ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu
༒ Dn Wegen ༒
+ የወይን ጠጅ ጠግበዋል +
‹በዓለ ሃምሳ› እስራኤል ከግብፅ የፋሲካን በግ አርደው ከወጡ ከሃምሳ ቀን በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ በሲና ተራራ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ የተጻፈ ሕግን የሠጠበት ዕለት ነው፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶ ከግብፅ ሳይሆን ከሲኦል ባርነት ፣ ከፈርዖን ሳይሆን ከዲያቢሎስ አገዛዝ ነፃ የወጣን እኛ ክርስቲያኖችም የጌታችንን ትንሣኤና የሐዲስ ኪዳኑን ፋሲካ ባከበርን በሃምሳኛው ቀን ልክ እንደ አይሁድ ልማድ በዓለ ሃምሳን እናከብራለን፡፡ ለዚህ ምክንያታችን ግን ከፋሲካ ነፃነት በኋላ በሃምሳኛው ቀን ለሙሴ በጽላት ላይ የተጻፈ ሕግን የሠጠው አምላክ በሐዋርያት ልብ ውስጥ በቅዱስ መንፈሱ አዲስቱን የወንጌል ሕግ የቀረጸበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡
በዚህች ዕለት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ሐዋርያት እንደ ደብረ ሲናው ነቢይ ሙሴ በፈጣሪ ‹በአንተ ካለው መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ› ተብሎ የተነገራቸውና ከእነርሱ ተወስዶ የሚሠጥባቸው አልነበሩም:: (ዘኁ 11:17) ሐዋርያት የተሠጣቸው መንፈስ ለሌላው ሲሠጡ እንደ ሻማ ብርሃን ለሌላው ቢለኮስ የማያልቅና እየጨመረ የሚሔድ ከሙሴ የሚልጥ ጸጋ ያላቸው ናቸውና ቤተ ክርስቲያን በዓለ ሃምሳ የተሠኘውን የደብረ ሲና በዓል ወርሳ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
ለነገሩ የሚገርመው ለሐዋርያት የተሠጣቸው ለሙሴ ከተሠጠው ባይበልጥ ነበር፡፡ ሙሴ እኮ የተከራከረው ከፈርዖን ጋር ነበር ፣ ሐዋርያት ግን ከዲያቢሎስ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን ውጊያቸውን አይቶም ነው እንደሙሴ ለኮልታፋ አንደበታችሁ አሮንን ልኬላችኋለሁ በማለት ፈንታ መንፈስ ቅዱስ አንደበት አድርጎ የሠጣቸው (መንፈስ ቅዱስ አሮን ይኩነኒ አፈ አለ ደራሲው!) እነርሱ የተሠጣቸው ኮልታፋን አንደበት የሚያቃና ብቻ ሳይሆን ሰባ ሁለት አዳዲስ ቋንቋዎችን እንደ ተወለዱበት ያህል የሚያናግር መንፈስ ነበር፡፡ ስለዚህ በዓለ ሃምሳ ከኦሪት ይልቅ ለሐዲስ የሚስማማ በዓል ነው፡፡
★ በሌላ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር ★
እግዚአብሔር ዛሬ በሰናዖር ሜዳ የበተነውን የዓለም ቋንቋ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰበሰበው፡፡ በቋንቋና በዘር የማትገደብ የሁሉ ቤት ትሁን ዘንድ የጠራትና ቤዛ የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደተወለደች አፏን ፈትታ በዓለም ቋንቋዎች ሁሉ መራቀቅ ጀመረች፡፡ አዲሶቹ ጳጳሳትና ካህናትዋ በቋንቋው ሁሉ እየተናገሩ ሁሉ ‹የገሊላ ሰዎች አይደሉም እንዴ እንዴት የተወለድንበትን ቋንቋ ይናገራሉ?› እያለ የሚያደንቃቸው ሆኑ፡፡
በእርግጥም ቤተ ክርስቲያንና ካህናት በአንድ ቋንቋ አጥር መታጠር ፣ በአንድ አካባቢ ሰው ብቻ መደመጥ አያምርባቸውም፡፡ ለዓለም የሚያበራ የወንጌል ብርሃን ይዘው ለተወለዱበት ቀዬ ብቻ ቢያበሩ ወይም ቢጨነቁ ምኑን ካህናት ሆኑ? አብርሃም የብዙኃን አባት ለመሆን የወገኖቹን ሀገር እንደተወ የብዙኃን አባት የሚሆን ካህንም ወገኑን ትቶ ካልወጣ አብራም (የጥቂቶች አባት) እንጂ አብርሃም (የብዙኃን አባት) መሆን አይችልም፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አገልጋዮችዋን ከቋንቋ እስራት ፈትታ ነጻ አወጣቻቸው፡፡ የገሊላውን ዓሣ አጥማጅ ጴጥሮስን በግሪክ ቋንቋ እያናገረች ፣ ሌዋዊውን ማቴዎስ በአረቢኛ እያራቀቀች ያለ ልምምድ ዓለምን የምትማርከዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተወለደች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከቋንቋና ከነገድ ከጎሣ እስራት የተፈታችበት ይህ ዕለት ‹የቤተ ክርስቲያን ልደት› ተብሎ ከተጠራ ቤተ ክርስቲያን መልሳ ዘር ቆጠራ ውስጥ የገባችበት ዘመን ምን ተብሎ ሊጠራ ይሆን?
★ ክርስቶስን በበዓለ ሃምሳ ስናስበው ★
በእርግጥ በዓለ ሃምሳ ጌታችን ካረገ ከዐሥር ቀናት በኋላ የተፈጸመ በመሆኑ በዚህ ዕለት በቃሉ መሠረት መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያቱ የላከበት ቀን ነው፡፡ ይሁንና ከሐዋርያቱ የማይለየውን ጌታ በዚህች ዕለት ሲያርግ አንጋጥጠው ፈዝዘው ካዩት ሐዋርያት ጋር ዋሊያ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ እየናፈቅን ለአፍታ እናስታወሰው፡፡
ጌታችን በዛሬው ዕለት የሦስት ዓመት ተማሪዎቹን እንደየአቅማቸው የሃያ ፣ የሠላሳ ፣ የሃምሳ ፣ የሰባ ቋንቋ ተናጋሪዎች አደረጋቸው፡፡ ከዓሣ አጥማጅነት የጠራቸውን ፣ ከተናቁበት የሰበሰባቸውን የገሊላ የገጠር ሰዎች ከአይሁድ አልፎ በዓለም የታወቁ ወደር የማይገኝላቸው የቋንቋ ሊቃውንት አደረጋቸው፡፡ እርሱ ሲገልጥ ልምምድ አያስፈልግምና በእግዚአብሔር የተማሩት ምስኪኖች የዓለምን ጠቢባን የሚያሳፍሩ ምሁራን ሆኑ፡፡ አጋንንት በተገዙላቸው ጊዜ "ጌታ ሆይ አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ብለው ሊነግሩት የሮጡት ደቀ መዛሙርቱ ጌታ ቀድሞ ባያርግ ኖሮ ዛሬ ወደ እርሱ እየሮጡ "ጌታ ሆይ በመንፈስህ ቋንቋ ሁሉ ተገለጠልን" ብለው በደስታ በነገሩት ነበር።
እዚህ ላይ የጌታን ፍቅሩ እንናገር ወይንስ ትሕትናውን? ከትሕትናው ከጀመርን ለሐዋርያቱ እስከ ሰባ ቋንቋ ገልጦ ያራቀቃቸው ጌታ ለሠላሳ ሦስት ዓመታት በምድር ሲመላለስ በአንድ ቋንቋ ብቻ መናገሩ ምንኛ ይደንቃል? ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ለፍጥረት ቋንቋን የሠጠ ፣ በሰናዖር ሜዳ ቋንቋን የበተነ እርሱ የዕብራይስጥን ፊደል ሊማር ከመምህር እግር ሥር ተቀመጠ›› ብሎ ያደነቀውን ጌታ ስለ ትሕትናው እናድንቀው፡፡ እርሱ ሁሉን ቋንቋ የሚያውቅ የሚሰማ ሆኖ ሳለ በአንድ ቋንቋ ብቻ መወሰኑ እንዴት ያለ ትሕትና ነው፡፡ እኛ አጥርተን የማናወራው እንኳንም ቢሆን የምናውቀው ሌላ ቋንቋ ያለ እንደሆን በየዐረፍተ ነገሩ እያስገባን እውቀት በዝቶ እንዳስጨነቀው ስንሆን ሁሉን አዋቂው ጌታ ግን በትሕትና አንድን ቋንቋ ብቻ ተናገረ፡፡
ምስኪኖቹን የገሊላ ሰዎች ሐዋርያትን በብዙ በማያውቁት ቃል እየተናገረ አላስጨነቃቸውም፡፡ ‹የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም ፤ መንፈስ ቅዱስን እልክላችኋለሁ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል› ብሎ አቆይቶ በዛሬው ዕለት ግን ቋንቋን ከእውቀትና ከድፍረት ጋር ሠጣቸው፡፡ ‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከዚያም የሚበልጥ ያደርጋል›› ብሎ ያስተማረ ጌታ በእርሱ ለሚያምኑ ደቀመዛሙርቱ እርሱ ያላስተማረበትን ብዙ ቋንቋ እንዲናገሩ አደረጋቸው፡፡ (ዮሐ. 14፡12)
ፍጡራን መምህራን ደቀመዛሙርቶቻቸውን ራሳቸውን አስመስለው ያደርሱ ይሆናል እንጂ ከራሳቸው በላይ አላደረጉም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ብቻ ለተማሪው ‹በእኔ ላይ ያደረ መንፈስ እጥፍ ድርብ ይሁንብህ› ብሎ በፍጡር አቅሙ መጎናጸፊያውን ወደ ሰማይ ሲወሰድ ላየው ኤልሳዕ ሰጥቶት ነበር፡፡ ፈጣሬ ልሳናት ክርስቶስ ግን አንጋጠው ሲያርግ ላዩት ሐዋርያት በእርሱ ሕያው ሆኖ የሚኖር መንፈስ ቅዱስን በላከላቸው ጊዜ እርሱ መናገር ሲቻለው በትሕትና ያልተናገረውን ብዙ ቋንቋ እንዲናገሩ አደረጋቸው፡፡
ይቀጥላል..........
