❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን ለአንዱ ለሆኑት በጸሎት ጊዜ የእጆቻቸው ጣቶች እንደ መብራት ያበራ ለነበሩት በአክሱም ከተማ አካባቢ የሚገኘውን ደብረ ቊንጽል ገዳም ለመሰረቱት #ለአባ_ሊቃኖስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሊቃኖስ፦ ቊጥራቸው ከዘጠኙ ቅዱሳን ሲኾን የመጡት ከቊስጥንጥንያ (ሮም) አገር ሲኾን በአክሱም ከተማ አካባቢ ደብረ ቊናጽል የሚል ገዳምን ገድመዋል፤ በዓለ ዕረፍታቸውም ኅዳር 28 ቀን ነው፤ በጸሎት እጃቸውን በዘረጉ ጊዜ ዐሥሩ ጣቶቻቸው እንደ መብራት ይበራ እንደነበር ዜና ገድላቸው ያስረዳል። ምንጭ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው።
ፍጹም ከእውነት የራቀ ውሸት ነው ከፈለጋችሁ ሙሉውን ከስር Show የሚለውን በመንካት ማረጋገጥ ትችላላችሁ
ሙሉ ታሪኩን ለማየት show የሚለውን ንኩት👇
SHOW
ሲሳየነ ዘለለእለትነ
የ ዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ እንላለን
የ ዕለት እንጀራ በ 7ት በ 8ት በአንደምታ ይፈታል
✅ አንዱ ትርጉሙ
በየቀኑ ፍትህ አታሳጣን ማለት ነው
እግዚአብሔር የሰጠን ይሄን ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር የሚመሰገነው ምስጋና
ቤተክርስቲያን ምታቀርበው ምስጋና
እኛ ተለይተን ከምንፀልየው ምስጋና ይበልጣልና
ስጣዌ ስጣዌያት እኛ ጠይቀን ከምናገኘው መልስ
ቤተክርስቲያን የምትጠይቅልን ጥያቄ ይበልጣል
አይን ብቻየን ሁኜ አሁን እንደው ቢመካ ማለት ነው
እኔ እኮ አይን ነኝ በአካላት ላይ ቢመካ ቅ.ጳውሎስ ፅፎታል
✅ እኔ አይን
ባላይልህ እኮ እግርም እጅም ጅብ በልቶህ ነበርኮ
ምትሮጠው እኮ እኔ ጅብ መኖሩን አይቸልህ እኮ ነው
✅ ጆሮም ደግሞ
አይ እኔ ሲጮህ ባልሰማው ምን ታውቅ ነበር ቢል ደግሞ
✅ እግር ደግሞ
አይ እኔ ባሮጥ አንተስ ምን ቁም ነገር አለህ ቢል
ሁሉም ተያይዞ መጥፋት
✅ እራስስ ቢሆን
እኔ እኮ ነኝ እግርን ማስተዳድረው እኔ ነኝ
መመርያ ምሰጥ እኔ ነኝ ያለራስ ምንቁም ነገር አላችሁ ቢል
እስቲ ተቆረጥና ህይወት ሲኖርህ እናያለን ቢሉት
ህይወት ይኖረዋል ?
✅ ዝም ብሎ
ከብለል ከብለል ሲል አንድ መርግ ጨፍልቆ ይጥለዋል ማለት ነው
ዱባ ማለት እኮ ነው እራስ ከህዋሳት ከተለየ
አዕምሮ ይጠፋል
አዕምሮ ከነዚህ ተለይቶ ከተቆረጠ ይጠፋል።
አንድ የአንገት ደምስር ቢቆረጥ አዕምሮ ዋጋ የለውም።
✅ ስለዚህ ምንድን ነው ?
ቤተክርስቲያን ህብረታዊት ተዋህዳዊት ናት
✅ ቤተክርስቲያን
በክርስቶስ እራስነት ዓለምን ሰብሰባ የምትይዝ ናት።
ሰላምም ፍቅርም አንድነትም ከቤተክርስቲያንም በላይ ምንጭም የለም በእውነቱ ማለት ነው ።
ሰላም ማለት እኮ የሁከት አለመኖር ነው
ሰላምን ሚሰጥ ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
"ይኩን ሰላም በኃይልከ" ይላል ቅዱስ ዳዊት።
ሰላም የሚመጣው በኃይለ እግዚአብሔር ነው
✅ ስለዚህ ከዚች ቤተክርስቲያን
ጠላቶቻችሁን ውደዱ
የሚረግሟችሁን መርቁ ከምትል ቤተክርስቲያን በላይ
ሰላምን የምታስተምር ማን ሊገኝ ይችላል።
ምን አይነት አስተምህሮስ ይገኛል።
✅ እናስ ቤተክርስቲያን
ከኪዳን ከቅዳሴ እየቀረን
ብቻችንን እያነበነብን
በዓመት አንድ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እየመጣን
ነው ኢትዮጵያ ሰላም ምትሆነው ?
