kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1940

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ dnwegen || telegram  ༒


👉 ከሚከተሉት አማራጮች መሀከል ጌታውን በ 30 ብር ሸጦ ራሱን ያጠፋ ሐዋርያ የትኛው ነው?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይቺ መንገድ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ታደርሰኛለችን አለቻቸው አዎን ታደርስሻለች አሏት። ከዚያም ጥቂት ተጉዛ ቁማ ረጅም ጸሎትን ጸለየች ወደ ዲዮቅልጥያኖስም ደርሳ ክብር ይግባውና ክርስቶስን የምታመልክ ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች። ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ስም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተመላ ወደርሱም እንዲአቀርቧት አዘዘ በቀረበችም ጊዜ ለአጵሎን ስገጂ አላት የሰው እጅ ለሠራው ለረከሱ የአጋንንትም ማደሪያ ለሆነው እንዴት እሰግዳለሁ አለችው።

ይህንንም ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከብረት በተሠራ ጅራፍም እንዲገርፏት አዘዘ ሁለተኛም በአንገቷ ከባድ ደንጊያ አሥረው ሥጋዋ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ በከተማው ጥጋጥግ እንዲጎትቷት አዘዘ ይህንንም አድርገው ወደ ወህኒ ቤት አስገቧት።

በማግሥቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ በመጣችም ጊዜ በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጵሎን ሠዊ አላት እርሷም ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ሕይወት ነው አለችው እርሱም ከገደልኩሽ በኋላ ድነሽ ትነሺአለሽን አላት አንተ ሰነፍ የእኔን ተወውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ አለችው።

ይህንንም በሰማ ጊዜ ዐጥንቶቿ ሁሉም እስቲሰበሩ በብረት በትሮች እንዲደበድቧት አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉባት። ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቿ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ ቀኑ በመሸ ጊዜ ወደወህኒ ቤት እንዲአስገቧት አዘዘ በዚያችም ሌሊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሠሥ አዳናት።

በማግሥቱም ያመጡአት ዘንድ አዘዘ እርሷም ምንም ሕማም እንዳላገኛት ሁና በእግርዋ መጣች ከመታጠቢያ ቤት ታጥባና ተቀብታ የወጣች ትመስል ነበር ንጉሡም ደኅንነቷን አይቶ አደነቀ የዚችን ክርስቲያን ሴት የሥራይዋን ጽናት እዩ ትላንት በእሳት አሠቃይተናት ነበር ዛሬ ድናለች አለ። እርሷም ሥራይንስ አላውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይን የሚሽር ነው አለችው።

ከዚህም በኋላ እሽ ያሰኛት ዘንድ ሊሸነግላት ጀመረ እምቢ በአለችውም ጊዜ ራስዋን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ሊቆርጧትም ይዘዋት ሲሔዱ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጸላት ብዙ ቃል ኪዳኖችንም ሰጣት በማይታበል ቃሉም መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ በስምሽም የሚመጸውተውን የገድልሽንም መጽሐፍ የሚጽፈውን ሁሉ እቀበለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አለ። ከዚህ በኋላም አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ በጌታችንም ዘንድ የድል አክሊልን ተቀበለች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሳኑሲ_ሰማዕት

በዚህች ቀን በልኪም ከሚባል አገር ሳኑሲ በሰማዕትነት ሞተ። ይህ ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እርሱ ሁልጊዜ እስከ ማታ ይጾም ነበር ዘመዶቹም የሚሠራውን አያውቁም ነበር። የታመሙ በሽተኞችንም ይጐበኛቸው ነበር።

በአንዲት ሌሊትም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ሳኑሲ ሆይ የክብር አክሊልን ትቀበል ዘንድ ተነሥተህ ወደ መኰንኑ ሒድ ክብር ይግባውና በፈጣሪህ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመን አለው። በነቃም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ እንደተገለጸለትና እንዳዘዘው ለእናቱ ነገራት እርሷም አዘነች አለቀሰችም ነገር ግን ትከለክለው ዘንድ አልተቻላትም።

ከዚህ በኋላ ስብራ በሚባል አገር ስሟ ማርያ የሚባል ድኆችንና መጻተኞችን የምትቀበልና የምትመግባቸው የተቀደሰች ሴት እንዳለች ስለርሷ ሰምቶ ወደርሷ ሔደ። በሰማዕትነትም ይሞቱ ዘንድ ከርሷ ጋራ ተስማማ።

አርሳኖስ ወደ ሚባልም መኰንን በአንድነት ሔዱ በምስር ወደብ በመርከብ ውስጥ ሁኖ አገኙትና እኛ ክርስቲያኖች ነን ብለው በፊቱ በግልጥ ጮኹ በየራሱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ቅድስት ማርያም በሥቃዩ ውስጥ ሳለች ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለች።

ቅዱስ ሳሉሲ ግን ክብር ይግባውና በላዩ በአደረው በጌታችን በኢየሱስ ኃይል የሚታገሥና የሚጸና ሆነ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው መኰንን ከብዙዎች እሥረኞች ሰማዕታት ጋራ ላከው እርሱም ያሠቃየው ጀመረ ተረከዙንም ሠንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ። እንዳዘዛቸውም አደረገ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰበትም ።

ሁለተኛም ሥራየኛ አመጣለትና መርዝ በተመላ ጽዋ ሥራዩን አድርጎ ጠጣ ብሎ አዘዘው። ቅዱሱም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ ጠጣው ምንም ምን ጉዳት ሳይደርስበት ቀረ።

ከማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና የከበረች ራሱን ቆረጡት የድል አክሊልንም ተቀበለ መሠርዩም አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አርቃድዮስና_ባልንጀሮቹ

በዚህችም ቀን የአርቃድዮስ የእኅቱ የዲሙናስያ የግብጻውያኑ የአሞኒና የሚናስ የንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም የገድላቸው ፍጻሜ ሆነ። እሊህን ቅዱሳን በእሳት ምድጃ ውስጥ ከአባ ብሶይ ጋራ በጨመሩዋቸው ጊዜ የመላእክት አለቃ ገብርኤል መጥቶ ከነበልባሉ መካከል አወጣቸው።

ወደ ንጉሡም ደርሰው ረገሙት እንዲህም አሉት የምስክርነት ሞት ፍጻሜያችንን የማትጽፍ ከዕለት ወደ ዕለት ለምን ትከፋለህ። ንጉሡም ሰምቶ ተቆጣ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡና ሥጋቸውን በእሳት እንዲያቃጥሉ አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀበሉ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Watch "ታላቁ ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቦ ገዳም" on YouTube
https://youtu.be/ZJcjYsjeoeQ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Check out ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህረት: /channel/orthdoxtemert

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ የህፃናት ጥበብ +

አንድ  ሱፉን ግጥም አድርጎ የለበሰ መናፍቅ አንዲትን ሕፃን መንገድ ላይ ጠራት እና
"ሚጣ በምድር ላይ ለዘላለም መኖር ትፈልጊያለሽ?" አላት ስብከት ሊጀምር

እሷም የዋዛ አይደለችምና "ሰማይና ምድር እኮ ያልፋሉ እንዴት በምድር ላይ ለዘላለም ልኖር እችላለሁ?" አለችው


"አይ ሚጣ እግዚአብሔር እኮ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ነው ብሎአል:: ሰማይና ምድር ካለፉ እግዚአብሔር የት ይሔዳል?" አላት ፈገግ ብሎ

ሚጣ አልተቸገረችም
"ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ ወደነበረበት ቦታ ይሔዳል" አለችው!!!      
     

