kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል: ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ እና አቡነ ስነ ኢየሱስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአ+ሕ+ዛ+ብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አ+ሕ+ዛ+ብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አ+ሕ+ዛ+ብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)

††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ✝ †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ ነው:: ሊቅም: ጻድቅም: ጳጳስም: ገዳማዊም ነው:: ከሁሉም በላይ ግን ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን በተድላ ለምትጠቀምባቸው መጻሕፍት (ስንክሳር: ግጻዌ እና ሃይማኖተ አበው) መሠረትን የጣለ ቅዱስ ሰው ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ በትውልዱ ግብጻዊ ሲሆን ጊዜውም 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ሞልቶ የተረፋቸው ባለ ጠጐች ነበሩ:: እንደ ሕጉ ወጣት እስኪሆንና ራሱን እስኪችል ድረስ አሳደጉት::

ከዚያ ግን ድንገት አባቱና እናቱ ተከታትለው ዐረፉ:: ከቁጥር የበዛ ሃብትን የግሉ ያደረገው ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንደሚያደርግበት ጨነቀው:: አንድ ትልቅ ነገር ግን ከማይሆን ጐዳና ጠበቀው::

ወላጆቹ ሁሌም መዝገብን በሰማያት ያገኙ ዘንድ ለነዳያን ይራሩ ነበርና ይህንኑ ለመቀጠል ወሰነ:: መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ ነውና (ማቴ. 7:16) ወላጅ ለልጁ ማውረስ ያለበት ምድራዊ ሃብትን ሳይሆን በጐ ሕሊናን ነው:: ሳይሠሩ ያገኙት ሃብት ብዙዎችን አጥፍቷቸዋል::

ለዛም ይመስላል ዛሬ አንዳንዶቻችን በቤተሰቦቻችን ሃብት ከእኛ አልፈን ትውልዱን እየገደልንበት ያለው:: ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ንስሃ ካልገባን ይመጣብናል:: መቅረዛችን (ሕይወታችንም) ከእኛ ላይ ይወስዳል::

ፍርድ የሚሆነው በክፉው ትውልድ ላይ ብቻ አይደለም:: ይህንን ትውልድ በፈጠርነውና መልካሙን መንገድ ባልመራነው በሁላችንም ላይ እንጂ:: (ራዕ. 2:5)

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ዮሐንስ በወላጆቹ ሃብት የእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶችን አንጾ ነዳያንን ይንከባከብ ገባ:: ሙሉውን ቀን ለነዳያን ሲራራ ይውላል:: አመሻሽ ላይ እንግዶችን ተቀብሎ: አብልቶ ያሳርፋል::

ከዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል:: በእንዲህ ያለ ሕይወት ዘመናትን ካሳለፈ በኋላ አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤቱ መጣ:: አስተናግዶት ሲጨዋወቱ አደሩ:: ሌሊት ላይ ግን ስለ ምንኩስና ሕይወትና ስለ ክብሩ ነግሮት ነበርና ልቡ ተመሰጠ::

መነኮሱን ከሸኘው በኋላም ይመንን ዘንድ ቆረጠ:: ነዳያንን ሰብስቦ ሃብቱን አካፈላቸው:: ከዚያም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ የታላቁ አባ ዳንኤል ደቀ መዝሙር ሆነ:: በትሕትና ለአባቶች እየታዘዘ ከቆየ በኋላ በጭንቅ ደዌ ተያዘ:: ሰይጣን በቅንዓት ገርፎት ነበርና::

እርሱ ግን በደዌው ምክንያት ለዓመታት መሬት ላይ ወድቆ ቢቆይም ፈጣሪውን ፈጽሞ ያመሰግን ነበር:: እግዚአብሔር ደግሞ በፈውስና በኃይል አስነሳው::

በጊዜው የቡርልስ ጳጳስ ዐርፎ ነበርና አባት ፍለጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥተው ነበር:: መንፈስ ቅዱስ መርጦታልና አበው ቅዱስ ዮሐንስ ጳጳስ ይሆን ዘንድ አስገደዱት:: እርሱም የፈጣሪ ፈቃድ መሆኑን ስላወቀ ሔደ::