ሰላሙን ፍቅሩን መድኃኔዓለም ያድለን አሜን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን❣️
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ድኽነት ትልቅ ሀብት ነው" የሚለው ስንፍናን እያስተማረ አይደለለም፡፡ “በጥበብ ለያዙት ሰዎች" ነው፡፡
ይህንን ከአላዛርና እና ከነዌ ልንረዳው እንችላለን፡፡
✅ አልዓዛር
የተመሰገነውና በአብርሃም ዕቅፍ የተቀመጠው
ነዳይ፣ ሕመምተኛና እጅግ ስቃይ ስለነበረበት ሳይኾን
በእነዚህ ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን ባለማማረሩና በመታገሡ ነው፡፡
ባለጸግነትም እንዲሁ በደፈና መጥፎ ነው አንለውም ፣
ሊቁም እያለ ያለው እንደዚህ አይደለም ።
✅ እንደ አብርሃም እንደ ኢዮብ
በጥበብ ከተጠቀሙበት ባለፀጋነት አይጎዳም ።
ድኽነትም
✅ እንደ አልዓዛር ከተጠቀሙበት አይጎዳም፡፡
ድኻ መኾን ግን የመንግሥተ ሰማያት ዋስትና አይደለም፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከት አይለየን❣️
በዚህ አለም ላይ
ተወዳጆች ሆይ
የእመቤታችን ፍቅር
እንደውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው።
አባ ጊዮርጊስ ለዚህ ነው
ፍቅርሽ እንደ ወይን እና እንደ ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሄ ወይን ነው ይሄ ውሃ ነው ማለት አይቻልም
እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም
እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን አለ
ምን ላድርግ ?
ፀጉሬ እንኳን አፍ አውጥቶ ቢዘምርልሽ አይበቃሽም ይላል
ስለዚህ ዝም ብየ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።
አምላክ እናቴ ያላትን እኔ እናቴ ላልላት ነው እንዴ
ፈጣሪ እናቴ ካላት እኔማ ሎሌሽ ነኝ ብላት
ኧረ! እናትም የሆነችን በቸርነቷ ነው
አንደኛ
የእግዚአብሔር ቸርነት ይገርማል
የእሱን እናት እኛም እናታችን ስንል
ለነገሩ ፈጣሪ ቅናት የለበት አይደል
እንጂማ የአምላክን እናት
እናቴ ማለትኮ እራሱ ትዕቢት እኮ ነው
ትዕቢት ነው አዛኘን
ሁለተኛ ደግሞ
የሷም ደግነት
እኔ አንተን ልጄ ባልኩበት
ዘማያውያንን ሁሉ ልጄ አልልም አለማለቷ
የረከሱት ሁሉ እናቴ ማርያም አይሉኝም
እንዳይሉኝ ከልክላቸው አለማለቷ
የምድር ንግስት ብትሆን እኮ
ዞርበል ያንተ እናት አይደለሁም ትለን ነበር።
እሷ ግን
ቸር እናት ስለሆነች
የመሀሪው እናት ፣ እርህርሂት ማርያም
የውሻ ያዘነች ስለሆነች እናታችን ስንላት አናፍርም
እናትነቷ ሲበዛብን እንጂ
የፈጣሪን እናት እናት እንድትሆነን የፈቀደልን እግዚአብሔር
ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን 🙏
ህዳር 26/2017 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል
👉የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 25-የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡
አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡
ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡
እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡
ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው የሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ተአምር ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ ኢስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የመሐመድን መቃብር ለመሳለም በሔደው ኢስላም ላይ ያሳየው ታላቅ ተአምር ነው፡፡
ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይድርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ከገድላት ከንደበት
ህዳር 24/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት #ለአባታችን_ለአቡነ_ተክለሃይማኖት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አባታችን #አቡነ_ተክለሀይማኖት በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም አስር 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡
👉በሕዳር 24 ቀን #ቅዱስ_ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው አወጣቸው #ከሐያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ ጋር ሐያ አምስተኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን #አሐዱ_አብ_ቅዱስ #አሐዱ_ወልድ_ቅዱስ #አሐዱ_ውእቱ_መንፈስ_ቅዱስ በማለት አጥነዋል
