kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ጻዲቁ ንጉሥ በእደ ማርያም ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን በእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የጠበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንችላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
ከገድላት አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወገኖቼ

ስንፀልይ እንዲህ እንላለን አደል ?

አቤቱ ወደፈተና አታግባን እንላለን

ምን ማለት ይመስላችኋል ?

ፈተና ማለት መከራ ፈርቶ ሃይማኖትን መካድ ነው ይላሉ።

ስለዚህ

ወደ ፈተና አታግባን ማለት ?

መከራ ፈርቼ ሃይማኖቴን ከምክድበት ቀን ሰውረኝ ማለት ነው ።

እግዚአብሔር

ረኃብ ፈርተን
በሽታ ፈርተን
ጦርነት ፈርተን
ሰይፍ ፈርተን
ክርስቶስን ከመካድ ይሰውረን 🙏

ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ
ያለ መጽሐፍ ለዚህ ነው

እዚህ ዉስጥ አሁን ሁላችንም ጀግና ጀግና እንሽታለን
ችግር የደረሰበት ቀን ግን ሰው ደካማ ነው ወገኖቼ
ሰዉ አፈር ነው ሰው ትቢያ ነው
ሁላችንም እንደነግጣለን
ፈርተን ከመካድ ይሰውረን
የሃይማኖት ብርታት ያድለን አሜን 🙏

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

እየጾመ የማይሰጥ ሰው

ቆጠበ እንጂ ጾመ አይባልም
የቁርሱ ለምፅዋት መሆን አለበት።
እኛ ለቤት መጥረጊያ ያደረግነው ሽሚዝ
ለሌላ ሰው የጌጥ ልብስ ይሆነዋል ።
እኛ ምሳ በልተን ጥሬ እንቆረጥማለን
ሌላ ጌጥ ያምረናል ያንን ለድሆች መራራት አለብን።
ያ ነው ጾም ማለት ያ ነው ደግነት ማለት


ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ


እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉ
መጨረሻው ያማረ ነው ይላል ሲራክ
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉ
መጨረሻው ያማረ ነው

እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰው

ግን ጀምሮ ነው የሚቀረው
ወዲያው ነው ሁሉም ነገር
ታይቶ ነው መጥፋት ነው ልክ እንደ ዕፀ ከንቱ

ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለው ሰው ግን

👉እሾህ ቢወጋው ነቅሎ ይሄዳል
👉እንቅፋት ቢመታው አንክሶ ይደረሳል
👉ቢሰበር እግሩን ጠምጥም ካሰበው ይደረሳል
👉እግዚአብሔርን መፍራት በልቡናው ያለው ሰው

እግዚአብሔርን ሳይፈሩ የጀመሩት ሥራ ግን

በጥሩ ፍጥንት ብንጀምረው
በተከናወነ አዕምሮ ብናከናውነው ብንጀምረው
በጣም ብዙ አእላፍን ይዘን ብንጀምረው
ይበላሻል።

እግዚአብሔርን መፍራት ይቀድማል።

እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምንማለት ይመስላችኋል ?

እግዚ አብሔርን ማክበር ለእግዚአብሔር መጠንቀቅ ማለት ነው።

እግዚአብሔርን እንድንፈራ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏


ርዕሰሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1) ሰላማዊ ሰው ማን ነው ።

ሀ ሰውን ያልበደለ
ለ የበደሉትን ይቅር የማይል
ሐ እንደ ክርስቶስ ዝም ብሎ የማይወድ
መ ቂመኛ የሆነ

2) ኃጢአት ማለት ምን ማለት ነው ?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆቹ

ሰላማዊ ሰው ማነው ካላችሁኝ
ሰውን ያልበደለ ሰው ነው
በሰው ቂም የማይቋጥር
እንዴት ብየ ቂም ይጥፋልኝ ? ልንል እንችላለን
የበደለኝ የበደለችኝ ብዙ ነው ልንል እንችላለን
እግዚአብሔር ላንተ ስንት ነገር ትቶልሀል ነው መልሱ
እግዚአብሔር የ30 ዓመት በደል ከተወልህ
አንተ የአንድ ቀን የሁለት ቀን የ3ት ቀን
የህትህን የወንድምህን በደል ለምን አተወውም
እግዚአብሔር ይሄን ሁሉ እዳ ትቶልህ የል

ሰርቀህ ዝም
ዘሙተህ ዝም
አመንዝረህ ዝም
ተሳድበህ ዝም
ደብድበህ ዝም

እግዚአብሔር ይሄን ሁሉ ዝም ብሎ አይቶሀል
ምን አለ የበደሉንን ይቅር ብንል ?

የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን🙏



ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️

ተፃፈ : - በ ዲ/ን ዑራኤል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 8/2017 #አርባእቱ_እንስሳ_ሱራፌል_ወኪሩቤኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳን መላእክቱ ስም ለምናመሰግንበት ለአርባእቱ እንስሳ ሱራፌል ወ ኪሩቤል አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ #የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው ስለ እሳቸውም ወንጌልን የፃፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው

👉የፊተኛው #አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም #ላም ይመስላል ሦስተኛውም #የሰው_መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር #ንስር ይመስላል

👉የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም

👉ሁለተኛውም ስለ እርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ #እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ #ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት

👉የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

👉ነቢዩ ዳዊትም #በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም #በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወፃት አለ ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል

👉በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው #የአንዱም_ፊቱ_አራት ነው ክንፉም አራት ነው

👉እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም #እሳት_ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል

👉ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ #መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው

👉ለዚያ ለተገደለው #በግ ኃይልን፣ ባለ ፀግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ

👉በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ #ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ በእውነት ይገባዋል እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ

👉ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ #አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ #እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገፀ #ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል ገፀ #አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገፀ #ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገፀ #ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና

👉ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን ስለ አለሙ #በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና

👉አርባእቱ እንስሳ #ሱራፌልና_ኪሩቤል በምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቁልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሴክስ ማድረግ ምትፈልግ ሴት inbox

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 6-በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገር ግን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡
እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡
ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡
ክብርት እመቤታችን ከስደቷ በረከት ትክፈለን!
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት አባ ፊልክስ ዐረፈ፡፡
አባ ፊልክስ፡- ይኸውም ቅዱስ ምግባር ሃይማኖቱ፣ ትሩፋት ተጋድሎው ያማረ ሆኖ ቢያገኙት በእግዚአብሔር ፈቃድ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት፡፡ በዘመኑም ከሃዲው ቴዎስድሮስ ቄሳር ነግሦ ምእመናንን ሲያሠቃያቸውና ሲገድላቸው ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊልክስንም ብዙ አሠቃጥቷቸዋል፡፡ አባ ፊልክስም በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ጽኑ መከራ እንዲቆም ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ይህን ከሃዲ ንጉሥ በነገሠ በ2ኛ ዓመቱ አጠፋው፡፡
ከዚህም በኋላ የክርስያኖችን ደም እንደውኃ ያፈሰሰው ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ነገሠና ክርስቲያኖችን በዓለም ላይ እያደነ ማሠቃየትና መግደል በጀመረ ጊዜ ይህ አባት አባ ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያሳየው ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ወዲያው በመጀመሪያው ዓመት ዐረፈ፡፡ ይህም አባ ፊልክስ ለክርስቲያን ወገኖች እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ድርሳናትንና ትግሣጻትን የጻፈ ነው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዘፈን የምትወዱ እናንተ የወለተ ሄሮድያዳ ወዳጆች ወዮላችሁ

ሱሪ የምትለብሱ ለዝሙት ምክንያት የምትሆኑ ቅርፅ የምታሳዩ አህቶች ወዮላችሁ

በየመሸታ ቤት እየሄዳችሁ በመደነስ የምትስክሩ ወዮላችሁ


በኋላ ትሉ የማያንቀላፋ እሳቱ የማይጠፋ ገሀነም ላይ ትገባላችሁና

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 6/2017 #በዐለ_ቁስቋም_ማርያም

👉በሰመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን እኛን ልጆቹን ከእናቱ ጋር ሆኖ ተሰዶ ስለፈለገን እያመሰገነዉ #ከእናታችን_ማርያም ከቅዱስ ዮሴፍ ከቅድስት ሰሎሜ ጋር ከስደት ለተመለሱበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

"የህፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ተነስ እናቱንና ህፃኑን
ይዘህ ወደ እስራኤል ተመለስ ማቴ.2፥19_20"

👉ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ አስበን በቃችሁ በለን ስደት ይብቃን እኛ ኢትዮጲያዊያን ፍቅር አጥተን አንዱ በአንዱ ላይ እየተነሣ አንዱ ተሳዳጅ አንዱ አሳዳጅ ሆነናልና በቃችሁ ብለህ በምህረት አይንህ ጎብኘን

👉የእመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ጋር የግብፅ ስደት አልቆ ወደ አገሯ ኢየሩሳሌም የተመለሰችበት ዕለት ናትና ክርስቶስ የአዳምን ከገነት የተሰደደውን ስደት በማሰብ ወደ ግብፅ ተሰደደ

👉የቅዱሳንን በእምነታቸው ምክንያት የሚሰደዱትን ስደት ይባርክ ዘንድ #ጌታ_ተሰደደ በነፍስ በስጋ ከቅድስና የሚሰደዱትን ወገኖች ወደ ህይወት ወደ ክብሩ ይመልስ ዘንድ እርሱ #ተሰደደ አሳዳጁን ጠላት ዲያቢሎስ ያዋርደው ዘንድ እርሱ ተሰደደ

👉ለህዝባችን ለሀገራችን #መመለስ ይሁን ስደት ይብቃ #ክርስቶስን ያሳደደው ሄሮድስ እንደሞተ ሁሉ የአገራችንና የህዝባችን #አሳዳጆችን ልቦና ሰጥቶ ይመልስልን

👉ኢትዮጲያዊያንና የዓለም ህዝቦችን ከመከራና ከስደት እርሱ አምላካችን በቃችሁ ብሎ ይጠብቅልን እናታችን አማላጃችን ወላዲተ ቃል #እመቤታችን_ማርያም በምልጃ ፀሎትሽ ሁላችንንም አስቢን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኀ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ።

🖌 ማርያም! አንድ ጊዜ በጀርባሽ፣
አንድ ጊዜ በጎንሽ ልጅን በማዘል በእጅጉ ደከምሽ
በእግሩ በሚሄድበት ጊዜም ትሸከሚው ዘንድ ያለቅሳል፣
ስንቅሽን ከሚሸከም ከሽማግሌ ዮሴፍና
ከሰሎሜ በቀር አንችን የሚያስተጋግዝሽ የለም፡፡

🌹🌹🌹ሰቆቃወ ድንግል 🌹🌹🌹

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 5/2017 #ቅዱስ_ጴጥሮስ_እና_ቅዱስ_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፃድቁ ስም ለሚመሰገንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስን
በምልጃ ፀሎቷቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ #ቤተ_እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማፀን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት አባታችን #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉መላእክት #በአክናፈ_እሳት_ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል ፃድቁ አዲሱ የምህረት አመት የሠላም የፍቅር የአንድነት ይሆን ዘንድ በምልጃ ፀሎታቸዉ ያስቡን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 5/2017 #ቅዱስ_ጴጥሮስ_እና_ቅዱስ_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፃድቁ ስም ለሚመሰገንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስን
በምልጃ ፀሎቷቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ #ቤተ_እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማፀን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት አባታችን #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉መላእክት #በአክናፈ_እሳት_ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል ፃድቁ አዲሱ የምህረት አመት የሠላም የፍቅር የአንድነት ይሆን ዘንድ በምልጃ ፀሎታቸዉ ያስቡን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 4/2017 #ወንጌላዊዉ_ቅዱስ_ዮሐንስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለወንጌላዊዉ ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ #ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14

👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ
✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✝️ ፍቁረ እግዚእ
✝️ ታኦሎጎስ
✝️ አቡቀለምሲስ
✝️ ቁፅረ ገፅ
✝️ ዮሐንስ ዘንስር

