kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1940

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰማዕታቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ-ሕመምተኞችን ያለዋጋ በነፃ ይፈውሱ የነበሩ ዶክተሮች!

እነዚኽም ሁለት ሰማዕታት ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው ሕመምተኞችን ያለዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ነበሩ። የእነዚህም ቅዱሳን እናታቸው ቅድስት ቴዎዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራ መጻተኞችንና ጦም አዳሪዎችን የምትረዳቸው ናት፡፡ አባታቸው ከሞተ በኋላም ብቻዋን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩታ ነው ያሳገቻቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው ሕመምተኞችን ያለዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ፡፡ የተቀሩት ሦስቱ ወንድሞቻቸው ግን ዓለምን ንቀው ወደ ገዳም ገብተው በመመንኮስ በጾም በጸሎት የሚጋደሉ ሆኑ፡፡

በእነዚህም ቅዱሳን ወንድማማቾች ዘመን አባ አጋግዮስ የተሰጣቸውን አደራ ባለመጠበቃቸው ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ መከራ መጣ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በዓለም ላይ ከ500 ሺህ በላይ ክርስቲያኖችን በግፍ ገድሎ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ክርስቲያኖች ደግሞ በእሥር ቤት አሠቃያቸው፡፡ ደገኛው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እስከነገሠ ድረስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዲዮቅልጥያኖስ አዋጅ ምክንያት እጅግ ብዙ የመከራና የሥቃይ ዘመናትን አሳልፋለቸ፡፡ ቅዱስ ቆዝሞስና ቅዱስ ድምያኖስም ይህ የዲዮቅልጥያኖስ አዋጅ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በታወጀ ጊዜ እነርሱ ግን የጌታችንን ወንጌል ያስተምሩ ነበር፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ
ቆዝሞስና ቅዱስ ድምያኖስ ወንጌልን እየሰበኩ ብዙዎችንም ክርስቲያን እያደረጓቸው መሆኑን በሰማ ጊዜ ጭፍሮቹን ልኮ አስመጣቸው፡፡ እርሱም እምነታቸውን በመረመራቸው ጊዜ
በክርስቶስ የሚያምኑ ክርስቲያን መሆናቸውን ነገሩት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ ብዙ እንዲያሠቃዩአቸው ለመኮንኑ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡

እርሱም ወስዶ በተለያዩ ማሠቃያዎች አሠቃያቸው፡፡ በእሳት አቃጠላቸው፤ ብዙ ግርፋትም ገረፋቸው ነገር ግን ጌታችን
መከራውን የሚታገሱበትን ኃይል ሰጣቸው፡፡ መኮንኑም ቅዱስ ቆዝሞስንና ቅዱስ ድምያኖስን ሌሎች ሦስት ወንድሞች እንዳሏቸው በሰማ ጊዜ እነርሱንም (አንቲቆስን፣ ዮንዲኖስን እና አብራንዮስን) አስመጥቶ አምስቱንም አንድ ላይ መንኮራኩር ውስጥ ጨምሮ አሠቃያቸው፡፡ ከሚነድ እቶን እሳት ውስጥ በጨመራቸው ጊዜ በውስጡ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆዩ፡፡ ከሦስት ቀንም በኋላ ያለምንም ጥፋት ጤነኞች ሆነው ወጡ፡፡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝቶ ከሥር እሳት አነደደባቸው ነገር ግን አሁንም ያለ ምንም ጥፋት ፍጹም ጤነኛ አደረጋቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች አመኑ፡፡

መኮንኑም እነዚህን አምስት ቅዱሳን ማሠቃየት በሰላቸው ጊዜ እነርሱም አልሞት ስላሉት መልሶ ወስዶ ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ሰጣቸው፡፡ ንጉሡም የተለያዩ ማሠቃያዎችን
በማፈራረቅ ብዙ አሠቃያቸው። እግዚአብሔርም ከመከራቸው ሁሉ ያድናቸው ነበር፡፡ እናታቸው ቅድስት ቴዎዳዳ ልጆቿን እስከመጨረሻው ተጋድለው የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀዳጁ ታበረታቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም እርሷ ሰማዕት ትሆን ዘንድ ተመኘች፡፡ ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶችንም እየረገመች ስትናገር ንጉሡ በታላቅ ቁጣ ሆኖ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጠውና የተመኘችው የሰማዕትነት አክሊልን ከልጆቿ ቀድማ አገኘች፡፡

የቅድስት ቴዎዳዳ ሥጋዋ በመሬት ላይ ወድቆ በቀረ ጊዜ ልጇ ቅዱስ ቆዝሞስ በሥቃይ ውስጥ ሆኖ ‹‹የዚህች አገር ሰዎች ሆይ! ይህችን ደካማ መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን›› ብሎ ጮኸ፡፡ በዚህም ጊዜ የንጉሡ የቅርብ አማካሪና ባለሥልጣን የነበረው የህርማኖስ ልጁ ቅዱስ ፊቅጦር ይህንን የቅዱስ ቆዝሞስን ቃል በሰማ ጊዜ ከመንግሥት ሰዎች መካከል ደፍሮ ሥጋዋን አንሥቶ ገንዞ ቀበራት፡፡ (ይህም ቅዱስ ፊቅጦር ስለ ክርስቶስ ፍቅር በኋላ በገዛ አባቱ እጅግ ተሰቃይቶ በ53 ችንካሮች ተቸንክሮ የሞተ እጅግ የከበረ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡)

ከዚኽም በኋላ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እነዚህን አምስት ቅዱሳን ወንድማማቾች ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ በትእዛዙም መሠረት አምስቱንም ቅዱሳን በ303 ዓ.ም በየተራ ሁሉንም አንገታቸውን ሰየፏቸውና የሰማዕትነት ፍጻሜአቸው ሆኖ የክብር አክሊልንም ተቀዳጁ፡፡ የቅዱስ ቆዝሞስ ማኅበርተኞች የሆኑ 262 ወንዶችና 49 ሴቶች በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡

የመከራውም ዘመን ሲያልፍ ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ፡፡ ከቅዱሳኑም ሥጋ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡

ኅዳር 22 ቀን እነዚህ አምስት ቅዱሳን ወንድማማቾች (ቆዝሞስ፣ ድምያኖስ፣ አንቲቆስ፣ ዮንዲኖስ እና አብራንዮስ ከእናታቸው ከቅድስት ቴዎዳዳ ጋር በሰማዕትነት ያረፉት ዕለት ነው! በዛሬዋም ዕለት በወርሃዊ በዓላቸው ስታስበው ይደውላሉ። የከበረች በረከታቸው ትደርብን! በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖✝ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ✝ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+✝

=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ
ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ
ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር
ደምሮ አስተምሮታል::

+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት
ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር::
ይሕ የተፈጸመ ገና
መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)

+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10
ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ
ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን
ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት
አምላኩን
አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ
መልዕክቱ
16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::

+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ
ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል
አብርተዋል:: እጅግ ብዙ
መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው
ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት
ቤቶችን አፍርሰው
አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::

+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን
ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን
አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር
ገንዞ ቀብሮታል::

+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+

=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ
የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::

+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር
የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ
ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ
ገስጾታል:: በዚህም
ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል::
እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት
ቀስፎታል::

❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ
ክብራቸውን ያድለን::

❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ

++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ:
ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

  + ከባቴ አበሳ +


👉 ግብፅ በረሀ አባ መቃርስ በሚኖሩበት ገዳም የሚኖር 1 መነኩሴ ነበር ያም መነኩሴ ሴቶችን ወደ ገዳሙ ያመጣ ነበር ይህን ተግባሩን ያዩ መነኮሳትም ወደ አባ መቃርስ በመሄድ ያደረገውን ነገር ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም ልጄማ ይሄንን አያደርግም ይላሉ ።

መነኮሳቱም ተበሳጭተው ይሄዳሉ ልጁም በሌላ ጊዜ ሴት ያስገባል እነዛ መነኮሳትም በድጋሚ ይሄዱ እና ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም አይ ልጄማ ይሄን አያደርግም ይላሉ በድጋሚ መነኮሳቱ ተበሳጭተው ይሄዱ እና ምን እናድርግ ? ብለው ይማከራሉ ከዛም በቃ ካሁን ቡሃላ ልክ ሴት ይዞ ሲመጣ እንነግራቸዋለን እስካሁን ያላመኑን እኛ ሴቶቹን ከሸኘ ቡሃላ ስለምንነግራቸው ነው በማለት ተማከሩ ። ያ መነኩሴም እንደ ለመደው ልክ ሌላ ሴት ይዞ ሲገባ መነኮሳቱ በሩጫ ሄደው ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም እንደ ተለመደው ልጄማ ይሄንን አያደርግም አሏቸው ።

መነኮሳቱም አባታችን ልጅቷ አልወጣችም ኑ ወደ ባዕቱ እንሂድ እዛው እንይዛቸዋለን ብለው ወደ ባዕቱ መሄድ ጀመሩ።

እየተቃረቡ ሲመጡ አባ መቃርስ ከሩቅ ሆነው ድምፅ (ሳል)  ያሰማሉ። መነኩሴውም ደንግጦ ልጅታን ቅርጫት ውስጥ ደበቃት።  ልክ እንደ ደረሱምና  ወደ ባዕቱ እንደገቡ አባ መቃርስ በመንፈስ ቅዱስ አውቀው ነበርና  ቅርጫቱ ላይ ተቀመጡ መነኮሳቱንም በሉ ገብታለች ያላቹኝን ሴት ፈልጋቹ አውጡልኝ አሏቸው ። መነኮሳቱ ቢፈልጉ ቢፈልጉ አጧት ወደ አባ መቃርስም ቀረብ ብለው አባታችን ይቅርታ እሱ ንፁህ ነው እኛ ነን ያጠፋነው አሉ አባ መቃርስም እኔኮ መጀመሪያም ነግሬያቹ ነበር ልጄ ንፁህ ነው በዚህም ያ  መነኩሴም ደስ አለው ። አባ መቃርስም በል ና ወደ በዓቴ ሸኘኝ ብለውት መንገድ ላይ ወግ ይጀምሩለት እና ምንኩስና እንዴት ነው ይሉታል እሱም ጥሩ ነው ይላቸዋል ።

እሳቸውም ያደረገውን ሁሉ እንደሚያውቁ እና ምን ማድረግም እንዳለበት መክረው ገስፀው ይልኩታል መነኩሴውም ልቡ ተነክቶ ከዛ ቡሃላ ታላቅ ተጋዳይ ሆነ ልጅቷም መነኮሰች!!!


