kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1876

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ኅዳር_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ ቀን #የሰማዕት_ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው፣ ሁለተኛው የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_አንያኖስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት

ኅዳር ሃያ በዚህችም ቀን የሠራዊት አለቃ የነበረ የሰማዕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው።

የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።

ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ።

አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።

ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው።

የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።

ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ አለው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ የበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና። ንጉሡም እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ አለው።

በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በእግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ አላቸው። እነርሱም ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን አሉት እርሱም ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ አላቸው።

ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ አሉት።

ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው ጌታዬ አምላኬ ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከአእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን።

ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በመስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።

አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።

በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው።

ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል እግዚአብሔርም ይበቀልላታል አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።

ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል።

በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት።

በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣ ወይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ

ለሁሉ ያስባል ሁሉንም ያጠግባል ።
ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል ።
የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል።
ጽሙማንን ያሰማቸዋል ።
የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል ።
ከሰውነት የለምጽን ልብሶች ገፎ
የሥጋን መጐናጠፊያ ያለብሳቸዋል ።

የደረቀውን (የሰለለውን) የእጅ ክንድ ያቀናል
የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ።
ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል ።
መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል ።

ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ❣️

ለሱ ለመድኃኔ ዓለም ክብር ምስጋና ይግባው🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አስቸኩአይ መልክት ከአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም አባ ጴጥሮስ የሚባሉ ለብዙ አመታት ተሰውረው የኖሩ አባት እንዲህ ብለዋል የመጨረሻው ምፃት ስለሆነ ንስሀ ግቡ ብለዋል።ቢያንስ(ለ10 ሰው) አስተላልፉ ሳታስተላልፉ ብትቀሩ በድንንግል ማርያም የተወገዘ/የተረገመ/ ይሁን ብለዋል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

የ ተ ቀ ደ ደ ል ብ ስ

" የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥..... ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል።"(ኦሪ ዘሌ.13፥45) እንደሚል የተቀደደ ልብስ የለበሰ ሰው የተዋረደና በኃጢአት እንደረከሰ እርኩስ ነኝ እያለን ነው ማለት ነው ። የቅዱስ ዳዊት ልጅ ትዕማር በወንድሟ በተደፈረች ጊዜ " ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብሷን ተርትራ፥ እጇንም በራሷ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች ይለናል፡፡ (1ኛሳ.13፥19)

ከእስራኤል ወገን በሆነው በአካን ምክንያት እሥራኤል በደረሰባቸው መከራ " ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ ......"እንዲል መጽሐፍ ቅዱስ። ( ኢያሱ . 7፥6) እኛም የተቀዳደደ ልብስ ስንለብስ እንደረከስንና በኃጢአታችን መከራ እንደደረሰብን እየገለጽን ነው፡፡ እንዲያም ቢሆን ደግሞ ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን በንስሃና በጸሎት ልንበረታ እንጂ ደረታችንን ነፍተን ባልዘነጥንበት ነበር።

ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ በሐዘን ምክንያት ልብሳቸውን የቀደዱና ያዘኑ እንዳሉ'' ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።'' ሲል አባታችን ያዕቆብ በዮሴፍ ምክንያት ያለቀሰውን ለቅሶ ጽፎልናል (ኦሪ.ዘፍ 37-34) እንዲህ አይነቱን ሐዘን እዮብም አድርጎታል። '' ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ....."(ኢዮ.1-20) ስለዚህ ክርስቲያን የተቀደደን ልብስ ሊለብስ አይገባም።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.instagram.com/jrusalem_21/profilecard/?igsh=MTBkbmVydGE4emY4bg==

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 18/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ሠላማ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት አባታችን #አቡነ_ሠላማ ጵጵስና ለተሾሙበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን

👉ወር በገባ በ18 #ፃድቁ_አቡነ_ሰላማ_ከሳቴ_ብርሃን ናቸው የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ ስመ ጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከአባቱ #ከቅዱስ_ምናጦስና ከ #ቅድስት_እናቱ_ማርያም ሰናይት በጢሮስ #ግሪክ ተወለዱ

👉እድሜያቸዉ ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ #ሃይማኖታዊ_ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር

👉ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ ፈላስፋ ወደ ህንድ አገር ሊያልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር በጀልባ ጉዞ ጀመረ ከእርሱም ጋር ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ የአንደኛው ስሙ #ፍሬምናጦስ የሁለተኛው ደግሞ #ኤዴስዮስ_ሲድራኮስ ይባላል

👉ሜሮጵዮስ እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ ወደ አፍሪካ ባህር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባህር ወደብ ውሃ ለመጠጣት እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ

👉በዚህ ጊዜ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የአዱሊስ ነዋሪዎች በጀልባዋ ላይ አደጋ በመጣል #ሜሮጵያስንና የጀልባዋን ቀዛፊዎች እዚያው ገድለው ሀብታቸውን ዘረፏቸው

👉ሁለቱ ወጣቶች ግን ተረፉ በማያውቁትም አገር ያለ ዘመድ ያለ ሃብት ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ሥር ተቀምጠው ሲፀልዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ያዟቸውና በጊዜው በአክሱም ነግሶ ለነበረው #ለንጉሥ_ታዜር በፈረስ አንገት በጦር አንደበት የተማረኩ ሰዎች አመጣንልህ በማለት አስረከቡት #ንጉሥ_ታዜርም በቤተመንግስቱ ውስጥ እንዲያድጉ ፈቀደላቸው

👉ከጊዜ ወደ ጊዜ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ተወዳጅነትንና ታማኝነትን አገኙ #የአብርሃ እና #አፅብሃ አባት የነበረው ንጉሥ ታዜር ኤዴስዮስን ጋሻ ጃግሬ ፍሬምናጦስን በጅሮንድ አድርጎ ሾማቸው

👉#ንጉሱ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ ልጆቹ ገና አካለ መጠን አልደረሱም ነበርና መንግስቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለእቴጌይቱ አደራ ሲል ሁለቱን ሶርያውያን ምርኮኞች ግን ነጻ ለቀቃቸው ነገር ግን በእቴጌይቱ ልመና ወደ አገራቸው መመለሳቸው ቀርቶ ልጆቿ እስኪያድጉ ድረስ በአስተዳደር በኩል ሲረዷትና ሲመክሯት ቆዩ

👉#ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተ መንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ #እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ #የተዋህዶ እምነት #ጥምቀትና_ክህነትን በሚገባ የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር

👉ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም #ልዑላኑ_አብርሃና_አፅብሐ አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስትሲረከቡ #ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ

👉 #ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብፅ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ #በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው በዚህ መሰረት ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ #ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ #እስክንድርያ ሄደ

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሠላማ በረከት "አሜን"✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ | ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ | ተቋማዊ ዕቅበተ እምነት
https://youtube.com/watch?v=HqyhPq_Jf-g&si=Atayu8P2g6qz4m24

