kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1940

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ሰኔ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

✞ ❇️አባ_ገሪማ (ይስሐቅ) መደራ❇️ ✞

=>አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም
ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ
እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት
ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ፡፡

+እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ
ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ
ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን
በፍትሕ
እያስተዳደረ: መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::

+አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው::
ላኪው አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ
ንግሥና ምን ያደርግልሃል?
ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና"
የሚል ነበር::

+ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው
ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት
ግን ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ
ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::

+እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው
አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ
መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና
ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል
ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::

+አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው
አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ
የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን
"ሰዎች ብቻ አይደሉም: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል"
ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (800 ሜትር)
ተጠራርጎ ሸሸ::

+ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን
"ወልድየ_ይስሐቅ_ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ)
አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም
"አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡

+አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና
ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም
ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል::

+ጻድቁ ወንጌልን: ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ
ተአምራትን ሰርተዋል:-

1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕ
ይዘርዕ: ወበሠርክ የአርር" እንዲል::
2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::
4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::
5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን
አቁመዋታል::

+ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን
ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው::
"ስምሕን የጠራ: መታሰቢያህን ያደረገ: እስከ 12 ትውልድ
እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው
ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ
ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡

✞ አባ ለትጹን የዋህ ✞

=>ስመ ጥሩ ጻድቅ አባ ለትጹን በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን
በግብጽ የተወለዱ:
¤በፍጹም ተግሣጽ ያደጉ:
¤ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን በሕገ ወንጌል የመሩ:
¤አንድ ቀን በሰሟት የወንጌል ቃል የመነኑ:
¤ገዳም ገብተው በትሕትና ለዘመናት ያገለገሉ:
¤በመጨረሻም ወደ ትልቅ ተራራ ወጥተው ተጋድሏቸውን
የፈጸሙ ታላቅ አባት ናቸው::

+ከየዋሕነታቸው የተነሳ ኃጢአተኛ ሰው ሲያገኙ ራሳቸው
ንስሃ ይገቡ ነበር:: አንዴ ግን እናቱን 10 ጊዜ በዝሙት
ያረከሰ: ስትጸንስም መርዝ አጠጥቶ ጽንሱን በማሕጸኗ
የገደለና በሥጋ ወደሙ ላይ የተዘባበተ ሰው ሊሞት ሲል
ደረሱ::

+አጋንንት ሲዖል ታች ሲጥሉትም ተመለከቱ:: ኃጢአቱ
ጭንቅ ቢሆንም የእርሱን ንስሃ ሊቀበሉ ጀመሩ: ከንስሃቸው
ጽናት
የተነሳ ሞቱ:: ጌታችን ከሞት አስነስቶ "አትለምነኝ:
አልምረውም" አላቸው::

+ጻድቁ ተስፋ አልቆረጡምና ቀጠሉ:: ለ2ኛ ጊዜ ሞቱ::
አሁንም ቀጠሉ: 3ኛ: 4ኛ: 5ኛ ጊዜም ሞቱ:: በ6ኛው ግን
መፍትሔ መጣ:: ጌታችን አእላፍ መላእክትን አስከትሎ:
ያችንም ኃጥእ ነፍስ ይዞ መጣ:: "ፍርዴ አይታጠፍምና
ወደ ገነት
አላስገባትም:: ስለ አንተ ጽድቅና የዋሕነት ደግሞ ሲዖል
አልጥላትም:: ስለዚሕም እንዳልተፈጠረች ትሁን" ብሎ
እፍ
አለባት:: ፈጥና ወደ ትቢያነት ተቀየረች::

+ጻድቁም የፈጣሪያቸውን ቸርነት አድንቀው ሰገዱ:: ከብዙ
ዘመናት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐረፉ::

✞ አባ_ዸላሞን_ፈላሲ ✞

=>ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ገዳማውያን አንዱ
አባ ዸላሞን የአባ ለትጹን ወዳጅ ነበር:: ይሕ ቅዱስ
ከአጋንንት
ጋር በገጠመው ጦርነት ምክንያት ለየት ይላል:: ከ60
ዓመታት በላይ እንኳን ሳቅና ደስታ ቀና ብሎም ሰው
አላየም::

+በነዚሁ ዘመናት ሁሉ ቅንድቡ እስኪላጥ አልቅሷል::
በዓለም ያሉ አጋንንት ሁሉ ተሰብስበው አሰቃይተውታል::
እርሱ ግን
በእግዚአብሔር ቸርነት: በወዳጁ በአባ ለትጹን ጸሎትና
በትጋት አሸንፏቸው ዛሬ ዐርፏል::

=>ቸሩ አምላካችን ከታላላቁ ቅዱሳን ጸጋ በረከት
ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::

=>ሰኔ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ብጹዕ አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ
2.አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ
3.አባ ዸላሞን ፈላሲ
4.ቅድስት አርሴማ ጻድቅት
5.ሰማዕታት እለ አኮራን
6፡ ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት
2፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ
3፡ ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ
4፡ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ

=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::ቅዱሳኑንም
አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን
ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን
ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ
ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የምንጸልየው

ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ ለመንገር ወይም የረሳው ነገር ኖሮ ለማስታወስ አይደለም፤

ወደ እርሱ እንድንቀርብ ቀረበን ወዳጆቹ እንድንሆን ዘወትር እንዲረዳን ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ ኃጢአታችንንም እንድናስብ ነው እንጂ።

ኃጢአት ምንድን ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:- ኃጢአት ማለት ለበጎ ስራ መታከት ለክፉ ስራ ግን መበርታት ማለት ነው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሳታቋርጡ ጸልዩ

ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በፀሎት መዋል አይችልም፤ አትበለኝ ይችላል ።

በጸሎት የሚያስፈልገው

ድምጽ ሳይሆን አሳብ ነው
እጅ ሳይሆን እደ ልቡናን ማንሳት ነው ፤
አፋአዊ ሳይሆን ውሳጣዊ እኳኋን ነው ።

ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም።

በጉልበትህ ባትንበረከክ ደረትህን ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከኾነ ጸሎትህ ስልጡን ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ከመዝሙር ማህደር +

ድል አለ በስምህ

ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ሰልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ሰልህ

አዝ ====

ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው  ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ሰምህ ነው

አዝ ====
 
በእልልታ ቢፈርሰ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው/2/

አዝ ======
      
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ

አዝ=====

የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግሰ
ሆነኸ ነው ክብርና

ዘማሪ ገ/ዮሀንስ ገ/ፃዲቅ

📍Chanel፦ /channel/+r1scfiBj_po2MjY8

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Menfesawi gtm kalachu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞ ✞ እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞

=> #4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ
ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ
እና #አባ_ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት
(ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው) ካህናትና ሃብታሞች
ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው::

+ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ
እየተቀበሉ: ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ
እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ
በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ
ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ:
ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ
ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ::

+በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር
ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ
መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ::
የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ
መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ:
ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ::

+በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ
አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ
መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና:
የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ::

+አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን
አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ
ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት
አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) አደረጉ::

+በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ
የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን
አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ::
በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ
ድፍረት ነበር::

+መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት
አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም:
በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን
አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ::
በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው
ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና
ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን
ተቀብለዋል::

=>የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

=>ሰኔ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አበው ሰማዕታት (አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ
አብጥልማ: አባ ፊልዾስ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_14

#ቅዱሳን_አባ_አክራና_ዮሐንስ_አብጥልማና_ፊልጶስ

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ አራት በዚች ቀን ቅዱሳን አባ አክራና፣ ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና፣ አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ።

መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አድረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም።

ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧችው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ቆረጡአቸው። ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጡ። እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዳሳን የፊልጶስን፣ ለአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገነዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቁጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ 𝐝𝐧𝐰𝐞𝐠𝐞𝐧 || 𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 ༒

👉 ከሚከተሉት አማራጮች መሀከል ክርስቶስ ለሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉሙ የሚሆነው የትኛው ነው?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝ከዚኸም በኋላ አቡነ ማትያስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው በጾም በጸሎት ተወስነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እየተቀበሉ ማገልገል ጀመሩ። በዚኸም ጊዜ ሰይጣን በሥጋቸው ፈተናቸው። እርሳቸውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው ‹‹ኦ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበላት፣ ግደለኝ፣ እንዴት ከተወለድኹ ጀምሮ እስከዛሬ ፍጹም የማላውቀው መጥፎ ሀሳብ ከሚመጣብኝ ሞት ይሻለኛል፣ ግደለኝ" እያለ ሲጸልዩ የክብር ባለቤት ጌታችን በአካል ተገልጦላቸው በመለኮታዊ እጆቹ ዳስሶ ፈጽሞ አዳናቸው።

✝ከዕለታት በአንደኛው ቀን አቡነ ማትያስ ከአንድ መነኵሴ ጋር ለገዳሙ ማኅበር ምግብ ለማዘጋጀት ወደ በረሓ እንደደረሱ የሚጠጡት ውኃ ሲያጡ አባታችን ማትያስ ጸሎት ካደረሱ በመላ በበትራቸው መሬትን ባርከው እንዴ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ውኃ አፈለቁ። እነርሱም የማኅበሩን ምግብ ይዘው ሲመለሱ በመንገድ ላይ ሽፍቶች አግኝተዋቸው ምግቡን ወሰዱባቸው፤ አባታችንም ጸሎት ቢያደርጉ ወዲያው እነዚያ ሽፍቶች ታመው ወደቁ። ከዚያም ሽፍቶቹ ‹‹እናንተ የአምላክ ሰዎች ሆይ! እባካችሁ ይቅር በሉን፣ የወሰድንባችሁንም እንኩ ውሰዱ፣ እኛንም እርዱን…›› እያሉ ለመኗቸው። አባታችንም ምራቃቸውን እንትፍ ብለው በትእምርተ መስቀል አማትበው በእርሱ ዳበሷቸውና ሽፍቶቹ ዳኑ። ዳግመኛም በአንደኛው ቀን መነኰሳቱ ሁሉም ሥራ ጨርሰው ተኝተው ሳለ አቡነ ማትያስ ግን ደከመኝ ሳይሉ መቶ ሃምሳውንም መዝሙረ ዳዊት ሲደግሙ አደሩ እግዚአብሔርም መላእክቱን ልኮ አንድ ፈረስ ሰጣቸው. አባታችንም በዚህ ተደስተው ለኹለተኛ ጊዜ መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት ሲደግሞ አሁንም ለኹለተኛ ጊዜ ፈረስ ተላከላቸው። ከእርሳቸውም ጋር የነበሩት መነኰሳት ምን እንደተፈጠረ ሳያውቁ ተኝተው አደሩ።

✝አቡነ ማትያስን መላእክት ወደ ሰማያት አውጥተዋቸው በገነት ተድላ ያሉ ጻድቃንን አሳይተው ዳግመኛም የኀጥአንን ፍዳና መከራ አሳዩዋቸው።
✝ አባታችንም የኀጥአንን መከራ አይተው አዝነው ደንግጠው አለቀሱ። በዚኸም ጊዜ ‹የተመረጥህ ማትያስ ሆይ! አትፍራ፣ እነዚህ ሕጌን የማያከብሩ ትእዛዜን ያፈረሱ ናቸው፣ በተድላ ገነት ያየኻቸውም ጻድቃን ናቸው›› የሚል ቃል አጽናናቸው። ከዚኸም በኋላ አባታችን ወደ ምድር ተመልሰው በመጡ ጊዜ አበ ምኔቱ አባ ተወልደ ምድኅን ዐርፈው በእርሳቸው መንበር አባ ፊቅጦር ተተኩ ከአባ ፊቅጦርም በኋላ አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት መሠረት አቡነ ማትያስን መርጠው ለመሾም ተስማሙ ነገር ግን አባታችን ማትያስ ሹመቱን እምቢ ሲሉ እጅና እግራቸውን አሥረው በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው።

✝አቡነ ማትያስም ወደ ሰማያት ወጥተው የጻድቃንን ደስታና የኀጥአንን ፍዳ መከራ ከተመለከቱና ወደምድር ተመልሰው ከመጡ በኋላ መነኰሳቱን ሁሉ ሰብስበው ሕግንና ሥርዓትን ተግብረው ይኖሩ ዘንድ ስለነገሯቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዳንድ ክፉዎች ወደ ንጉሡ ዘንድ ሔደው በብዙ ነገር በሐሰት ከሰሷቸው።

ንጉሡም የተነገረው ሁሉ እውነት መስሎት አባታችንን ከሥልጣን አወረዳቸውና አሳደዳቸው።
✝ አቡነ ማትያስም ከገዳሙ ወጥተው ሲሔዱ ከአንተ ከአባታችን አንለይም ብለ230 መነኰሳት አብረዋቸው ሔዱ። ከዚኸም በኋላ ‹‹ትኹል ጎዳዕ፣ ጨዓት፣ ቃቕብዳ፣ ኣቄታብ፣ ወኪ፣ ምድረ ባሕር ወደተባሉ የተለያዩ ቦታዎች ሔደው በተጋድሎ ኖሩ። በየበረሓውም ሲጓዙ ልጆቻቸው ውኃ ሲጠማቸው✝አባታችን መሬትን ባርከው ውኃ አፍልቀው አጠጧቸው። አባታችንም በምድረ ባሕር ሣሉ እህል ሳይቀምሱ በአንዲት ዋሻ ለኹለት ሳምንት ከቆዩ በኋላ በዚኸች ቦታ ላይ በሞት ማረፍ ፈለጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ‹‹ለአንተ የምትሆን ምድር አዘጋጅቼልሃለሁና ወደልጆችህ ተመለስ›› አላቸው።

✝አባታችን ዳግመኛም ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ወደ ዓንደቕ ከዚያም ወደ ዒላ ሔደው ለ66 ቀናት ከቆዩ በኋላ ደብረ ብርሃን ደረሱ። አባታችንም ይኸችን ቦታ ‹‹እግዚአብሔር የሰጠን ገዳማችን ናት›› አሉ። ቦታዋንም ደብረ በረከት ብለው ሰየሟት።

✝የዕረፍታቸውም ጊዜ ሲደርስ ልጆቻቸውን ሰብስበው በቃለ እግዚአብሔር አጽናንተው “በሥጋ ብለያችሁም በመንፈስ ግን ከመካከላችሁ አልለያችሁምና አትፍሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፡ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስንና የአቡነ አብሳዲን ሥርዓት ጠብቁ…›› ብለው ከመከሯቸው በኋላ በእርሳቸው ቦታ ዮሐንስን ሾመውላቸው ከጌታችን ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ሠኔ 13 ቀን በሰላም ዐረፉ።

✝አቡነ ማትያስም ካረፉ በኋላ ለልጆቻቸው በአካለ ነፍስ እየተገለጡ አጽናንተዋቸዋል። ከማረፋቸውም በፊት አስቀድመው ‹‹…ከእናንተ ውስጥ የሚማረኩ አሉ፣ ነገር ግን እኔ አድናችኋለሁ›› ብለዋቸው ስለነበር ትንቢታቸው ደርሶ ኹለቱ መነኰሳት ተማረኩ ነገር ግን በአባታችን ጸሎት ወደ ገዳማቸው ተመለሱ። ዳግመኛም ከመነኰሳቱ ውስጥ ሰባቱን ዐረማውያን ማረኳቸው፣ ንብረታቸውንም ወስደው ኹለቱን ገድለው፣ አምስቱን በባሕር ውስጥ ጣሏቸው፤ በዚኸም ጊዜ አባታችን ማትያስ በአካለ ነፍስ መጥተው ‹‹ልጆቼ አይዟችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና" አወጣችኋለሁ ባሕሩንም በእሳት አቃጥለዋለሁ "ብለው ካወጧቸው በኋላ ባሕሩን በእሳት አቃጥለውታል።
የአቡነ ማትያስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጽሎታቸው ይማረን።
ምንጭ #በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ የተወስደ
ሠኔ 13/10/2015ዓ.ም
Kuwait

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ከመዝሙር ማህደር +

+ ብዙ ልጆች አሉት +

ብዙ ልጆች አሉት ለሥሙ ምሥክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃው ለእኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል

ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል በአለበት ይሸሻል ጠላቴ

አዝ

ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ

አዝ

በባሕራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና

አዝ

በጉዞ የረዳችሁ በባሕር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ ዕንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ

አዝ

ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት


Chanel፦ /channel/+r1scfiBj_po2MjY8

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይድረስ ለብዙ አፎምያዎች
ይድረስ ለብዙ ባሕራኖች

የአፎምያ ጥያቄ የባሕራን መልስ
#ቅዱስ_ሚካኤል
_________

እርግብ የምታገባው አንድ ብቻ ነው። ቢሞት እንኳን ሌላ መጥቶ እንዳይተናኮላት ምላሷን ትሰነጥቃለች። ድንገት ቢመጣባት በደንብ መጮህ እንድትችል እና ሌሎች መጥተው ደርሰውላት እንዲያባርሩላት ነው። ቅድስት አፎምያም እንደ እርግ የምትኖር ደገኛ ሴት ነበረች።

የኬልቅያ መስፍን የነበረው የምትወደው ባሏ አስተራኒቆስ በሞት ከተለያት በኋላ በዕውቅ አስሎ የሰጣትን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ይዛ በጾም በጸሎት ተስና ስትኖር ጸላዬ ሰናያት የመልካም ነገሮች ሁሉ ጠላት የሆነ ሰይጣን ዲያቢሎስ ደግ መነኩሴ መስሎ መቶ ጾም ጸሎት እንድትተው ሌላ ባል አግብታ ተድላ ደስታ እንድታደርግ መከራት እርሷ ግን አባ አለባበሶት ደግ ነበር ንግግሮት ግን የከፋ ነው። ጾም ፣ጸሎት ና ምጽዋት ደገኛ ሥርዓት አይደሉምን? ስለምንስ ዳግመኛ እንዳገባ ይመክሩኛል በሉ ከኔ ወግዱልኝ ብላ አሳፍረችው። ይህን ግዜ የደበቀውን ሰይጣናዊ ግብር ገልጦ ቆቡን ጥሎ ከቁራ ሰባት ጅ ጠቆረ ሰኔ አሥራሁለት ቀን ተመልሼ እመጣለሁ አጠፋሻለሁም ብሎ ዝቶባት እንደ ጢስ ተኞ እንደ ትብያ ተኖ ጠፍቶ ሄደ ።

ሰይጣን ዲያቢሎስ እንዳለሁም ግብሩን ለውጦ በሰኔ አሥራ ሁለት ቀንም የመላእከት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን መስሎ ባማረና በተዋበ ልብስ ወደ ቤቷ መጥቶ ተገለጠላት “ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” ተብሎ እንደተጻፈ 2ኛ ቆሮ 11፥14

ቤቴን በብርሃንህ የሞላህ አንተ ማነህ ? አለችሁ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ይህ ከብርሃኔ ተረጂ አላት ቆየኝ መጣው ብላ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጂ የነበረው ባሏ አስተራኒቆስ አስሎ ነሰጣትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕለ አድህኖ ይዛ መጣች ። እያመሳሰለችሽ ንጉሥ ለጭፍሮቹ መታወቂያ ማኅተቡን አትሞ አስይዞ ይልካቸዋል የእግዚአብሔር መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ከሆንክ ማዕተመ መስቀልህ የንጉሥህ መታወቂያ በትረ መስቀልህ የታለ ?አለችሁ። እርሱም ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና እኛ በእግዚአብሔር ፊት የምንቆም መላእክት መስቀል መያዝ ለምናችን ጨርሶ አያስፈልገንም አላት ይህን ጊዜ አንተማ መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል አይደለህም አላምንህም አለችሁ ያን ጊዜ እንዳ ወቀችበት ሲረዳ ግብሩ ቀይሮ በብርሃን የመላው ቤቷን በጽልመት መላው ቀንዱ በቀለ ፣ጥፍሩ እረዘረዘ፣ ዐይኑ ፈጠጠ ፣ጥርሱ ገጠጠ አንቺንስ ካላጠፋሁ ሠላሜን አላገኝም ብሎ ተወርውሮም አንቆ ያዛት ቅድስት እናት አፎምያም እውነተኛው ታላቁ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እርዳኝ ብላ በጣር ውስጥ ሆና ተጣራች እውነተኛው የእግዚአብሔር መላእክም ከዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጣና ዲያቢሎስን ረግጦ ያስጨንቀው ገባ ሰይጣንም ሚካኤል ሆይ ጊዜዬ ሳይደርስ እንዳታጠፋኝ በፈጣሪህ እለምንሃለው እያለ ጮኸ ቅዱስ ሚካኤልም ለቀቀው በኖ ተኖ ጠፋ ቅድስት እናት አፎምያንንም ያረጋጋት ጀመር ። “ #የእግዚአብሔር_መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” እዳለ መጻሕፍ #መዝ (33) 34፥7

*አንባቢ ሆይ አንተስ በክርስቶስ ክርስቲያን ነኝ ትላለህንን እንግዲያውስ መስቀልህ የታል?
*አንባቢት ሆይ የንጉሥሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ትያለሽን? መልካም ትያለሽ ግን የንጉሡ ደመ ማዕተብ በትረ መስቀልሽ ከወዴት አለ? የአፎምያ ጥያቄ ይህ ነበር መስቀልህ የታለህ? ለአፎምያ ትክለኛ ጥያቄ መልስ የሆናት እውነተኛው ቅዱስ ሚካዬል በትረ መስቀሉን ጨብጦ ይዞ በመታየት ነው።ወዳጄ የድልህ ዐርማ የሆነውም " ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል። " #ምሳ 6÷21-22 የደሃ አደጊቱ ልጅ ባሕራንም የሞት ደብዳቤውን ተቀብሎ የደስታ የፍስሐ የሰርግ ደብዳቤ አድርጎ የመለሰለት የደስታ ሁሉ መልስ ቅዱስ ሚካኤል በዚህች ዕለት በነገዱ ሁሉ ላይ የተሾመበት የሹመቱ በዓል ነው!

መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን ሰይጣን የሸመቀው ከጠላት የተንኮል እንቆቅልሽ ሁሉ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የደስታ መልስ ይሁንልን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
ሰኔ ፲፪ ቀን /፳፻፲፫ ዓ.ም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከመውጣታችን በፊት ላይክና ሼር እናርግ ሳንረሳ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

https://youtu.be/dRB-B8ssiRs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ dnwegen || telegram ༒ቁ .77

👉 በብሉይ ኪዳን እስራኤልን በ 7 አመደ ደመና እየመራ ከግብፅ ባርነት ነፃ ወደ ሚወጡበት ከነአን  የወሰዳቸው እና  ወር በገባ 12ት የሚከበር  መጋቤ ብሉይ ተራዳይ ሀዲስ መላክ ስሙ ማን ነው?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔እለተ ቅዳሜ እንዴት ነበር.. ?

🙏የቀኖች ሁሉ ባለቤት የተመሰገነ ይሁን🙏

መልካም ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏

#besufkadbogale #bsquadcompanyy
Besufkad Bogale

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒ Dn Wegen ༒

+ ቴቄል +

መናፍቃን ፦ " እኔ መንገድና እውነት ነኝ። በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም.." ዮሐ 14÷6

ይሄን ቃል ይዘው ኢየሱስን ያማልዳል ይሉታል። ከሱ በቀርም አማላጅ የለም ምክንያቱም ከኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ስላለ ይሉናል።

መልስ

እኚህ ወንድሞቻችን በዚህ አባባላቸው ክብር ይግባውና አብንም አማላጅ ሳያረጉት አልቀረም ምክንያቱም በሌላ ቦታ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለና
" አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሚመጣ የለም " ዮሐ 6÷44

ስለዚህ ከአብ በቀር አማላጅ የለም!!!!
ለምን ወደ ወልድ ለመሄድ የአብ መሳብ "ማማለድ " ስለሚያስፈልግ ማለት ነው!

በዚህ ጥቅስ ዮሐ 14÷ 6 "ከኔ ...በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " ስላለ አማላጅ ይሆናል የሚለው ሀሳብ ውድቅ ይሆናል!!!!


ዮሐ 14÷ 6 ትርጓሜ

ጌታችን እዚህ ምዕራፍ ላይ ያለውን ቃል የተናገረው እነሱ እንዳሉት አማላጅቱ ለማሳየት ሳይሆን የቶማስን " የመንግስተ ሰማያትን መንገድ እና ስለ እግዚአብሔር አብ አናውቅም እኮ" የሚል የግራ መጋባት ጥያቄን ለመመለስ ነበር።

ዮሐ 14÷1 ስንጀምር ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መንግስተ ሰማያት ፣ ስለ ዕርገቱ እና ስለ ዳግም ምፅአት እየተናገረ እናገኘዋለን።

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።

ይቀጥልና ለናንተስ የመንግስተ ሰማያት መንገዱ አይጠፋችሁም ሲል እንዲህ ይላቸዋል።

“ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።”
— ዮሐንስ 14፥4

ይሄኔ ጥርጣሬ የማይጠፋው ቶማስ "ጌታ ሆይ ወደ አባቴ እሄዳለሁ ብለሀል ታዲያ አባትህን አብን ሳናውቅ እንዴት መንግስተ ሰማያት ምንገባበት መንገድ ልናውቅ እንችላለን። ሲል ጥያቄን አቀረበ

“ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው።”
— ዮሐንስ 14፥5


ጌታችንም ቶማስ ሆይ አብን ስለ ማወቅ ተጨነክን አብን ለማወቅ እኮ እኔን ማወቅ ይበቃል እኔን ልጅ ብለህ ስታመን አብን አባት ብለህ ታምናለህ እኔን ቃልነቴን ስታውቅ የአብን ልብነት ትረዳለህ። አብን ሆነ መንፈስ ቅዱስን ወደ ማወቅ መምጣት የሚቻልህ መንገድ የሆንኩትን እኔን ስታውቀኝ ብቻ ነው ምክንያቱም እኔ ሰው ባልሆን ኖሮ ሚስጢረ ሥላሴን አብ (አባት ) መንፈስ ቅዱስ (ህይወት) ወልድን (ልጅ) ብለህ መናገረ ባልተቻለህም ነበርና። ሲል በሱ መንገድነት በቀር ሚስጢረ ሥላሴን መረዳት አለመቻሉን ነገረው።

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
⁷ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።

ሀሳቡን ለመጠቅለል ያህል የዚህ ጥቅስ ሀሳቡ እኔ መንገድ ነኝ ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም የሚለው ቃል እግዚአብሔር አብን አባት ብላችሁ ምታውቁት በስጋ ተወልጄ በዮርዳኖስ ላይ አንድነቴን ሶስትነቴን በመግለጥ እና ሚስጢረ ሥላሴን ወደ ማወቅ በወሰድኳችሁ መንገድ በሆንኩት በእኔ ብቻ ነው። እኔን ልጅ (ወልድ) ካላላችሁ በቀር አብን አባት ወደ ሚል እውቀትም እምነትም ልትመጡ አትችሉም የሚል ነው እንጂ አማላጅነቱኝ ለማሳየት አይደለም!!!!


✍️ ዲ/ን ወገን

Channel ፦ /channel/+M7qVg_GW8IFjNTZk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከልብ የመነጨ ጸሎት

እኔ ጸሎት የምለው እንዲሁም በከንፈር የሚነበነበውን አይደለም።

እኔ ፀሎት የምለው ከልብ ጥልቀት የሚወጣውን ነው።

ጥልቅ የኾነ ሥር ያላቸው ዛፎች አውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ በቀላሉ አይነቅላቸውም።

ከልብ ጥልቀት የሚወጣና ሥሩ እዚያ ውስጥ ያደረገ ፀሎት እንደዚሁ አማን በአማን ወደ መንበረ ጸባኦት ያርጋል።

እንደ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ሁከት በቀላሉ አሳቡ አይበተንም።

ክቡር ዳዊት:- "አቤቱ ከጥልቅ ጠራሁህ " ያለውም ይህን ነው መዝ 129፥1


ጸሎት:-

እሳትን ዉኃ አንበሳን በግ ታደርጋለች

ጦርነትን ታስቀራለች

የመንግስተ ሰማያትን ደጅ ትከፍታለች

የሞት ሰንሰለትን ትበጥሳለች

ሁከትን ታቀዘቅዛለች

አጋንንት እንደ ጢስ ተነዉ እንዲጠፉ ታደርጋለች

ብዙ ከተሞችን ከመፍረስ ትጠብቃለች

ፀሀይ መሔዷን እንድታቆም ታደርጋለች

ሐሰትን ታርቃለች የነፍስ የስጋ ንውጽውጽታን ታረጋጋለች።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👉አስተውል👈

➯ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል።

➯ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

➯ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_15

#ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የሰማይ ጭፍራ የተባለ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው። የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና።

እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያንም ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።

ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን አለ ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል ሚናስ ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት ። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ አረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ አረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ።

መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።

ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ ። በዚያንም ጊዜ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊሎችን ሲያቀዳጇቸው አየ። ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና።

መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።

የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈፀም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።

በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት።

እነርሱም በባሕር ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱስ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጠለቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።

ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በግመል ላይ በጫኑት ጊዜ ግመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ግመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እምቢ አለ። አብዝተውም ደበደቡት ግመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው በዚያ ቀበሩት።

ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ፡፡ ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ፥ የቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበቀ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጉድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ። እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ።

ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ፡ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋር አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ። ለንጉሡም የቁስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው። ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ በዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አላት።

ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች። የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ሰሟም መርዩጥ ተባለች።

እግዚአብሔርም ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቁጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋራ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ_እና_ዘወርኀ_ኅዳር_15)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ለ 19 ❤❤ ለ አባቴ ለአብሳሪው 19❤❤

አባት ብቻ 😍
ቃሉ የማይገልፅህ😍
ስጠብቀኝ አለህ😘
መቼም አልሰለቸህ 😍
ከቤትህ አኑረህ😘
በእቅፍህ ሸሽገህ ❤
ልጅህ ያደረከኝ😍
በፍቅርህ ገዝተህ❤
የዋዐ ነህ የለህ አምሳያ😍
የሰማያት ድምቀት😘
ኮከቤ ነህ ለኔ የብርሀኔ መታያ😘
ገብርኤል አባቴ ❤
የሰላም አብሳሪ የነብሴ አፎይታ😍
ስምህን ሳልጠራ 😘
መዋል አልችልም ለአንድ አፍታ 😍
ከአፌ የታተመው ስምህ ሰላም አለው❤️
የሰላም አብሳሪ የኔ ገብርኤል ነው ❤❤❤❤
19 19 19😍😍😍😍😍😍😍😍😍
ይለይብኛል ገብርኤል ይለይብኛል ❤
በፍቅሩ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል

በ19 መወለድ ምነኛ መታደል 😍😍❤
19የኔ ቀን selina ❤19😍እየሉጣ 😘

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒𝐃𝐧 𝐖𝐞𝐠𝐞𝐧 ༒

      + ቴቄል +

መናፍቃን ፦ "“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”
  — ሮሜ 8፥34

ስለ እኛ የሚማልደው ይላልና ኢየሱስ አማላጅ ነው ይሉናል።

            መልስ

አኚህ ወንድሞቻችን  በዚሁ  አተረጓገማቸው ከፀኑ በጊዜ ሂደት እግዚአብሔር አብ ራሱን አማላጅ ማረጋቸው አይቀሬ ነው። ምክንያቱም  ትንቢተ ኤርሚያስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ።

“አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር።”
  — ኤርምያስ 7፥25

እየማለድሁ ብሎ እየተናገረ ያለው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር አማላጅ ነው ማለት ነው??!!!!

አኛ ብቻ በወንድሞቻችን አተረጓጎም ስልት እንፅና እንጂ  ምን  እግዚአብሔር አብን ብቻ መንፈስ ቅዱስንም አማላጅ ሆኖ እናገኘዋለን!

“.... ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”
  — ሮሜ 8፥26

እዚህ ቁጥር ከላይ ጀምሮ ስለ  መንፈስ ቅዱስ አርዳታ እየተናገረ የሚመጣ ቁጥር ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስም አማላጅ ነው??!!!

ስለዚህ ማንኛቸው ሊያማልዱን ነው? አብወልድ ወይስ መንፈስ ቅዱስ???

======================
ሮሜ 8÷34 ትርጓሜ
 
   ይሄ ሮሜ 8÷34 የሚማልደው የሚለው ቃል    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በምትቀበለው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጨርሶ የሌለ ትርጓሜ አልባ  የሆነ መፅሐፉን ሲያሳትሙ ለምንፍቅና ትምህርታቸው እንዲመቻቸው ሲሉ ብቻ የጨመሩት አዲስ ባንዳ ቃል ነው!!!! 

ይሄን ለመረዳት ያህል ከፍ ብለን ከ ቁ 33 ማንበብ እንጀምር ቃሉ እንዲህ ይላል

“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?”
  — ሮሜ 8፥33

እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል  ማንስ ይቃወማቸዋል ይልና  የሚኮንን ማን ነው ብሎ ይጠይቃል።    መኮነን የሚለው ቃል ሳይተረጎም ቀጥታ "ኮነነ" ከሚል የግዕዝ ቃል የተወሰደ  ሲሆን ትርጉሙም "ፈረደ፣ ገዛ "  የሚል ይሆናል።  ተርጉመን ጥቅሱን ስናስቀምጠውም

“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚፈርድስ ማን ነው?”
  — ሮሜ 8፥33  የሚል ይዘት ያለው ይሆናል።  ቀጣይ ምናገኘውን ጥቅስ የፃፈው ከላየኛው ለጠየቀው ጥቅስ መልስ መልስ ለመስጠት ነው።

በዚህ መልኩ መልን ይሰጥበታል

""የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ __ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”
  — ሮሜ 8፥34
ይሆናል።

እንደ ወንድሞቻችን አካሄድ ከሄድን እና በባዶው ቦታ የሚማልደው የሚለውን ቃል ካስገባን  ምናገኘው ትርጓሜ 

" የሚኮንንስ (ሚፈርድስ) ማን ነው? ..... ስለ እኛ ሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው"" የሚል ትርጉም እናገኛለን።

በቀላሉ እንድትረዱት  ሌላ ሰዋሰዋዊ ምሳሌ ልስጣችሁ

" የሚለበስ ነገር ምንድነው?" ለሚል ጥያቄዊ አረፍተ ነገር መልሱ ልብስ ነው መባል ሲገባው ከዚህ ይልቅ ግን "" ከጥጥ ፣ ከሐር ወዘተ አምሮ ተውቦ የሚዘጋጅ መጠጥ ነው ""  ወደ ሚል ግራ የገባው ዐረፍተ ነገር እንደ ማምራት ማለት ነው። 

የሚኮንን (የሚፈርድ ) ማን ነው?ለሚል ጥያቄ መልሱ   በአብ ቀኝ ያለው ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ የሚል መሆን ሲኖርበት በአንፃሩ ግን ስለ እኛ የሚማልደው የሚለውን ቃል ማስገባቱ ሀሳቡንም ሆነ ትርጓሜውን የሚያውክ ነገር ነው! 

ወንጌላዊው ዮሐንስም ለነዚህ አይነቱ ሰዎች ነው ይሄንን ቃል የተናገረው

“.....ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤”
  — ራእይ 22፥18

በነገራችን ላይ እነሱ ያስገቡት ያማልዳል የሚል ቃል ከስር ክርስቶስ በተናገረው ጥቅስ ወዳቂ ይሆናል!

“በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤”
— ዮሐንስ 16፥26


በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ያለው ብላችሁ በስሜ ትለምናላችሁ እኔ ግን ስለ እናንተ አብን የምለምን (የምማልድ ) አይደለሁም ሲል ነው ምክንያቱ ደግሞ

“ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም”
— ዮሐንስ 5፥22-23


ይሄ የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። ለወልድ የተሰጠው የወልድ ተግባር መፍረድ እንጂ ማማለድ ስላልሆነ

ለማጠቃለል ፦ ይሄ የሚማልደው የሚለው ጥቅስ ኦርቶዶክሳዊያን ጋርም ሆነ ሌሎች Oriental Church ጋር የሌለ  ፈፅሞ ትርጉም የማይሰጥ ባዕድ ቃል ነው። 

ስለዚህ የሚማልደው በሚለው ቃል ኢየሱስን አማላጅ የማድረጉ ሀሳብ ውድቅ ይሆናል!!!

✍ዲ/ን ወገን

እግዚአብሔር በቸርነቱ እንዲያስበኝ ስለ እኔ አጥብቃችሁ ፀልዪልኝ🙏

Chanel ፦ /channel/+M7qVg_GW8IFjNTZk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/C_JVTgcb12c

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

༒𝐃𝐧 𝐖𝐞𝐠𝐞𝐧 ༒

+ ከመዝሙር ማህደር +

✞ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ✞

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሀይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደደረሰ
ከእራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ

ህልምንም አለመ ታላቁን ራዕይ
መሰላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሰማይ
ሲወጡ ሲወርዱ መላዕክት በርሷ ላይ
እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፏ ላይ

✞ አዝ ....

ያባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ
ይህን ምድር ለርስትህ እሰጥሀለሁኝ
ዘርህ እንዳሸዋ በምድር ይዘራል
ባ'ራቱም ማዕዘን ህዝብህም ይሆናል

✞ አዝ ....

አበው በምሳሌ እንደተናገሩት
ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋት
በላይዋ ተቀምጦ በግልጽ የታየባት
የያዕቆብ መሰላል እመቤታችን ናት

✞ አዝ ....

ሰማይና ምድር የሚታረቁባት
ወልድእጓለመ ህያው የተወለደባት
መላዕክት ከሰማይ ባንድ የዘመሩላት
ታላቋ መሰላል እመቤታችን ናት


📍Chanel፦ /channel/+r1scfiBj_po2MjY8

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† ቅዱስ ገብርኤል :-
¤በራማ ከሚኖሩ ሊቃናት አንዱ::
¤አርባብ በሚባሉ አሥር ነገዶች ላይ አለቅነትን የተሾመ::
¤የስሙ ትርጓሜ "እግዚእ ወገብር" (ጌታና አገልጋይ) አንድም "አምላክ ወሰብእ" (የአምላክ ሰው መሆን) ማለት የሆነ::
¤በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ያረጋጋ::
¤ብርሃናውያን መላእክትን የሚመራ::
¤በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብሣሪነቱ በስፋት የተነገረለት::
¤በተለይ ደግሞ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ዜና ይሸከም ዘንድ ያደለው::
¤ከድንግል ማርያም ጎን በፍጹም የማይርቅ::
¤በፈጣን ተራዳኢነቱ ብዙ ቅዱሳንን ያገለገለ ታላቅ ቀናዒ መልአክ ነው::

በዚሕች ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ባቢሎን ልኮታል:: ሊቀ መላእክት ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስቱ ጥርስ እንዳዳነው መጽሐፍ ነግሮናል::

ይልቁኑ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል የተማረኩ ወገኖቹን መመለስ እያሰበ በሃዘን ሲጸልይ በዚሕ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ዳስሶታል:: ባርኮታል:: አጽናንቶታል:: ለዳንኤል በዋነኛነትም ሦስት ምሥጢራትን ገልጾለታል:-

1.የቤተ እሥራኤልን ከሰባ ዘመን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ::

2.የክርስቶስን ሰው መሆንና መሞት::

3.የሐሳዌ መሲሕን በመጨረሻ ዘመን መምጣት ነግሮታል:: ስለዚህም እኛ ቅዱስ ገብርኤልን እንድናከብረው : በጸሎትም እንድንጠራው አባቶቻችን አዝዘውናል::

††† አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም †††

††† ጻድቁ ሃገራቸው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ሲሆን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ባልንጀራ ናቸው:: ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በክርስትና አድገው : ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው ወደ ገዳም መንነዋል::

ከታላቁ ኮከበ ገዳም አባ ኢላርዮን ሥርዓተ መነኮሳትን አጥንተው አባ ኤስድሮስን በረድዕነት አገልግለዋል::

ከብዙ ዓመታት ትሕርምትና ገዳማዊ ሕይወት በኋላ የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል:: በጵጵስናቸው ዘመን አንድ ከባድ ስሕተት ሠርተው ነበር::

እርሱም ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ከምእመናን የተሠበሠበውን ገንዘብ ለግል ጉዳያቸው አውለው ልብሳቸውና ቤታቸው ወርቅ በወርቅ ሆኖ ነበር:: ፈጣሪ ግን ይሕንን ብክነት ከእርሳቸው ያርቅ ዘንድ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ላከው::

እርሱም በምክንያት ከቆጵሮስ ኢየሩሳሌም ገባ:: ጓደኛ ናቸውና አሳምኖ የወርቅ ንብረቶቹን ሁሉ ወሰደ:: ለነዳያንም ሰጣቸው:: አባ ዮሐንስ ሊቁን "እቃየን ካልመለስክ" ብለው ቢይዙት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸልዮ ዐይናቸው እንዲታወር አደረገ:: አንዳንዴ የታወረ ልብ የሚገለጠው እንዲሕ ነውና::

በደቂቃዎች ልዩነት ዐይነ ስውር የሆኑት አባ ዮሐንስ አለቀሱ:: ሊቁንም "ራራልኝ : አማልደኝ?" አሉት:: እርሱም ጸልዮ አንድ ዐይናቸውን ብቻ አበራላቸው:: "ለምን?" አሉት:: "ተግሳጽ ነው" አላቸው::

ከዚያች ቀን በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ልቡናቸው ተመለሱ:: ቤታቸውን ገዳም አደረጉት:: በሚደነቅ ቅድስና : ፍቅርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ምዕመናንን አገልግለው በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል::

††† የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት : የአባ ዮሐንስ በረከት አይለየን::

††† ሰኔ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ወደ ዳንኤል የወረደበት)
2.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባታችን ቃይናን (ከአዳም አራተኛ ትውልድ)
4.አባ ማትያን ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† " . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም: ተናገረኝም:: እንዲህም አለ:- "ዳንኤል ሆይ! ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ::" †††
(ዳን. ፱፥፳-፳፪)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለአቡነ ማቲያስ ዘምራራ የዕረፍት በዓል አደረሳችሁ አደረስን
❤️አቡነ ማትያስ ዘምራራ❤️

✝በኤርትራ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ገዳማት ውስጥ አንዱ “ደብረ ብርሃን ወደብረ በረከት ወደብረ ሰማዕት›› ተብሎ የሚጠራው የአቡነ ማትያስ ገዳም ነው። ይኸ ገዳም የሚገኘው በሰሜናዊ ባሕር ፍሸይ ምራራ በሚባለው ቦታ ሲሆን የመሠረቱት ጻድቁ አቡነ ማትያስ ዘምራራ ናቸው።

የአቡነ ማትያስ (ማይታን) አባታቸው በዚህ ዓለም ሀብትና ንብረት ያፈራ ቢሆኑም በመጀመሪያ የክርስትና እምነትን ግን አልተቀበለም ነበር። ሀብቱንም የሚያወርሰው ልጅ ስላልነበረው በዚህ ይጨነቅ ነበር። የአቡነ ማትያስም እናት ‹‹ ክርስቲያን ሴቶች እኮ ወደ እግዚአብሔር ለምነው ልጅ ያገኛሉ፣ እኛም ወደ እግዚአብሔር እንለምንና ልጅ ካገኘን ለእግዚአብሔር ይሆናል በማለት ለበሏ ነገረችው። እነርሱም ከተመካከሩ በኋላ ‹‹ልጅ ካገኘን እኛም ክርስቲያን እንሆናለን ብለው ስዕለት ተሳሉ ።
ለቤተክርስቲያንም ዕጣን ስጥተው ካህኑን <"እግዚአብሔር ልጅ እንዲስጠን ጸልይልን" >አሉት

✝እመቤታችንንም በጸሎት ሲማጸኗት ቆይተው እግዚአብሔር ስዕለታቸውንና ጸሎታቸውን ተቀብሎ ልጅ ሰጣቸውና እጅግ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርንና እመቤታችንን አመሰገኑ። ከዚኸም በኋላ ወላጆቻቸው አምነው ተጠመቁና ስማቸው አብርሃም እና ኂሩተ ማርያም ሲባሉ የሕፃኑም ስም ድኁነ እግዚእ ተባለ። አብርሃምና ኂሩተ ማርያምም ፍጹም ክርስቲያኖች ከሆኑ በኋላ እግዚአብሔር በበረከት ጎበኛቸውና ሌሎች ፈቃደ እግዚእ፣ ባርያ እግዚእ፣ ንዋየ እግዚእ፣ ደጋፊነ እግዚእ እና ጥሪተ እግዚእ የሚባሉ አምስት ልጆችን ወለዱ። ስለዚህም አቡነ ማትያስ በ14 መ/ክ/ዘ ጽልማ ታኸታ በሚባል ቦታ ተወለዱ። እርሳቸውም በመጀመሪያ ስማቸው ጥሪተ እግዚእ ተብለው እንደ ቅዱስ ዳዊት የመጨረሻ ልጅ ሆነው በእረኝነት ወላጆቻቸውን ያገለግሉ ነበር።

✝ጥሪተ እግዚእ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከእርሱ ጋር በግ የሚጠብቁ ጓደኞቹ ከሰው ማሳ እሸት ሰርቀው አምጥተው ‹ና ከእኛ ጋር ብላ አሉት። እርሱ ግን የሌላን ሰው እህል አልበላም ብሎ እምቢ አለ፤ ለእናቱም ሲነገራት እናቱ ተደስታ አቅፋ ሳመችው። ጓደኞቹም በሌላ ጊዜ እንዲሁ የተሰረቀ እያመጡ ይበላ ዘንድ ቢፈታተኑትም እርሱ ግን እሺ አይላቸውም ነበር።

✝በዚኸም ነገር ይህ ታናሽ ብላቴና ጥሪት እግዚእ ኢትዮጵያዊውን ታላቅ ጻድቅ አቡነ ሀብተ ማርያምን መሰላቸው። ከዕለታትም በአንደኛው ዕለት አባታቸን ሀብተ ማርያም በጐችን ሲጠብቁ ሌሎች እረኞች በአመጻ ከሰው ሰርቀው ቆርጠው ያመጡትን እሽት ‹‹ና እንብላ›› አሏቸው። አባታችን ግን ከየት እንዳመጣቸሁት ምንም ስለማላውቅ አልበላም›› አሏቸው። እረኞቹም ሀብተ ማርምን በቁጣ ዐይን እያዩአቸው ተቀምጠው ሲበሉ አባታችን ‹‹የማንችለው ዝናብ መጥቷልና ተነሡ በፍጥነት ወደቤታችን እንሂድ›› አሏቸው። እረኞቹም “ሰማዩ ብራ ነው ምንም ደመና የለውም፤ ነፋስም አይነፍስም። እኛ የማናየው አንተ ብቻ የምታየው ምን ነገር አለ?›› እያሉ በአባታችን ላይ ተዘባበቱባቸው። አባታችን ግን በጎቻቸውን እያስሮጡ በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሔዱ፤ ወዲያውም በጣም ኃይለኛ ዝናብ ዘነበ፤ የጥፋት ውኃው በላያቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ እነዚያን እረኞች ከቦታቸው አልተነቃነቁም ነበርና በጥፋቱ ውኃ አለቁ። በዚያችም ሌሊት አቡነ ሀብተ ማርያን ከሰማይ ሦስት ጊዜ ‹ሀብተ ማርያም፣ሀብተ ማርያም" የሚል ድምፅ ጠራቸው። አባታችንም እንደ ሳሙኤል ጌታ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር ሲለ ጌታችን አናገራቸው። ከዚህ በኋላ . ለመረጥኳቸው ቃሌን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔም ጋር በምሥጢር በባለሟልነት ትነጋገር ዘንድ መርጨሃለሁ አላቸው ።

✝ከጥቂት ቀንም በኋላ አባታችን ዳግመኛ በጐችን እየጠበቁ ሳሉ አንድ አመጸኛ መጣና በትራቸውን በኃይል ነጥቆ ወሰደባቸው አቡነ ሀብተ ማርያም በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ እቋቋምህ ዘንድ ኃይል የለኝምና በትሬን መልስልኝ ቢሉት የትዕቢትን ቃል ተናገራቸው። አባታችንም እምቢ ካልክስ እሺ የእግዚአብሔርን ኃይል ታያለህ አሉት። ወዲያም ያ አመጸኛ ላዩ ታች ታቹ ላይ ግራ ቀኝ ቀኙ ግራ ሆኖ በአየር ላይ ተሰቅሎ ዋለና እየጮኸ አባታችንን ለመናቸው አባታችንም የቀጣህ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ባሉት ጊዜ ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ። በዚያ የነበሩና ይህንን ተአምር ያዩ እረኞችም እጅግ ፈርተው ሔደው ለወላጆቻቸው ያዩትን ተናገሩ። የሀገሩ ሰዎችም ተድሞ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያለ ሲጸልይ ሲሰግድ አይተነዋል፡ አሁንም ጠላቱን በነፋስ የሚቀጣ ይህ ልጅ ወደፊት ምን ይሆን እያሉ አደነቁ ወላጆቻቸውም ይህን በሰሙ ጊዜ በግ ጠባቂነቱን አስተዋቸውና ሃይማኖትን ይማሩ ዘንድ ወስደው ለመምህር ሰጧቸው።

✝ወደ ጥሪተ እግዚእ ዜና ገድል እንመለስና እርሱም ከአመጸኞች ጋር ባለመተባበር ፈሪሃ እግዚአብሔርን ገንዘብ አደረገ። መንፈስ ቅዱስ በእናቱ ማሕፀን ሳለ እንደነቢዩ ኤርምያስ መርጦታልና በዋዛ ፈዛዛም ከእነርሱ ጋር አይተባበርም ነበር። ፊደልን እንኳን ሳይማር መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት መጻሕፍትን ዐወቀ፣ ትእዛዛትንም ሁሉ ጠበቀ። አባቱ አብርሃምም ዳግመኛ በጎችን መጠበቅ ትቶ ከብቶችን እንዲጠብቅ ስላዘዘው ሕፃኑም በኅብረት የማንንም ከብት ሳይለይ ይጠብቅ ነበር።

✝በዚኽም ወቅት ፈቃደ እግዚእ የተባለው ወንድማቸው ዓለምን ንቆ ገዳም ገብቶ ስለመነኰሰ ወንድሞቹ ሔደው ለአባታቸው ነገሩት፤ አባታቸውም የእኛ ፈቃድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አላቸው። እርሱም ከነልጆቹ እንደሚመነኩስ ራእይ አይቶ ልጆቹን ጠርቶ ልጆቼ ሆይ! እኛም እንደ ፈቃደ እግዚእ እንመነኩስ ዘንድ አለን ሲላቸው ልጆቹም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ስሙ በእኛ በባሪያዎቹ ይክበር ይመስገን› አሉ።

✝ከዚኽም በኋላ አራቱ የአብርሃም ልጆች ታኺታ የምትባለውን ቦታ ትተው ወንድማቸው ወደመነኰሰበት ገዳም ለማየት ሲሔዱ ታናሹ ጥሪተ እግዚእም አብሮ ለመሔድ ተነሣ። እነርሱም መንገዱ ሩቅ ነው አንተ ትንሽ ልጅ ነህ ከዚሁ ቆይ›› ብለው ትተውት ቢሔዱም እርሱ ግን ከኋላ ከኋላቸው እየተከተላቸው ሲሔድ እንዲመለስ ያባርሩት ነበር። ከዚያም ሕርሻ የሚባል ቦታ ላይ ሲደርሱ እንመለሳለን›› ብለው ትተውት ሔዱ። እርሱም በዚህ ጊዜ በደብረ ማርያም ያለ መነኰሳትን ተመለከተና የሚጠብቀውን ንብረትና ስንቅ ትቶ መነኰሳቱን ተከትሎ ወደ ገዳም ሲገባ ወንድሙን ፈቃደ እግዚእን በዚሁ ገዳም ውስጥ አገኘው። ፈቃደ እግዚእ እና መነኰሳቱም ከየት እንደመጣ እየጠየቁት አቅፈው ሳሙት። ጥሪተ እግዚእም አመጣጡን ነገራቸው።

✝ወንድሞቹም ከሔዱበት ሲመለሱ ጥሪተ እግዚእን ስላጡት እያዘኑ ሳለ የገዳሙ አንድ መነኩሴ ሕፃኑ ወደ ገዳም እንደገባና ከታላቅ ወንድሙ ጋር እንደተገናኘ ነገሯቸው። ወንድሞቹም ወደ ገዳሙ ገብተው አበ ምኔቱን አባ ተወልደ መድኅንን አግኝተው ተባረኩ። አበ ምኔቱም ከወንድሞቻቸው ጋር አገናኛቸውና እያለቀሱ ተሳሳሙ። ከዚያም ወንድሞቹ ወጥተው ወደ ማሳቸው ሲሔዱ ሕፃኑ ጥሪተ እግዚእ ግን በገዳም ቀረ። በዚያም መመንኰስ እንደሚፈልግ ሲናገር መነኰሳቱ ‹ልጄ ሆይ! ይህ ለአንተ ይከብድሃል ምንኩስና ለትልልቆች ነው የሚገባው፣ ትዕግሥት አድርግ…›› ሲሉት እርሱም ‹‹…ለእኔ የሚሻለኝን ዐውቃለሁ›› ብሎ መለሰ። እነርሱም በመልሱ ተገርመው አመነኰሱትና ማትያስ የሚል ስም ሰጡት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† ✝✝✝🌹እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††

†††✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝✝✝

††† በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ ቅዱስ ላሊበላ: ቅድስት አፎምያና ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ይከበራሉ::

††† ✝ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት †††✝

††† ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::

††† ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::

††† ✝✝ቅዱስ ላል ይበላ ንጉሥ †††✝✝

††† በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በሃገራችን የነገሠው ቅዱስ ላሊበላ:-
¤በብሥራተ መልአክ ተወልዷል
¤ቅዱሳት መጻሕፍትን ገና በልጅነቱ አጥንቷል
¤የንጉሥ ዘር ቢሆንም በጾምና ጸሎት: በትሕርምት አድጓል
¤በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም
¤ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል
¤በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ ነበር
¤ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት የእንጀራውን ቅርፍት (ጠርዝ) ብቻ ነበር::

በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል
¤በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን (ላስታን) ገንብቷል
¤ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች ናቸው::

ሥራውን ከፈጸመ በኋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ: በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ በዚሕች ቀን አርፏል:: ጌታችን ስምህን ያከበረ: ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን: ከርስተ መንግስተ ሰማያት አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

††† በረከቱን: ክብሩን ያድለን::

††† ቅድስት አፎምያ †††
ከቅዱስ አስተራኒቆስ ጋር በተቀደሰ ትዳር የኖረች
¤ምጽዋትን ያዘወተረች
¤በፍቅረ ቅዱሳን የጸናች
¤ንጽሕናዋን ጠብቃ ሰይጣንን ያሳፈረች ደግ እናት ናት:: ዛሬ የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል ታቅፋ: በትእምርተ መስቀልም አማትባ አርፋለች: ቅዱሱ መልአክም ወደ ገነት አሳርጓታል::

††† ✝✝ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ †††✝✝

የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ:
¤በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ:
¤በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ:
¤በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ:
¤ምጽዋትን ያዘወተረ: አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤በዚህች ቀን አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

††† አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ በረከት ይክፈለን:: አሜን:: †††

††† ሰኔ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅድስት አፎምያና ባለቤቷ ቅዱስ አስተራኒቆስ
4.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
5.ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሊቅ
6.አባ ዮስጦስ ሊቀ ዻዻሳት (የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ደቀ መዝሙር)
7.አባ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ድሜጥሮስ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

††† "በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ::" †††
(ራዕይ. 12:7)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለሀያሉ ለቅዱስ ሚካኤል  በአል አደረሳችሁ አደረሰነ


/channel/+QuWsAnpEDG83ODU0
/channel/+QuWsAnpEDG83ODU0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔እለተ እሁድ እንዴት ነበር.. ?

🙏የቀኖች ሁሉ ባለቤት የተመሰገነ ይሁን🙏

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ🙏

#besufkadbogale #bsquadcompanyy
Besufkad Bogale

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Amen🙏🙏🙏🙏🙏lehulcnm yehun

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዋጋ ክፈል !

የምትፈልገውን ህይወት ለመኖር መጀመርያ የሚያስፈልገውን ዋጋ መስጠት መቻል አለብህ ፤ ዋጋ ያልተከፈለበትን እቃ መውሰድ እንደማትችል ሁሉ ዋጋ ያልከፈልክበትም ስኬት ያንተ ሊሆን አይችልም !

መልካም ቀንን ተመኘሁ🙏

#besufkadbogale #bsquadcompanyy
Besufkad Bogale

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዋጋ ክፈል !

የምትፈልገውን ህይወት ለመኖር መጀመርያ የሚያስፈልገውን ዋጋ መስጠት መቻል አለብህ ፤ ዋጋ ያልተከፈለበትን እቃ መውሰድ እንደማትችል ሁሉ ዋጋ ያልከፈልክበትም ስኬት ያንተ ሊሆን አይችልም !

መልካም ቀንን ተመኘሁ🙏

#besufkadbogale #bsquadcompanyy
Besufkad Bogale

Читать полностью…
Subscribe to a channel