kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 19-የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከሚነደው እቶን እሳት በተአምራት ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
+ ቅዱስ በጥላን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ ጨካኙ መኮንን አርያኖስ በሰማዕትነት የገደላቸው የእስና አገር ሰማዕታት፣ አራቱ መኳንንት፣ ባሕታዊ ይስሐቅ፣ ቅድስት ደላዢን እና አራት ልጇቿ እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሰማዕታት በአንድነት በዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ታስበው ይውላሉ፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከሚነደው እቶን እሳት እንዳዳናቸው፡- ሦስት ዓመት ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር 15 ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ቅዱስ ቂርቆስም በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡
ንጉሡ እስክንድሮስ ጭፍሮቹን "ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምሩበት" ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ከፈጸሙ በኋላ መጥተው "ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል" አሉት፡፡ "ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ" አሉት፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡
"ነገር ግን እናቴ ሆይ አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ ሶስናን ከሀጢያተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን ያድነናል፡፡ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እርሱ ያድነናል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ ይገባናል፡፡ እርሱ ልጆቹንና ሚስቱን ያገኘው ገንዘቡን አጥቶ በመጨረሻው ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረለት አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል..." እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገር ግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፡፡ አቤቱ ይህነን ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፡፡ አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡ እንጨቱንም ቅጠሉንም ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ ሁሉ ይህን ያየ ዘንድ፡፡ ማዳን የሚችል አምላክ ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ እንዳይጠራጠር፡፡ ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፣ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለእናቴ ስጣት አበርታት..." ብሎ ጸለየ፡፡
በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፡- በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዲቱን እንኳን የራስ ጸጉራቸውን ሳይነካቸው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ የራማው ልዑል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
+ + +
አርያኖስ በሰማዕትነት የገደላቸው የእስና አገር ሰማዕታት፡- ጨካኙ አርያኖስ ወደ እስና ከተማ ሦስት ጊዜ ሲመጣ በመጀመሪያ መስተጋድልት የሆነች ዳላዢን በሰማዕትነት ገደላት፡፡ ቀጥሎም ሱርስ፣ ኅርማን፣ ያኑፋ እና ስንጣንያ የተባሉን የከበሩ ቅዱሳን ልጆቿንም ግንቦት 17 ቀን በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ በሁለተኛም ጊዜ ስማቸው አውሳፍዮስ፣ ታማን፣ ኅርማንና ባኮስ የተባሉ አራት መኳንንትን ሰኔ 7 ቀን በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ በሦስተኛም ጊዜ በቤቷ ውስጥ በአልጋዋ ላይ ተኝታ የነበረችውን አሮጊት ስለእነዚህ ቅዱሳን ከጠየቃት በኋላ ገደላት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ብትኑና ተሰርቶ ይደውሉልን በ 0931559466 ወይም በ 0916868783
0939429098 groupachin @binyammk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/5_BYH_8yrlc

ላይክ ሼር ሰብስክራይብ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝ጻድቁ ከበዓታቸው ጣና ዘጌ ተነስተው አቡነ ሐራ ድንግልን እየሄዱ ይጎበኟቸው እንደነበር በአቡነ ሐራ ድንግል ገድል ላይ ተጽፏል። አቡነ በትረ ማርያም ከበዓታቸው ወጥተው ወደ ሌላ ቦታ የሚሔዱት ለምነው ለነዳያን የሚሰጡትን ለመሰብሰብ ሲፈልጉና ገዳማትን ተሳልመው የቅዱሳንንም በረከት ለመቀበል ሲፈልጉ ብቻ ነበር። ቅዱሳንን ጎብኝተው ወደ ገዳማቸው ዘጌ የሚመለሱትም ለነዳያን የሚሰጡትን ከሰበሰቡ በኋላ ነው። ለነዳያን የሚሰጡትን ገንዘብ የሚሰበስቡትም እንደባርያ እየተሸጡ ለፈረስ ሳር በማጨድና የመንገደኞችን ዕቃ በመሸከም የሚከፈላቸውን ገንዘብ በማጠራቀም ነበር። ‹‹ላጡ ለድኆች የሚሆን ምግብ ለማግኘት ሲሉ ለፈረስና ለበቅሎ ሣር ያጭዱ ዘንድ ባሪያ ሆነው የተሸጡበት ጊዜ አለ። ከባለጸጋ ቤት ቁራሽ እንጀራን ተቀብለው ለድኆች ይሰጡ ዘንድ በባለጸጋው ደጅ ከድኆች ጋር ተቀምጠው የሚለምኑበት ጊዜም ነበር። በመንገድ የሚያልፉ ሰዎችን ዕቃቸውን ይሸከሙ ዘንድ በመንገድ የሚቆሙበት ጊዜም ነበር›› በማለት ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል የአቡነ በትረ ማርያምን የትሩፋት ሥራ ይነግረናል።
✝አቡነ በትረ ማርያም ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን በማድረግ ይታወቃሉ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባታችን ከመነኰሳት ልጆቻቸው ጋር በገዳማቸው ሳሉ በህርመት የሚኖሩ መሆናቸውን የሰማ አንድ መነኵሴ ከሩቅ መጣና እንደገዳሙ ሥርዐት በእንግዳ ቤት ተቀመጠ። መነኰሳቱም የጸሎተ ማዕድ አድርሰው እንደመነኰሳቱ መቁነኑን ለእንግዳው ሰው አደሉት። መነኵሴው ግን መቁነኑን ሳይበላው ደብቆ ይዞ በአኩፋዳው ውስጥ ከተተው። በልቡም ‹‹እነዚህ መነኰሳት የሚመገቡት ይኸንን ነው› ብዬ ለሀገሬ ሰዎች ማሳየት አለብኝ›› ብሎ አሰበ።

ወዲያም በአኩፋዳው የደበቀውን መቁነን ሰውሮ ይዞ ለመሔድ ሲነሣ ቡራኬ ሊቀበልና ሊሰናበት ከአቡነ በትረ ማርያም ፊት ቆመ። አባታችንም ሰውዬው ደብቆ የያዘውን መቁነን በመንፈስ ቅዱስ ዐወቁበትና ‹‹…ይኸ እንግዳ እኛ የሰጠነው እንደሆነ ክብራችንን ከገዳሙ ውጭ አውጥቶ ሊገልጽ አይገባም፣ ይኽንን ይበላሉ እያለ ሊገልጽብን ነው›› አሉ። ዳግመኛም የየራሱ የሆነው ይባረክለት፡ የገዳሙ
መቁነን የሆነው ግን ከይሲ ይሁን›› በማለት እንደተናገሩ ወዲያው ከአኩፋዳው ውስጥ ሰባት ክንድ የሚሆን እባብ ራሱን ከአኩፋዳው ውስጥ ብቅ አደረገ። በዚኸም ጊዜ እንግዳው ሰውዬ እጅግ ደንግጦ ከአባታችን እግር ሥር ወድቆ ‹ በድያለሁ፣ ኀጢአት ሠርቻለሁ፣ ይቅር በሉኝ›› እያለ የሠራውን ሁሉ እየተናዘዘ ይቅርታ ያደርጉለት ዘንድ ለመናቸው። አቡነ በትረ ማርያምም ‹‹እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ዳግመኛ እንዳትበድል›› አሉትና ወደመጣበት መለሱት።

