህፃኒቱን እስቲ ተጠጊ ብለዋት ስትጠጋው መልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት አረገ ይህም የሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ነው

👉 በተጨማሪም #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ፋኑኤል ድርሳነ ፋኑኤል ላይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ሰዳዲ ሰይጣናት ወመድፍነ አጋንንት እያለ ይጠራዋል ይሕም ማለት ሰዎችን በልዩ ልዩ በሽታዎች እና እንቅፋቶች ሰዎችን የሚያሰናክሉ አጋንንትን እያሳደደ ወደ ጥልቁ የሚከታቸው መልአክ ነው ሲል ነው

👉ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ፋኑኤል በ2ኛ ነገ.6፥14 ላይ የሶሪያ ንጉስ ወልደ አዴር እስራኤልን በቁጥጥር ባደረገ ጊዜ ኤልሳዕንም ሆነ የእስራኤልን ልጆች ለማዳን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ሰራዊቱን አስከትሎ በከተማዋ ሰፈረ ከዛም የጠላትን ሰራዊት ዓይን አጠፋ ለኤልሳዕም ሆነ ለእስራኤል ልጆች የድል ካባ በአንድ ምሽት አልብሷቸው ከአይናቸው ተሰወረ

👉ይህ ታላቅ መልአክ በ1ኛ ነገ.19፥5-18 በምናገኘው ታሪክ ላይ ነብዩ ኤልያስን ከተኛበት እየቀሰቀሰ እንጎቻን ብላ ሲለው የነበረው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ነው

👉ሌላው የአዳም 7ኛ ትውልድ የሆነው ሞትን ሳያይ የተሰወረው ሄኖክ እንዲህ ሲል ጠቅሶታል አራተኛውም የዘላለም ሕይወትን የሚወርሱ ሰዎች ተስፋ ሊሆን ንሰሐ በሚገቡ ሰዎች ላይ የተሾመው ፋኑኤል ነው ሔኖክ.10፥15 የመልአኩ ጥበቃ እና ተራዳኢነት አይለየን "አሜን"

💒 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 💒

👉ዳግመኛም በዚህች ቀን #የፃድቁ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው አባ ዜና ማርቆስ በሃገራችን በተለይ በደቡብ ምድረ ጉራጌ ስመ ጥር ሐዋርያዊ ጻድቅ ናቸው ምድረ ሽዋ ደግሞ እርሳቸውን ጨምሮ የብዙ ቅዱሳን መፍለቂያ ናትና ክብር ይገባታል ነቢየ ጽድቅ ዳዊት "ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ" "የጻድቃን (የቅኖች) ትውልድ ይባረካል" (መዝ.111) ያለው ነገር በምድረ ዞረሬ (ጽላልሽ) ተፈጽሟል።

👉ሦስት ወንድማማች የተባረኩ ካህናት በስፍራው ነበሩ ስማቸው ጸጋ ዘአብ፣ እንድርያስና ዮሐንስ ይባላል ከእነዚህ መካከልም ጸጋ ዘአብ እግዚእ ኃረያን አግብቶ ኮከበ ከዋክብት ተክለሃይማኖትን ሲወልድ፤ ካህኑ ዮሐንስ ደግሞ ዲቦራ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ #ዜና_ማርቆስን ወልዷል

👉የአቡነ #ዜና_ማርቆስ ጽንሰታቸው ሚያዝያ 30 በብሥራተ ማርቆስ ወንጌላዊ ሲሆን ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 24 ቀን በበዓለ #ሱራፌል_ካህናተ ሰማይ ነው ዘመኑም 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው።

👉 #ዜና_ማርቆስ በተወለዱ በ40 ቀናቸው አጐታቸው ቀሲስ እንድርያስ (የ72 ዓመት ሽማግሌ ናቸው) ሊያጠምቁ ቀረቡ ሕፃኑ #ዜና_ማርቆስ ግን ከእናታቸው እቅፍ ወርደው 3 ጊዜ "እሰግድ #ለአብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ" እያሉ ቢሰግዱ የመጠመቂያው ገንዳ ውኃ ፈላ ይህንን የተመለከቱት ካህኑ ደንግጠው ወጥተው ሲሮጡ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ተገልጦ "አትፍራ ይልቁኑ ከጠበሉ ራስህን ተቀባ" አላቸው እንዳላቸው ቢያደርጉ #ራሰ_በራ_ነበሩና_ፀጉር በቀለላቸው

👉ሕፃኑ #ዜና_ማርቆስ ግን 5 ዓመት ሲሞላቸው ወደ ጉባኤ ቤት ገብተው በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ አጠናቀቁ ዲቁናን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ሽፍቶች አግኝተው በትራቸውን ቀምተው አንገላተው ሰደዋቸዋል ወዲያው ግን ያቺ በትር እባብ ሁና ሽፍቶችን አጥፍታቸዋለች

👉ፃድቁ ለቤተሰብ እየታዘዙ ንጽሕናቸውንም እየጠበቁ ኑረው 30 ዓመት ሲሞላቸው ወላጆቻቸው ግድ ብለው ማርያም ክብራ ለምትባል ወጣት አጯቸው እሳቸው ግን በሠርጉ ሌሊት ከጫጉላ ቤት ጠፍተው በርሃ ገቡ ከዚያም በቅዱስ መልአክ መሪነት ሃገረ ምሑር ደረሱ በቦታውም ጣዖትን ሰባብረው ተአምራትንም አድርገው ሕዝቡን ወደ ክርስትና መለሱ

👉መስፍኑ አውጊት ግን ተፈታተናቸው አሠራቸው አሥራባቸው (በረሀብ ቀጣቸው) በጦር እወጋለሁ ሲል ግን መሬት ተከፍታ ከነ ተከታዮቹ ውጣዋለች ከ5 ዓመታት በኋላ ግን ማልደው ከሰጠመበት አውጥተው አጥምቀውታል ቀጥለውም ምድረ ጉራጌ ወርደው ሕዝቡን አሳምነው አጥምቀዋል