በዚያም (በሃገረ ቡርልስ) ታላቁን ገድል ተጋደለ:: ወደ ከተማዋ ሲገባ ብዙ ነገሮች ከሚገባው ሥርዓት የወጡ ነበሩ:: ብዙ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ይልቅ ባላስፈላጊ ነገሮች ላይ ተጠምዶ ነበርና መንጋውን ያድን ዘንድ ተጋ::

ሳይሆኑ "ባሕታዊ": "አጥማቂ" ነን እያሉ ሕዝቡን የሚያሳስቱ ተኩላዎችንም አስወገደ:: ለሕዝቡ አጉል ሕልም: ሟርትን የሚያስተምሩትን ገሠጸ:: አንመለስም ያሉ መ+ና+ፍ+ቃንን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው::

ቅዱስ ዮሐንስ ከቅድስናው ብዛት ዘወትር ሲቀድስ መድኃኒታችንንና አእላፍ መላእክትን ያይ ነበር:: ከከዊነ እሳት ማዕረግ በመድረሱም አካሉ በመፈተት ሰዓት እንደ እሳት ይነድ ነበር:: እንባውም እንደ ውኃ ይፈስ ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ጐን ዛሬም ድረስ የሚታወቅበትን ታላቅ ሥራም ሠርቷል:: መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ቅዱሱና የሃገረ አትሪብ ጳጳስ የነበረው ሊቁ አባ ሚካኤል መጽሐፈ ስንክሳርን : መጽሐፈ ግጻዌንና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጅተዋል::

"ስንክሳር" የቅዱሳንና የፈጣሪን ነገር በየዕለቱ የሚዘግብ መጽሐፍ ሲሆን "ግጻዌ" የየዕለቱን በዓላት ከምስባክና ምንባባት ጋር አስማምቶ የያዘ መጽሐፍ ነው:: "ሃይማኖተ አበው" ደግሞ የዶግማ መጽሐፍ ሆኖ ከሐዋርያት እስከ ሊቃውንት ድረስ የጻፉትን የያዘ ነው:: ሦስቱን የሚያመሳስላቸው "ስብስብ / እስትጉቡዕ / Collection" መሆናቸው ነው::

ቅዱሱ ዮሐንስ በሃገረ ቡርልስ በከፍተኛ ድካም ይህንን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† ✝አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ✝ †††

††† ጻድቁ በመካከለኛው (የብርሃን) ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያዊ::
*ከምድረ ሽዋ ወደ ታች አርማጭሆ የሔዱ መናኝ:
*ጭው ባለ በርሃ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን ያነጹ አባት:
*ብዙ አርድእትን ያፈሩ መናኝ:

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

𒈞𐄪☞እስመ ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ ወቅድመት ኮነ በመትከፍቱ ወይሰመይ ስሙ ዐቢየ ምክር ወመልእክ እስመ ኣመጽእ ሰላመ ለመላእክት ሕይወትሰ ዚአሁ༻▒
▒༺ “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”𐄪☜𒈞  — ኢሳይያስ 9፥6

꧁እንኳን ለአምላካች ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም በጤና አደረሳችሁ።꧂
              ┃ᬊ᭄𝕐𝕠𝕤𝕖𝕗_𝕋𝕒𝕣𝕚𝕜𝕦ᬊᬁ┃

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ ኦ! ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት::
ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ:: #ድንግል_ወለደቶ_ለገባሪሃ:: ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ . . . ✝✞✝

=>ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል!
~ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው::
~#ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው::
~#እርሱም_እናቱን_ፈጠረ:: ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ::
~ተዋርዶ በእኛ ባሕርይ ተወለደ::
~እርሱም እኛን ስለ መውደዱ ፈጠረን::

(ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ #ኤፍሬም_ሶርያዊ ቁ. 2)