ይሄ ታሪክ ምታነብ ወዳጄ እስቲ አንዴ ወደ ራስህ ተመለስና ልጠይቅህ አሁን ከነገርኩህ ታሪክ ውስጥ  አንተነትህን በየት አገኘኸው ።   ከሰው  ተሸሽጎ በእግዚአብሔር ፊት ግን በደል እየፈፀመ  ከነበረው መነኩሴ ነውን?


ልክ ከሆንኩ ይሄ ስራህ ምነኛ እግዚአብሔር አስዝኖት ይሆን ብለህ አስበኸው ታወቃለህ በሰው ፊት ምንም ያልበደልክ መስለህ ስትቀርብ ምነኛስ ታዝቦህ ይሆን የእውነትም ይሄን መነኩሴ መስለኸው ከሆነስ   ጌታዬ   እንደድክመቴ ሳይሆን እንዳተ ምህረት ብለህ  እንደ መነኩሴው ለመመለስ ያብቃህ


ይሄን መነኩሴ አልመስለውም ካልክ ሌላ አማራጭ ልስጥህ    የራሳቸውን ሀጢያት ትተው የባልጀራቸውን ሀጢያት በመሰብሰብ በደከሙት እኚያ መነኮሳት ውስጥ ራስህን አግኝተህ ይሆን?  በነሱ ውስጥ አግኝተኸው ከሆነ ጌታ እንዲህ ይልሀል 

ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?
⁴ ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ።

ስለዚህ ወደ ራስህ ተመለስ የወንድምህን ሀጢያት በመሰብሰብ እና   በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በመክሰስ አትፀድቅም ይልቁን በእግዚአብሔር የተናክ ትሆናለህ የሚያፀድቅህስ ወደ ራስህ ተመልሰህ በደልህን ስትመለከትና ራስህን ለእግዚአብሔር ስትከስ ብቻ ነው።

አይ እኔ ከሁለቱም የለሁም ካልከኝ ግን እንድ የመጨረሻ እድል ስጠኝና  ምስያህን ላፋልግህ ምን አልባትም ከመነኩሴው ጋር  የነበረችው ሴት ትሆንን? ለፅድቅ ሳይሆን ለኃጢአት ተባባሪ ከጠፉት ጋር ጠፊ እሷንስ ሆነህ ከሆነ ከጠፊዎች ጋር መጥፋትህን ትተህ እንደ ጠፋው ልጅ ወደ አባታቸው ቤት ከሚመለሱት ጋር ለመተባበር ያብቃህ!


እንደ እኔ ግን ራስህን በ ሶስቱ ውስጥ አግኝተኸው ከሆነ ግን  ከሁሉ ይልቅ ምህረት የሚገባን እኔና አንተ ነንና የምህረቱን ፊት እንዲመልስልና እንዲምረን  በንስሐ ከደጁ ለመቆም ይርዳን።


✍ ዲ/ን ወገን


የእግዚአብሔርን ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ  Share በማድረግ እንድታግዙኝ በትህትና ጠይቃለሁ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አሁን የነግህ (ከጠዋቱ 12፡00) ምስጋና እና ጸሎት ሰዓት ነው።

ሰው ሆነን የተፈጠርንበት ዋነኛው አላማ ከመላዕክት ጋር እግዚአብሔርን ለማመስገን ስለሆነ በዙሪያችን ካሉ ከቅዱሳን መላዕክት ጋር አምላካችንን አብረን እናመስግን።

በዚህች ሰዓት ልዑል እግዚአብሔር የሌሊቱን ጨለማ አሳልፎ ብርሃኑን ያሳየን ሰዓት ነው። ለእኔ ህይወቴን የቀየረልኝ የአንድ ደቂቃ ጸሎት አብረን እንጸልይ። በስራ፡ በትምህርት፡ በጉዞ፡ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብንሆን ይህን ጸሎት በህሊናችን መጸለይ እንችላለን።

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፡ ስላደረክልን ነገር ሁሉ እናመሰግንሃለን። የሌሊቱን ጨለማ አሳልፈህ ብርሃኑን ባሳየህን በዚህ ሰዓት ምግባር እና ሃይማኖትን ይዘን እንድንገኝ እርዳን፡ ሃጢያታችንን ይቅር በለን።

1. እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ (ከ12-41 ጊዜ የምንችለውን ያህል)
2. በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ (ከ12-41 ጊዜ የምንችለውን ያህል)
3. መሃሪው አምላክ ማረን ይቅር በለን.... (በክርስትና ስም የምናስባቸውን ሰዎች መጥራት)
4. ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ልብለኪ... (ከ1-3 ጊዜ የምንችለውን ያህል)
5. አቡነ ዘበሰማያት"


ልዑል እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይቀበለን። አሜን!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝#እንኳን_አደረሳችሁ✝

†††ግንቦት 21 እንኳን ለአምላክ እናት ለእኛም እናት ለሆነች ለእናታችን
ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለንጽሕተ ንጹሐን ለወላዲተ አምላክ የመገለጥ
አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ከእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ዜና ሲኖር ለሰው ልጆች ያበስር ዘንድ ከመላእክት መካከል ቅዱስ ገብርኤል የተመረጠ ነው። ለድንግል ማርያም ያበሰረበት መንገድ እና ለዘካርያስ የነገረበት መንገድ ይደንቀኛል። ወደ ዘካርያስ ተልኮ በስተእርጅና "ልጅ ትወልዳለህ" ሲለው ዘካርያስ በመጠራጠሩ ቅዱስ ገብርኤል ሊያስረዳው አልወደደም። ይልቅ በተሰጠው ሥልጣን "ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ" ብሎ ፈርዶበት ሄደ እንጂ።

በተመሳሳይ መንገድ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ማርያም ተልኮ "ልጅን ትወልጃለሽ" ብሎ በነገራት ጊዜ እርሷም ጥያቄ አቅርባለታለች። "ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?" ብላ። እዚህ ጋር ግን ቅዱስ ገብርኤል ተጠንቅቋል። ማንን እያናገረ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። መላእክት በሰማይ እየተንቀጠቀጡ የሚያመሰግኑት፣ ዘወትር "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ" እያሉ የሚሰግዱለትን አምላክን የምትወልድ ናት እና ድንግል ማርያም ላይ የዘካርያስን አይነት የሥልጣን ቃል ሊናገር አይችልም። ይልቅ በትህትና "የልዑል ኃይል ይጸልልሻል" ብሎ ወደ ማብራሪያ ገባ እንጂ። አመስግኗት ብሥራቱን አድርሶ ወደ ላከው ተመልሶ ሄዷል።

እመቤቴ ሆይ ምን ብዬ ላመስግንሽ? በበደላችን ምክንያት ያጣነውን ጸጋ ባንቺ አገኘን። አንቺ ከመላእክት ትበልጫለሽ። ሰው የመሆናችን የባህሪያችን መመኪያ ነሽ እና እናመሰግንሻለን። በመጀመሪያ እናታችን በሔዋን ያጣነውን ክብር በአማናዊት እናታችን በአንቺ አግኝተነዋል። ድንግል ሆይ ፍቅርሽ በልቤ ይብዛልኝ። እንደ ዮሐንስ እድለኛ ልሁንና ወደ ቤቴ ግቢልኝ። እንደ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ከአንደበቴ አትለይ እና በሄድሁበት ላመስግንሽ። እንደ ኤፍሬም በልቤ ኑሪ እና ዘወትር አዳዲስ ምስጋና ላመስግንሽ፣ አዳዲስ ስንኝ ልጻፍልሽ። አደራ እናቴ!

☞እናታችን እመቤታችን ለእኛ አንቺ ለመገለጥ የሚያበቃ ሥራ ስለሌለን ወደ
አንቺ እና ወደ ልጅሽ የሚወሰደውን ቀናውን መንገድ ምሪን፡፡🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ይህችን ዓመት ተወኝ!+


ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ
አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ
አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ
ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ
ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ
የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!

አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር
‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ
ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ -
ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ
ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም
ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም!
እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ
የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ!
አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ!
ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው
ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው!
ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው!
እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት
ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት
ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!.. 
ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት!
ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ! 

✍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒


+ ሰይጣን የማይነካው ዕቃ +


👉 በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ "ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየተት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ።

ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር አልቆጠራቸውም።  "እስቲ አሁን ደግሞ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ ...." ማለቱን ቀጠለ፡፡

በነገሩ ያዘኑት አባት "ኧረ ንጉሥ ሆይ አይተው ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው" ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። "የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይሄማ ይልቅ እርስዎ የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!" አላቸው።
ጠንቋዩም "የፈለጉትን ላምጣልዎት....ምን ይፈልጋሉ? የሞተ ዘመድ አለዎት.... ወይስ ከቤትዎ ዕቃ ላምጣልዎት?" አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። "እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልክ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና" አሉት። ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ።
ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ማስመሰል ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣትም ሆነ ማስመሰል  አይችልም። አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም አይወድም ይላሉ።

በአሁን ዘመን ደግሞ ዲያብሎስ እንደ እባብ አይነት ምግባር ያላቸውን ሰዎች ላይ አድሮ መስቀል እኮ እንጨት ነው ይለናል። ለመስቀል ለምን ትሰግዳላችሁ ለመስቀል መስገድ ጣዖት ማምለክ ነው... የመሳሰሉትን መርዝ ንግግር ሲናገር እንሰማዋለን። ይሄን ነገሩን የሰሙ ብዙ ሄዋኖችም ነገሩን ሳያጣሩ ቃሉን ተቀብለው ከኦርቶዶክስ ተባረዋል። እኛ ግን የሄዋን ሳንሆን የድንግል ልጆች ነንና ይሄንን ለእባቡ እንመልሳለን!


ፊልጵስዩስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
¹⁹ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።

ይሄን መርዝ አምነው ለሄዱ ሄዋኖች ደግሞ መልሳችን ይህ ነወ!

“ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።”
  — ገላትያ 6፥14



✍ ዲ/ን ወገን


ይቺን ታናሽ አገልግሎቴን Share በማድረግ አግዙኝ!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይገርማችኋል እኮ

❤እግዚአብሔር ላይ ብዙ ትርፍ እኮ ነዉ ያለን

👉ንጉሥ አባት መሆን አይችልም
አባት ንጉሥ ሁኖ አይፈርድልንም

👉ወላጅ አባታችን ንጉሥ ሁኖ ፈርዶ
ፍትህ ሊሰጠን አይችልም
ምክንያቱም ሹም አይደለምና

👉ንጉሡ ደግሞ አባት ሊሆነን አይችልም ደግሞ ሌላውንም ያስተዳድራልና

👉ንጉሥ ደግሞ መድኃኒት ሊሆነን አይችልም ሀኪም አይደለምና

👉 እግዚአብሔር ንጉሳችን ነዉ
ፍትህ ይሰጠናልና

👉መድኃኒታችን ነዉ ያድነናል ይፈወሰናልና

👉አባታችን ነዉ ያዝንልናልና

👉 ያሳድገናልም ጭምር ለዚያውም ስጋዉን አብልቶ ደሙን አጠጥቶ ነዋ

👉በ40 ቀን በ80 ቀን የብርሃን ልብስ አልብሶ ነዋ የሚያሳድገን በመላእክት ጠብቆ ነዋ የሚያሳድገን

👉ከገደል ወድቀን ከባህር ጠልቀን እንዳንሞትበቅዱስ መላአክ እጅ ጠብቆ ነዉ የሚያሳድገን እግዚአብሔር ።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“የንጹሐን ጻድቃን ዕርገት ያስረዳ ዘንድ ዐረገ” በትንሣኤው ትንሣኤያችን እንደገለጸልን በዕርገቱም እርገታችንን አጸደቀልን ከዚህም የተነሣ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት የሰው ልጆች ዕርገት ገልጾ አስተምሮአል፡፡ “ እኛ ሕያዋን ሆንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ጌታን በአየር ለመቀበል ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናልን ስለዚህ እርስ በእርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ” (1ኛ ተሰ 4፡15-18) በማለት የክርስቶስ ዕርገት ለምዕመናን ዕርገት መሠረት መሆኑን ገልጾልናል፡፡

ቅዱሳን አረጉ መባላቸውም ከእርሱ ስለሆነ እነኤልያስ ዐረጉ እነ ሄኖክ ከሞት አመለጡ ብለን ብንናገር በእርሱ ኃይል ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስ "ከእርሱ በቀር ከሰማይ የወረደ ወደ ሰማይ የወጣ የለም" ብሎ ሰው መሆኑን አምላክነቱን ነገረን፡፡ በእርግጥም ቅዱሳን ዐረጉ ብንል ድንግል ማርያም ዐረገች ብንል ምዕመናን ያርጋሉ ብንልም ሰዎች ናቸው እንጂ የአምላክነት የፈጣሪነት ባህርይ የላቸውም፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ግን ከሰማይ የወረደ በአምልኮነት በየማነ አብ በዘበነ ኪሩብ ለመቀመጥ ያረገ ነው፡፡ የቅዱሳን የዕርገት መሠረትም እርሱ ነው፡፡

በክብር ያረገው የአምላካችን ቸርነቱ አይለየን!

(ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት እና የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት መካነ ድር ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
"አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ" መዝ 46፡5፡፡ "ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ" መዝ 67፡18፡፡ “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ መዝ.67፡33፡፡

“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ አረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” ማር 16፥19፡፡ “እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ” ሉቃ.24፥50፡፡

ከዘጠኙ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው፡፡ በዓለ ዕርገት ከትንሣኤ በዓል በኋላ በ40ኛው ቀን ስለሚውል ሐሙስን አይለቅም፡፡ ዕርገት ማለት ዐርገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወደ ላይ መውጣት ከምድር ከፍ ከፍ ማለት... እስከ ሰማየ ሰማያት መምጠቅ ማለት ነው፡፡ የጌታ ዕርገት እንደ ኤልያስ እንደ ሔኖክ እንደሌሎቹም ቅዱሳን ያይደለ በገዛ ሥልጣኑ የሆነ ነው ሌሎቹ አጋዥ አስነሽ ይሻሉና ነው፡፡

ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ቅዱስ ዳዊት «አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ» (መዝ 46:5) በማለት በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ በመንፈስ ዘምሯል። ይህም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ ይዟቸው ሄዷል።ሉቃ 24፡50 ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ቦታ ተገልጾ ታይቷቸዋል። ትምሕርትም አስተምሯቸዋል። «ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው»ሐዋ 1:3። በነዚህ ቀናት ውስጥ ጌታችን ሥርዓትን አስተምሯቸዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ትምሕርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀናት በምድር ቆይታ ባደረገበት ወቅት በግልጽ ተገልጦ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና መጽሐፈ ኪዳንን አስተምሯቸዋል፡፡ ጉባኤ ዘርግቶ ያስተማራቸው ለሦስት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዮሐ.21፤14 እነሱም
1. ሞትን ድል አድርጎ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በተነሳበት በትንሣኤ ዕለት
2. ምሳ ባበላቸው /በአግብኦተ ግብር/ ዕለት
3. በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ናቸው፡፡
በዚህ በዕርገቱ ዕለት ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቁን ሹመት የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻን ቁልፍ ተሰጥቶታል ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሞትን ሳይቀምስ እስከ እለተ ምፅአት እንደሚቆይ ተገልጿል ዮሐ. 21፤15-23

እንዴት ዐረገ?
ሐዋርያትን ከባረካቸው በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ በማነስ፣ በመርቀቅ፣ በመጥፋት ሳይሆን በመራቅ ሐዋርያት በዓይናቸው እየተመለከቱት በጥቂት በጥቂት ምድርን ለቆ ከፍ ከፍ እያለ በፍጹም ምሥጋና ፈጽሞ ወደ አልተለየው ወደ ባሕሪ አባቱ ዐርጓል፡፡ በሥጋና በነፍስ፣ በአጥንትና በደም፣ በጅማት፣ በጸጉርና በፂም እንዳለ በጥንተ አኗኗሩ በአብ ቀኝ ተቀመጠ በሰማይ በምድር ያሉትን ረቂቁም ግዙፉም ሁሉ ተገዙለት፡፡ 1ኛጴጥ. 3፤22 ክርስቶስ የሰውን አካል የሰውን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲገለጥ ሰውም የአምላክን ገንዘብ ገንዘብ አድርጎ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በዘባነ ኪሩቤል የመላእክትንም ምሥጋና ለመቀበል በቃ፡፡

ለምን ዐረገ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክቡሩ ማረጉ… በሙሴ የሕግ መጽሐፍት በነቢያትም የትንቢት መጽሐፍ እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት የተነገረው ትንቢት አለና ይህ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ መዝሙረኛው ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለጌታችን ዕርገት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡ መዝ. 47፡5 ‹‹…. አምላክ በእልልታ በእግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ›› መዝ. 67፡18 ‹‹ወደ ላይ ዐረግህ ፣ምርኮን ማረክ ፣ስጦታን ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ. 16፡10 ‹‹ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስም ክንፍ በረረ….›› በማለት በትንቢት መነጽር ተመልክቶ የዘመን ግድግዳ ሳያግደው የተናገረው ኃይለ ቃል ነው፡፡

ዕርገቱን ለምን በተነሳ በ40ኛው ቀን አደረገ?
★ አዳም በ40 ቀን አግኝቶ ያጣትን ልጅነት እንደተመለሰለት ለማጠየቅ
★ አንድም ጌታ በረቀቀ ጥበቡ ተሸብሮ የነበረውን የሐዋርያትን ልቡና እያረጋጋና እያጽናና መቆየቱን መርጦ ነው፡፡
★ አንድም ለአይሁድ ምክንየት ለማሳጣት ነው ዕርገቱን ከትንሳኤው አስከትሎ ወዲያው ቢያደርገው ዕርገቱ ምትሐት ናት እንዳይሉ በእርግጥ በሞቱ ሞት ድል አድረጎ የተነሣው ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መሆኑን እንዲረዱ እንዲገነዘቡበ የጥርጣሬ መንፈስ በአዕምሯቸው እንዳይሰርጽ ነው፡፡
★ አንድም ላላመኑት ለእስራኤላውያን (ለአይሁድ) የንስሐ ጊዜ ሲሰጣቸው ነው ብዙዎች በክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት አምነው የተመለሱ አሉና፡፡