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ ኅዳር 17 በእረፍት በዓሏ ታስባ የምትውለው እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ማነች?
☞ይቺ ደገኛ ሴት አባቷ ባሕር ሰገድ እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡
☞የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ነው፡፡
☞ይቺ የተቀደሰች እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በሕግ በሕግ በሥርዓት
በሊቀ ጳጳስ ትዕዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነው መላክአ
ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ
ነበርና ከልጆች ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደጀመረች፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ
እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የሚያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው፡፡ ብላ ከጸለየች
በኃላ እንደፋላጎቷ ሦስት ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡
☞ባለቤቷ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ይህን ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል፡፡ ብላ
ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች፡፡ በዚያም
በተጋድሎ ስትኖር ባሏ አበምኔቱን ለምን ገዳም አሰገበሀት ብሎ ከሰሳቸውና
ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኮል ገዳም
ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡
☞በዘመኗ የነበረው ገዢ ጨካኝ ለጣዎት የሚሰግድ ሰለነበረ በትልቅ ገደል
ወረውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅድስ ሚካኤል
ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፋ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓን አሳይቶ
መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡
☞ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስ ወደ ጉምዝ ሀገርም ተስዳ ሳለ በነደደ አሳት
ውስጥ ቢጨምሯት ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕር
ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ቧላም እምነቱን ቀይሮ
ከካቶሊኮች ጋር ሰለተዛመደ ቅድስ እናታችን ካቶሊኮቶችንና ባሏን አጥበቃ
ሰለተቃወመች በገመድ አሰረዋት በጎንንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃያት፡
☞ቅድስ ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700በላይ በሚሆኑ
ወንዶች መነኮሳትና ሴቶች መነኮሳት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ
አገልልግላለች፡፡
☞ከመነነችበት ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረረ ቅጠል፤ኮሶና አመድ ነበር፡፡
ቅድስት እናታችን ታላቁን የራማ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን
እያነሳች ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17ቀን
በታላቅ ከብር ዐርፋለች፡፡ ወርሐዊ የመታሰቢያ ዕለቷ ወር በገባ በ17 ነው፡፡
በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምስሶ ከምድር ሰማይ
ተተክሎ ታይቷል፡፡
☞የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዐፅሟ በራሷ በመሠረተችው በሬማ መድኃኔአለም
አንድነት ገዳም ውስጥበክብር ተቀምጦ ይገኛል ፡፡በዚህ ገዳም ውስጥ በቅድስ
ሥላሴ ምሳሌ የተሠሩ ሦስት የተለያዩ ድምፆችን የሚያወጡ ደወሎች ይገኛሉ፡፡
ሦስቱም ደውሎች የሚያወጡት ድምጽ ፍጽም የተለያየ ነው፡፡
☞የእናታችን የወለተ ጵጥሮስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ☞መዝገበ ቅዱሳን
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞16-3-2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" ከመረጥዃቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
መዝ. ፹፱፥፫ /89፥3/
❤️ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር አምላካችን በተለያዩ ጊዜያት ከመረጣቸው ከወዳጆቹና ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በየዘመናቱ ቃል ኪዳን ፈጽሟል
❤️ በየካቲት ፲፮ (16) ቀንም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የማይጠፋ የዘላለም ቃል ኪዳንን አደረገ
❤️ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በሚማፀኑ፣ መታሰቢያዋን በሚያደርጉ፣ ለችግረኞች ለሚራሩና በስሟ ቤተክርስቲያንን ለሚያንጹ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ ለእናቱ ቃል ኪዳን ገባ
➻ እኛም ይህንን ዕለት ኪዳነ ምህረት እያልን እናከብረዋለን
❤️ በቤተክርስቲያናችንም ይህ ታላቅ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፣ ቃል ኪዳኑም ይታወሳል
አምላካችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይክፈለን። የእመቤታችን አማላጅነትም አይለየን። /channel/Tewahedomender

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 16/2017 #እናታችን_ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት

"ከመረጥኋቸዉ ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግኹ"መዝ.88፥3

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን

👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው

👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ.9፥16

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የአበዉ ነብያት ረድኤት በረከት አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🖌 ሦስት ዓመት ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነት የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዛሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ሲሆን በኅዳር 15 ቀን ተወልዷል፡፡ 

🖌 ዛሬ ኅዳር 15 የልደቱ መታሰቢያ ቀን በቤተክርስቲያናችን ታስቦ ይውላል። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃልኪዳኑን ሰቶታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን አሜን።


#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ

" ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል ማቴ.10፥42 "

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #መልአክ_በክንፉ_ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል

👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች

👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሣኑን ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ያድለን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💕ቅዱስ   ዮሐንስ  አፈወርቅ 💕

👉ራሱ  ጌታችን ተሰዉቶ  በመሠዉያዉ (በጻሕሉ ) ላይ  ሁኖ

 
👉 ካህኑ  ቁሞ ለመሥዋዕት  በቀረበው  ላይ ሲጸልይ 

👉ምእመናን  በሙሉ  በከበረዉ   ደሙ  ፈሳሽነት  ነጽተዉ ስታይ 

👉አሁንም  በሰዎች  መኻከልና  በምድር  ላይ  እንደቆምህ  አድርገህ  ታስባለህን?

👉ይልቁንስ በተቃራኒው  ወደ ሰማየ ሰማያት  ወጥተህ ፣

👉ምድራዊ  አስተሳሰብን  ኹሉ  ከሕሊናህ አሽቀንጥረህ  ጥለህ

👉 በመንፈስና በርቱዕ ሕሊና  ሰማያዉያን ነገሮችን አታስብምን?

👉ወዮ!  እንደምን ይረቅ?
እንደምን ይደንቅ?
ለሰዎች  የተደረገው  የእግዚአብሔር  ቸርነት 
እንደምን  ያለ ቸርነት  ነዉ?