#ግንቦት_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የማርያና የማርታ ወንድም #ጻድቅ_አልዓዛር አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ዮሐንስ
ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ደግ የተማረም ነበር። ከልጅነቱም ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ነበር። ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። የትሩፋቱና የዕውቀቱም ዜና በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ እግዚአብሔርም በዘመኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን አጸና።
ይህ አባት በተሾመበት ወራት ደግ ምእመን አንስጣስዮስ የሚባል ንጉሥ ነበር። በአንጾኪያም የከበረ አባት አባ ሳዊሮስ ነበረ እርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲህ ብሎ በመልእክቱ ውስጥ ጻፈ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶው በኋላ እንደ አባቶቻችን እንደ አባ ድሜጥሮስና እንደ አባ ዲዮስቆሮስ እምነት ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ ያለ መለያየትና ያለ መጨመር አንዲት ባሕርይ አለችው።
አባ ዮሐንስም መልእክቱን ተቀበለው ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ተለያይተው የነበሩ ሕዋሳትም ተመልሰው አንድ ስለ ሆኑ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት።
ከዚህም በኋላ ለመልእክቱ መልስ አባ ዮሐንስ ለአባ ሳዊሮስ እንዲህ ብሎ ጻፈለት። ይኸውም ስለ መለኮትና ትስብእት የአንድ ባሕርይ ህልውና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ያለ መለያየት ያለ መቀላቀልና ያለ መለወጥ ሁለት ያይደለ የሰውን ባሕርይ ከመለኮቱ ባሕርይ ጋራ አንድ አድርጎ በመዋሐድ ሰው ስለ መሆኑ።
ጌታችንንም የሚከፋፍሉትን ወይም ተጨመረበት የሚሉትን ወይም ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚሉትን በመለኮቱ ባሕርይ መከራ ተቀበለ የሚሉትን አወገዘ። የቀናች ሃይማኖትስ ይቺ ናት እግዚአብሔር ከእኛ በነሣው ሥጋ ስለ እኛ መከራ እንደ ተቀበለ እናውቃለን እኮን። ይቺም የሚጓዝባት የማይሳሳትባትና የማይደናቀፍባት የሕይወት መንገድ ናት አለ።
አባ ሳዊሮስም ይቺን የአባ ዮሐንስን መልእክት በአነበባት ጊዜ በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በአንጾኪያ አገርም ሰበከባት ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመካከላቸው ሰላም ፍቅርና ስምምነት ሆነ። ይህም አባት ሕዝቡን እያስተማረ ዐሥራ አንድ ዓመት ኑሮ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቅ_አልዓዛር
በዚችም ዕለት የማርያና የማርታ ወንድም ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኃኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ።
አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ በሰላም በፍቅር አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
Enkuwan ለጰራቅሊጦስ beal beselam aderesachu aderesen
Читать полностью…🥰🥰🥰በ1 ጉዞ ሁለት ገዳማትን
ታላቅ መንፈሳዊ ደርሶ መልስ ጉዞ ሰኔ 4 እሁድ
1, አርቱ አርሴማ
2, ካህኑ መልከ ጼዴቅ ( በኢትዮጵያ ብቸኛው ገዳም )
ለመመዝገብ በውስጥ መስመር አናግሩኝ🥰🙏
🥰🥰🥰በ1 ጉዞ ሁለት ገዳማትን
ታላቅ መንፈሳዊ ደርሶ መልስ ጉዞ ሰኔ 4 እሁድ
1, አርቱ አርሴማ
2, ካህኑ መልከ ጼዴቅ ( በኢትዮጵያ ብቸኛው ገዳም )
ለመመዝገብ በውስጥ መስመር አናግሩኝ🥰🙏
✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+
=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::
+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::
+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::
+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)
+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-
1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::
+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::
+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::
+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::
+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::
+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::
+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::
+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::
=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::
=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ እንዲገርፉትና እሾህ ባላቸው በብረት ዘንጎችም እንዲደበድቡት ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ጌታችንም በመልአኩ እጅ አጽንቶ አዳነው ጤነኛም ሆነ። ሕዝቡም ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አረፉ። ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ነው። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።
እነሆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸለትና እንዲህ አለው። ብፁዕ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ እኔ ፈጣሪህ ክርስቶስ ነኝ እነሆ መቀመጫህን ከቅዱሳን ጋራ በሰማያት አዘጋጅቼልሃለሁ። በእውነት እነግርሃለሁ በመታሰቢያህ ቀን መከራ ድካምህን አስቦ መሥዋዕት ለሚያቀርብ ለድኃ ምጽዋትን ለሚሰጥ በእንስሶቹ ውስጥ ርባታ ይሆናል። በቤቱም የተባረከ ልጅ አይታጣም ሰይጣንም በእርሱ ላይ በሥራውም ሁሉ ላይ ሊበረታታበት አይችልም።
የገድልህን መጽሐፍና ስምህን የሚጽፈውንም እኔ በሕይወት መዝገብ ስሙን እጽፋለሁ የዕዳ ደብዳቤውን እደመስሳለሁ። ደግሞ በችግር በመከራ ውስጥ ስምህን ጠርቶ የሚለምነኝን ከመከራዉ ሁሉ እኔ አድነዋለሁ። መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ በደሉን ሁሉ እተውለታለሁ ሰላሜም ከአንተ ጋራ ይሁን ይህንንም ብሎ መድኃኒታችን ከእርሱ ዘንድ ዐረገ።
የከበረ አባ ኄሮዳም ፍጹም ደስታን ተደሰተ። ተጋድሎውንም በሚፈጽምበት ጊዜ በዚያ ወደ አሉት ሕዝብ ተመልሶ ከውስጣችሁ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ያለ ከሆነ ሥጋዬ በጎ በረከትን እስከሚያደርግለት ድረስ ሥጋዬን ወስዶ በእርሱ ዘንድ ያኑረው አላቸው።
ያን ጊዜም አንገቱን ዘረጋላቸው በሰይፍም ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም በግንቦት ወር በሃያ አምስት ቀን ተቀበለ። ከሦስት ወር በኋላም ዘመዶቹ መጡ ሥጋውንም ወሰዱ ተሸክመውም ወደ ሀገሩ ስብስጣ አድርሰው በአነፁለት ቦታ አኖሩት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ለድውያን ፈውስ ተገኘ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኄሮዳ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለኄሮዳ እግዚአብሔር ዘሐወጾ። ከመ የሀቦ ኪዳነ በኢሐስዎ ወዐምዖ። ለዝ መዋዒ ትግርምተ መኰንን ኢያደንገፆ። በብልሐ ቅትራት አመ ገቦሁ ደጐዖ። በአእዳወ ኅፂን ካዕበ እንዘ ይጸፍዕ ገጾ።
ሰላም ዕብል ለሠለስቱ እልፍ። እለ በማኅፄ ተገምዱ ወበአፈ ሰይፍ። ሰሚዖሙ ቃለ እንዘ ይትናገር በአፍ። ዐቃቤ ኄሮዳ እንተ ተሠይመ ለዘልፍ። ፍጡነ ረድኤት ሚካኤል ዖፍ።
፨፨፨
=>በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን የዮሴፍን በትሮች በአረንጓዴ ቦታ ላይ ተከለ ወዲያው ዛፎች ሆኑ። ደግሞ የከበሩ በላኖስ እሎንትራን ራምኔሳ መቶ ኃምሳ ሰማዕታት ቈስጠንጢኖስና እናቱ ሔላም መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
=>ግንቦት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት)
2.ታላቁ አባ ሔሮዳ ሰማዕት
3."30,000" ሰማዕታት (የአባ ሔሮዳ ማሕበር)
4.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
5.ቅዱስ ቅብዐ ሜሮን
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
=>+"+ ሰንበትም ካለፈ በሁዋላ መግደላዊት ማርያም: የያዕቆብም እናት ማርያም: ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ። ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በሁዋላ ወደ መቃብር መጡ . . . ወደ መቃብርም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል አዩና ደነገጡ። እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ። ተነስቷል: በዚህ የለም . . . አላቸው። +"+ (ማር. 16፥1-8)
፨፨፨፨
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፨፨፨፨
( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወሰ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡
ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
Watch "የመርቆሬዎስ ድንቅ ዝማሬ በዘማሪት ረድኤተ አምላክ (ቁጥር 1)ዝማሬዋ" on YouTube
https://youtu.be/3Cn3SW71fow
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ።
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ።
😭😭😭 ይህን ጸሎት እንዴት መጸለይ እንችላለን? እግዚአብሔር ይቀደስበት ዘንድ ህሊናችንን መቼ አዘጋጀነው?