<<< ከበረከተ ልደቱ ይክፈለን !! >>>

Dn Yordanos Abebe

ዝክረቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/ortdt?videochat=d44102be4991cba997

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ኹሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ _ _ አድርጉላቸው" (ማቴ.7፡12)፡፡

ይኸውም፡- “የሚያስፈልገው ብዙ ኃይለ ቃል፣ የሕግ ርዝማኔ፣ ወይም የተለያየ ዓይነት ትምህርት አይደለም፡፣

ወዳጄ

አንተው ራስህ ሕግ ኹን፡፡

ርኅራኄን መቀበል ትፈልጋለህን? ለሌላው ርኅሩኅ ኹን፡፡
ቸርነትን መቀበል ትፈልጋለህን? ለባልንጀራህ ቸርነትን አሳየው፡፡
ልትመሰገን ትወዳለህን? ሌላዉን አመስግን፡፡
እንድትወደድ ትፈልጋለህን? ፍቅርን አሳይ፡፡
የመጀመሪያ ቦታን ማግኘት ትወዳለህን? መጀመሪያ ያንን ሥፍራ ለሌላው ስጥ፡፡

አንተው ራስህ በራስህ ሕይወት ላይ ዳኛና ሕግ አውጪ ኹን፡፡

ዳግመኛም

“ለራስህ የምትጠላዉን ለማንም አታድርግ' (ጦቢ.4፡16)” ሲል ነው፡፡

ለራስህ” በማለት ሰውዬው ከክፋት እንዲርቅ አደረገው፤ “ለሌላው” በማለት ደግሞ በጎ ግብርን እንዲያሳይ አደረገው፡፡

ስለኾነም፡- “ለራስህ የምትጠላዉን ለማንም አታድርግ" አለ፡፡

“ስድብን ትጠላለህን? ሌላዉን አትሳደብ፡፡
ሲቀኑብህ ትጠላለህን? በሌላው ላይ አትቅና፡፡
መታለልን ትጠላለህን? ሌላዉን ሰው አታታልል፡፡


በአጭር አገላለጽ እነዚህን ኹለት ትእዛዛት ከጠበቅን ሌላ ትምህርትን አንፈልግም፡፡

ምክንያቱም በጎዉን የማወቅ ጸጋ በባሕርያችን ውስጥ አስቀምጧል፤ ይህን በጎ ነገር የማድረግና የመቅናት ፍላጎት ግን ለምርጫችን ትቶታል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Amen yemsgen esu new yemefilgwe

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

indemin ameshachu ye egzabere beteseboch

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እዴት አመሻችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አንድ ሰው እግዚአብሔርን ወደደ የሚባለው
እግዚአብሔር የሚጠለውን ነገር
ለእግዚአብሔር ብሎ የተወ እንደሆነ ነው ።


ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 25/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስን በምልጃ ፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሉ እንኳን አደረሰን

👉ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ #እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ፤ዉዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.7

👉 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈፀመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል #የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ ፕሉፓዴር ነው ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው በጥበብ በፈሪሀ #እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ

👉ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል መምለኬ ጣዖት ነበር በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ #እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና

👉አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አፅናንቶት ዘመቱ #መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን

👉ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ #መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል

👉ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት ዘኁልቁ.22፥28 #ለእግዚአብሔር የሚሣነዉ ነገረ ስለሌለ

👉 #የቅዱስ_መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን በምድረ ተጉለት በስሙ ከታነፀ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ ቀና ሲል እንደሚታይ ይነገራል የሰማዕቱ #የቅዱስ_መርቆሬዎስ ረድኤቱ በረከቱ አማላጅነቱ ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ ማቴ.10፥38-40

👉እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን የእምነታችንንም ራስና ፈፃሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ #በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና ዕብ.12፥1-2

👉የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ምልጃና ፀሎቱ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን በዚህ እለት የሚታወሱ ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸዉ ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 25/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30

አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን  ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን  ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።

የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን      ዋጋቸው

1 ኪሎ እጣን                         1300 ብር

2ኪሎ  ዘቢብ                          900 ብር

1ሙሉጧፍ                              1000ብር    
 
1ፓኮ ሻማ                                80 ብር

እነዚህን በመርዳት  ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ

አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት   በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ

ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 3000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን   ለመብል ለመጠጥ  ለሌሎች ነገር

ቅን ልብ ይኑረን

ማስቀደስ የምትፈልጉ አውሩን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

             ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን

             አቡነ ተክለሃይማኖት

❤️ እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። ✞✞✞🙏🏻


ይሄንን ይጫኑ
👇👇👇
@orthodox_tewahdo_mezmurs
@orthodox_tewahdo_mezmurs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 24/2017 #ፃድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት

"የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለአባታችን #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት አመታዊ የልደት ክብረ በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

👉በዚህች ቀን ታላቁ አባታችን ፃድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ፅላልሽ አዉራጃ ዞረሬ ነው የአባታቸው ስም ፀጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ #እግዚአብሔር ዘወትር ይፀልዩ ነበር መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

👉ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ፀጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚሐርያ ግን ተማርካ ሄደች በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ #ቅዱስ_ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ

👉 #እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ #ፀጋዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ ከሁለት ቀን በኋላ መጋቢት 24 ቀን #ተክለሃይማኖት ተፀነሱ

👉በዛሬዋ ቀን 1197 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር በተወለዱ በሶስተኛዉ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት #አሐዱ_አብ_ቅዱስ #አሐዱ_ወልድ_ቅዱስ #አሐዱ_ውእቱ_መንፈስ_ቅዱስ ብለው ሥላሴን አመሰገኑ ሁለተኛ ተአምር ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህፃን እያሉ ነው በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያም አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም #የቅዱስ_ሚካኤል ዝክሩ ታጎለብኝ ብላ እንጂ

👉ህፃኑ #ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ

👉ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ #የቅዱስ_ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

👉 #ተክለሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል በደብረ ሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለፀጎች ነን ከበዓሉ በረከት አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ያሳትፈን የፃድቁ #ተክለሃይማኖት ፀሎት ሐገራችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 24/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታኅሣሥ 23 ዕረፍቱ ለቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ::ጌታ ቅዱስ ዳዊትን እንደ ልቤ የሆነ፣ ፈቃዴን የሚፈጽም "ባሪያዬን፡ዳዊትን፡አገኘኹት፥ቅዱስ፡ዘይትም፡ቀባኹት" መዝ.88÷20

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/Orthodox_Mezmur_For_All/1824

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

☞ታኅሣሥ ፳፱

✝በዓለ ልደት ስቡሕ

✝በዓለ ማርያም ድንግል እግዝእትነ (እሙ ለእግዚአብሔር)

✞ወበዓለ ቅዱሳን፦

✿ዮሴፍ ወሰሎሜ
✿ኢያሱ ወልደ ነዌ
✿አቃርዮስ ዘሮሃ
✿ቆሪል ገመላዊ
✿አብርሐ ወአጽብሃ
✿ላሊበላ ጻድቅ
✿አብሳዲ ዘመጉና
✿ፍቅርተ ክርስቶስ ዘሲሐት
✿ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንኂሣ
✿ሰብአ ሰገል
✿ትጉኃን ኖሎት
✿ማኅበረ መላእክት
✿ዳዊት ወነቢያት
✿ቤተ ልሔም ዘይሁዳ
✿ሰማዕታተ አክሚም
✿ያዕቆብ ወፈሊስ ወቴዎድሮስ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/Xsj1t78uHx8?si=IMiwaZQozYyUsKre

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ማርያም ሳታገባ ፀነሰች
ማቴዎስ 1:18-25 ሉቃስ 1:56

    ማርያም የዮሴፍ ሚስት ሆነች
    ዮሴፍ፣ ማርያም ማርገዟን አወቀ

ማርያም ከፀነሰች አራተኛ ወሯን ይዛለች። በእርግዝናዋ የመጀመሪያ ወራት፣ በስተ ደቡብ በይሁዳ ኮረብቶች የምትገኘውን ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ሄዳ ነበር ። አሁን ግን ናዝሬት ወደሚገኘው ቤቷ ተመልሳለች። ብዙም ሳይቆይ የአካባቢዋ ሰዎች መፀነሷን ሊያውቁ ነው። ሁኔታው ማርያምን ምን ያህል እንደሚያስጨንቃት መገመት አያዳግትም!