👉የአዳልን ሕዝብና ንጉሡን #አብደልማልን አስተምረው ያጠመቁም እርሳቸው ናቸው #ድል_አሰግድ የሚባለውን መስፍንም ያሳምኑ ዘንድ ጠንቋዮቹን ድል አድርገው አጥፍተዋል።

👉 ፃድቁ ዜና ማርቆስ ከዚህ ሐዋርያዊ ሥራቸው በተጨማሪ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምንኩስናን ከተቀበሉባት ቀን ጀምረው በጾም፣ በጸሎትና በሰጊድ ኑረዋል #ፀሐይን በምድረ ጉራጌ እስከ ማቆም ደርሰውም ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል

👉አእላፍ ደቀ መዛሙርትን ሲያፈሩ 200 አንበሶች በቀኝ 200 ነብሮች በግራ ይከተሏቸው ነበር ደብረ ብሥራትን ጨምሮም ገዳማትን አንፀዋል በመጨረሻም የምሕረት ቃል ኪዳንን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብለው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል።

👉#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእናታችን #በቅድስት_ድንግል_ማርያም በመልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል #በፃድቁ_ዜና_ማርቆስ ፀሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር አሜን ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 3/2017 ዓ/ም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ምስባክ ዘቅዳሴ አመ ፫ ለታህሳስ
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፫ ለታኅሣሥ በዓታ ለማርያም
🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵🟢🟡🔴🏵
የታህሳስ በዓታ ለማርያም
#ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
የየትኛውም ሥርዓተ ማህሌት መጀመርያ ነግስ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ለማርያም ዘምሩ፤ለማርያም ዘምሩ፤መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
አመላለስ
ለማርያም ዘምሩ/፪/
ለማርያም ዘምሩ/፬/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ወብሥራት ለገብርኤል፤ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
አመላለስ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል/፫/
ወብሥራት ለገብርኤል/፫/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክዐ ኪዳነ ምሕረት(ነግሥ)
ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክት ሰማይ፤እንዘ ሀሎኪ ማርያም ወመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕት ሠርክ ኅሩይ፤ለእመ ኅፍነማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን፤ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት፤ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ስቴክኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ፤ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ፤እምአንስት ቡርክት አንቲ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
አመላለስ
ወመሠረቱ/፪/
ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ነግሥ
መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ወእሙ ለእግዚእነ፤በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ፈንዊ ለነ እግዚእትነ፤ፋኑኤልሃ መልአከኪ ሄረ፤በኃይለ ጸሎቱ ይዕቀበነ ወትረ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
አመላለስ
ፈንዊ ለነ እግዚእትነ/፪/
ፋኑኤልሃ መልአከኪ ሄረ/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ይዌድስዋ ኲሎሙ በበነገዶሙ፤ወበበማኅበሮሙ ለቅዱሳን፤ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ወረብ
"ይዌድስዋ ኲሎሙ"/፪/በበነገዶሙ/፪/
ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ማርያም
ሰላም ለልሳንኪ ሙኀዘ ኃሊብ ወመዓር፤ዘተነብዮ ወፍቅር፤ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ኅብእኒ እምዓይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር፤እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ፤ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፤ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ፤ውስተ አውግረ ስኂን።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ወረብ
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ እምከናፍርኪ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ/፪/
ወይቤላ ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ለማርያም ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ ወደብረ ብርሃን/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ወረብ ፪
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ/፪/
ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ ደብረ ገነት /፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ማርያም
ሰላም ለእመታትኪ እለ ፀንዓ ይፍትላ፤ሜላተ ወወርቀ በናዝሬት ወበገሊላ፤ማርያም ድንግል ለዮዲት ጥበበ ቃላ፤ብጽሂ በሠረገላ ንትመኃል መኃላ፤ከመ ታኅድርኒ በብሔር ዘተድላ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ወዜነዋ ጥዩቀ፤በዕንቊ ባሕርይ እንዘ ትፈትል ወርቀ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
አመላለስ
ገብርኤል መልአክ መጽአ/፪/
ወዜነዋ ጥዩቀ/፬/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ወረብ
ገብርኤል መልአክ መጽአ"ወዜነዋ"/፫/ጥዩቀ/፪/
"በዕንቊ ባሕርይ"/፫/እንዘ ትፈትል ወርቀ/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ማርያም
ሰላም ለአብራክኪ በስብሐተ ልዑል ዘአስተብረካ፤እምአመ ወሀቡኪ ብፅአ ውስተ ኦሪታዊት ታዕካ፤ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ፤ጊዜ ስደቶሙ ለኃጥአን እምዓጸደ ዓባይ ፍሲካ፤ጼውውኒ መንገሌኪ እኩንኪ ምህርካ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤አስተርዓያ መልአክ፤ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ፤ግሩም ርእየቱ፤ኢያውአያ እሳተ መለኮት።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ወረብ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር/፪/
አስተርአያ መልአክ ዘኢኮነ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ ኢኮነ/፪/
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
መልክአ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
ዚቅ
ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለወለተ ሀና፤ኅብስተ ሕይወት ተጸውረ በማኅጸና፤ጽዋዓ መድኃኒት፤ዘአልቦ ነውር ወኢሙስና፤እፎ አግመረቶ ንስቲት ደመና፤ኢያውአያ በነበልባሉ፤ወኢያደንገጻ በቃሉ፤አላ ባሕቱ ትብራህ፤ረሰያ ዘበጸዳሉ፤ይዜኑ ብሥራተ፤መልአኮ ፈነወ፤ዮም ተሠገወ በከመ ተዜነወ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዓለም ሁሉ መመኪያ