በዓለ ዕርገት መቼ ነው?
ጥንተ ዕርገቱ በወርሐ ግንቦት ስምንት ሐሙስ ቀን በ34 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡ የዕረገት በዓል አከባበር እስከ አራተኛው መቶ ዓመት ድረስ እንደ ዛሬው ሐሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ በአራተኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በአርባኛው ቀን ብቻ እንዲከበር ቅዱስ ዲሜጥሮስ በባሕረ ሐሳብ ቀመሩ ስሌት መሠረት ይከናወን ዘንድ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡
የይሁዳ ምትክ መምረጥ ፊት አውራሪ ሆኖ ጌታን ለመስቀል ሞት አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ቁጥሩ ከ12 ሐዋርያት ነበር ይህን ማዕረግ አርክሶ አጉድፎ በመገኘቱ ከሐዋርያ አንድነት ሕብርት ሊገለል በቅቷል የሰው ልጅ እኩይ ተግባርን በፈጸመ ቁጥር ጸጸት በውስጡ ያድር ዘንድ የገዛ ሕሊናው ወጥሮ ይይዘዋል፡፡ ይህ የሕሊና ፍርድ ይሁዳንም ስላስጨነቀው ‹‹ ንጹህ ደም አፈሰስኩ ጻድቅ ሰው አስገደልኩ አወይ አላበጀሁም›› በማለት ጌታን ለማስያዝ የተቀበለውን 30 ብር ከዕቃ ቤት አፍስሶ ገመድ ይዞ ዛፍ ላይ በማሰር ለመታነቅ ሙከራ ቢያደርግም ዛፏ በሰው አንደበት ‹‹ እንደወንድምህ ጴጥሮስ ንስሐ ግባ ›› እያለች ዘንበል ብትልም ራሱን አላዘጋጀም ነበርና ለሦስተኛ ጊዜ ለመታነቅ ሲሞክር ከመሬት ደባልቃዋለች በዚህ ክፉኛ ተጎድቷል ምድርም ላይ ወድቆ ሳለ ነጋድያን ሲያልፉ አይተውት ለዘመዶቹ ‹‹…ያክፉ ዘመዳችሁ ከዚያ ወድቆላችኋል›› ብለው ስለነገሯቸው ዘመዶቹ አንስተው ወሰዱት ለአርባ ቀን ያህል ሆዱ አባብጦ ተኝቶ ነበርና ጌታ ሲያርግ ‹‹…ያሰቀልከው አረገልህ ›› ብለው ቢነግሩት ለማየት ሲወጣ የክፍሉ መወጣጫ አደናቅፎት ቢወድቅ የሳንቃው መወርወርያ ጎኑን ቢወጋው ያበጠው ሆዱ ፈንድቶ ሞቷል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ †✝†

†✝† ግንቦት 16 †✝†

†✝† ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ †✝†

=>አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል::

+ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል::

+ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::

+ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

+3 መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† ቅዱሱ በኤፌሶን †††

=>ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል:: ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ::

+ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ:: ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው:: በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች::

+ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ:: ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ:: ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ::

+እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም:: በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው:: 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ:: እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ::

+አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ::
1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው::
2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው:: ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች::

+ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ:: እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ::

+ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው:: ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ:: የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ::

+ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው:: ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ::

+ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው:: መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ:: በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ::

+ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው:: በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ:: እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን: ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው::

+በስመ ሥላሴ አጥምቆ: ካህናትን ሹሞ: ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል:: በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል:: ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች::

+ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው:: በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች:: አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት::

+ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል:: ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው:: በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት: በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል:: ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል::

††† የፍቅር ሐዋርያ †††

=>ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች:: ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል:: ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል:: በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር::

+በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር:: በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል::

+ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል:: ሊቁ:-
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ:
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው:: (መልክዐ ኢየሱስ)

=>ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው:: እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና::

+ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት:: ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል:: ከመላእክትም በላይ ከብሯል:: ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል::

+ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው::

+ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች:: ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ:-
"በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ:
ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት::

+ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል:: ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል:: ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው::

††† ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት:: †††

=>እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-

*ወንጌላዊ
*ሐዋርያ
*ሰማዕት ዘእንበለ ደም
*አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
*ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
*ወልደ ነጐድጉዋድ
*ደቀ መለኮት ወምሥጢር
*ፍቁረ እግዚእ
*ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
*ቁጹረ ገጽ
*ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ፅድቅ- ፈጣሪ


📌ወዳጅ ባይኖረኝ ከጎኔ
📌አለሁ የሚለኝ በወኔ
📌ቢርቁም ከውስጥ ልቤ
📌መቼም ባይቀር ማሰቤ

♦️ቢደክም ቢዝል ጉልበቴ
♦️ሊፈርስ ቢደርስ ህይወቴ
♦️የእዝነት እምባ ማንባቴ
♦️እምነቴን ብዬ መምጣቴ

📌ፈጣሪ እንዳለ አምኜ
📌አምላኬን ብቻ ኮንኜ
📌ከቶ የላቀ አሳቢን
📌ፍጡሩን ሁሉ ሰብሳቢን

♦️እኔ ግን ክህደቴ
♦️ብቸኛ ነኝ ስል ሁኜ ከቤቴ
♦️አውሎ አሳዳሪዬን ዘንግቼ
♦️ከማሰቢያ ህሊና ወጥቼ

📌ታዲያ ለዚህ ሁሉ ጥፋቴ
📌ማፈንገጥ መራቅ ከእምነቴ
📌ምንም አያዋጣም ማሳበቄ
📌ከእኩይ ተግባር መደበቄ

♦️በአይለኬው ጥበቡ ፈጥሮኛል
♦️እሱን ብቻ ልገዛው ግድ ይለኛል
♦️እንደሚረዳኝም አምናለሁ
♦️በፈጣሪም ተስፋ አደርጋለሁ



✍ fayeDid




@uniquepoem

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ቅጥ ያጣው ጸሎታችን በድርሳኑ እንዲህ ሲል ይመክረናል:

"ጉዳትህን ነግረህዋልን? የደረሰብህን መከራ ሁሉ አዋይተህዋልን? እንዴት አንተን መርዳት እንዳለበት አትንገረው። ለአንተ የሚረባህ የተሻለው መንገድ እርሱ ራሱ በትክክል ያውቀዋልና።"

ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያን የምንለምነውን አናውቅምና የጸሎት መጽሐፍ አዘጋጅታ ይህን ጸልዩ ብላ የሰጠችን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን "

ታላቅ መንፈሳዊ ደርሶ መልስ ጉዞ ወደ ፃድቃኔ ማርያም
ወደ ፃድቃኔ ማርያም የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የንግስ እና ታላቅ የሆነው የህንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ምክንያት በማድረግ በማህበሩ መንፈሳዊ ጉዞ ተዘጋጅቷል ።

ትራንስፖርትና ምግብ ጨምሮ=➣ 650 ብር

መነሻ ሰአት ➣ 11:00
መነሻ ቦታዎች
◎ ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
◎ መገናኛ ውሀ ታንከሩ ጋር
◎ ወሰንና ጣፎ አደባባይ
ለበለጠ መረጃ
📞
+251985654083
📞
+251911663419
📞
+251915858525


● ከጉዞው የሚገኘውን ትርፍ ማህበሩ ለጀመረው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሀን መጠለያ ላሉት የሚውል ድጋፍ  ይሆናል ።


አዘጋጅ ማኅበረ ኤዶምያስ ጉዞ ክፍል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም. የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳማት መነኰሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩዋቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኰሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኰሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኰሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፤ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፥26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡
ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአኵሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፤ ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ስለተጓዙ በዚህ ምክንያት 'መናኔ መንግሥት' ይባላሉ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፥ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመንም ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስም አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ወደ ‎ዋልድባ፤ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ ከዚያ ወደ ጐጉቤን ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ::
አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኀኔዓለምን ጽላት እንዲያወጣላቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኀኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፤
✣ የጌታችንን እግር ያጠቡት የገዳመ መጕናው አቡነ አብሳዲ፤
✣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፤
✣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፤
✣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፤
✣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡
*** ገዳሙን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ፤ በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ መነኰሳት የሚጠሩበት የአባት ስማቸው በጻድቁ በአቡነ ያሳይ ስም ነው፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ የማኅጸን ውስጥ ሸንጎ +


መንትያ ሕጻናት በእናታቸው ማኅጸን ውስጥ ተጸንሰው እየኖሩ ነው፡፡ አንደኛው ሕጻን ሌላኛውን ጠየቀው ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት አለ ብለህ ታምናለህ?››

ሌላኛው መለሰ ፡- ‹‹እንዴታ! ከማኅጸን ከወጣን በኋላማ የሆነ ሕይወት ሳይኖር አይቀርም፡፡ ምናልባት አሁን ማኅጸን ውስጥ የምንቆየው ለዛኛው ሕይወት ራሳችንን እያዘጋጀን ሊሆን ይችላል፡፡›› አለው፡፡

‹‹የማይመስል ነገር!!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን፡፡ ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት የሚባል ነገር የለም! እስቲ አስበው ከማኅጸን ውጪ የሚኖረው ምን ዓይነት ሕይወት ነው?›› አለ እየሳቀ፡፡



ሁለተኛው መለሰለት ‹‹እኔም አላውቀውም ግን እዚህ ካለው የተሻለ ብርሃን እዚያ ያለ ይመስለኛል፡፡ ምናልባት በዚያኛው ሕይወት በእግራችን ለመሔድ ፣ በአፋችን ለመጉረስ የምንችል ይመስለኛል፡፡ ምናልባት አሁን ልንረዳቸው የማንችላቸው ሌሎች ስሜቶችም ሊኖሩን ይችሉ ይሆናል፡፡››
የመጀመሪያው ሕጻን በብስጭት ቀጠለ ‹‹ይኼ ቅዠት ነው፡፡ በእግር መሔድ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ጭራሽ በአፍ መጉረስ? የማይሆን ነገር ታወራለህ እንዴ?! ምግብ የምንበላውንና የሚያስፈልገንን ነገር የምናገኘው በእትብታችን በኩል ነው፡፡ እትብታችን ደግሞ በጣም አጭር ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጡ በኋላ ሕይወት አለ የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም፡፡››

ሁለተኛው ሕጻን ግን ውትወታውን ቀጠለ ‹‹እኔ ግን የሆነ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ማኅጸን ውስጥ ካለው ነገር የተለየ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም እትብትም ላያስፈልገን ይችል ይሆናል፡፡››

የመጀመሪያው ሕጻን ግን አልተረታም ‹‹አይዋጥልኝም! እሺ የምትለውን ልቀበልህና እንዳልከው ከማኅጸን ውጪ ሕይወት ካለ እዚያ ደርሶ የተመለሰ ሰው ለምን አናገኝም? ከማኅጸን መውጣት የሕይወት መጨረሻ ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጣን በኋላ በጨለማ ውስጥ በዝምታ ከመጣል በስተቀር ምንም ነገር የለም፡፡ ወዴትም አንሔድም!››