👉በሐይቅ 10 ዓመት በደብረ ዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል አባታችን #አቡነ_ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡
👉ለ22 ዓመት ቆመው #በመፀለያቸዉ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡
👉በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን አረፉ አባታችን ባረፉ በ54 ዓመታቸው ለአባታችን ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልፀው አፅማቸው #ከደብረ_አስቦ ወደ #ደብረ_ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡
👉ለሃይማኖታችን መፅኛ ለሀገራችን አፅር ቅፅር የአባታችን #ፀሎት ኃይል ይሁነን ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን "አሜን"
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እንኳን በሰላም በያላችሁበት ቦታ ለታላቁ አባታችን #ለአቡነ_ተክለ_ሐይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረስን ከሃያ አራቱ ካህናተ ስማይ ጋር አባታችን #የሥላሴን_መንበር ያጠኑበት ያመስገኑበት ቀን የበረከትና የረድኤት ቀን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ታቦትን ከጣዖት አጠገብ የማስቀመጥ “ፍልስጤማዊ አባዜ” ያለበት ሰው ግን ይህን ለመረዳት ይቸገራል:: "ዳጎንም እንጨት ታቦተ ጽዮንም እንጨት" ይልሃል:: ሁለቱም እንጨት ነው ነገር ግን ታቦተ ጽዮን እግዚአብሔር ያደረባት ስትሆን ዳጎን ሰይጣን የሰፈረበት ነው:: "የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና" መዝ. 96:5
ሙሴ የያዘውን በትር የግብፅ ጠንቋዮች ይዘውት ነበር::ሁለቱም እባብ ሆነ ልዩነቱን ግን የሙሴ በትር የአስማተኞቹን ዕባብ ውጣ አሳየች:: "ያም በትር ነው ይሄም በትር ነው" ካልከኝ ፈርዖን ይታዘብሃል:: ጌታ የለበሰውም ቀሚስ ነው ፤ ሕዝቡ የለበሱትም ቀሚስ ነው:: በሕዝብ መካከል እንደ እባብ እየተሳበች በብዙ ቀሚሶች እየተዳሰሰች መጥታ የመሲሑን ቀሚስ ስትነካ ደምዋ ቀጥ ላለላት ሴት "ቀሚስ ቀሚስ ነው" በላትና ትመልስልህ::
አዎ ዳጎንም ታቦተ ጽዮንም የተቀረጸ ምስል ናቸው:: ነገር ግን ታቦት የእግዚአብሔር ዙፋን ሲሆን ጣዖት ግን በእሳታዊ ዙፋኑ ፊት እንድ ማገዶ የሚሰባበር እንጨት ነው፡፡ ታቦትን ከጣዖት ጋር ከመመደብ ይሠውረን:: አንድም ታቦት ሰውነታችንን ከዳጎን ኃጢአት ጋር ከማስቀመጥ ይሠውረን::
‘ብርሃን ከጨለማ ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው’ 2ቆሮ. 6፡14-16
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 21 2017 ዓ.ም.
ህዳር 23/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉ታላቁ ሰማዕት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አባቱ የፍልስጤም መኮንን ዞሮንቶስ (እንስጣቴዎስ) እናቱ ደግሞ (አቅሌሲያ) ቴዎብስታ ትባላለች በፍልስጤም ልዳ ጥር 20 በ277 ዓ.ም ተወለደ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሀረገ ወይን ፀሐይ ዘልዳ ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ጊዮርጊሰ በፋርስ በኢራን ዱድያኖስ የተባለ ንጉሥ ነገስታቱን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታትን ሲያሰግድ ተመለከተ በዚህን ጊዜም ቤተ መንግስት ድረስ በመገስገሰሰ ተቃውሞውን በማሰማት ክርስቲያን መሆኑን መስክሯል ከዚህም በኋላ በተለያዩ ነገስታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰው ህሊና ሊታሰቡ የማይቻላቸው አስራ ዘጠኝ መከራዎች ደርሰውበታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ጊዜ ሞቶ ሶስት ጊዜ ተነስቷል #የእግዚአብሔር ተአምር በተደጋጋሚ ተገልፆለታል
👉 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ መከራ በጥቂቱ ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ እጆቹንና እግሮቹን ታስሮ ተገረፈ የብረት ጫማ አጥልቀው አስኬዱት ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው እሳት አነደዱበት እጆቹን የኋሊት አሰሩት በመጋዝ ለሁለት ሰነጠቁት የጋለ ሳህን ከጭንቅላቱ ላይ አስቀመጡበት ሰውነቱን በጩቤ ፈተፈቱት ችቦ እና እሳት አንድደው በግራና በቀኝ አቃጠሉት
👉ምላሱን በቢላዋ ቆረጡት በአፍንጫው ቀዳዳዎች በሚስማር መተው ቸነከሩት በመጥረቢያ ፈለጡት ቅጥራን አፍልተው በጭንቅላቱ ላይ ደፉበት በበሬ አስረው ጎተቱት ጥርሶቹን በጉጥ አስረው ነቃቀሉት ከብረት ድስት ውስጥ ጨምረው ቀቀሉት አስጎንብሰው አሸዋ ጫኑበት ከእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት አጋዩት በወፍጮ ፈጩት