ድንግል እናት ሆይ


ከሚያሰጥመው ካመፀኛ አፍ በደምም ከሰከረች ምላስ አድኝኝ፡፡

መንፈሳዊት መርከብ ሆይ ድንግልናዊት መፆር ሆይ

ከክፉ ዘመን መከራ አድኝኝ፡፡

የሁላችን መመኪያ የመድኃኒት ሽቱ ብልቃጥ ያለ ርኩሰት ሙሽራ ሆይ

ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ አድኝኝ፡፡

የእመብርሃን አማላጅነት አይለየን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሁሉም ጊዜያቶች በዑደታችን...አልፈው ይጓዛሉ። በጊዜ ዑደት መሐል የምንይዛት ነጥብ ለማስታወሻ የምናስቀምጣት ምስል ነች። ያቺ ምልስ በሌላ የጊዜ ዑደት የምትባክን ግን እንደነበረችበት ዑደት የምናገኛት ሕይወት ናት።✍️ ጼሌቅ/Yo/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አንድ ሰው እግዚአብሔርን ወደደ የሚባለው
እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር
ለእግዚአብሔር ብሎ የተወ እንደሆነ ነው ።

እለ ታፈቅርዎ ለእግዚአብሔር ጽልእዋ ለእኪት
(" እግዚአብሔርን የምትወዱት ከሆነ
እግዚአብሔር የሚጠላውን ጥሉ ማለት ነው") ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።


        ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ገብርኤል

ሀዋሳ ገብርኤል


ታህሳስ 18 መነሻ
ታህሳስ 19 መመለሻ

በዕለቱ የሚኖሩን ፕሮግራሞች


-መንፈሳዊ ትምህርቶች
-የተለያዩ ዝማሬሞች
-የንግስ ላይ አገልግሎቶች
-የፀሎት ፕሮግራም
- የበረከት ስራዎች

እንዳያመልጦት 🙏🙏🙏

ዋጋ ከሙሉ መስተንግዶ ጋር

1500 ብር ብቻ

     
ለበለጠ መረጃ




0991119629
0925492634


ይደውሉ 📞📞

አዘጋጅ ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አንድ ሰው ቃለ እግዚአብሔር እንዳይሰማ የሚያደርገው
ምግበ ሥጋ መብላቱ ሳይኾን የገዛ ግድየለሽነቱ ነውና፡፡
አንተ ግን አለመጾም ነውር እንደ ኾነ - እያመንክ
በዚህ ላይ እጅግ ትልቅና ከባድ የኾነ ሌላ ስሕተት -
ይኸውም ከቅዱሱ መዓድ አለመካፈል
ማለትም ቃለ እግዚአብሔርን አለመማር ጨመርህበት፣
ሥጋህን መግበህ ነፍስህን ግን አስራብሃት

ታዲያ እንዲህ ለማድረግህ የሚደረግልህ ይቅርታ
እንደ ምን ያለ ይቅ ይቅርታ ነው?


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿ኪሮስ ጻድቅ (ዘገዳመ ምዕራብ)
✿ሳሙኤል ቡሩክ (ዘደብረ ቀልሞን)
✿ተክለ አልፋ (ዘደብረ ድማኅ)
✿እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዘአስጋጅ)
✿ሴት ሐዋርያ (ዘዓዲቀታ)
✿ሙሴ ጳጳስ (ዘገዳመ ድባ)
✿ያሮክላ ሊቀ ጳጳሳት
✿ኤሲ ወቴክላ (ሰማዕታት)
✿ዮሐንስ ሊቅ (ዘደማስቆ)
✿ገብረ ማርያም (ተአማኒ)
✿እንባ ምሬና (ብጽዕት)
✿በርባራ ወዮልያና (ደናግል)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ #ታኅሣሥ ፰ (8) ቀን

❤ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለደብረ ድማሕ(ዲማ) ገዳም አበምኔት በፊትም በኋላም የሚያዩ ለሆኑ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ለተክለ_አልፋ ለዕረፍት በዓል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ማልኝ ብለው በአባይ ወንዝ ውስጥ ለዘጠኝ ዓመት ለጸለዩ #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ_ለልደት በዓል፣ በክርስቶስ ለሚታመን የሰማዕታትንና የጻድቃንን በየዕረፍታቸው ቀን ለእያንዳንዳቸው ርኁባንን በማጥገብ የተራቆቱትን በማልበስ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ለነበረ #ለቅዱስ_ገብረ_ማርያምና፣ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ኪሮስና ከግብጽ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ተሾመው ለመጡ በኢትዮጵያ ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲያንን ላነጹ #ለብጹዓዊ_ለአቡነ_ሙሴ_ዘድባ ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

✝ ✝ ✝
❤ #ስለ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ_ልደት፦ (የተወለዱበት) ቦታ ዳውንት ፀወን ዓባይ ይባላል። በአካባቢውም በገዳሙ አንፃር በሰሜን በኩል የእናታቸው አገር ደብረ ድባ የቄርሎስ ቦታ ይባላል የአባታቸውም አገር የእግዚአብሔር አብ ደብር አጠገብ ዳውንት ወይም ደብረ አስጋጅ ይባላል።

❤ አባታቸው ስም ቅዱስ መልአከ ምክሩ ሲሆን የእናታቸው ስም ቅድስት ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘው በሕጉ ጸንተው ተስማምተው የሚኖሩ መልካም ሥራን በመሥራት እንደ ዘካርያስና እንደ ኤልሳቤጥ እውተኞች ነበሩ። እነርሱም ሁለት ደጋጎች ልጆች አሏቸው፤ የተባረከ መልካም ፍሬ በመጾምና በመጸለይ እግዚአብሔር የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር እግዚአብሔር በዓይነ ምሕረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም ሰምቶ አባታች አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ ሚያዝያ 8 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ8 ቀን ተወለዱ፤ በተወለዱበትም ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ጣዕም ባለው አንደበትም አመሰገኑ ዘጠኝ ጊዜም ሕፃናትን ለሚያናግሩ ገዢ ለሚሆኑ ለሥላሴ፣ ለእመቤታችንና ለመስቀሉ ሰገዱ፡፡