‹‹በእርግጥ ምንም አላውቅም›› ቀጠለ ሁለተኛው ሕጻን ‹‹ነገር ግን ከማኅጸን ከወጣን በኋላ እናታችንን እናገኛለን፡፡ እስዋ ትንከባከበናለች፡፡››

‹‹እናት? በእናት መኖር ከልብህ ታምናለህ ማለት ነው? በጣም የሚያስቅ ነገር ነው!!! እሺ እናት ካለች አሁን የት ነው ያለችው?
ሁለተኛው ቀበል አድርጎ ‹‹እናታችንማ በዙሪያችን አለች፡፡ በእርስዋ ተከብበን ነው ያለነው፡፡ የተገኘነው ከእርስዋ ነው፡፡ የምንኖረውም በእርስዋ ውስጥ ነው፡፡ ያለ እርስዋ ያለንበት የማኅጸን ውስጥ ዓለም ሊኖር አይችልም፡፡›› አለው፡፡

  ‹‹አላየኋትማ! የት አለች? ስለዚህ አለች የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን
ሁለተኛው ሕጻን ግን ይህን አለ ‹‹በማኅጸን ውስጥ ስትኖር አንዳንድ ጊዜ በዝምታ ውስጥ ሆነህ በጥሞና የምታዳምጥ ከሆነ የእናትህን መኖር ትገነዘባለህ ፤ በፍቅር የተሞላ ድምጽዋን ከላይ ሆኖ ሲጠራህ ትሰማዋለህ›› ብሎ ክርክሩን ቋጨው፡፡



ይህች ዓለም እንደ ማኅጸን ናት ፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ለወዲያኛው ኑሮ የምንዘጋጅበት አጭር ጊዜ ነው፡፡ ብዙዎች ለማመን ቢቸገሩም ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወት አለ ፤ በጥሞና በተመስጦ ከፈለግነው የዓለም መጋቢና ሠራዒ አምላክ ልዑል እግዚአብሔርም አለ፡፡ የምንሞትበት ቀን ከጠባቡ ወደ ሰፊው የምንሔድበት ለዘላለም ሕይወት የምንወለድበት የልደታችን ቀን ነው፡፡

✍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 22 ከ72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ዐረፈ፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ምስራቃዊ ያዕቆብ መታሰቢያው ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ፡- ይኽንንቅ ቅዱስ በመጀመሪያ የክብር ባለቤት ጌታችን መረጠው፡፡ እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታችን ከመከራው በፊት ከላካቸው ከ72ቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው፡፡ በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከከበሩ ሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ የከበረች ወንጌልን በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ፡፡ ብዙዎችንም አስተምሮ በማሳመን አጠመቃቸው፡፡

ከዚኽም በኋላ በኒውብያ አገር ላይ ሐዋርያት በአብሮተ እድ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት፡፡ በውስጧም የከበረች ወንጌልን በሰበከ ጊዜ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙ አረማውያንን የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ሃይማኖት አስገባቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ ሐዋርያውን ዮልዮስን ወሰደውና አብረው በአንድነት በብዙ አገሮች ዞረው በማስተማር አልጫውን ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፈጡት፡፡ ብዙዎችንም በእጆቻቸው አጠመቁ፡፡ ተአምራትንም በማድረግ ከብዙ ሰዎች ላይ አጋንንትን አስወጡ፡፡ በርካታ ድውያንንም ፈወሱ፡፡ ሙታንንም አስነሡ፡፡ የጣዖታት ቤቶችን አፍርሰው በምትካቸው በጌታችን ስም አብያተ ክርስቲያናትን አነጹ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስና ወዳጁ የሆነ ሐዋርያው ዮልዮስም አገልግሎታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ፡፡ ወዲያውም ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚኽች ዕለት ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ ቀበረው፡፡
የእነዚህ የከበሩ ሐዋርያት ረድኤት በረከታቸው ትደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግድ የላችሁም

👉 ሰዉ በልብስ ደስ ይበለኝ ቢል ሌላ የተሻለ ልብስ ለብሶ መጥቶ ደግሞ ደስታውን ያደበዝዘዋል እስከሚገዛ ድረስ

👉በዕውቀት ደስ ይበለኝ ቢል ሌላ ዕውቀት ያለው ይመጣና ያደበዝዝበታል

👉በመልክ ደስ ይበለኝ ቢል ሌላ መልከኛ ይመጣና መከበሩን ያጠፋዋል ታዲያ ምን ይሻለዋል የሰው ልጅ

👉የሚወደዉን ምግብ ቢያገኝ ከመደጋገሙ የተነሣ ይሰለቸዋል

👉የማይቀማ ደስታ ❤ ክርስቶስ ❤ነው

❤በክርስቶስ❤ ደስ ያላቸው ሰዎች ደግሞ

-ሰይፍ አይቀማቸዉም
-ስለት አይቀማቸዉም
-ገደል መወርወር አይቀማቸዉም

👉ቅዱስ ቂርቆስን አልሰማችሁትም
ከንጉሡ ፊት ለእሳት ለስለት ቀርቦ
እንዴት ብሩህ ፊት ያለህ ደስ የምትሰኝ ህጻን ነህ አለዉ


👉አወ እኔ ይገባኛል ጥሩ ብለሃል
ለአንተ ግን ደስታ የለህም

ለምን ?

👉ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ይላል መጽሐፍ አለዉ ለኔ ግን ደስታ ይገባኛል አለው

👉ይሄ ደስታ ግን የት ዉስጥ ነዉ የሚገኘዉ ካላችሁኝ መስቀል ዉስጥ ነዉ መስቀል መከራ ነዉ ከመስቀሉ ላይ ግን ያለም ደስታ ተገኝቷል።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒


† ደብረ ምጥማቅ †

በቅድሚያ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ !


👉 የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፈው ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላትም ነበር::

ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::

+በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:-
እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::

+እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::

+የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::

+እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::





† አባ መርትያኖስ †

=>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር::

+አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው::

† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: †

👉 ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት


1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)

2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)

3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ

👉 ወርኀዊ በዓላት

1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ

" የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ "

(መዝ. 44:12-17)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

✍ ዲ/ን ወገን


ይችን ታናሽ አገልግሎቴን Share በማድረግ ደግፉኝ🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+++... የእናት ነገር... +++



ይህች ወጣት የልጅዋን መርፌ መወጋት ማየት አቅቷት ዓይኗን ጨፍና ስትሸማቀቅ ያየ ሁሉ መቼም ምንም እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብ ቢኖረው እንኳን ለአፍታ ማዘኑ ና ከንፈር መምጠጡ የማይቀር ነው፡፡

(ፎቶዋን ከስር አቅርቤላችኋለሁ )

የሚያሳሳው ሕጻን ልጅ ያለ አንዳች ፍርሃት ክትባቱን እየሠጠችው ያለችውን ሐኪም አተኩሮ እያየ ነው ፤ እናት ግን ለልጁ ያልተሰማው ሕመም ከመጀመሪያው ተሰምቷት ጥርሷን ነክሳለች፡፡  እናት የሆኑ የእስዋ ስሜት ይሰማቸዋል ፤ እናት ያለን ሁላችን ደግሞ እናቶቻችንን እናስባለን፡፡ የስነ ልቡና እውቀት ቢኖረኝና ስለ እናትና ልጅ ትስስር ጽንሰ ሃሳብ (mother child attachment theory) መተንተን ቢቻለኝ ኖሮ ይህች እናት ይህ ፎቶ በተነሣበት ቅጽበት ምን ዓይነት ስሜት ተሰምቷት እንደነበር ብዙ ነገር በተናገርኩ ነበር፡፡

ያለሙያዬ ገብቼ እንዳልዘባርቅ ይህን ለባለሙያዎቹ ልተወውና በዚህ ፎቶ ምክንያት ላነሣት ስለወደድሁት ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ስለነበረች እናት ላስታውሳችሁ፡፡
ልጅዋ በጅራፍ ሲገረፍ ቆማ ያየች ፣ የእሾህ አክሊል ሲደፉበት የተመለከተች ፣ ከመርፌ በሚበረታ ጦር ጎኑን ሲወጉት የተመለከተችዋን ኀዘንተኛ የድንግል ማርያምን ነገር እስቲ ለአንድ አፍታ እናስታውሰው፡፡

በእርግጥ በዕለተ አርብ ድንግል ማርያም ምን ተሰምቷት ነበር? ኢትዮጵያዊው አባ ጽጌ ድንግል ‹‹ከቀለም ጋር ዕንባዬን እያንጠባጠብሁ የድንግልን ሰቆቃዋን እጽፋለሁ... በማንኛውም ጊዜ የእርስዋ ዓይነት ኀዘንና ስደት የደረሰበት ሰው ካለ የልብ ዓይን ያለው ሰው አይቶ ያልቅስ›› (ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ ... ከማሃ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ በኩለሄ ረከቦ ... ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ) እንዳለው እስቲ ለደቂቃ የድንግል ማርያምን ኀዘን መለስ ብለን እናስታውሰው፡፡ በእርግጥ ግን በዚህ ፎቶ ላይ ያለችውን እናት ስናይ የተሰማን የሃዘን ስሜት ድንግል ማርያም ከመስቀሉ ስር ቆማ ተስሎ ስናይ ተሰምቶን የማያውቀው የልብ ዓይን ስለሌለን ይሆንን?