👉#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሲል በሰይፍ ተቀልቶ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ወደ እቶን እሳት ተወርውሮ ለአእምሮ በሚከብድ መልኩ ብዙ መከራን ተቀብሎ በ 27 አመቱ ሚያዚያ 23 ቀን መከራን ተቀብሎ በሰማዕትነት አርፏል
👉እግዚአብሔር ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በተጋድሎ ያፀናል አምላክ እኛንም #በሀይማኖት_በምግባር እንድንፀና መልካም ፈቃዱ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ህዳር 22/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ዑራኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው
👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ ዕዝ ሱቱኤል.13፥39
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው ድርሳነ ዑራኤል ገፅ.26፥ምዕ 4
👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
መምህር ዘመድኩን ለአህዋዝ ልክ ልኩን ነገረው
የዘማሪ አህዋዝ ሚስጥር
እንደምታውቁት ከቀናት በፊት ዘማሪ አዕዋዝ ከነበረበት የተሐድሶ እንቅስቃሴ ወደ ኦርቶዶክስነት መመለሱን ሰምተናል ለዚህም ብዙ ምክኒያቶች እየተነገሩ ይገኛል ዛሬ በወጣው አንድ መረጃ ግን ዘማሪው በተገኘበት ሚስጥራዊው ቪዲዮ ቅጂ መሆኑ ታውቋል
ኦርቶዶክሶችም ፕሮቴስታንቶችም በማይሆን ነገር ጫፍ ለጫፍ ቁጭ ብላችሁ ከምትተራረቡ እውነታውን ከታች ያለውን Play የሚለውን በመንካት ሙሉ ሚስጥራዊውን ቪዲዮ አይታችሁ እውነታውን ፍረዱ
Play የሚለውን ንኩት👇
Play
ህዳር 21/2017 #እናታችን_ፅዮን_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን #ለእናታችን_ማርያም_ፅዮን አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ፅዮን ማለት " አምባ፤መጠጊያ" ማለት ነው አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው ፅዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ፅላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።
👉 #እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን #በቅዱስ_ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል ዘጸ.31፥18 ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።
👉ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ #መስቀሉንና ታቦተ #ፅዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።
👉ያም ሆኖ #ታቦተ_ፅዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን ግን አንጨነቅም ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ #እግዚአብሔር ነውና እንፀልያለን እንጂ አንጨነቅም በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።
👉 #ታቦተ_ፅዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ፅሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል ስምምነት" ነው።
👉 #ታቦት ማለት "ማሕደር ማደሪያ" እንደ ማለት ነው ሕጉ የተፃፈባቸውን ሰሌዳው "ፅላት" ስንላቸው #የፅላቱ_ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል ፅላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን 2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19
👉በመጨረሻም #ኅዳር_ሃያ_አንድ ቀን ፅዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።
👉 በዚህች ቀን #ታቦተ_ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።
👉 #ታቦተ_ፅዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ #የአህዛብን_ጣኦት_አድቅቃ_በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።
👉በዘመነ ልበ አምላክ #ቅዱስ_ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ታላቁ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ አገለገለ ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ #ለእግዚአብሔር ማደሪያ #ለታቦተ_ፅዮን የተቀኘላትን በማሰብ።