✝አቡነ በትረ ማርያም መልካሙን ተጋድሏቸውን ፈጽመው ሩጫቸውን ጨርሰው የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ ተገለጠላቸውና “ወዳጄ በትረ ማርያም ሆይ! በዚኽች ዕለት ከኀዘን ወደ ደስታ፣ ከሕመም ወደ ሕይወት ልወስድህ ነፍስህንም አሳርፋት ዘንድ መጣሁ፤ ቦታህን እንደ ኢየሩሳሌም አደረግሁልህ፤ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሠራ፣ ዕጣን የሰጠውን መብዓ ያቀረበውን፣ ሥጋህ የተቀበረበትን ዐፅምህ ያረፈበትን ገዳመ ዘጌን የተሳለመውን፣ ወንዱ በ40 ቀን ሴቷ በ80 ቀን ጥምቀተ ክርስትና የተቀበለውን፣ በቦታህ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን የተቀበለውን፣ በስምህ ገድልህን የጻፈውን፣ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ልብ ያላሰበውን እንደ አንተ ላሉት አባቴ ያዘጋጀውን አወርሰዋለሁ። በገዳመ ዘጌ ላይ መብረቅና ነጎድጓድ፣ በምድር የሚሳቡ በመርዛቸው ሰውን የሚጎዱ እባቦች፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩ አራዊቶች ሁሉ በዘጌ የሚኖረውንና በአንተ ያመነውን አይጣሉ (አይጉዱ)፣ በገዳሙ የሚኖሩ መነኰሳትና ምእመናን እንደ መላእክት ኀጢአት የሌለባቸው ይሁኑ፣ ደምህ ከፈሰሰበት ከገዳመ ዘጌ መቃብርህ ላይ አፈር ቆንጥሮ የተቀባ ከሕማሙ ይፈወስ፣ መቃብርህን እጅ የነሣ የእኔን መቃብር እጅ እንደነሣ ይሁንልህ›› በማለት አስደናቂ የምሕረት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ዐሥራ ኹለት የክብር አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ጌታችን በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ።
✝አባታችንም ከዚህ በኋላ መነኰሳት ልጆቻቸውን ሰብስበው የዕረፍታቸው ጊዜ መድረሱን ነግረዋቸው በመጨረሻው ዘመን ወደ ገዳሙ ክፉ ሰዎች ይመጣሉና ከእነርሱ ጋር አትጨመሩ… እያሉ ከመከሯቸውና ካስተማሯቸው በኋላ ረዳታቸውን አቡነ በርተሎሜዎስን በእርሳቸው ቦታ ከሾሙላቸው በኋላ በዕለተ ዐርብ ከቀኑ በሦስት ሰዓት በ89 ዓመታቸው ሐምሌ 17 ቀን በክብር ዐርፈው በዚያው በመሐል ዘጌ ተቀበሩ። ቅድስት ነፍሳቸውን ቅዱሳን መላእክት በምስጋና በማኅሌት ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ።
ጻድቁ ከዘጌ ጊዮርጊስ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ በተቀበሩበት ቦታ ላይ ሌላ ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት ሲሆን ከመካነ መቃብራቸው ላይ እየተወሰደ ለምእመናን የሚሰጠው እምነት በዘመናችንም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል።
የአቡነ በትረ ማርያም ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን።
(ምንጭ$$$ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ ገጽ 320-327)
ሐምሌ 17/11/2015 ዓ.ም
Kuwait
✝✝✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሐምሌ17/11/2015 #ቅዱስ_እስጢፋኖስ

👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ለሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጸሎቱና በረከቱ በህዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር እና ወር በገባ በ 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም አክሊል ማለት ነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር

👉ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር

👉ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል

👉በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ

👉ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው በመጨረሻም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ነፍሱን ሰጠ

👉ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር ተንበርክኮም ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ይህንም ብሎ አንቀላፋ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር ዮሐ ሥራ 7፥58—60

👉የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው ፀሎቱ አይለየን ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝††† እንኳን ለቅዱስ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)✝ †††

††† ቅዱሱ "ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች ዮሐንስ ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ የማይለየውና አቅፎት የሚተኛ በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ስለ ነበረው ነው::

የቅዱስ ዮሐንስ ታሪኩ ከመርዓዊ (ሙሽራው) ገብረ ክርስቶስ እና ከቅዱስ ሙሴ ሮማዊ ጋር ተመሳሳይነት አለው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በሮም ግዛት ሥር የሚኖሩ አጥራብዮስና ብዱራ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ:: እግዚአብሔር በቀደሰው ትዳር የሚኖሩና ነዳያንን የሚዘከሩ ነበሩና ይህንን ቅዱስ ወለዱ:: ስሙን ዮሐንስ ብለው: እንደሚገባም አሳድገው: ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን እንዲረዳ ለመምህር ሰጡት:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመምህሩ ዘንድ ቁጭ ብሎ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ተማረ::

ለወላጆቹ ቅንና ታዛዥ ነበርና አባቱ "ልጄ! የምትፈልገውን ጠይቀኝ:: ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለው:: ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድሮ እኛን የሚያምረን ሁሉ አላሰኘውም:: አባቱን "ቅዱስ ወንጌልን ግዛልኝ: በወርቅም አስለብጠው" አለው:: አባትም የተባለውን ፈጸመ::

ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ዓለም ተለይቶ እስካረፈባት ቀን ድረስ ቅዱስ ዮሐንስና የወርቅ ወንጌሉ ተለያይተው አያውቁም:: ሁሌም ያለመታከት ያነበዋል:: ሲቀመጥም ሲነሳም: ሲሔድም ሲተኛም አብሮት ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ወጣት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይድሩት ዘንድ ተዘጋጁ:: ልብሰ መርዐም (የሙሽራ ልብስ) አዘጋጁ:: በዚያው ሰሞን ግን አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤታቸው መጥቶ ያድራል:: በዚያች ሌሊት መነኮሱ በጨዋታ መካከል ስለ ቅዱሳን መነኮሳት ተጋድሎና ክብር ነገረው:: የሰማው ነገር ልቡናውን የማረከው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚያች ቀን ጀምሮ ወደ ፈጣሪው ይለምን ነበር::

አንድ ቀን ግን ያ መነኮስ በድጋሚ መጥቶ አደረ:: ቅዱስ ዮሐንስ መነኮሱን ወደ ገዳም እንዲወስደው ቢጠይቀው "አይሆንም: አባትህ ያዝንብኛል" አለው:: ቅዱሱ ግን "በእግዚአብሔር ስም አማጽኜሃለሁ" ስላለው ሁለቱም በሌሊት ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

አበ ምኔቱ "ልጄ! የበርሃውን መከራ አትችለውም: ይቅርብህ" ቢለውም "አባቴ! አይድከሙ:: ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር አይለየኝም::'' ስላላቸው እንደሚገባ ፈትነው አመንኩሰውታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመነኮሰ በኋላ በጾም: በጸሎት: በስግደትና በትሕርምት ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን አስደነቀ::

ለሥጋው ቦታ አልሰጣትምና በወጣትነቱ አካሉ ረገፈ:: ቆዳውና አካሉም ተገናኘ:: ሥጋውን አድርቆ ነፍሱን አለመለማት:: በእንዲሕ ያለ ሕይወት ለሰባት ዓመታት ከተጋደለ በኋላ በራዕይ "ወደ ወላጆችህ ተመለስ" እያለ ሦስት ጊዜ አናገረው::
ቅዱስ ዮሐንስ ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ቢጠይቀው "ራዕዩ ከእግዚአብሔር ነው" ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ አሰናበተው::

ቅዱስ ዮሐንስ በላዩ ላይ የነበረችውን ልብስ በመንገድ ለነዳይ ሰጥቶ: በፈንታው ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ ከወላጆቹ በር ላይ ለመነ:: "እባካችሁ አስጠጉኝ" አላቸው:: ወላጆቹ በጭራሽ ሊለዩት አልቻሉም:: ነገር ግን አሳዝኗቸዋልና በበራቸው አካባቢ ትንሽ ቤት ሠሩለት::

በዚያች በዓት ውስጥ እንዳስለመደ በትጋት ለሰባት ዓመታት ተጋደለ:: በእነዚህ ዓመታት እንኳን ሌላው ሰው ወላጆቹም ቢሆኑ ፍርፋሪ ከመስጠት በቀር አይቀርቡትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ "ይሸተናል" የሚል ነበር:: በመጨረሻም መልአከ እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ "ከሰባት ቀናት በኋላ ታርፋለህ" አለው::

እናቱን ጠርቶ "አንድ ነገር ልለምንሽ" አላት:: "እሺ" አለችው:: "ከሞትኩ በኋላ በለበስኳት ጨርቅ እንድትገንዙኝ: በበዓቴ ውስጥም እንድትቀብሩኝ" አላትና የወርቅ ወንጌሉን አውጥቶ ሰጣት:: ያን ጊዜ አባቱም ደርሶ ነበርና ደነገጡ::

የወርቅ ወንጌሉን ለዩት:: ልጃቸውን ግን መለየት አልቻሉምና እያለቀሱ ስለ ልጃቸው የሚያውቀው ካለ እንዲነግራቸው ለመኑት:: እርሱም "ልጃችሁ ዮሐንስ እኔ ነኝ" አላቸው::

በዚያ ቅጽበት ወላጆቹ የሰሙትን ማመን አልቻሉም:: በፍጹም ዋይታ እየጮሁ አለቀሱ:: ለቅሷቸውን የሰሙ ሁሉ ተሰበሰቡ:: ለሰባት ቀናት እኩሉ እያለቀሰ: እኩሉ እየተባረከ በዓቱን ከበው ሰነበቱ:: በሰባተኛው ቀን መልአኩ መጥቶ በክብር ነፍሱን ተቀበለ::

እናቱ የልጇን አደራ ረስታ (እሷስ መልካም አደረግሁ ብላ ነው) ለሠርጉ ባዘጋጀችው የወርቅ ልብስ ገነዘችው:: ወዲያው ግን በጽኑ ታመመች:: አባት ግን ፈጠን ብሎ በዚያች ጨርቅ ገንዞ በበዓቱ ውስጥ ቀበረው:: ያን ጊዜ እናት ፈጥና ዳነች:: ከቅዱሱ መቃብርም ብዙ ተአምራትና ፈውስ ተደርጓል::