የቅዱሳን  አማላጅነት  አይለየን !!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ አዳዲ ማርያም🙏
መነሻ ቀን በ21
የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ አዳዲ ማርያም
መነሻ ቦታ ፣፣ አስኮ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
በእለቱ የ ፀበል መጠመቅ የፀሎት ፕሮግራም የተለያዩ ሰባኪ መምርሀን ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ ።


ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 600 ብር ብቻ።


ስልክ 09-91-11-96-29
09-25-49-26-34 ይደውሉልን

ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

የሰው ስህተት የሚለቅም እሱ ሰይጣን ነው።
እኩይ ፍልስጣ የሚባል ሰይጣን አለ

✅ የሰይጣንም ድርሻ ድርሻ አለው

የሚያሰርቀው ሰይጣንሌላ ነው
የሚያዘሙተው ሰይጣን ሌላ ነው
የሚያጣላው ሰይጣን ሌላ ነው

እኩይ ፍልስጣ

ደሞ የሰውን ክፋቱ ሁልጊዜ ነው የሚመዘገብ

✅ ለምሳሌ

እኔ ዝክር ስዘክር አይመዘግብም

የሰርቅኩ ዕለት ሰርቋል እያለ ይፅፋል
ዛሬ ስፀለይ አደረኩ ነገ ተኝቼ አደርኩ ተኝቷል ብሎ ይጽፋል

በፍፁም አንድ መልካም ነገር አይመዘግብም

ሁልጊዜ ክፋት የሚመዘገብ ሰው እኩይ ፍልስጣ ይባላል ።

በ ነገራችን እቤትም በሰላም ማትኖሩት ለዚህ ነው ።
መልካም መልካሙን ብትቆጥሩ ምን አለ ።

እግዚአብሔር መልካም መልካሙን ቆጥሮ ነው
ክፉ ክፉን ቆጥሮ ነው የሚያድነን ?

✅ መልስ

መልካሙን ቆጥሮ ነው

✅ እግዚአብሔር

እገሌ አርብ ሰርቋል ሰርቃለች የሚለውን ሳይሆን
ሐሙስ ዘክሯል ዘክራለች የሚለውን ነው የሚያየው

አባቶቻችን እንደሚሉት

ሰይጣን ሰውን ለማጥፋት ምክንያት እንደሚፈልግ
እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ምክንያት ይፈልጋል።

✅ ምክንያት ከመፈለጉ የተነሳ

ጠጅ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል
በሬ እረዱ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል።
በግ ብላቸው ስንቱ ይሳካለታል ።
ወርቅ ብላቸው ስንቱ ይሳከለታል ብሎ

ቀዝቃዛ ዉኃ ሰጣችሁ ዳኑ አለ
ሰውን ለማዳን ወርዶ እስከዚህ ድረስ ዋጋ ይከፍላል ።

✅ ስለዚህ እግዚአብሔር

መንግስተ ሰማያትን ያህል ሀገር
በቀዝቃዛ ውኃ ሽጣት
ይላሉ ሊቃውንቱ

ክፍትን ከመመዝገብ ፈጣሪ አምላክ ይጠብቀን🙏

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዘማሪ አህዋዝ ሚስጥር

እንደምታውቁት ከቀናት በፊት ዘማሪ አዕዋዝ ከነበረበት የተሐድሶ እንቅስቃሴ ወደ ኦርቶዶክስነት መመለሱን ሰምተናል ለዚህም ብዙ ምክኒያቶች እየተነገሩ ይገኛል ዛሬ በወጣው አንድ መረጃ ግን ዘማሪው በተገኘበት ሚስጥራዊው ቪዲዮ ቅጂ መሆኑ ታውቋል

ኦርቶዶክሶችም ፕሮቴስታንቶችም በማይሆን ነገር ጫፍ ለጫፍ ቁጭ ብላችሁ ከምትተራረቡ እውነታውን ከታች ያለውን Play የሚለውን በመንካት ሙሉ ሚስጥራዊውን ቪዲዮ አይታችሁ እውነታውን ፍረዱ

Play የሚለውን ንኩት👇

Play

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ጨለማን ያሳደደው ብርሃን
ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና
የማይነዋወጥ መሠረትና የማይፈርስ ግንብ
የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማኅደር ።
ያማረ ቀንበርና የቀለለ ሽክም
እርሱ ለአባቱ ኃይሉ ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/Tewahedomender/55

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።"
ዳን. ፱፥፳፩ /9፥21/

❤ በቅዱሱ መጽሐፍ ስማቸው ከገነነ የእግዚአብሔር መላእክት አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ነው