       ያለ አባት የወለደችውን አንድያ ልጇን አጥንቱ እስኪታይ ሲገርፉት በእርግጥ ድንግል ማርያም ምን ተሰምቷት ይሆን? ከሔሮድስ ሰይፍ ይዛው የሸሸችውን ልጇን በወታደሮች ተከብቦ ስታየው ምንኛ ቆስላ ይሆን? አቅፋ ያሳደገችውን

በጉያዋ ይዛው የተሰደደችውን ልጅዋን መስቀል አሸክመው ሲያዳፉት ፣ በወደቀበት ቦታ በጭካኔ ሲረግጡት ባየች ጊዜ የድንግል ልብ ምንኛ ታመመ ይሆን? እስቲ በንጹሕ ሕሊና ተመልከቱት ፣ ይህ የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን አይጠይቅም፡፡ እናት የሆነና እናት ኖራው የሚያውቅ ሁሉ ሊመልሰው የሚችል ጥያቄ ነው፡፡ በምድር ላይ እጅግ አሰቃቂ የተባለውን ሞት ልጅዋ ሲቀበል ያየችውን ድንግል እስቲ በዓይነ ሕሊናችን እንመልከታት፡፡


       ጌታችን የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ እያለ ወደ
ኢየሩሳሌም ይዘውት በሔዱ ጊዜ ጠፍቶባቸው ነበር፡፡ ዮሴፍና ድንግል ማርያምም የአንድ ቀን መንገድ ከሔዱ በኋላ መጥፋቱን አወቁ ፣ ከዘመዶቻቸው ጋርም ፈልገው አጡት፡፡ በመጨረሻም ከሦስት ቀን በኋላ በቤተ መቅደስ ቁጭ ብሎ ከመምህራን ጋር ሲጠይቅና ሲሰማ አገኙት፡፡

ድንግል ማርያም ይህን ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።›› (ሉቃ. 2፡48) ለሦስት ቀን ያህል በመጥፋቱ ምክንያት መጨነቅዋን ተናገረች ፣ ‹ለምን እንዲህ አደረግብን?› ብላም ጠየቀችው፡፡

       ለሦስት ቀን መጥፋቱ ያስጨነቃት ድንግል ደሙ ሲፈስስ ባየች ጊዜ ምንኛ ተጨንቃ ይሆን? ከመስቀል ጋር በሚስማር ተቸንክሮ በስቃይ ላይ ሆኖ ስታየው ምን ያህል ተሰቃይታስ ይሆን? በእርግጥም አረጋዊው ስምዖን እንዳለው በጌታችን ሰውነት ውስጥ ሚስማርና ጦር ሲገባ በእናቱ ደግሞ ‹‹በነፍስዋ ሰይፍ ያልፍ ነበር›› (ሉቃ. 2፡35)
ያዕቆብ አሥራ አንድ ልጆች እያሉት ‹ልጅህ ዮሴፍ ሞተ›

ብለው ብለው በነገሩት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ። (ዘፍ. 37፡34) ኢትዮጵያዊው ሊቅ ርቱዐ ሃይማኖት ታዲያ ስለ ድንግል ማርያም ኀዘን ሲናገር ‹‹የያዕቆብ ልቅሶ ዛሬ ታደሰች አለ›› በእርግጥም ያዕቆብ አሥራ አንድ ልጆች እያሉት እንዲህ ካለቀሰ ድንግል ማርያም በድንግልና ስለወለደችው አንድ ልጅዋ ምንኛ ታለቅስ ይሆን? ያዕቆብ ያለቀሰው የልጁን የዮሴፍን ልብስ በእጁ ይዞ ነበር፡፡ ድንግል ማርያም ግን የልጅዋን ልብስ ይዛ እንዳታለቅስ ልብሱን ቀድደው ተካፍለውታል ፣ በቀሚሱም ላይ ዕጣ ተጣጥለዋል፡፡ የእርስዋ ኀዘን ከያዕቆብ ኀዘን ይበረታል፡፡

       አንዳንድ ሰዎች ‹‹እርሱ ተሰቀለ እንጂ እርስዋ ምን ሆነች? አንተ ብትቆነጠጥ እናትን ያማታል ወይ?› እያሉ ሊፈላሰፉ ይሞክራሉ፡፡  ለእነዚህ ሰዎች ‹የልጅ ስቃይ ለእናት ምንዋ እንደሆነ እናቶቻችሁን ሒዱና ጠይቁ› ከማለት በቀር ምን እንመልሳለን? የሱ መከራ ለእርስዋ ምንም አይደለም የሚለው አመለካከት የሰይጣን የራሱ አስተሳሰብ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል፡፡

ታስታውሱ ከሆነ ጻድቁ ኢዮብ ዐሥር ልጆቹ በአንድ ጊዜ መሞታቸው ሲነገረው አምላኩን ባለመሳደቡ ሰይጣን አፍሮ ነበር፡፡ በኢዮብ ጥንካሬ ደስ ያለው ፈጣሪም ሰይጣንን ‹‹ባሪያዬን ኢዮብን አየኸው?›› ብሎ ቢጠይቀው ‹‹ቁርበት ስለ ቁርበት ነው ፤ በሰውነቱ መከራ ብታመጣበት ይክድሃል›› አለ፡፡

በሰይጣን አስተሳሰብ አንድ አባት ልጆቹ ቢሞቱም እንኳን የራሱ ሰውነት እስካልተነካ ድረስ ዘልቆ አይሰማውም ፣ ሕሊናውንም አይፈትነውም፡፡

ይሄ አስተሳሰቡ ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ጌታ ተሰቀለ እንጂ ድንግል ምን ሆነች የሚሉ የግብር ልጆችን አስገኝቷል።

ኢዮብስ ልጆቹ የመሞታቸውን ዜና ሰማ እንጂ አሟሟታቸውን አላየም፡፡ ልጅዋ ሲሰቃይ ያየች ድንግል ማርያም ‹እስዋ ምንም አልሆነችም› የሚል ሰው ሃሳቡ ሰይጣን ከተናገረው በምን ይለያል?


✍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ለበጎ ነው +

አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን አራዊትን ለመያዝ ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ይቆርጠዋል።

ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ "ንጉስ ሆይ አይዞህ ለበጎ ነው ይለዋል" ንጉሱም እጅግ ይበሳጭና የእኔ እጅ መቆረጥን ለበጎ ነው ትላለህ ይሄማ መሳለቅ ነው ብሎ ያሳስረዋል።

ከብዙ ቀን ቆይታ በኋላ ንጉሱ ለብቻው ወደ አደን ሲሄድ ሰው ገድለው ለአማልክቶቻቸው መስዋዕት የሚያቀርቡ ሽፍቶች ይይዙታል። ሊሰውትም ሲሉ ንጉሱ እጁ የተቆረጠ ነውና በባህላቸውም መሠረት አካለ ጎዶሎ ሰው ለመስዋዕት አይቀርብምና ይተውታል።

ንጉሱም ወዳሰረው አሽከር ሄዶ "ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ያልከው እውነት ነበር ብሎ ታሪኩን ያጫውተዋል። ባደረገውም ተጸጽቶ "ይቅርታ አድርግልኝ አንተን ማሰሬ ልክ አደለም" ይለዋል

አሽከሩም "ንጉስ ሆይ አንተም እኔን ማሰርህ ለበጎ ነው ባታስረኝ ኖሮ  ካንተ ጋር አብሬ እሄድ ነበር። አንተን ሲለቁህ እኔን ደግሞ ሙሉ አካል ነው ብለው ይሰዉኝ ነበር" አለው።

እግዚአብሔር በኛ ላይ የሚያመጣቸው መጥፎም ሆኑ ጥሩ ነገር ለበጎ ናቸውና ከአፋችን ተመስገን አይጥፋ🙏


" እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28)


✍ ዲ/ን ወገን


ይቺን ታናሽ የሆነች አገልግሎቴን Share በማድረግ ደግፉኝ🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግንቦት 19/9/15 #ቅዱስ_ገብርኤል

👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለመልአኩ #ለቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ከመልአኩ ክብር የተነሳ ምድር በራች /ራእ ፲፰ ÷፩ /18፥1

👉ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡

👉ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎትና በምሥጋና ታከበራለች በተለይ ታኅሣሥ ፲፱ /19 / ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን ሠለሥቱ ደቂቅን ከዕቶነ እሳት ከነደደ እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው

👉እንዲሁም ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእቶነ እሳት በእግዚአብሔር ቸርነት ያዳነ ይኸዉ ቅዱስ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ነዉ የመልአኩ ጥበቃና ተራዳኢነት ከሁላችንም አይለየን "አሜን"

👉ሊቀ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ዛሬም ለኛም ይድረስልን
በምናውቀውና በማናውቀው መንገድ በሀገራችን በሕዝባችን ላይ ከሚነደዉ እሳት በምልጃው በተራዳይነቱ ያድነን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
"አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ" መዝ 46፡5፡፡ "ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ" መዝ 67፡18፡፡ “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ መዝ.67፡33፡፡

“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ አረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” ማር 16፥19፡፡ “እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ” ሉቃ.24፥50፡፡
በክብር ያረገው የአምላካችን ቸርነቱ አይለየን!
@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድም ለማየት ሲወጣ መልአኩ የእሳት ሰይፍ ቢያሳየው ተደናግጦ ወደ መኝታው ሲመለስ የአልጋው ሸንኮር ሆዱን ወግቶት ነዋየ ውስጡ ፈሶ ለህልፈት በቅቷል በዚህም የጌታን ትንሣኤ እንዳላየ ሁሉ ዕርገቱን ለማየት ሳይታደል ቀርቷል፡፡
አስቀድሞ በዳዊት አፍ እንደተናገረው መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባት አይኑር ደግሞም ሹመቱ ሌላ ይውሰዳት ተብሎ እንደተጻፈ ጌታን በ30 ብር ለሞት አሳልፎ በሰጠው ከሐዋርያት አንድነት በሞት በተለየው በይሁዳ ምትክ ክፍተቱን የሚሞላ ሐዋርያዊ ተልዕኮውን ሊወጣ የሚችል መምረጥ እንዳለባቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ለ120 ቤተሰብ በማሳወቅ ሁለት ፍጹማን ዮሴፍና ማትያስ ለምርጫ ቀረቡ፡፡ በመቀጠል ‹‹ የሁለቱን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ ይሁዳ ያቃለላትን ይህችን የሐዋርያት ማኅበር /አንድነት/ ይቀላቀል ዘንድ ከሁለቱ አንዱን ሹመው ›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ከጸለዩ በኋላ ዕጣ ቢጣጣሉ ለማትያስ በመውጣቱ ከ11ዱ ሐዋርያት ጋር 12ኛ ሆኖ ተቆጠረ፡፡
ሐዋርያት ማን ብቁ እንደሆነ የሚያውቁ ሆነው ሳለ በዕጣ ለምን አደረጉት?
★ ለትህትና
★ በሰው ሰውኛ ሥርዓት ከእከሌ ይልቅ ለእከሌ አድልተው መረጡ ብለው እንዳይሰናከሉባቸው ለቢፅ ሐሳውያን ምክንያት እንዳንሆንባቸው ሲሉ
★ ሥርዓት ሊሰሩ ሊያስተምሩ ፈቅደው በመንፈሳዊ አገልግሎት እኩል የሆኑትን አገልጋዮች በዕጣ በመለየት ምረጡ ሲሊ በዕጣ መረጡ