ነገሩን ይበልጥ ከባድ የሚያደርገው ደግሞ ማርያም ለአናጺው ለዮሴፍ የታጨች መሆኗ ነው። አምላክ ለእስራኤላውያን በሰጠው ሕግ መሠረት ለአንድ ወንድ የታጨች ሴት ከሌላ ወንድ ጋር በፈቃደኝነት የፆታ ግንኙነት ከፈጸመች በድንጋይ ተወግራ እንደምትሞት ማርያም ታውቃለች። (ዘዳግም 22:23, 24) በመሆኑም ማርያም የሥነ ምግባር ብልግና ባትፈጽምም እንኳ ማርገዟን ለዮሴፍ እንዴት ብላ እንደምትገልጽለትና ከዚያ በኋላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳያሳስባት አይቀርም።

ማርያም ሦስት ወር ቆይታ ስለመጣች ዮሴፍ እሷን ለማየት እንደናፈቀ ጥርጥር የለውም። ሲገናኙ ማርያም ሁኔታውን እንደምትነግረው የታወቀ ነው፤ የፀነሰችው በአምላክ ቅዱስ መንፈስ አማካኝነት እንደሆነ ለማስረዳት የተቻላትን ማድረጓ አይቀርም። ሆኖም ዮሴፍ ይህን መረዳትና ማመን በጣም እንደሚከብደው መገመት ትችላለህ።

ማርያም፣ መልካም ስም ያላት ጥሩ ሴት እንደሆነች ዮሴፍ ያውቃል። ከዚህም በላይ በጣም ይወዳታል። ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ብትናገርም ዮሴፍ ከሌላ ሰው እንዳረገዘች ተሰምቶታል። ያም ሆኖ ዮሴፍ፣ ተወግራ እንድትሞት ወይም በሕዝብ ፊት እንድትዋረድ አልፈለገም፤ ስለዚህ በሚስጥር ሊፈታት ወሰነ። በዚያ ዘመን የተጫጩ ሰዎች እንደተጋቡ ይቆጠሩ ነበር፤ እነዚህ ሰዎች መለያየት ከፈለጉ መፋታት ነበረባቸው።
የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት

ዮሴፍ ጉዳዩን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆይቶ ተኛ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦  “ሚስትህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ እሷን ወደ ቤት ለመውሰድ አትፍራ። ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እሱንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና።”—ማቴዎስ 1:20, 21

ዮሴፍ ሲነቃ፣ ጉዳዩ ይበልጥ ግልጽ ስለሆነለት ምንኛ ተደስቶ ይሆን! ምንም ጊዜ ሳያጠፋ መልአኩ ያለውን አደረገ። ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት። በሕዝብ ፊት የተፈጸመው ይህ ድርጊት እንደ ጋብቻ ሥነ ሥርዓት የሚቆጠር ሲሆን ዮሴፍና ማርያም እንደተጋቡ የሚያሳይ ነው።

https://youtu.be/rsGUqMSJ-yg

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታኅሣሥ 27
አባ በግዑ ጻድቅ

=>እኒህ አባት በመካከለኛው ዘመን የሃገራችን ታሪክ ሰፊ ቦታን ይዘው ይገኛሉ:: ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በደብረ ሐይቅ ነው:: ጻድቁ ብዙ ጊዜ የሁዋለኛው ዘመን ሙሴ ጸሊም ይባላሉ:: ብዙ የሕወታቸው ጐዳና ተመሳሳይ ነው::