❤ የስሙም ትርጓሜ "ከእግዚአብሔር የሆነ አለቃ" ማለት እንደሆነ መጽሐፍት ይነግሩናል

❤ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን በማወጅ የሚታወቅ መልአክ ነውና የደስታና የብሥራት መልአክ ይባላል

❤ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሐዲስ ኪዳን ተደጋግሞ ስሙ በመጠቀሱ "መጋቤ ሐዲስ" ይባላል

አምላካችን እግዚአብሔር መላእክቱን ልኮ የነደደብንን እሳት ያጥፋልን። የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን።

#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#ቅዱሳን
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 19/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል

" እኔ #በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው #ገብርኤል ነኝ "
ሉቃስ.1፥19

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ገብርኤል ‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው

👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንሰኝበትን ፀጋ አሰጠን

👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው #ክፉ_ቀንና_እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን

👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች ሟርተኞች ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃህ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን

👉#ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን #የጥፋት_ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን

👉 #ለእውነተኛ_ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን

👉 ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብን ቁጥር እያለቀስን እንጠራሃለን ጎስቋላ የምንሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምንገኝ ልጆችህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት እንፈልጋለንና ፈጥነህ ናልን

👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ፊት ዘወትር ትቆማለህና ፀሎትና ልመናችንን ስማ

👉ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንንና ለእኛ ለቃል ኪዳን ልጆችህ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን

👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ #የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን

👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው #ድንግል_ማርያምን በጣም እንወዳታለን

👉በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን #በመንግስተ_ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን

👉#ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ በአምላካችን #በክርስቶስ ፊት ቆመህ ለምንልን የሀገራችንና #የህዝቦቿ የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አስታግስልን ጦርነትና ረሐብ ከምድራችን ላይ ይወገድ ዘንድ ለምንልን "አሜን" ✝️⛪️✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።'' ዘዳ 22 ፤5

ብርድ ልብስ ለብሰን እንኳን በማንቋቋመው የብርድ ወቅት ሰውነትን በቅጡ የማይሸፍን ብጣሽ ጨርቅ ጣል አድርጎ መውጣት እንዴት ያለ ምቾት ነው? እጅግ አስጨናቂ ሙቀት ባለበት ሰዓት ሰውነት ላይ ተጣብቆ ሌላ ጭንቀት የሚፈጥር አለባበስ በእውነት እንደምን ብሎ ያስደስታል? እህቶች ሆይ ለእኛ የማይገባውን ልብስ ስለ ምን እንለብሳለን? በእውነት እግዚአብሔር ይገስፀን ።

መሰናክሎች በልዩ ልዩ መንገዶች ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን መስናክሉን የሚያመጣው ሰው ወዮለት ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ። የእህቶቻችን አለባበስ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያስተምረናል ። ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ መሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ እርግጥ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊ ሕይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢያት አጋልጦ ይሰጣል፡፡

እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት ይቻል ይሆናል። እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ የሚለውን ጭምር ነውና በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢያት ነው፤ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡ ማቴ 18 ፤ 6

አንዳንዶቻችን ሴቶች "እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም'' ይላሉ ፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል ''እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው፡'' ''ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል'' የሐዋ 5 ፤ 29

ታዲያ ቀሚስን የወንድ ሱሪን የሴት ማን አደረገው? የሚሉ ሴቶች ገጥመውኛል። ይህ የሰነፍና ለስህተታቸው ምክንያትን የሚሹ ሴቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል አውቀን ልንፈፅመው እንጂ በቃሉ ላይ የምንፍቅና ጥያቄ እናነሳ ዘንድ ተገቢ አይደለም ። ግን ደግሞ ተፈጥሯችንን ብቻ በማየት ህሊናችን እራሱ ቢናገር ሱሪ የሴት ነውን?

ቀሚስስ የወንድ ነው እንዴ?

''ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 17/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉የትውልድ ሀገሩ #ኢየሩሳሌም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች ዘመኑም የመጀመሪያው ምእተ ዓመት ነው

👉እንግዲህ በዘመነ ሐዋሪያት የማዕዱን እና የውስጡን አገልግሎት እንዲያስተናብሩ መንፈስ እና ጥበብ የሞላባቸው ሰባት ሰዎች ተመርጠው በሐዋሪያት አንብሮተ እድ ሆነው ከተሾሙት ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስቲያኖች አብነት የሆነው ሰማዕቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ይገኝበታል እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም #አክሊል ማለት ነው

👉መፅሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ምንም እንኳን ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው

👉ወላጆቹ ይህንን ስም የሰጡት ተብሎ የሚታመነዉ ወላጆቹ በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለ ነበር የግሪክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል

👉 #ቅዱስ_እስጢፋኖስ በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር በእርሱም ታላላቅ ተአምራት ይፈፀሙ ነበር

👉ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ #እስጢፋኖስ ላይ በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም

👉ስለዚህም #እግዚአብሔርን ሙሴን ሲሳደብ ሰምተነዋል ሙሴ የሠራልንን ሥርዐት ይለውጣል በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን ቃል ይናገራል ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ ብሎአል እያለ ያስተምራል እያሉ ሕዝቡን ሽማግሌዎችንና ፀሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት

👉ቅዱስ #እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ #መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው

👉 #ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው #ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ ይህንን ራእይ የክርስቶስን ትንሣኤን ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ

👉እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት ነገር ግን #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ እንደ መምህሩ #አቤቱ_ይህን_ኃጢአት_አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለ ክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ሆኖአል

👉በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ የነበረ ብላቴና ነበር

👉ነገር ግን #ቅዱስ_ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ የሰማእቱ #የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቆአቸዋል ይህ ደግሞ ድንቅ ነው በቤተክርስቲያን መፅሐፈ ስንክሳር የበዓላት ዝርዝር ላይ የመታሰቢያ ቀን በመስጠት ይከበራል

👉በጥቅምት "17" ቀን የድቁና ማዕረግን በአንብሮተ ዕድ በሐዋርያት የተቀበለበትን፣ ጥር "1" ደግሞ የእረፍቱ መታሰቢያ ሆኖ ይከበራል፣በየወሩ በ "17" የሰማእቱ መታሠቢያም ነው በረከቱ ምልጃና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ፀሎቴን ቶሎ ሰምቶ አልመለሰልኝም ያልነው አምላክ
ሀጥያትም ስንሰራ ቶሎ ያልቀጣን አምላክ ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅድስት ኪዳነ ምህረት

እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" ከመረጥዃቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
መዝ. ፹፱፥፫ /89፥3/

❤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር አምላካችን በተለያዩ ጊዜያት ከመረጣቸው ከወዳጆቹና ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በየዘመናቱ ቃል ኪዳን ፈጽሟል

❤ በየካቲት ፲፮ (16) ቀንም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የማይጠፋ የዘላለም ቃል ኪዳንን አደረገ

❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በሚማፀኑ፣ መታሰቢያዋን በሚያደርጉ፣ ለችግረኞች ለሚራሩና በስሟ ቤተክርስቲያንን ለሚያንጹ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ ለእናቱ ቃል ኪዳን ገባ

➻ እኛም ይህንን ዕለት ኪዳነ ምህረት እያልን እናከብረዋለን

❤ በቤተክርስቲያናችንም ይህ ታላቅ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፣ ቃል ኪዳኑም ይታወሳል

አምላካችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይክፈለን። የእመቤታችን አማላጅነትም አይለየን።

#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ተዋህዶ
#ድንግል
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ሹመትም አይኑራችሁ እውቀትም አይኑራችሁ
ጤናም አይኑራችሁ ሀብትም አይኑራችሁ
ማርያም ስላለችልን ብቻ ደስ ሊለን ይገባል።
እሷ ስላለችን ይበቃናል ።

የ አክል ሐይማኖት ዘአልቦ ጥልቀት
ወእምነት
በ ቅድስት ድንግል ከመ
ይዕቲ ወላዲተ አምላክ

✅ ዘአልቦ ጥልቀት አለ

ጥርጥር የሌለበት ሐይማኖት ለምንም ነገር ይበቃል።
ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ ማመን ለሁሉም ይበቃል

ለልብስ ይበቃል ክርስቶስን እንለብሳለን
ለምግብ ይበቃል የህይወት እንጀራ ልጇን እንበላለን።
ለጥበቃ ይበቃል መልካም እረኛ ልጅ አላትና በእሷ ይጠብቀናል ።
ስለዚህ ምንም የሚጎልብን ነገር የለም
ሰው ማርያምን ከወደደ የሚያጣው ነገር የለም ።