❤ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን አወቁ። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ እስትፋሰ ክርስቶስ።

✝ ✝ ✝
❤ #ስለ_አቡነ_ኪሮስ_ልደት፦ በሮም አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ስሙ ዮናኒ የሚባል አንድ ሰው ነበር። በአባቱ ዙፋን ተቀምጠ ድንቅ ሥራንም ሠራ አባቱ ከሠራው ሥራም ምንም አላጐደለም ስድሳ ዓመት ኖረ ስሙ አብያ የሚባል ልጅም ወለደ በክብርም ዐረፈ።

❤ አብያም በአባቱ ዙፋን ነገሠ አባቱ ከሠራው መልካም ሥራ አንድም ስንኳን አላጐደለም። የሚስቱም ስሟ ሜናሴር ይባል ነበር ሠላሳ ዓመትም መካን ሆና ኖረች። ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ሜናሴርም ፀነሰች ሁለት ልጆችም ወለደች ታላቁን ቴዎዶስዮስ ታናሹን ዲላሶር አለችው። በመልካም አስተዳደግ አሳደጓቸው ከዚህ በኋላ አባታቸው አብያ በክብር ዐረፈ።

❤ ቴዎዶስዮስም በአባቱ በአብያ ዙፋን ነገሠ። ከሦስት ዓመት በኋላ ዲላሶር ቴዎዶስዮስን "ከአባቴ ገንዘብ ድርሻዬን ስጠኝ" አለው። ቴዎዶስዮስም "ወንድሜ ሆይ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው የአንተም የእኔ ነውና ከእኔ በታች የፈቀድከውን የሚከለክልህ ማነው?" አለው። "ልጅ ስለሆንክ ግን ፈጽሜ ከፍዬ አልሰጥህም" አለው በዚህም ምክንያት እርስበርሳቸው ተጣሉ። ዲላሶርም በሌሊት ተነስቶ ተሸሽጐ ወጥቶ አድርስ ወደ ሚባል ተራራ ሄደ። በዚያም ትንሽ ዋሻ አግኝቶ እስከ ዐሥር ቀን በውስጧ ተቀመጠ። መንፈስ ቅዱስም "ኪሮስ ሆይ ብሎ ጠርቶ ለብዙዎች አባት ትሆናለህ በቃልህም እንክርዳድ ኃጢአት ይነቀላል ጽድቅ ስንዴ ያፈራል። አሁንም ከዚህ ተነስተህ ወደ ፊትህ የአንድ ቀን ጐዳና ሒድ። በዚያም ባሕታዊ መነኵሴ ታገኛለህ ከእርሱም የምንኵስናን ልብስ ትለብሳለህ" አለው። ይህን ብሎት ከእርሱ ተሰወረ። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ኪሮስ።

✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ተክለ_አልፋ_ዘደብረ_ድማህ (ዲማ) ፡- ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ አልፋ ልደታቸውም ዕረፍታቸውም ታኅሣሥ 8 ነው፡፡ "ተክለ አልፋ" ማለት ለዘለዓለም የሚኖር ድንቅ ሥራ ማለት ነው፡፡ ጻድቁ ቀደምትና ዓበይት ከተባሉት ከ72 ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በደብረ ድማህ አበምኔትነት ተመርጠው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ የሴቶችን ማኅፀን የምታበላሸውንና መካን የምታደርገውን "እመ ሙላድ" የተባለችውን ዛር አቡነ ተክለ አልፋ በመቋሚያቸው እንደ አውሬ አባረው አጥፍተዋታል፡፡ እርሷም እንደ ሰው ትልካ ሄዳ ማኅፀን የምታጠፋ ነበረች፡፡

❤ ከዚህም በኋላ አቡነ ተክለ አልፋ ሹመትን አልፈልግም ብለው በጸሎት ብቻ ተወስነው የኖሩ በዲማ ትልቅ ክብር ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በተወለዱበት ዕለት ታኅሣሥ 8 ቀን ሲያርፉ ማረፋቸውን መቁዋሚያቸው ናት በሰው አንደበት "አባታችን ዐረፉ" ብላ ለመነኮሳቱ የተናገረችው፡፡ ጻድቁ የጠቀበሩት በተሾሙበትና ለ35 ዓመታት ባገለገሉበት በዚያው በዲማህ (ዲማ) ነው፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ተክለ አልፋ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።

✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_አባ_ገብረ_ማርያም፡- ይህም ቅዱስ የሰማዕታትንና የጻድቃንን በየዕረፍታቸው ቀን ለእያንዳንዳቸው ርኁባንን በማጥገብ የተራቆቱትን በማልበስ መታሰቢያቸውን የሚያደርግ ነው፡፡ እንዲህም ባለ ሥራ ላይ እያለ ይን ጊዜ እስላሞች ወደ ሸዋ አገር መጡ፡፡ እርሱም ያማሩ የክህነት ልብሶቹን ለብሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ጸሎትን ጸለየ ሲጸልይም እስላሞች ወደርሱ መጥተው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት በቅዱስ ገብረ ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 8 ስንክሳር።

✝ ✝ ✝
❤ #ብፁዕ_አቡነ_ሙሴ_ዘድባ፦ በአባታቸው የእቤታችን ጠባቂ የአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የልጅ ልጅ ሲሆኑ፤ በእናቸው በኩል ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በቃና ዘገሊላ ሰርግ የተገኘችበት የዶኪማስ የልጅ ልጅ ናቸው። የአባታቸው ስም ቅዱስ ዮስጦስ ሲባል፤ የእናታቸው ስም ቅድስት ጵስርስቅላ (ሶልያና ማርያም) ይባላል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ #ታኅሣሥ ፰ (8) ቀን

❤ እንኳን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አረጋዊ ደቀ መዝሙር ለነበሩት #ለደብረ_ዳሞ_ገዳም_ሁለተኛ አበምኔት #ለአቡነ_ማትያስ_ዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