+ልክ ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ከኃጢአት ከሽፍትነት ሕይወት እንደ መጣው ሁሉ አባ በግዑም አስቸጋሪ ሰው እንደ ነበሩ ይነገርላቸዋል:: ከዚያ የከፋ የኃጢአት ኑሮ እግዚአብሔር ሲጠራቸው ግን ክሳደ ልቡናቸውን አላደነደኑም:: "እሺ" ብለው ንስሃ ገቡ እንጂ::

+ከዚያም በደብረ ሐይቅ (ወሎ) በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል:: ያዩ ሁሉም ፍጹም ያደንቁ ነበር:: ስትበላ: ስትጠጣ የኖረችውን ሰውነት ራሳቸውን ውሃ ለዘመናት በመከልከል ቀጥተዋታል:: ስለዚህም "ውሃ የማይጠጣው አባት" ይባሉም ነበር:: ጻድቁ ሲያርፉ ፈጣሪያቸው አክብሯቸዋል::

አምላከ አበው ቅዱሳን አሠረ ፍኖታቸውን ይግለጽልን::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/40xyg2LW-sU?si=SWC9pFEXVnEa38N1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Egizabehir yimesgin dehna ameshehe

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 26/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ሐብተ_ማርያም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሳን አባቶቻችን ወርሐዊ መታሰቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉አረጋዊዉ #ቅዱስ_ዮሴፍ በእርጅና ዘመኑ እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ለመጠበቅ የተመረጠና በመፅሐፍ ቅዱስም ፃድቅ ተብሎ የተመሠከረለት ነዉ ማቴ.1-19

👉ቅድስት #ድንግል_ማርያምን ለመጠበቅ የተመረጠዉም በ92 አመቱ ሲሆን ከ1985 አረጋዊያን መካከል በሦስት ምልክቶች የተመረጠ ነዉ

👉ማለትም በትሩ በአንድ ቀን አብባ የበለስን ፍሬ አፍርታና በበትሩ ላይ #ዮሴፍ_ሆይ_እጮኛህ_ማርያምን ጠብቅ የሚል ፅሑፍ በተአምር ተፅፎባት በመገኘቱ በትሩን ሲቀበል ነጭ እርግብ መጥታ በራሱ ላይ በማረፏና ሦስተኛውም በእጣ ነዉ

👉በቅዱስ መፅሐፍ እንደተፃፈው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በከብቶች በረት በቤተልሔም ሲወለድ #ከእናታችን_ማርያም ከቅድስት ሰሎሜ ጋር አብሮ ነበር አባታችን #ቅዱስ_ዮሴፍ እናታችን ማርያም ከልጇ ከወዳጇ #ከክርስቶስ ጋር ስትሰደድ አብሮ ነበር

👉አባታችን #ፃድቁ_ቅዱስ_ዮሴፍ ከዚህ አለም ድካም ያረፈው በ114 አመቱ ሲሆን ጌታችን የገነዘዉ ብቸኛም ፃድቅ ነዉ ከፃድቁ አባታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሰቢያው በዐሉ የምናስበው ፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም ረድኤት በረከቱ ለሁላችንም ይድረሰን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 26/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ሕፃን ሞዓ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