መለመን ያለብን

የእናትህን ፍቅር ጨምርልን ብለን ነው
መፀለይ ካለብን እሷን ነው
በኃጢአት የመረረው ህይወታችን ሊጣፍጥ የሚችለው
ጥዕምተ ስም ማርያም በልቡናችን ያደረች እንደሆነ ነው

እሷ ስታድርብን

መራራው ንቅል ንቅል ንቅል እያለ ይጠፋል

መራራውን ህይወታችን
መራራውን ኃጢአታችን
በእናቱ በጣፈጠው ሥሟ ነቅሎ ይጣልልን 🙏


ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

ወዳጄ ሆይ

👉ባልንጀራህን በቁጣ ገንፍለህ ልትመታዉ ትችላለህ

👉ልብሱንም ልትቀድበት ትችላለህ

👉የከፋው ቅጣት የምትቀበለው ግን አንተው ራስህ ነህ

👉ምክንያቱም በቡጢ ብትመታዉ ሥጋውን ነዉ

👉አንተ ግን የምትጎዳው ነፍስህን ነዉ።

👉የባልንጀራህን ልብስ ልትቀድበት ትችል ይሆናል

👉አንተ ግን ከሁለት የምትተረትራት የገዛ ነፍስህን ነወ።

👉ባልንጀራህን ብትመታዉ ሥጋዉን ነዉ

👉አንተ ግን የምትጎዳው ነፍስህን ስለ ኾነ ሥቃይህም የነፍሰ ነዉ።

የ💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💕 አማላጅነት አይለየን !!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የልደት ፆም መች ነው ሚጀመረው ?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም በእመቤታችን  በድንግል ማርያም  ስም በአክብሮት እንጠይቃለን ተሰውረው የሚኖሩ አባቶች እንዲሕ ብለዋል የመጨረሻ ዘመን ስለሆነ ዛሬ እንጠራ ነገ እንጠራ ስለማናዉቅ ንሰሀ ግቡና ታጥባችሁ ጠብቁኝ ብለዋል።ቢያንስ (ለ10ሰው) አስተላልፉ  ሳታስተላልፉ ብትቀሩ በድንግል ማርያም ስም የተወገዛችሁ(የተረገማችሁ ) ሁኑ?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 13/2017 #አምላካችን_እግዚአብሔር_አብ
#አእላፋት_መላእክት
#መልአኩ_ቅዱስ_ሩፋኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ኅዳር 13 በዚህች ቀን #የአእላፋት_መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ #ለዓለሙ_ሁሉ_የሚማልዱ ናቸው እንኳን ለአመታዊ ክብረ በአላቸው አደረሰን

👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ

👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም_መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ

👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ #ረቂቃን_መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ

👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው ሁለተኛም #የእግዚአብሔር_ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ

👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስኪዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉር እንደ ብዝት ነጭ ነው ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል #የእልፍ_እልፍ_መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መፃሕፍትን ገለጠ

👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ #የሰማይ_ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ #ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ

👉ማቴዎስም እነሆ መላእክትም ሊያገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ #ቅዱሳን_መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል

👉ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም_መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው

👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ #ቅዱሳን_መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ

👉የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓርጋቸውን ደረጃ እንዲህ ብለው ተናገሩ #መላእክት_አጋዕዝት ሥልጣናት #ኃይላት_መናብርት መኳንንት ሊቃናት #ኪሩቤል_ሱራፌል ብለው ተናገሩ

👉 #የእልፍ_አእላፋት_መላእክት ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የሚዉለዉ የጦቢትን አይን ያበራ ተራዳኢዉ መልአክ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃዉ ተራዳኢነቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ጊዜዉ ያላችሁ የበአሉ መታሠቢያ #በደብረ_ሲና_ቅዱስ
#እግዚአብሔር_አብ ቤተክርስቲያን አዲሱ ገበያ በድምቀት ይከበራል የበረከቱ ተሣታፊ ሁኑ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ጻዲቁ ንጉሥ በእደ ማርያም ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣ በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን በእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡›› የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የጠበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን እንችላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናቸዋል፡፡ እነሆ ይህ ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ነገር ግን ወደቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300 የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
ከገድላት አንደበት

Читать полностью…
Subscribe to a channel