የክርስቶስ ዕርገት በትንቢተ ነቢያት
“ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ” መዝ17፥9፡፡
“አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ” መዝ.46፥5፡፡
"ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ" መዝ.67፥18፡፡
“በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ መዝ.67፥33፡፡
“በሌሊት ራእይ አየሁ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለው ደረሰ /ወደ አብ/ ወደፊቱም አቀረቡት፡፡ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ሥልጣን ተሰጠው ግዛቱም የማያልፍ የዘለዓለም ግዛት ነው፡፡ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው” ዳን.7፥13፡፡ ከዚህ ላይ ዳንኤል ስለጌታችን ዕርገት የተናገረው ዮሐንስ ከተናገረው ጋር ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ግዛት ሥልጣን የዘለዓለም መንግሥት ተሰጠው በማለት ጌትነቱን አምላክነቱን አጉልቶ ዮሐንስ ከእርሱ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ያለውን ቀደም ሲል በመንፈስ ረድኤት ጸንቶ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ተናግሮታል ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር እያለ አምላክነቱን ገልጾታል አረገ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ ነግሮናል ዳዊት እግዚአብሔር ብሎ የገለጸውን ዳንኤልና ዮሐንስ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የሰው ልጅ በማለት ገልጸውታል፡፡ ፍጹም ሰው ሆኖአልና፡፡ ክርስቶስ ራሱም “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል” ማቴ.16፥15 በማለት ከጠየቀ በኋላ እነዳንኤል የተናሩት ስለ እርሱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የክርስቶስ ዕርገት በትምህርተ ሐዋርያት
“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ አረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” ማር 16፥19፡፡
“እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ” ሉቃ.24፥50፡፡

“ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል አሏቸው” ሐዋ.1፥9-12፡፡
ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በእርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡ ጌታችን በዚህ ዓለም ሲመላለስ ሲያስተምር የቅዱሳን መላእክት ምስክርነት አልተለየም በልደቱ “ለዓለም ሁሉ የሚሆን መድኀኒት ተወልዶላችኋል ታላቅ የምሥራችን እንነግራችኋለን” ሲሉ ለእረኞች አብስረዋል፡፡ ሉቃ.2፥10-15፡፡ ክርስቶስ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾሞ ዲያብሎስን ድል በነሳ ጊዜ “መላእክትም ያገለግሉት ዘንድ መጡ” (ማቴ.4፥11) በትንሣኤውም “እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ክርስቶስ እንድትሹ አውቃለሁ ተነሥቶአል ከዚህ የለም” (ማቴ.28፥4-11) ብለው ለሴቶች የትንሣኤውን የምሥራች ነግረዋል፡፡ በመስቀሉ ስርም ደሙን በብርሃን መነሳንስ ሲቀበሉ ለከ ኃይል እያሉ ሲሰግዱ ችሎታውን ቸርነቱን ሲያደንቁ ብሎ የቤተ መቅደስ መጋረጃ በሰይፋቸው ለሁለት ሲከፍሉ ታይተዋል፡፡ ማቴ.27፥51፡፡ ዛሬም በዕለተ ዕርገት በዕለተ ልደት ያመሰገኑት ምሥጋና እያመሰገኑ የምሥራች ለሰው ልጆች ሲነግሩ እርገቱን ከዳግም ምጽአቱ ጋር አስተባብረው ሰብከዋል፡፡

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ዕርገቱ መስክሯል “በሥጋ የተገለጠ መንፈስ የጸደቀ ለመላእክት የታየ በአሕዛብ የተሰበከ በዓለም የታመነ በክብር ያረገ” 1ጢሞ.3፥16፡፡ ልደትን እንደ ዘር ዕርገትን እንደ መከር አድርጎ ገልጾልናል ወርሐ ዘር የመከር ጊዜ ነው፡፡ ገበሬ በጎተራ ያለውን እህል እያወጣ ሲዘራ ከላይ ዝናም ከታች ጭቃውን ታግሶ ነው፡፡ በመከር ጊዜ ያን የዘራውን ምርት በጥፍ ሲያገኝ ደስ ይለዋል መከራውን ይረሳዋል፡፡ ምነው በጨመርኩበት ይላል፡፡ የክርሰቶስም ልደቱ ስለኛ መከራን ለመቀበል ነውና፥ በሥጋ የተገለጠ ብሎ ትሕትናውን አሳየ፡፡ ዕርገቱን ግን በክብር ያረገ ብሎታል፡፡ ምክንያቱም የሰውነትን ሥራ ፈጽሟልና ድል ነስቶአልና ይህን በሥጋ ዕርገቱን ስናስብ ለምን ዕለቱን ተነሥቶ እለቱን አላረገም ለምንስ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ ቆየ? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ የቆየው ትንሣኤው በግልጽ እንዲረዳ ደቀ መዛሙርቱንም መጽሐፈ ኪዳንን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምር ዘንድ ነው፡፡ ሌላው አራት ባሕርየ ሥጋና አምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ላለው የሰው ልጅ እንደ ካሰ ለማጠየቅ ነው፡፡ አርባን ለአምስት ቢያካፍሉት ስምንት ስምንት ይደርሳቸዋል፡፡ ይህም ስምተኛው ሺህ ሲፈጽም የዚህ ዓለም ምግብና እንደሚጠናቀቅና፥ ክርስቶስ አራት ባሕርያተ ሥጋ አምስት ባሕርየ ነፍስ ላለው የሰው ልጅ እንደየ ሥራው ለመክፈል መምጣቱን ያስረዳናል፡፡ ከዚህ የሐዋርያት ትምህርት ተነሥተው ሊቃውንት አባቶቻችን ስለ ጌታችን ዕርገት አምልተው አስፍተው አጉልተው ጽፈዋል፡፡
ሠለስቱ ምዕትም /318ቱ ሊቃውንት/ “ታመመ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ መንግሠቱም ፍጻሜ የለውም” ጸሎተ ሃይማኖት፡፡
“በእርሱ ዕርገት በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ዕርገት ታወቀ” ስንክሳር ግንቦት 8፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

*ንስር ሠራሪ
*ልዑለ ስብከት
*ምድራዊው መልዐክ
*ዓምደ ብርሐን
*ሐዋርያ ትንቢት
*ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
*ኮከበ ከዋክብት

=>በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር::

=>ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን:: ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን::

=>ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ)
3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ

=>+"+ በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ: የእናቱም እህት: የቀለዮዻም ሚስት ማርያም: መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር:: ጌታ ኢየሱስም እናቱን: ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት:: ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው:: ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት:: +"+ (ዮሐ. 19:25)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+

+በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት
መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ
ሐዋርያ ነው::

+ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ
ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን
ይታወቃል ቢሉ
እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ
እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ
በቅርጫት ውስጥ
አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው
ነበር::

+ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል::
በባልንጀሮቹ
ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ
ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት
ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር::

+በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል
የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ
የጠራበት አንዱ
ምክንያትም ይሔው ነው::

+ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ
ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም
ይተክዝ
ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን
አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል::

+ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን
ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት
ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል
አመስግኖታል::

+ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር
ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ
ቅዱስም ሰክሮ ብዙ
አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ
ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::

+የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ
ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ
ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ
አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል::
በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል::
በገድለ
ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው
በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች
በመጨረሻ
ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::

❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን
ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን::
ከበረከቱም አይለየን::

=>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ
3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት
4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና

=>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 15-ከዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ስምዖን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡ እርሱም ናትናኤል ተብሎ የሚጠራ የገሊላ አውራጃ የቃና ሰው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት በላይኛው ግብፅ በመደራ አውራጃ የሚኖሩ 400 ሰዎች በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን በከሃድያን ተይዘው ብዙ ሲሠቃዩ ከኖሩ በኋላ በከሃዲው ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት መጨረሻ አንገታቸውን በመሰየፍ ሰማዕትነታቸውን የፈጸሙ ናቸው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል፡- ሐዋርያው ናትናኤል በሌላኛው ስሙ ስምዖን እየተባለም ይጠራል፡፡ ናትናኤል ብሎ የሰየመው ጌታችን ነው፡፡ የተወለደው በናዝሬት ቃና ዘገሊላ ሲሆን ከነገደ ብንያም ነው፡፡ የትውልድ ዘመኑ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ሄሮድስ ዕሜአቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ የቤተልሔም እልፍ ሕፃናትን በሚያስፈጅበት ጊዜ የናትናኤል እናቱ ከበለስ ሥር ደብቃ አትርፋዋለች፡፡
ፊሊጶስ ናትናኤልን ጠርቶት ወደ ጌታችን ካመጣው በኋላ ናትናኤል ጌታችንን ‹‹ወዴት ታውቀኛለህ?›› ሲለው ጌታችንም ‹‹ፊሊጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ሥር ሳለህ ዐውቅሃለሁ›› በማለት ከሕፃንነቱ ጀምሮ የጠበቀው አምላኩ እርሱ መሆኑን ነግሮታል፡፡ ቅዱስ አውግስጢኖስ ናትናኤል ምሁረ ኦሪት እንደነበር ጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም ፊሊጶስ ሲጠራው ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር አይወጣም›› በማለት የነቢያትን ቃል የጠቀሰው የመጻሕፍትን ቃል በማወቁ ነው፡፡ ዮሐ 11፡44-52፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል በባቦሎን፣ በሶርያ፣ በግብፅና በኑቢያ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ብዙውን የአገልግሎት ጊዜውን ያሳለፈው በሰሜን አፍሪካ ነው፡፡ በግብፅ ሲያስተምር አማኞች በመብዛታቸው አረማውያን ቀኑበትና በሐሰት ‹‹ሕዝቡ የማይፈልገውን ሃይማኖት ያስተምራል›› ብለው በከንቱ ከሰሱትና ከንጉሡ ፊት ለፍርድ አቅርበው በሐሰተኞች አስመስክረው ሐምሌ 10 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሟል፡፡ ይኽችም የዛሬዋ ዕለት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ናት፡፡ የሐዋርያው ስምዖን ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
(ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ፣ ግንቦት፣ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ-ማኅበረ ቅዱሳን ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በዝማሬ ማኀቶት channale
የምንሰጣቸው አገልግሎት
1, አዳዲስ ዝማሬ
2, መዝሙር በትግሪኛ
3, የየለቱ ስንክሳር
4, ዝማሬ በኦሮሚኛ
5 , የvoic ዝማሬ በመዘምራን
6, ትረካ
እና የተለያዮ መረጃዎችን እንሰጣለነ
ኦርቶዶክስ ተወህዶ የሆነ ብቻ ሼር ያድርግ
ለማያውቁአሳቁ
/channel/zemaritederosyosife