✝ ✝ ✝
❤ #የአቡነ_አረጋዊ_ደቀ_መዝሙር_አቡነ_ማትያስ፦ ቅዱስ አባታችን ማትያስም ገድልን ትሩፋትን በማብዛት ጸና እየበረታም ሄደ የእህሎችን ወይም የምግቦች ጣዕም እስኪለየው ድረስ ጾምን አበዛ። ለሁሉ ራሱስን ዝቅ ያደርጋል እንደቀድሞው ለቤተ ማኅበሩ በሁሉ ቦታ ይታዘዛል የሃይማኖትን ትምህርት ለሁሉ ያስተምራል የወንጌልን ቃል ባማረ አንደበት ይሰብካል ወንድሞቹ የሱን በጎ ሥራ ተመልክተው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት የእርሱን ፈለግ ይከተሉ ዘንድ ለሁሉ ራሱን ዝቅ ያደርጋል። መነኰሳትም በየቀኑ እየመጡ በገዳሙ ውስጥ ቊጥራቸው እየበረከተ ሄደ።

❤ ይህ አባታችን ማትያስም በሁሉ ዘንድ ስሙ የተጠራ የታወቀ ሆነ የሃይማኖትን ቃል ለሁሉ ያስተምራል ሕዝቡም ቃሉን ይሰሙታል በእውነትም ትምህርቱን ይቀበሉታል።

❤ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ የእግዚአብሔርን ቃል ያስቡ ዘንድ ወይም በልቡናቸው ሠርፆ ይገባ ዘንድ ከወንድሞቹ ጋር በኅብረት ጸለየ። ጸሎታቸውንም ከጨረሱ በኋላ በመጽሐፉ ውስጥ የተመለከቱትን በአእምሯቸው ቀርፀው ወደ በዓታቸው ይሄዳሉ ለያንዳንዳቸው የሚናገሩትና የሚያስታውሱትም ቀድሞ በመጽሐፋ የተባለውን ነው።

❤ እንግዲህ ከነሱ መካከል የአሉባልታና ወይም የሥራ ፈት ወሬ ወይም ዋዛ ፈዛዛ ለመናገር ከቶ አፉን የሚከፍት እስከመቼም ድረስ የለም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት የተማሩትን ያነባሉ ትርጓሜውንም ይሻሉ ስበጎ ሥራዎች ሁሉ ቀና መንገድ ይቀይሳሉ እንጂ። የሚሠራውን ነገር ለማየት አንዱ ወደሌላው ቤት ፈጽሞ አይገባም እያንዳንዱም ለራሱ ልብስ አያከማችም ነገር ግን የሚለብሱትን እስኪአጥቡ ድረስ በቤተ ማኅበሩ አዝዥ ወይም አለቃ በግምጃ ቤቱ ይጠበቃል ወይም ይቀመጣል እንጂ።

❤ የልብስ ለውጥ ሲፈልጉ በማኅበሩ አለቃ ሥልጣን ይሰጣቸዋል ከነሱ ወገን ማንም ወርቅና ብር ወይም ሌላ ገንዘብ የሚያይ ወይም የሚወስድ የለም። ብዙዎች ለሥራ ጉዳይ ከመላላክ በስተቀር ይህን ሳያዩ የሞቱ አሉ እነሱ ወደገዳሙ በገቡ ጊዜ በእጃቸው ይዘው እያቆዩም ለገዳሙ መጋቢ ፈጥነው ያስረክባሉ እንጂ።

❤ ቅዱስ አባታችን አባ ማትያስም ከአባቱ ከብፁዕ አባ አረጋዊ እንደተማረው ሕገ ምንኵስናውን በጥንቃቄ ፈጽሞ በእግዚአብሔር ቸርነት ታኅሣሥ 8 (ስምንት) ቀን ዐረፈ። ከአባታችን አቡነ ማትያስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ አረጋዊ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኦ ሥሉስ ቅዱስ ተመስገን
የአብ ፍቅር የወልድ ቸርነት
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት
የእመቤታችን አማላጅነት
የቅዱሳን ፀሎት በያለንበት
አይለየን ይጠብቀን አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ከመጠጥ በላይ አዕምሮን የሚያዞር ነገር አለ ?

✅ በዚህ ዓለም እኮ

አለምን የሚያሸንፉ መጠጥ, ሴት እና ንጉስ ናቸው ።
ምንም ጀግና ሊቅ ቢሆን ሲጠጣ በገዛ እጁ ይወድቃል።
ብዙ ጠላቶች ተኩሰው ያልጣሉትን
መጠጥ በ3ት ኩባያ ይጥለዋል።
ይህ እኮ ነው የሰው ልጅ አዕምሮ
ለምንድን ነው ግን የምትሰክሩት ?

✅ መጽሐፍ የሚለው

እባብ ከነደፈው ሰው መጠጥ የነደፈው ሰው ይበልጣል ነው የሚለው ።

✅ለምሳሌ ፦

ተረከዙ ላይ ቢነድፈው
ወደ ላይ እንዳይወጣ ባቱ ላይ እናስረዋለን

የሰከረን ሰው ምን ላይ እናስረዋለን ጠቅላላ ተመርዟላ
ምን ላይ ሊያዝ ይችላል።

በእውነቱ በጣም አስቸጋሪ ነው

የመስቀሉ ልጅ ከሆናችሁ ስካር አቁሙ
🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ #ታኅሣሥ ፭ (5) ቀን።

❤ እንኳን #ዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው ለኬልቅዩ ልጅ ለታላቁ ነቢይ #ለቅዱስ_ናሆም_ለዕረፍት_በዓል፣ ከሮም አገር ለሆነች #ለቅድስት_አውጋንያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓልና አስዩጥ አውራጃ ሻው ከሚባል ከተማ ለሆነ #ለቅዱስ_ፊቅጦር_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ኤስድሮስ_ሰማዕት፣ #ቅዱሳን_ከፊንጦስ፣ #ከሐናንያ_ከባርክዮስ_ከዮሐንስ_ከተጋዳይዋ #ከቅድስት_አውጋንያ_አባት_ከፊልጶስና ከሰማዕት #ቅዱስ_ኤላውትሮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ በረከትን ረድኤትና ያሳትፈን።