††† ቸሩ አምላካችን ከቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

††† ሐምሌ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ

††† "እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ: የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ: በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ:: በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ:: የመዳንንም ራስ ቁር: የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ:: እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው:: በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ:: በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ::" †††
(ኤፌ. ፮፥፲፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዕድለኞች መልካም ዜና ይዞ መጥቷል
#የ1.1_ትሪሊየን ትርፍ #ያጋሩ ይሸለሙ
https://t.me/joinchat/VlbTFePq5Sl4cT5M

እንኳን ደስ አላቸችሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት 1.1 ትሪሊየን ትርፍ ምክንያት በማድረግ የባንካችን ፕሬዝዳንት #አቶ_አቢ_ሳኖ እስከ መስከረም_5 ብቻ የሚቆይ #የቴሌግራም_ገፅ ማነቃቂያ የሚሆን ሽልማቶች ተዘጋጅቷል።

https://t.me/joinchat/VlbTFePq5Sl4cT5M
እስከ_መስከረም_5 ድረስ የሚቆይ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት እድለኞችን በርካታ # ስጦታዎችን ለመሸለም ተዘጋጅተናል!
# 1ኛ . ለ200 እድለኞች ከ300,000 ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችና እያንዳንዳቸው ከ50,000 ብር በላይ ግምት ያላቸው ሙሉ የቤት እቃዎች
# 2ኛ . ለ 220 እድለኞች 50ሺ ብር እና እያንዳንዳቸው ከ15,000 ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የማቀዝቀዣ ፍሪጆች፤
# 3ኛ . ለ 245 እድለኞች 10ሺ ብር እና እስከ 7,000 ብር የሚያወጡ Infinix ሞባይል ቀፎዎች
# 4ኛ . ለ 150 እድለኞች 10ሺ ብር እና የTECHNO SPARK የሞባይል ቀፎዎች
# 5ኛ . ለ 100 እድለኞች 5ሺ ብር እና የTechno spark የሞባይል ቀፎች እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ የአዲስ አመት ስጦታዎችን አዘጋጅተናል። #ይፍጠኑ እስከ #መስከረም_5 2016 ድረስ የእነዚህ አጓጊ ሽልማቶች ባለ እድል ይሁኑ።
ልብ ይበሉ!
በሽልማት ፕሮግራሙ ከመሳተፍዎ በፊት # በጥንቃቄ መመሪያዎችን ያንብቡ!
ለመሸለም እነዚህን መመሪያዎች በጥንቃቄ ይከተሉ።
1.መጀመርያ ከታች ባለው ማስፈንጠርያ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/VlbTFePq5Sl4cT5M
2. በመቀጠል ይህንን መልዕክት ከ50 በላይ ለሆኑ ሰዎች በፍጥነት ሼር ( Forward) ያድርጉ፤
(ልብ ይበሉ! ብዙ ሰዎችን # add ባደረጉ ቁጥር የሽልማት ዕድልዎን ያሠፋሉ!)
https://t.me/joinchat/VlbTFePq5Sl4cT5M

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👉 ሐምሌ. 15
////7 ቀን ውዳሴ ማርያም /// አድረሱ
👉ቅዱስ ኤፍሬም
👉ማሪ ኤፍሬም
👉.አፈ በረከት ኤፍሬም
👉ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
👉ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
👉አበ ምዕመናን ኤፍሬም
👉ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን ነው
የ 7 ቀን ውዳሴ ማርያም. አድረሱ ተበርከቱ ተሳተፍ በእምነት ሁሉም ይደረጋል
ለማስታወስ ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝††† እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እና ለመነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝

†††✝ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት✝ †††

††† ቅዱሱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: አባቱ ደግ ክርስቲያን የነበረ ሲሆን ስሙ #ክርስቶፎሮስ ይባላል:: "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ ማለት ነው:: እናቱ ግን #ቴዎዳስያ የምትባል አረማዊት ነበረች:: ምንም እንኩዋ አባቱ ክርስቲያን ቢሆን እናቱ ኃይለኛ የቤተ መንግስት ሰው ስለነበረች በልጅነቱ አብሮኮሮንዮስ ክርስትናን ሊማር አልቻለም::

የልጁን አረማዊ መሆን ያልወደደ አባት አማራጩ አንድ ብቻ ነበር:: እሱም ወደ ጌታ መለመን ነበር:: በእንዲሕ ያለ ግብር ዘመናት ጐርፈው አብሮኮሮንዮስ ክርስቶስን ሳያውቅ 20 ዓመት ሆነው:: እናቱ ወስዳ: አሰልጥና ለጣዖት አምላኪ ንጉሥ ሰጠችው:: ንጉሡም የጦር አለቃ አድርጐ ሾመውና አንድ ትዕዛዝ ሰጠው:: "ክርስቲያኖችን ሁሉ ባገኘህበት ቦታ ጨፍጭፍ:: ቤታቸውንም አቃጥል::"

#አብሮኮሮንዮስ የታዘዘውን ሊፈጽም ሠራዊት አስከትሎ ሲወጣ ግን የአባቱ የ20 ዘመናት ለቅሶና ጸሎት ፍሬ አፈራ:: ገና መንገድ ላይ ሳለ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ድምጹን ከሰማይ ላከለት:: "ወደ እውነተኛ መንገድ ተመለስ:: ካልሆነ ግን ሾተሉን ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል" አለው::

አብሮኮሮንዮስም እየተንቀጠቀጠ "አቤቱ አንተ ማነህ?" አለው:: ጌታም "ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" ሲል መለሰለት:: ዳግመኛም "ምልክት ስጠኝ" ቢለው የብርሃን #መስቀል በሰማይ ላይ ገለጠለት:: ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ጊዜ አላጠፋም::

ሠራዊቱን ይዞ ወደ ንጉሡ ከተማ ተመልሶ ንጉሡን በድፍረት አለው:- "እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስንም አመልካለሁ::" ካነጋገሩ የተነሳ አባቱን ደስ ሲለው ንጉሡና እናቱ ግን ደነገጡ:: ንጉሡ ሊያስፈራራው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ከዚያማ ያሰቃየው ገባ::

አንድ ቀን አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት:: በእሳትም አቃጠሉት:: ሞተ ብለው አስበው ነበር:: ወደ እርሱ ሲመለሱ ግን ጌታችን አድኖታልና የሰንበር ምልክት እንኩዋ በአካሉ ላይ አልተገኘም:: እናቱ #ቴዎዳስያ ከዚህ በላይ ምልክትን አልፈለገችም:: በደቂቃዎች ልዩነት እርሷም ወደ #ክርስትና ተመለሰች:: ልጇንም ቀድማ ሐምሌ 6 ቀን ሰማዕት ሆነች::

ቅዱስ አብሮኮርዮስን ግን ለበርካታ ጊዜያት አሰቃይተው ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩት ባለመቻላቸው በዚህች ቀን ገድለውታል:: አባት: እናትና ልጅ (ክርስቶፎሮስ: ቴዎዳስያና አብሮኮሮንዮስ) ለሰማያዊ ርስት በቅተዋል:: አባት ይሏቹሃል እንዲህ ነው!

†††✝ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ✝ †††

††† በገዳማዊ ሕይወቱ እንደ ዘንባባ ያፈራው: የመነኮሳት ሁሉም አለቃቸው ቅዱስ መቃርስ አንድ ቀን እንዲህ አደረገ:-
አንድ በከተማ የሚኖር ባለ ጸጋ ስለ ቅዱስ መቃርስ ዝና ሰምቶ ሊባረክ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ይመጣል:: አባ መቃርስ ባለ ጠጋው ወደ እርሱ እየመጣ መሆኑን ሲያውቅ በወንድሞች መነኮሳት መካከል ልብሱን ጥሎ እንደ አበደ ሰው አለል-ዘለል እያለ ይጫወት ጀመረ::

ያ ከተሜ ባለ ጠጋ እንደ ደረሰ ወደ መነኮሳቱ ጠጋ ብሎ "የታላቁን መቃርስ ዝና ሰምቼ ልባረክ ነበር የመጣሁት:: ከእናንተ መካከል ማንኛው ነው?" ቢላቸው "ያውልህ" ብለው አሳዩት:: ሲያየው እንደ እብድና ሕጻን እየዘለለ ይጫወታል:: ባለጠጋውም "ወይኔ! እኔኮ ደኅና ሰው መስሎኝ ነው:: በከንቱ ደከምኩ" ብሎ እያዘነ ሔደ:: ወዲያው መነኮሳት ተሰብስበው ቅዱስ መቃርስን "ለምን እንደዚህ አደረግህ?" ቢሉት "መጀመሪያ እንደ ሰውነቴ ሊያከብረኝ ይገባል" በሚል መልሷል:: በርግጥም ከምንም ነገር በፊት ሰውን በሰውነቱ (በእግዚአብሔር አርአያ በመፈጠሩ) ብቻ ልናከብር ይገባል::

††† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ በቤተ ክርስቲያን ዛሬ በዓሉ ይከበራል::

††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታችቸውም ያድለን::

††† ሐምሌ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ክርስቶፎሮስና ቴዎዳስያ (ወላጆቹ)
3.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት አለቃ)
4.ቅዱስ አሞንዮስ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

††† "ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጐ ስለቆጠረኝ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን #ጌታችንን አመሰግናለሁ:: አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ: አንገላችም ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ:: ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ:: የጌታችንም ጸጋ #በክርስቶስ_ኢየሱስ ካሉ: ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ::" †††
(1ጢሞ. 1:12)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝††† እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ብስንድዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን✝። †††

††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ †††

††† ✝ቅዱስ ብስንድዮስ ጻድቅ✝ †††

††† ቅዱስ ብስንድዮስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ድንቅ ሥራ ከሠሩት እንደ አንዱ ሆኖ ይዘከራል:: ቅዱሱ ግብጻዊ ሲሆን በልጅነቱ ወደ ትምሕርት ቤት ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: የሚገርመው የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በሙሉ ያጠናቸው በቃሉ ነበር::

በእርግጥ ይሕንን ማድረግ የቻሉ በርካታ የሃገራችን ሊቃውንት ዘንድሮም አሉ:: ልዩነቱ ግን ወዲህ ነው:: ቅዱስ ብስንድዮስ መጻሕፍቱን ያጠናቸው ለሕይወት እንጂ ለእውቀት አልነበረምና ሁሌም ነግቶ እስከ ሚመሽ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እያጣጣመ ይጸልይ ነበር:: ይሕንን ሲያደርግ ደግሞ
ባጭር ታጥቆ
ጫማውን አውልቆ:
በባዶ ሆዱ ቁሞ ነው::

ታዲያ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ክፍል ሲጸልይ ነቢይ ቢሆን ሐዋርያ ወደ እርሱ ይወርድለት ነበር:: ለምሳሌ ዘፍጥረትን ሲጸልይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ይመጣና ከፊቱ ተቀምጦ ይሰማዋል:: ትንቢተ ኢሳይያስ ላይ ሲደርስ ኢሳይያስ: ወንጌለ ማቴዎስ ላይ ሲደርስ ቅዱስ ማቴዎስ ይመጡና ደስ እያላቸው ያደምጡት ነበር::

አንዱ ነቢይ: ወይ ሐዋርያ ሲወጣ ቅዱስ ብስንድዮስን ባርኮ ሌላኛውን ተክቶ ነው:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሕይወት በምድር እያለ ሰማያዊ ሆነ: ሰማንያ አንዱን አሥራው መጻሕፍት የጻፉ ቅዱሳንን ለማየት በቃ:
በእጆቻቸውም ተባረከ::

የቅዱስ ብስንድዮስ ቀጣይ የሕይወቱ ተግባር ብሕትውና ሆነ:: ዓለምንና ግሳንግሷን ትቶም ወደ በርሃ መነነ:: በአጽንዖ በዓት:
በጾምና በጸሎት:
በትሕርምትም ተጋደለ:: በየደረሰበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር በእጆቹ ድንቅ ተአምር ይሠራ ነበር:: ብዙ ድውያንን ፈወሰ: አጋንንትንም ከአካባቢው አሳደደ::

በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ግን ስዕለት ስላለበት ሴቶችን ላለማየት ይጠነቀቅ ነበር:: በሆድ ሕመም ትሰቃይ የነበረችና ጥሪቷን በመድኃኒት የጨረሰች አንዲት ሴት ስለ ቅዱሱ ዝና ትሰማለች:: ችግሩ ግን እርሱ ከውዳሴ ከንቱና ከሴት የሚርቅ ነውና እንዴት ብላ ታግኘው? አንድ ቀን ከበዓቱ አካባቢ ተደብቃ ውላ ሲመጣ የልብሶቹን ዘርፍ ለመንካት በእምነት አሰበች::

ልክ ከበዓቱ ሲዘልቅ ስሉጥ(ፈጣን) ነበርና ገና እንዳያት ሩጦ አመለጣት:: እንዳትከተለው ድውይ ናትና አልቻለችም:: አዝና ዝቅ ስትል ግን የረገጠውን ኮቲ ተመለከተች:: በፍጹም ልቧ: በእምነት "የጻድቁ አምላክ ማረኝ" ብላ ከአፈሩ ቆንጥራ በላች:: ደቂቃ አልቆየችም:: ፈጥና ከደዌዋ ዳነች:: እንደ እንቦሳ እየዘለለች ወደ ከተማ ሔዳ ተአምሩን ተናገረች::

ከእነዚህ ዘመናት በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅፍጥ(Qift) በምትባል ሃገር ጵጵስናን (እረኝነትን) ተሹሟል:: ወደ ከተማ ሲገባ የቀደመ ተጋድሎውን ቸል አላለም:: ይልቁኑ ይተጋ ነበር እንጂ:: ከብቃት መዓርግ ደርሷልና ሲቀድስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገሃድ ያየው: ሠራዊተ መላእክትም ይከቡት ነበር::

ሕዝቡ ሊቆርቡ ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይታየው ነበር:: የበቁትን እያቀበለ: ያልበቁትን እየመከረና ንስሐ እየሰጠ ይመልሳቸዋል:: እንዲሕ በጽድቅ: በሐዋርያዊ አገልግሎትና በንጽሕና ተመላልሶ ቅዱስ ብስንድዮስ በዚህች ቀን ዐርፏል::

ቅዱስ ብስንድዮስ ካረፈ በኋላ ደቀ መዝሙሩ ከመግነዙ ጥቂት ቆርጦ አስቀርቶ ብዙ ድውያንን ፈውሶበታል::

††† ቸር አምላክ ለአባቶቻችን የሰጠውን ጸጋ ለእኛ ለባሮቹም አይንሳን:: ከቅዱሱ በረከትም ያድለን::

††† ሐምሌ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብስንድዮስ ሊቅ ወጻድቅ
2.ቅዱስ አሞን ሰማዕት (ዘሃገረ ጡህ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† "አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር:: ከማን እንደተማርኸው ታውቃለህና:: ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል:: የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምሕርትና ለተግሣጽ: ልብንም ለማቅናት: በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል::" †††
(፪ጢሞ. ፫፥፲፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!!

ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው

ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር
የሚፈልገው 

ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም
መማር ማወቅ የሚፈልገው

  እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ 

ከሲዖል የሚጠብቅ የእግዚአብሔር ቃል
እንዳያመልጥዎ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ✝️ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ✝️ሐምሌ ፲፪✝️ ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ሚካኤል ሊቀ መላእክት"
የተአምር በዓልና ለሰማዕቱ "አባ ሖር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል "*+

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት
ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ
መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም
በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት
#ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር::
ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን
ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ
አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ
ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም
ነበር::

+ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት
የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት::
ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም
በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ
ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ
እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::

+"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን
ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም
አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም
ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት::

+ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን
ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ
ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ
ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ
አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ
የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::

+መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ
ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን
ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ
አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን
መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ
አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት
ከተማዋን አድናታለሁ::"

+በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል
ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር
ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው
ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ::
በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ
ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::

+በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ
ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው
ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ
ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ
የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1)

+*" ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት "*+

=>ዳግመኛ በዚህ ቀን #አባ_ሖር ሰማዕቱ ይታሠባል::

+ቅዱሱ:-

¤ስርያቆስ በምትባል የግብጽ አውራጃ ተወልዶ ያደገ:
¤ገና በልጅነቱ መንኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ:
¤ዘመነ ሰማዕታት በመጣ ጊዜም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመነ:
¤ከመኮንኑም ብዙ ስቃይ የደረሰበት:
¤ብዙ ተአምራትን በመስራቱ ያሰቃየው የነበረውን መኮንን
ወደ ክርስትና መልሶ ለሰማዕትነት ያበቃ አባት ነው::

+እርሱም የሰማዕትነትን ክብር በእጅጉ ሽቷታልና ወደ ሌላ
ሃገር ሒዶ በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል
ተቀዳጅቷል:: በሐዋርያዊ አገልግሎቱ ያሳመናቸው 127
ወንዶችና 20 ሴቶችም አብረውት ተሰይፈዋል::

=>እግዚአብሔር በሊቀ መላእክት ክንፍ ሃገራችንን
ከአሕዛብ ስውር ጦር ይጠብቅልን:: ከሰማዕቱም በረከት
ያሳትፈን::

=>ሐምሌ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ንጉሥ
2.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
3.ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት
4."147" ሰማዕታት (የአባ ሖር ማሕበር)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

=>+"+ እግዚአብሔር ይላል:- ስለ እኔም ስለ ባሪያየም
#ስለ_ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ::
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ::
ከአሦራውያንም ሠፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ::
ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ:: +"+
(1ነገ. 19:34)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!!

ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው

ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር

የሚፈልገው ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም
መማር ማወቅ የምፈልገው እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ ከሲዖል የሚጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል እንዳያመልጥዎ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†††✝ እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ✝ቅዱስ ናትናኤል✝ †††

††† በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር::

ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::

ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::

ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል::

ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል::

ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::

የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በመቶ ሃምሳ ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::

†††✝ አባ ብስንዳ ✝†††

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ አባ ብስንዳ ይታሠባል::
አባ ብስንዳ በዘመነ ጻድቃን ምድረ ግብጽ ውስጥ ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱን ከገድሉ ጽናት የተነሳ መላእክት በእጅጉ ይወዱት ነበር:: "እኔ ልሸከምህ - እኔ ልሸከምህ" እያሉ ይሻሙበት: በተራ በተራም ተሸክመውት ይውሉ ነበር:: እርሱም ለበርካታ ዓመታት ውኃ የሞላበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ይጸልይ ነበር::

እንደ እሳት በሚባላው በረዶ ውስጥ ገብቶ መጸለዩ የፈጣሪውን ሕማማት ለመሳተፍ እና ለኃጥአን ምሕረትን ይለምን ዘንድ ነው:: ሁሌም በዘጠኝ ሰዓት መላእክት ተሠብስበው ይመጡና በብርሃን ሠረገላ ይሸከሙታል:: ከመሬትም ዘጠኝ ክንድ ከፍ ያደርጉት ነበር::
ከብዙ ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሒዷል::

††† እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከሐዋርያው እና ከጻድቁ አባ ብስንዳ በረከትም አይለየን::

††† ሐምሌ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ታላቁ አባ ብስንዳ ጻድቅ
3.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእሥራኤል ንጉሥ ነህ' አለው::" †††
(ዮሐ. ፩፥፵፰-፶፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሐምሌ_9

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ታውድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መስተጋድል #አባ_ኅልያን አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡

መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡

አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡

አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን "ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው" ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል።

አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን በዚህች ዕለት ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ "ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ" በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ" ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ "አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ" ስትላቸው "እግዚአብሔር ይፍታሽ" ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡

ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ (ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡) ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)

ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር።

ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።

ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም። መኰንኑም በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ ይምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው አለው።

መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ታውድሮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን ከቆጵሮስ አገር ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ አረፉ።

ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Amen amen enkon abiro aderesen🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/d12iSMeqtsg

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ማንም የማይቀርበት
@ELFAZ_GFX

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝
✝ የረገጡት የጸለዩበት መሬትና ድንጋይ ሁሉ እምነት ሆኖ ብዙ ድውያንን ይፈውስ የነበረ በትራቸውም በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ የወይን ዘለላ ፍሬ እያፈራ ይለቀም የነበረ አቡነ በትረ ማርያም ዘዘጌ ✝
✝እንኳን ለዕረፍት በዓላቸው አደረሳችሁ አደረስን
በጣና ሐይቅ ደሴት ውስጥ ካሉት 37 ደሴቶች ውስጥ በአጠቃላይ 30 ያህል ጥንታዊ ገዳማት ይገኛሉ። ከእነዚኽም ውስጥ ሰባቱ በዘጌ ባሕረገብ መሬት ላይ የሚገኙ ናቸው። ከእነርሱም ውስጥ ዋነኛውና ቀደምቱ የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ነው። ይኽንንም ገዳም በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በ1264 ዓ.ም የመሠረቱት አቡነ በትረ ማርያም ናቸው።
✝አቡነ በትረ ማርያምና ስድስቱ ወንድሞቻቸው ሰባቱ ከዋክብት ተብለው ይጠራሉ። እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት ቅዱሳን እየራሳቸው ከገደሟቸው ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ አቡነ በትረ ማርያም (መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስን) ፣አቡነ ኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስን)፣ አቡነ ያሳይ (ማንዳባ መድኀኔዓለምን)፣ አቡነ ዘካርያስ (ደብረ ገሊላን)፣ አቡነ አፍቅረነ እግዚእ (ጒጒቤንና ጣና ቂርቆስን)፣ አቡነ ታዴዎስ (ደብረ ማርያምን) እና አቡነ ዘዮሐንስ (ክብራን ገብርኤልን) ገዳማትን ገድመዋል።
የጻድቁን ገድል በአጭሩ ከገዳሙ ታሪክ ጋር አንድላይ ገዳመ ዘጌ ያሳተመው መጽሔት እንደሚገልጠው አቡነ በትረ ማርያም የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ሙገር ነው። አባታቸው ተክለ ማርያም እናታቸው ኢላርያ ይባላሉ። ወላጆቻቸውም በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን እንደ ቅዱስ ኢያቄምና እንደ ቅድስት ሐና ልጅ ስላልነበራቸው የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ዘወትር በጾም በጸሎት ይለምኑት ነበር። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተኝተው ሳለ ኢላርያ ራእይ ተመለከተች። ተክለ ማርያምም ተመሳሳይ ራእይ ተመልክቶ ኹለቱም ስላዩት ራእይ ተነጋግረው “ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› አሉ። እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ምእመናንን ስቦ በወንጌል ጎዳና የሚመራ የተመረጠ ልጅ እንደሚወልዱ ነገራቸው። መልአኩም በነገራቸው መሠረት አቡነ በትረ ማርያም ነሐሴ 16 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 21 ቀን ተወለዱ። የተወለዱትም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለክርስቲያኑም ለእስላሙም በምትገለጥበት ዓመታዊ በዓል ላይ ስለሆነ አንድም ይረዳናል ምርኩዛችን ይሆናል ብለው ወላጆቻቸው ስማቸውን በትረ ማርያም አሏቸው።
✝አቡነ በትረ ማርያም ሰባት ዓመት በሆናቸው ጊዜ ወላጆቻቸው ሃይማኖትን እንዲማሩ ወደ ደብረ ኤዎስጣቴዎስ አባታችንም ገዳም ላኳቸው። ትምህርታቸውን እየተማሩ ገዳማውያን አባቶችን ዕንጨት በመስበር በመቅዳትና ውኃ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ እየተራዱ ብሉይንና ሐዲስን ተምረው አጠናቀቁ። በኋላም አስኬማ መላእክትን ከኣቡነ ዜና ማርቆስ ተቀብለው ከጳጳሱም ዘንድ ሔደው ሥልጣነ ክህነትንና ቁምስናን ከተቀበሉ በኋላ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የከበረች ወንጌልን ሰበኩ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ከሥዕለ ማርያም ፊት ቆመው ሲጸልዩ ክብርት እመቤታችን ተገልጣላቸው ሕሙማንን የሚፈውሱበት ጽዋ ሰጠቻቸው። በአንድ ወቅት የረኀብ ዘመን ሆኖ ሳለ አቡነ በትረ ማርያም ግን ለመንፈሳዊ ወንድማቸው የረኀቡን ዘመን ማሳለፊያ እንዲሆነው ብለው ጌታችን በተሸጠበት ዋጋ በሠላሳ ብር ተሸጠው በጉልበታቸው ሠርተው በማገልገል ለወንድማቸው የረኀብ ዘመን ማሳለፊያ ሆነዋል። በተሸጡበትም ቦታ በጉልበታቸው እያገለገሉ ሳለ የመኰንኑ ልጅ በጽኑ ሕመም ታማ ለሞት ስትደርስ አባታችን እመቤታችን በሰጠቻቸው ጽዋ ውኃ አድርገው ጸልየው አጥምቀው አድነዋታል።

✝ከዚኸም በኋላ አቡነ በትረ ማርያም ከሸዋ ወደ ዳሞት (ጎጃም) አውራጃ ተሻግረው በጣዖት ያመልኩ የነበሩ ሰዎችን አስተምረው አጥምቀው በወንጌል ሕግ እንዲኖሩ በማድረግ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመዋል። በጎጃም ካስተማሩ በኋላ ወደ ቤጌምድር ሔደው በዚያም በተጋድሎ እየኖሩ የከበረች ወንጌልን ሰበኩ። አባታችን የረገጡትና የጸለዩበት መሬትና ድንጋይ ሁሉ እምነት ሆኖ ብዙ ድውያንን ይፈውስ ነበር። በትራቸውም በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ የወይን ዘለላ ፍሬ እያፈራ ይለቀም ነበር። በዚያም አካባቢ ጠበል አፍልቀው ብዙ ሕሙማንን እየፈወሱ ዜና ተኣምራቸው በየቦታው ሲናገር ውዳሴ ከንቱን ሸሽተው ክብራቸው እንዳይታወቅ ወደ ምድረ ደንቢያ ሔዱ።

✝አቡነ በትረ ማርያም በምድረ ደንቢያም ለስድስት ዓመት ምንም እህል ሳይቀምሱ በተጋድሎ እየኖሩ ወንጌልን እየሰበኩ ብዙ ሕሙማንን ፈወሱ። ከዚኸም በኋላ ከስድስት ወንድሞቻቸው ጋር ተገናኝተው በእግዚአብሔር ተእዛዝ ወደ ጣና መጡ። ሰባቱም ከዋክብት አንድ ላይ የጣናን ባሕር በእግራቸው ጫማ እየጠቀጠቁ ተሻግረው ዳጋ ደሴት ደረሱ። ከእነዚህ ሰባት ከዋክብት በፊት ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባት ቀድመው ወደ ደሴቱ እንደገቡ ታሪካቸው ያስረዳል። አቡነ በትረ ማርያምም በዳጋ ደሴት ምንም ሳይቀምሱ የዐቢይ ጾምን ከጸሙ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ዕጣ ክፍላቸው የሆነችውን ዛሬ ላይ ቤተ መቅደሳቸው የታነጸበትን ደሴት አሳያቸውና ‹‹የእስራኤልን ልጆች በሙሴ በትር የኤርትራን ባሕር እንዳሻገርኳቸው አንተንም በያዝካት በትር አሻግርሃለሁ› ካላቸው በኋላ በበትራቸው ባሕሩን ተሻግረው ዘጌ ምድር ደረሱ። በዚያም በኣት አበጅተው በጸሎት ተወስነው በተጋድሎ ጸንተው ሲኖሩ ከእግራቸው ሥር ሕሙማንን የሚፈውስ ሙት የሚያስነሣ ዐይነ ሥዉራንን የሚያበራ፣ አጋንንትን የሚያወጣ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት የሚያደርግ ፈዋሽ ጠበል ፈለቀ። ከየቦታው የሚመጡ ሕሙማንም በዚኽ ጠበል በአባታችን እጅ እየተጠመቁ የተፈወሱት በርካቶች ናቸው።
✝አቡነ በትረ ማርያም በዘጌ ምድር እየተዘዋወሩ ሲያገለግሉ አሁን አዝዋ ማርያም ከምትባለው ቦታ የሥዕል ቤት አድርገው ሲጸልዩ ከንጉሥ ዓምደ ጽዮን የተላኩ መልእክተኞች መጥተው ‹‹አባታችን ወዴት ናቸው?›› ብለው ሲጠይቁ በቦታው የነበሩ መነኰሳት እዛ ናቸው›› በማለት ስላመለከቱ ቦታዋ በዚያው አዝዋ ተባለች። አባታችን ከዘጌ አናት ተራራ ላይ አራራት ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ሆነው በአራቱም ማዕዘን እየባረኩ የታቦተ ማርያምንና የታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ይዘው ‹‹ለኖኅ የሰጠኸውን ቃልኪዳን አትርሳብኝ›› በማለት እየባረኩ ይጸልዩ ነበር። ከዚኽም በኋላ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ላይ ሆኖ ተገለጠላቸውና እየመራቸው ጣና ባሕርን ተሻግረው መሐል ዘጌ አደረሳቸው። ከዚያም ‹‹እዚሁ ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን ሥራ› ብሎ በፈረሱ ድንጋዩን ረግጦ እንደሰም አቅልጦ እንደጭቃ ረግጦ የፈረሱን ኮቴ ምስል አስቀመጠላቸው። አቡነ በትረ ማርያም የመሐል ዘጌን ቤተ ክርስቲያን ሲያንጹ ሳንቃዎቹ (መዝጊያዎቹ) በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በነፋስ ተጭነው የመጡ ናቸው። ጻድቁም የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው የጸሎት ልብሳቸውን እርሱም 25 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ከብረት ሰንሰለት የተሠራው ቀሚሳቸውን ለብሰው ወደ ጣና ሐይቅ እየገቡ ጸሎት እያደረጉ ለ23 ዓመታት በእንዲህ ዓይቱ ጽኑ ተጋድሎ ኖረዋል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://vm.tiktok.com/ZM2buPb5R/

አበው ይናገሩ


ላይክ ሼር ፎሎ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አድራሻችን ቁጥር አንድ ፒያሳ ከኬራውድ ህንፃ ገባ ብለው ያገኙናል ቁጥር ሁለት አዲሱ መናኽርያ ትንሽ ወረድ ብለው አንደኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል በስልክ ቁጥሮቻችን 0916868783 ወይም በ 0931559466 ለአዲሱ መናኽርያ በ 0938306001 ያገኙናል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝

††† ✝ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ ✝†††

††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም)

ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::

ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::

ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::

እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር::

በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::

ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::

በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::

አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::

ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::

እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል::

በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል::

††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::

††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::

†††✝ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✝†††

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሠባሉ::

ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጥምቀዋል:: ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃይቷቸዋል::

ስለ ቅዱሳኑ ግን ፈረሶቹ ሰግደው: በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መስክረዋል:: በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል:: በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል::

††† ✝ከአባቶቻችን አበው ሐዋርያት በረከት ይክፈለን::✝

††† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ
3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅድስት እንባ መሪና
4.ቅድስት ክርስጢና

††† "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" †††
(ማቴ. ፯፥፯)

††† "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. ፴፯፥፴)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክቡራን የእግዚአብሔር ወዳጆች  እግዚአብሔርን የምትወዱ  እግዚአብሔር የሚወዳችሁ  

ምእመናን  ኾይ 

👉በተዋህዶ  ምን  እንደሚፈልግ  እናዉቃለን  ትላላችሁ 

👉 ማወቅ  ደስ ይላል  ታዲያ  ማወቅ  ዝምብሎ   ምን  ዋጋ  አለዉ 

👉 ያወቁትን  መኖር  ሲቻል  እንጂ  ።

✝️መኖር  ምንድን  ነዉ 

👉ሀይማኖትን  መኖር  ብየ  እመልሳለሁ

✝️ሀይማኖትን  መኖር  ምንድን  ነዉ?

👉የአለምን  ፍላጎት  መተዉ  ነዋ!

ለምሳሌ

-ዘፈንን   ከስልክህ  መደምሰስ
- መደነስ  መተዉ
- ወንድ  ጸጉርን  መንጨፍረር መተዉ
-  ምንስቲኮች  የተባሉትን መተዉ
-  ሴት  ሱሪ መልበስን  መተዉ
-  ለተራበ  አምስት አስር መስጠት
-  ሁሌም  ጸሎት  ማድረግ  

👉ከነዚህ  ጀምሮ  ወደ ከፍታ   መዉጣት ይቻላል

👉እና  የመዳን  ቀን  አሁን  ነዉ ።
የተዋህዶ  ልጆች  ንቁ   መማር   ያለ ተግባር ከሆነ 

👉መማር   አባቱ  ከንቱ  ይሆናል  

ሁላችንም ከከንቱ  አባት  ለመዉጣት  አሁን  ጀምሮ  እንንቃ !!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መረጃ (ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም በትግራይ ክልል ለሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንትና ምዕመናን ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ የሰላምና የአንድነት ጥሪ አቀረቡ።)


➯ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች በተለይም በትግራይ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ከሕግ ውጭ በሆነ መልኩ " ኤጲስ ቆጶሳትን " እንሾማለን በማለት እየተደረገ ያለው ዝግጅት አስመልክቶ እንዲቆምና የውይይት መድረኮች ተመቻችተው ችግሮችን በሰላማዊና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በጠበቀ መልኩ ለመፍታት በቦታው ካሉ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ለሊቃውንት ኦቶዶክሳውያንና ለሌሎች እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት የሰላምና የአንድነት ጥሪ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አቅርበዋል።

➯ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም መገለጫቸው ጉዳዮቹን ለማጥራትና ሁሉም አካል ወደልቡ እንዲመለስ ያለመ መሆኑን በመግለጽ መልእክታቸውን ማስተላለፍ የቀጠሉ ሲሆን በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሞቱ የተጎዱና ከቀያቸው በተፈናቀሉ በአጠቃላይ በደረሰው መከራና ሞት እጅግ ማዘናቸው ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ጉዳዮች እዚህ ከመድረሳቸው በፊት በሰዓቱ አባቶች ከግል ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ የተደረጉ ሰላማዊ ተግባራት እንደነበሩ አብራርተዋል።

➯ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን በትኩረት ከማየቷ በተጨማሪ "በችግሩ ወቅት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጊዜ የሀገር ሰላምን በተመለከተ በያዘው አጀንዳ በተወያያበት ሰዓት ከብፁዓን አባቶች የተወጣጣ የሰላም ኮሚቴ ተዋቅሮ ችግሩ እንዲፈታ የሰላም አየር እንዲነፍስ በሚባልበት ወቅትም በአሁኑ ሰዓት በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት ከሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል "እኛ ጋር ሰላም ነው ችግር ወዳለበት አካባቢ ሂዱ" የሚል ምላሽ እንደሰጡ ኦርቶዶክሳውያን ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።

➯ከዚህ ይልቅ ችግር በችግር አይወገድምና እንደጥፋትም ከሆነ የጋራ እንጂ ራስን ንጹሕ አድርጎ ሌላውን እንደበደለኛ መቁጠር ተገቢነት እንደሌለው ገልጸዋል። አያይዘው ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሊቃውንት በጎጥ በጎሳ በቋንቋና በብሔር በሌላ ምድራዊ ሐሳብ ሳትከፋፈሉ ለሰማያዊ መንግሥት ዓላማ ያለውን መልካም ተግባር በማድረግ አደራችሁን እንዲወጡ በማለት አሳስበዋል።

➯ቀጥለው ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ባስተላላፉት መልእክት ትናንት እናት ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ከፍተኛ ችግር በእስከ መሥዋዕትነት በደረሰ ሁለንተናዊ ራስን መስጠት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንደተወጣችሁ ሁሉ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን ጠብቃ ለመሄድ በምታደርገው የእውነት መንገድ ከምንም በላይ ክርስቶስ በገዛ ደሙ ፈሳሽነት ለመሠረታት ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር በመሸነፍ ለአንድነቷና ለሰላሟ በጸሎት በሐሳብና በተግባር በተገለጠ ሕይወት እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል። ከዚሁ ጋር በልዩ ልዩ ሃይማኖት ላሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንድትጠበቅ ከዚህ በፊት ያደረጋችሁትን መልካም አስተዋጽኦ ዛሬም ጥንታዊት እና ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ሰላሟ ተጠብቆ እንዲቀጥል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትወጡ እንጠይቃለን በማለት መልእከታቸውን አድርሰዋል።

➯የኢፌዴሪ መንግሥት ትናንት ተፈጥሮ በነበረው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ችግር በውይይትና በምክክር በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲፈታ ማድረጉን ያስታወሱት ብፁዕነታቸው አሁንም በትግራይ ክልል ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለውን መፍትሔ የማይሆነውን ችግር በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እምነታችን ነው ብለዋል።

➯ይህ ካልሆነ ግን ይላሉ ብፁዕነታቸው "በታሪክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትን ማን ከፋፈለ ሲባል የፌደራልና የክልሉ መንግሥት" የሚል የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል። ስለሆነም ይህን በትግራይ ክልል ይፈጸማል የሚለውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገወጥ የሆነ ሹመት እንዲቆም ብሎም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በማመቻቸት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች ብለዋል።

➯ቅዱስ ሲኖዶስ ለትልቁ ጉልበትና ቅዱስ ትዕዛዝ "ለይቅርታ" ራሱን በማስገዛት መንጋው እንዳይበተን ይፋዊ ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ርዕሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመሩት የሰላም ልዑክ ወደ መቐለ አቅንቶ ችግርን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ተወቃቅሶ ለመፍታት ቢሞከርም አለመሳካቱ አስታውሰው ጉዳዩ እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

➯በመጨረሻም የባለውለታዋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚያሳስበው ሰላሟ የሚናፍቀው ሁሉም አካል ከትልቁ ጉልበት ጸሎት ጀምሮ የሚቻለውን አበርክቶት እንዲወጣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም አሳስበዋል።

#EOTCTV ሐምሌ 13

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

📕#ተአምር_ዘአቡነ_ዘርዓ_ብሩክ🌹
📘☞•••ወር በገባ በ13 ታስበው የሚውሉ አባታችን ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታአምር ይህ ነው ስሟ ፋሲካዊት በምትባል ሴትዮ ቤት እግዚአብሔር ዳግመኛ ታላላቅ ተአምራት አደረገ፡፡ ያቺም መልካም ሴት ሁል ጊዜ የዘርዐ ብሩክ መታሰቢያውን ታደረግ ነበር አሱንም ከመውደዷ የተነሳ ተገዛችለት ለቃሉም ታዙችለት፡፡

☞በአንድ ወር ለመታሰቢያው የሚሆን የማኀበሯ ተራ በደረሰ ጊዜ ትደክም ጀመር ብዙ ቀን ሰትጥር ስትግር ሰይጣን ቀንቶባት የመታሰቢያውን የወይን ጠጅ አጠፋባት፡፡

☞ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ሰለ ኃጢአቴና ሰለ በደሌ ነው ብላ ብዙ ምሾ እያወጣቸ
ፈጽማ አለቀሰች፡፡
☞እግዚአብሔርም የለቅሶዋን ጽናትና ኅዘኗን አይቶ በሰይጣን ቅናት የጠፋባትን ያን ወይን ጠጅ የቃናን ውሃ ለውጦ የጣመ እንዳደረገው ያን ቦዶ እንስራ ወደ ወይን ለወጠው ፈጽሞም ጣፈጠ፡፡
☞በዚያ በጻድቁ አባቷ ዘርዐ ብሩክ ጸሎት ያ የወይን ጠጅ ተለውጦ እንዳ ጣፈጠ ያቺ ሴት አይታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ እናቱ ድንግል ማርያምንም
አመሰገነች በጸሎቱና በአማላጅነቱ ተአምራትን መንክራትን ያየረገላት ቅዱስና
ብፁዕ የሚሆን አባታችን ዘርዐ ቡሩክ እጅግ ወደደችው፡፡

☞የጣፈጠው ያ የወይን ጠጅም በክቡር የሚካኤል በዓል ቀን ዳግመኛ
አለቀባት የነበሩ ብዙ ማኀበርተኞችም እጅግ አዘኑ የወይን ጠጅ ትበደራቸው
ዘንድ በየሀገሩ ዞረች የምትሰጣቸው የወይን ጠጅ ባጣች ጊዜ ከዚያ
ከሚጣፍጠው የወይን ጠጅ የቀረ(የተረፈ)አንድ ማድጋ ቅራሪ አመጣችላቸው
በቀዱት ጊዜ አተላ ሆነ፡፡

☞ያዚ ሴትም እጅግ አዘነች ማኀበርተኞችም ሁሉ እንደ አርሷ አዘኑ ዳግመኛ ቀዱት ንጹህና ጣፈጭ ሆነው አገኙት እጅግ ተደነቀች ማኀበርተኞችም እንደ እርሷ አደነቁ፡፡ ☞ይህ ሁሉ ተአምር የተደረገ በጻዱቁ አባታችን ዘርዐ ብሩክ ጸሎትና ልመና ነው፡፡

☞መታሰቢያውን ለምናደርግ ስሙን ለምንጠራ እንደ እርሷ ተአምራትን
ያድርግልን ለዘለአለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ ዘርዐ ቡሩክ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከመጀመሪያው አዳም ያለመገናኘት ሴት /ሔዋን እንተፈጠረች ክርስቶስም ያለግንኙነት ከእመቤታችን ተወለደ፡፡ የጌታችን ነፍስ ከድንግል ማርያም አይደለችም ለማለት ከደፈርህ የማርያም ነፍስም ከአዳምና ከሔዋን አይደለም : ማለት : ነዋ! ወይስ የሕፃናት ነፍስ ከእናትና ከአባታቸው አይደለችም ማለት ይቻልሃልን?

ሰነፍ ሰው ሆይ ጌታችን ነፍሱን የነሳው ከድንግል ማርያም አይደለም ማለት እንደማይቻልህ ስማ፤ በእርግጥም የእመቤታችን ማርያም ነፍስ ከአዳምና ከሔዋን ነው፣ ሥጋዋም ከሥጋቸው ነው፡፡ እንደዚሁም ለክርስ ቶስም ከድንግል ማርያም ነው። ለሕፃን ነፍሱም ሥጋውም' ሕሊና ውም ከእናትና ከአባቱ ነውና፤ የወንድ ዘር በማሕፀን አንድ ከሆነ በኋላ ደም ይሆናልና፡፡ እርሱም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነፍስና ሥጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህም አዳም የዓለም ሁሉ አባት ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ የእርሱ ልጅ ነውና፡፡

እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!!

ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው

ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር
የሚፈልገው 

ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም
መማር ማወቅ የሚፈልገው

  እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ 

ከሲዖል የሚጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል እንዳያመልጥዎ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!!

ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው

ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር
የሚፈልገው

ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም
መማር ማወቅ የሚፈልገው

እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ

ከሲዖል የሚጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል እንዳያመልጥዎ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†††✝ እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝ †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††✝ ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ወሰማዕት ✝†††

††† ቅዱስ ዮሐንስ በቀደመው ዘመን ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ መርባስ ትባላለች:: ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚወዱ: ምጽዋትን የሚያዘወትሩና በበጐው ጐዳና የሚኖሩ ነበሩ:: ነገር ግን ልጅ በማጣታቸው ምክንያት ፈጽመው ያዝኑ: ይጸልዩም ነበር:: በተለይ ለመጥምቁ ዮሐንስ ልዩ ፍቅር ስለ ነበራቸው ዝክሩን ይዘክሩ: በስሙም ይማጸኑ ነበርና መጥምቁ ሰማቸው::

ወደ ፈጣሪውም ልመናቸውን በማድረሱ መልክ ከደም ግባት የተባበረለት ደግ ልጅን ወለዱ:: እጅጉን ደስ ስላላቸው በአካባቢያቸው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስን ቤተ ክርስቲያን በገንዘባቸው አነጹ:: ሕፃኑንም በመጥምቁ ስም "ዮሐንስ" አሉት:: ጻድቁ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አድሮበታልና ሕይወቱ ግሩም ነበር::

በሕፃን ገላው ይጾምና ይሰግድ: በልጅ አንደበቱም ተግቶ ይጸልይ ነበር:: ወላጆቹ ወደ እረኝነት ባሰማሩት ጊዜም መፍቀሬ ነዳያን ነውና ቁርስና ምሳውን ለነዳያን እያበላ እርሱ ጾሙን ይውል ነበር:: አባቱ የሚያደርገውን ሰምቶ ለማረጋገጥ ተከተለው:: እንዳሉትም እናቱ ጋግራ የሰጠችውን ትኩስ ዳቦ ለነዳያን ሲሰጥ አየው::

ሊቆጣው ፈልጐ "ዳቦህ የታለ?" ቢለው ሕፃኑ ቅዱስ ዮሐንስ "በአገልግሉ ውስጥ አለ" ሲል መለሰለት:: አባት ለመቆጣት እንዲመቸው አገልግሉን ሲከፍተው ግን ያየውን ማመን አልቻለም:: በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ዳቦዎቹ ትኩስ እንደሆኑ ተገኙ::

አባትም ወደ ቤቱ ወስዶ "ልጄ! አንተ የእግዚአብሔር ሰው ስለሆንክ እኛን ሳይሆን እርሱን አገልግል" ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላከው::

በዚህ ምክንያት ቅዱስ ዮሐንስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ ትምህርት ገባ:: በስድስት ዓመታትም ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አሥራ ስምንት ዓመት ሲሞላው ደግነቱን ወደዋልና በግድ ቅስና ሾሙት:: እርሱ ግን ለተወሰነ ጊዜ አስተምሮ ዘመዱ የሆነውንና ዲያቆኑን ቅዱስ ስምዖንን አስከትሎ መነነ::
በዚያም በፍጹም ገድል ሲኖር ብዙ ተአምራትን ሰርቷል::

¤አንድ ወታደር (አንድ ዐይና ነው) ሊባረክ ብሎ ሲጐነበስ የታወረች ዐይኑን የቅዱስ ዮሐንስ ልብስ ቢነካት በርታለታለች:: ከዚህ አልፎም ቅዱሱ ብዙ ድውያንን ፈውሷል: ለምጻሞችን አድኗል: አጋንንትን ከማደሪያቸው (ከሰው ላይ) አሳድዷል::

ታዲያ አንድ ቀን የወቅቱ የአንጾኪያ ንጉሥ የቅዱስ ዮሐንስን ዜና ይሰማል:: የእርሱ ልጅ ደግሞ አጋንንት አድረውባት ስቃይ ላይ ነበረችና የሚያድናት አልተገኘም:: ንጉሡ "ጻድቁን አምጡልኝ" ብሎ መልዕክተኛ ሲልክ ቅዱስ ዮሐንስ ደመና ጠቅሶ: በዚያውም ላይ ተጭኖ ከተፍ አለ:: ንጉሡ አይቶት ደነገጠ:: አባ ዮሐንስ ግን "እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ሰው ለምን እንዲህ ትፈልገኛለህ?" ብሎ ታማሚዋን አስጠራ::

ጻድቁ እጆቹን አንስቶ ወደ ፈጣሪው ሲጸልይ በወጣቷ ላይ ያደረው ሰይጣን ሕዝቡ እያዩት ከሆዷ በዘንዶ አምሳል ወጥቶ ሔደ:: ንጉሡ ስለተደረገለት ውለታ ለቅዱስ ዮሐንስ ወርቅና ብር ብዙ ሽልማትም አቀረበ:: አባቶቻችን እንዲህ ዓይነት ነገር አይወዱምና ቅዱሱ "እንቢ አልወስድም" አለ::

ቅዱስ ዮሐንስ "ልሒድ" ብሎ ሲነሳ ንጉሡ "አባቴ ወድጄሃለሁና አትሒድ" ብሎ የልብሱን ዘርፍ (ጫፍ) ያዘው:: በቅጽበት ግን ደመና መጥታ ነጥቃ ወሰደችው:: የቀሚሱ ቁራጭም በንጉሡ እጅ ላይ ቀረች:: እርሱም ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ያችን የተባረከች ጨርቅ በክብር አኑሯታል::

ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ) ግን ከብዙ የተጋድሎ ዓመታት በኋላ ሌላ ክብር መጣላቸው:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" የሚል ንጉሥ በመነሳቱም ሒደው በጌታችን ስም መሰከሩ:: በገድል በተቀጠቀጠ ገላቸው ላይ ግርፋትን: እሳትን ታገሱ:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተቆርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል::

††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታችቸውም ያድለን::

††† ሐምሌ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ)
3.አባ ኢሳይያስ ዘገዳመ አስቄጥስ
4.አባ ገብርኤል ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት

††† "ሒዳችሁም መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ:: ድውዮችን ፈውሱ: ሙታንን አንሱ: ለምጻሞችን አንጹ: አጋንንትን አውጡ:: በከንቱ ተቀብላችሁ በከንቱ ስጡ:: ወርቅ: ወይም ብር: ወይም ናስ በመቀነታችሁ: ወይም ለመንገድ ከረጢት: ወይም ሁለት እጀ ጠባብ: ወይም ጫማ: ወይም በትር: አታግኙ:: ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና::" †††
(ማቴ. ፲፥፯)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።

ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።

ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ኅልያን_ገዳማዊ

በዚህችም ቀን መስተጋድል አባ ኅልያን አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።

በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ አላት።

ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።

ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።

ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር።

የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።

ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።

ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እመቤታችን በአበው ቀደምት የተመሰለላት ምሳሌ እና እመቤታችን በቅዱሳን ነቢያት የተነገረላት ትንቢትና እመቤታችን በሊቃውንት ትርጓሜ

ወላዲተ አምላክ በዘመነ አበው/በሕገ ልቦና

ሀ) የያዕቆብ መሰላል:: (ዘፍ ፳፰÷፲-፳)

"ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ ።ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አረፈ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚሀ ስፋራ ተኛ፡፡ ሕልምም አለመ እንሆ መሠላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደረሶ እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር " " ዘፍ ፳፰፥፫-፳

👉ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራዕይ ያያት ወሠላል :- የእመቤታችን

👉የተንተራሰዉ ድንጋይ ትንቢተ ነቢያት:- እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ፀንታ ለመግኘቷ ምሳሌ ነዉ፡፡

👉 ያዕቆብ መሠላል ከምድር እስከ ሰማይ ደርሶ ማየቱ :-በሰዉና በእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጥላቻ ተወግዶ
ምድራዊያን ሠዎችና ሰማያዊያን መላዕክት እግዚአብሔር ወልድ ስጋዋን ለመዋሐድ የወረደና ያደረባት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነዉ፡፡

የያዕቆብ❤️ ምሰጢር፡ ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳዉ ጋር ተጣልቶ ወደ አጎቱ ወደ ላባ በሚሄድበት ወቅት መንገድ ላይ መንጋቸዉን እየጠበቁ ከዉኃዉ አፍ ላይ የተገጠመዉን ድንጋይ የሚያነሳላቸው አጥተዉ በችግር ላይ የነበሩት እረኞችን እንደ አገኘና ራሔል ከመጣች በኋላ ያን ታላቅ ድንጋይ ከጉድጓድ ዉኃ አፍ ላይ አንስቶ በጎቻቸውን እንደ አስጠላቸዉ ቅዱስ መፅሐፍ ይናገራል። ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ምስጢራዊ ምሳሌዉ።

ውኃ - የማየ ሕይወት
ድንጋይ- መርገም
አባግዕ በጎች -የምዕመናን
ኖሎት(እረኞች)- የነቢያት
ራሔል - የእመቤታችን
ያዕቆብ- የክርስቶስ

👉እረኞች በላቻቸውን ለማስካት ድንጋርን ማንሳት አለመቻላቸዉ ነቢያትም በትምህርታቸው በተጋድሏቸዉ መርገምን አርቀው ማየ ህይወት ለማጠጣት አልቻሉም።

👉እረኞች ራሔል እስክትመጣ ድረስ እንደጠበቁ ሁሉ ነቢያትም በትንቢታቸዉ የእመቤታችንን መምጣት ይጠባበቁ ነበር።

👉ራሔል በመጣች ጊዜ ብዙ እረኞች ማንሳት ያልቻሉትን ድንጋይ ያዕቆብ ብቻዉን አንስቶ በጎቹ እንዲከጡ አደረገ።

👉 እመቤታችን ከተወለደች በኋላም ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነቢያት በተጋድሎአቸዉ ሊያርቁት ያልቻሉትን መርገም በፍቃዱ በተቀበለዉ ፀዋትወ መከራ አራቀዉ:: አባግዕ ምእመናንም ከማየ ህይውት አጠጣ (ዮሐ ፬÷፯)

Читать полностью…
Subscribe to a channel