“.... በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ......”
— 1ኛ ጴጥሮስ 3፥15
                  
✍ ዲ/ን ወገን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/zemaritederosyosife
/channel/zemaritederosyosife
/channel/zemaritederosyosife

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://givepasture.cyou/5930cn11UkF4AUllQFFoX1gPL0IELwJaUHtTLQwmFiApNzEuZBwVIFo1MwVXDBMIEV47PiwrXXcORUcNGwJ2EBNzDhcOCit3LWlSC3AkVjkW&p=pdxztg&_mi1686258594395

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞

❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖

❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+

=>ቤተ_ክርስቲያን
በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል
የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ
ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል::
ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ
ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::

+ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን
ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን
ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል::
ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ
ተብሏል::

+መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም
ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ
ሴት
ሔኖክ
ኖኅ
ሴም
አብርሃም
ይስሐቅና
ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ
ላይ ይደርሳል::

+ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት
ሚስቱ ራሔል
ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም
እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ
ነበረው::
ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::

+እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን
አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ
ሊፈልጋቸው
በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
+መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን
አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ
አድርጐ
መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ
ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም
"ሊነግሥብን
ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
+በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን
ሸጠውታል:: በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና
ሕማማት) ምሳሌ
ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ
ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት
በተሸጠበት በዺጥፋራ
ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
+ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ
ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ
አላንበረከከውም:: "ማንም
አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ
እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት
ኃጢአትን
አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ
ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና
አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት"
እንዲል
መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች
ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ
አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው::
+ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ
ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት
ወንድሞቹም መጋቢ
ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም
ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል::
+በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ
ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ
በዚህች ቀን በመልካም
ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ
ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት
መሠረትም ልጆቹ
(እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ
ከነዓን አፍልሠዋል::

+" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+

=>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ
ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት
ነገሥታቱን
ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ
ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

+እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር
ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ
ይጸልየው:
ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት
የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት:
ከክፋት ወደ
ደግነት መልሷል::

+የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን
ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ
ጊዜም
አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት:
ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

+በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል::
ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና
በእምነት
እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት
ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና
የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

=>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ልደታ ለማርያም
2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

=>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ
ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ
አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን
ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር
ላይ
ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም
አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ.
45:4-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ መንፈሳዊ ጥያቄ +

#1 ስዕለ ማርያምን ትርጓሜ አስረዳኝ! 

(እናንተም የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎቸን በ @dnwegen_bot ላይ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ)

👉  በዚህ ጥያቄ ውስጥ የሚመለሱ ጥያቄዎች

—> ድንግል ማርያም ለምን ልጇን በግራ ብቻ ታቅፋው እንድትሳል ይደረጋል?

—> ለምን ከላይ ሰማያዊ እና ከውስጥ ቀይ ያለብሷታል ትርጉሙም ምንድነው?

—> ውጫዊ ልብሷ ላይ ከዋክብት አሉ ምንድነው ትርጉማቸው?

—> ጌታችን በስዕለ ማርያም በኦርቶዶክሳዊ ስዕል አሳሳል አክሊል ይደረግለታል?

—> እመብርሃን ስትሳል ፀጉራን ምትሸፈነው ለምንድነው?

—> ቅዱስ ሚካኤል ፦ ለምን በቀኝ ይሳላል?

—> ቅዱስ ገብርኤል ፦ ለምን በግራ ይሳላል?

—> ኦርቶዶክሳዊ ስዕል አሳሳል ይዘው ያልጠበቁትን ቅዱሳን ስዕላት ምን እናርጋቸው?

..........ወዘተ

እግዚአብሔር ጥበቡን ይግለጥልን!


*******
1ኛ ጌታችን በግራ መሳሉ ምከንያት  

፦ እመቤታችን ጌታችንን
በግራ ይዛ ምትሳልበት

1ኛ  ትንቢቱን ለመፈፀም
     እሱ ለሷ በግራዋ ሲሆን እሷ ለሱ በቀኙ ትሆናለች በዚህ ምክንያት

“....በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።”
  — መዝሙር 45፥9

የሚለው ትንቢት ይፈፀማል!


2ኛ የሴትን የበታችን ለማቆም
    በብሉይ ጊዜ በፍርድ ቤት 3 ምስክር እስፈልገው ሁለቱ ወንዶች መስክረው በቀረው አንድ ወንድ ፋንታ 10 ሴቶች ለምስክርነት ቢቀርቡ እንደ አንደ ሰው ተቆጥረው ምስክርነታቸው ተቀባይነት አያገኝም ለዚህም ምክንያት ከሆኑት ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ

አዳም ሄዋንን ያለ ሴት አመጣት እንጂ መች ሄዋን ያለ ወንድ አዳምን አመጣችው። የሚል ነበረና   እመብርሀን ለሴት ዘር በሙሉ ሞገስ ሆና ሁለተኛው አዳምን ያለ ወንድ  እሷ ብቻ ሆና አስገኝታለች በዚህ የሴቶች የበታችነት ቀርቷል! 
አዳም ያለ ሴት ከግራ ጉኑ ሄዋንን እንዳስገኘ  ድንግልም ያለ ወንድ ዳግማይ አዳምን ክርስቶስን አስገኝታለች
ይህን ለማሳያ ይሆን ዘንድ በግራ ታቅፈዋለች!

ሁለተኛው  ምክንያት ደግሞ


በሴቶች ነው ከገነት የተባረርነው እሷ ባትሰጠው አዳም አይበላም ነበር የሚል አቤቱታ ነበር። ይህ በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት የሌለው ሆኗል ምክንያቱም የሁሉ አምባ በሆነች በድንግል  ስለተሻረ  ድንግል ጌታን አስገኘች ጌታም ገነትን ከፈተልን ለመውደቃችን ምክንያት የነበረችው ሴት ዛሬ ለመዳናችን ምክንያት ሆናለችና!


...............................................
✍ ዲ/ን ወገን
...............................................
የቀሩትን ጥያቄዎች መልስ ከስር ባለው Channel ላይ ያገኙታል!

Channel ፦ /channel/+_MOh2zIT8ZhiZGQ0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እናታችን_ቅድስት_አርዋ

በዚችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች ቅድስት አርዋ አረፈች። ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ::

ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት (ቁንጅና) በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: ቅድስት አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: ገና በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ::

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች) አስብሏታል::

የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ::

አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጉዋል:: ከዚሕ በሁዋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች::

አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት::
እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች:- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች::

እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል::

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ወለተ_ማርያም_ዘጎንደር

በዚህች እለት እናታችን ቅድስት ወለተ ማርያም መታሰቢያዋ ነው፡፡ ትውልዷ ጎንደር ሲሆን በዐፄ ወናአግ ሰገድ ዘመን የነበረች ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነች ጻድቅ እናት ናት፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ከመነኰሰች በኋላ ወደ ጣና ገዳም ገብታ በጣና ባሕር ውስጥ ለ11 ዓመት ቆማ የጸለየች ድንቅ እናት ናት፡፡ ከእናታችን ከቅድስት ወለተ ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን እኛንም በጸሎቷ ይማረን።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት፣ #ከገድላት_አንደበት እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም ኦርቶዶክሳውያን እንደምን አላችሁ። ዛሬ አንድ መረጃ ላቀብላችሁ ቴሌግራም ላይ አንድ በኦርቶዶክስ ስም ተከፍቶ የክህደት የምንፍቅና ትምህርት የሚሰጥበት መንፈሳዊ ግሩፕ አለ እናም በግሩፑ 50% የሚሆኑት ኦርቶዶክስአዊያን ናቸው እና ግሩፑ በአሁኑ ሰዓት 195,000 አባል ያለው ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተዋህዶ ልጆች ባለማወቅ በግሩፑ ይገኛሉ እናም ምናልባት አንተ የምታነበውም ልትኖርበት ላትኖርበት ትችላለህ ነገር ግን ብዙ ኦርቶዶክስአዊያንን ጋር በእርግጠኝት አለ እናም ግሩፑ የእኛ የኦርቶዶክስአዊያንን እንዳልሆነ ያውቁ ዘንድ ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ30 ሰዎች ሼር በማረግ ኦርቶዶክሳዊያንን ከምንፍቅና ከክህደት  ት/ት እንጠብቃቸው።
የግሩፑ ስም = { ጉባኤ ቅዱሳን }

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ይቅር እንደምንል  +


  በአባታችን ፀሎት ላይ ቂመኞች የሆንን ሰዎች ባትገባ ምንወደው አንድ አስጨናቂ ቃል አለች። አሷም

"በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደልነው ይቅር እንደምንል "

ይቺን አንዳንድ የዋሆች ላለመቀበል ሲሉ ቀይረው እንዲህ ሲሉ ይፀልያሉ

"በደላችንን ይቅር በለን አኛም
የበደሉንን ይቅር እንድንል"

በዚህ በሁለቱ አረፈተ ነገር ውስጥ ያለው ልዪነት በቀላል የሚታይ አይደለም።  የእግዚአብሔር ሀሳብ ፍላጎት ሽሮ የሰውዬውን ሀሳብ የሚያፀባርቅ ከባድ ግድፈት ነው።

የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ትርጉሙ  ፦ ጌታ ሆይ በደሌን ሁሉ ይቅር በለኝ  የበደሉኝን ይቅር እንደምል ። " እኔ በአቅሜ የበደሉኝን ይቅር እላለሁ አንተ ደግሞ እኔን ይቅር በለኝ " ሲሆን በሌላ ትርጉም የበደሉኝን ይቅር እስካላልኩ መቼም ይቅር አትበለኝ የሚለውን ይሰጣል።  ማቴ 18÷25