👉ታቦተ #ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት #ቤተ_መቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ
👉የቀደሙ ነብያት ስለ #እመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ
👉ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን #አዛሪያስንና_ታቦተ_ፅዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ
👉በዘመነ አፄ ባዜን በ4 ክ/ዘመን አካባቢ አማናዊት ፅዮን #ድንግል_ማርያም ወደ አክሱም ፅዮን በስደት መጥታ ገብታለች በዚህ ጊዜም 2ቱ ፅዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ
👉 #በአብርሃ_ወአፅብሐ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ
👉አብርሃ ወአፅብሐ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል #ቤተ_መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ
👉በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል #ታቦተ_ፅዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ
👉በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት #አክሱም_ፅዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።
👉እናታችን #ታቦተ_ፅዮን_ማርያም የቃል ኪዳን ሀገርሽን ኢትዮጵያን በሠላም በፍቅር ጠብቀሽ ለአመቱ በአንድ ልብ ሆነን የቀድሞ ሠላማችን ተመልሶ በደጅሽ ተሰብስበን ለማክበር አብቂን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ህዳር 27/2017 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ
👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት
👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር
👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን ሲሰቀል በመሰቀሉ የተገኙት እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ተወዳጆች ሆይ
✅ ስድብን በሚመለከት
በፍትሐ ብሔር ሕጋችን ልቡና ግምት ውስጥ የማይገባ ሲኾን
በወንጀል ሕጋችን ደግሞ የተሰዳቢው ልቡና/ ሐሳብ ወሳኝ ነው፡፡
✅ ስድብን መናቅ ማለት
ለምሳሌ አንድ ሰው “አንተ አህያ” ቢለን
“እኔ'ማ አህያ ለመባል አልበቃም።
ምክንያቱም አህያ ታዛዥ ነው፡፡
ባለቤቱን ያገለግላል፡፡
እኔ ግን አምላኬን አልታዘዝም፧ አላገለግልምም"
ብለን ከመለስንለት ስድብ መኾኑ ይቀራል፡፡
✅ “አንተ ውሻ ቢለንም “
እኔ'ማ ውሻን አላክልም፡፡
ውሻ ለጌታው ታማኝ ነውና፡፡
ቢደበድቡትም ቂም ይዞ አያማርርምና'' ካልን
ስድብ ስድብ መኾኑ ይቀራል፡፡
ሌሎች ነገሮችንም እንደዚህ በጥበብ ከያዝናቸው
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለን አይጎዱንም፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከት አማላጅነት አይለየን🙏
ህዳር 26/2017 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል
👉የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ፍጹም ከእውነት የራቀ ውሸት ነው ከፈለጋችሁ ሙሉውን ከስር Show የሚለውን በመንካት ማረጋገጥ ትችላላችሁ
ሙሉ ታሪኩን ለማየት show የሚለውን ንኩት👇
SHOW
ህዳር 24/2017 #ሀያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ኅዳር ሃያ አራት #በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ #ካህናተ_ሰማይ አመታዊ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው
👉እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት #ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም #ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋር እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ፀሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለ እነርሱም አቅራቢነት ፅድቅና ምፅዋት ወደ #እግዚአብሔር አይቀርብም
👉ወንጌላዊ #ቅዱስ_ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም #ሃያ_አራት_አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ።
👉ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ፅንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ፀሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት የዕጣኑም ጢስ #ከቅዱሳኑ ፀሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ #እግዚአብሔር ፊት ዐረገ ።
👉የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ
👉እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን #ኃይልና_ምስጋና_ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና
👉እነርሱ #በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና #ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ
👉በጌታ ዙፋን ፊት ለምስጋና የሚተጉ #24ቱ_ሽማግሌዎች #ካህናተ_ሰማይ የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ጊዜዉ ያላችሁ በአሉን ለማክበር የምትፈልጉ የተዋህዶ ልጆች በእንጦጦ ደብረ ኃይል #ቅዱስ_ራጉኤል ወ #ቅዱስ_ኤልያስ ቤተክርስቲያን #የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ የንግስ በአል በታላቅ ድምቀት ይከበራል በቦታዉ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሣታፊ ሁኑ
👉 #24ቱ_ካህናተ_ሰማይ ስማቸዉ እነማን ይባላሉ
1 አካኤል 2 ፋኑኤል 3 ጋኑኤል 4 ታድኤል 5 አፍድኤል
6 ዘራኤል 7 ኤልኤል 8 ተዳኤል 9 ዮካኤል 10 ገርድኤል
11 ልፍድኤል 12 መርዋኤል 13 ኑራኤል 14 ክስልቱኤል
15 ኡራኤል 16 ባቱኤል 17 ሩአኤል 18 ሰላትኤል
19 ጣርኤል 20 እምኑኤል 21ፔላልኤል 22 ታልዲኤል
23 ፐሰልዲኤል 24 አሌቲኤል
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ኩክየለሽ ማርያም ገዳም
መነሻ ቀን :-ታህሳስ 6(እሁድ)
የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ ኩክየለሽ ማርያም
መነሻ ቦታ:-አስኮ ገብርኤል/መገናኛ/ጣፎ አደባባይ
በእለቱ የ ፀበል መጠመቅ የፀሎት ፕሮግራም የተለያዩ ሰባኪ መምርሀን ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ ።
ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 600 ብር ብቻ።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
ስልክ 09-91-11-96-29
09-25-49-26-34 ይደውሉልን
ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር🙏🙏
06 ወደ ኩክ የለሽ ማርያም
📲📲📲📲📲📲📲📲
+ ታቦትን ከጣዖት ጋር አታስቀምጡ +
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው ፦ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም››(ዘጸ. 20፡4)
ይህንን ትእዛዝ በእሳት ቀለም የጻፈበት ድንጋይ ሳይደርቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ሌላ ትእዛዝ አዘዘው ፦ ‘ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ’ (ዘጸ. 25፡18) እግዚአብሔር ለሙሴ ምን እያለው ነው? ‘የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ’ ካለው መልሶ የሁለት ኪሩቤል ‘የተቀረጸ ምስል ማሠራቱ ለምንድን ነው?’ መርቅያን የተባለው ጸረ ብሉይ ኪዳን የነበረ ውጉዝ ይህንን ተቃርኖ በመጥቀስ የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔርን ክብር ይግባውና ‘በሃሳቡ እንደሚወላውል’ አድርጎ ሐሰትን ተናግሯል፡፡ እውን እግዚአብሔር ‘የተቀረጸ ምስል አታድርግ’ ያለውን የራሱን ቃል ‘ታቦት ሥራ ፣ ኪሩቤልን ቅረጽ’ ሲል እየጣሰው ይሆን?
ታሪኩ በዚህ አላበቃም ፤ እስራኤላውያን ‘የወርቅ ጥጃ ምስል’ ሰርተው ሲያመልኩ እግዚአብሔር አይቶ ቁጣው ነደደ ፤ ቀሠፋቸውም፡፡ (ዘጸ. 32፡4) ቆይቶ ደግሞ ‘እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው’ (ዘኁ. 21፡8) ነገሩ እንዴት ነው? ከወርቅ ጥጃ መሥራት ጥፋት ከሆነ ከነሐስ እባብ መሥራት እንዴት ልክ ሊሆን ይችላል?
ሳዊሮስ ዘገብሎን የእባቡን ምስል አስመልክቶ ሙሴን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ‘የተረገመ ሥዕል በመከራ ለተናወጠ ሕዝብ እንዴት ድኅነትን ሊያመጣ ይችላል? የተነደፋችሁ ሁላችሁ አንጋጥጣችሁ ወደ ሰማይ ወደ እግዝዚአብሔር ተመልከቱ ወይም ወደ መገናኛው ድንኳን ተመልከቱና ትድናላችሁ’ ቢል አይሻለውም ነበር? ከምድርም ፣ ከሰማይም የተቀረጸ ምስል አታድርግ ያለ ሙሴ ስለምን ይህንን አደረገ? እጅግ የታመንከው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ሆይ የከለከልከውን ነገር ራስህ እየሠራህ ነውን? ‘የተቀረጸ ነገር አታድርግ’ ያልህ አንተ ፣ የጥጃ ምስል የሰባበርህ አንተ የናስ እባብን እንዴት ሠራህ? ያውም በምሥጢር ሳይሆን በገሐድ ነበረ!’ (Severian Bishop of Gabala , Homily on the Serpent pg 56)
ነገሩ ወዲህ ነው ፤ በመጀመሪያ ወደ ማብራሪያው ሳንሔድ ‘የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ’ የሚለው ትእዛዝ ራሱ የተጻፈው በተቀረጸ ምስል ላይ መሆኑን በማስተዋል እንጀምር፡፡ ትእዛዛቱ የተጻፉት ከድንጋይ በተቀረጸ ጽላት ላይ ሲሆን የሚቀመጡት ደግሞ ከግራር እንጨት ተሠርቶ በወርቅ በተለበጠና ከወርቅ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ኪሩቤል ያሉበት ታቦት ውስጥ ነበር፡፡ ስለዚህ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ የሚለውን ቃል እያነበብን ያለነው ከተቀረጸ ምስል ውስጥ ባገኘው በተቀረጸ ሰሌዳ ላይ የመሆኑን ምፀት (irony) እንደ ዋዛ አናልፈውም፡፡ ቃሉ የተጻፈበት ፊደልም ቢሆን ሌላው በጣት የተቀረጸ ነገር መሆኑም የሚዘነጋ ነገር አይደለም፡፡
እግዚአብሔር ‘የተቀረጽ ምስል ለአንተ አታድርግ’ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ግን ብዙዎች ከምስሉ ጀምረው አነበቡት እንጂ ቃሉ የሚጀምረው ‘ከእኔ በቀር ሌላ አማልክት አይሁኑልህ’ በሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ‘ሌላ አምላክ አለ ብለህ አትመን ፤ ይህንን አምነህም የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ ፣ አትስገድላቸው አታምልካቸውም’ ብሎ ከጣዖት አምልኮ እንድንርቅ ያዘዘው ትእዛዝ ነው፡፡ በራሱ ፈቃድ እንዲሠሩ ያዘዛቸው ሁለቱ ኪሩቤልም ‘በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ’ (ይሣሉ ብሎ ያሣላቸው) ሲሆኑ አምላክ ናቸው ተብለው ሊመለኩ አይደለምና የላይኛው ትእዛዝ እነርሱን አይመለከትም፡፡ የናሱን እባብም ኃይሉን ሊገልጥበት ወድዶ አሠራው እንጂ ይመለክ ብሎ አላሠራውም፡፡ በኋላ ዘመን የናሱን እባብ እንደ አምላክ ቆጥረው ከሐውልቶች መካከል አቁመው ያመለኩትን ደግሞ ራሱ እንዲሰባበርባቸው አድርጓል፡፡ (2 ነገሥ. 18፡4)
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የተቀረጸ ምስል ሁሉ ጣዖት እንዳልሆነ ፤ በተመሳሳይ እንጨት ፣ በተመሳሳይ ወርቅ ቢሠራ እንኳን የተሠራበት ዓላማ እንደሚለየው ፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሠራ ታቦት እግዚአብሔርን ለመተካት ከተሠራ ጣዖት ጋር ልዩነት እንዳለው ነው፡፡
የታቦትንና የጣዖትን ልዩነት በተመለከተ የፍልስጤም ሰዎችን ያህል ግን እውቀት ያለው ያለ አይመስልም፡፡ ፍዳቸውን አይተው ታቦትን ከጣዖት የለዩ እነሱ ናቸው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ፦
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ብዙዎች በግንባራቸው ተደፍተው ስለመስገዳቸውተጽፎአል:: መስፍኑ ኢያሱ በእግዚአብሔር ታቦት ፊትሰግዶአል:: የእስራኤል ሽማግሌዎችም ሙሉ ቀን በታቦቱፊት ወድቀው ምሕረት ለምነዋል:: (ኢያ. 7:6) በታቦት ፊት ከሰገዱ ሁሉ ግን እጅግ በጣም የሚያስደንቀውከፍልስጤማውያን ዘንድ የታየው ሰጋጅ ብቻ ነው::
ዳጎን ይባላል:: ዳጎን ሰው አይደለም:: ደህና አናጢ እጅ የገባ የፍልስጤማውያን ዛፍ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ከእንጨት ጠርበው ያቆሙት ሰው ሠራሽ አምላክ ነው::አይሰማም አይለማም:: አይበላም አይጠጣም::። ለክብሩ መቅደስ ተሠርቶለት ሰዎች በስሙ እየተሰየሙለት (አብደናጎ ገብረ ዳጎን ማለት ነው እንዲል) ይኖራል::
ዳጎን ተንቀሳቅሶ ባያውቅም ታቦተ ጽዮን ተማርካ አጠገቡ ስትመጣ ግን ተንቀሳቀሰ:: ፍልስጤማውያን ዳጎንን ከታቦተ ጽዮን ጋር እኩል አድርገው አስቀመጡት::በማግሥቱ ሲመጡ ግን ሌላ ነገር ጠበቃቸው:: ‘እነሆም፥ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር ፤ ዳጎንንም አንሥተው ወደ ስፍራው መለሱት" 1ኛ ሳሙ.5:3
አይሰሜ አይለሜው ዳጎን በታሪኩ ቁምነገር ሠርቶ አያውቅም ነበር:: በታቦተ ጽዮን ፊት ሰግዶ ማደሩ ግን ብቸኛው ቁምነገሩ ነው:: ታቦትን ከጣዖት እኩል አድርገው ለሚያስቡ እና ጎን ለጎን ላስቀመጡት የአዛጦን ሰዎች"የእግዚአብሔር ታቦት ይኼ ነው እኔ ግን ጣዖት ነኝ" ብሎበተግባር አሳያቸው:: ለእርሱ ሲሰግዱ ለነበሩት ሰዎች ስግደት የሚገባው በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንደሆነ ሰግዶ አሳያቸው:: በእውነት ዓይን እያለው የማያየው ፣ ጆሮ እያለውየማይሰማው ጣዖት እንኩዋን የገባው እውነት ከብዙዎች ተሰውሮ ታቦትን ጣዖት ሲሉ ማየት ያሳዝናል::