✝ ✝ ✝
❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ናሆም፦ ከስምዖን ነገድ የሆነ ይህ ጻድቅ ነቢይ ከነቢዩ ሙሴ በትንቢት ዐሥራ ሰባተኛ ነው። በካህኑ ዮዳሄ በነገሥታቱ በኢዮአስ፣ በአስሜስያስ፣ በልጁ በኦዝያን ዘመን ትንቢት ተናገረ ስለ ክህደታቸውና ጣዖታትን ስለ ማምለካቸውም የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። እግዚአብሔርም ምንም መሐሪና ይቅር ባይ ምሕረቱም የበዛ ቢሆን ካልተመለሱ ጠላቶቹን ይበቀላቸው ዘንድ እንደ አለው ለሚቃወሙትም የፍርድ ቀን እንደሚጠብቃቸው በትንቢት ገለጠ።

❤ ዳግመኛም ስለ ከበረ የወንጌል ትምህርትና ስለ ሐዋርያት እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "የምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግራቸው እንሆ በተራራ ላይ ቁሟል ሰላምንም ይናገራሉ"። ስለነነዌም ውኃና እሳት ያጠፋአት ዘንድ እንዳላቸው ትንቢት ተናገረ እንደ ቃሉ ሆነ ከዕውነት መንገድ ተመልሰው በበደሉ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በውስጡ ታላቅ ንውጽውጽታ አድርጎ እሳትም አውርዶ እኩሌታዋን አቃጥሏልና። በንስሐ ጸንተው ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ግን ከክፉ ነገር ከቶ ምንም ምን አልደረሰባቸውም። የትንቢቱንም ወራት ሲፈጸም እግዚአብሔርም አገልግሎ በዚች ቀን ታኅሣሥ5 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነቢይ በቅዱስ ናሆም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_አውጋንያ፦ የዚችም ቅድስት የአባቷ ስም ፊልጶስ ነው እርሱም የእስክንድርያ አገር ገዥ ነበር ጣዖትንም ያመልካል ስሙ መምድያኖስ የሚባል የሮም ንጉሥም ለጣዖት የሚሰግድ ነው ይቺም ቅድስት አውጋንያ በእስክድርያ ከተማ ተወለደች እናቷም ክርስቲያን ስለሆነች በሥውር የክርስቲያን ሃይማኖትን አስተማረቻት።

❤ በአደገችም ጊዜ ታላላቆች መኳንንት አጯት አባቷም ይህን በነገራት ጊዜ "አባቴ ሆይ መጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ገዳም እንድገባና እንድጎበኝ ተራሮችን በማየት ዐይኖቼ አይተው ደስ ይለኝ ዘንድ ፍቀድልኝ" አለችው አባቷም ሰምቶ ሁለት ጃንደረቦችን ጨምሮ የወደደችውን ታደርግ ዘንድ ፈቀደላት። በወጣችም ጊዜ የመነኰሳትን ገዳማት ሁሉ ዞረች ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል ጻድቅ ደግ ኤጲስቆጶስ ወደሚኖርባትም ቤተ ክርስቲያን ደረሰች ቀረብ ብላም በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው ካጃንደረቦቿም ጋር ተጠምቃ በዚያ መነኰሰች በወንድ አምሳልም ሁና ስሟን አባ አውጋንዮስ አሰኘች እርሷ ሴት እንደሆነች ማንም አላወቀም። ወደ አባቷም ባልተመለሰች ጊዜ በቦታው ሁሉ ፈለጋት ሲአጣትም በርሷ አምሳል ጣዖት ሠርቶ ማታና ጧት እየሰገደላት ኖረ።

❤ አንድ ዓመትም ከኖረች በኋላ የዚያ ቦታ አበ ምኔት አረፈ መነኰሳቱም መረጧትና አበ ምኔት አድርገው ሾሟት እግዚአብሔርም አጋንንትን ታስወጣ ዘንድ የዕውራንን ዐይኖች ትገልጥ ዘንድ ደዌውን ሁሉ ታድን ዘንድ ሀብተ ፈውስን ሰጣት።

❤ ከዚህም በኋላ ሰይጣን በአንዲት ሴት ልብ ክፉ አሳብ አሳደረባት ከአዳነቻት በኋላ ወንድ መስላታለችና "ገዳምህንና ምንኵስናህን ትተህ ለእኔ ባል ሁነኝ ብዙ ገንዘብ አለኝና" አለቻት። አባ አውጋንዮስ የተባለችው ቅድስቷም "እናቴ ሆይ ከእኔ ዘንድ ሒጂ ሰይጣን በከንቱ አድክሞሻል" አለቻት በአሳፈረቻትም ጊዜ ወደ እስክንድርያ ገዥ ሒዳ እንዲህ አለችው "እኔ ወደ ዕገሌ ቦታ በሔድኩ ጊዜ ሊደፍረኝ ሽቶ ወጣት መነኵሴ በሌሊት ወደእኔ መጣ ወደ አገልጋዮቼም ስጮህ ከእኔ ዘንድ ወጥቶ ሸሸ"። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ይኸውም የቅድስት አውጋንያ አባቷ የሆነ መነኰሳቱን ሁሉ አሥረው ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ በአደረሷቸውም ጊዜ እንዲአሠቃያቸው ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣቸው ከሥቃይም ጽናት የተነሣ ከእርሳቸው የሞቱ አሉ።