የሁለተኛው ደግሞ ፦ አንተ እኔን ይቅር በለኝ ያኔ እኔ የበደለኝን ይቅር እለዋለሁ የሚል ትርጉምን ይሰጣል።

እንዲህ አይነቱን ፀሎት የሚፀልየውን ሰው ባለ ራዕዪ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ይገስፀዋል።

“......ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።”
  — ራእይ 22፥19

ወደ ርዕሳችን እንመለስና ክርስቶስ በአባታችን ሆይ ፀሎት ላይ "የበደሉንን ይቅር እንደምንል " የምትለዋን ቃል ያስገባበት ምክንያት  የሰው ልጆች ስንባል  ካሳለፍናነው ሺ መልካም ነገር ይልቅ አንዷ መጥፎ በጥብጣን ስለምታለያየን መልሶ አንድ ለማድረግ  ነው።

  ይቅርታ ማድረግን ከልጅነታችን ጀምረን በወላጆቻችን በጓደኞቻችን በመምህራን ጭምር ስንሰበከው ያደግነው ስብከታችን ቢሆንም  አሁንም ግን ለይቅርታ አዲስ ሆነን ይቅር በሉ ይቅር አትበሉ እየተባልን አተከራ ውስጥ ምንገባ አሳዛኝ ፍጡሮች ነን ለዚህም ምክያታችን
፦ ስንቴ ነው ይቅር ምለው ፣ አሱስ አበዛው ሁሌ ጥፋት ፣ ቢንቀኝና እንደ ሞኝ ቢቀጥረኝስ ፣ ይቅርታ ያረግልኛል ብሎ ነው ያጠፋው ..... ወዘተ  የሚሉ የህሊና ጥያቄዎች ናቸው።  እኚህን ከመመለሳችን  በፊት ስለ ይቅርታ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያለውን እናስቀድም


"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡

በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡

እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “(እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - ) አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ወዳጄ ሆይ እኔ እና አንተ ከእግዚአብሔር በፊት ምህረትን የምንለምን ደሀዎች ስንሆን ለምን በሌሎች ላይ ቂም በመያዝ እግዚአብሔር የሚሰጠንን ምፅዋት እናጣለን እስቲ ዛሬ እንደ ታናሽ ወንድም አንድ ነገር ልምከርህ። 

አውቆ ነው ያጠፋው ስለዚህ ይቅርታ አላደርግለትም አትበል ይሄ ውሳኔህ ከእግዚአብሔር ምህረትህን ያሳጣሀል እንጂ የትም አያደርስህም። እሱንም አውቆ ማጥፋቱን እርግጠኛ ላትሆን ትችላለህ ይልቁን እኔ ልንገርህ  ያጠፋውን ጥፋት ሰብስበህ ለእግዚአብሔር አቅርበው ከዛ አንተ ይቅር በለው።   እግዚአብሔር  እንደሆነ ልብን ነው ሚያየው አውቆ፣  ይቅርታኝ ተገን አድርጎ በድሎህ ከሆነ አሱ ይበቀልልሀል ከሰው ቅጣት የእግዚአብሔር እጅጉን ይበልጣልና አንተ ግን ፍፁም ይቅር በለው! 

***


ስንቴ ይቅር ልበለው ትለኝ እንደሆነ ጌታ ለጴጥሮስ ያለውን ያህል!

ሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ ክርስቶስን ወንድሜ ቢበድለኝ ስንቴ ይቅር ልበለው ብሎ ቢጠይቀው ሰባ ጊዜ ሰባት ብሎታሌ ይህ ማለት አባዝተህ 490 ጊዜ ሳይሆን ፍፁም ይቅር በለው ማለት ነው።   አንተም ጌታ እንዳለው ፍፁም ይቅር ባይ ሁን።

**

ሁሌ ይቅር ሲለው ሞኝ ቢያረገኝስ
ለሚለው የህሊናህ ጥያቄ ጌታ እንዲህ ሲል ይመልስልሀል


አንተ እንደ እኔ ይቅር ባይ ሁን እንጂ ይሄን ይቅር ባይነትህን እንደ ሞኝነት ቢቆጥርብህ አንደ ቀራጭ ይሆንልሀል! እግዚአብሔር እንተን  ይቅር ስለማለትህ ሲያከብርህ አሱ ደግሞ አንተን ሞኝ አርጎ በማሰቡ በእግዚአብሔር ፊት አረመኔ ይሆናል ስለዚህ ይቅር ከማለት አትስነፍ

  — ማቴዎስ 18፥17


የመጨረሻዋ ጥያቄህ ይመስለኛል ያጠፋው ጥፋት ከባድ ነው ነው!

ወዳጄ እስቲ አንዴ ወደ ራስህ ተመለስ በፈጣሪ ፊት አንተ እና እሱ ምታወቁትን በሰው ፊት ቢገለጥ የሚያዋርድህ ከባድ ሀጢያትህን አስብ! አሱን ይቅር የሚልህ ይሄን ይቅር ስትል ነው።  በሌላ በኩል እግዚአብሔር ለዚች ይቅርታ አድራጊነትህ ክብር ይሰጣሀል በአንቀፀ ብፁአን ላይ እንደ ተናገረው።  ይሄን ስታረግ ሳትሳቀቅ


"በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደልነውን ይቅር እንደምንል " ትላለህ


✍ ዲ/ን ወገን


እግዚአብሔር በቸርነቱ እንዲያስበኝ ስለ እኔ ፀልዪልኝ።

ለሌሎች እንዲደርሱ Share ያደርጉ! እርሶም ቤተሰብ ካልሆኑ ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መዝራዕተ ክርስቶስም አባቱ ጭፍሮቹን ልኮ እንደገና ወደ ዓለም እንዳይወስደው ፈርቶ ቶሎ እንዲያመነኩሱት ‹ታመምኩ›› ብሎ ተኛ፡፡ መነኮሳቱም ‹‹ሳይመነኩስ ቢሞት ኩነኔ ይሆንብናል›› ብለው አበምኔቱን ለምነው አመነኮሱት፡፡ ከመነኮሰ በኋላ በሳምንቱ አባቱ ልጁ ያለበትን ገዳም ዐውቆ ታናሽ ወንድሙን ከጭፍሮቹ ጋር በመላክ ለአባ ስነ ክርስቶስ ‹‹ልጄ መዝራዕተ ክርስቶስ አንተ ጋር እንዳለ ሰምቻለሁና ከመመንኮሱ በፊት በአስቸኳይ እንድትልክልኝ›› ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ አባ ስነ ክርስቶስም ለመጡት ጭፍሮች መዝራዕተ ክርስቶስ እንደመነኮሰ ነገራቸው፡፡ ጭፍሮቹም ከአባ ጋር ብዙ ስለተጨቃጨቁ መዝራዕተ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ለመሄድ ተስማማ፡፡ ከእነርሱም ጋር ሳለ ከጭፍሮቹ አንዱና መሪያቸው የሆነውን ሰውም ‹‹ተሳልሜ ልምጣ፣ ጋቢህን ስጠኝ›› ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በምሥራቅ ባለው በር ወጥቶ ጠፍቶ አርማጭሆ ጫካ ውስጥ ገብቶ ጠፋ፡፡ አጎቱና ጭፍሮቹም ፈልገው ቢያጡት ተስፋ ቆርጠው ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ወደ አንገረብ ወንዝ ሄዶ በዚያ ከርኩሳን መናፍት ጋር እየተዋጋ በተጋድሎ በጾም ጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ ተመልሶ ወደገዳም ቢመጣ አባቱና ዘመዶቹ እንደማያስቀምጡት ስላወቀ አባ ስነ ክርስቶስን አስፈቅዶ ወደላይ አርማጭሆ ደብረ ሙጅና አባ አብሳዲ ገባሬ ተአምር ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም 7 ዓመት በተጋድሎ ከኖረ በኋላ ወደ ዋልድባ ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረሲና የተባለች በዋልድባ የምትገኝ ቅድስት ቦታ ተገለጠችለት፡፡ በደብረ ሲና ተራራ ላይ ወጥቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሱባኤ ያዘ፡፡ በዋልድ 11 ዓመት እንደተቀመጠ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹በዚህ ገዳም የምትኖርበት ጊዜ አልቋልና ውጣ›› ብሎ አዘዘው፡፡ ከዚያም ከዋልድባ ወጥቶ ወደ ሰሜን ተራራ ሄዶ ከቅዱስ ያሬድ ገዳም ተባርኮ ወደ ትግራይ ገርዓልታ ሄደ፡፡ ቀጥሎም ወደ ጉንዳጉንዲ ማርያም ገዳም ገብቶ በተጋድሎ መኖር እንደጀመረ አንድ የበቃ ባሕታዊ መጥቶ ‹‹ክፍልህ በዚህ ገዳም አይደልምና ወደ ሌላ ገዳም ሂድ›› አለው፡፡ ወደ መጠራ መቃብረ ጻድቃን ዘንድ ሄዶ ዐጽመ ቅዱሳንን ሲያጥን ‹‹ይህ ገዳም ክፍልህ አይደለም›› የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣለት፡፡ ተነሥቶም ወደ ደብረ ቢዘን ሲጓዝ ሌሎች መነኮሳትን አገኘና በመረብ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ ብዙ መናንያን እንዳሉ ሲነግሩት በሌላ አቅጣጫ ወደ መረብ ወንዝ አቀና፡፡ በዚያም ሸንፋ በተባለ ቦታ ገዳም መሥርቶ ሲቀመጥ መንፈሰ እግዚአብሔር የጠራቸው 12 መነኮሳት መጥተው አርድእት ሆኑለት፡፡ እነርሱም በወባ በሽታ ታመው ስላረፉ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ‹‹ወንድሞቼን አጥቼ በዚህ መኖር ለእኔ አይገባኝም፣ ክፍሌ አይደለም›› ብሎ ወጥቶ ወደ ትግራይ ሄደ፡፡