"ታቦትን ጣዖት ስትሉ እኛ እንደሰማን ፍልስጤማውያን እንዳይሰሙ፣ ዳጎን እንዳይሰማችሁ” ያሰኛል:: የአዛጦን መቅደስ ታቦት ገብቶበት እንኳን አልተቀደሰም:: የእግዚአብሔር ታቦት ደግሞ ጣዖት ቤት ገብቶ አልረከሰም:: ታቦት ቢማረክ ቢሸጥ ቢለወጥ ታቦትነቱን አያስቀረውም:: እግዚአብሔርም ኃይል የለውም አይባልም:: ልብ አድርጉ ይህ ሁሉ ታሪክ የሚሆነው የእንስሳ ደም ይረጭበት በነበረው በኦሪት ታቦት ላይ ነው::የክርስቶስ ደም የሚፈስስበት ሥጋው የሚፈተትበት አልፋና ኦሜጋ የሚል ስሙ የሚጻፍበት የሐዲስ ኪዳኑ የመሠዊያ ታቦትማ ምንኛ እጥፍ ክብር ይገባው ይሆን? ዳጎን ለዚያኛው ታቦት ከወደቀ ለዚህኛው የቁርባን ጠረጴዛ እንዴት ይሰባበር ይሆን?
ህዳር 22/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ዑራኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው
👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ ዕዝ ሱቱኤል.13፥39
👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው ድርሳነ ዑራኤል ገፅ.26፥ምዕ 4
👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
የአቡላ ጉድ እንደቀጠለ ነው ዛሬ ደግሞ ለአህዋዝ ጥብቅና ቆሟል ሙሉውን ከታች Play የሚለውን በመንካት ተመልከቱ
የዘማሪ አህዋዝ ሚስጥር
እንደምታውቁት ከቀናት በፊት ዘማሪ አዕዋዝ ከነበረበት የተሐድሶ እንቅስቃሴ ወደ ኦርቶዶክስነት መመለሱን ሰምተናል ለዚህም ብዙ ምክኒያቶች እየተነገሩ ይገኛል ዛሬ በወጣው አንድ መረጃ ግን ዘማሪው በተገኘበት ሚስጥራዊው ቪዲዮ ቅጂ መሆኑ ታውቋል
ኦርቶዶክሶችም ፕሮቴስታንቶችም በማይሆን ነገር ጫፍ ለጫፍ ቁጭ ብላችሁ ከምትተራረቡ እውነታውን ከታች ያለውን Play የሚለውን በመንካት ሙሉ ሚስጥራዊውን ቪዲዮ አይታችሁ እውነታውን ፍረዱ
Play የሚለውን ንኩት👇
Play
ድንግል ሆይ
የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውን ያስገኘ ሽልን ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ
ሕይወትንና ደኅንነትን የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች
የማይላመጥ ጽኑ ነው
ይኸውም ኃያል የሚሆን የአድማስ ደንጊያ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለሚጠጡ ሰዎች
ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትንም የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለማይጠጡ ሰዎች
የሚያሰክርና የሚያፍገመግም
የሚጥልና ኃጢአትን ስለሚያስተው ፈንታ
ኃጢአትን የሚጨምር ነው ።
አሁንም ላንተ ምስጋና ይገባሃል ።
ለመንግሥትህም ምስጋና ይገባል እያልን እናመስግነው
ከንጹሕ ዕጣን ጋራ ምስጋናን እናቀርብልሃለን ።
ቅዳሴ ማርያም❣️
ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት አንተ ከሀዲ እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ።
ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም ። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው።
ከዚያ በኋላም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩለት ስብጥ በሚባል በአባቱ አገርም በተሠራች ገዳም ሥጋውን አኖሩ ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ተደረጉ ታላቅ ፈውስም ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_አንያኖስ
ዳግመኛም በዚህችም ቀን ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ። እርሱም ለወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ነው።
የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸው እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስም ወደ እስክንድርያ አገር መጀመሪያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ አታኦስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ክርስቶስን አመሰገነው።
ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው።
ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን፣ መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ፣ ስለ ትንሣኤውና፣ ስለዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ።
የአንያኖስም ልቡ ብሩህ ሆኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸው ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።
ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምዕራብ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።
ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_እና_ሐምሌ)