አስተሳሰባችንን ሳንቀድስ! በህሊናችን ዝሙትን እያሰላሰልን እንዴት አምላካችንን ስምህ በህሊናችን ይቀደስ እንለዋለን?
በአለባበሳችን ሳንቀደስ! በአለባበሳችን ክርስቲያን አሰዳቢ ሆነን በጸጉር ቀለም፡ በጥፍር ቀለም፡ በፊት ቀለም፡ ጸጉር በመቀጠል፡ የዲያብሎስን ግብር እየፈጸምን እንዴት በሰውነታችን ስምህ ይቀደስ ብለን እንጸልያለን?
በሃገራችን በቤተክርስቲያናችንን መከራ ያበዛንባት እኛው ክርስቲያኖች ነን። ለውጥ ማምጣት የምንችለውም በማንም ላይ ጣታችንን ሳንቀስር ራሳችንን መለወጥ ስንችል ነው። እንቁላል ራሱ ቅርፊቱን ከሰበረ ህይወት ያለው ጫጩት ይሆናል። ከውጪ ከተሰበረ ግን ህይወት የሌለው ፈሳሽ ሆኖ ይቀራል።
ልዑል እግዚአብሔር ይቀደስበት ዘንድ የሚያርፍበት ህሊና እና ሰውነት አጥቷል። ስለዚህ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ከማለታችን በፊት ስሙ ይቀደስበት ዘንድ ራሳችን ዝግጁ መሆናችንን እንፈትሽ።
የልዑል እግዚአብሔር የስሙ መቀደሻ መቅደሶች ለመሆን ህሊናችንን ሰውነታችንን ይቀድስልን። ለዚህ እንድንዘጋጅ ልቦናችችንን ያንቃልን። አሜን።
እንዴት አመሻቹህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እባካችሁ ይህንን 👉 https://youtube.com/channel/UCAe0Vv9bIkCTTkeilxcUoYQ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ፫ 🙏🙏🙏
Читать полностью…༒ Dn Wegen ༒
+ እርግጠኛ ነበርኩ +
ከአንድ ከባድ ጦርነት በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡
አለቃውም "ይኑር ይሙት ለማይታወቅ ሰው ብለህ
ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም"
በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡
ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋው በኋላ እጅግ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል።
አለቃውም በንዴት "ይሞታል ብዬህ አልነበረም?
ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ.. አንተ ራስህ ልትሞት እኮ ምንም አልቀረኽም?" በማለት ይወቅሰዋል፡፡
ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበርና ወቀሳውን ከምንም ሳይቆጥር አለቃውን "
አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም
ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሼ ያለኝን ብትሰማ እንዲህ ባልተናገርከኝ ነበር " ይለዋል።
አለቃውም "ምን አለህ?" ሲለው
ወታደሩም በፈገግታ እና በሀዘን
" እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ"
በእውኑ ልብ የሚነካ ጓደኝነት ነው። ወዳጄ ያንተስ ጓደኛህ የት ነው? በሀጢያት ሞቶ
" አረ እሱንስ ተወው ቢመጣም መንፈሳዊ ህይወት የለውም "
ተብሎ ተስፋ የተቆረጠበት በሜዳ ላይ የወደቀ ይሆን? ምን አልባት ልክ ሆኜ ከሆነ ከመሞቱ በፊት ተስፋ ያረጋሀልና ድረስለት ለምን ብቻህን ትኖራለህ እሱን ማታስበው እስከ መቼ ነው? ሄደህ ፈልገው ምን አልባት ብዙ መስዋት ያስከፍልህ ይሆናል ምን አልባትም ቆስሎ አልያም ሞቶ ታገኘው ይሆናል አንተ ግን ከመፈለግ አትስነፍ አንተ ብቻ እሱን ይዘኸው ለመምጣት ያብቃህ እንጂ እናትህ ቤተክርስቲያን ቢቆስልም ታክመዋለች ቢሞትም ሞትን ድል የነሳ ጌታ አሷጋ ነውና ከሞተ ታነሳዋለች ብቻ አንተ ይዘኽ ለመምጣት ያብቃህ!!
ወይስ ወዳጄ ወዳቂው ራሱ አንተ ትሆን?
ምን አልባት አንተ ራሱ ወዳቂው ሆነህ ከተገኘህ ሰዎች የሞተ ነው ተስፋ የለውም ብለውህ ከሆነ እኔ መፍትሔ ልንገርህ። አኪያ ብለህ ተጣራ መፍትሔ ታገኛለህ። አኪያ ማለት እግዚአብሔር ጓደኛዬ ነው ማለት ነው። አየህ ሰው ራሱን ራሱን እያለ ፈፅሞ ላያስታውስህ ይችላል ፈፅሞ የማይረሳ እግዚአብሔር ነውና እሱን ጓደኛ አድርግ እሱስ ይከብደኛል ካልከኝ እሺ ይሁን ለሁሉ አዛኝ የሆነች በርህራሄዋ ና በትህትናዋ አምላክን እስከ መውለድ የበቃች አንዲት የህያዋን እናት አለች። እሷን እናት አድርጋት
"ድንግል ሆይ አለም ከተባለች የጦር ሜዳ በኃጢያት ቁስል ወድቄ ለሞት ቀርቤያለሁና ድረሽልኝ። ድንግል ሆይ ወደ ልጅሽ መሄዱን መች ጠላሁ ነገር ግን በአለም ሀሳብ ዝዬ ደክሜያለሁ ለዚህም ደጋፊ ጓደኛ ረዳት የለኝምና እናቴ ሆይ ደግፊኝ። ከሁሉ የደከምኩ እኔን አስቢኝ ምነው ልጄን ብትጠይቀው ምትመጣበትን ጉልበት አይሰጥህም ትዪኝ ከሆነ አሱ መች ከበደኝ ነገር ግን በልጅ ፊት እንደኔ አይነት ሀጣኖች ፀሎታቸው ይሰማላቸው ዘንድ ሞገስ የላቸውምና አይቻለኝም ባይሆንስ በእግዚአብሔር ፊት ፀጋን የተሞላሽ ታናሿ ብላቴና አንቺ ነሽና በሱ ፊት ወዳጅህ ሜዳ ላይ ወድቋል ወደ አንተ መምጣት አቅቶታልና መምጣቱን ስጠው ብለሽ አደራ አሳስቢልኝ። ድንግል ሆይ እኔስ እንደ ኤልሳቤጥ በእግዚአብሔር ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ የሄድኩ ሆኜ አይደለም አንቺን ማውራቴ ይልቁንም ፅድቅ የሌለኝ በእግዚአብሔር ፊት የተዋረድኩ ነኝ
ግን ቢሆንም አዛኚት ነሽና እኔነቴን አይተሽ ፀሎቴን እንደማትተዪ አምኜ ነው አንቺን ማውራቴ። ድንግል ሆይ ከሰው ይልቅ ያንቺን እናትነት እሻለሁ እና ወዳለሁበት ነይ። ከቁስሌ እንድድን ምን አልባት ሞቼ ቢሆን እንኳን ልጅሽ አላዛር ከሞት እንዳነሳው ታነሽኝ ዘንድ እማፀነሻለሁ እንደ ምትመጪም ተስፋ አደርጋለሁ ""
ብለህ ተማፀናት ያኔ ፈጣኗ ደመና ሩሩህ የሚሆን ሚካኤልን ፍሱህ የሚሆን ገብርኤልን አስከትላ እንደ ዘመዳ ኤልሳቤጥ ልትጎበኝህ ተራራን አቋርጣ ትመጣልሀለች። አንተ ብቻ በእምነት በላት!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✍ ፀሀፊ ዲያቆን ወገን
ቃለ እግዚአብሔር በአቅሜ ለማድረስ እንደበረታ ስለኔ ፀልዪ።
ይህቺ ትንሽ ፅሁፍ ለሌሎችም ይዳረስ ዘንድ Share በማድረግ አግዙኝ🙏
እናንተም ቤተሰብ ይሁኑን የሚለውን በመጫን የ telegram ፔጁን join አድርጉ🙏
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ሐዋርያት ዮልዮስና አፍሮዲጡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
✞✞✞ ዮልዮስ ወአፍሮዲጡ ሐዋርያት ✞✞✞
=>ቅዱሳን ሐዋርያትና አርድእት በቁጥር 84 ቢሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪኩ በዝርዝር የተጻፈለት ቅዱስ ዻውሎስ ነው:: የሌሎቹ አልፎ አልፎ የተጠቀሰ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግን የት እንደ ደረሱም አልተጻፈም::
+በዚሕ ምክንያት ወደድንም ጠላንም አዋልድ መጻሕፍትን መጠቀማችን አይቀርም:: ምክንያቱም "ሑሩ ወመሐሩ" ያላቸው ሁሉንም ሐዋርያትና አርድእት ነውና::
+የቅዱሳን ሐዋርያትን ሕይወት ከያዙ ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል በቀዳሚነት ዜና ሐዋርያትና ገድለ ሐዋርያት የሚጠቀሱ ሲሆን ስንክሳራችንም አልፎ አልፎ ያወሳቸዋል:: በዚሕም መሠረት ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከ72ቱ አርድእት የሚቆጠሩትን ቅዱስ ዮልዮስንና ቅዱስ አፍሮዲጡን ታከብራለች::
+ሁለቱም ከጌታችን እግር ሥር ለ3 ዓመታት ተምረው: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው: ከባልንጀሮቻቸው ሐዋርያት ጋር ለወንጌል አገልግሎት ሃገራትን ዙረዋል:: በሐዋርያት ሲኖዶስም ዽዽስናን ተሹመዋል::
+በአገልግሎት በነበሩባቸው የእስያና አውሮዻ ሃገራት አእላፍ ነፍሳትን ወደ ሕይወት ሲማርኩ ግፍን በአኮቴት ተቀብለዋል:: ከጌታቸውም የማይጠፋ የሕይወት አክሊልን ተቀዳጅተዋል::
+በተለይ ቅዱስ ዮልዮስ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር መከራን በመቀበሉ በሮሜ መልዕክቱ (16:7) ላይ አወድሶታል:: ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋርም በጣም ይዋደዱ ነበርና ትናንት እርሱን ገንዞ ቀብሮ በእንባ ወደ ጌታው ፀለየ:: ጌታችንም በማግስቱ (ማለትም ዛሬ) አሳርፎታል::
=>አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያቱ ትጋትና በረከት ያድለን::
=>ግንቦት 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮልዮስ (ዮልያን) ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ አፍሮዲጡ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱሱ ሕጻን ሰማዕት (በዘመነ ሰማዕታት ገና የ2 ወር ሕጻን ቢሆንም ጌታችን አፉን ከፍቶለት ክርስቲያን ነኝ በማለቱ ከእናቱ ጋር ተሠይፏል)