አድዋ አውራጃ የሐ አቡነ አፍጼ ገዳምን ከተሳለመ በኋላ ገዳሙን ከከበቡት ተራሮች መካከል በአንደኛው ማይ ዱር ወደሚባለው ተራራ ወጥቶ አዲስ ገዳም መሠረተ፡፡ ታቦተ ማርያምን አስገብቶ ሲኖር ከየአቅጣጫው መናንያን መነኮሳት ወደ እርሱ መጡ፡፡ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስም እስከ 93 ዓመቱ ገዳሙን በአበምኔትነት እያስተዳደረ በታላቅ ተጋድሎ ከኖረ በኋላ ግንቦት 29 ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፈ፡፡ ‹‹ማይዱር›› በተባለው ገዳሙ ራሱ በሠራት በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተቀበረ ሲሆን ገዳሙም እስከዛሬ ድረስ ‹‹እንዳ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ገዳም›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለፆመ ሐዋርያት (ሰኔ ፆም) በሰላም አደረሰን!
ፆሙ ነገ ሰኞ ግንቦት 28 ይገባል።
የበረከት ፆም ያድርግልን!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል::  የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ?  እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

✍ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ አራት በዚህችም ዕለት ሐራቅሊ ከሚባል አገር #ቅዱስ_አባት_ዮሐንስ አረፈ፣ ተጋዳይ የሆነች #ቅድስት_ሶፍያ በሰማዕትነት አረፈች፣ በልኪም ከሚባል አገር #ቅዱስ_ሳኑሲ በሰማዕትነት ሞተ፣ #የአርቃድዮስ_የዲሙናስያ_የአሞኒና_የሚናስ የገድላቸው ፍጻሜ ሆነ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ

ሰኔ አራት በዚህችም ዕለት ሐራቅሊ ከሚባል አገር ቅዱስ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባት ስሙ ዘካርያስ ነው እርሱም የጳንጦስና የአብልያ ሀገሮች ገዢ ነበር የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም ይህን የተባረከ ልጅ በተሰጡ ጊዜ ስሙን ዮሐንስ ብለው ጠሩት እርሱ ከአባቱና ከእናቱ ጀምሮ ከመጥምቀ አምላክ ዮሐንስ ጋራ በስም አንድ ሁኗልና በተግሣጽና በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ሂሣቦችንና ጥበቦችን ሁሉ አስተማሩት እናቱም በዘመኗ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይወጣ ታማፅነው ነበር። አባቱም እንዲሁ ይመክረውና ያስተምረው ነበር።

ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ የሃያ ዓመት ልጅ ሲሆን መስፍን ሆነ የጳንጦስና የሐራቅሊ ሌሎችም አገሮች ሁሉ ተገዙለት።

እንዲሁም እያለ የመልአክ አምሳል ሰይጣን ታየው እንዲህም አለው አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሒደህ የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ አግባ ብሎ ጌታ አዝዞሃል አለው ቅዱሱም በውኑ ይህ መልአክ ነውን ግን ከአፉ የእግዚአብሔር ስም ከሰማሁ አንጾኪያ እሔዳለሁ አለ።

ከዚህ በኋላም ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ተገናኘው ንጉሡም በአየው ጊዜ አከበረው እጅግም ወደደው። በማግሥቱም በምሳ ላይ ከእርሱ ጋራ እያለ ከሃድ ድዮቅልጥያኖስ አጵሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ ያንንም ጣዖት ባመጡት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ አቃለለው ስለዚህም ሥራ ንጉሡን ረገመው ሰደበውም።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገውን በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በእሥር ቤት አሠረው። በእሥር ቤትም ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ታየዉ ከእርሱ ጋራም መላእክት አሉ። ይዞም ሳመው ብዙዎች ቃል ኪዳኖችንም ሰጠው። በማግሥቱም ንጉሡ ልኮ ከእሥር ቤት አወጣዉ ወደ ርሱም አቀረበውና ለአጵሎንና ለአርዳሚስ ስገድ አለው ቅዱሱም የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ አለው ንጉሡ ግን ከእርሱ ጋር መታረቅ ሽቶ ብዙ የሽንገላ ነገርን ተናገረው።

ከዚህም በኋላ ግብርን ያስገብር ዘንድ ከሹመት ጋራ ወደ ግብጽ አገር ላከው ወደ ግብጽ ገዢ ወደ ስርያቆስም ስለ ርሱ እንዲህ ሲል ጽፎ ላከ እነሆ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤቶች አፍርሶ አዲስ እንዲአሠራ ከግብጽና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁ።

ቅዱሱም ይህን ምክንያት ይዞ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሶ ተዋቸው። በዚያም ወራት ወኰንኑ ስርያቆስ የሰማዕታትን ራስ መቆረጥን ሊያዝዝ በፍርድ አደባባይ ተቀመጠ በዚያን ጊዜ ከስዒድ ዲዮስቆሮስ፣ ቢፋሞን፣*አሕራጋኖስ፣ ኪሮስ፣ ዮልዮስ፣ እለእስክንድሮስ፣ ዮሴፍ ፣ይስሐቅና፣ እስጢፋኖስ የሚሉአቸው ሰዎች መጥተው እሊህ ሁሉም እኛ ክርስቲያኞች ነን እያሉ በግልጥ ጮኹ ያን ጊዜ መኰንኑ ይዞ ያለርኅራኄ ያሠቃያቸው ጀመረ።

ቅዱስ ዮሐንስም ይህን በአየ ጊዜ የሹመቱን ሥራ ትቶ እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በግልጥ ጮኸ መኰንኑም ተቆጥቶ በእግር ብረት እንዲአሥሩትና ወደ እንድና አገር ወደ መኰንኑ አርያኖስ እንዲወስዱት አዘዘ እርሱም ስለሆነው ሁሉ መረመረው ከቃሉ መልስም የተነሣ ተቆጣ በባላ እንጨት ላይ ሰቅለው በመንኰራኲር አጣብቀው እንዲጨምቁት ከዚያም ከባላው አውርደው ሥጋው እስኪቀልጥ ሆዱ ላይና ራሱ ላይ በቀጭኔ እንዲደበድቡት አዘዘ ምድሪቱም በደሙ ተመላች ከዚያም ወደ እሥር ቤት አስገቡት።

ከጥቂት ቀኖች በኋላም በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ ያሹት ዘንድ ዳግመኛም አመድ ጐዝጉዘው በላዩ የእሳት ፍም ከጐኑ በታች አድርገው በላዩ እንዲአስተኙት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።

ሁለተኛም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በፊቱ ላይ በጀሮዎቹም ላይ እንዲያኖሩዋቸው አዘዘ እንዲህም አድርገው ከወህኒ ቤት ጨመሩት። በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ሰላምታ ሰጥቶ አጸናው። በማግሥቱም ከወህኒ ቤት አውጥተው በጋሉ ብረት ዘንጎች ደበደቡት።

ከዚህም በኋላ ግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጭራ ላይ በገመድ አሠሩ። ከዚህ በኋላም ባለ ሰይፍ ወጥቶ እግሮቹንና እጆቹን ራሱንም ቆረጠ እንዲህም የምስክርነቱን ተጋድሎ ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፍያ_ሰማዕት

በዚህችም ዕለት በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ተጋዳይ የሆነች ቅድስት ሶፍያ አንገቷን በመቆረጥ በሰማዕትነት አረፈች። የዚች ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያን ነበሩ በወለዱዋት ጊዜም በመልካም አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የአባቶቻችን ሐዋርያትንም ሕግና ሥርዓት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጓት።