እስኪ ከጻድቁ አንድ ተአምር ለዛሬ እናስነብባችሁ

፪. ቃል ኪዳን በተቀበለበት በጥቅምት ሃያ አምስት ያደረገው ተአምር
   አባታችን አቡነ ሕፃን ሞዓ በተወለደበት አካባቢ የሚኖሩ ምዕመናን የአባታችንን የአቡነ ሕፃን ሞዓ ክብረ በዓል ጥቅምት ሃያ አምስት ለእኛ ለልጆቹ ቃል ኪዳን የተቀበለበትን በዓል አናክብር ብለው ከተወያዩ በኃላ ለዝክሩ የሚሆን መዋጮ በአንድ ሰው አንድ እንስራ ጠላ እና በቁጥር ሃያ እንጀራ እንዲያዋጡ  ተስማምተው ይለያያሉ፡፡ የአቡነ ሕፃን ሞዓ መታሠቢያ በዓል እለት ከአንድ ሰው በስተቀር  ቃል የገቡትን አንድ እንስራ ጠላ እና በቁጥር ሃያ እንጀራ ሲያዋጡ አንዱ ግን ቃል የገባውን ሳያመጣ ይቀራል፡፡ ያን ሰው አንተስ ለምን አላመጣህም? ይሉታል፡፡ እሱም እኔ አልሞላልኝም ይላቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ከባድ ጠብ ይነሳል፡፡ አባቶች ጩኸትና ጠቡን አይተው ከመሃል ገብተው ተውት አባታችን የስራውን ይሰጡት የለም  ብለው ሲያስሟሟቸው አባታችንን ዋሽቷልና አቡነ ሕፃን ሞዓ  ይፍረድ ብለው ከስምምነት ደርሰዋል፡፡ የአባታችን የአቡነ ሕፃን ሞዓ ታቦተ ሕጉ አቡነ ሕፃን ሞዓ ከበሬ ጋር ተጠምዶ ሦስት ትልም እጎተተበት መሬት ላይ ደርሶ ሲመለስ ቤተ ክርስቲያኑ አውደ ምህረት ላይ ዑደት ላይ እንዳለ ጥቅል አውሎ ንፋስ አባታችን አቡነ ሕፃን ሞዓ ከተነፈሰበት መሬት ተነስቶ በመውረድ የአባታችንን የአቡነ ሕፃን ሞዓን ዝክር ያስቀረውን ሰውዬ አምስት በግንብ የተሰራ የሳር ቤት እና በደጅ ያለ የእህል ፣ የገለባ ክምር በጥቅሉ ንፋስ ደምስሶበታል፡፡ ሰውዬውም በዚህ ምክንያት ከሀገሩ ወጥቶ ቀርቷል፡፡ የአባታችን የአቡነ ሕፃን ሞዓ በረከት ይደርብን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

☞ታኅሣሥ ፳፭

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿ጉባዔ ሐዋርያት ቡሩካን
✿፭ቱ መቃብያን
✿ዮሐንስ ከማ ካህን (ወብእሲቱ)
✿ሲኖዳ ጻድቅ (ረድአ ዮሐንስ ከማ)
✿ዮሐንስ ከማ ካልዕ (ኢትዮጵያዊ)
✿ኒቆላዎስ መኮንን (ወብእሲቱ)
✿ዳንኤል መነኮስ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔርን፡—
አንተ መታመኛዬ ነህ፡ እለዋለሁ፤
አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱም እታመናለሁ።

አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤
ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥
የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/Tewahedomender/69

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/pPhpoEvnMzw?si=-iNXomdVN0jGHh34

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/Tewahedomender/66

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

☞ታኅሣሥ ፳፫

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿ዳዊት ልበ አምላክ (ንጉሠ እስራኤል)
✿እሴይ ጻድቅ (አቡሁ)
✿አሳፍ ነቢይ (አርኩ)
✿ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
✿ሳሙኤል ዘአርምሞ
✿ይስሐቅ ግብጻዊ
✿አሞኒ ወአቦሊ
✿መቃርስ ወአይተለአትካ
✿ፊንጦስ ወመርቆሬዎስ
✿ሳሙኤል ወስምዖን ወገብርኤል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30

አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን  ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን  ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።

የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን      ዋጋቸው

1 ኪሎ እጣን                         600 ብር

2ኪሎ  ዘቢብ                          900 ብር

1ሙሉጧፍ                              1000ብር    
 
1ፓኮ ሻማ                                80 ብር

እነዚህን በመርዳት  ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ

አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት   በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ

ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 3000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን   ለመብል ለመጠጥ  ለሌሎች ነገር

ቅን ልብ ይኑረን

ማስቀደስ የምትፈልጉ አውሩን

Читать полностью…
Subscribe to a channel