4.አባ አንስያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ታኦድራጦስ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.አባ ሳሙኤል
6.አባ ስምዖን
7.አባ ገብርኤል
=>+"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ: ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 23 በዚኽች ዕለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ወሰማዕት አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ ልደታቸው ነው።
አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፡- አባታቸው ካህኑ ሮማንዮስ የደብረ ሊባኖሱ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት ሲሆኑ እናታቸው ማርታ ይባላሉ፡፡ የትልድ ቦታቸው ጽላልሽ ዞረሬ ነው፡፡ ሐገራቸው ጽላልሽ ዞረሬ ድርቅ ሆኖ ረሀብ ጸንቶ የነበረ ቢሆንም ግንቦት 23 ሲወለዱ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ የታየ ሲሆን እርሳቸውም በብርሃን ልብስ ተጠቅልለው ታይተዋል።ቤታቸውም በበረከት ተሞልቶ ለሀገሬውም ዝናብ ዘንቦለታል፡፡ በተወለዱ በ40 ቀናቸው ክርስትና ሲነሱ የተዘራው እህል ሁሉ አንድ ሳይቀር አፍርቶ ተገኝቷል።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ለሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ በጽዮን ተሰጥተው ሃይማኖትን በሚገባ ተምረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት ተሻግረው ሞተሎሚን አስተምረው ካሳመኑት በኋላ አቡነ ታዴዮስን ወደ እርሳቸው እንዲመጡ ልከውባቸው ሄደው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ ዘጠኝ ዓመት ተቀመጡ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ግን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ አቡነ ታዴዎስም ወደ ጽላልሽ ተመልሰዋል፡፡ ሁለቱም ከ32 ዓመት በኋላ ተመልሰው በጽላልሽ ተገናኘተው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአቡነ ታዴዎስ ማዕረገ ምንኩስናን ሰጥተዋቸዋል፡፡
አቡነ ታዴዎስም በሥጋ ዕድሜ ታላቅ ቢሆኑም እንደታናሽ ብላቴና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ በደብረ ሊባኖስ ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ታዴዎስን ወደ ጽጋጋ እንዲሄዱ ነገሯቸው ምክንያቱም አቡነ አኖሬዎስ በዚያ ሲያስተምሩ ከሃዲያን ደብድበው አስረዋቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ታስረው ሳለ ወደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘንድ የሚላካቸው ሲያስቡ ቁራ መጥቶ ‹‹እኔ እላክሃለሁ›› ቢላቸው ‹‹ክፋትህ እንደ መልክህ ነው›› ብለው እምቢ አሉት፡፡ ርግብ መጥታ ‹‹እኔ እላክሃለሁ›› ብትላቸው ‹‹መጥተህ አድነኝ›› ብለው በክንፏ ላይ ጽፈው ልከዋት እርሷም መልእክቱን ለተክለ ሃይማኖት አድርሳ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው አቡነ ታዴዎስን ሕዝቡን ከኃጢአት ግዞት አኖሬዎስን ከእስራት እንዲያስፈቱ የላኳቸው፡፡
አቡነ ታዴዎስም በነፋስ ሠረገላ ተጭነው መዩጥ ከተባለውና አኖርዮስን ካሰራቸው ንጉሥ ፊት ቢደርሱ ንጉሡ በግንጋጤ መልአክ የመጣበት መስሎት ሲፈራ ከሰው ወገን መሆናቸውን ነግረው ክርስትናን አስተማሩት፡፡ ጋኔን ከእሳት ጥሎት ሲሠቃይ የሚኖርና ሊሞት የደረሰ ልጁን ቢፈውሱለት በትምህርታቸውና በተአምራታቸው አምኖ ሕዝቡ ክርስትናን እንዲቀበል በአዋጅ አስነገረ፡፡ አፍጃል የሚባለው ባለጸጋ ወደ አቡነ ታዴዎስ ቀርቦ ሲማር ‹‹ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል›› (ማቴ 19፡24፣ ማር 10፡25፣ ሉቃ 18፡25) የሚለውን የወንጌል ቃል ሲሰማ ለአእምሮው ረቆበት ‹‹እስቲ አድርገህ አሳየኝ?›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም እናቲቱን ግመል ከነልጇ ቀጥሎም 28 ግመሎችን በየተራ በመርፌ ቀዳዳ እያሾለኩ አሳይተውታል፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በእጅጉ ሲገረምና ‹‹በአምላከ ታዴዎስ ስም አምናለሁ›› ሲል የባለጸጋው ልጅ ሙሳ ግን ‹‹በምትሃት አሳይቶን ነው እንጂ የእውነት አይደለም›› በማለት አባቱንም እንዳያምን ይናገር ጀመር፡፡ ይህንንም ሲናገር በመጀመሪያ ያለፈችው እናቲቱ ግመል እረግጣ ገደለችው፡፡
አቡነ ታዴዎስም ንጉሡን፣ አባቱን አፍጃልንና ሕዝቡን የሞተ እንደሚነሣ ሲያስምሯቸው ‹‹የሞተ ይነሣልን? እስኪ ይህ የሞተው ልጅ ይነሳና ሁሉም አይቶ ይመን›› አሏቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ዛሬ ተቀብሮ ይዋልና ነገ በሦስተኛው ይነሣል›› ብለዋቸው ተቀብሮ ዋለ፡፡ በማግሥቱም አፍጃልን ጠርተው ‹‹‹አልዓዛርን ከሞት ባስነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ሆይ ና ውጣ› ብለህ ከልጅህ መቃብር ላይ አኑረው› ብለው ዘንጋቸውን ሰጡት፡፡ ሄዶም እንዳሉት ቢያደርግ ልጁ አፈፍ ብሎ ተነሥቷል፡፡ ይህንን ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እሳቸውም 12 አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸው ሞቶ የተነሳውን ሙሳን ሙሴ ብለው ሰይመው አስተምረው ሊቀ ካህናት አድርገው ሾመውት አቡነ አኖሬዮስን ይዘው ወደ ጽላልሽ ዞረሬ ተመልሰዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ አባ ያዕቆብ የተባሉ ጳጳስ ከግብፅ መጡ፡፡ የአቡነ ታዴዎስን ዜና ሲሰሙ ተደስተው ከአቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው አስጠርተዋቸው ‹‹የአባታችሁን ዜና ገድል ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም ‹‹ጨዋታ በአስተርጓሚ አይሰምርም›› ብለው ወደ ጌታችን ቢጸልዩ የጳጳሱ ቋንቋ ለታዴዎስ፣ የታዴዎስም ቋንቋ ለጳጳሱ ተገልጦላቸው የመሸ የነጋ ሳይመስላቸው 40 ጾምን ሲጨዋወቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጳጳሱ ከንጉሡ ተማክረው ‹‹ሊቀ ካህናት ዘጽላልሽ›› ብለው ሾመዋቸዋል፡፡
በነግህና በሰርክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ፣ ቀን ወንጌልን እየሰበኩ፣ ሌሊት ከባሕር ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ ሳለ ከ10 ዓመት በኋላ ሰይጣን በንጉሡ በዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አሳድሮበት በክፉዎችም ምክር አታሎት የአባቱን ቅምጥ አገባ፡፡ አቡነ ታዴዎስም ይህን ሲሰሙ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ገሥጸው አወገዙት፡፡ ገሥጸውና አውግዘው አቡነ ማትያስን አስከትለው ሲመለሱ ቅምጧ የንጉሡ ሚስት በፈረስ ተከትላ ደርሳ የኋሊት አሳስራ ዛሬ ‹‹ማርያም ገዳም›› ከሚባለው ቦታ ፊት ለፊት ካለው ትልቅ ገደል ውስጥ ሁለቱንም ጣለቻቸውና ጥር 29 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው ‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005 ዓ.ም ከኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያናቸው በታላቅ ክብር ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
የሰማዕታት አባቶቻችንን የአቡነ ታዴዎስ ወማትያስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
ይህች ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡
ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡
በዚያም ዕለት በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡
በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!