ከዚህ በኋላም በአደገች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ መስፍን ልጅ ሊአጋቧት ፈለጉ ቅድስቲቱም ይህን በመንፈስ ቅዱስ ዐውቃ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ፊቷን ወደ ምሥራቅ መልሳ መቶ ስግደትን ሰገደች ቆማም ረጅም ጸሎትን ጸለየች በጸሎቷም ውስጥ እንዲህ አለች የክብር ባለቤት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህን ለእኔ ለባርያህ ለሶፍያ ምራኝ ወደ ጥፋት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ የሚጠፋውንም ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው ወላጆቼ በሚመክሩብኝም በረከሰ በሥጋ ፍትወት ውስጥ የኃጢአት ባሪያ እንድሆን አቤቱ አትተወኝ የከበደ የዓለማዊ ፍላጎት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትክሻዬን ዘንበል አድርገው እንጂ።

ጸሎቷንም ከፈጸመች በኋላ በዐልጋዋ ላይ ተቀመጠች ጥቂትም ቆይታ እንዲህ የሚል ሃሳብ መጣባት ተነሥቼ በሥውር ልውጣ ወደ ሩቅም ሒጄ ከበረሀ ውስጥ ገብቼ ለልዑል አምላክ ላገልግል።

ከዚህም በኋላ ወላጆቿ የሰጧትን የምታገለግላትን ብላቴናዋን ጠራች ወይን አምጥታ እንድታጠጣትም አዘዘቻት በአመጣችላትም ጊዜ እርሷ ጥቂት ቀምሳ ያመጣችው ወይን እስቲያልቅ ትጠጣ ዘንድ ብላቴናዋን አዘዘቻት። ከስካርም የተነሣ ልቧ በተሰለበ ጊዜ ልብስሽን አምጪ የእኔንም ልብስ ወሰጂ አለቻትና ሰጠቻት የወይኑ ስካር አእምሮዋን ነሥቷታልና ተኚ አለቻት በላይዋም እንቅልፍ በከበዳት ጊዜ ማንም ሳያያት ቅድስት ሶፍያ በሥውር ወጣች ከወላጆቿ ማደሪያ የራቀ ነበርና።

ርቃ በሔደችም ጊዜ በተራራና በዋሻዎች ውስጥ ሊሠወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሚሸሹ ሰዎችን አገኘች እናንተ ከወዴት ናችሁ ብላ ጠየቀቻቸው የየአንዳንዳቸውን አገራቸውን ነገሩዋት ደግማ ወዴት ትሔዳላችሁ አለቻቸው እነርሱም ስለሃይማኖት ከዲዮቅልጥያኖስ የሆነውን ሁሉ ነገሩዋት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ dnwegen || telegram ༒


👉 ከሚከተሉት አማራጮች መሀከል ጌታውን ዶሮ ሳይጮህ 3 ጊዜ ክዶ ብኋላ በንስሐ የተመለሰው ሐዋርያ የትኛው ነው?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 3 በትኅርምትና በተጋድሎ የጸናች ክብርት ማርታ ዕረፍቷ ነው፡፡ ይኽችውም ቅድስት ከቀድሞው የዝሙት ሕይወት በንስሓ ተመልሳ በመመንኮስና ገዳም በመግባት በታላቅ ተጋድሎ 25 ዓመት የኖረችና ሰይጣንንም ድል ነስታ ተአምራትን እስከማድረግ ድረስ የተጋደለች ታላቅ እናት ናት፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከሃድያን አንድ ዓመት ሙሉ ያለማቋረጥ በጽኑ ካሠቃዩት በኋላ በዓመቱ በሚነድ እሳት ውስጥ ቢጨምሩት እሳቱ ምንም ሳይጎዳው በውስጡ ሆኖ ሲጸልይ በመታየቱ ብዙዎችን ያሳመናቸው ኤጲስቆጶስ አባ ኤላርዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ ሰማዕቱ ቅዱስ ኮርዮን ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
+ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን መታቢያቸው ነው፡፡
ቅድስት ማርታ፡- ከምስር ተወላጆች ውስጥ ስትሆን ወላጆቿም እጅጋ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ እርሷም በመጀመሪያ በዝሙት ሕይወት የምትኖር ነበረች፡፡ የከተማ ጎልማሶችና ታላላቆችም ወደ እርሷ እየመጡ ያመነዝሩ ነበር፡፡ ከዚኽም በኋላ ሥራዋ ተገለጠ፣ የርኩሰት ሥራንም በግልጥ አብዝታ የምትሠራ ሆነች፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና የጌታችን የከበረ የልደቱ በዓል በሆነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደች፡፡ ልትገባም በፈለገች ጊዜ ጠባቂው ከለከላት፡፡ ‹‹አንቺ በምግባር የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት አይገባሽም›› በማለት ተናገራት፡፡ ይተዋትም ዘንድ በከለከላት ጊዜ ብታባብለውም እምቢ ስላላት በመካከላቸው ታላቅ ጸብ ሆነ፡፡ ኤጲስቆጶሱም ጩኸት ሰምቶ ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲስያኑ ደጃፍ ደረሰ፡፡ ማርታንም ባያት ጊዜ ‹‹የእግዚአብሔር ቤቱ የከበረና የነጻ እንደሆነ አታውቂምን? አንቺም የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገቢ ዘንድ አይባሽም›› አላት፡፡

በዚኽም ጊዜ ማርታ እያለቀሰች ለኤጲስቆጶሱ ‹‹ንስሓ እገባለሁ እንጂ ወደዚህ የረከሰ ሥራ ከእንግዲህ አልመለስም፣ ብትቀበለኝም እመነኩሳለሁ›› አለችው፡፡ ኤጲስቆጶሱም ‹‹ገንዘብሽንና ጥሪትሽን ሁሉ ወደዚህ አምጥተሸ በፊትሽ ካላቃጠልሽው አላምንሽም›› አላት፡፡ ያንጊዜም ሄዳ ጥሪቷንና ዋጋው ውድ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶሱ ፊት ጣለችው፤ እርሱም በፊቷ አቃጠለው፡፡ ከዚኽም በኋላ የራሷን ጠጉር ተላጨች፡፡ ኤጲስቆጶሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት፡፡

ቅድስት ማርታም በዚያ ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች፡፡ ነፍሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር፡- ‹‹በጭቃና በድንጋይ ወደታነጸው ቤት ለመግባት ካልቻልሽ በብርሃን ወደተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ?›› ዳግመኛም በጸሎቷ ‹‹አቤቱ ቤተ ክርስቲያንን ከሚጠብቀው ሰውዬ ያደረሰብኝን ሐፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ›› አለች፡፡
ይኽችም ቅድስት ሰይጣንን ድል እስካደረገችው ድረስ 25 ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በእነዚኽ ዘመናት ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም፡፡ ከዚህም በኋላ በሰላም ዐረፋ ነፍሷን ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጠች፡፡ የቅድስት ማርታ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + +
አባ ኤላርዮስ፡- ይኸውም ቅዱስ ከሃዲውን ንጉሥ ዮላኪዎስን ጣዖታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር፡፡ ንጉሡም ‹‹አይሁድ የሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሃዲ ትለኛለህን? እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያንን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ›› አለው፡፡
ከዚኽም በኋላ ንጉሡ ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኮንን እንዲያሠቃየው አሳልፎ ሰጠው፡፡ መኮንኑም አባ ኤላርዮስን ባለመራራት ያለማቋረጥ አሠቃየው፡፡ መኮንኑም ለአንድ ዓመት ያህል ያለምንም ማቋረጥ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮች ሲያሠቃየው ኖረ፡፡
በዓመቱም ፍጻሜ አባ ኤላርዮስን ወስደው እሳት ውስጥ ጣሉት፡፡ እርሱም ከእሳቱ ውስጥ ቆሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ፡፡ ስለዚኽችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ከዚኽም በኋላ ከአትክልት መካከል እንደሚወጣ ሆኖ ከእሳት አወጡት፡፡ መኮንኑም ማሠቃየት በሠለቸው ጊዜ የአባ ኤላርዮስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ በትእዛዙም መሠረት ጭፍሮቹ አባ ኤላርዮስን ሰየፏቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+++
ዳግመኛም በዚህች እለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን መታቢያቸው ነው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::

ሕጻን እያሉ ቃለ እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን፣ ነብሩን፣ ተኩላውን ሰብስበው "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ፣ ከፍየሉ፣ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ ማርያም ሔደው መንኩሰዋል::
ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ኖረዋል፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል፣ ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) እንዲሁም "7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::

ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ ዮሐንስ ዘመን) ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬም በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል።
የአቡነ ተጠምቀ መድኅን ረድኤት በረከታቸው ትደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Watch "ዝማሬ ማኅቶት ቲዩብ" on YouTube
zemarimahetotetube" rel="nofollow">https://youtube.com/@zemarimahetotetube

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ †††

†††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:-
¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:-
ነቢይ:
ሐዋርያ:
ሰማዕት:
ጻድቅ:
ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት:
ጸያሔ ፍኖት:
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::

††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ †††

††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:-
¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
¤መናኔ ጥሪት የተባለ
¤በድንግልና ሕይወት የኖረ
¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::
ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል::
ቅዱስ ዮሐንስ
¤ቁመቱ ልከኛ
¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ
¤የራሱ ጸጉር በወገቡ
¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ
¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር::
ቅዱስ ኤልሳዕ
¤በጣም ረዥም
¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ)
¤ቀጠን ያለ
¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር::

በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት::

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት::
ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል::

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል::

††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን::

†††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ)
3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ

†††ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

†††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" †††
(ማቴ. 11:7-15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ መንፈሳዊ ጥያቄ +

#1 ስዕለ ማርያምን ትርጓሜ አስረዳኝ! 

(እናንተም የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎቸን በ @dnwegen_bot ላይ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ)

👉  በዚህ ጥያቄ ውስጥ የሚመለሱ ጥያቄዎች

—> ድንግል ማርያም ለምን ልጇን በግራ ብቻ ታቅፋው እንድትሳል ይደረጋል?

—> ለምን ከላይ ሰማያዊ እና ከውስጥ ቀይ ያለብሷታል ትርጉሙም ምንድነው?

—> ውጫዊ ልብሷ ላይ ከዋክብት አሉ ምንድነው ትርጉማቸው?

—> ጌታችን በስዕለ ማርያም በኦርቶዶክሳዊ ስዕል አሳሳል አክሊል ይደረግለታል?

—> እመብርሃን ስትሳል ፀጉራን ምትሸፈነው ለምንድነው?

—> ቅዱስ ሚካኤል ፦ ለምን በቀኝ ይሳላል?

—> ቅዱስ ገብርኤል ፦ ለምን በግራ ይሳላል?

—> ኦርቶዶክሳዊ ስዕል አሳሳል ይዘው ያልጠበቁትን ቅዱሳን ስዕላት ምን እናርጋቸው?

..........ወዘተ

እግዚአብሔር ጥበቡን ይግለጥልን!


*******
1ኛ ጌታችን በግራ መሳሉ ምከንያት  

፦ እመቤታችን ጌታችንን
በግራ ይዛ ምትሳልበት

1ኛ  ትንቢቱን ለመፈፀም
     እሱ ለሷ በግራዋ ሲሆን እሷ ለሱ በቀኙ ትሆናለች በዚህ ምክንያት

“....በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።”
  — መዝሙር 45፥9

የሚለው ትንቢት ይፈፀማል!


2ኛ የሴትን የበታችን ለማቆም
    በብሉይ ጊዜ በፍርድ ቤት 3 ምስክር እስፈልገው ሁለቱ ወንዶች መስክረው በቀረው አንድ ወንድ ፋንታ 10 ሴቶች ለምስክርነት ቢቀርቡ እንደ አንደ ሰው ተቆጥረው ምስክርነታቸው ተቀባይነት አያገኝም ለዚህም ምክንያት ከሆኑት ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ

አዳም ሄዋንን ያለ ሴት አመጣት እንጂ መች ሄዋን ያለ ወንድ አዳምን አመጣችው። የሚል ነበረና   እመብርሀን ለሴት ዘር በሙሉ ሞገስ ሆና ሁለተኛው አዳምን ያለ ወንድ  እሷ ብቻ ሆና አስገኝታለች በዚህ የሴቶች የበታችነት ቀርቷል! 
አዳም ያለ ሴት ከግራ ጉኑ ሄዋንን እንዳስገኘ  ድንግልም ያለ ወንድ ዳግማይ አዳምን ክርስቶስን አስገኝታለች
ይህን ለማሳያ ይሆን ዘንድ በግራ ታቅፈዋለች!

ሁለተኛው  ምክንያት ደግሞ


በሴቶች ነው ከገነት የተባረርነው እሷ ባትሰጠው አዳም አይበላም ነበር የሚል አቤቱታ ነበር። ይህ በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት የሌለው ሆኗል ምክንያቱም የሁሉ አምባ በሆነች በድንግል  ስለተሻረ  ድንግል ጌታን አስገኘች ጌታም ገነትን ከፈተልን ለመውደቃችን ምክንያት የነበረችው ሴት ዛሬ ለመዳናችን ምክንያት ሆናለችና!


...............................................
✍ ዲ/ን ወገን
...............................................
የቀሩትን ጥያቄዎች መልስ ከስር ባለው Channel ላይ ያገኙታል!

Channel ፦ /channel/+_MOh2zIT8ZhiZGQ0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ በገነት ያሉ ሦስት አስደናቂ ነገሮች +

አንድ አባት ወደ ገነት ከገባ በሁዋላ ለሌላ አባት በሕልም እንዲህ ሲል ነገረው

ወደ ገነት በገባሁ ጊዜ ሦስት ነገሮች አስደነቁኝ
የመጀመሪያው ገነት ውስጥ ይገኛሉ ብዬ ፈጽሞ የማልጠብቃቸውን በእኔ ዓይን ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው::
ሁለተኛው በገነት እንደሚኖሩ በእርግጠኝነት የምገምታቸውን ጻድቃን መስለው የታዩኝን ሰዎች በገነት ውስጥ አለማግኘቴ ነው::

ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ግን እንደ እኔ ዓይነቱን እጅግ ኃጢአተኛ ሰው በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው" አለ::

"ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡— እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል" ማቴ 21:31

✍ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ግንቦት_30

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሠላሳ በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት #አባ_ሚካኤል አረፈ፣ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያ_ቆሮስ አረፈ፣ የእናታችን #ቅድስት_ዜና_ማርያም መታቢያ ነው፣ ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች #ቅድስት_አርዋ አረፈች፣ እናታችን #ቅድስት_ወለተ_ማርያም መታሰቢያዋ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሚካኤል_ሊቀ_ዻዻሳት

ግንቦት ሠላሳ በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ሚካኤል አረፈ። ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸው በቃሉም አጠናቸው።

ከዚህም በኋላ ንጽሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ።

ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አድርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ።

የትሩፋቱ የጽድቁና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማው ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚአመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅድሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል።

ሕዝቡንም ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። አንድ ጊዜ ከመጻሕፍት አንድ ጊዜም ከቃሉ። መልካም አገልገሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕመም በላዩ አመጣ።

ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መላ ዕድሜውም ዘጠና ዓመት ከስምንት ወር ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ቆሮስ

በዚህችም ዕለት ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ ቆሮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል ከዕርገቱ በኋላም ሐዋርያትን አገልግሏቸዋል ከእሳቸውም ጋራ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ጳውሎስ ጋራ በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ አገለገለው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

ከዚህ በኋላም በምሥራቅ ወዳሉ አገሮች ሔደ ከመኵራቦችም ብዙ መከራ ደርሶበት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቋ_ቅድስት_ዜና_ማርያም

በዚህች ዕለት የእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም መታቢያ ነው፡፡ ከአባቷ ከገብረ ክርስቶስ ከእናቷ አመተ ማርያም በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30ቀን የተወለደች ሲሆን ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንፅህ ድንግልና በምድረ ሂንፍራንስ ጣራ ገዳም አካባቢ በሚገኘው በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25ዓመት በጾም በፀሎት ምንም አይነት የላመ የጣፈጠ እህል ሳትቀምስ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) በመዘፍዘፍ ከ3 ቀን በኃላ በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ላይ የቀመሰውን መራራ ሐሞትን በማሰብ ሙሉ ሕይወቶን እየተመገበች ታላቅ ተጋድሎዋን ፈፅማለች፡፡ ከዚህ የተነሳ ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜ ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ ተብሎ እስከ አሁን ድረስ በስሞ እየተጠራ ይገኛል፡፡