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✤ ‹‹አትማረኝ›› ዋሻ፤ ከአቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንድ ተራራ ሥር ደግሞ ‹‹አትማረኝ›› ዋሻ የሚባል አለ፤ ይህ ዋሻ ለብዙ ዘመናት አንድ ታላቅ አባት የጸሎት በዓት አድርገውት ‹‹ማረኝ ማረኝ›› የሚለው ጸሎት ጠፍቶባቸው ‹አትማረኝ›› እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ያሳይ እንደ ጀልባ በሚጠቀሙበት አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ፣ አትማረኝ፣ አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?›› አሏቸው፡፡ ያም አባት ‹‹አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው ‹አትማረኝ› እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው›› በማለት መለሱላቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ‹‹እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው ‹ማረኝ› እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው በድንጋይ ጀልባቸው ወደ ገዳማቸው ይመለሳሉ፡፡ ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም ‹‹ማረኝ›› እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ ያሳይ ድንጋዩን እንደጀልባ ተጠቅመው እየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸው እኛ አባት በውኃ ላይ በእግራቸው እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፤ እባክዎን እንደገና ያስተምሩኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ያሳይም፤ ሐይቁን በእግራቸው እየረገጡ ሳይሰጥሙ እስኪሄዱ ድረስ ጽድቃቸው የተገለጠውን የእኚህን አባት መብቃት ተመልከተው ‹‹አባቴ እግዚአብሔር የሚመለከተው የልብ ነውና እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል›› ብለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡
ጌታችንም "ወዳጄ! ስለ ድካምህ: ደጅህን የረገጠውን: መታሰቢያህን ያደረገውን: በስምህ የተማጸነውን ሁሉ ከነ ትውልዱ እምርልሃለሁ" ብሏቸው ነፍሳቸውን አሳረገ:: አበውም ሥጋቸውን ገንዘው እዚያው መንዳባ መድኀኔ ዓለም ውስጥ ቀበሩት:: ዐጽማቸው ዛሬም ድረስ ይገኛል:: (ክብረ በዓላቸውም ያረፉበት መስከረም 14ትና በመሠረቱት በመጋቢት 27 በጥንተ ስቅለት በመድኀኔዓለም ቀን እጅግ በጣም ደምቆ ይከበራል፡፡)
ምንጭ፤ *የቃል አስረጅ የገዳሙ አበምኔትና የገዳሙ መነኰሳት (በተለይም አባ ኀይለሚካኤል ያሳይ)፤
*የቅዱሳን ታሪክ፣ ገጽ 152፤
*ሐመር 21ኛ ዓመት ቊ.11፣ 2006 ዓ.ም፤
*ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet እና Dn Yordanos Abebe መጽሐፈ ገጽ (Facebook)
(ከቦታው ድረስ በመሄድና ከአበውና ከተለያዩ መጻሕፍት ይህንን ጽሑፍ ላዘጋጀልን የሰ/ትቤታችን አባል አቡነ ያሳይ ይስጡልን፡፡)
አምላከ አበው(ያሳይ ዘመንደባ) በበረከት ረድኤት ይጠብቀን፤ ፍጻሜያችንን ያሳምረው፡፡
ከአበው በረከት፤ ከሥላሴ ልጅነት አያናውጠን፡፡
የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍ/ሕ/ሰ/ት/ቤት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ (ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ ይጓጓዙ ስለነበር /ማን እንደ አባ የተባለላላቸው፤ ከ7ቱ ከዋክብት ቅዱሳንና ከ7ቱ ከዋክብተ ጣና ከኹለቱም ወገን የሚመደቡ) የዕረፍታቸው ዕለት ነው፤ መድኀኔዓለም አምላካችን ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
/ስዕሉ 1ኛ አቡና ያሳይ በጣና ባሕር ላይ እንደሔዱ የሚያሳይ፣ 2ኛ ጻድቁ እንደ ታንኳ ይጠቀሙበት የነበረው ድንጋይ ዛሬ በገዳሙ ቅጽር ግቢ የሚገኝ፣ 3ኛ መንደባ መድኀኔዓለም ገዳም (የጻድቁ አጽም ያረፈበት) 4ኛ የአቡነ ኒቃላዎስ አጽም ያረፈበት ቤት/
አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፡- አቡነ ያሳይ ‹‹ሰባቱ ከዋክብትና›› ‹‹ሰባቱ ከዋክብተ ጣና›› ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡
ልዩ ማስታወሻ፤ በብዙ የታሪክ መጻሕፍት ላይ ሰባቱ ከበዋክብት (ሰባቱ ቅዱሳን)፤ እና ሰባቱ ከዋክብተ ጣናን ያዛቧቸዋል፤ እንደዚሁም 5ቱ ከዋክብትን እንዲሁ ያዛቧቸዋል፤ ትክክለኛው ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጠነዋል፤
✤✤ ፯ቱ ከዋክብተ ጣና፤ በመባል የሚጠሩት አባቶችም (የጣናን ባሕር በእግራቸውና በልዩ ልዩ ልዩ ተዓምራት ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን በደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው)፡፡ እነዚህም፤
፩. አቡነ በትረ ማርያም ዘዘጌ
፪. አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
፫. አቡነ ታዴዎስ ዘደብረ ማርያም
✣፬. አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጐጉቤን
፭. አቡነ ያሳይ ዘመንደባ(ዘማን እንደ አባ መድኀኔዓለም)
፮. አቡነ ኖብ ዘጎርጎራ
፯. አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላ
✤✤ ፯ቱ ከዋክብት (፯ቱ ከዋክብተ ኢትዮጵያ)፤ በአቡነ መድኀኒነ እግዚእ እጅ የመነኰሱ ፭ቱ ከዋክብት እና እንዲሁም ሌሎች በአንድ ቀን ምንኵስናን የተቀበሉ ፯ቱ ከዋክብት፤ ሰባቱ ቅዱሳን በመባል የሚጠሩ ቅዱሳንን አመንኵሰዋል፡፡ እነዚህም፤
✤✤ ፯ቱ ከዋክብት በመባል የሚጠሩ ቅዱሳን፤
፩. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፪. አቡነ ሳሙኤል ዘቈየጻ
፫. አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ
፬. አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቋ
፭. አቡነ ያሳይ ዘመንደባ (ዘማን እንደአባ መድኃኔዓለም)
፮. አቡነ ታዴዎስ ዘባልተዋር
✣፯. አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጐጉቤን፤
ለቡ!፤ አቡነ ያሳይ ዘመንደባ(ዘማን እንደአባ) እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጐጉቤን ከሰባቱ ከዋክብት፤ እና ከሰባቱ ከዋክብተ ጣና ከሁለቱም ገብተው ይቈጠራሉ፡፡
እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኵሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኰሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ታላቁን ገዳም ደብረ በንኰልን (አኵሱም አጠገብ) መሥርተው፤ ያስተማሯቸውና ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቊጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን ያመነኰሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት፡፡
አቡነ መድኃኒነ እነዚህንም ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኵሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል(ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ ነበር)፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ እንዲሁም እነዚሁ ቅዱሳን በአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ መላዋን ኢትዮጵያን በወንጌል ኮከብ ብርሃንነት አብርተዋታልና፤ በእነዚህ ምክንያት አንድ ላይ የመነኰሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
✤✤ ፭ቱ ከዋክብት በመባል የሚጠሩት
፩. አቡነ አሮን ዘክቱር
፪. አቡነ መርቆሬዎስ ዘዶባ
፫. አቡነ ዘካርያስ ዘኬፋ
፬. አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘዳኅና
፭. አቡነ ዳንኤል ዘጸዐዳ
ከላይ ካየናቸው ፯ቱ ከዋክብተ ጣና፥ ፯ቱ ቅዱሳንና፥ ፭ቱ ከዋክብት መካከል ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፣ በአጽፋቸው (በልብሳቸው) እንደጀልባ ተጠቅመው የሚጓዙ አሉ፤ በየብስ ላይ ኾነው መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ……. ዛሬ መስከረም 14 ክብረ በዓላቸው የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው እንደ ጀልባ የሚጓጓዙ ናቸው፡፡
አቡነ ያሳይ፤ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፤ በዚህም ምክንያት በጣና ከተደረጉት ተዓምራት ማን እን አባ ያሳይ ይኾናል የሚሰጥመውን ድንጋይ ሳይሰጥም እንደ ጀልባ አድርጎ መጓዝ ብለው አበው ገዳሙን ‹‹ማን እንደ አባ ያሳይ /ማንዳባ(መንደባ)/ ብለው ሰየሙት፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ፥ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በገሃድ ተልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ(ዋልድባ) ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሏቸውን በዚያ ፈጸሙ፡፡
ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel