✞እንኳን አደረሰን !
•ብጹዕ አባ #ኪሮስ፥
ዘአንደየ ርዕሶ በእንተ መንግሥተ ሰማያት፤
•ብጹዕ አባ ኪሮስ፥
ዘአጥረየ ንዴተ ከመ ሐዋርያት፤
ወትረ ትጋሃ ከመ መላእክት፤
መዓልተ ጸሎታተ፤
ወሌሊተ ስግደታተ፤
ፈጸመ ሥርዓተ መነኮሳት፤
አዕረፈ በክብር ወበስብሐት!
•ቅዱስ ወክቡር፤
ብእሴ እግዚአብሔር፤
ለአሕዛብ መምህር፤
አባ ብሶይ ኮከበ ገዳም፤
ዘደብረ አባ መቃርስ ወዘኲሉ ዓለም!
ቸሩ መድኀኔ ዓለም ከበረከታቸው ይክፈለን!
††† ✝እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን ወከዋክብተ ገዳም አቡነ ኪሮስ: አባ ብሶይ እና አባ ሚሳኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝ †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝አቡነ ኪሮስ ጻድቅ✝ †††
††† የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል::
#አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ::
እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል::
ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::
ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::
ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ::
#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም::
†††✝ የበርሃው ኮከብ አባ ብሶይ✝ †††
††† ታላቁ አባ ብሶይ (ቢሾይ):-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ
¤በመላእክት መሪነት የመነኑ
¤የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ባልንጀራ
¤የአባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር የነበሩ
¤በአጭር ጊዜ የብዙዎች አባት የሆኑ ሰው ናቸው::
††† እንቅልፍን የማያውቁ
¤በ40 ቀን ብቻ እህል የሚቀምሱ
¤የጌታችንን እግር በየቀኑ እያጠቡ የሚመገቡ
¤ፈጣሪያቸውን በጀርባቸው ያዘሉ (ነዳይ መስሎ አግኝተውት)
¤በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጉ
¤በርካታ ጻድቃንን የወለዱ ታላቅ የፍቅር ሰው ናቸው::
በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሰርተው: #ቤተ_ክርሰቲያንን በንጽሕናቸው አስደስተው: ሐምሌ 8 ቀን ዐርፈዋል:: ግብፅ ውስጥ የሚገኘው ገዳማቸው ዛሬም ቤተ አበው: ተአምራት የማይለዩትና ተወዳጅ ነው:: ቦታው #መካነ_ሱባዔ_ወመንክራት ነውና::
††† ✝አባ ሚሳኤል ነዳይ✝ †††
††† መቼም ያ ዘመን (4ኛውና 5ኛው ክ/ዘመን) እጅግ የተባረከ ነው:: ቅዱሳኑ በብዛት የባለጸጐችና የነገሥታት ልጆች ናቸው:: አባ ሚሳኤልም የኬልቄዶን ንጉሥ ልጅ ሳሉ መንነው በበርሃ ለ65 ዓመታት ተጋድለዋል:: በመጨረሻ ግን በደዌ ምክንያት ወደቁ:: ለ5 ዓመታት መነኮሳቱ ሲጠይቁዋቸው ቆይተው ሰለቹ::
ከዛም ለ15 ዓመታት ላበታቸው በግንባራቸው እየተቀዳ: ያለ ምንም ምግብ እያቃሰቱ በበዓታቸው ወድቀው ኑረዋል:: ቸሩ አምላክ ግን 4ቱን ሊቃነ መላእክት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል: #ሩፋኤልና #ሳቁኤልን) አዞላቸው ሲጠብቁዋቸው ኑረዋል::
በዚህች ቀንም #አቡነ_ኪሮስ መጥተው አጽናንተው: ጌታችንንም ጠርተው እንዲያርፉ አድርገዋል:: መላእክት እያጠኑና እየዘመሩ ጻድቁ ቀብረዋቸዋል:: በመቃብራቸውም ላይ ፈውስ የሆነ ጸበል ፈልቁዋል::
††† እግዚአብሔር የእኛን ያይደለ የጻድቃኑን ቅድስና አስቦ ይራራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ሐምሌ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ኪሮስ ጻድቅ (አረጋዊና ገዳማዊ)
2.አባ ብሶይ ጻድቅ (ኮከበ ገዳም)
3.አባ ሚሳኤል ነዳይ (ጻድቅ)
4.አባ ቢማ ሰማዕት
5.አባ በላኒ ሰማዕት
6.ቅዱሳን አቤሮንና አቶም (ሰማዕታት)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
4.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
††† "በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው::" †††
(ምሳ. 10:7)
††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28-31)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ሰላም ቻናሉን ሰብስክራይብ ለማድረግ 200 ኢቲቢ አግኝቻለሁ፣ ሂዱና ሰብስክራይብ ለማድረግም ገንዘብ ያግኙ! ለሰጠህው አትኩሮት እናመሰግናለን! 👇
Читать полностью…ጥያቄ
1 የእስክንድርያ ሊቀ ዻዻስ ሲሆን ስለ❤️እመቤታችን❤️ ሲናገር፡-
ከማይመረመር ልደቱ በኋላ ማነህተመ ደንግልናዋ
አልተለወጠም ስለዚህ ወላዲተ ኣምላክ እንደሆነች አመንን ህፃን ሆኖ ተወለደ በጨርቅም ተጠቀለለ በጎል ተጣለ።
ይህን ጊዜ ተገኘ የማይባል ከአብ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር የነበረ ያለ ለዘለዓለም እርሱ ዘመን ተቆጠረለት፣ ጊዜ ተነገረለት እርሱ አንድ ወልድ ሲሆን በየጥቂቱ አደገ ።
ሀ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለ አባ መቃርስ
ሐ ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም
መ ቅዱስ ቄርሎስ
=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+
=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+
=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::
+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::
+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )
+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+
=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::
+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::
+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)
+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር
+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::
=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
††† ✝እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝†††
†††✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝†††
††† ✝ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ ✝†††
††† ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው::
ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው::
ስሙ የግብር (በሥራ የሚገኝ) ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው::
ቅዱስ መርቄሎስ በ60ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው::
በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ::
ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል::
ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?"
ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል::
†††✝ ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ✝ †††
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመት አካባቢ የነበረ
¤እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ
¤ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት
¤በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ
¤ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት
¤ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት
¤መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና
¤በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው::
††† ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል::
††† እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን::
††† ሐምሌ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት
5.ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
††† "እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
👉"ውበትን ደስታ አታድርጉትየረገፈና የታመመ፣ የቆሰለ ዕለት ታዝናላችሁ፣
👉ሀብታችሁን ደስታ አታድርጉት ሲቀሟችሁ ታዝናላችሁ፣
👉 ዘመድን የደስታ ምንጭ አታድርጉ ሲታመም፣ ሲሞት ትጎዳላችሁ
👉 ባልንጀራችሁን የደስታምንጭ አታድርጉ ሲለያችሁ፣ ሲከዳችሁታዝናላችሁ፣
👉ጉልበታችሁን የደስታ ምንጭ አታድርጉት፣ ስትደክሙ፣ ስትታመሙ ሁሉም ይቀራል የደስታምንጭ ክርስቶስ ነው"
👉 በክርስቶስ ደስ ይበላችሁ፡፡
አባታችን አባ ገብረ ኪዳን❤️
ረድኤት በረከታቸው ይደርብንና ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዛሬዋ በዕረፍታቸው ዕለት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- ቅዱስ ጳውሎስ ኔሮን የሞት ፍርድ ፈርዶበት ሳለ ሊሰይፉት ሲወስዱት የኔሮን ወገን አንዲት ብላቴና ቅዱስ ጳውሎስን አገኘችው፡፡ በጌታችንም አመነች፡፡ ስለ ጳውሎስም አለቀሰች፡፡ እርሱ ግን ‹‹መጎናጸፊያሽን ስጪኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ›› አላትና ሰጠችው፡፡ ራሱ ወደሚቆረጥበት ቦታም ሄዶ ለሚሰይፈው ወታደር ራሱን አዘንብሎ ካዘጋጀለት በኋላ ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፈነው፡፡ ሰያፊውም የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፊያ እንደተሸፈነ ጣለው፡፡ ሰያፊውም ለንጉሡ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችውና ‹‹ያ ጳውሎስ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ ወታደሩም ‹‹ራስ የሚቆረጥበት ቦታ ወድቋል፣ ራሱም በመጎናጸፊያሽ ተሸፍኗል›› በማለት ያደረገውንና የሆነውን ነገር ነገራት፡፡ እርሷም መልሳ ‹‹ዋሽተሃል፣ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በዚህ ዘንድ አልፈው ሄዱ፤ እነርሱ የመንግሥት ልብሶችን ለብሰዋል፤ በራሳቸውም ላይ በዕንቁ የተጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፤ መጎናጸፊያዬንም ሰጡኝ፤ እነኋት ተመልከት›› ብላ አሳየችው፡፡ ለሰያፊውና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ወታደሮች ሁሉ አሳየቻቸው፡፡ አይተውም እጅግ አድንቀው ‹‹በጴጥሮስና በጳውሎስ አምላክ አምነናል›› እያሉ ስለ ጌታችን መስክረው እነርሱም ሰማዕት ሆኑ፡፡
ልዩ ስሙ አዲቃሾ በሚባለው ቦታ የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ይገኛል፡፡
የከበሩ ሐዋርያት የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ:-ከገድላት አንደበት፤መዝገበ ቅዱሳን ሁለተኛ እትም ገፅ 527
✝✝††† እንኳን ለዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† ✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝✝†††
††† ✝✝ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ✝✝ †††
††† ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " #ዓምደ_ሃይማኖት- የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ #አባ_ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: #መንፈስ_ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ #ቤተ_ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንንየአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)
ነገሩን #ቅዱስ_ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም #በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 #ቅዱሳን_ሊቃውንት ተገኙ::
የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት #ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: #ድንግል_ማርያምም #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::
††† ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም " #ታኦዶኮስ(የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን:-
¤የአምላክ እናት:
¤ዘላለማዊት ድንግል:
¤ፍጽምት:
¤ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::
ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ444 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
††† ሐምሌ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)
2.ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ (ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
3.አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
††† "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና::" †††
(ዕብ. 13:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
እንደ ለመነውም አደረገለት የሃይማኖትንም ሕግ አስተምሮ የክርስትናን ጥምቀትም አጠመቀው ሥጋውንና ደሙንም አቀበለው ሁሉንም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከዚህ በኋላ ከዚያ ወጣ በሰላምም ሸኙት በብዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ ከአይሁድና ከአረማውያንም መከራ ደረሰበት። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)
" እኔ ሞቆኝ ወገን ሲበርደው አላይም "
ሀገራችን ከባድ ፈተና ገጥሟታል። ዜጎቿ ቤትና ንብረታቸውን በትነው ቅያቸውን ለቀው ተፈናቅለዋል። አርሶ ያበላው ገበሬ እጅ አጥሮታል። በሀገሩ እንግዳ ተቀባይ የነበረው ያ ደጉ ባላገር ዛሬ የእኛን የወገኖቹን ድጋፍ ፈልጓል።
ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሀን መጠለያ ላሉ ወገኖቻችን አልባሳትን ከሀምሌ 2 - ሀምሌ 12 ድረስ በፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አልባሳትን ስለምናሰባስብ ድጋፋችሁ አይለየን ።
➾ አስተባባሪ ማኅበረ ኤዶምያስ በጎ አድራጎት ማኅበር
ለበለጠ መረጃ
0967722490
0904198419
እግዚአብሔር አምላክ
ክፋት ፡ የሌለበት ፡ ቸር :
በቀል የሌለበት ፡ የዋህ ፡
ቍጣ ፡ የሌለበት ትዕግሥተኛ
ኃጢአት የሌ ለበት ፡ ጻድቅ ፡
እድፍ ፡ የሌለበት ፡ ንጹሕ ፤
ጠማምነት የሌለበት ፡ ቅን ነው ።
ያለ መከልከል ሰጪ
ያለመንፈግ ለጋስ፣
ያለ ቂምና፡ ያለ ፡ ቅናት ፡ ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ነው ።
ለሚጠሩት ፡ ሰዎች ፡ የቀረበ ፡ ነው ፣
ለሚፈሩትም ፡በጎውን ፡ ነገር ፡ የሚያደርግ ፡ ነው
ለሚመቱትሰዎች ፡ የተከፈተ ፡ በር ፡ ነው ፡
ያለ ፡ መሰናክል ፡ጥርጊያ ፡ ጐዳና ፤
እሾህ ፡ የሌለበት ፡ ንጹሕ ፍለጋ : ነው ::
የአማልክት ፡ አምላክ ፤ የአጋዕዝት ፡ ጌታ ፡
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ።
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ❤️
Share 👉 @uraman4u13
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
እንኳን ለሠኔ 30 የመጥምቁ ዮሐንስ ልደት አደረሳችሁ
መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ስላቀረበው ስግደት ያዕቆብ ዘሥሩግ ያቀረበው ቅኔያዊ ውዳሴ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ የእነዚኽ ዘመዳሞች (የኤልሳቤጥና የእመቤታችንን) መልካም ገጠመኝ አኹንም ያስደንቀኛል፤ ውበቱን እገልጥ ዘንድም አንድ ዐሳብ ይጎነትለኛል፤ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) እና አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) አንድ አስደናቂ ታሪክ አስተምረውኛል፤ እየተደነቅኊ ስለ ርሱ እናገር ዘንድም ፍቅር ይወተውተኛል፡፡
❖ ድንግሊቱ በፍቅርዋ መካኒቱም በደስታዋ፤ ስለ ኹለታቸውም እሰብክ ዘንድ ፈልገውብኛል፤ ርስ በርስ የተያዩት አጽናፋት በተከሥቷቸው እንደሚተያዩት ነበር፣ የየራሳቸው የጊዜ ኹኔታ ቁልጭ ብሎ እንደሚታይባቸው እንደ ምሥራቅ እና እንደ ምዕራብ ናቸው፡፡
❖ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ምሽት የሚታይበትን፤ በዕድሜው ብዛት (በርጅናው) ብርሃንን የሚሸፍነውንና የሚቀብረውን አጽናፍ ትመስላለች ብላቴናዪቱም (እመቤታችን) ቀኑን በዕቅፏ ተሸክማ ወደ ምድር የምታመጣውንና፤ የንጋት እናት የኾነችውን ምሥራቅን ትመስላለች።
📖ሕዝ 44፥2
📖ዮሐ 5፥35
❖ በወጣትነት እና በእርጅና ጊዜ የመደነቅ ስሜት ይበዛ ዘንድ ንጋት እና ምሽት የሚተያዩት በፍቅር ነው፤ ታላቁን የጽድቅ ፀሓይ (ጌታን) የምትሸከመው ንጋት (እመቤታችን)፣ እና ብርሃንን (ጌታን) የሚያበሥረው ኮከብ (ዮሐንስ) የሚወጣባት ምሽት፡፡፡
📖ሚልክ 4፥2
❖ ታላቁ ንጉሥ በብላቴናዪቱ (በእመቤታችን) ዐድሮ ዘውዶችን ያበጃል፣ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) መንግሥቱን የሚያውጀውን አገልጋይ ትሸከማለች፤ በድንግልና የፍጥረታት ጌታ ይከበራል፤ በመካንነት የሌዋውያን (ወንድ) ልጅ ከፍ ይደረጋል፡፡
❖ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) አዳምን የፈጠረው ቀዳማዊዉን ሕፃን ትሸከማለች፤ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ዛሬ በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ሕፃን ትሸከማለች፤ የይሁዳ ብላቴና ውስጥ ያዕቆብ ስለ ርሱ የጻፈው ያ የአንበሳ ደቦል አለ፤ በሌዋዊቱ ውስጥ ደግሞ ጥምቀትን የመሠረታት ካህን።
📖ሉቃ 3፥3
📖ሉቃ 1፥24-28
📖ዘፍ 49፥9
❖ ከአረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ጋር ስለዚኽ ዐዲስ ፅንስ ሐሤት ታደርግ ዘንድ፤ ድንግል በቅድስና ልቃ እና ተመልታ መጣች፤ በረከትን (ጸጋን) የተመላችው (እመቤታችን) እና የሌዋውያን ሴት ልጅ የኾነችው (ኤልሳቤጥ)፤ እንዲኹም ምድር በመላ የበለጸገበት የከበረ ሀብት የመሉባቸው ኹለቱ ጀልባዎች ርስ በርስ ተገናኙ (ተያዩ) ኹለት ወላዶች አንደኛዋ ተበሣሪና አንደኛዋ አብሣሪ ኾና፣ የዚያኑ የአንዱን (ተመሳሳዩን) ለዓለም ኹሉ የኾነ የመዳን መልእክት ይዛ፡፡
📖ሉቃ 1፥39
❖ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) ጐበኘቻት፣ እና አንጸባራቂ በኾነ ሰላምታ ተናገረቻት፤ ወዲያውም በርሷ (በኤልሳቤጥ) ውስጥ ተሸፍኖ ያለው ሕፃን አውቆ በደስታ መዝለል ዠመረ፤ ማርያም ሰላምን መናገርዋ ያማረ ነበረ፣ በቅርብ እና በሩቅ ላሉት ሰላምን ዘርታለችና ርሷ ለሰው ዘር በሙሉ የኾነ ሰላም እንደመላበት ክቡር ስጦታ ነበረች፣ በጠላትነት ለነበሩት የሚኾን ታላቅ ሰላም (ወሀቤ ሰላም ጌታ) በርሷ ውስጥ ተሰውሮ ነበርና፡፡
📖ሉቃ 1፥41
❖ ርሷ ራሷ ከላይ ሰላምን እንደተቀበለች፣ እንዲኹ ደግሞ ለዓለም ኹሉ ሰላምን ሰጠች፤ በርሷ አፍ ሰላም በብዛት ተትረፍርፎ ይነገር ነበር፣ ይኽች ቡርክት የኾነች እንዲኽ ሰላምን ታውጅ ዘንድ የተገባት ነበር፡፡ ሰላም በውስጧ (በማሕፀኗ) ነበረና በከንፈሯ ሰላምን ሰጠች፣ ይኽነን የሰማው ሕፃንም በደስታ ይፈነድቅ ዠመር
📖ሉቃ 2፥14
📖ሉቃ 1፥41
❖ ገና ሳያየው በፊት ያውቀው እንደነበር በማሳየቱ፣ ሲያየውና “ይኽ ርሱ ነው” ብሎ ሲናገር ነገሩን የሚጠራጠረው አይኖርም ገና ሳይወለድ ርሱን (ጌታን) ለዓለም አስተዋወቀው፣ ከተወለደ በኋላ ርሱን ሲያውጀው ማንም ከምስክርነቱ እንዳይሸሽ፤ በተፈጥሮ ላይ ጌታ የኾነው በብላቴናዪቱ ማደሩ ይገለጥ ዘንድ፣ ተፈጥሮን በማሸነፍ ከተፈጥሮ ውጪ (ዮሐንስ) ስለ ወልድ መሰከረ፡፡
📖ዮሐ 1፥29-30
❖ ስለ ወልድ የኾኑት ነገሮች ኹሉ ለመግለጽ እጅግ ከባድ ናቸው፣ በእምነት ዦሮ ካልኾነም በቀር አይሰሙም፤ እነዚኽ ነገሮች ኹሉ ዐዲስ ነበሩና ሰው አልተረዳቸውም ነበር፤ ፍቅር ባለው ሰው በአድናቆት ካልኾነ በቀርም አይታዩም፤ ለማርያም አድናቆት ለኤልሳቤጥም ታላቅ ሙገሳ ይገባል፣ ማስተዋል ለሚችል ሰው በኹለቱም ውስጥ ዐዳዲስ መገለጦች አሉባቸውና፡፡
❖ ስለኹለቱም ለመናገር ቃላት በቂዎች አይደሉም፣ አንደበትም (ንግግርም) ዝም ይላል፤ ከአድናቆት የተነሣ ዝምታ ንግግርን ይውጠዋል፤ ቃላት ስለማንኛዪቱ ለመናገር ይበቃሉ?፣ እነሆ ኹለቱም ከንግግር (ከአንደበት ገለጻ) በላይ ናቸውና፤ ማርያምን በቀረብናት ጊዜ አንደበት በዝምታ ይዘጋል፣ ምክንያቱም የድንግልናን ማስረገጫዎች (ምልክቶች) በርሱም ያደረውን ሕፃን ይመለከታልና፤ ወደ ኤልሳቤጥም ስንመጣ ትንታኔ ይከዳናል፣ ከርሷ ማሕፀን ውስጥ አስደናቂውን ብሥራት ይሰማልና፡፡
❖ ድንግሊቱ ፀንሳለችና እነሆ የመካኒቱም ልጅ በደስታ ይዘልላል፤ ስለ ታላላቆቹ ሕፃናት ዕጥፍ ድርብ መደነቅ ይይዘናል፤ ኧረ በማንኛቸው እንደመም (እንደነቅ)? አንደኛዪቱ (እመቤታችን) ያላገባች ኾና ሳለች ወንድ ሳያውቃት ፍሬ በውስጧ አለ፤ በሌላኛዪቱም (በኤልሳቤጥ) ማሕፀን ውስጥ ገና ያልተወለደ ሕፃን በደስታ ይዘልላል፡፡
❖ ማንኛዪቱን እናድንቅ ልጅዋ የምሥራች ነጋሪ የኾነውን በዕድሜ የገፋችውን ሴትን፣ ወይንስ ድንግል ኾና ግን ደግሞ ሕፃን በውስጧ የተሸከመችዪቱን ብላቴና? ይኽችኛዪቱ (እመቤታችን) ወንድን ፈጽማ አታውቅም ግን ደግሞ ማሕፀኗ ሙሉ ነው፤ ያቺኛዪቱም (ኤልሳቤጥ) ልጇ ገና ሳይወለድ በፊት መንገድ ያዘጋጃል፤ ያለጋብቻ ውሕደት የኾነችው ርሷ (እመቤታችን) ከንፁሕ ፅንሷ የተነሣ እጅግ ታስደንቃለች፣ ያልወለደችዪቱም (ኤልሳቤጥ) ደግሞ ልጇ ብሥራትን ለማብሠር ይላወሳል (ይዘላል)፡፡
📖ሉቃ 1፥44
📖ማቴ 1፥18
በእናቱ ማሕፀን በደስታ የዘለለው የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን
📌ምንጭ
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
📚የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናና ወላዲተ አምላክነት በቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ድርሳን በሚል ርዕስ ካሳተምኩት መጽሐፍ በጥቂቱ ከገጽ 96-97 የተወሰደ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
ረድኤት በረከቱ ትደርብንና በዚኽች ዕለት ሰኔ 30 በዓመታዊ የልደት በዓሉ ታስቦ የሚውል የእግዚአብሔርን መንገድ የሚያዘጋጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገው ተዐምር ይኽ ነው ።
በምድረ ኢትዮጵያ እንዲህ ኾነ፡፡ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት የምትታመን አንዲት ሴት ነበረች። ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ደብር እየሔደችም በጽኑ ልቡና በመማፀን ትለምነው ነበር ፡፡ ለዚኽች ሴትም ብዙ ልጆች ነበሯት ፡፡ ከልጆቿም አንዲቷ በሽተኛ ነበረች ። ቀንና ሌሊት ደም ይፈሳት ነበረና ከሰው መሐል መዋል መቆም መቀመጥም አትችልም ነበር ።
ይኽች የታመመች ልጅ እናት ግን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ እየተመላለሰች ዘወትር ወዳጄ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ይኽን ኀዘኔንና ልመናዬን አትሰማኝምን ይኽችን ልጅ ማርልኝ ። እንደሊሎች ልጆቼ ትኾን ዘንድም ይኽን በሽታና ጭንቀት ከእርሷ አስወግድልኝ እያለች በመጥምቅ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል ሥር ትማፀን ነበር ፡፡
ይኽቺም ሴት አንድ ቀን በብዙ እንባ ስትማፀን ስሙ ገብረ እግዚአብሔር የተባለ አንድ ካህን አንቺ የተከበርሽ እኀቴ ሆይ እንዲህ የሚያስለቅስሽ ምንድር ነው በጥቡዕ ልብ ወደእርሱ ለሚማፀኑት ኹሉ የሚረዳቸው ቅዱስ ዮሐንስን የምትለምኚውስ ምንድር ነው አላት፡፡ ያቺ ሴትም ልጁ ደም እየፈሰሳት ታማብኛለች ይፈውሳት ዘንድ እለምነዋለሁ አለችው።
ያንጊዜም ያ ካህን ልጇን ታመጣት ዘንድ ነገራት ፡፡ ልጇንም ከእኅቶቿ ጋራ ወደመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደብር አመጣቻት ፡፡ ካህኑም ከነቢዩ ዳዊት መዝሙር በሽተኛነኝና አጥንቶቼም ታውከዋል ፡፡ አቤቱ ይቅር ብለህ ፈውሰኝ የሚለውንና ሌሎችንም ቃላተ መዝሙር ከወንጌልና ከመልእክታት ጸሎተ ኪዳንንም ይጸልይ ጀመር ፡፡
ያ ካህንም በውኃው ላይ ኀቡእ የእግዚአብሔርን አዳኝ ስም ጠርቶ ጸሎቱን ከጨረሰ በኋላ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ፀበል ጨምሮ የታመመችውን ልጅ አጠመቃት ። ይኽቺ ልጅም ከሚፈስ ደሟ ፈጥና ተፈወሰች። ቅዱስ ዮሐንስን የምትታመን እናቷም እልል ብላ እግዚአብሔርን አመሰገነች ፡፡ ፈጥኖ የደረሰላትን የቅዱስ ዮሐንስን አማላጅነትም አደነቀች።
የነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
(ምንጭ ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተአምር ዘሰኔ)
22ቱ ፍጥረታት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው። እሑድ ሰባት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። አንዳንድ ሰዎች ስምንት ይላሉ። ነገር ግን መጽሐፈ ኩፋሌ ሰባት ብሎ በማያሻማ ቃል ስለነገረን ስምንት የሚለው ተቀባይነት የለውም።
፩) ሰባቱ ሰማያት
፪) እሳት
፫) መሬት
፬) ነፋስ
፭) ውሃ
፮) ቅዱሳን መላእክት
፯) ጨለማ
፰) ጠፈር
፱) በእጅ የሚለቀሙ ጥቃቅን ዕፀዋት
፲) በማጭድ የሚታጨዱ መካከለኛ ዕፀዋት
፲፩) በምሳር የሚቆረጡ ታላላቅ ዕፀዋት
፲፪) የገነት ዕፀዋት
፲፫) ፀሐይ
፲፬) ጨረቃ
፲፭) ከዋክብት
፲፮) ከውሃ የተፈጠሩ በክንፋቸው የሚበሩ
፲፯) ከውሃ የተፈጠሩ በእግራቸው የሚሽከረከሩ
፲፰) ከውሃ የተፈጠሩ በሆዳቸው የሚሳቡ
፲፱) ከየብስ የተፈጠሩ በክንፋቸው የሚበሩ
፳) ከየብስ የተፈጠሩ በእግራቸው የሚሽከረከሩ
፳፩) ከየብስ የተፈጠሩ በሆዳቸው የሚሳቡ
፳፪) ሰው
ናቸው። ማክሰኞ አራት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። እሑድ ሰባት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። ሰኞ አንድ ፍጥረት ተፈጥሯል። ረቡዕ ሦስት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። ኃሙስ ሦስት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። ዓርብ አራት ፍጥረታት ተፈጥረዋል። በጠቅላላው 22ቱ ፍጥረታት የሚባሉት እነዚህ ናቸው። አንዳንዶች ብርሃንን እንደ አንድ ፍጥረት ይናገሩታል። ነገር ግን ብርሃን በእሳት ይቆጠራል። ብርሃን፣ ሙቀት የእሳት ግብረ ባሕርይዎች ናቸው እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ፍጥረታት አይደሉም። ወይቤ እግዚአብሔር ለይኩን ብርሃን ሲል እንኳ ይገለጥ ማለት እንጂ ግብር እም ግብር የተፈጠረ መሆኑን የሚገልጥ አይደለም። የእሑድ ፍጥረታት እምኀበ አልቦ ኀበቦ ተፈጥረዋል። ከእሑድ በኋላ ያሉት ደግሞ ግብር እም ግብር ተፈጥረዋል።
© በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናሌ:-
በትረማርያም አበባው
/channel/betremariyamabebaw ነው
።
የዩቲይብ ቻናሌ:-
ንሕነ ዘክርስቶስ
እምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም ፤ መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም ፤ እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም ፤ አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም።
እንኳን ለሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ !
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ
👑🌿#ሐምሌ7,
❤️አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ የአብርሃምን ቤት የባረኩበት ታላቅ እለት ነውና እንኳን አደረሰን|አደረሳችሁ!!! የእኛንም ቤት ይባርኩልን🙏🍇🙏
🌺 🌿 እኛን ማን ፈጠረን ??? 🌺 🌿
🌲🌱. ቅድስት ሥላሴ ሲሆኑ "ሥላሴ" ማለት ሠለሰ (ሦስት) አደረገ ከሚለው ግስ የወጣ ነው ፍቺም ሶስትነት ማለት ነው🙏
🌿 ቅድስት ሥላሴ ስንት ናቸው???
🌲🌱. አንድም ሶስት ናቸው!!!
📌. አንድነታቸው :- በህልውና ፣ በአገዛዝ ፣ በስልጣን፣ በመለኮት ፣ ዓለምን በመፍጠር አንድ ናቸው!!! (ዘፍ 1:1)
🌱 " እኔ ና አብ አንድ ነን "🌱 (ዮሐ 10:30)
📌. ሦስትነታቸው :- በስም ፣ በአካል ፣ በግብር ሶስት ናቸው
❣️በስም :- አብ ፣ ወልድ ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው
🌿 በአካል:- አብም ፣ ወልድም ፣ መንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አላቸው🙏❣️🙏
❣️ በግብር➡️የአብ ግብሩ መውለድ, መስረጽ ነው!!!
➡️የወልድ ግብሩ መወለድ ነው!!!
➡️የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው!!!
( መዝ 2:7)
🌱" ምስክር የሚሆኑ ሦስት ናቸውና እነርሱም መንፈስ ፣ ውሃና ደም ናቸውና ሦስቱም አንድ ናቸው" 🌱(1ዮሐ 5:8)
🌱" ሂዱና በአብ፣ በወልድ ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው" 🌱 ብሎ ለደቀመዛሙርቶቹ ነገራቸው
( ማቴ 28:19, ምሳ 30:4 )
🌱" መጀመሪያ ቃል ነበር፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ " 🌱 (ዮሐ1:1)
🍒 " እግዚአብሔር " ማለት እኮ ሚስጥረ ሥላሴን ይገልጻል!!! " ቃል" እግዚአብሔር ወልድ ነው!!!
➡️እግዚእ - ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ
➡️ አብ - ማለት አባት
➡️ ሔር - ማለት ጠባቂ ፣ ቸር፣ ሩህሩህ ነው
( መንፈስ ቅዱስ)
✝️🌿 ቅድስት ሥላሴ ህይወታችንን፣ ሀገራችንን፣ ሃይማኖታችንን ይጠብቁልን, በረከታቸው አይለየን
1 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዘሩ ከዕብራውያን፣ ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በ __ ከተማ ነው፡፡
ሀ በጠርሴስ
ለ በአንጾኪያ
ሐ በእየሩሳሌም
መ በሮም
2 ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው
ሁለት ችግር ምን ነበር?
3 የቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ
ሀ ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ ቅዱስ ጳውሎስ
ሐ ቅዱስ ማትያስ
መ ቅዱስ በርናባስ
4 "በእስጢፋኖስ ጸሎት ቤተ ክርስቲያን የጠፋውን ጳውሎስን አገኘች፡፡"በማለት ተናግሯል።
ሀ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለ ቅዱስ እንድርያስ
ሐ ቅዱስ ኤፍሬም
መ ቅዱስ አውግስጢኖስ
5 የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት _____ነበረ?
U ዕብራዊ
ለ ሮማዊ
ሐ ፅራዊ
መ ብንያሚ
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞
❖ ሐምሌ ፭ ❖
✞✞✞✝ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝
=>ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን
ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን
ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::
+" ✝ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት✝ "+
=>የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን
ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ
ማለት ነው::
¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ
አድጐ
¤ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን
የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ:
በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል::
ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: (ማቴ. 16:17, ዮሐ.
21:15)
+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው
ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ
እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ
ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት
አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን
ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::
+በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ
ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል::
እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር
ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው
ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::
+ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ም
የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው::
"እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም"
አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ
እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ
ነበር::
✝=>#የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:-✝
1.ሊቀ ሐዋርያት
2.ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ)
3.መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
4.ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት)
5.አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)
+"+✝ #ቅዱስ_ዻውሎስ_ሐዋርያ ✝+"+
=>የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን
ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን?
¤ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ
ሰው ነው?
¤የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን
እጽፈዋለሁ?
¤ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን
መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::
+#ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል
የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ
ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት
ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ
ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ::
ጨው ሆኖ አጣፈጠ::
+ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን
(የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል
ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ:
በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ::
በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ25 ዓመታት
ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::
+እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ:
በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል::
ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ
አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው
ማለት ነው::
=✝>የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች:-✝
1.ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2.#ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3.#ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4.#ብርሃነ_ዓለም
5.#ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6.#የአሕዛብ_መምሕር
7.#መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8.#አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9.#ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10.#መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11.#መርስ (ወደብ)
12.#ዛኅን (ጸጥታ)
13.#ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14.#ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .
=>ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን::
ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ሐምሌ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ)
4.ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)
6.ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
7.ቅዱሳት አንስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና
አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
4.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
=>+"+ ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "የዮና
ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና
ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም
እልሃለሁ:: አንተ #ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ
ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም
አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች
እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ
ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ
ይሆናል::" +"+ (ማቴ. 16:17)
=>+"+ በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት
ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን
ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን
ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል::
ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ
ያስረክባል:: +"+ (2ጢሞ. 4:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኳን ለአባቶቻችን ቅዱሳን 12ቱ ደቂቀ ነቢያት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
✞✞✞ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት ✞✞✞
=>ነቢይ ማለት ከእግዚብሔር ተመርጦ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን): መጻዕያትን (ለወደፊቱ የሚደረገውን) የሚያውቁ ሰዎች ሲሆኑ ሕዝቡን እንዲመሩ: እንዲገስጹም ይላካሉ:: ሕይወታቸውም በቅድስና የተለበጠ ነው:: ነቢያትን በቁጥር መግለጽ ከባድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን እንድንረዳቸው እንዲህ ትከፍላቸዋለች::
=>በኩረ ነቢያት_አዳም
=>ሊቀ ነቢያት_ሙሴ
=>ርዕሰ ነቢያት_ኤልያስ
=>ልበ አምላክ_ዳዊት
=>15ቱ ነቢያት (ከአዳም ጀምሮ እስከ ሳሙኤል)
=>4ቱ ዐበይት ነቢያት (ኢሳይያስ: ኤርምያስ: ሕዝቅኤልና ዳንኤል)
=>12ቱ ደቂቀ ነቢያት ደግሞ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ያሉት ናቸው::
+በዚህች ቀን ታዲያ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት በአንድነት ይታሠባሉ:: እነዚህም:-
1.ቅዱስ ሆሴዕ (ኦዝያ)
2.ቅዱስ አሞጽ
3.ቅዱስ ሚክያስ
4.ቅዱስ ኢዩኤል
5.ቅዱስ አብድዩ
6.ቅዱስ ዮናስ
7.ቅዱስ ናሆም
8.ቅዱስ እንባቆም
9.ቅዱስ ሶፎንያስ
10.ቅዱስ ሐጌ
11.ቅዱስ ዘካርያስ እና
12.ቅዱስ ሚልክያስ ናቸው::
+ቅዱሳኑ ደቂቀ ነቢያት የተባሉት
1.የነቢያት ልጆች በመሆናቸው
2.የጻፏቸው ሐረገ ትንቢቶች በንጽጽር ከዐበይቱ (ከነኢሳይያስ) ስለሚያንስ ነው::
+በምግባር: በትሩፋት: በአገልግሎት ግን ያው ናቸው:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እሊህን ነቢያት "እለ አውኀዙ ተነብዮ በእንተ ስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ" ይሏቸዋል:: ( ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መውረድ: መወለድና የማዳን ሥራ የትንቢት ጐርፍን ያፈሰሱ እንደ ማለት ነው :: )
+ቅዱሳኑ ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ባሻገር ዓለማችን ላይ ከነበሩበት ዘመን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሊደረጉ ያላቸውን ነገሮችም ተናግረዋል:: የነበሩበት ዘመን በአማካኝ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ከ900 እስከ 500 ነው:: በትንቢት ደረጃም እንደነ ሆሴዕና ዘካርያስ 14 ምዕራፎችን: እንደነ አብድዩም አንዲት ምዕራፍ ብቻም የጻፉ አሉ::
+በሕይወታቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያሻቸው ናቸውና በየጊዜው ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገሩ የእርሱን ድምጽ ለእሥራኤል (አንዳንዴም ለአሕዛብ) ያደርሱ ነበር:: ፊት አይተው የማያዳሉ ናቸውና ሕዝቡንም ሆነ ነገሥታቱን ስለ ኃጢአታቸው ይገሰጹ ነበር:: በዚህም ምክንያት ከነገሥታቱና ከሕዝቡ አለቆች መከራ ደርሶባቸዋል:: አልፎም ያለ አበሳቸው ሕዝቡ በኃጢአቱ ሲማረክ አብረውት ወርደዋል::
+በመጨረሻ ሕይወታቸውም አንዳንዶቹን ክፉዎች ሲገድሏቸው አንዳንዶቹ ደግሞ በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል:: ዛሬ ነቢያት ከእነርሱ ባሕርይ በተገኘችና ብዙ ትንቢትን በተናገሩላት በእመቤታችን ምክንያት ክርስቶስ ድኅነትን ፈጽሞላቸው በተድላ ገነት ይኖራሉ:: ስለ እኛም ይማልዳሉ::
=>" ናጥሪ እንከ ትሕትና ዘምስለ ንጽሕና"
(እንግዲህ እንደ ነቢያት ትሕትናን ከንጽሕና ጋር ገንዘብ እናድርግ)
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ"
(ነቢያት መንፈስን ንጹሕ በማድረግ እግዚአብሔርን አይተውታልና: ፊት ለፊትም ተያይተዋልና)
/ቅዳሴ ማርያም/
=>ከአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት በረከት ይክፈለን::
=>ሐምሌ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1."12ቱ" ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት
2.ቅዱስ ሶፎንያስ ነቢይ (ዕረፍቱ)
3.ቅዱሳን ሰማዕታት አቡቂርና ዮሐንስ (ቅዳሴ ቤታቸው)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ /ወንጌላዊው/
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ /ሰማዕት/
=>+"+ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት:: በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በሁዋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሠከረ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር:: +"+ (1ዼጥ. 1:10)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
✝ቀዳማይ ምኒልክ✝
✝ የቅዱስ ሰሎሞን እና የንግስት ሳባ ልጅ።
✝ የቅዱስ ዳዊት የልጅ ልጅ።
✝ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት ታቦተ ጽዮንን ወደ ኢትዮጵያ ያመጣ።
✝አምልኮተ እግዚአብሔርን ያስፋፋ።
✝ሥርዓተ ኦሪትን ያመጣልን ደግ ሰው።
ሐምሌ 3 ዕረፍቱ ይከበራል።
ከበረከቱ ይክፈለን።
#ሐምሌ_2
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሁለት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላያቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚአምር ጐልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን አሉት።
እርሱም ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ አላቸው እነርሱም እንዳልክ አሉት። ያ ሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኅፍረት ነው ያ ሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና አለ። ይህንንም ብሎ ተነሥቶ እርፉን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበረና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችንም አረሰ።
የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን አላቸው እነርሱም እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን። ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት።
እኛም ወደዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውስጧ ለመኖር እንሻለን አሉት። ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት።
ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው አሉት እርሱም ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻችሁ ታይዋቸዋላችሁ አላቸው።
ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ አሉ። እኩሌቶቹም ልንገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማው መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም አሉ።
እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ታዴዎስም በአያት ጊዜ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ላክልን አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ስዎችም አዮዋት ያቺ ሴትም ከከተማዋ መኳንንቶች አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና ።
ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ስደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለችውን ሴት አወረዳት።
ከዚህ በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ ዕውሮች አዩ ሐንካሶችም በትክክል ሔዱ ዲዳዎች ተናገሩ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ አጋንንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን እስኪያምኑ ሙታን ተነሡ።
ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልብ አድሮም በሐዋርያው ታዴዎስ ላይ አነሣሣው ወደርሱም መጥቶ ሰገደለትና እንዲህ አለው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው አትግደል አትስረቅ አታመንዝር በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ ደግሞም ገንዘብህን ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ አለው።
ይህንንም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተመልቶ ሐዋርያው ታዴዎስን ይገድለው ዘንድ አነቀው። የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሣ ዐይኖቹ ተመዝዘው በወጡ ነበር። አባት ጴጥሮስም የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ አለው ያን ጊዜም ተወው ሐዋርያው ታዴዎስም ጌታችን እንዳንተ ላለው ሀብታም ባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ገመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብሎ በእውነት ተናገረ አለው።
ጐልማሳው ባለጸጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል አለ። በዚያን ጊዜም በዚያ ጐዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ። መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያውን ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያውም እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣልን አለው።
.ከዚህ በኋላ ባለ መርፌው ቀዳዳው ጠባብ የሆነውን መርፌ ባቀረበለት ጊዜ ኃይልህን ግለጥ ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ እጁንም ዘርግቶ ባለ ገመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋራ በመርፌ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ አለው ገብቶም አለፈ ሕዝቡ የፈጣሪያችን የክርስቶስን ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ አለው ባለ ገመሉም በመርፌው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከገመሉ ጋራ አልፎ ሔደ።
ሕዝቡም አይተው ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ያም ጐልማሳ ባለጸጋ መጥቶ ከሐዋርያው እግር በታች ወድቆ ሰገደና ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ ገንዘቤንም ሁሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፋፍል አለው።
የባሕር ፡ መመላለስዋ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፤
ድንቅስ ፡ በልዕልናው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፤
የሚመስለው: የለም ! ከፍጥረትም ፡ ሁሉ ፡ ከአማልክትም ፡ ልጆች ፡ ሁሉ የሚተካከለው ፡ የለም ፡
እርሱ ፡ ብቻ ፡ አምላክ ፡ ነው ፤
እርሱም ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡
ፈጣሪም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፤
ሠሪም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ።
ስላሰበው ፡ ጥበብ ፡ ረዳት ፡ አይሻም ፣
ስለ ፡ ወደደ ውም ፡ ሥራ ፡ መካር ፡ አይሻም ፡
ሳይሆን ፡ ቀድሞ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ አድርጎ ፡ ያልተደረገውንም ፡ እንደ ፡ ተደ ረገ ፡ አድርጎ ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል ።
ሳይጠይቅ ፡ ሕሊናን ፡ ይመረምራል ፤
ሳይመረምር ' ልቡናን ፡ ይፈትናል ፤
ያለ ፡ መብራት ፡ በጨለማ ፡ያለውን ፡ ያያል ።
ጻድቁን ፡ ጽድቅን ፡ ሳይሠራ ' ያውቀዋል ፤
ኃጥኡ ንም ፡ ኃጢአት ፡ ሳይሠራ ፡ ያውቀዋል ፤
ልበኞችን ከአባታቸው ፡ ወገብ ፡ ( አብራክ ፡ ) ሳይወጡ ፡ ያው ያውቃቸዋል ።
ኃጥኣንንም ፡ ከእናታቸው : ማኅፀን ፡ያውቃቸዋል
የሚሸሽገው ፡ የለም ፤ የሚሠወረውም ፡ የለም ፤
ከእርሱም ፡ የሚሠወር የለም ፡
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ዘንድ ፡ የተገለጸ ፡ ነው ፡
በዓይኖቹም ፡ ፊት ፡ ሁሉ ፡ የተዘረጋ ፡ ነው ፡
ሁሉ ፡ በመጽሐፉ ፡ የተጻፈ ፡ ነው ፤
በሕሊናውም ፡ ሁሉ ፡ የተጠራ ፡ ነው ።
ቍጥር፡የሌላቸው፡ታላላቆችን
መመርመር የሌለባቸውን የተደነቁ የከበሩ ሥራዎችን ይሠራል።
ሥራው፡ ከአየነው፡ይልቅ ዕፁብ ነው፤
ኃይሉም፡ከሰማነው ይልቅ ድንቅ ነው፤
ጌትነቱም ከነገሩን ይልቅ ድንቅ ነው።
ከጨለማ ፡ ለይቶ ፡ ብርሃንን ፈጠረ
ደመናውን መለየት ያውቃል ፡
ውኃውን፡እንደ፡ወደደ ይከፍለዋል ፤
የተመረጡትን ፡ በደመና ' ይሠውራል ።
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ❤️
Share 👉 @uraman4u13
†††✝ እንኳን ለተባረከ ወር ሐምሌ እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ✝†††
††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝
††† እግዚአብሔርን ቸር የምንለው በባሕርዩ ፍጹም ቸር በመሆኑ ነው:: ይሕንን ደግሞ ለማረጋገጥ መቅመስ ይቻላል:: ይገባልም:: (መዝ. 33:7) ይሔው ደግሞ ያን ሁሉ ኃጢአታችንን ታግሶ ከወርኀ ሐምሌ አደረሰን:: ለዚሕ ቸርነቱ አምልኮ : ውዳሴና ስግደት ይገባዋል::
ለወርኀ ነሐሴ ደግሞ እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::
††† ✝ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሊቅ ✝†††
††† ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት ቅዱስ አግናጥዮስ ገና በልጅነቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየ : ራሱ ጌታችን ትንቢት የተናገረለት (ማቴ.18:1) እና ከጌታ ዕርገት በኋላ ሐዋርያትን የተከተለ አባት ነው:: ጌታ ሲያርግ የአምስት ዓመት ሕፃን ሲሆን ከሰላሳ ስድስት ዓመታት በላይ ሐዋርያትንና ቤተ ክርስቲያንን አገልግሏል::
ዕድሜው ወደ አርባዎቹ ሲደርስ (ኢየሩሳሌም በጠፋችበት ዓመት - በ70 ዓ/ም) እርሱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ ተሹሟል:: አስቀድሞ ከወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እግር ምሥጢርና ፍቅርን ጠጥቷልና የተለየ ሰው ነበር:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከአንጾኪያ እየተነሳ ምድረ እስያንም በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሷል::
በአካል ያልደረሰባቸውን በጦማር (በክታብ) አስተምሯል:: በአካሉ እንኳ ምንም በጾም በጸሎትና በብዙ ድካም የተቀጠቀጠ ቢሆን ግርማው የሚያስፈራ ነበር:: ከነገር ሁሉ በኋላ የወቅቱ ቄሣር ጠራብሎስ ይዞ አሰቃይቶ ለአንበሳ አስበልቶታል:: በዚህ ምክንያት "ምጥው ለአንበሳ-ለአንበሳ የተሰጠ" እየተባለ ይጠራል::
††† ✝አባ ብዮክ እና አባ ብንያሚን✝ †††
††† እነዚህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ናቸው:: ካህን አባታቸው በሚገባ ቢያሳድጋቸው እነሱም ገና በወጣትነት የሚደነቅ የክህነት አገልግሎትን ሰጥተዋል:: ሙሉ ሌሊት ለጸሎት : ሲነጋ ለኪዳን : በሠርክ ደግሞ ለቅዳሴ ይፋጠኑ ነበር:: ሁሌም በየቤቱ እየዞሩ የደከመውን ሲያበረቱ : የታመመውን ሲፈውሱ : ያዘነውን ሲያጽናኑ ውለው ትንሽ ቂጣ ለራት ይመገባሉ::
ሰውነታቸው በፍቅር ሽቱ የታሸ ነበርና ብዙዎችን መለወጥ ቻሉ:: አንዴ ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ "አባታችሁ ሊሞት ነው" ቢሏቸው "ሰማያዊው አባት ይቀድማል" ብለው ቀድሰዋል:: አባታቸውንም ቀብረውታል:: በመጨረሻ ግን አንድ ቀን ለመስዋዕት ብለው ያዘጋጁትን የበረከት ሕብስት እባብ በልቶባቸው አገኙ:: እንደ ምንም ፈልገው እባቡን ገደሉት::
ነገር ግን ያ የተባረከ ሕብስት በሆዱ ውስጥ ነበርና ምን ያድርጉት? ጌታን ስለ ማክበር ሊበሉት ፈልገው ጌታን ቢጠይቁት መልአኩ መጥቶ "ሰማዕትነት ሆኖ ይቆጠርላቹሃል" አላቸው:: ሁለቱ ወንድማማቾች ብዮክና ብንያሚን ፈጣሪያቸውን አመስግነው በሉት:: ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ሁለቱንም እንደተቃቀፉ ዐርፈው አገኟቸው:: መልካም እረኞቻቸው ናቸውና ከታላቅ ለቅሶ ጋር ቀብረዋቸዋል::
††† ✝ቅድስት ቅፍሮንያ ሰማዕት ወጻድቅት✝ †††
††† ይህቺ ቅድስት እናታችን ደግሞ ገና በአሥራ ሁለት ዓመቷ ታላቅ እህቷን ተከትላ ገዳም ትገባለች:: በሚገርም ተጋድሎ በጥቂት ጊዜ አጋንንትን አሳፍራ መነኮሳይያትንም አስገርማቸዋለች:: ትጋቷ ግሩም ነበርና ስትታዘዝ : ስትጸልይና ስትሰግድ ያለ እንቅልፍና ምግብ ቀናት ያልፉ ነበር:: በዚህ የተቆጣ ሰይጣን አረማዊ መኮንንን ይዞባት መጣ::
ሌሎች ደናግል ሲያመልጡ እርሷ ለመከራ ተዘጋጅታ ጠበቀችው:: አዕምሮ የጎደለው መኮንኑም ክርስቶስን ካልካድሽ ብሎ ጽኑዕ ጽኑዕ መከራን አመጣባት:: በተጋድሎ ባለቀ አካሏ ሁሉንም ቻለች:: በዚህች ቀን ግን አንገቷን በሰይፍ አስቆርጧታል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የወዳጆቹን ትዕግስትና ጽናት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ✝ቅዱስ ቶማስ ✝†††
ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል::
ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን "ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሽሹ" ብሎ መከራቸው::
ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::
እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ (መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች::
ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ::
የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል የገደልኩሽ እኔ:: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው:: እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::
††† ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::
††† ሐምሌ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሰማዕት
2.አበው ቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን
3.ቅድስት ቅፍሮንያ (ሰማዕት ወጻድቅት)
4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
5.አቡነ ገብረ መድኅን ጻድቅ
6.አባ ክልዮስ ዘሮሜ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
††† "በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርበው "በመንግስተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?" አሉት::
ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ:: እንዲህም አለ:- "እውነት እላቹሃለሁ:: ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ አትገቡም::
እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግስተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው::" " †††
(ማቴ. ፲፰፥፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
አማኑኤልም ፡ ተባለ ❤️
ትርጓሜውም፡እግዚአብሔ አምላካችን ፡ ከእኛ ፡ ባሕርይ ፡ ጋር ፡ አንድ ፡ ሆነ ማለት ፡ ነው ፤ ያለ ፡ መቀላቀል ፡ ያለ ፡ መለወጥ ሰው ፡ የሆነው ፡ አንድ ፡ ገጽ ፡ አንድ ' አካል አንድ ፡ ባሕርይ ፡ ነው፡ ከመለኮትና ፡ ከትስብእት የሆነ ፡ ተዋሕዶ ፡ የማይነገር ፤ የማይመረመር ነው በእውነት ፡ መቀላቀል ፡ የሚገባቸውስ ' ርጥበት ፡ ያላቸው ፡ ሥጋት ፡ ናቸው ፤ እነዚህም ፡ ግዘፍ ፡ ከሌ ለው፤ ባሕርይ ፡ የተለዩ ፡ ናቸው ።
ከተዋሕዶ ፡ በኋላ ፡ ወደ ፡ ሁለት ፡ ባሕርይ ፡ አይ ከፈልም ፤ ተዋሕዶ መንታነትን ፡ አጥፍቷልና ተዋሕዶም ፡ ከሁለት የተገኘ ፡ ሁለት ፡ መባል ፡ 'ፍርድ ' ፤ ፡ አለበት ፡ የሚለውን ፡ ፍርድ ' ይለውጣል ፤ ይህ ፡ ፡ ተዋሕዶ ፡ የማይከፈል ፡ አካላዊ ፡ ነውና ፡ ፍጡር፡ ያይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ወደ ፡ መሆን ይለወጣል ፤ በባሕርይ ፡ የሚመስለን ፤ ከንጽሕት ድንግል ፡ የተገኘ ፡ ሥጋም ፡ ከባሕርዩ ፡ የመለኮት ባሕርይ ፡ ወደ ፡ መሆን ፡ ተለወጠ ፡ ብሎ ፡ መናገር ፡ እውነተኛ ፡ ነገር ፡ እንደሆነ ፡ የሚያስብ ፡ ማነው
የሙሴ ፡ በትር ፡ ተለውጣ ፡ የምድር ፡ እባብ ፡ እን ደሆነች
የፈሳሽ ፡ ውኃም ፡ ተለውጦ ፡ ደም ፡ እንደ ፤ ፡ ሆነ ፤
የግብጽ ፡ ብርሃንም ፡ ተለውጦ ፡ ጨለማ ፡ እንደሆነ ፤
እንዲሁ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃልም ፡ የሰው ፡ ባሕርይን ፡ ወደ ፡ መሆን ፡ የተለወጠ ፡ አይደለም እነርሱ ፡ የተፈጠሩ ' ናቸውና ፣
በመፈጠርም ፡ የታ ወቁ ፤ ናቸውና ፤ ከዘመንም ፡ በኋላ ፡ የተገኙ ፡ ናቸውና ፤
ስለዚህም ፡ መለወጥ ፡ አገኛቸው ፤ የመለኮት ፡ ባሕርይ ፡ ግን ፡ መለወጥ ፡ የለበትም ፤ ፍጻሜ፡ ሳይኖረውም ፡ ሁልጊዜ ፡ ይኖራል ፤ አይወሰንም፡ መለወጥ ፡ መናወጥ ፡ የለበትም ። ዘፀአ ' ፬ ፡ ፩ : ፫ : ፲፯ " ፲ ፡ ፳፪ "
ቅዱስ ባስልዮስ ❤️
Share👉 @uraman4u13
በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::
ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: (ቅዳሴ ማርያም) ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች:: ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች::
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)