༒ Dn Wegen ༒
+ ብልጥ እንደ ይሁዳ +
👉 ጌታችን በዚህ ምድር ለ 3 አመታት እየተመላለሰ ሲያስተምር የተቻላቸው ቀኑን በሄደበት እየሄዱ ሲማሩ ያልቻሉ እንደ ኒቆዲሞስ ያሉ ደግሞ ሌሊት በሚያድርበት በደብረ ዘይት ዋሻ አብረው እያደሩ ይማሩ ነበር። ክርስቶስም ሁሉም እንደሚገባው ምሳሌ እየመሰለ ያስተምራቸውም ነበር።
ይሄንን ትምህርቱን በሚያስተምርበት ወቅት ከስሩ ማይለዪት ሐዋርያት ማጉረምረም ይጀምራሉ። ምክንያታቸውም ምግብ ካዩ 2 ቀናት ስላሳለፋቸው ነበር። ጌታም ሐዋርያቱን በደብረዘይት ሰብስቦ ""ለ2 ቀናት ያለምግብ እንደተማራችሁ አውቃለሁ አሁን ምግብ ከመመገባችሁ በፊት አንዲት ትምህርት ትቀራቸዋለች እሷን ተምራችሁ ትብላላችሁ " ይላቸዋል።
በዚህ ንግግሩ ግማሾቹ "ምግብ ትበላላችሁ የሚለን ከየት ሊያመጣ ነው አሳ እና እንጀራ እንዳበረከት እንዳያበረክት እጃጅን ላይ ምንም የለም ወይስ እንደ ሙሴ መና ሊያወርድልን ነው "" ሲሉ
ይሁዳ ደግሞ "ሁለት ቀን ያለ ምግብ መማሬ ሳያንስ አሁን ደግሞ ጭራሽ ሌላ ትምርት " እያለ ይበሳጭ ነበር።
ክርስቶስም ቀጥል አርጎ "አሁን ማስተምራችሁ ግን በቃል ሳይሆን በተግባር ነውና ለዚህ ደግሞ ሁላችሁም ድንጋይ ይዛችሁ ኑ " ብሎ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጣቸው።
ይሁዳ ነደደ "ጭራሽ ድንጋይ ተሸክሜ ልመጣ ነው ?!" ግን ምን ሊያደርግ አልቻለም ብኋላ ይሰጥሀል የተባለውን ምግብ ተስፋ አድርጎ ከወንድሞቹ ከሐዋርያት ጋር ለማምጣት ከተራራው ከመውረድ በቀር።
10ሩ ሐዋርያት ያቅማቸውን ያህል የታዘዙትን ተሸክመው ሲመጡ የጌታ ወዳጅ ጴጥሮስ ግን ጌታ ደስ ይበለው ብሎ የ2 ቀን ረሁቡን ወደ ጎን አድርጎ ከአቅሙ በላይ እየተጎተተ እየጎተተ ይዞ መምጣቱን ተያያዘው።
በአንፃሩ ይሁዳ ደግሞ አይበላው አይጠጣው አስተምሮ ለሚጥለው ድንጋይ ለምን ራሴን አደክማለሁ ብሎ የእጁን እልፍኝ የማትሞላ ድንጋይ ይዞ መጣ።
ክርስቶስም ሁሉ እስኪገቡ ጠብቆ እንዲህ አላቸው " ይህን ከመናገሬ በፊት አንድ ትዕዛዝ ልዘዛችሁ ሁላችሁም የየራሳችሁን ድንጋይ ያዙ አንዱ ለሌላው እንዳይሰጥ በሉ ርቧችሁ አልነበረምን? የያዛችሁት ድንጋይ ዳቦ ይሁን! "
ይሁዳ የሞት መርዶ የሰማ ሰው ይመሰል እጅግ ደነገጠ የያዛት ድንጋይ እንኳን ካለበት ረሀብ ልታወጣው ትንሽም ልታስታግስለት እንኳን ማትችል ነበረች። በአንፃሩ ጴጥሮስ የያዘው ድንጋይ ደግሞ እንኳን አሁን ካለበት ረሀብ ለ 10 ቀን እያረፈ መብላት የሚያስችለው ያህል ነበረና እሱ ጠግቦ ሲያድር ይሁዳ ግን በረሀብ ሲጨነቅ አደረ።
ወዳጄ እንደ ይሁዳ በሀይማኖትህ ላይ ብልጠት እና ስልቹነት ለረሀብ ብሎም የዘላለም ህይወት እስከ መጣት ዋጋ ሊያስከፍልህ ይችላል።
ንስሐ ገባለሁ ብለው ኃጢያትን የሚያደርጉ ፣ ጠዋት ፀሎት ሊፀልዪ ሲነሱ ፀሎቱን እንደ እዳ ቆጥረው ሚሰላቹ ፣ ምክንያትና ሰበብ ለራስ እየሰጡ ከቤተክርስቲያን የሚርቁ ፣ 100 ውን ሰርቀው 10ሩን ለቤተክርስቲያን የሚሰጡ እንዲህና የመሳሰሉትን የሚያደርጉ የይሁዳ የግብር ልጆች ናቸውና
ምን አልባት ከዚህ ተግባር ውስጥ ኖረንበት ከሆን እንደ ጴጥሮስ አልቅሰን ልንመለስ ይገባናል!
ከጌታችን ጋር መኖር ሚቻለን እንደ ጴጥሮስ በፍፁም ፍቅር እንደ አብርሀም በእምነት እንጂ እንደ ይሁዳ በብልጠት በስልቹነት እና ከሱ በመለየት አይደለም!
✍ ዲ/ን ወገን
እግዚአብሔር በቸርነቱ አስቦ ፀጋውን ይሰጠኝ ዘንድ ፀልዩልኝ።
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ እንዲዳረስ ለወዳጆ Share ያድርጉ እናተም ቤተሰብ በመሆን የተለያዩ ትምህርቶችን ያግኙ
Watch "ዝማሬ ማኅቶት" on YouTube
user-oj2te9ln4g" rel="nofollow">https://youtube.com/@user-oj2te9ln4g
༒ Dn Wegen ༒
+ "እየጠላን የምናደርገው" +
ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው።
የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5)
የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት
(Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።
ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር።
"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።
ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።
ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።
"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15
✍ ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ይቺን ታናሽ አገልግሎቴን Share በማድረግ ደግፉኝ።
እኔም እግዚአብሔር በምህረቱ እንዲያስበኝ ፀልዪልኝ🙏
༒ Dn Wegen ༒
+ እንደ ህፃናት +
👉 በ 15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነገሰው ንጉስ እንዲህ የሚል አዋጅ ይወጣል።
" የሀገሬ ህዝብ እስከ አሁን ዝም ማለትህ ለምንድነው? ስለምንስ ፈጣሪህን በፀሎት ከመለመን ሰነፍህ? ይኸው ዛሬ ይሄ ስንፍናህ ፍሬ አፍርቶ ሀገሪቷ በረሀብ ማለቋ ነው! ስለዚህ እንደ ሀገር ለ 3 ቀን ሁሉም በየእምነቱ ፈጣሪውን ዝናብ እንዲያዘንብ ይለምን ! ከዚህ ትዕዛዝ ፈቀቅ ብሎ የተገኘውን ግን በንጉስ ቃል ላይ መዘበት ነውና ከፍ ቢል አንገቱን ዝቅ ቢል ባቱን ተቆርጦ ይገደል"
ይህን ትዕዛዝ ከንጉሱ ከወጣ ብኋላ ማን ፀሎቱን ያስጀምር ለሚለው ካህናቱ እጣ አውጥተው ሲዘጋጁ ህዝቡ ደግሞ ራሱን ለፀሎት ማዘጋጀትን ተያያዘው።
ያለው አስከ ዛሬ ያላየውን የፀሎት መፅሐፍ ፈልጎ ሲያዘጋጅ የሌለው ደግሞ ለመግዛት በየፊናው መሯሯጥ ጀመረ። ምን አለፋችሁ ሁሉም የንጉስን ትዕዛዝ ለማክበር ለፀሎት አዘጋጀታቸው በባዘቦት ቢሆን ኖሩ የዛሬዋ ኢትዮጲያ ከነአን (ማርና ወተት ምታፈልቅ ሀገር) እየተባለች በተጠራች ነበር።
በጠዋቱ ህዝቡ ለፀሎት ከ11 ጀምሮ ወደ የእምነቱ ሲሄዱ አንድ አባትም ከዚሁ መርሀ ግብር ሊሳተፉ ልጃቸውን ይዘው ይወጣሉ። ልጁም በሁኔታው ገርሞት አያቴ " በዚህ ምሽት ሳይነጋ ወዴት ነው ምንሄደው?" ሲል ይጠይቃል። አባትም "ቤተ ክርስቲያን ነው አሁን ይሄን ከምትጠይቀኝ ረፍዷል ቶሎ ጫማህን እሰር " ብለው ይመልሳሉ። ይህ ትንሽ ልጅም "አባዬ ቤተ ክርስቲያን ሳይነጋ ሄደን አናውቅም ዛሬ ለምን እንሄዳለን" ሲል ረፍዷል ሲብለው ሚቆራጠጡትን አዛውን ይጠይቃቸዋል። አሳቸውም " ዛሬ እግዚአብሔር ዝናብ እንዲያዘንብልን በቸርነቱ እንዲያስበን ልንፀልይ ነው! " ብለው እጁን ይዘውት ከቤቱ ይወጣሉ
ልጁም በጥሞና ካዳመጠ ብኋላ ከእጃቸው አምልጦ ወደ ቤት ይመለሳል ። አያቱ ምን አልባት ከባድ ህመም ቢኖርባቸው ያኔ የተናደዱት ንዴት ተስፋ የተደረገውን ዝናብ ሳያሳይ ይገላቸው ነበር! በቁጣ " ምን ልሰራ ገባህ ? ና ውጣ ረፍዷል ብዬ አልበረም " ብለው ጮሁ። ልጁም በቀኝ እጁ እቃ ይዞ እየሮጠ ተመለሰ። አያትም የያዘውን እቃ ሲመለከቱ ለምን ይሄን ይዘህ መጣህ ብለው ጠየቁት።
ልጁም "አያቴ ቤተ ክርስቲያን የምንሄደው ፈጣሪን ዝናብ እንዲያዘንብልን ልንጠይቅ ነው አላልከኝም ታዲያ ስንመለስ ከዝናቡ በምን እንጠለላለን? ብኋላ በስብሰን ብርድ እንዳይመታን ብዬ ነው" ብሎ መለሰላቸው።
የህፃኑ እምነት እጅግ ያስገርማል። ይሄኔ ይህ ልጅ ጌታ በነበረበት ዘመን ኖሮ ቢሆን እንደዚህ አይነት እምነት ከቶ በ ኢትዮጲያ አላየሁም ብሎ በመሰከረለት ነበር። ይሄ ህፃን ፀሎታችን ይሰማ ይሆን ባያደርግልኝስ ብለን በጥርጣሬ ማዕበል ለምንገላታ ለኛስ ምነኛ ተግሳፅ ይሆነን ይሆን?!
ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ፀሎት በፃፈው ተግፃፅ ላይ እግዚአብሔር አይሰማኝም ባያረግልኝስ ብሎ እየተጠራጠረ የሚፀልይ ሰው እግዚአብሔርን ከዶሮ አሳንሶ የሚያየውን ክፉ ሰው ይመስላል።
ምክንያቱም ዶሮስ ከበራሪ አዋፍ ፈርተውም ይሁን ተርበው ድምፅ ለሚያሰሙት ጫጩቶቿ ካለችበት መጥታ አቅፋ ከሚፈሩት ታስጥላቸዋለች እንደ ፍላጎታቸውም ታደርግላቸዋለችና።
ወዳጄ ሆይ ፀሎቴን አይሰማኝም ምትል ከሆን ጌታም እንዲህ ይልሀል።
“ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን?”
— መዝሙር 94፥9
በኃጢያቴ ብዛት ፣ እንዲህ ሆኜ ፣ እንዲህ ስላደረኩ አትበለኝ ያንተ ሀጢያት ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት አይበልጥም ይልቁንም ይሄን ሰበብ መሰብሰብህን ትተህ በሙሉ እምነት በፊቱ ቅረብ!
አፌ ኮልታፋ ነው ፀሎት አልችልም ምለምነውን አላቅም እና የመሳሰሉትን ምትል ወዳጄም በንጉስ ፊት ሚለመነውን ጠቅቀው የሚያውቁ አንደበታቸው በእግዚአብሔር ፊት ወዝ ያለው ቅዱሳን አሉልህ። ከዚህ ስንፍናህ ወጥተህ ፊትህን ወደ ቅዱሳኑ አዙርና እንዲህ በላቸው።
"ቅዱሳን ሆይ እኔ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ማልችል አንደበቴ ኮልታፋ በንጉስ ፊት የሚለመነውን ማላውቅ ከንቱ ነኝና ለሙሴ አሮን አንደበቱ እንደሆነ እናንተም ለኔ አንደበት ሁኑኝ። ምፈልገውን ሳይሆን ሚያስፈልገኝን እንዲሰጠኝ በእግዚአብሔር ፊት አሳስቡልኝ """ ይሄኔ ፀሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ሞግስ ታገኝልሀለች።
***
እኔኮ ብዙ ጊዜ ፀልዬ ነበር። ግን አላደረገልኝም ምትል አንተ ሰው።
እግዚአብሔር ፀሎትን ቶሎ መልስ ማይሰጥባቸው ብሎም ማይመልሳቸው 2 ምክንያቶች እንዳሉት ልነግርህ እወዳለሁ።
1ኛ የፀሎትህ ዋጋ ሚሰጥበት ጊዜው ካልሆነ።
በዚህ ስር በሉቃ 1:1 የተፃፉትን ፃድቁን ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥን እስቲ አስታውሳቸው። ልጅ እንዲሰጣቸው ደጋግመው ቢጠይቁትም በጠየቁት ጊዜ ልጅን አልሰጣቸውም። እግዚአብሔር በጠየቁት ጊዜ ቢሰጣቸው ኖሮ የተራ ልጅ ወላጆች እንጂ የመጥምቁ ዮሐንስ ወላጆች አይሆኑም ነበር። ምክንያቱም ዮሐንስ ተፀነሰ ማለት ጌታ ወደ ምድር ሊመጣ እና ሊፀነስ 6 ወራት ቀሩት ማለት ስለሆነ። በዚህ ምክንያት የፀሎታቸው ዋጋ ዘገየባቸው ጊዜው ሲደርስም በቅድስናው የክርስቶስ አጥማቂ እስከ መሆን የበቃ ልጅን አገኙ።
2 ኛ የጠየከው ነገር ከቶ ማያስፈልግህ አልያም ሚያጠፋህን ወይም ብኋላ ምታዝንበትን ነገር ሲሆን መልስ አይሰጥህም !
ለዚህ ምክንያትና ጥቅስ አያስፈልገኝም። አንተ አባት ብትሆንና ልጅህ አሳት አይቶ ያን የሚያበራና የሚያምር የሚያብለጨልጭ ነገር አስነካኝ ወደዛ ወስደህ ጨምረኝ እና ልጫወት ብሎ ቢጠይቅህ ቆይ እስቲ ይሞክረው ብለህ ትጨምረዋለህ። ከሚነዘንዘኝማ ቢሞክረው ይተወኛል ብለህ እሳቱንስ ታስጨብጠዋለህ መቼም ሰው ከሆንክ እንዲህ አታረግም። ይልቁን ሌላ የሚያምር ነገር ግን እንደ እሳቱ የማያቃጥለውን እቃ ፈልገህ ትሰጠዋለህ እንጂ። የእግዚአብሔርም ስራው እንዲሁ ነው።
ስለዚህ ምትፀልየው ነገር
ቶሎ ባይመለስ እስኪ መለስ ፀሎትህን አታቋርጥ። ጭራሽ ባይሰጥህም ደግሞ ሌላ ያማረ እስኪሰጥህ ፀሎትህን አታቋርጥ።
ስትፀልይ ግን እንደ ህፃኑ መሆንን አትርሳ
✍ ዲ/ን ወገን
እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቺን ታናሽ አገልግሎቴን እንድቀጥልበት ፀጋውን እንዲሰጠኝ ስለ እኔ ፀልዪ።
ቤተሰብ በመሆንና ለወዳጅዎ Share በማድረግ ደግፉኝ🙏
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
† ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፳፭ †
+ ቅድስት ሰሎሜ +
=> አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ አምስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል የእመቤታችን የአክስቷ ልጅ ብፅዕት ሰሎሜ አረፈች። እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህን አሮን ልጅ ናት። ለማጣት ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱ ስም ማርያም ነው የሁለተኛዪቱ ስም ሶፍያ የሦስተኛዪቱም ሐና ነው ይቺም ማርያም ሰሎሜን ወለደቻት ሶፍያም ኤልሳቤጥን ወለደቻት ሐናም አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት።
እመቤታችንም ድንግል ስትሆን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወለደችው ጊዜ ይቺ ቅድስት ሰሎሜ የእመቤታችንን አወላለድ እንደ ሴቶች ሁሉ አወላለድ መስሏት ተጠራጠረች ከዚህም በኋላ የድንግል እመቤታችን ገላዋን ዳሠሠቻት ያን ጊዜ እጇ ተቃጠለ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ደግሞ ዳነች።
በዚህም በኅቱም ድንግልና አምላክን እንደወለደች አወቀች። ከተረገመ ኄሮድስ ፊት እመቤታችን በሸሸች ጊዜ ከዮሴፍ ጋራ በመሆን አብራ በመሰደድ የእመቤታችንን ድካሟን ተካፍላ አገለገለቻት ከስደት እስከ ተመለሱ ድረስ ሕፃኑን ታዝለዋለች የምታጥብበትም ጊዜ አለ።
መድኃኒታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ አልተለየችም በመከራውም ቀን ከእመቤታችን ጋራ ከከበሩ ሁሉ ሴቶች በትምህርቱ ወራት ከተከተሉት ጋራ እያለቀሰች ነበረች።
በተነሣባት ዕለት ወደ መቃብር ገሥግሣ ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት። በኃምሳኛውም ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከባልንጆሮቿ የከበሩ ሴቶች ጋራ ሰማያዊ ሀብትን ተቀብላ በክብር ባለቤት መድኃኒታችን ስም ሰበከች ብዙዎችንም አሳመነች። ከአይሁድም ብዙ ስድብና ሽሙጥ አገኛት ከዚያም አረፈች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከሁላችን ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለሰሎሜ በከመ ሰምዐት በዜና። ልደተ አምላክ ዘርእየት እማርያም በድንግልና። ትቤሎ አሜሃ እንዘ ተሐቅፎ በሕፅና። ስብሐት ለከ እግዚኦ በኵሉ ሕሊና። ዘመጻእከ ውስተ ምድር በዝንቱ ትሕትና።
፨፨፨
=>በዚችም ቀን ከእንዴናው አገር የከበረ ኮጦሎስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ እናትና አባቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው አባቱም የእንዴናው ገዥ መኰንን ነው ልጅ አልነበረውም ይህን ቅዱስ ልጅ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንን አዘውትሮ ይለምነው ነበር የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት አስተማረው።
ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ሆነ ለራሱም ሥርዓት በመሥራት በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልያል። ጥቂት በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊአጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልፈቀደም። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የተወለደች ሴት ልጅ ነበረቻቸውና እርሷን ከአርያኖስ ጋራ አጋቧት።
አባቱም ከሞተ በኋላ ለስደተኞች የእንግዳ መቀበያ ቤት ሠርቶ ስደተኛውንና እንግዳ መቀበልን ጀመረ። ከዚህም በኋላ የጥበብ መጽሐፍ ተምሮ ሐኪም ሆነ። በሽተኞቹ ሁሉ ወደ ርሱ ይመጣሉ እርሱም ያለ ዋጋ ይፈውሳቸዋል።
ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለ ሹመቱ ከንጉሡ ጋራ ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃያቸው ሆነ። ይህ ቅዱስም ሰማዕት ለመሆን ይተጋ ነበር ወደ ፍርድ አደባባይም ሒዶ አርያኖስን ንጉሡንም አለቆቹን ሁሉ ረገማቸው ጣዖታቱንም ሰደበ።
አርያኖስም ስለ እኅቱ በእርሱ ክፉ ሊአደርግበት አልተቻለውም ወደ እኅቱ ላከው እንጂ። እርሷም ከመታሠር አዳነችው። ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኰንን ተሾመ የዚህ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና ነገሩት። ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና በርሱ ላይ በመቆጣት ለአማልክት ካላጠንክ ይህ ካልሆነ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ አለው። ቅዱሱም እኔ ለረከሱ አማልክት ዕጣን አላቀርብም ለክብር ባለቤት ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መሥዋዕትን አቀርባለሁ እንጂ ብሎ መለሰለት። በዚያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። የእግዚአብሔር መልአክም ወደ ርሱ መጥቶ ይፈውሰው ያጽናናውና ያረጋጋው ነበር።
ጌታችንም በእጆቹ ታላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ። ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ በሰይፍ ራሱን ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ። የሰማዕታትንም አክሊል ተቀበለ ቤተ ሰቦቹም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩት። ከሥጋውም እጅግ ብዙ ድንቆች ተአምራት የሚታዩ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን።
፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለኮጦሎስ እንተ ይጼሊ ጸሎተ። በመዓልት ምእተ ወበለያልይ ምእተ። ወአመ ፈቀደ ይኩን በእንተ ክርስቶስ ሰማዕተ። ረገመ ንጉሠ ወዘያመልክ ጣዖተ። እስከ በመጥባሕት መተሩ ካሣዶ ክብርተ።
፨፨፨
አባ ኄሮዳ ሰማዕት
=>በዚችም ቀን ስብስጣ ከሚባል አገር አባ ኄሮዳ በሰማዕትነት አረፈ። ከከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ የስደት ወራት በሆነ ጊዜ ይህ ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር።
በአንዲት ሌሊትም በዐልጋው ተኝቶ ሳለ እርሱም ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ በማሰብ በኃላፊው ዓለም ውስጥ መኖር ምን ይጠቅመኛል። በከበረ ወንጌል የተናገረውን የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ይህን ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም ያለውን ሰምቻለሁና አሁንም ተነሥቼ ሔጄ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ደሜን አፈሳለሁ አለ።
ይህንንም በልቡ ሲያስብ እነሆ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጥቶ የከበርክና የተመሰገንህ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አትፍራ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ። እኔም ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋራ እሔዳለሁ በከበረ ሥጋህም ላይ ምንም የሚበረታብህ የለም ብሎት ሰላምታም ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ።
ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባ ኄሮዳ ወደ ምዕራባዊ አገር ወጣ። ፊቱንም ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ ብሎ ጸለየ ልዩ ሦስት አንድ አምላክ ሆይ ጌትነት በረከት ክብር ገንዘብህ የሆነ ለአንተም ለብቻህ ስግደትና አምልኮት የሚገባህ የተሳልኩትን እስከምፈጽም ታጸናኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
ይህንንም ብሎ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሔዶ እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በግልጥ ጮኸ። መኰንኑም ክርስቲያንስ ሆነሃል አገርህ ወዴት ነው አንተ ማነህ ስምህስ ማነው ወገንህስ ምንድነው አለው። የከበረ ኄሮዳም በብህንሳ አውራጃ ስብስጣ ከሚባል አገር ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ለምድራዊ ሟች ለሆነ ንጉሥ ሳገለግል ኖርኩ እንግዲህስ ሕያው ለሆነ ሰማያዊ ንጉሥ አገለግላለሁ ብሎ መለሰለት።
ሉክያኖስ መኰንንም ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ ከጭፍሮቹ ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ ለአማልክት ለአጵሎንና ለአርዳሚስ ለመሠዋት ተዘጋጅ አለው። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ልብ የሌለህ ደንቆሮ ሆይ እምነቱን በሰው ላይ ላደረገ ሰው ወዮለት። ግን እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ የሆነ የተመሰገነ ነው የሚል በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፏል እኔም ለረከሱ አማልክት አልሠዋም አለኝታዬ እግዚአብሔር ስለሆነ ለእርሱ ብቻ እሠዋለሁ።
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 25-እመቤታችንን በስደቷ ጊዜ አብራት ተሰዳ ድካሟን የተካፈለቻትና ልጇን መድኃኔዓለምን በጀርባዋ አዝላ ገላውንም አጥባ ትንከባከበው የነበረችው ቅድስት ሰሎሜ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ በዚኽችም ዕለት ጌታችን የደረቁ በትሮችን ያለመለመበት ዕለት ነው፡፡ ይኸውም የአረገዊ ዮሴፍን በትሮች በአረንጓዴ ቦታ ላይ ቢተክላቸው ወዲያው ዛፎች ሆኑ፡፡
+ ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን የተቀበሉት አቡነ ሕፃን ሞዐ በዓለ ፅንሰታቸው ነው፡፡
+ ከእንዴና አገር የተገኘው የከበረ ቅዱስ ኮጦሎስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ ስብስጣ ከሚባል አገር የተገኘው የከበረ አባ ኄሮዳ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ + +
ቅድስት ሰሎሜ፡- ይኽችም ቅድስት የእመቤታችን የአክስት ልጅ ናት፡፡ እርሷም የማጣት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የሚልኪ ልጅ፣ የካህን አሮን ልጅ ናት፡፡ ማጣትና ሄርሜላ ሶፍያ፣ ማርያምና ሐና የሚባሉ ሴቶች ልጆችን ወልደዋል፡፡ ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ወለደች፣ ድንግል ማርያምም መድኃኔዓለም ክርስቶስን ወለደች፡፡ ሶፍያ ኤልሳቤጥን ወለደች፣ ኤልሳቤጥም መጥምቁ ዮሐንስን ወለደች፡፡ ማርያምም ሰሎሜን ወለደች፡፡
እመቤታችን ጌታችንን በወለደችው ጊዜ ቅድስት ሰሎሜ የእመቤታችን አወላለድ እንደ ሌሎቹ ሴቶች ያለ አወላለድ መስሏት ነበርና የእመቤታችንን ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡ በዚህም ጊዜ እጇ ተኮማትሮ ተቃጠለ፡፡ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ግን እጇ ዳነችላት፡፡ በዚህም እመቤታችን አምላክን እንደወለደች ዐወቀች፡፡ እመቤታችንን በስደቷ ጊዜ አብራት ተሰዳ ድካሟን ተካፍላታለች፡፡ ጌታችንንም በጀርባዋ አዝላ፣ በክንዶቿ ታቅፋዋለች፡፡ ገላውንም የምታጥብበትም ጊዜ ነበር፡፡ ጌታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ ከእርሱ አልተለየችም፡፡ በመከራውም ጊዜ እያለቀሰች ተከትላዋለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ በተነሣም ጊዜ ወደ መቃብሩ ገስግሳ ትንሣኤውን ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት፡፡ በ50ኛም ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሌሎቹ ሴቶች ጋር ሆና ሰማያዊ ሀብትን ከተቀበለች በኋላ ቅድስት ሰሎሜ በጌታችንም ስም ወንጌልን አስተራለች፡፡ ብዙዎችንም አሳምና ያስጠመቀች ድንቅ እናት ናት፡፡ ከአይሁድም የሚደርስባት መከራ በጸጋ ተቀብላ ግንቦት 25 ቀን ዐርፋለች፡፡ የቅድስት ሰሎሜ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + +
ሰማዕቱ ቅዱስ ኮጦሎስ፡- የዚኽም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸውና ጌታችንን ልጅ እንዲሰጣቸው አጥብቀው ከለመኑትና እርሱም የተባረከ ልጅ ከሰጣቸው በኋላ ልጃቸውን በሃይማኖት በምግባር አሳደጉት፡፡ አባቱም የእንዴናው ገዥ መኮንን ነው፡፡
ቅዱስ ኮጦሎስም ለራሱ ሥርዓትን በመሥራት በቀን አንድ መቶ በሌሊትም አንድ መቶ ጸሎታትን ይጸልያል፡፡ ዕድሜውም በደረሰ ጊዜ ወላጆቹ ሊያጋቡት ሲሹ እርሱ ግን እምቢ አላቸው፡፡ ነገር ግን ወላጆቹ ታናሽ እኅቱ የሆነችውን ሴት ልጃቸውን ከአርያኖስ ጋር አጋቧት፡፡ አባቱም ከሞት በኋላ ቅዱስ ኮጦሎስ የስደተኞችና መጻተኞች መቀበያ ቤት ሠርቶ እንግዳን ሁሉ የሚቀበል ሆነ፡፡ ከዚኽም በኋላ የጥበብ መጻሕፍትን ተምሮ ሐኪም ሆነ፡፡ ሕሙማንም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ያለምንም ዋጋ የሚፈውሳቸው ሆነ፡፡
ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስም ጌታችንን በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለሹመቱ ከንጉሡ ጋር ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃይ ሆነ፡፡ በዚኽም ጊዜ ቅዱስ ኮጦሎስ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ተመኝቶ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ወጥቶ አርያኖስን፣ ንጉሡን ዲዮቅልጥያኖስንና አለቆቹን ሁሉ ስለ ጣዖት አምልኮአቸው ሰደባቸው፣ ጣዖታቱንም ሰደበ፡፡ አርያኖስም ስለ እኅቱ ብሎ በቅዱስ ኮጦሎስን ከእሥር ፈታው፡፡ ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኮንን በተሾመ ጊዜ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና እና ገድል ነገሩት፡፡ ጭፍራ ልኮ ወደ እርሱ ካስመጣው በኋላ ለአማልክት እንዲሰግድ አስገደደው፡፡ ቅዱስ ኮጦሎስም ‹‹ከዕውነተኛው አምላክ ከክርስቶስ በቀር የሚገዙለት አምላክ የለም፣ ለእርሱ ብቻ እሰግዳለሁ›› አለው፡፡ በዚኽም ጊዜ መኮንኑ ተቆጥቶ ልዩ ልዩ በኾኑ ሥቃዮች አሠቃየው፡፡ ነገር ግን የታዘዘ መልአክ እየመጣ ቅዱስ ኮጦሎስን ከቁስሉ ሁሉ ይፈውሰውና ያጽናናው ነበር፡፡ ጌታችንም በዚኽ ቅዱስ እጆች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገ፡፡
መኮንኑም ቅዱስ ኮጦሎስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ እንደትእዛዙም ሰየፉትና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ኮጦሎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
ሰማዕቱ አባ ኄሮዳ፡- ይኽም ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕጻንነቱ ጀምሮ በፈሪሃ እግዚአብሔር ያደገ ነው፡፡ በዘመኑም ከሃዲው ንጉጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ነበርና አባ ኄሮዳ አንድ ቀን ተኝቶ ሳለ ስለዚኽች ከንቱ አላፊ ዓለም አሰበ፡፡ ጌታችን ‹‹ይኽን ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ያለውን አስታውሶ በስሙ ሰማዕት ይኾን ዘንድ ወደደ፡፡ ይኽንንም በልቡ ሲያስብ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹የከበርክና የተመሰገንክ ኄሮዳ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፣ ከመከራውም አጸናሃለሁና ሰማዕትነትህን በድል ትፈጽማለህ›› ብሎት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ከዚኽም በኋላ ቅዱስ አባ ኄሮዳ ወደ ምዕራባዊ ክፍል ወጥቶ ከጸለየ በኋላ ወደ ፍርድ አደባባይም ሄዶ ‹‹እኔ የክብርን ባለቤት ክርስቶስን የማመልክ ክርስቲያን ነኝ›› ብሎ በግልጥ ጮኸ፡፡ ከሃዲው መኮንን ሉክያኖስም ይዞ የመጣበትን ጠየቀው፡፡ አባ ኄሮዳ ከብሕንሳ አውራጃ ስብስጣ ከምትባል አገር እንደሆነና አስቀድሞም የምድራዊ ንጉሥ ባለሟል እንደሆነ ነገረው፡፡ መኮንኑም ‹‹ለአማልክት ሠዋና ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ ከጭፍሮቼ ሁሉ የበላይ አድርጌ ልሹምህ›› አለው፡፡ አባ ኄሮዳ ግን ስለ አምኮተ ጣዖቱ ሉክያኖስን ገሠጸው፣ ጣዖታቱንም ረገመበት፡፡ መኮንኑም እጅግ ተቆጥቶ እሾህ ባላቸው የብረት ዘንጎች በጽኑ አስደበደበው፣ ከሥቃዩም የተነሣ የቅዱሱ ደሙ እንደውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም መልአኩን ልኮ ፈወሰውና ፍጹም ጤነኛ አደረገው፡፡ ዳግመኛም ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም አሠቃየው፡፡ ይኽንንም ተአምር ያዩ ሰዎች ‹‹በአባ ኄሮዳ አምላክ በክርስቶስ አምነናል›› ብለው እየመሰከሩ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ሆነ፡፡
መኮንኑም አባ ኄሮዳን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ በዚኽም ጊዜ ጌታችን ለአባ ኄሮዳ ተገለጠለትና ‹‹በችግርና በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ቢኖር በስምህ ቢማጸን ፈጥኖ ከችግሩና ከመከራው ይድናል›› የሚልና ሌላም ብዙ ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ኄሮዳ ወደ ሕዝቡና ወደ ሰያፊዎቹ ተመልሶ ካረፈ በኋላ ስለ ሥጋው ነገራቸው፡፡ በታላቅ ደስታም ተመልቶ ለሰያፊዎቹ ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ብሎ አንገቱን አውጥቶ ሰጣቸው፡፡ በዚኽችም ዕለት ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ አስቀድሞ ጌታችን ቃል የገባለትን የድል አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ከ3 ወርም በኋላ ቅዱስ ሥጋውን ወደ አገሩ ወስደው ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጧ አኖሩት፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ፡፡ የአባ ኄሮዳ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::
+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::
+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::
+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::
+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::
+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::
+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::
=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?
1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)
2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)
4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::
6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
=>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
=>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት
ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ:
ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ::
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር
ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::
+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::
+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::
+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::
+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::
+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::
+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::
=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?
1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)
2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)
4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::
6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
=>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
=>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት
ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ:
ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ::
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር
ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
༒ Dn Wegen ༒
+ ፈተናውን እርዳኝ +
(ይህ ፅሁፍ ያቀረብኩት ፈተና ደርሶብኛል ምን ላድርግ ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ ወዳጆቼ ሲሆን ከፈተናችሁ በፊት ያሉትን ቀናቶች ጥናታችሁን ሳታስታጉሉ ከፀሎታችሁ ውስጥ ከታች ያለውን ፀሎት በማስገበት ከአሁኑ መፀለይ እንድትጀመሩ በማሰብ ነው)
+ ታሪክ +
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡
ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡)
በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡
ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡
ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡
+ ጸሎት +
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
አቅራቢ ፦ ዲ/ን ወገን
ይቺ አገልግሎቴ ለሁሉ እንዲደርስ ለወዳጆ በማጋራት ደግፉኝ🙏
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጰራቅሊንጦስ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ወንጌል ከተነበበ በኃላ
አርያም፦
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
ምልጣን፦
ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።
አመላለስ፦
'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/
ወረብ፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/
እስመ ለዓለም፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።
አመላለስ፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/
ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ ሰላም ይፃፋል
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።
አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ/፬/
ወቦ ዘይቤ አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ
መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ
ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይበውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
አመላለስ፦
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/
ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።
ከዚህ በኃላ ወደ ስርዓተ ቅዳሴ
+++++++++++++++++++++++
#Join & share