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞላታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን #ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከት እና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 11/2017 #እናታችን_ቅድስት_ሐና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅድስት #ሐና ስም ለምናመሰግንበት #ለቅድስት_ሐና አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በዚህ ዕለት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያቱ እንዲሁም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች #የቅድስት_ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው

👉ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ #አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት

👉ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት #ከአረጋዊ_ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል #ማርያምን ያገለገለቻት ናት

👉ሶፍያም ለባል ተድራ #ለመጥመቁ_ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ይችንም #ቅድስት_ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ፃድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን #ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ #ለቅድስት_ሐና የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው

👉የዚችንም #የቅድስት_ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና #ከሴቶች_ሁሉ_የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ፀጋ ባልተገባት ነበር

👉ይህችም #ፃድቅት_ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በፀሎት ትተጋና ትማልድ ነበር #እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ናት

👉ስለዚህም ይህን ታላቅ ፀጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷ እና ረድኤቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ "አሜን"✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

እግዚአብሔር ትዝ ብሎት ሚያለቅስ አለ ?
ክርስቶስ ትዝ ብሎት ሚያለቅስ አለ ?

የሚያለቅሰውን ሰው እዩት

ሆዱ ሲነካ ያለቅሳል
ሹመቱ ሲነሳ ያለቅሳል
ለገዛ ኃጢአቱ ያለቅሳል
ለዘሩ ሲሆን ይብከነከናል
አንድ የነኵት ለት ማለት ነው

መጀመርያ ለእግዚአብሔር
አርብ እንኳ እንባው መጥቶት አያውቅም


ሲርበው ሲታመም ሲብሰው ሲገፋ ብቻ

እስኪ አሁን ማያለቅስ ማን አለ ?

መጀመርያ ሰው የሚያለቅሰው ለምንድን ነው ?

ለሴት ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለወንድ ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለዝሙት ነው ሚያለቅሰው ሰው
ለዚያ እየየ ሌሊቱን ሙሉ ያለቅሳል
ጣዖት ነው ያሁሉ ነገር

ለገንዘብ ነው ስናለቅስ የኖርነው
ለኩራታችን ነው ስናለቅስ የኖርነው
ለደስታችን ነው ስናለቅስ የኖርነው


የእግዚአብሔር ፍቅር ተለወጠ ያቀረ ጎደልን በሉ

ክርስቶስን እያሰብን እንድናለቅስ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏


ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 10/2017 #መስቀለ_ኢየሱስ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ቅዱስ እፀ መስቀል ለተገኘበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውራንን የሚያበራው ድውያንን የሚፈውሰው ሰላመ #እግዚአብሔርን ያገኘንበት የድህነታችን አርማ ሀይላችን የምንመካበት የምንድንበት ቅዱስ #እፀ_መስቀላችን ነው

👉የድህነታችን አርማ የሆነውን ቅዱስ #እፀ_መስቀል አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ቀበሩት ለዘመናት የቆሻሻ ክምር በመጣል መስቀሉ እዲሰወር አደረጉ

👉በ 320 ዓ.ም የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት #ቅድስት_እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ከ አረማዊ እምነት ወደ ክርስትና እንዲመለስ ስለት ተሳለች በስለቷ መሰረት ልጇ ወደ ክርስትና አምነት ከተመለሰ #የጌታችን_ኢየሱስን_መስቀል ለማግኘት በተሳለችው ስለት መሰረት መስከረም 16 ደመራ ደምራ እጣን በውስጡ ጨምራ አበራች

👉በዚህም ወቅት ጢሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ ወደ ምድር ሰግዶ በዘመኑ ከነበሩት ብዙ የቆሻሻ ክምር ተራራዎች የጌታችን #ቅዱስ_እፀ_መስቀል ወዳለበት ተራራ አመለከተ

👉 #ቅድስት_አሌኒም መስከረም 17 ቁፋሮውን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን ቅዱስ እፀ መስቀሉ ተገኘ።

👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመስቀሉ መታሰቢያ ክብረ በአል በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 9/2017 #ፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው

👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው

👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል

👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡

👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል

👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል

👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች

👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ #መልክአ_መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ፀሎት በፀለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ

👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል

👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ፃድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወጣትነትን ለቅድስና ህይወት
(youth for aholy life)💠💠

በዚህ ገፅ በሃይማኖታችን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሥርዓት መሰረት መንፈሳዊ አስተምሮ እናስተላለፍበት። የምናውቀውን ለማያውቀው ማሳወቅ፤ መንፈሳዊ ትምህርት ማሰራጨት አንዱ ነፍስ የማዳን ስራ ነውና።
ትናትናን አሳልፎ ዛሬን ከሀጢአታችን በንሰሐ እንድንመለስ ተጨማሪ እድሜ የሰጠን እግዚአብሔር ምንሰጠው ስጦታ ምስጋና ነውና ይክበር ይመስገን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ድንግል ማርያምን የያዘ ሰው የክርስቶስ በግ ነው ።
ምልክት የሌለው የላባ ነው ማለት
ምልክቲቱ ድንግል ማርያም ናትና
ድንግል ማርያም የሌለቻቸው ሰዎች የዲያብሎስ ናቸው ።
የክርስቶስ በጎች አይደሉም አንዱ ምልክታችን መስቀል ነው።
መስቀል የላቸውም አያምኑትም ይክዱታል።

ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ።

እኔ ከክርስቶስ መስቀል በቀር በምንም ባንዳች አልመካም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ሥላሴን ስማቸውን ውደዱ

ሥላሴ ተመስገን ሥላሴ ተመስገን ሥላሴ ተመስገን በሉ
ለሰይጣን ከዚህ በላይ ጦር የለውም
ቀኑን ሙሉ ዝምብላችሁ ሥላሴ ተመስገን በሉ
ተመስገን ካላችሁ ዲያቢሎስ እንዴ
ይሄን ሁሉ እያረኵት አይመረውም እንዴ ብሎ
እኛን ማሰልቸት ሲያቅተው እራሱ ስልችቶ ይሄዳል

ሥላሴ ተመሰገን በሉ

የእናት አማላጅ ስለሰጠን
ስጋወ ደሙን ስለሰጠን
የሰማይ በር ስለከፈተልን
በንስኃ ስለሳበን
አንድ ልጁን ስለሰጠን

ሥላሴ ተመሥገን በሉ

ሰማይን ማን አፀናው ?
የ ሥላሴ ስም
ምድርን ማን አፀናት ?
መላእክትን ማን አፀናቸው ?
ፍጥረታትን ማን አፀናቸው ?

ለሁሉ ነገራችሁ የሥላሴን ሥም ተጠቀሙ

የሥላሴ በረከት እረድኤት አይለየን🙏

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

ተፃፈ ፦ በ ዲ/ን ዑራኤል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኃጢአት ማለት ማጣት ማለት ነው

ሰው ኃጢአት ሲሰራ ማንን ያጣል?
እግዚአብሔርን ያጣዋል እግዚአብሄርን ያህል አባት
ገነትን ያጣል ቤተክርስቲያኑን ያጣል ራሱን ያጣል
ወዳጅም ያጣል

ገንዘብ እራሱ ኃጢአት ከበዛ አይበረክትም አይቀመጥም
ገንዝብን ሚያጠፋው ኃጢአት ነው
ስለዚህ ኃጢኣት ራስን ያሰጣል ጉልበት ያሳጣል
ሐብት ያሳጣል ወዳጅ ያሰጣል ቁመናን ያሳጣል
አዕምሮን ያሳጣል አስተሳሰብን ይነሳል ይጎትታል
ተስፋ ያስቆርጣል ነገን ያሳጣል አላማ የለሽ ያደርጋል።
እምንኖርለት ነገር እንዳይኖር ያደርጋል።
ሰማይ እንዳይታየን ያደርጋል ኃጢአት

የማይጠቅም ገመድ ነው አስሮ የሚይዝ
ለጊዜው ደስ የሚል በለስ የተባለ ለዚህ ነው
በለስ መጀመርያ ሲበሉት ይጣፍጣል በኋላ ይመራል ።

ዲያቆኑ

በቅዳሴ ሰዓት የተቀመጣችሁ ተነሱ ይላል

የተቀመጣችሁ ተነሱ ማለት

በኃጢአት አለጋ የተኛችሁ ሰዎች በንስኃ ተነሱ ማለት ነው ።

ፈጣሪ አምላክ ከኃጢአት ይጠብቀን 🙏

ርዕሰ ሊቃወንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️

ተፃፈ :- በ ዲ/ን ዑራኤል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክርስቶስ እኮ አለሙን ሲወድ እንዲሁ ነው
ሰዉ ግን ሰዉን ሲወድ የሆነ ነገሩን አይቶ ነው
ለዚያውም አይቶም መልሶ ማየት ላይፈልግ ይችላል
አግኝቶም በኋላ ማግኘት ላይፈልግ ይችላል
ሁሌም የሆነ ነገር አይቶ ፈልጎ
ለጥቅሙ ብቻ የሚወድ ከዚያም የሚገፋ
ብቸኛው ፍጡር ሰው ነው።

እግዚአብሔር ግን አለሙን ሲወድ እንዲሁ ነው።
ያለምንም ምክንያት ያለምንም ጥቅም ነው።

እንዲሁ እንዋደድ ዘንድ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

🌹 #ኅዳር ፮ (6) ቀን።

🌹 እንኳን #ክብር_ይግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም #ከአረጋዊ_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ #ደብረ_ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም #ላአረፉበት_ዓመታዊ_መታሰቢያ በዓል፣ #ለሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ፊልክስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ፍሞስ_ከቅዱሳን_ለንዲዎስ_ከይላጥስ፣ #ከማርትሮስ_ከኢላስዎስ_ከቆርናልዮስ_ከሱኪሮስ #ከናውኔኖስ_ከሊባዲቆ_ከሲላስዮስና #ከሰማዕት_ኤስድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ከሁለት_መቶ_ሰባ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✝ ✝ ✝
🌹 #በዚች_ቀን_ክብርግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_ከአረጋዊው_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋር በስደት በሚመለሱ ጊዜ #ወደ_ደብረ_ቊስቋም ገባ በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም ዐረፉ።

🌹 ዳግመኛም በኋላ ዘመን በዚህ ደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው። ለዚህም የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮችን ሆኑ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።


✝ ✝ ✝
🌹 #የሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ፊልክስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው።

🌹 ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ፊልክስን መረጡት በእግዚአብሔርም ፈቃድ በሮሜ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የክርስቶስንም መንጋዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ።

🌹 ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር ነገሠ። እርሱም በምዕመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት። ስርሱም ወደ እግዚአብሔር ማለደ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህንን ከሀዲ በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው።

🌹 ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አብዝቶ ማሠቃየትን ጀመረ ይህም አባት ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያይ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዲዮቅልጥያኖስም በመጀመሪያው ዘመነ መንግሥት ኅዳር 6 ቀን ዐረፈ።

🌹 ይህም አባት ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጾችን ደርሶአል ከእርሳቸውም ስለ ውግዘትና ስለ ቀናች ሃይማኖት የተመላለሰብት አለ እሊህም ለክርስቲያን ወገን እጅግ የሚጠቅሙ በጎዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ፊልክስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 6 ስንክሳር።


✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የማኅሌቱ_ምስባክ፦ "ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ። ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር ዕጐሊሃ። ምሥዋዒከ እግዚኦ እግዚአ ኃያላን"። መዝ 83፥3 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ22፥14-24።

✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ። ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ። ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ"። መዝ 36፥35። የሚበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 8፥1-16፣ 2ኛ ዮሐ 1፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ማቴ 2፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቊስቋም ማርያም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

1, ሴት ሱሪ መልበስ ኃጢአት ነው
2, ዘፈን ማዳመጥ ኃጢአት ነው
3, መስከር ኃጢአት ነው
4, ዝሙት ኃጢአት ነው

እስኪ ከዚህ ሁሉ የቱን ነው ማትሰሩ ?