❤ የመነኰሳቱንም መጐሳቈል በአየች ጊዜ መኰንን አባቷን እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ምሥጢሬን ዕውነቱን እነግርህ ዘንድ የምፈልገውንም እንዳትከለክለኝ ማልልኝ" አለችው። በማለላትም ጊዜ ወደ ሥውር ቦታ ወስዳ ምስጢርዋን ሁሉ ገለጠችለትና ልጁ አውጋንያ እርሷ እንደሆነች አስረዳችው። መኰንኑም አይቶ "በእውነት አንቺ ልጄ አውጋንያ ነሽ እኔም በአምላክሽ አመንኩ" አላት። በዚያንም ጊዜ መነኰሳቱን ይፈቷቸው ዘንድ በመሠቃየት የሞቱትንም ይቀብሩአቸው ዘንድ አዘዘ ወዲውኑ ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ተጠምቆ ሁሉም ክርስቲያን ሆኑ።

❤ የእስክንድርያ ሰዎችም የሃይማኖቱን ጽናት በአዩ ጊዜ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት ክብር ይግባውና የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ብዙ ዓመታትን ኖረ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ላይ ሌላ ከሀዲ መኰንን ተነሥቶ ይህን ሊቀ ጳጳሳት ፊልጶስን በሥውር ይገድሉት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ገደሉት የሰማዕትነት አክሊል አገኘ።

❤ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳትም የቅድስት አውጋንያን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ ወስዶ እርሱ በሠራው ገዳም ላይ እመ ምኔት አድርጎ ሾማት የመነኰሳይያቱም ብዛት ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ነው እነዚያንም ከእርሷ ጋር የኖሩ ሁለት ጃንደረቦች በሁለት አገሮች ላይ ኤጲስቆጶስትነት ሾማቸው። ከዚህም በኋላ ሌላ ከሀዲ መኰንን በተሾመ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሷን ለሞት አሳልፋ እስከ ሰጠች ድረስ ቅድስት አውጋንያን ይዞ በጽኑ ሥቃይ አሠቃያት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አውጋንያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ፊቅጦር፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መርመር የእናቱ ስም ማርታ ይባላል እነርሱም ያለ ፍርሀት እግዚአብሔርን የሚያመልኩት እውነተኞች ጻድቃን ናቸው ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውምና ክብር ይግባውና ጌታችንን እየለመኑ ኖሩ ለድኆችም ምጽዋትን ይሰጡ ነበር። እግዚአብሔርም ልመናቸውን ተቀብለ ይቺ የተባረከች ማርታም ይህን ሊቅ ፊቅጦርን ፀንሳ ግንቦት ዘጠኝ ቀን ወለደችው እግዚአብሔርን በመፍራትም ሠርተው ቀጥተው አሳደጉት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✝በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል (ውስተ ቤተ መቅደስ)

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿ፋኑኤል ሊቀ መላእክት
✿ዘካርያስ ሊቀ ካህናት
✿ስምዖን ካህን
✿ኢያቄም ወሐና
✿ዜና ማርቆስ ዘወግዳ
✿እንጦንስ ኢትዮጵያዊ (ወላዴ አእላፍ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
በረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 13 በዕለተ እሁድ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ተዓምራዊ ቦታ ወደ ስውሯ ማርያም ጉዞ ስለተዘጋጀ የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል ።
ደርሶ መልስ ሲሆን ዋጋው መስተንግዶን ጨምሮ 600 ብር ብቻ ነው ።
ገቢው ; አስተርዕዮ ማርያም ነድያንን ለመዘከር የሚውል ።


ማህበረ ማርያም ወ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ምስባክ ዘነግህ አመ ፫ ለታህሳስ
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 3/2017 #እናታችን_ባዕታ_ማርያም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን #ባዕታ_ማርያም ስም ለምናመሰግንበት ለእናታችን #ባዕታ #ማርያም አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ታኅሣሥ ፫ #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወደ ቤተ #መቅደስ የገባችበት ቀን ነው ይህንን ቀን ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች

👉እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ #ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት #ሐና ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ግንቦት1ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ ተወለደች፡፡

👉እመቤታችን በፆም በፀሎትም የተገኘች የስዕለት ልጅ ናት ንጽሕት በመሆኗም #የእግዚአብሔር_ማደሪያ ሆናለች ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት ፫ ዓመት ተቀመጠች

👉ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ #እግዚአብሔርን ፈጽመው እያመሰገኑት 3 ዓመት ኖሩ በጾም እና በጸሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ፡፡

👉ልጃቸውንም #ድንግል_ማርያምን በንጽሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ #ሐና ባሏን #ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን ለቤተ #እግዚአብሔር ብፅዐት አድርገን እንስጥ ልጃችን ቤተ #እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው።

👉ነቢየ #እግዚአብሔር ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን ንጽሐ ባሕርይሽን ወድዷልና መዝ 44፡10-11 ብሎ እንደተናገረ #ለወላጆቿ_የብፅአት_ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ 3 ቀን በ 3 ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች

👉#በዕታ_ለማርያም ማለትም የድንግል #ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው #ካህኑ_ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጐናጽፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ጽዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ተመልሷል

👉እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየዘመረች ፈጣሪዋን እያመሰገነች 12 ዓመት #በቤተ_መቅደስ ተቀመጠች

👉የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ እያልን ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለፀች #እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ለበላኤ ሰብዕ የተለመች #እመ_አምላክ ለኛም ትለመነን ከልጅዋ ከወዳጅዋ #ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን

👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ኢትዮጲያን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን የእናታችን ቅድስት #ባዕታ_ማርያም በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 3/2017 ዓ/ም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ \ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል::

እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ።

ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ስለ ኃጢአቶቻችን እየወቀሰ በማረም ከሚመጣው ፍርድ እንድናመልጥ ይረዳናል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው ይህንኑ ነው:- «ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር» (1ኛ ቆሮ 11:31)።

ራሳችንን ብንመረምር በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አይፈረድብንም ነበር ለማለት ነው፡፡ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ \ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡

በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል:: እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ።

ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ስለ ኃጢአቶቻችን እየወቀሰ በማረም ከሚመጣው ፍርድ እንድናመልጥ ይረዳናል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው ይህንኑ ነው:- «ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር» (1ኛ ቆሮ 11:31)።

ራሳችንን ብንመረምር በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አይፈረድብንም ነበር ለማለት ነው፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ #ታኅሣሥ ፪ (2) ቀን።

❤ እንኳን #ለሠለስቱ_ደቂቅ_ለአናንያ_ለአዛርያና_ለሚሳኤል #እግዚአብሔር_ኃይል_ላደረገላቸው ለመታሰቢያ በዓላቸው፣ #ለቅዱስ_አውክያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከላይኛው ግብጽ ከሚኖሩ ሰዎች ወገን ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ሖር ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ አገልጋዮቹና ዘመዶቹ ከሆኑ #ከሰባት_ሺህ_ሠላሳ_ሦስት_ከሆኑ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከአብላፍታን፣ ከዐረብ ወገን ከሆነ #ከሰማዕት_አንበስና_ከመነኰስ_ናትናኤል ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


✝ ✝ ✝
❤ #ሠለስቱ_ደቂቅ፦ በዚች ቀን ናቡከደነፆር ከአባታቸው ጋር ለማረካቸው ሦስቱ ለሆኑ ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆች እግዚአብሔር ኃልን አደረገላቸው። እሊህም አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ናቸው በቤቱም ውስጥ አሳድጎ በባቢሎን አገሮች ውስጥ ሾማቸው።

❤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉ በዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ እሊህ ቅዱሳን ግን መስገድን እምቢ አሉ በወነጀሏቸውም ጊዜ ከቀድሞው ሰባት እጅ ወደ አነደዱት የእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሯአቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። በእሳቱ መካከል ረጅም ጸሎትን ጸለዩ የእግዚአብሔር መልአክም ቅዱስ ገብኤልም ወርዶ እንደ ቀዘቀዘ ነፋስ አደረገው።

❤ ንጉሥ ናቡከደነፆርም ይህን ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ አደነቀ ለእግዚአብሔርም በመገዛት ሰገደ እነርሱንም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ አወጣቸው እጅግም አከበራቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን በሠለስቱ ደቂቅ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አውክያኖስ፦ እርሱም ሃይማኖቱን ጠብቆ ሰዎች አባለ ዘሩን እስከ ቆረጡት ድረስ ተጋድሎውን የፈጸመ ነው እግዚአብሔርም አመሰገነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውክያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሖር፦ ይህም አባት ደግነት ያለው መነኰስ በመሆን ጽኑዕ ገድልን ተጋደለ በአምልኮቱና በተጋድሎው ከቅዱሳን ሁሉ ተለይቶ በብዙዎች ላይ ከፍ ከፍ አለ ለብቻ መኖርን ስለወደደ ወደ በረሀ ወጥቶ በገድል ተጠምዶ ብዙ ዘመናት ኖረ። የበጎ ሥራ ጠላት የሆነ ሰይጣንም ቀንቶበት በግልጥ ታየውና "በበረሀ ውስጥ ግን አንተ ድል ትነሣናለህ በዚህ ሰው የለምና ጽኑ ኃይለኛ ከሆንክ ወደ እስክንድርያ ከተማ ና" ብሎ ተናገረው።

❤ አባ ሖርም ይህን በሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኃይል ተማምኖ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሒዶ ለእሥረኞችና ለችግረኞች ደካሞች ውኃ የሚቀዳ ሆነ በአንዲት ዕለት ሦስት ፈረሶች በከተማው ውስጥ እየዘለሉ ሲያልፉ አንዱ ፈረስ አንዱን ሕፃን ረገጠውና ወዲያውኑ ሞተ ሰይጣንም በሰዎች ልብ አደረና "ይህን ሕፃን ያለዚህ አረጋዊ መነኵሴ የገደለው የለም" ብለው አሰቡ አባ ሖርም መጣና ሕፃኑን አንሥቶ ታቀፈው በልቡም በመጸለይ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ማለደ በመስቀል ምልክትም በላዩ አማተበ የሕፃኑም ነፍስ ተመለሰች ድኖም ተነሣ ለአባቱም ሰጠው ወደ ከተማ ውጭ ሸሽቶ በመሔድ ወደ በዓቱ ገባ ፈልገውም አላገኙትም ጽድቅንና ትሩፋትንም በመሥራት ብዙ ዘመናት በገድል ተጠምዶ ኖረ።

❤ የሚሞትበት ጊዜ ሲቀርብ ብዙዎች ቅዱሳንን ሲጠሩት አያቸው እጅግም ደስ አለው ልጆቹንም ሰብስቦ በምንኵስና ሥርዓት ጸንተው ትሩፋትን እንዲሠሩ አዘዛቸው ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እርሱ እንደሚሔድ ነገራቸው እርሱም እጅግ አዘኑ ጥቂት ቀንም ታሞ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ሖር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ2 ስንክሳር።

✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሖር_በምንሀብ_ፍቱን። እስከ ተለዓለ ጥቀ ላዕለ ብዙኃን። ሶበ ተንሥኡ ላዕሌሁ በምክረ ጸላኢ ሰይጣን። ከመ ኢቀተሎ እስከ አእመሩ አብዳን። በኃይለ ጸሎቱ አንሥኦ ለምውት ሕፃን"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_2።

✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ። ወእነግር ኲሎ ስብሐቲከ። እትፌሣሕ ወእትሐሠይ ብከ"። መዝ 9፥1-2 ወይም መዝ 65፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥35-39 ወይም ማቴ 19፥10-15።

✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ደቂቀ እጓለ እምሕያው እስከ ማዕዜኑ ታከብዱ ልበክሙ። ለምንት ታፈቅሩ ከንቶ ወተኀሡ ሐሰተ። አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ"። መዝ 4፥2-3 የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 2፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 5፥1-6፣ የሐዋ ሥራ 5፥31-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel