#ሰኔ_30
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ፣ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ #አባ_ጌራን አረፈ፣ የአልዓዛር እህቶች #የቅዱሳን_ማርያ_እና_የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።
በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።
ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ገድለኛው_አባ_ጌራን
በዚህችም ዕለት ደግሞ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ገድለኛ የሆነ አባ ጌራን አረፈ። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራውና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።
ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ የነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጐራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው። የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ለአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ። እርሱም ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ አላት።
በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጐኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋር ተኝቶ ኃጢአት እንደሚሠራ ሆነ።
ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ። ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ደንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።
ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ሊቀሰቅሱት ጀመሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።
ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳት_ደናግል_ማርያ_እና_ማርታ (የአልዓዛር እህቶች)
በዚህችም ዕለት ከአራት ቀኖች በኋላ ጌታችን ከመቃብር ያስነሳው የአልዓዛር እህቶች የማርያ እና የማርታ መታቢያቸው ሆነ፡፡ በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት ከኃጢአት የተመለሰች': 2ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር - በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል 12:1 ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: (ዮሐ.11)
ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: (ዮሐ. 12:1)
በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
አቡነ ዓምደ ሚካኤል፡- ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው፡፡ ወላጆቻቸው ገላውዲዮስና ኤልሳቤጥ ሁለቱም በሃይማኖትና በዓለም ገንዘብ የበለጸጉ ናቸው፡፡ ይህንንም ጻድቅ ልጃቸውን የአርባዕቱ እንስሳ በዓል ዕለት ወለዱትና ስሙን ዓምደ ሚካኤል ብለው ጠሩት፡፡ ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ለዐፄ በእደ ማርያምና ለዐፄ እስክንድር የሠራዊት አለቃ የነበረ ጻድቅ ነው፡፡ በአንድ ዓመቱ ወላጆቹ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይዘውት እንደሄዱ ከወላጆቹ ተለይቶ ጠፍቶ ሳይገኝ ቀረ፡፡መልአክም ከቤተ መቅደስ አግብቶ እየመገበው 3 ቀን አቆይቶታል፡፡ በ3ኛው ቀን ቄሱ ሊያጥን ሲገባ በከርሰ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን አገኘውና ወስዶ ለወላጆቹ ሰጣቸው፡፡ባደገም ጊዜ በመመጽወትና አብያተ ክርስቲያናትን በማደስ የሚተጋ ሆነ፡፡ለድኆችም በቅንነት በመፍረድ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ፡፡ለነገሥታትም ገዢ ከሆነ በኋላ በጸሎቱና በበረከቱ በሀገራችን ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዝተው ይገብሩ ነበር፡፡ በበጎ ምግባሩ የቀኑ ዐመፀኞችም በክፋ ተነሡበት፡፡ ጻድቁ በመንፈስ አድጎ መንኩሶ በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ነገር ሠሪዎች በሐሰት ወንጅለው ከሰሱት፡፡ንጉሡም እጅግ ስለሚወደው የራራለት ቢሆንም በነገራቸው ባስጨነቁት ጊዜ ወደ ሩቅ አገር አስሮ አጋዘው፡፡ አባታችንም በግፍ ታስረው ሳሉ በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን ወረደላቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ሰማያዊ መና እያመጣ ይመግባቸው ነበር፡፡ የጌታችንንም ሥጋና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ነበር፡፡ ነገረ ሠሪዎቹ ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት፡፡ በዓመፃቸውም ብዛት ወደ ፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሏቸው፡፡አንድ ጻድቅ መነኩሴ የቅዱስ ዓምደ ሚካኤልን ሥጋ ሦስት ቅዱሳን መላእክት ሲያጥኑ አገኛቸውና ያየውን ለሕዝቡ ተናገረ፡፡ በሌላም ጊዜ የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድላቸው ብዙ ቀን የተመለከቱ ብዙ ቅዱሳን ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ንጉሡም ይህንን ሁሉ ሲሰማ በአሳቾቹ ልበ ደንዳናነትና ክፋት እጅግ ተጸጽቶ በሞት ቀጣቸው፡፡ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤልንም በአባቶች መቃብር በክብር አስቀበራቸው፡፡ ስማቸውንም በበጎ እንጂ በክፋ ማንም እንዳያነሳቸው በአዋጅ አስነገረ፡፡ መታሰቢያም አቆመላቸው፡፡ከዚህም በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ የአባቱን የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋም ጻድቁ ሲያርፉ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተቀበሩ ቢሆንም ከብዙ ዘመን በኋላ ዐፅማቸውን አፍልሰው በተድባበ ማርያም እንደቀበሯቸው ጽፈዋል፡፡ የሰማዕቱ የአቡነ ዓምደ ሚካኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
እግዚአብሔር በሥልጣንና በስም የሠለጠነ ነው እንደርሱም ያለ ስም የለም ።
ከአራቱ መሠረት በታች
ከሰባቱም ሰቀላዎች (ሰማያት) በላይ
ሁሉን የፈጠረ ነው
የሚታየውንና የማይታየውን
የሚታወቀውንና የማይታወቀውን
የሚዳሰሰውንና የማይዳሰሰውን
የተሠወረውንና የተገለጸውን
የላዩንም የታቹንም የፈጠረ ነው ።
የአምላክ እጅ ሥራ የሚሆን አንዱ አዳም ሳይቀር ሁሉን ባለመድከም የፈጠረ ።
አሁንም አቤቱ አምላካችንና መድ ኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በፊትህ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ ስላደ ረጉ ሰዎች እንለምንሃለን እንማል ድሃለንም ታሰናብታቸው ዘንድ ።
ልጆቻቸውን አሳድግ
ጕልማሶቻቸውንም አጐልምስ
ሽማግሎቻቸውን ደግፍ
የተንቀጠቀጡትን አጽና
ሴቶቻቸውን ጠብቅ ልጆቻቸውንም አደራ አስጠብቅ ።
የተራቡትን አጥግብ
የተጠሙትንም አርካ
ለተራቆቱት አልብስ
የተጨነቁትንም አሳርፍ
የተከዙትን ደስ አሰኝ
ያዘኑትንም ደስ አሰኝ
የታመሙትንም አድን ።
ሕሙማኑንም ፈውስ ።
የዕውራኖቻቸውንም ዓይን አብራ
የደንቆሮዎችንም ጆሮ አሰማ
እሥሮቻቸውንም ፍታ የተማረኩትንም አድን ።
ሥጋቸውን አንጻ ነፍሳቸውንም አክብር ወደ ቤታቸውም በሚገቡበት ጊዜ አቤቱ አንተ መርተህ ከዚያ አድርሳቸው ።
አቤቱ ለዘላለሙ ጠብቃቸው ከፍከፍም አድርጋቸው ።
ቅዱስ ያዕቆብ❤️
🍂ከዚኽም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በገዳማቸው በጽኑ ተጋድሎ ላይ ሳሉ የጌታችን ጾም በደረሰ ጊዜ ልጆቻቸውን ጠሩና ሰባት ክንድ የሚሆን ጉድጓድ ቆፍራችሁ እኔ እዚያ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ጉድጓዱን ሸፍኑት፣ ከላይ የዕንጨት ሰሌዳ አድርጋችሁ በድንጋይና በጠጠር አድርጋችሁ በመቃብር ምልክት ዝጉት” በማለት ነገሯቸው። ዳግመኛም ሰዎች የት ናቸው? ብለው ቢጠይቋችሁ የት እንዳለ አናውቅም, በሏቸው፤ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሲሆን ግን ከፍታችሁ አረጋግጡ አሏቸው። አብርሃም የተባለው ደቀ መዝሙራቸውም ወደ ጉድጓዱ አብሯቸው በመግባት የአቡነ ክፍለ ሥላሴን እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሰንሰለት ካሠራቸው በኋላ ወጣ፣ ጻድቁም እንዳዘዙት ጉድጓዱን ዘጉትና ሰው እንዳያውቀው አንድ ትልቅ መደብ ሠሩለት። ነገር ግን በማግሥቱ “ወዳጄ ክፍለ ሥላሴ ሆይ! ለምን እንደዚህ አደረግህ? አንተ ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገብተህ ማነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚያቀርብ? ማንስ ዕጣን ያጥናል? ስለዚህ አሁን ና ከዚህ ተነሥተህ ውጣ የሚል ራእይ ተመለከቱ፡ ወዲያውም የተዘጋው ጉድጓድ በተኣምር ተከፈተ፡ ታስሮ የነበረው እጅና እግራቸውም ሰንሰለቱ በተኣምር ተፈታ። እርሳቸውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በእጃቸው ሲያጨበጭቡ አስሯቸው የነበረው ልጃቸው ድምፅ ሰምቶ ሲመጣ አባታችንን ሲመለከት ደነገጠና አባቴ ሆይ! ማን አወጣህ?›› ማንስ እጅህንና እግርህን ፈታህ አላቸው። እርሳቸውም ለልጆቻቸው የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው።
🍂አቡነ ክፍለ ሥላሴ ደብረ መድኀኒት ብለው በሰየሟት ገዳማቸው ባምብቆ አካባቢ የከብት በሽታ (ጉልሓይ) ተከስቶ ነበር ነገር ግን ያንን በሽታ ያመጣውን ክፉ ሰይጣን ጻድቁ በጸሎታቸው ኀይል እያስጮኹ አባረው ጣሉት፤ ድምፁንም ሰምተው የአካባቢው ሰዎች ጠላታቸው እንደወደቀ ዐውቀው ከብቶቻቸውም ጤነኞች ስለሆኑላቸው የአቡነ ክፍለ ሥላሴን አምላክ አመሰገኑ።
🍂ጻድቁ የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበር፤ አንድ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ የማያስችል ሕማም አጋጠማቸውና በእርሳቸው ፋንታ አንድ እግሩን የሚያመው ወዳጃቸውን ሔዶ ዕጣን እንዲያጥን ነገሩት። እርሱም ሔዶ ግድግዳውን ተጠግቶ በሰሜንና በደቡብ አጥኖ በምዕራንና በምሥራቅ ሳያጥን ተመልሶ ሊጠይቃቸው ሲመጣ አባታችንም ‹‹አንተ ወንድሜ ስለምን እንደዚህ ታደርጋለህ? ለምን
እንደአባቶቻችን አድርገህ በምዕራብና በምሥራቅ : አላጠንክም?›› አሉት ይህንንም ሲሰማ ያ ካህን ደንግጦ በሠራው ስሕተት ንስሓ ገባና እግዚአብሔርን አመሰገነ።
🍂በመጨረሻም የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ካህን “ወንድሜ ሆይ! እኔ ማክሰኞ ቀን በአባታችን በአብርሃም በዓል ዕለት እሞታለሁ›› በማለት የሚያርፉበትን ቀን ነገሩት። በተናገሩትም መሠረት ከምንኵስናቸው በፊት 20 ዓመት ከምንኩስናቸው በኋላ 8 ዓመት ኖረው በ28 ዓመታቸው ሰኔ 28 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ዐረፉ። ጻድቁ ራሳቸው በተከሏትና በጸለዩባት በደብረ መድኀኒት ቅድስት ሥላሴ ባምብቆ ከተቀበሩ በኋላም ብዙ ተኣምራት አድርገዋል። ዝክራቸውን ያደረገ በጸሎታቸው የተማጸነ በዚህ ዓለም ከመከራ ሥጋ፣ በሚመጣውም ዓለም ከመከራ ነፍስ እንደሚድን ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ቃልኪዳን ስለገባላቸው የባምብቆ ሕዝብና የዛውል ሕዝብ ሰኔ 28 ቀን በዓላቸውን በታላቅ ክብር ያከብራሉ።
🍂የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ ጸሎታቸውና በረከታቸው ከኹላችን ከሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ይሁን።
ምንጭ $ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወስደ
ወንድማችን ገብረ ሥላሴ እግዚአብሔር በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን
ጥቅምት 28 /2/2015 ዓ.ም
Kuwait
https://youtube.com/channel/UCAe0Vv9bIkCTTkeilxcUoYQ ሰላም የተዋህዶ ልጆች ቢያንስ 800 የሚያህል ሰብስክራይበር ስለሚያስፈልገኝ መተቻላቹህ መጠን ተባበሩኝ ካልለሆነ ቻናሉ ስለሚዘጋብኝ ነው እባካችሁን አይታቹህ ዝም አትበሉ ሰብስክራይብ አድርጉት 🙏🙏🙏
Читать полностью…የተሰበሰብን እኛም የማይ ሞት የርሱን ሞቱን እንናገራለን ።
የማይታመም የርሱን ሕማሙን እንናገራለን ።
ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተቀመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ ።
👉ሁሉን የያዘውን ያዙት
👉ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት
👉የሕያው የአምላክን ልጅ አሠሩት በቍጣ ጐተቱት
👉በፍቅር ተከተላቸው በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋሕ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት ።
👉ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት
👉 ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት በመኳንንት በሚፈርደውም በርሱ ፈረዱበት ።
👉ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን እሾህ ዘውድ አቀዳጁት ።
👉 ለኪሩ ቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸ ውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ።
👉ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሠወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው።
👉የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ ።
👉ይህን ያህል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው
👉 ይህን ያህል ትዕግሥት እንደ ምን ያለ ትዕግ ሥት ነው ።
👉ይህን ያህል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው ።
👉ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው ።
👉 ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው።
👉ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው ።እስከ ሞትም አደረሰው ።
👉 በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት ።
👉ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት ።
👉አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ
👉ወዮ በገነት የተመላለሱ _ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ።
👉ወዮ በአዳም ፊት የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋራ የተቀላቀለ የኮመጠጠ መጻጻን ጠጣ ።
👉ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምንአፍ ነው ምን ከንፈር ነው ምን አንደበት ነው ።
👉የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ሕሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል ።
👉የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ::
👉ሙታንን ያድናችው። ዘንድ ሞተ ።
👉የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
@uraman4u13 ሼር አድርጉ
@uraman4u12 ሼር አድርጉ
@uraman4u123 አድ አድርጉ
👉ምግብ በራሱ መጥፎ አይደለም ጣዖትን ማምለክ እንጂ፡፡
👉ልጅ መውለድ ኃጢአት አይደለም ዝሙት እንጂ፡፡
👉ገንዘብ በራሱ መጥፎ አይደለም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ እንጂ፡፡
👉ከተፈጠሩት ነገሮች በርግጥም በራሱ መጥፎ ነገር የለም አጠቃቀሙ ክፉና በጎ ያደርገዋል፡፡
👉 ስለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እኛ ከሀብት ጀርባ ያለ ትእቢትን እንጂ ሀብታሞችን አንቃወምም በማለት የተናገረው፡፡
/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/❤️
👉አንዳንድ ሰዎች ነፃነት የሚለውን ቃል የሚረዱት የወደዱትን ሁሉ የመፈጸም ፈቃድ አድርገው ነው፡፡
👉ሰዎች አብዝተው ራሳቸውን የኃጢአት ባሪያ እያደረጉ በመጡ መጠን ሕጉን ለራሳቸው እንደሚስማማቸው ሊተረጉሙላት ይዳዳቸዋል፡፡
👉 እንዲህ ዓይነት ሰዎች ውጫዊ ነፃነትን የሚጠቀሙበት በሣሣተ መንገድ ለተሣሣተ ዓላማ ነው፡፡
ባስልዮስ ዘቂሳርያ❤️
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ሐሤቶሙ ለመላእክት፡፡
የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ለሊሁ ዓለሞሙ ወለሊሁ ተድላሆሙ ወለሊሁ ሀገሮሙ እንዲል፡፡ አንድም ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት የሚነግሩ መላእክት ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት ፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ብለው አመስግነውት ፤ በጣዕም ላይ ጣዕም ፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋልና አንድም የመላእክት ደስታቸው የምትሆኝ ጌታን የወለድሺው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እያዩ ደስ ይላቸዋልና ሐሴቶሙ ለመላእክት አለ፡፡
ተፈሥሒ ኦ ድንግል ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡
የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ኦ ድንግል አምሳል ወትንቢት ፤ ዘነቢያት እንዲል፡፡
ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡
እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ፤ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ሆኗልና፡፡ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡
ተፈሥሒ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍሥሓ ኩሉ ዓለም፡፡
የሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን የመልአኩን ቃል ፤ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ እንደ ዘካሪያስ ሳትጠራጠሪ አምነሻልና ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ሰብአ ፊንቆን ተወክፍዎ ፤ ወእለሰ ተወክፍዎ ወሀቦሙ ሥልጣነ እንዲል ፍሥሐ ኩሉ ዓለም ያለውን ለመልአክ ቢቀጥሉ ምስጋናው ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ነውና ቃል ላለው ቢቀጽሉ ወነዋ ተወልደ ፍሥሐ ዘይከውን ፣ ለክሙ ለኩሉ ዓለም ይለዋልና፡፡
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም።
ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
††† ✝እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ✝†††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን ✝†††
††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::
አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው::
ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል::
ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::
ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ40 ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል (አገልግሎታል):: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል::
በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::
††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ
¤ሕዝቡን አሻግሮ
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::
ሰባት አሕጉራተ ምስካይ (የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው:-
"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::
††† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::
††† ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
༒ Dn Wegen ༒
+ ፈተናውን እርዳኝ +
(ይሄ ፅሁፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ (Remedial program) ወስዳችሁ ሰኞ ፈተና ለምትጀምሩ ተማሪዎች ይድረስልኝ)
+ ታሪክ +
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡
ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡)
በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡
ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡
ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡
+ ጸሎት +
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
📍Chanel፦ /channel/+r1scfiBj_po2MjY8
✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖
❖ ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ) ✝+"+
=>ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው
ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም
ነው:: በእኛ
ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ (በ24)
በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::
=>ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ
ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ
ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር::
ሙሴ ጸሊም
ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም
መምለክያነ ጣዖት (ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች) ጋር
ይኖር ስለ ነበር
ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::
+ቅዱስ_ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው
አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ
ይበላል: ያሻውን
ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው
አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ
ከሆንሽ
አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::
+ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን
መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም
ክርስቲያኖችን
አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ_አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት
ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ::
መነኮሳቱ
ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ_ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::
+"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት
ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ
ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው
ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ_መቃርስ_ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና
ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::
+ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት
ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ
ይጋደል
ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት
የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ
አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን
አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም
በአካል
እየመጡ ይፈትኑት ነበር::
+እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት
አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ::
በበርሃ ለሚኖሩ
አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ
ሆነ::
<< በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም
አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ_ጸሊም ይል ጀመር ፡፡ >>
+በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን
መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን
ራሱን "አንተ
ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ:
ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም
በመነኮሳት ላይ
እረኛ (አበ ምኔት) ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ::
የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ
አጣፍጦ:
ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::
+ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ
ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ375 ዓ/ም
በርበረሮች
(አሕዛብ) ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት
ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር
በዚሕች
ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::
=>ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ
ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው
ያድለን::
=>ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
2."7ቱ" ቅዱሳን መነኮሳት (ደቀ መዛሙርቱ)
3.አባ ኤስድሮስ ታላቁ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
2፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
4፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
5፡ ቅዱስ አብላርዮስ
6፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
7፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
=>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና
ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ
ሊፈልገው
የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት
በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ
ወዳጆቹንና
ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን
አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል::
እላችሁአለሁ:
እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን
ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ
ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✞✞✝ የሰኔ 23 ✝✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ እንኳን አደረሳችሁ✝ ❖
❖ ✝ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ_ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል✝ +"+
=>መፍቀሬ ጥበብ:
¤ጠቢበ ጠቢባን:
¤ንጉሠ እሥራኤል:
¤ነቢየ ጽድቅ:
¤መስተሣልም (ሰላማዊ) . . . እየተባለ የሚጠራው
ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ
አምላክ ቅዱስ_ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) ልጅ ነው:: ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ
ሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ
ጋር
አድጉዋል::
+ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን
መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም
አልተሳካለትም::
እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱ
ነገሠ:: ልበ_አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው::
"ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ"
አለው::
+ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር
መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?"
አለው::
ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ::
በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ
እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ
ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት
ተሠወረ::
ቅዱስ ሰሎሞን ለ40 ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ::
+ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት::
እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ_ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን (እብነ_መለክን) ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ_ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል_ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት
ሴቶችን አብዝቶ ነበር::
+ነገር ግን:-
¤አንደኛ ሰው (ሥጋ ለባሽ) ነውና:
¤ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል
ከአንዷ እመ_ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ
(ከፈርዖን ልጅ) ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው::
እግዚአብሔር እጅግ አዘነ::
+በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ
ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ:
አመድ
ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ
ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው::
+የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን 5
መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም:-
1.መጽሐፈ ጥበብ
2.መጽሐፈ ተግሣጽ
3.መጽሐፈ መክብብ
4.መጽሐፈ ምሳሌ
5.መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው::
+ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ_መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ
ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው
ሔዷል::
+"+ አባ_ኖብ +"+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል::
በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው
ቅዱስ
ነው::
+አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ
ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ
ሰማዕታት
ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ
ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም
"ሰማዕት
ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ 72ቱ
ከዋክብትም አንዱ ነው::
=>ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ
ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን::
=>ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ)
3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
4፡ አባ ሳሙኤል
5፡ አባ ስምዖን
6፡ አባ ገብርኤል
7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
=>+"+ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት
ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት
ሳይደርሱ:
ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም
ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ
እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: +"+
(መክ. 12:1-9)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
💚 @Addis_Mezmure 💚
💛 @Addis_Mezmure 💛
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 29-ንግሥናን ንቀው በመተው ሀብታቸውንም ሁሉ ሸጠው ለድኆች በመመጽወት መንነው ገዳም ገብተው ብዙ የተጋደሉት ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አቡነ ቴዎድሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥጋና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው የነበሩት ሰማዕቱ አቡነ ዓምደ ሚካኤል ፍልሠተ ዐፅማቸው ነው፡፡
+ በድንግልና ሆኖ ሲያገለግል የነበረውና በንግሥናም አገርን ሲመራ የነበረው የእመቤታችን ሥዕል በሰው አንደበት ያናገረችው የሮሜው ጻድቅ ንጉሥ ቅዱስ ማርቆስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ አባ አብሲዳ፣ አባ ኮቶሎስ፣ አባ አርድማ፣ አባ ሙሴ፣ አባ እሴይ፣ አባ ኒኮላስ እና አባ ብሶይ የተባሉ ከቆና ገዳም የተገኙ ሰባት መስተጋድላን ቅዱሳን አባቶች በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
+ ቅዱሳን አባ ብሶይና አባ ሖር ከእናታቸው ከቅድስት ይድራ ጋር በሰማዕት ዐረፉ፡፡ ከአንጾኪያ ሠራዊት ውስጥ የሆነ ሖርሳም አብሯቸው ሰማዕት ሆነ፡፡
+ + + + +
አቡነ ቴዎድሮስ፡- የኢትዮጵያው ንጉሡ የዐፄ ዳዊት ልጅ ናቸው፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ ጠንቅቀው የተማሩ ናቸው፡፡ለድኆች በመመጽወትና በበጎ ምግባር ኖረዋል፡፡ በመጨረሻም ንግሥናን ንቀው በመተው ያላቸውንም ሀብት ሁሉ ሸጠው ለድሆች በመመጽወት መንነው ገዳም የገቡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ወደ ኢየሩሳሌምም ለመሄድ አስበው አባ ማርቆስን ሲያማክሯቸው በመንፈስ ቅዱስ ያውቁ ነበርና ክፍልህ አይደለም አሏቸው፡፡ ጻድቁ ባረፉ ጊዜ በክረምት አስክሬናቸውን ተሸክመው ወንዝ ሊያቋርጡ ሲሉ ወንዙ በተአምራት ለሁለት ተከፍሎላቸው በሰላም ተሻግረዋል፡፡ በተቀበሩበት ቦታም ፈዋሽ ጸበል ፈልቋል፡፡ጻድቁ አቡነ ቴዎድሮስ በስማቸው የተሰየመው ታቦትና ቅዱስ ገድላቸው በደብረ ዳሞ ይገኛል፡፡ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
ሰባቱ ሰማዕታት መስተጋድላን አባቶች፡- እነዚህም ቅዱሳን አባቶች አባ አብሲዳ፣አባ ኮቶሎስ፣ አባ አርድማ፣ አባ ሙሴ፣ አባ እሴይ፣ አባ ኒኮላስ እና አባ ብሶይ ከቆና ገዳም የተገኙ ሰማዕታት ናቸው፡፡በመጀመሪያ የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና በጌታችን ስም ሰማዕት እንዲሆኑ አዘዛቸው፡፡ ያን ጊዜም ወደ ከሃዲው መኮንን ዘንድ ሄደው በፊቱ የጌታችንን አምላክነት መሰከሩ፡፡ መኮንኑም ሀገራቸውን ከጠየቃቸው በኋላ ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ማሠቃያዎች አሠቃያቸው፡፡በአንገታቸውም ላይ ከባድ ድንጋዮችን አንጠልጥሎ አሠራቸው፡፡ ጌታችንም በእሥር ቤት ሳሉ ተገልጦላቸው አጽናንቶ ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡ከዚህም በኋላ መኮንኑ ወደ እስክንድርያ ላካቸው፡፡ በዚያም ከሃድያኑ ብዙ
አሠቃዩአቸው፡፡ ዝፍጥና የብረት ድኝ በተሞሉ የብረት ምጣዶች ውስጥ ከጨመሯቸው በኋላ ነበልባሉ አስከ 20 ክንድ ከፍ ከፍ እስኪል ድረስ ከታች እሳት አነደዱባቸው፡፡ ዳግመኛም ከምጣዶቹ ውስጥ አውጥተው ከምድጃ እሳት
ውስጥ ከተቷቸው፡፡ ነገር ግን ጌታችን አሁንም ተገልጦ ያለ ምንም ጉዳት አዳናቸው፡፡ ሰማዕታቱም ዳግመኛ ወደ መኮንኑ ቀርበው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ፡፡ይህንንም ድንቅ ሥራ ያዩ 130 ሰዎች በጌታችን አምነው እነርሱም መስክረው ሰማዕት ሆኑ፡፡ከዚህም በኋላ መኮንኑ ቅዱሳኑን አስጨናቂ የሆኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው፡፡አጵሎን የሚሉትን ጣዖትም አምጥቶ በፊታቸው በወንበር ላይ አስቀምጦ
እንዲሰግዱለት አዘዛቸው፡፡ ቅዱሳኑ ግን በእግሮቻቸው ቢረግጡት ጣዖቱ ወድቆ ተሰበረ፡፡ መኮንኑም ይህንን ሲያይ ተቆጥቶ የቅዱሳኑንም እግሮቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸው፡፡ የከበረ ቀሲስ አብሲዳንን ግን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠውና
የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ቅዱስ ኮቶሎስንም በእሳት አቃጠለው፡፡ የቀሩትን አምስቱንም ከብዙ ሥቃይ በኋላ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸውና ሁሉም ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የድል አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት
ተቀዳጁ፡፡ የእነዚኽ የከበሩ ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
ቅዱሳን ሰማዕታት አባ ብሶይ፣ አባ ሖር፣ ቅዱስ ሖርሳ እና እናታቸው ቅድስት ይድራ፡-እነዚህም ቅዱሳን በእስክንድርያው ከሃዲ መኮንን ፊት የጌታችንን አምላክነት በመሰከሩ ጊዜ መኮንኑ አባ ብሶይን ይዞ ቀኝ እጁን አሥሮ በከተማዎች መካከል በበሬዎች አስጎተተው፡፡ የተሳሉ ብረቶችንም በእሳት አግሎ ሰውነቱን በመውጋት አቃጠለው፡፡ ግራ እጁንም ቆረጠው፡፡ ዳግመኛም እርሳስ አግሎ በአፉ ውስጥ ጨመረ፡፡ መርዛማ እባቦችና ጊንጦች ወደተሞሉበት ቦታም ወስዶ ጣለው፣ ነገር ግን እነርሱ አባ ብሶይን አልነኩትም፡፡ከዚህም በኋላ በብረት በትሮች በኃይል በደበደቡት ጊዜ አባ ብሶይ ወደጌታችን ጮኸ፡፡ ጌታችንም አጸናውና እንደቀድሞው ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡ እናቱም ወደ እርሱ መጥታ ባረጋጋችው ጊዜ መኮንኑ ያዛትና እርሷንም አሠቃያት፡፡በእሳት
በጋሉ ብረቶች ጎኖቿን ወግቶ አቃጠላት፡፡ እርሷም በዚህ መከራ ውስጥ ሆና ትዘምር ነበር፡፡ ሰማዕትነቷንም ፈጽማ ነፍሷን አሳልፋ ለእግዚአብሔር ሰጠች፡፡ቅዱስ አባ ሖርንም ከቅባትና ከተቀመመ ነዳጅ ጋር ቀላቅለው በብረት ምጣድ
ውስጥ አበሰሉት፡፡እርሱንም ጌታችን አጽንቶታልና ያለ ሕማም ሆኖ ፈጣሪውን ሲያመሰግን መኮንኑ ሰምቶ በመደንገጥ እጅግ አድርጎ አደነቀ፡፡ ንጉሡ ግን ተቆጥቶና ተናዶ አባ ሖር በብረት ምጣዱ ላይ ሆኖ በእሳት እንደተጣደ በጦር ወጋው፡፡ ሰማዕትነቱንም በዚሁ ፈጸመ፡፡ ወንድሙን አባ ብሶይንም ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ራሱን በሰይፍ ሰይፈውት ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ሁለቱም የድል አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ከእነርሱም ጋር ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ የሆነ አባ ሖርሳም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
የሮሜው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ማርቆስ፡- ይኽም ቅዱስ በድንግልና አምስት ዓመት ነገሠ፡፡ ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ፡፡ ሕዝቡም እርሱን ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስት እንዲያገባ መኳንንቱ አስገደዱት፡፡ እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ሰግዶ ጸለየ፡፡‹‹እመቤቴ ሆይ! ለአንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደምሄድበት
ምሪኝ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወደ ቶርማቅ ተራራ ሂድ፣ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይኑር›› አለችው፡፡ እርሱም በሌሊት ወጥቶ በመሄድ ወደ ባሕር ወደብ ደረሰ፡፡በመርከብም ተሻግሮ ወደ ቆርማቅ ተራራ በደረሰ ጊዜ ቦታውን ደረቅ ሆኖ አገኘው፡፡ በዚያም ከአጋንንት ጋር እየተጋደለ በውስጡ 60 ዓመት ኖረ፡፡ ባረፈም ጊዜ ቅዱሳን መላእክት በታላቅ ክብር ቀበሩት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣
በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥጋና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው የነበሩት ሰማዕቱ አቡነ ዓምደ ሚካኤል ፍልሠተ ዐፅማቸው ነው፡፡ጻድቁ ኅዳር ሦስት በሰማዕትነት ካረፉ በኋላ መጀመሪያ በንጉሥ እስክንድር ዘመነ መንግሥት ወደ አባቶቹ መቃብር ዳግመኛም በንጉሥ ልብነ ድንግል ዘመን በዐረፉ በ40 ዓመታቸው ፈለሱ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው፡፡
"" ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ::
አሜን:: ""✝
+*✝" ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ (እል-በረዳይ) ✝"*+
(St. Jacob baradaeus)
(በተለይ በሃገራችን የተዘነጋ የሚመስለው የምሥራቅ ኮከብ -
ኮከበ ጽባሕ)
=>"ያዕቆብ" ለሚል ስም ትርጉምን የሰጡ አበው በ2 መንገድ
ያትቱታል::
1.አኃዜ ሰኮና:: ነገሩ ከወልደ ይስሐቅ ወርብቃው ርዕሰ አበው
ያዕቆብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አበው ግን ለትህትና
ይተረጉሙታል::
2.አእቃጺ / አሰናካይ:: ነገሩ ስድብ (አሉታዊ) ይምሰል እንጂ
በዚህ ስም የተጠሩ አበው ሁሉ ለአጋንንትና ለመናፍቃን ትልቅ
መሰናክል ሆነውባቸው ኑረዋልና አባባሉ ምስጋና እንጂ ነቀፋን
አይወክልም::
+የ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ምሥራቃዊ ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብም
ለመለካዊ መናፍቃንና ለተዋሕዶ ተገዳዳሪዎች ትልቅ መሰናክል
ሆኖባቸዋል:: የቀናችውን ቀርነ ሃይማኖትንም አጽንቷል::
+ብዙ ጊዜ "ዘ"-እልበረዲ መባሉን ይዘው በ"ዘ" ምክንያት
እልበረዲን እንደ ሃገር የቆጠሯት አልጠፉም:: በረከታቸው
ይድረሰንና ትጉሑ ዻዻስ አቡነ ጐርጐርዮስ ካልዕ ግን ለዚሁ
መላምት "የለም!" ባይ ናቸው::
+'የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ' በተሰኝ ተወዳጅ
መጽሐፋቸው "እል-በረዲ" ማለትን በዓረብኛ ከሠጋር በቅሎ :
ከሥሙር ሠረገላ ጋር አነጻጽረው አስቀምጠውታል:: ለምን ቢባል
- እንደ ሠረገላ በተፋጠነ አገልግሎቱ ወዳጅንም ጠላትንም
አስደምሟልና::
+ቅዱስ ያዕቆብ የተወለደው በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ
(በ500 አካባቢ) ሲሆን ያረፈው ደግሞ በ578 ዓ/ም እንደሆነ
ይታመናል:: ነገሩን ልብ ስንለው ቅዱስ ማኅሌታይ ያሬድን -
ወዲህ በዘመን : ወዲያ ደግሞ በአገልግሎት ይመስለዋል::
እርግጥ ነው ለውለታው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት"
ስትባል የእኛዋስ ምናለ "ያሬዳዊት" ብትባል የሚል ቁጭትን
ያመጣል::
+ጊዜው (5ኛውና 6ኛው መቶ ክ/ዘመን) ወዲህ ወርቃማ :
ወዲያ ደግሞ ጨለማ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ዘመን ነበር::
¤በብርሃንነቱ በተለይ በምሥራቁ ዓለም ያበሩ አበው እነ ያዕቆብ
ዘስሩግ : ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ : ያዕቆብ ዘእልበረዲን የመሰሉ
አበው ተገኝተውበታል:: ሲያልፍ ደግሞ ዘይኑንና አንስጣስዮስን
የመሰሉ ደጋግ ነገሥታት በዘመኑ መነሳታቸውን እናስባለን::
+በተቃራኒው ግን ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ለ2 የተከፈለችበት :
መለካውያን የነገሥታቱ ደጀን አላቸውና ተዋሕዶ ሃይማኖትን
ከሥሯ ነቅሎ ለማጥፋት ብዙ የሞከሩበት ዘመን ነውና ጨለማነቱ
ይጐላብናል::
+በእርግጥም ከመርቅያን እስከ ዮስጢኖስ ዳግማዊ ዘመን
ድረስ ለ100 ዓመታት መለካውያኑ የልዮን ልጆች 2 ባሕርይ
ማለትን ሊያሰፉ : ተዋሕዶንም ሊያጠፉ የከፈቱት ዘመቻ ሊሳካ
ጫፍ የደረሰ ይመስል ነበር::
+ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔ
ዓለም አርመኖቹን ስቦ በ490ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ::
በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን : በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ
ሳዊሮስን አስነስቷል:: ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ
ንግሥት ታኦድራን ማርኯል:: በእነዚህ ቅዱሳን ትጋት
የለመለመችው ተዋሕዶ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ያለ
አርበኛን ግን ያገኘችው በጭንቅ ቀን ነበር::
+ሰው መሆን ሰው በጠፋባቸው ቀናት ነውና : በግብጽና
በቁስጥንጥንያ በትምህርትና ምናኔ ላይ የነበረው ቅዱሱ ታጥቆ
ለአገልግሎት የተሰለፈው በ530ዎቹ አካባቢ ነበር::
+ጊዜው ወዲህ አንበሳው ቅዱስ ሳዊሮስ ከሶርያ ወደ ግብጽ
እንደተሰደደ ያረፈበት ነበር::
ወዲያ ደግሞ ሊቁ አባ ቴዎዶስዮስ የግብጹ ለግዞት የተዳረገበት
ነበርና የተዋሕዶ ምዕመናን ያለ እረኛ ተቅበዘበዙ:: የቤተ
መንግስቱ ተጽዕኖ ደግሞ 2 ባሕርይ በማይሉት ላይ እሥራትና
ግድያን ወደ ማወጅ ተሸጋግሯልና የምእመናን ቁጥር እጅጉን
መመንመኑ ቀጠለ::
+ይህ ዕረፍት የነሳው ቅዱስ ያዕቆብ በበኩሉ ነገሩን በዝምታ
ሊያልፈው አልወደደምና አገልግሎቱን አሰፋ:: ሌሊቱን በጸሎት
ያድራል:: ቀን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማስተማር ባይችል
በየቦታው እየዞረ ያስተምር ነበር::
+ከትምህርቱ ጣዕምና ከመልእክቱ ሥምረት የተነሳም ምእመናን
እንደገና ተነቃቁ:: እርሱም ከግብጽ እስከ ሶርያ : አልፎም እስከ
ቁስጥንጥንያ ድረስ ያለ ዕረፍት ሲሰብክ 40 ዘመናትን አሳለፈ::
በተለይ አዲስ አማኞችን ያጠምቅ ዘንድ በእሥረኛው ቅዱስ
ቴዎዳስዮስ ኤዺስ ቆዾስነትን ተቀብሏል::
+የሶርያ (አንጾኪያ) የፕትርክና መንበሩ ክፍት ሆኖ እርሱን
ቢጠብቀውም እርሱ ግን የዚህ (የስልጣን) ፈላጊ አልነበረምና
ሌሎች እንዲሾሙበት አድርጉዋል::
+ቅዱስ ያዕቆብ በስብከት አገልግሎት ምሥራቁን ዓለም ሲያበራ
የተባበሩት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም ያሳለፈው ድካምና መከራ
ግን ተወዳዳሪ አልነበረውም:: በተለይ የወቅቱ የአንጾኪያ ኃያላን
መኩዋንንትና ሹመኛ መናፍቃን ብዙ አሳደውታል::
+እርሱ ግን በጥበብና በፈሊጥ እዚያው ደጃቸው ላይ የነበሩ
ምዕመናንን በእረኝነት ጠብቁአል:: ለዚህ ሲባልም ራሱን
እየቀያየረ የመሣፍንቱን አጥሮችና ቅጥሮች አልፏል:: ለቤተ
ክርስቲያን ክብርም እንደ እብድ : እንደ ሴትም መስሎ የወንጌልን
ዘር ዘርቷል::
¤ከብዙ ፈተናና አገልግሎት በሁዋላም በተወለደ በ78 ዓመቱ
(በ578 ዓ/ም) ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
¤ትልቁ መታሰቢያው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" :
ምዕመኑ "ያዕቆባውያን" መባላቸው ሲሆን እኛ ደግሞ
በአንገታችን ላይ እንድናስራት ባስተማረን ማዕተብ (ማኅተም)
ዘወትር እናስበዋለን:: ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብን በአንገት ላይ
ስለ ማሰር ያስተማረ እርሱ ነውና::
¤የምሥራቁን ኮከብ እል-በረዲ ያዕቆብን በየዓመቱ ሰኔ 28 ቀን
በነገረ ቅዱሳን መደበኛ ጉባኤ (ጐንደር) እናከብራለን::
ሶርያውያን ደግሞ July 31 (ሐምሌ 24 ቀን) ያከብሩታል::
=>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር
አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም
እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል::
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን
እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+
(ማቴ. 5:13-16)
=>አምላከ ቅዱስ ያዕቆብ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን::
ከቅዱሱ በረከትም አይለየን::
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር:: አሜን:: >>>
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለአባታችን ክፍለ ሥላሴ የእረፍት በዓል አደረሳችሁ አደረስን
“አፉሁ ለጻድቅ ይትሜሀር ጥበበ፤ወልሣኑ ይነብብ ጽድቀ/የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፤አንደበቱም ፍርድን ይናገራል”””
መዝ.37፥30
🌹🍂...የ 28 ዓመቱ ወጣት ታላቅ ጻድቅ መነኩሴ
🍂ከምድረ ዛውል(በድባሩባ ወረዳ/ዞን የምትገኝ ኤርትራ ውስጥ) የወጡ፤የሃይማኖት ብርሃን፤የሥነ ምግባር ዓምድ የሆኑ በእድሜ የ28 ዓመት ወጣት፤በመንፈሳዊ ብስለት ግን አረጋዊ የሆኑ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በረከት፣ቅዱስ ታሪካቸውን እንካፈል ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን፡፡
🍂ኣቡነ ክፍለ ሥላሴ ከአባታቸው ከተክለ ማርያም ወልደ ዘኪዎስ እና ከእናታቸው ከርግበ ዳዊት ዛውል በሚባለው ቦታ ተወለዱ። በመጀመሪያ የወጣላቸው ስም መሓርየ እግዚእ› የሚባል ነው። አእምሮአቸው ንጹሕና ብሩሕ የሆኑት አቡነ ክፍለ ሥላሴ በልጅነታቸውም በጎችንና ፍየሎችን እያገዱ (እየጠበቁ) ወላጆቻቸውን አገለገሉ።
🍂አቡነ ክፍለ ሥላሴ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የተመረጡ ስለነበሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ይታወቁ ነበር፡ ስመ ሥላሴን በከንቱ እያነሡም ነበር። ስመ እግዚአብሔርም ከተጠራባቸው በፍርሃት ይታዘዛሉ። እረኞችም ከብቶቻቸውን እንዲመልሱላቸው የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩባቸው ይታዘዟቸው ነበር። በዚኸም ነገር አቡነ ክፍለ ሥላሴ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእን መሰሉ። በትግራይና በጎንደር በእጅጉ የሚታወቀው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩበት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይልም ነበር። ከልጆችም ጋር ሲጫወቱ ልጆቹ ስለ እግዚአብሔር ብለህ ይህን አድርግልን " ሲሉት ያደርግላቸዋል። በእረኝነት ሳሉ ምሳውንም ሆነ እራቱን ለምስኪኖች ይሰጣል። ለእግዚአብሔር ስም እጅግ ቀናተኛ ስለነበረ ስሙን በመፍራት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ‹‹ይህን ክፉ ነገር በራስህ ላይ. አድርግ›› ባሉት ጊዜ እንኳን በራሱ ላይ አንዳች ክፉ ነገር ወይም አደጋ ለማድረስ ወደኋላ አይልም ነበር። ይህንንም ሊፈትኑት ብለው አንድ ቀን ስለታም ጦር አምጥተው ስለ እግዚአብሔር ብለህ እስቲ ራስህን በዚህ ስለታም ጦር ትወጋ ዘንድ ና› ባሉት ጊዜ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ በሕሊናው እንደወሰነ እርሱም በቁርጥ ሕሊና ሆኖ ራሱን በጦሩ ሊወጋ ሲል ዘለው ያዙት። በሌላም ጊዜ እንዲሁ ሊፈትኑት በጭነት ምክንያት ጀርባው የቆሰለ አህያ አምጥተው ዓበዐ እግዚእ ስለ እግዚአብሔር ብለህ የዚያችን አህያ ቁስሏን ላስ አሉት። እርሱም ያን ጊዜ ርኩስን ብስም ኃጢአት ይሆንብኛል፣ አይሆንም ካልኳቸው ደግሞ ስመ እግዚኣብሔርን ጠርተንበት እምቢ አለ ስለሚሉ የፈጣሪዬን ስም መዳፈር ይሆንብኛል ብሎ በልቡ አሰበና ያን ጊዜ ይስም ዘንድ ተመለሰ። ባልንጀሮቹም በቁርጥ ሕሊናው እንደወሰነ ባወቁ ጊዜ ሊያደርገውም ሲሔድ ተመልክተው ቶሎ ብለው ሮጠው ከኋላው ያዙት። እርሱም «እኔስ የፈጣሪዬን ስም እፈራለሁ ስሙን ተደፋፍሬ በምድር በሕይወት ከምኖር ሞት ይሻለኛል» አላቸው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም እንዲሁ በፈሪሃ እግዚአብሔር ይታወቃሉ። ስመ ሥላሴን በከንቱ ፈጽመው ጠርተው አያውቁም፣ ስመ እግዚአብሔር ከተጠራባቸው ማንኛውንም ነገር ያደርጉ ነበር።
🍂ከዚኸም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ወደ አቡነ ሳሙኤል ገዳም ደብረ ዓባይ ሔደው በሚያስደንቅ ትሕትና ለአባቶች እየታዘዙ መዝሙረ ዳዊትን ተማሩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አጠኑ። ከዚያም የአባቶችን ቡራኬ በመቀበል ወደ ደብረ ቢዘን በመሔድ የአቡነ ፊሊጶስንና የአቡነ ዮሐንስን ልጆች በማገልገል የቅዱሳኑን አሠረ ፍኖታቸውን ተከትለው በተጋድሎ ኖሩ። ሌሊትና ቀን በእያንዳንዱ ሥርዓተ ጸሎት ላይ አንድ አንድ ሺህ እየሰገዱ ይጸልዩ ስለነበር የእንቅልፍና የዕረፍት ጊዜ አልነበራቸውም። በእንደዚህም ዓይነት ተጋድሎ ከቆዩ በኋላ ከአቡነ ፊሊጶስ 6ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ገብረ ማርያም እጅ ምንኩስናን ተቀበሉ። ከመነኰሱም በኋላ መነኰሳቱ እህል እንዲፈጩ ሲያዟቸው አባታችን ክፍለ ሥላሴ በመታዘዝ ወደ እህል መፍጫው ቤት ገቡ፣ ነገር ግን አባታችን እህል መፍጨት አይችሉም ነበር። እርሳቸውም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ ሁሉም ሊፈጭ ተዘጋጅቶ የነበረው እሀል በተኣምራት ተፈጭቶ ተገኘ። መነኰሳቱ ግን ይህን አላወቁም ነበር።
🍂አቡነ ክፍለ ሥላሴ ከዚኽ በኋላ ወደ ሀገረ ደምብያ ሔደው ከጳጳሱ እጅ ሥልጣነ ክህነትን ተቀበሉ። ከዚያም ሲመለሱ መረብ ወንዝ ሲደርሱ አብሯቸው የነበረውን የሥጋ ወንድማቸውን ‹‹ኦ ወንድሜ እነሆ በሥጋ የወለደን አባታችን ዛሬ
ዐረፈ" በማለት የአባታችቸውን መሞት በመንፈስ ቅዱስ ዐውቀው ነገሩት ወደ ሀገራቸውም ክገቡ በኋላ የሀገራቸው የውል ሰዎች ያላወቁ መስሏቸው የአባታቸውን መሞት ለኣቡነ ክፍለ ሥላሴ ነገሯቸው። አባታችንም አባቲ እንደሞተ አስቀድሜ ዐውቄያለሁ፤ እግዚአብሔር ወደ ገነት እንዲያስገባው በጸሎት አግዙኝ እንጂ አታልቅሱ›› አሏቸው። ሰዎቹም የተሰጣቸውን ጸጋ አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
🍂ጻድቁ ወደ ደብረ ቢዘን ተመልሰው ሔደው በክህነት እያገለገሉ ሳለ ወደ አቡነ እንድርያስ ሰፍኣ ደብረ ጽጌ ገዳም ለመሔድ እሰቡ፤ ነገር ግን ትልቅ ዋርካ ያለበትን ባምብቆ የተባለውን ተራራ በራእይ ከተመለከቱ በኋላ ወደዚያ እንዲሔዱ እምላካዊ መልእክት መጣላቸው። እርሳቸውም የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ በደስታ ተቀብለው ወደ ባምብቆ በመሔድ ቤተ ክርስቲያን አንጸው የቅድስት ስላሴን ታቦት አስገብተው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፤ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈሩ።
🍂አቡነ ክፍለ _ ሥላሴ በባምብቆ ሳሉ ታቦተ ጽዮን ለነቢዩ ዕዝራ ባዘነች ሴት አምሳል እንደታየችው እንዲሁ ለአባታችንም አንዲት ያዘነች ሴት በራእይ መጥታ ዕጣን በማይታጠንበትና መሥዋዕተቍርባን በሌለበት ቦታ እንደ ሽኮኮ በጉድጓድ ውስጥ እንዳስቀመጧት ነገረቻቸው። በዚያም በበረሓ ውስጥ ደብቀው ያስቀመጧት ዮልዮስ የተባለ አንድ አመጸኛ መኰንን ቤተ ክርስቲያንን ሊያቃጥል በፈለገ ጊዜ ነው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም ወደተነገራቸው ቦታ በመሔድ ካህናቱን በጉድጓድ ውስጥ ስላስቀመጡት ታቦት ሲጠይቋቸው እነርሱ ግን የደበቅነው ታቦት የለንም› አሏቸው። አባታችንም “ወንድሞቼ ሆይ! እውነቱን ተናገሩ›› በማለት በራእይ የተመለከቱትን ነገር
ነገሯቸው። ካህናቱም ፈርተው አዎን አባታችን ይቅር በሉን፣ ዮልዮስን ፈርተን ታቦቱን ዋሻ ውስጥ ደብቀነዋል›› ብለው ቦታውን አሳዩአቸውና አውጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን መለሱት።
በስመ ዓብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
እስኪ ጉለሀ የማር ሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ለሚገኙት መነኮሳት አንድረስላቸው ሁላችሁም አቅማቹ የቻለውን በመለገስ እኝህን ደጋግ አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ገዳሙን እንታደግ አመሰግናለሁ ። 🙏🏼🙏🏼🙏🏼
ንግድ ባንክ : 1000480421209
አቢሲኒያ ባንክ : 95999328
ሙሉ መረጃ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ 👇
https://vm.tiktok.com/ZM2m3tMBY/
መድኃኔዓለም ስምህ ገናና | ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ †††
††† ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ : በሕገ ኦሪት አድጐ : ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው::
ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ : ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::
በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::
ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል::
ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: 2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው : ፈወሰው : አጠመቀው : በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19)
ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ:: መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::
††† ቅዱስ ቶማስ ዘሰንደላት †††
††† በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ሰማዕታት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ወደ ሰማዕትነት ሕይወት የገባው በ11 ዓመቱ በመላእክት መሪነት ነው:: ገና ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደ ቀረበ መኮንኑ "ክርስቶስን ካድና ልሹምህ" ቢለው ሕጻኑ ቅዱስ ቶማስ ተቆጥቶ : "አንተ ሰነፍ መኮንን" ብሎ ገስጾ : በጐችን ይመልስባት በነበረችው ጅራፍ ገርፎታል:: ይሔም በዘመኑ የመጨረሻው የድፍረት ደረጃ ነበር::
††† በዚህም ምክንያት በሕጻን ገላው ላይ የተቀበለው መከራ ሊናገሩት ይከብዳል::
¤ግርፋት:
¤እሳት:
¤አራዊት በእርሱ ላይ አልፈዋል::
አካሉ ተቆራርጧል:: አንድ ጊዜም "ለጣዖታችሁ እንድሰግድ አምጡት" ብሏቸው ልክ ከፊቱ ሲደርሱ ወደ ጌታ ቢጸልይ መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች::
እሱን ያሰቃየው የነበረውን መኮንንም ከደዌው አድኖ ከነ ሠራዊቱ አሳምኖታል:: ሕጻኑን ቅዱስ ቶማስን ግን ያላመኑ አረማውያን በዚህች ቀን አንገቱን ሰይፈውት በሰማዕትነት ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::
††† አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያው በረከት : ከሰማዕቱም ምልጃ አይለየን::
+"+ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ +"+
=>#በቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ በደራሲነታቸው: በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::
+ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::
+አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ #ቤተ_መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "#አንሰ_እፈርሕ_ሠለስተ_ግብራተ-እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::
+ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:-
1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "#እግዚአብሔር_በዚሕ_ሕጻን_አድሮ_ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::
+ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::
+"እንግዲያውስ #ትንቢተ_ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በሁዋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን: ዕጸበ ገዳምን: ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ: #ጾምና_ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
+በዘመኑም:-
1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል
2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል
3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል
4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::
+በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በሁዋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::
=>#አምላከ_ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::
††† ሰኔ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት (ዘሰንደላት)
3.ቅዱስ አልዓዛር ነዳይ (በነዌ ደጅ የወደቀ : ቀጥሎ ደግሞ በአብርሃም እቅፍ ውስጥ የተገኘ ጻድቅ - ሉቃ. 16:19)
4.ቅዱስ ማማስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
††† "በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ:: ጌታም በራዕይ:- "ሐናንያ ሆይ!" አለው:: እርሱም "ጌታ ሆይ! እነሆኝ" አለ:: ጌታም:- ተነስተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሒድ:: በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ:: እነሆ እርሱ ይጸልያልና:: ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቷል" አለው::" †††
(ሐዋ. 9:10-18)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ
ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፡፡ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁኖ ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ አፍሬም ትለዋለች : እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድስኒ ትለዋለች በዕለት ሰኑይ ክርክር አልቋልና ባርከኒ ይላታል፣፣ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ትለዋለች፡፡ ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሓፊ ነው፡፡ እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ብሎ ይጀምል፡፡
አክሊለ ምክሕነ፡፡
አክሊል የወዲህኛው ፤ ምክሕ የወዲያኛው::
ወቀዳሚት መድነኒትነ፡፡
ቀዳሚት የወዲህኛው ፡ መድኃኒት የወዲያኛው።
ወመሠረተ ንጽሕነ፡፡
መሠረት የወዲህኛው፤ ንጹሕ የወዲያኛው፡፡
ኮነ በማርያም ድንግል።
በማርያም ድንግል ሆነልን አለ፡፡ ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን ፤ ከመሳፍነት ኢያሱን ፤ ከደናግል ኢሊያስን አስከትላ መጥታለች፡፡ ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ብትባል የመመኪያችንን ውድ ማምጣት አልተቻልህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የድኅነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤሊያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል ፣ የንጽሕናችን መሠረት መሆን አልተቻለህም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ ፤ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ፡፡
ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይውት የሚባል ጌታ አኃዜ ዓለም በአራኈ ኩሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረት ዓለም !ይጸውር ድደ ወይነብር ፈረ እንዲል፤ መሠረተ ዓለም የሚባል ጌታ ፣ በድንግል ማርያም ተሰማልን፡፡ ትላንት ስሟን አላነሳም ዛሬ ስሟን አነሣ በአንግዳ ልማድ እንግዳን ዕለቱን ስሙን እየጠሩትም ፣ ከዋለ ካደረ በኋላ ስሙን ይጠሩታል በዚያ ልማድ ፣ ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው : ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተግታለች፡፡ ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና፡፡
አንድም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው ለጊዜው ለናት ላቲ ጸጋ ሁና ተስጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁላ ጸጋ ሁና ተስጥታለችና አንድም መርሕ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ምእመናን መርታ ገነት መንግስተ ሰማያት አግብታለችና::
አንድም ልዕልት ማለት ነው፡፡ ሮም አርያም ማለት ልዑል ማለት እንደ ሆነ፡፡ እርሷንም መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሐይምናን ሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ፤ ወተሐሰዩ ቤተ ይሁዳ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡
እንተ ወለደት ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ፡፡
መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው አካላዊ ቃልን በወለደች በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡
እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ፣፣
ዘኮነ ሰብእ በአንተ መድኃኒትነ፡
እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ፡፡
ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ሐራ ጥቃቃል ሥጋ ኮነ ያለውን ይዘው ወደ ታች ተለወጠ ይላሉና ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው::
ስለዚህ ነባር ማኅተመ ድንግግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡
ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡
መንክር ኅያለ ወሊዶታ ዘኢይትነገር፡፡
ድንቅ የሚሆን የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
††† ✝እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ✝†††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን ✝†††
††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::
አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው::
ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል::
ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::
ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ40 ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል (አገልግሎታል):: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል::
በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::
††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ
¤ሕዝቡን አሻግሮ
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::
ሰባት አሕጉራተ ምስካይ (የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው:-
"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::
††† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::
††† ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
በየዘመናቱ የድንግል ማርያምን ድንግልና ለማቃለል የሚሞክሩና ብዙ ልጆች አሏት ሊሉ የሚደፍሩ አሳዛኞች ተነሥተዋል፡፡
ነቢዩ ሕዝቅኤል በራእይ አይቶ :-
ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል' ብሎ የተናገረላት እግዚአብሔር ገብቶባት ያልተከፈተችው በር ድንግል ማርያም ናት፡፡ ሕዝ.፵፬፥፪
“ሕዝቅኤል ሆይ ትናገር ዘንድ ዛሬ የመናገር ዕጣው የእንተ ነው፡፡ ስለ ማርያም ተናገርና ስለአርስዋ የሚደረገውን ምርምርንም ግታ ፤ ስለማትመረመረው ድንቅ እናት የተናገረውን የነቢዩን ትንቢት ኑ አንስማ፡፡
እርስዋ ቅድመ ዓለም ወልድን ብቻውን የወለደው የአብ ምሳሌ ናትና እርሱ ከወልድ በቀር ልጅ እንደሌለው እርስዋም ሌላ ልጅ የላትም፡፡
የእግዚአብሔር አብ ምሳሌ ናትና ከሥግው ቃል በቀር ለዕሩቅ ብእሲ እናት መሆን ፣ በባሕርይዋ ሁለተኛ መውለድ አትችልም፡፡
በጳጳስ ወንበር ቄስ ፣ በንጉሥ ወንበር ራስ ደፍሮ ይቀመጣልን? ወይስ ሊቀመጥ ይገባዋልን? እንዲሁም አምላክ ባደረበት ማሕፀን ዕሩቅ ብእሲ አያድርም፡፡
ሠዓሌ ሕፃናት በተሣለበት ሰሌዳ በተቀረጸበት ሰፋድል ዘርዐ ብአሲ ቀለም ሆኖ ሊሣልበት ሊቀረፅበት አይቃጣም አይታሰብም፡፡
ዐውደ ማሕፀንዋ አስቀድሞ በትንቢት ታጥሯል በብፅዓት ተቀጥሯል ፤ ተዘግቶ ይኑር አይከፈት ሰው አይግባበት የሚል አዋጅ ተነግሮበታል'
ወዳጄ እስቲ አስተውለን እናስበው::
እውነት ድንግል ማርያም የወለደችው ልጅ ሌላ ልጅ የሚያስመኝ ልጅ ነውን?
የእርስዋ ልጅ አዳምና ሔዋን በዝተው ተባዝተው ያልሞሉትን ምድርና ሰማይ በመለኮቱ የሞላ ፣ ምድርን በደሙ ያጠበ ፣ በሥጋው የመገበ ፣ በብርሃኑ ያበራ ሁሉ በእርሱ ፣ ለእርሱ ፣ ከእርሱ የሆነለት ንጉሥ ነው፡፡
የእመቤታችን እረድኤት በረከት አይለየን!!!
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ✝እንኩዋን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝
=>ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው (ጽጌ): ሐጋይ (በጋ): ጸደይ (በልግ)ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::
+በተለይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና "ሽሽታችሁ (ስደታችሁ) በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና (ማቴ. 24:20) ልንጸልይ ይገባናል:: በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ: አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችምና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ:-
"በዝንቱ ክረምት በመዋዕሊነ:
እንበለ ፍሬ እንዘ በቆጽል ኀሎነ:
ናስተበቁዐከ እግዚኦ ኢይኩን ጉያነ::"
(ክረምት በተባለ በእኛ እድሜ:
ፍሬ ሳናፈራ በቅጠል /ያለ መልካም ሥራ/ ሳለን:
አቤቱ ጌታ ሆይ ስደትን አታምጣብን)
=>ቸሩ አምላካችን ከዘመነ መጸው በሰላም ያድርሰን:: ተረፈ ዘመኑንም የንስሃ: የፍሬና የበረከት ያድርግልን::
=>በዚሕች ዕለት እነዚህ ቅዱሳን ይከበራሉ:-
+" ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ "+
+በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች:: አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::
ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ. 14:22)
+ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል:: አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው:: ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል::
+" ቅዱሳን ዺላጦስና አብሮቅላ "+
=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም::
+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል::
+ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::
=>ጌታችን ከሐዋርያው ይሁዳ: ከዺላጦስና አብሮቅላም ጸጋ በረከትን ያድለን::
=>ሰኔ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን
3.ቅድስት አብሮቅላ (ሚስቱ)
4.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት
5.የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
=>+"+ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: +"+ (ይሁዳ. 1:1)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
እመ ፡ ብከ ' ሠቅ ፡ ዘትለብስ ፡ ከመ ፡ ትብኪ ፡ ቦቱ በእንተ ጌጋይከ ፡ ኢትኅድጎ ፡ ለሰብእ ፡ ክሡተ ይትረአይ ፡ከመ ኢትትኃጐል፣ ፃማከ ፡ አላ ፡ ይኩን፡ ሠቅከ ፡ ኅቡአ ' እምውስጥ ፡ ወኢትትዐጸፍ ፡ አም ዕስተ ፡ ከመ ፡ ያእኩቱከ ፡ ሰብእ ። ማቴ ' ፮ ' ፭ ።
(ኃጢአትህን ፡ እያሰብክ ፡ ታለቅስበት ፡ ዘንድ ፡ በው ስጥ ፡ የምትለብሰው ፡ ሠቅ ' ማቅ ፡ ቢኖርህ ፡ ዋጋህ እንዳይቀርብህ ፡ ለሰው ፡ በግልጥ ፡ እንዲታይ ፡ አታድርግሠቅህ፡ማቅህ ፡ በውስጥ የተሠወረ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ' ሰዎች ' እንዳያመሰግኑህዳባ ፡ አትልበስ ። ማቴ ፡ ፮ ' ፭ ።)
ወኢታንኀ ፡ ዐጕረ ' ድማኍከ ፡ እስመ ፡ ሐዋርያ ፡ አብጠለ ፡ ዘንተ፡ አምሳለ ወኢትንሣእ፡ እምፅሕምከ ፡ አመ ፡ ትላፂ ፡ ርእሰከ ወኢትኅድግ ፡ ላዕሌከ ሠርጐ፣ እምፀጕርከ ። ፩ ፡ ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፲፬ ።
( የራስህን ፡ ጠጕር ፡ አታሳድግ ፡ ይህን ፡ ሥራ ፡ ሐዋ ርያ ፡ ነቅፎዋልና ፡ ራስህን ፡ በላጨሀ ፡ ጊዜ ፡ ከጽ ሕምህ ፡ አትንካ ፡ (አትላጭ)ከፀጉርህ ፡ በአንተ ፡ ላይ፡ ጌጥ ፣ ጋሜ ፣ ቁንጮ ፡ አትተው ። ፩ ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፲፬።
ሠለስቱ ምዕት❤️
በሰው ላይ ያለ የመለኮት መልክ የተረዳ (የታወቀ) እንደሆነም እነሆ አስረዳህ፡፡
የራስ፣ የጸጉር፣ የዐይን፣ የጆሮ፣ የፊት፣ የአፍ፣ የእጅ፣ የእግር፣ የጣት መልክ አለውና፡፡
ሰነፍ ሰው ሆይ ይህን በሰማህ ጊዜ ልዑልን (እግዚአብሔርን) ከሰው፣ ከትል፣ ከነቀዝ ጋር አታስተካክለው፡፡
ግርማቸው በሚያስፈራ
በመባርቅትም ቢሆን፣
ከብርሃኑ የተነሣ በፀሐይም ቢሆን፣
ከከፍታው የተነሣ በሰማይም ቢሆን፣
ከስፋቷ የተነሣ በምድርም ቢሆን፣
ከጥልቅነቱ የተነሣ በባሕርም ቢሆን፣
ከማቃ ጠሉ የተነሣ በእሳትም ቢሆን፣ ከረቂቅነቱ የተነሣ በነፋስም ቢሆን በማና ቸውም ፍጡራን ይመስሉት ዘንድ አይገባም፡፡
ፈጣሪን ከማንኛውም ስም ጋር የሚያስተካክለው፣ የሚያመሳስለው ሰው የሚናገረው በአጋንንት አለቃ፣ ለዘለዓለሙ ለገሃነም በተዘጋጀ መንፈስ ነው፡፡
ኃጢአቱም አይሰረይለትም በሦስቱ ስም፣ በሁሉም የብርሃን ሠራዊት (በመላእክት) የተረገመ የተወገዘ ነው እንጂ፡፡
ይህም የእግዚአብሔር አኳኋን እንደዚህ ነው ብለው በሚናገሩት ላይ ሁሉ ይደርስባቸዋል፡፡ ስለዚህም አኳኋኑ የማይታወቅ ባሕርዩን ልንመረምር አይገባንም፡፡
ከወደደ ከጸናች መለኮታዊት ባሕርዩ ፈጽሞ ሳይለይ በማይመረመር ባሕርዩ ይገለጣል እንጂ፡፡
በሙሴ ፊት እሳትን ሆነ፤
በዕዝራ ፊት መብረቅን ሆነ፤
ለሄኖክም በአረጋዊ ሰው አምሳል ተገለጠ፡፡ ለዳንኤልም ጎልማሳ ሆነ፤
በሕዝቅኤል ሕፃን፣
በዕንባቆም በግ፣
በዮሐንስፍጹም ሰው፣
በማርያም ርግብ፣
በዮርዳኖስ ንስር፣
በመሥዋዕት ጊዜ ኅብስት
በመልከ ጼዴቅ እና በቃና ወይን፣ አስኔት በተባለች ሀገር ንብ፣
በዕፀ ጳጦስ መልአክና ነበልባል
በምድረ ርስት መዓርና ወተት፣
በሄርማ ኢጦያ የተባለ ዕንጨት፣
በአብርሃም እንግዳ፣
በይስሐቅ የታሰረ በግ፣
በያዕቆብ አርበኛ (ተጋዳይ)፣
በኤልያስ ቀጭን ፉጨት፣
በሐዋርያት የእሳት ልሳን፤
በእንጦንስ ፀሐይ፤
በሰብአ ሰገል ኮከብ፣
በዮስጣቴዎስ ኃይለኛ አውሬ፣
በመቃራ ድንግል ብላቴና፣
በኖኅ ቀስተደመና፣
በወንጌል በር' የመንጋ እረኛ፣
በዳዊት ነጎድጓድ፣ ፍም፤ መብራት፣
በሰሎሞን እንኮይ፣
በዮሐንስ መንገድ፣ ልብስ፣ ነጭ ሐር፣
በባቱኤል ተራራ፣ ነፋስ አንበሳ፣
በሄጲሊጦስ የአንበሳ ግልገል፣
በጌዴዎን ልምላሜ፣
በእስክንድርያስ ሐመር (መርከብ)፣
በምሕረቱ ብዛትም ባህር ዝናም፣ የቅድስናው ተራራ በሆነች በጽዮንም ጨረቃ በመምሰል ተገለጠ፡፡
ርቱዓ ሃይማኖት ❤️