ከአቡነ እድርያስ ዋሻ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ተነስተን ስንጓዝ አዲስ ዘመን ከተማ በስተቀኝ በኩል ተገንጥለን 15ኪሜ ያክል የጥርጊያ መንገድ እንደተጓዝን በስሞ የተሰየመውን ደሪጣ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ገዳም ላይ ቀሪ ሕይወቶን ምንም አይነት ዋሻ ባልነበረበት በከፍተኛ ተራራ ላይ እጅግ አስቸጋሪ ቀዝቃዛ አየር ባለበት ብርዱን፣ ፀሐዩን፣ ቁሩን፣ ረኃቡንና ጥሙን በመቋቋም ራቁቶን በመሆን መራራ ምግቦችን አዋህዳ በመመገብ በጾም በፀሎት በመትጋት አስቸጋሪ የሆነውን ተጋድሎዋን በመፈፀም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን በታላቅ ክብር አርፋለች፡፡

በዚህም ወቅት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አላፋት ቅዱሳ መላዕክት ጋር እንዲሁም ከሐዋርያት ፣ ከሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከደናግል ጋር በመሆን ከሰማይ በመውረድ በታላቅ ክብር ዕረፍቷን አክብሮላታል ታላቅ ኪዳንም ገብቶላታል፡፡

በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ወይንም በአሁኑ ሰዓት መቃብሯ በሚገኝበት ዋሻ ቤተመቅደስ አካባቢ በተጋድሎዋ ጊዜ ራቁቷን በሆነች ሰዓት መላ ገላዋን የሸፈነላት ፀጉር በእየ ዛፎቹ ላይ እስከ አሁን ድረስ አለ ፡፡ ይህም የጸጉር አምሳያ ከገዳሙ በመውሰድ ብዙ ሰዎች በቤታቸው በመታጠን ከአስም እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች እየተፈወሱና እየዳኑ ሲሆን ታላላቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ ገዳም ከሌሎች ገዳማት ለየት የሚያደርገው ታሪክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ በመውረድ ራሱ የባረከው ልዩ ታሪክ ያለው ጠበል የሚገኝ ሲሆን ይህም ጠበል በቦታው ላይ ሆኖ የተጠመቀ ፣ የጠጣ ፣ አልያም በአለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀመ እስከ አሁን ድረስ መካን የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ልጅ የሚያገኙ ከመሆናቸው ባሻገር ከማንኛውም ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ታላላቅ ታምራትን እየሰራ ይገኛል፡፡

በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ላሊበላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሰረት ወደዚሁ ታላቅ ስፍራ በመምጣት የጻድቋ ማረፈያ/መታሰቢያ ዋሻ ቤተ መቅደስ በመፈልፈል የሰራላት ሲሆን በመቀጠል አፄ ይስሐቅ በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህን ገዳም በስሟ በመገደም በዚሁ ዋሻ ውስጥም የጻድቋ የቅድስት ዜና ማርያም መቃብሯ እንዲሁም የመታሰቢያዋ ፅላት የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢው ያሉት ሕዝበ ክርስትያን ከካህናት ጋር በመሆን ሥርዓተ አምልኮ በመፈፀም እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡

ይህ ዋሻም አስቀድሞ ሦስቱ ቅዱሳን ማለትም አቡነ እንድርያስ ዘጣራ ገዳም ፣አቡነ ተክለኃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፣ ጻድቋ ቅድስት ዜናማርያም ዘደሪጣ ውስጥ ለውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በፀጋ እግዚአብሔር ይገናኙበት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓትም እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ይመላለሱበታል፡፡

ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ስፍራ ተነስቶ የጻድቋ ደጃን የረገጠ ለ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ

የሚል ቃል ኪዳን ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ተሰቶታል። ከእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ከጵጵስና ሽሽት +

ረዣዥሞቹ ወንድማማቾች ተብለው የሚጠሩት አውሳብዮስ ፣ አሞንዮስ ፣ ዲዮስቆሮስና አውሳሚዮስ በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ላይ በብዙ መልኩ ይጠቀሳሉ። "አውሳብዮስ አሞንዮስ ተናግረውታል" የሚል ማስረጃ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜ መጻሕፍት ላይ ማግኘት የተለመደ ነው። እነዚህ ቁመታምና መልከ መልካም የነበሩት ወንድማማቾች ሕይወታቸውን ለቤተ ክርስቲያን የሠጡ የዘመኑን ፍልስፍና ተምረው በሃይማኖት እውቀት የመጠቁ ነበሩ። የእስክንድርያ ትምህርት ቤት ቀደምት ሊቃውንትን መጻሕፍትም እጅግ ያነበቡ ፣ ከሊቃውንት ተርታ የሚመደቡ የታሪክና የትርጓሜ መምህራን ነበሩ።

ከእነዚህ ወንድማማቾች መካከል አንዱ አባ አሞንዮስ ነው። ይህ አባት ከእውቀት ጋር ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት የነበረው ነበር። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በዚያን ዘመን የዓለም ማእከል ወደነበረችውን ሮም በሔደበት ወቅት ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ አብያተ ክርስቲያናት ውጪ አንድም ነገር ሳይጎበኝ መመለሱ ነው።

አባ አሞንዮስ በበአቱ ተወስኖ በሚኖርባት ሄርሞፖሊስ የምትባል ከተማ የነበሩ ምእመናን መንፈሳዊ ሕይወቱንና ጥልቅ እውቀቱን ተመልክተው ጳጳስ ሆኖ እንዲሾምላቸው ተመኙ። ስለዚህም ወደ እስክንድርያው ፓትርያርክ ጢሞቴዎስ ሔደው አመለከቱ። ፓትርያርኩ የአባ አሞንን መንፈሳዊነትና እውቀት በመረዳት ጳጳስ አድርጎ ሊሾምላቸው ፈቀደ። ምእመናኑ ተደስተው ወደ አባ አሞንዮስ እየገሰገሱ ደረሱ። ወደ በአቱ ሲገቡ ግን ያጋጠማቸው ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነበር።

አባ አሞንዮስ ሕዝቡ ወደ ፓትርያርኩ ሔደው ጳጳስ አድርገው ሊያሾሙት እንደሆነ ሰምቶ ጳጳስ ሆኖ ላለመሾም የቀኝ ጆሮውን ቆርጦት ነበር። ይህንን ያደረገው በሥርዓቱ መሠረት ጳጳስ የሚሆነው ለአገልግሎት የሚከለክል የአካል ጉድለት የሌለበት ሰው እንደሆነ ስለሚያውቅና ምእመናኑም "ጳጳሳቸው ጆሮው ቆራጣ ነውእንዳይባሉ ፈርተው ይተዉኛል" ብሎ አስቦ ነበር።

ይህን ያዩት ምእመናን በሁኔታው ቢደነግጡም ይህን የመሰለ አባት ማጣት ስላልፈለጉ ወደ ፓትርያርኩ ተመለሱ። ነገሩን የሰሙት ፓትርያርክ ጢሞቴዎስ ግን "ይህን ሥርዓት አይሁድ ይጠብቁት እኔ ግን አፍንጫውም ቢቆረጥ እሾመዋለሁ" አሉ።

ምእመናኑ ደስ ብሏቸው ወደ አባ አሞንዮስ ተመለሱ። አባ አሞንዮስ በአቱን ጥሎ ሮጠ። ምእመናኑ ተከታትለው ያዙት። እየተንፈራገጠ እያለቀሰ ወደ ፓትርያርኩ ሊወስዱት ሞከሩ። አባ አሞንዮስ ግን "እባካችሁ ተዉኝ ግድ ብላችሁ ብትወስዱኝና ብታሾሙኝ ምላሴን እቆርጣለሁ" አላቸው። ይህንን ከማድረግ እንደማይመለስ ስለተረዱ ምእመናኑ እያዘኑ ተዉት።

መጽሐፈ መነኮሳት ሹመትና ክብር እንደ ጥላ ነው ይላል። የሚከተሉትን ይሸሻል የሚሸሹትን ይከተላል። በቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት እንጂ ሥልጣን ባይኖርም  ቤተ ክርስቲያን ግን ከትናንት እስከ ዛሬ መሾምን እንደ ጦር የሚፈሩና በግድ እያለቀሱ የሚሾሙ አባቶች ነበሯት ፣ ዛሬም አሏት። እያለቀሱ የተሾሙትም የቤተ ክርስቲያንን ዕንባ ይጠርጋሉ።

ይህን ታሪክ የጻፍሁት "ዛሬ ምን አባት አለና ..." የሚለውን የተለመደ የስድብ ዶፍ ለመቆስቆስ አይደለም። ይህን ማድረግ ለአሕዛብ መሳለቂያ ከመሆን በቀር ምንም አይጠቅምም።  "ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪን የሚሠጥ" እያልን በማለዳ ደጅ የምንጠናው አምላካችን ወደ መንፈሳዊ ማዕረግ ሊመጡ የታሰቡትን የቀደሙትን አበው መንፈስ እንዲያድልልን የምንጸልይበት ብርቱ ጊዜ ግን አሁን ነው። 

አንድ ገጣሚ እንዳለው "ቤተ ክርስቲያን እንደ ኦሪቱ ዘመን ምነው በድንኳን በሆነችና ምነው ጠቅልለን ይዘናት በሸሸን" የሚያሰኝ ጊዜ ላይ ነን።  ለምናየው ክፉ ነገር የኛን ኃጢአት ምክንያት ብናደርግና ብናነባ የሚሻልበት ጊዜ ነው። ለአንዱ ደግ መሪ ለሙሴ ሕዝቡን አጥፍቼ ሌላ ሕዝብ ልቀይርልህ ያለ ፈጣሪ ሕዝቡ ቅን ሆኖ ቢገኝ ደግሞ መሪ መቀየር የሚሣነው አይምሰለን። መሰዳደቡን ትተን ሃይማኖታቸው የቀና ደገኛ አባቶችን እንዲሾምልን እንጸልይ።
(ይ ዲ "ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን)

"በውስጥሸ ሰላም ይሁን አልሁ ፣ ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ። "
(መዝ 122:9)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+

=>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ)
ቅዱሳን ነው::

+"+ አባ አፍፄ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና
በሕጻንነታቸው
ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም
በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ
የመጡት
በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው::

+ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል::
ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር::

❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:-

1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት
ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት
አገልግለዋል::

2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት
ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ
ሕይወትን አስፋፍተዋል::

3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ
ግዕዝ ተርጉመዋል::

4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል::
ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ
(አፈ-ዐፄ)"
ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም
"ንግግር አዋቂ" ማለት ነው::

+ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን
አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል::
እግዚአብሔርም
በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት
ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::

+"+ አባ ጉባ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም
በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው
ቴዎዶክስያ ደጐች
ነበሩ::

+አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን
ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን
ተሞልቶ
ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው
አመስግነዋል::

+በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ
አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ
በኋላ ሊቀ
መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ
ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን
መጥተዋል::
በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር::

+ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል:
መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ
ክርስቲያናትን
በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት
የእርሳቸው ናት ይባላል::

+ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ
ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም
አንስተዋል::
እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ
ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው
በገዳማቸው
ተቀብረዋል::

+በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው
ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው::
(በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ-
ልሳን" ማለት ነው)

❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት
ያድለን::
በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::

❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81
ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ)
4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ
2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል
3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ
5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ
8፡ ጉባኤ ሰማዕታት

++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል::
ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም::
+"+ (ማቴ. 10:41)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ እኔንም አስበኝ +

ዮሴፍ በበደል ላይ በደል የበዛበት ሰው ነው:: ሆድ ብሶታል:: ከሀገሩ የወጣው ፈልጎ ሳይሆን የገዛ ወንድሞቹ  ሸጠውት ነበር::  ከመሸጡ በላይ በሥጋ ወንድሞቹ መጠላቱ ልቡን አቁስሎታል:: ዐሥር ወንድሞቹ ጨክነው ተስማምተው መሸጣቸውን ማሰብ ደግሞ በጣም ከባድ ነበር::

ባይተዋሩ ዮሴፍ እንደተከፋ ወደ ግብፅ ሲወርድ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር አብሮ ተሸጠ እንጂ ብቻውን አልተወውም::  በመከፋቱ አብሮት ተከፋ:: ስለኀዘኑም አብሮት አዘነ::

ዮሴፍ ጲጥፋራ በተባለ ሰው ቤት ባሪያ ሆነ:: በአባቱ ተወዳጅ ሆኖ ላደገው ቅምጥሉ ዮሴፍ በሰው ቤት ባሪያ መሆን እጅግ ከባድ ነበር::
ሆኖም በሰው ቤት ባሪያ በሆነ ጊዜ ግን የጌቶች ጌታ የሆነው እግዚአብሔር አብሮት ነበረ:: በጌታው ፊት ሞገስ ሠጥቶት ስለነበር የቤቱ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ ተሾመ::

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ ባሪያ ሆነህ ብትሸጥም ባለ ሥልጣን ትሆናለህ::

እረፍት አልባው ዮሴፍ በተሾመበት ቤት ብዙም ሳይቆይ ግን የጌታው ሚስት ለዝሙት አስቸገረችው::  እግዚአብሔር ን ፈርቶ አሻፈረኝ ሲላት ራስዋ ገርፋ ራስዋ ጮኻ እስር ቤት ጣለችው::

መከረኛው ዮሴፍ እስር ቤት ወረደ:: የታሰሩ ሁሉ ወንጀለኞች አይደሉም:: የአንዳንዶችን ኃጢአት ለመሸፈን የሚታሰሩ ንጹሐን ብዙ ናቸው::

ዮሴፍ ያለ በደሉ ሲታሰርም ብቻውን አልሆነም::
እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር አብሮ ታሰረ::  በበደል ላይ በደል ደርሶበት በገባበት ወኅኒ ቤት  "እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሠጠው"  ዘፍ. 39:21

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ እስር ቤት ውስጥም ትሾማለህ:: ዮሴፍ የወኅኒው ባለ ሥልጣን ሆነ::

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ በወኅኒው ለሁለት ሰዎች ሕልም ይፈታላቸው ጀመር:: የአንዱ ሕልም ፍቺ "ተሰቅለህ ትሞታለህ" የሚል ሲሆን የሌላኛው ሕልም ፍቺ ደግሞ "በፈርኦን ፊት ዳግመኛ ትሾማለህ" የሚል ነበር::

ወደ ፈርኦን ቤተ መንግሥት ተሹሞ የሚሔደውን ሰው ዮሴፍ እንዲህ አለው :-

"ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ::  እኔን ከዕብራውያን አገር ሰርቀው አምጥተውኛልና፤ ከዚህም ደግሞ በግዞት ያኖሩኝ ዘንድ ምንም አላደረግሁም።" ዘፍ. 40:14

ዮሴፍ "እኔንም አስበኝ ምሕረት አድርግልኝ" ብሎ የተማጸነው የፈርኦን ጠጅ አሳላፊ ግን "ዮሴፍን አላሰበውም፥ ረሳው እንጂ" ዘፍ. 40:23

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለሁለት ዓመታት በእስር ቆየ እንጂ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም::

ባሪያ ሆኖ ሲሸጥ አብሮት የተሸጠው እግዚአብሔር
እስር ቤት ሲገባ አብሮት የታሰረው እግዚአብሔር
አሁን ግን ዮሴፍን ዝም አለው::

ለምን?

ዮሴፍ  "እኔንም አስበኝ ምሕረት አድርግልኝ" ብሎ የለመነው የጠጅ አሳላፊውን ነበር:: በግፍ ከሀገሩ እንደወጣ ያለ በደሉ እንደታሰረ ያስረዳው ለፈርኦን ቤት ሹመኛ ነበር:: ስለዚህ እግዚአብሔር "ዮሴፍ ሆይ ጠጅ አሳላፊውን አስበኝ አልክን? በል እሱ ያስብህ" ብሎ ተወው::

በሕይወትህ ሰውን አደራ ያልክ ቀን እግዚአብሔር ይተውሃል:: "አውጣኝ"  ያልከው ሰውን ከሆነ  ፈጣሪ የሰውን ነገር እንድታይ ዝም ይልሃል::

ሁላችንም አደራ አስበኝ ብለን የተማመንንባቸው ጠጅ አሳላፊዎች አይጠፉም:: እንደ ዮሴፍ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሰው አለኝ ብለን ተስፋ የጣልንባቸው ፣ ዘመድ አለኝ ብለን የሙጥኝ ያልናቸው ሰዎች አይጠፉም:: "በአንድ ስልክ ልጨርሰው እችላለሁ እኮ" ብለን የተመካንባቸው ሰዎች አናጣም::

ወዳጄ እመነኝ ሰው አደራ በላ መሆኑ አይቀርም:: ቃል የገባልህ ሰው ወደ ሹመቱ ሲገባ አያስታውስህም::
ሥጋ ለባሹን አደራ ብለህ ከፈጣሪህ አትጣላ::

ሰውን በቤተ መንግሥት አስበኝ ከማለት ፈጣሪን በመንግሥትህ አስበኝ ማለት ይሻላል::

"በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል" መዝ. 118:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 6 2015 ዓ.ም.
ዲላ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+*" ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ "*+

=>ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት::

+አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች::

+አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች::

+በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር::

+ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች::

+ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::"

+ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች::

+በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ38 ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት::

+ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ:- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው::

+ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ38 ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም::

+እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም::

+አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት 28) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ::

+አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች::

=>አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን::

=>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት)
3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ
4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት)
5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት)
6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

=>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…
Subscribe to a channel