👇👇👇👇👇
/channel/uraman78tu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ ኅዳር 5 ቀን ጌታ መድኃኔ ዓለምን ጎኑን በጦር የወጋው የሰማዕቱ የለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡
☞ለንጊኖስ ሰማዕት ☞ አስቀድሞ ጌታችንን ጎኑን በጦር የወጋው ነው፡፡ በኃላም
በጌታችን አምኖ ወንጌልን ሰብኮ በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
☞ከዮናናውያውን ወገን ሲሆን የሮማውያን ወታደር ነበር፡፡ ጲላጦስ ጌታችንን
እንዲሰቅሉት ለአይሁድ አሳልፎ ሲሰጠው ይህ ለንጊኖስ ከጲላጦስ ጭፍሮች
ውስጥ አንዱ ስለነበር የጌታችንን ሥቃይ አይቶ በክፋ ግብራቸው ላለመተባበር
ብሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ነበር፡፡
✞በዕለተ ዐርብ ግን ሮማውያን በጌታችን መከራ ያልተባበረን ሁሉ እንደ ንጉሥ
ጠላት ሰላዩት መድኃኔዓለምን ክርስቶስ በመጨረሻ ሰዓት "ተፈጸመ"ካለ በኃላ
ለንጊኖስ ወደ ቀራንዮ ተራራ ወጣ፡፡
☞ሮማውያን የሁለቱን ሽፍቶች አጥንቶች ሲሰብሩ ለንጊኖስ ደግሞ ከሞት
መቼም አልጎዳውም ብሎ አስቦ የጌታችንን ጉኑን ወጋው፡፡ በዚያም ጊዜ አንዱ
ዐይኑ ዕውር ነበርና ከጌታችን ከግራው ጉኑ ውኃና ደም ሲወጣ የታወሰ ዐይኑን
ቢነካው ዐይኑ በራችለት፡፡
☞በዚህም እጅግ ተገርሞ እየተደሰ የሆነውን ሁሉ ማስተዋል ጀመረ፡፡ ጌታችንም
ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ሲለያት የተፈጸመውን ተአምራት አስታወሰ፡፡ ትንሳኤውን
ሲሰማ ይህን ምሥጢር ይገልጽለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ጀመረ፡፡
☞ጌታችንም ሐዋርያውን ቅዱስ ጴጥሮስን ላከለትና ሁሉን ምሥጢር ገለጠለት፡፡
ያን ጊዜም በሙሉ ልቡም አምኖ አእስከሞት ድረስ ለመታመን ተዘጋጅቶ
በክፋዎች አይሁድ ፊት ስለ ጌታችን አምላክነት መመስከር ጀመረ፡፡
☞ወደ ታናሹዋ እስያ ወደ ቀጵዶቅያ ሄዶ በዚያ ወንጌልን እንደ ሐዋርያት
በመስበክ ብዙዎችን ወደ፡ቀናች እምነት መልሷቸዋል፡፡
☞አይሁድም በክፋት ተነሥተው የሐሰቶ ምስክር አቁመው ሰለከሰሱት የሮማ
ወታደሮች ይዘውት በንጉሡ በጢባርዮስ ቄሣር አስፈርደው ሐምሌ 23 ቀን
አንገቱ ሰይፈውት በሰማዕትነት እንዲርፍ አድርገውታል፡፡
☞ ይቺ ራሱንም ብቻውን ወደ እየሩሳሌም ወሰዷት፡፡ በምስክርነቱ የቀኑና
የተናደዱ በዚያ የሚኖሩ አይሁድም ባዩአት ጊዜ እጅግ ተደስተው ከከተማ ውጭ
በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሯት፡፡
☞ከብዙ ቀንም በኃላ በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዴት ሴት በቀጵዶቅና
አገር ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምሮ በተቆረጠበት ቦታ በሐቆም ስለ እርሱ
ታለቅስ ነበር፡፡ ከጊዜ በኃላ አይኖቿ ታወሩ፡፡
☞የጌታችንን መቃብር ለመሳለም ተነሥታ ከልጇ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡
በደረስችም ጊዜ ልጇ ሞተ፡፡
☞በሀዘን ሆና ሳለ ወደ ሀገሯ መርቶ የሚወስዳት ስላጣች መሪር ለቅሶን አልቅሳ
ደክሞት ተኛች፡፡ ተኝታም ሳለች ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞት ልጇ ጋር በራእይ
አየችው፡፡ ራሱ ተቀብራ ያለቾበትንም ቦታ ነገራትና ሄዳ እንድታወጣ አዘዛት፡፡
☞ወደ ቦታውም ሄዳ ስታስቆፍረው መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ
ወጣ፡፡ አናም ያቺ ሴት የቅዱስ ለንጊኖስ ራስ ያለችበት ቦታ ስትደርስ ታላቅ
ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿ በሩላት፡፡ የቅዱስ ለንጊኖስ ራስና የልጇን ሥጋ ይዛ
ወደ ሀገሯ ወስዳ ባማረ ቦታ አኖረቻት፡፡ ይኽም ተዓምር ኅዳር 5ቀን ተፈጸመ፡፡
☞( መዝገበ ቅዱሳን)
☞የሰማዕቱ የቅዱስ ለንጊኖስ የጸሎቱ በረከት አይለያችሁ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞4-3-2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ሴት ሱሪ መልበስ ኃጢአት ነው
ዘፈን ማዳመጥ ኃጢአት ነው
መስከር ኃጢአት ነው
ዝሙት ኃጢአት ነው
እስኪ ከዚህ ሁሉ የቱን ታሟላላችሁ ?
👇👇👇👇👇
@uramant78tu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ አበው ቅዱሳን፦

✿አቢማኮስ ወአዛርያኖስ (ዘሮሜ)
✿ያዕቆብ ወዮሐንስ (ዘፋርስ)
✿ቶማስ (ዘደማስቆ)
✿ዘካርያስ ክቡር (መምህር)
✿አባ አበይዶ (ዘደብረ ዓሣ)
✿ጉባዔ ሰማዕታት (ዘብሔረ ግብጽ)
✿ወጴጥሮስ (ሊቀ ጳጳሳት)

ኅዳር ፬፦

✝ማርያም ድንግል ጸዋሪተ ቁርባን ጵርስፎራ፤
ወጽዋዐ ልቡና እሳተ ዘይመስል ኅብራ፤
ዘሰትየ ወጎስዐ ጠቢበ ጠቢባን ዕዝራ፤
ታሕተ ሰግላ አሐቲ አመ አገትዋ ሐራ፤
ዘምስለ ዮሴፍ ወሰሎሜ ስብሐተ ወልዳ ሠወራ!

✝ሰላም ለአበይዶ ረድአ ጻድቅ ዮሐኒ፤
ወዘካርያስ ዘገደፈ ግብረ ዓለም ማሳኒ፤
አቢማኮስ ወአዛርያኖስ ሰማዕታተ ክርስቶስ አዶኒ፤
ቶማስ ዘደማስቆ ፍትወታተ ሥጋ መናኒ፤
ያዕቆብ ወዮሐንስ ወብእሴ ሰላም አርሳኒ!

✝ሰማዕታተ ሮሜ ክቡራን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ፤
ያዕቆብ ወዮሐንስ ዘአብርሁ በብሔረ ፋርስ፤
ኮከበ ደማስቆ ወአድሚሃ ቶማስ ኤጴስ ቆጶስ፤
ብእሴ ሰላም ዐቢይ ወትሩፈ ምግባር ዘካርያስ፤
ወአበይዶ ረድአ ዮሐኒ ዘሎቱ ሞገስ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አይታችሁ እንደሆን

30 ዓመት ሙሉ እግዚአብሔር ትዝ ብሎት የማያውቅ ሰው
ሲያመው ፀበል ሲገባ ነው እግዚአብሔርን የሚያሰበው
እግዚአብሔርን ማሰቢያስ መቼ እናግኝ ብላችሁ ነው
ስንባክን ስንባክን ስንባክን ባይንስ ሲያመን እግዚአብሔርን እንድንአስበው ነው
እሱ በመንግስቱ እንዳያስበን እኛ ታመን እንድናስበው
እግዚአብሔር በሽታ ይሰጣል ።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

Читать полностью…
Subscribe to a channel